ቅዱሳት መጻሕፍት
7.45K subscribers
1.36K photos
61 videos
332 files
802 links
በዚህ ቻናል

👉ቅዱሳት መጻሕፍት ይጠናሉ::
👉መጽሐፍ ቅዱሳዊ ትምህርቶች ይቀርባሉ::
👉 ለቅዱሳት መጽሐፍት ጥናት የሚያግዙ መጻሕፍት ይለቀቃሉ።

⭐️⭐️⭐️⭐️⭐️

@Holy_scriptures
Download Telegram
#እራሳችንን_እንመርምር

የሰው ልጅ በምድር ላይ ሲመላለስ ይልቁን ክርስቲያን ለሽያጭ፣ ለድርድር ወይንም ለጥቅም ከማስቀመጥ ይልቅ ዋጋ የሚከፍልላቸው እና የሚከፍልባቸው ብዙ ነገሮች አሉ። ከእነዚህም መካከል እውነት አንዷ ናት! መንፈሳዊ ነገር፣ የወንጌል ነገር ለራስ ጥቅም በገበያ ወጥተው አይቸረቸሩም። ስንት ጊዜ ኑሮን ለማሸነፍ ይሁን በሌላ ሰበብ እውነትን በርዘናት፣ ደልዘናት፣ ሸቅጠናት. . . ለገበያ እንዳሰጣናት ፈጣሪ ይወቀው! ግን እሷን ሽጠን የት ለመድረስ? ምን ለመሆን?

“እውነትን ግዛ አትሽጣትም፥ ጥበብን ተግሣጽን ማስተዋልንም።”
ምሳሌ 23፥23

“እኛኮ ትርፍ ለማግኘት ብለን የእግዚአብሔርን ቃል ቀላቅለው እንደሚሸቃቅጡት እንደ ብዙዎቹ አይደለንም፤ ነገር ግን ከእግዚአብሔር እንደተላኩ ሰዎች በክርስቶስ ሆነን በእግዚአብሔር ፊት በቅንነት እንናገራለን።”
2ኛ ቆሮንቶስ 2፥17 (አዲሱ መ.ት)



ወደ ቻናሉ ለመ🀄️🀄️ል፦ @Holy_scriptures
2👍1
.       ──•◈•─────•◈•─
                          የዕለቱ ጥቅስ
        ──•◈•─────•◈•─
“ጨው መልካም ነው፤ ጨው ግን አልጫ ቢሆን በምን ታጣፍጡታላችሁ? በነፍሳችሁ ጨው ይኑርባችሁ፥ እርስ በርሳችሁም ተስማሙ።”
ማርቆስ 9፥50



ወደ ቻናሉ ለመ🀄️🀄️ል፦ @Holy_scriptures
4👍2🙏2
Audio
#መጻሕፍትን_በድምጽ

📔ርዕስ፦ የመጽሐፍ ቅዱስ አስተምህሮ
👤ጸሐፊ፦ ዶ/ር ቻርልስ ሲ.ራይሪ
🗣ተርጓሚ፦ ሲሳይ ደሳለኝ
👉ክፍል-6

ይቀጥላል...


ወደ ቻናሉ ለመ🀄️🀄️ል፦ @Holy_scriptures
👍3
#በዓለ_ኀምሳ
#ጰራቅሊጦስ


ጴንጤቆስጤ! የጴንጠቆስጤ ቀን የዋለው ከኢየሱስ ትንሣኤ በኋላ በሃምሣኛው ቀን ነው። በግሪክ ጴንጠቆስጤ ማለት «ሃምሣኛ» ማለት ነው። በብሉይ ኪዳን መሠረት ጴንጠቆስጤ የሚውለው የአይሁድ ፋሲካ በዓል ከሆነ በኋላ በሚቀጥለው እሑድ በሃምሳኛው ቀን ሲሆን (ዘሌ. 23፥15) ይኸው ቀን ደግሞ ክርስቲያኖች ትንሣኤን ካከበሩ በሃምሳኛው ቀን መሆኑ ነው። በዓለ ኀምሳ (ጴንጤቆስጤ)፣ የሰባቱ ሱባዔ በዓል (ዘዳ 16፥10)፣ የመከር በዓል (ዘጸ 23፥16)፤ የበኩራት ቀንም(ዘኁ 28፥26) ይባላል። አይሁዶች የመከር በዓልን የሚያከብሩት በጴንጠቆስጤ ዕለት ነበር (ዘጸ. 34፥22፤ ዘዳ. 16፥9–10)። በተመሳሳይ ሁኔታ ጰንጠቆስጤ ለቤተ ክርስቲያን በዓለም ውስጥ ያሉ ነፍሳት የእግዚኣብሔር መከር በመሆን የሚሰበሰቡበት ጅማሬ ነው፡፡

አይሁዶች የጴንጠቆስጤ ዕለትን የሚያከብሩበት ሁለተኛ ምክንያትም አላቸው። ይኸውም እግዚአብሔር ሕጉን የሰጣቸው በዚያ ቀን እንደሆነ ስለሚያምኑ ነው። ስለዚህም በዚያን ቀን እግዚአብሔር ለደቀ መዛሙርቱ ለመጀመሪያ ጊዜ የመንፈስ ቅዱስን ጥምቀት መስጠቱ በጣም ተስማሚ ነበር ማለት ነው።

በቀጣይ ጌታ ቢፈቅድ መንፈስ ቅዱስ ማን ነው? ምን ሊሰራ መጣ ወይም ዋና ሥራው ምንድን ነው? የሚለውን  እንመለከታለን።


ይቀጥላል...



ምንጭ፦ የአዲስ ኪዳን ማብራሪያ፤ ገጽ 292፣ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ከማጥኛ ጽሑፍ ጋር፤ ገጽ 1646፣ ምሉእ ሕይወት፤ ገጽ 1668



ወደ ቻናሉ ለመ🀄️🀄️ል፦ @Holy_scriptures
6🥰5👍2🔥2👏1
.       ──•◈•─────•◈•─
                          የዕለቱ ጥቅስ
        ──•◈•─────•◈•─
“እግዚአብሔርንም መፍራት ባስተማረ በዘካርያስ ዘመን እግዚአብሔርን ይፈልግ ዘንድ ልብ አደረገ እግዚአብሔርንም በፈለገ ጊዜ እግዚአብሔር ነገሩን አከናወነለት።”
2 ዜና 26፥5


ወደ ቻናሉ ለመ🀄️🀄️ል፦ @Holy_scriptures
7
Audio
#መጻሕፍትን_በድምጽ

📔ርዕስ፦ የመጽሐፍ ቅዱስ አስተምህሮ
👤ጸሐፊ፦ ዶ/ር ቻርልስ ሲ.ራይሪ
🗣ተርጓሚ፦ ሲሳይ ደሳለኝ
👉ክፍል-7

ይቀጥላል...


ወደ ቻናሉ ለመ🀄️🀄️ል፦ @Holy_scriptures
👍1
ቅዱሳት መጻሕፍት
#መጻሕፍትን_እንመርምር የኢየሱስ ክርስቶስ ትንሣኤ የአካል ወይስ የመንፈስ?                         ክፍል-፮                                           ሀ. “ከእናንተ አንዳንዶቹ ትንሣኤ ሙታን የለም እንዴት ይላሉ?” (ቊጥር 12) ጳውሎስ ይህን መልእክት የጻፈው ከአቴና ትንሽ ኪሎ ሜትር ወረድ ብላ በምትገኘው ቆሮንቶስ ነው:: በዚያ የሞቱ ሰዎች ዳግም ሕይወት…
#መጻሕፍትን_እንመርምር

የኢየሱስ ክርስቶስ ትንሣኤ የአካል ወይስ የመንፈስ?


                        ክፍል-፯

መ. “እንዲሁ ደግሞ፣ ፊተኛው ሰው አዳም ሕያው ነፍስ ሆነ ተብሎ ተጽፎአል፤ ኋለኛው አዳም ሕይወትን የሚሰጥ መንፈስ ሆነ” (ቊጥር 45)

በዚህ ክፍል ላይ የተነጻጸሩት ነፍስ (ግሪክ “ሱቼ” ) እና መንፈስ (ግሪክ “ኒውማ”) መፈታት ያለባቸው ከቊጥር 44 አንጻር ነው:: ስለዚህ በቊጥር 44 ላይ ያለው ንጽጽር በሚሞተው አካል (ለኀጢአትና ለውጤቱ ሰለባ የሆነው) እንዲሁም በትንሣኤ አካል (ከኀጢአት ተጽእኖ ውጪ የሆነው) መካከል ነው:: በቊጥር 45 ላይም የምናገኘው ንጽጽር ይኸው ነው፡፡ አካል በሚፈጠርበት ጊዜ ኀጢአተኛ ስላልነበር የኀጢአትም ጥቃት አልደረሰበትም:: ነገር ግን በኀጢአት በመውደቁ ምክንያት ተበላሸ፣ ረከሰ፣ ደከመ፣ ሞተ፡፡

ሠ. “የፊተኛው ሰው ከመሬት መሬታዊ ነው፤ ሁለተኛው ሰው ከሰማይ ነው” (ቊጥር 47)

ይህ ክፍል ኢየሱስን ሰው ይለዋል። ለኀጢአት ክፍያ ኢየሱስ ሰብአዊነቱን ትቶአል ከሚለው የይሖዋ ምስክሮች ትምህርት በቀጥታ ይጣረሳል፡፡ የትንሣኤ አካል ዐፈር ብቻ አይደለም፤ ነገር ግን ለሕይወት ብቁ እንዲሆን የተለወጠ ነው (ቊጥር 48)።

ረ “ሥጋና ደም የእግዚአብሔርን መንግሥት ሊወርሱ አይችሉም፤ የሚበሰብሰውም የማይበሰብሰውን አይወርስም” (ቊጥር 50)

የይሖዋ ምስክሮች አብዛኛውን ጊዜ የመጀመሪያውን ዐረፍተ ነገር ብቻ መጥቀስ ይወዳሉ፡፡ ነገር ግን ተከታዩ ዐረፍተ ነገር የክፍሉን ሐሳብ በተሟላ መልኩ ይገልጻል። የሚሞተው አካላችን ችግሩ ቊሳዊ አካል መሆኑ ሳይሆን፣ ስለተበላሸ፣ የሚበሰብስ ስለሆነ ነው:: በመጽሐፍ ቅዱስ፣ “ሥጋና ደም” የሚለውን አገላለጽ በምድር ብቻ የተወሰነ መሆንን፣ ድካምን የሚገልጽ ሥዕላዊ ቋንቋ ነው (ማቴዎስ 16÷17፤ ገላትያ 1÷16፤ ኤፌሶን 6÷12፤ ዕብራውያን 2÷14)።

የእግዚአብሔርን መንግሥት ያለመውረሳችን ምክንያቱ በኀጢአት መውደቃችን ነው (1ቆሮንቶስ 6÷9-10፤ ገላትያ 5÷12)። ስለዚህ የእግዚአብሔርን መንግሥት ለመውረስ ቊሳዊ አካልን መተው ሳይሆን (1ቆሮንቶስ 15÷50) የተበላሸውን ሁኔታችንን የሚያድስና የሚያስተካክል የመንፈስ ቅዱስ ሰማያዊ ሕይወት ማግኘት ነው (1ጴጥሮስ 1÷4)::

ሰ. “ሙታን የማይበሰብሱ ሆነው ይነሣሉ፤ እኛም እንለወጣለን፡፡ ይህ የሚበሰብሰው የማይበሰብሰውን ሊለብስ ይህም የሚሞተው የማይሞተውን ሊለብስ ይገባዋል” (ቊጥር 52-53)

ጳውሎስ በዚህ ክፍል እያጠናከረ ያለው ትምህርት፣ ሥጋና ደም የእግዚአብሔርን መንግሥት ሊወርስ መለወጥ የግድ እንደሚያስፈልገው ነው። እሱን በማጥፋት መንፈሳዊ በሆነው አካል መቀየር አስፈላጊ አይደለም፡፡ ይህ የተበላሸ፣ ሟች የሆነው ሰብአዊነት የማይሞተውንና የማይበሰብሰውን መልበስ ያስፈልገዋል፡፡ አሁን ያለን ይህ አካላችን ቀጣይነት ይኖረዋል፤ ነገር ግን የሚበሰብሰው ክፍል ሊለወጥ ይገባዋል፡፡

ሸ.  “በዚያን ጊዜ ሞት ድል በመንሣት ተዋጠ ተብሎ የተጻፈው ቃል ይፈጸማል” (ቊጥር 54)

ትንሣኤ ሞትን ድል የሚያደርገው የሚሞተው አካል በሕይወት ሲታደስ ብቻ ነው::


ይቀጥላል...



ምንጭ፦ ዶ/ር ተስፋዬ ሮበሌ፤ በሥጋ ትንሣኤ አምናለሁ! የአስተምህሮተ ትንሣኤ መጽሐፍ ቅዱሳዊ፣ ታሪካዊና ሥነ አመክንዮአዊ ትንታኔ፤ ከምእራፍ ሰባት የተወሰደ




ወደ ቻናሉ ለመ🀄️🀄️ል፦ @Holy_scriptures
3👏2👍1
ቅዱሳት መጻሕፍት
#በዓለ_ኀምሳ #ጰራቅሊጦስ ጴንጤቆስጤ! የጴንጠቆስጤ ቀን የዋለው ከኢየሱስ ትንሣኤ በኋላ በሃምሣኛው ቀን ነው። በግሪክ ጴንጠቆስጤ ማለት «ሃምሣኛ» ማለት ነው። በብሉይ ኪዳን መሠረት ጴንጠቆስጤ የሚውለው የአይሁድ ፋሲካ በዓል ከሆነ በኋላ በሚቀጥለው እሑድ በሃምሳኛው ቀን ሲሆን (ዘሌ. 23፥15) ይኸው ቀን ደግሞ ክርስቲያኖች ትንሣኤን ካከበሩ በሃምሳኛው ቀን መሆኑ ነው። በዓለ ኀምሳ (ጴንጤቆስጤ)፣…
#ጰራቅሊጦስ

የቀጠለ...




በቅዱሳት መጸሕፍት መንፈስ ቅዱስ ጰራቅሊጦስ ተብሎ ተገልጿል። ጰራቅሊጦስ (ግሪክ፡ παράκλητος፣ ላቲን፡ ጰራቅሊጦስ) ጠበቃ ወይም ረዳት ማለት ነው። በክርስትና ውስጥ፣ “ጰራቅሊጦስ” የሚለው ቃል በአብዛኛው የሚያመለክተው መንፈስ ቅዱስን ነው። ጰራቅሊጦስ የመጣው ከኮይኔ የግሪክ ቃል ነው παράκλητος (paráklētos)። ይህ ስያሜ የሁለት ጥምር ቃል ውህደት ነው። “ፓራ” (በጎን/ጎን) እና “ካሌይን” ("to call" ወይም ለመጥራት)። በመጀመሪያ በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ በዮሐንስ 14፡16 ይገኛል።
በአጠቃላይ በአዲስ ኪዳን 5 ጊዜ የተጠቀሰ ሲሆን 4 ጊዜ በዮሐንስ ወንጌል(14፥16፤ 14፥26፤ 15፥26፤ 16፥7) አንድ ጊዜ ደግሞ በ1ኛ ዮሐንስ መልእክት (2፥1) ውስጥ ይገኛል። በ1ኛ ዮሐንስ ያለው ቃል የሚናገረው ስለጌታችን እና መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ነው።

በእግዚአብሔር ቤዛነትን የመስጠት ዐላማ ውስጥ መንፈስ ቅዱስ የሚሠራውን አስፈላጊ ሥራ አማኞች መረዳት ይኖርባቸዋል፡፡  ያለ መንፈስ ቅዱስ ኀይል ፍጥረት፣ ፍጥረተ ዓለም እንዲሁም የሰው ዘር (ዘፍ 1:2፤ ኢዮ 33:4) አይኖርም ነበር:: ያለመንፈስ ቅዱስም መጽሐፍ ቅዱስ (2ጴጥ 1፥21)፣ አዲስ ኪዳን (ዮሐ 14፥26፤ 15፡26-27፤ (ቆሮ 2፡10-14)፣ ወንጌልን ለማወጅ የሚያስችል ኀይል (ሐሥ 1፥8) አይኖርም፡፡ ያለ መንፈስ ቅዱስ እምነት፣ አዲስ ልደት፣ ቅድስና እውን አይሆንም እንዲሁም ክርስቲያኖች በዓለም ውስጥ አይኖሩም ነበር፡፡

የመንፈስ ቅዱስ አካል፣ በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ መንፈስ ቅዱስ የራሱ የሆነ የግል ማንነት እንዳለው ተገልጾአል (2ቆሮ 3፥17-18፤ ዕብ 9፥14፤ 1ጴጥ 1፥2)። እርሱ ልክ እንደ እግዚአብሔር አብና እንደ እግዚአብሔር ወልድ መለኮታዊ ማንነት አለው፡፡ ስለዚህ መንፈስ ቅዱስ ስሜት አነሣሽ ወይም ኀይል ብቻ አይደለም:: የራሱ የሆነ ባሕርይ አለው፤ ያስባል (ሮሜ 8፥27)፤ ስሜት አለው (ሮሜ 15፥30)፣ ፈቃድ አለው (1ቆሮ 12፥11) እንዲሁም ኅብረትን የመውደድና በኅብረትም ደስ የመሰኘት ችሎታ አለው፡፡ አማኞች ከኢየሱስ ጋር ወደ ቀረበ ሀልዎትና ኅብረት ውስጥ ይገቡ ዘንድ መንፈስ ቅዱስ በእግዚአብሔር አብ ተልኮአል (ዮሐ 14፥16-18፥26)፡፡ ከእነዚህ እውነቶች አንጻር መንፈስ ቅዱስን እንደ አንድ አካል በመቊጠርና በልባችን ውስጥ የሚኖር ዘላለማዊ ሕያው አምላክ እንደ ሆነ በማሰብ አምልኮአችን፤ ፍቅራችንና መገዛታችን ለእርሱ እንደሚገባው ሆኖ መቅረብ ይኖርበታል (ማር 1፥11)፡፡

የመንፈስ ቅዱስ ሥራ

1.  በብሉይ ኪዳን መንፈስ ቅዱስ ራሱን የገለጠበት ሥራ፡፡

የቃሉ ምንነት፣ “መንፈስ” የሚለው የዕብራይስጥ አቻ ቃል፣ “ሩሕ” የሚል ነው፣ ይህም ቃል አንዳንድ ጊዜ፣ "ነፋስ” ወይም “ትንፋሽ" ተብሎ ይተረጐማል፡፡ ስለዚህ ብሉይ ኪዳን የእግዚአብሔር ትንፋሽ ወይም ከእግዚአብሔር የሆነ ነፋስ ሲል (ለምሳሌ ዘፍ 2፥7፤ ሕዝ 37፥9-10፡14) የሚያመለክተው የእግዚአብሔርን መንፈስ ሥራ ሊሆን ይችላል፡፡

መጽሐፍ ቅዱስ በብሉይ ኪዳን ዘመን የነበረውን ልዩ ልዩ የመንፈስ ቅዱስን ሥራ ይገልጻል፤

ሀ. ፍጥረት በተፈጠረበት ጊዜ መንፈስ ቅዱስ የፈጣሪነት ተግባሩን አከናውኖአል፡፡

የመጽሐፍ ቅዱስ ሁለተኛው ጥቅስ፣ ለዓለም መልክና ቅርጽ በመስጠት ለእግዚአብሔር ፈጣሪ ቃል ለማዘጋጀት፣ “የእግዚአብሔር መንፈስ በውሆች ላይ ይረብብ ነበር” (ዘፍ 1፥2) ይላል፡፡ የእግዚአብሔር ቃልና (ይኸውም ከሥላሴ ሁለተኛው አካል) የእግዚአብሔር መንፈስ ሁለቱም፣ ፍጥረት ሲፈጠር ፈጣሪዎች ነበሩ (ኢዮ 26፥13፤ መዝ 33፥6)። በተጨማሪም መንፈስ ቅዱስ የሕይወት ፈጣሪ ነው፣ እግዚአብሔር አዳምን በፈጠረ ጊዜ፣ የሕይወትን እስትንፋስ ወደ እርሱ እፍ ያለበት ያለጥርጥር መንፈሱ ነበር (ዘፍ 2፥7፤ ከኢዮ 27፥3)፤ መንፈስ ቅዱስም ለእግዚአብሔር ፍጥረት ሁሉ ሕይወትን በመስጠት ረገድ ዛሬም ቢሆን እንደ ቀጠለ ነው (ኢዮ 33፥4፤ መዝ 104፥30)።


ይቀጥላል...


ምንጭ፦  lsj.gr/wiki/paracletus፣ ምሉእ ሕይወት፤ ገጽ 1314፣ 1679



ወደ ቻናሉ ለመ🀄️🀄️ል፦ @Holy_scriptures
🔥32👍2
በቅዱሳት መጻሕፍት ውስጥ ጳውሎስ በነበረበት ዘመን ቆሮንቶስ የየትኛው አውራጃ ዋና ከተማ ነበረች?
Anonymous Quiz
50%
ሀ. መቄዶንያ
36%
ለ. አካይያ
9%
ሐ. ፍርግያ
6%
መ. ጵንፍልያ
.       ──•◈•─────•◈•─
                          የዕለቱ ጥቅስ
        ──•◈•─────•◈•─
“እውቀትን ጠልተዋልና፥ እግዚአብሔርንም መፍራት አልመረጡምና፤”
ምሳሌ 1፥29



ወደ ቻናሉ ለመ🀄️🀄️ል፦ @Holy_scriptures
6
Audio
#መጻሕፍትን_በድምጽ

📔ርዕስ፦ የመጽሐፍ ቅዱስ አስተምህሮ
👤ጸሐፊ፦ ዶ/ር ቻርልስ ሲ.ራይሪ
🗣ተርጓሚ፦ ሲሳይ ደሳለኝ
👉ክፍል-8

ይቀጥላል...


ወደ ቻናሉ ለመ🀄️🀄️ል፦ @Holy_scriptures
1
ቅዱሳት መጻሕፍት
#ጰራቅሊጦስ የቀጠለ... በቅዱሳት መጸሕፍት መንፈስ ቅዱስ ጰራቅሊጦስ ተብሎ ተገልጿል። ጰራቅሊጦስ (ግሪክ፡ παράκλητος፣ ላቲን፡ ጰራቅሊጦስ) ጠበቃ ወይም ረዳት ማለት ነው። በክርስትና ውስጥ፣ “ጰራቅሊጦስ” የሚለው ቃል በአብዛኛው የሚያመለክተው መንፈስ ቅዱስን ነው። ጰራቅሊጦስ የመጣው ከኮይኔ የግሪክ ቃል ነው παράκλητος (paráklētos)። ይህ ስያሜ የሁለት ጥምር ቃል ውህደት ነው።…
#በዓለ_ኀምሳ
#ጰራቅሊጦስ

የቀጠለ...



ለ. መንፈስ ቅዱስ የእግዚአብሔርን መልእክት ለሕዝቡ ለመንገር ይሠራ ነበር፡፡

ለምሳሌ በምድረ በዳ እስራኤላውያንን ይመራ የነበረው መንፈስ ቅዱስ ነው (ነህ 9፥20)፡፡ የእስራኤል መዘምራን መዝሙራቸውን በዘመሩ ጊዜ፣ የዘመሩት በጌታ መንፈስ ነው (2ሳሙ 23፥2፤ ከሐሥ1፥16፣20)፡፡ እንደዚሁም ነቢያት ቃሉን ለሕዝቡ ለመንገር በእግዚአብሔር መንፈስ ይመሩ ነበር (ዘኊ 11፥29፣ 1ሳሙ 10፥5-6፡10፣ 2ዜና 20፥14፤ 24፥19-20፤ ነህ 9፥30፤ ኢሳ 61፡1-3፤ ሚካ 3፥8፤ ዘካ 7፥12፤ ከ2ጴጥ 1፥20-21)። ሕዝቅኤል በገለጸው መሠረት ሐሰተኛ ነቢያት ተለይተው የሚታወቁበት አንዱ መንገድ፣ የእግዚአብሔርን መንፈስ ከመከተል ይልቅ፣ የራሳቸውን መንፈስ መከተላቸው ነው (ሕዝ 13፥2-3)፤ የእግዚአብሔርን ሕዝብ በተመለከተ ትክክለኛውን መልእክት ለመንገር የእግዚአብሔር መንፈስ፣ ከእግዚአብሔር ጋር ትክክለኛ ኅብረት በሌለውም ሰው ላይ ይመጣ እንደ ነበር ማስተዋል ተገቢ ነው (ዘኊ 24፥2)፡፡

ሐ. በብሉይ ኪዳን ዘመን የእግዚአብሔር ሕዝብ የአመራር ኀይልን ያገኝ የነበረው በጌታ መንፈስ ነው::

ለምሳሌ ሙሴ ከእግዚአብሔር መንፈስ ጋር ኅብረት በማግኘቱ የእግዚአብሔርን ሐሳብ በመጋራት፣ እግዚአብሔር ሲያዝን ዐዘነ፤ በኀጢአት ላይ ሲቈጣም ተቈጣ (ዘፀ 33፥11፣ ከዘፀ 32፥19)፡፡ ሙሴ እስራኤላውያንን በመምራት የሚያግዙትን ሰባ ሽማግሌዎች በታዛዥነት በመረጠ ጊዜ፣ እግዚአብሔር በእርሱ ላይ ከነበረው መንፈስ ወስዶ በእነርሱ ላይ እንዲሆን አደረገ (ዘኊ 11፥16-17፤ 11፥12)፡፡ እንደዚሁም ኢያሱ ሙሴን እንዲተካ በተሾመ ጊዜ እግዚአብሔር፣ “መንፈስ” (ይኸውም መንፈስ ቅዱስ) በእርሱ ላይ እንደ ነበር አመለከተ (ዘኊ 27፥18)፡፡ ያው መንፈስ በጌዴዎን (መሳ 6፥34)፣ በዳዊት (1ሳሙ 16፥13) እና በዘሩባቤል ላይ መጥቶአል (ዘካ 4፥6)፡፡ በሌላ አገላለጽ በብሉይ ኪዳን ለመሪነት የሚያስፈልገው ዐቢይ የብቃት መለኪያ፣ የእግዚአብሔር መንፈስ በሰውየው ላይ መገኘቱ ነው፡፡

መ. የእግዚአብሔር መንፈስ አንዳንድ ግለሰቦችን ለተለየ አገልግሎት ብቁ ለማድረግ በእነርሱም ላይ ሊመጣ ይችላል፤

በብሉይ ኪዳን በጣም የታወቀውና በምሳሌነት ሊጠቀስ የሚችለው ዮሴፍ ነው፤ ለእርሱም በፈርዖን አገዛዝ ውስጥ በመሪነት ቦታ ላይ ሆኖ ፍሬ ያለው ተግባር እንዲያከናውን የእግዚአብሔር መንፈስ ተሰጥቶት ነበር (ዘፍ 41፥38)፡፡ ባስልኤልንና ኤልያብም ለማደሪያው ድንኳን ሥራ ለሚሆነው የጥበብ ተግባርና ሌሎችንም ለማስተማር እግዚአብሔር በመንፈስ ሞልቶአቸው ነበር (ዘፀ 31፥1-11፤ 35፥30-35)፡፡ ከዚህ ላይ፣ “በመንፈስ ቅዱስ መሞላት” ሲባል በአዲስ ኪዳን ላይ ከሚገኘው ከመንፈስ ቅዱስ መጠመቅ ጋር ሙሉ በሙሉ አንድ አለመሆኑን ማስተዋል ተገቢ ነው፡፡ በብሉይ ኪዳን መንፈስ ቅዱስ፣ በተመረጡና የተለየ ሥራን ለእግዚአብሔር ለማከናወን በተለዩ ጥቂት ሰዎች ላይ መጣ፤ ኀይልም ሰጣቸው (ዘፀ 31፥3)። መንፈስ ቅዱስ እንደ ጎቶንያል (መሳ 3፥9-10)፣ ጌዴዎን (መሳ 6፥34)፣ ኢዮሣፍጥ (መሳ 11፥29) እና ሳምሶን ባሉት በአያሌ መሳፍንት ላይ መጣ፤ እነዚህ ምሳሌዎች የእግዚአብሔርን ዘላቂ መርሕ ያሳያሉ፤ እግዚአብሔር ሰዎችን በእጅጉ ሊገለገልባቸው ሲፈልግ፣ መንፈሱ በእነርሱ ላይ ይመጣል፡፡


ይቀጥላል...



ምንጭ፦ ምሉእ ሕይወት፤ ገጽ 1314-1315፣ 1679




ወደ ቻናሉ ለመ🀄️🀄️ል፦ @Holy_scriptures
8👍2🥰1
ቅዱሳት መጻሕፍት
ክርስቲያናዊ ዓቅብተ እምነት – CHRISTIAN APOLOGETICS ክፍል-1 መግቢያ “ዳሩ ግን ጌታን እርሱም ክርስቶስ በልባችሁ ቀድሱት። በእናንተ ስላለ ተስፋ ምክንያትን ለሚጠይቁዋችሁ ሁሉ መልስ ለመስጠት ዘወትር የተዘጋጃችሁ ሁኑ፥ ነገር ግን በየዋህነትና በፍርሃት ይሁን።” 1ጴጥ. 3፥15 የክርስቶስ ቤተ ክርስቲያን ያለ ተግዳሮት የኖረችበት ዘመን የለም፡፡ በየዘመናቱ የነበሩት…
ክርስቲያናዊ ዓቅብተ እምነት – CHRISTIAN APOLOGETICS



          ክፍል-2

1.2. የክርስቲያን ዓቅብተ እምነት ታሪክ

የክርስቲያን ዓቅብተ እምነት ታሪክ ከመጀመርያው ክፍለ ዘመን የሚጀምር ቢሆንም እንደ አንድ የጥናት ዘርፍ የጎለበተውና ወጥ የሆነ መልክ የያዘው ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ነው፡፡ ክርስቲያናዊው ዓቅብተ እምነት በተለያዩ የዕድገት ደረጃዎች ውስጥ አልፏል፡፡

ክርስትና በተጀመረበት ዘመንና ተከትለው በነበሩት ጥቂት ክፍለ ዘመናት መካከል ክርስቲያኖች በሮማ መንግሥት ከፍተኛ ስደት ይደርስባቸው ነበር፡፡ ይህንን ስደት ለመቀስቀስና ለማጽደቅ ተቃዋሚዎች የተለያዩ የሐሰት ክሶችን ይጠቀሙ ነበር፡፡ ኔሮ የተባለው የሮም ንጉሥ ክርስቲያኖች ላይ ስደት ለማስነሳት በ64 ዓ.ም. ለስድስት ተከታታይ ቀናት በመንደድ የሮምን ከተማ አብዛኛውን ክፍል ያወደመውን የእሳት አደጋ ያቀጣጠሉት ክርስቲያኖች እንደሆኑ በሐሰት እንደወነጀላቸው ታሲተስ የተባለ ሮማዊ ጸሐፌ ታሪክ ዘግቧል፡፡ የጌታን እራት በቀጥታ በመተርጎም ክርስቲያኖች የሰው ሥጋ እንደሚበሉም ተከሰው ነበር፡፡ እንዲሁም ክርስቲያኖች “ወንድምና እህት” በማለት እርስ በርሳቸው የመጠራራት ልማድ ስለነበራቸው ይህንንም በቀጥታ በመተርጎም የዝምድና ጋብቻ (incest) እንደሚፈጽሙ ተወርቶባቸዋል፡፡ የይሁዲ ኃይማኖት፣ ኖስቲዝምና የግሪክ ፍልስፍና የክርስትናን አስተምህሮ የሚገዳደሩ አስተሳሰቦችም ነበሩ፡፡ እነዚህን የመሳሰሉ ውንጀላዎችንና ስም ማጥፋቶችን እንዲሁም አስተምሕሯዊ ተግዳሮቶችን ለመከላከል የጥንት የቤተ ክርስቲያን አበው የተለያዩ ጽሑፎችን መጻፍ አስፈልጓቸው ነበር፡፡

በጥቅሉ ሲታይ የአበው ጽሑፎች ሦስት ዓላማዎችን ያነገቡ ነበሩ። እነርሱም፦

1⃣ክርስትናን ከሐሰት ክሶችና ውንጀላዎች መከላከል

2⃣የብሉይ ኪዳን ትንቢቶች ፍጻሜ ላይ በመመሥረት የክርስትና አስተምህሮ እውነት መሆኑን ማስረዳት

3⃣ክርስትና የግሪክ ፍልስፍና ላዕላይና ምልዓት መሆኑን ማስረዳት ናቸው፡፡

የኋለኞቹ ክርስቲያን ዓቃቤ እምነታውያን ሥራዎች የተለያዩ የክርስትና አስተምሕሮዎችን ከተቃዋሚዎች በመከላከልና ስለ እግዚአብሔር መኖር አመክንዮአዊ ማስረጃዎችን በማቅረብ ላይ ያተኮሩ ናቸው፡፡

1.2.1. የጥንት ቤተ ክርስቲያን አቃቤ እምነታውያን


በዓቃቤ እምነታዊ ሥራቸው ከሚታወቁ የጥንት ቤተ ክርስቲያን አበው መካከል ዮስጦስ ሰማዕት (100-165 ዓ.ም.) ይጠቀሳል፡፡ ይህ አባት ከፕሌቶ የፍልስፍና አስተምሕሮ ወደ ክርስትና የተለወጠ ነበር፡፡ “ከአይሁዳዊው ትሪፎ ጋር የተደረገ ውይይት” በሚለው ጽሑፉ ውስጥ ኢየሱስ አይሁድ ሲጠብቁት የነበሩት መሲህ መሆኑን ለማሳየት የብሉይ ኪዳንን ትንቢቶች እንደ ማስረጃ ተጠቅሟል፡፡ “አፖሎጂስ” በሚል ርዕስ በተጻፉት ሁለት ጽሑፎቹ ውስጥ ደግሞ ክርስትና ነጻነትን ማግኘት ይችል ዘንድ የተለያዩ የሐሰት ክሶችን ውድቅ በማድረግና ከግብረ ገብነት አንጻር ክርስትና የበላይነት ያለው እውነተኛ ፍልስፍና መሆኑን በማመልከት ተከራክሯል፡፡ ዮስጦስ ሰማዕት የክርስቶስን ማንነት በተመለከተ ይከተል የነበረው አስተምሕሮ መጠነኛ ችግር የነበረበት ቢሆንም የአዲስ ኪዳን ጽሑፎች ከተጻፉ በኋላ ከተነሱት አበው መካከል ለክርስቲያናዊው ዓቅብተ እምነት መሠረት የጣለ ሰው እንደነበር መናገር ይቻላል፡፡


ይቀጥላል...



ወደ ቻናሉ ለመ🀄️🀄️ል፦ @Holy_scriptures
10👏1
ወደ ቻናሉ ለመ🀄️🀄️ል፦ @Holy_scriptures
3
አዲሱ_መደበኛ_ትርጉም_ከማጥኛ_ጹሑፍ_ጋር.pdf
198.9 MB
📜ርዕስ፦ አዲሱ መደበኛ ትርጉም
ከማጥኛ ጽሑፍ ጋር
💾መጠን፦ 198.9MB



ወደ ቻናሉ ለመ🀄️🀄️ል፦ @Holy_scriptures
👏76👍3
.       ──•◈•─────•◈•─
                          የዕለቱ ጥቅስ
        ──•◈•─────•◈•─
“ትክክለኛና ቀና የሆነውን በማድረግ የእግዚአብሔርን (ያህዌ) መንገድ ይጠብቁ ዘንድ ልጆቹንና ከእርሱ በኋላ ቤተ ሰቦቹን እንዲያዝ መርጬዋለሁ፤ ይኸውም እግዚአብሔር (ያህዌ) ለአብርሃም የሰጠው ተስፋ ሁሉ እንዲፈጸም ነው።”
ዘፍጥረት 18፥19 (አዲሱ መ.ት)



ወደ ቻናሉ ለመ🀄️🀄️ል፦ @Holy_scriptures
7
Audio
#መጻሕፍትን_በድምጽ

📔ርዕስ፦ የመጽሐፍ ቅዱስ አስተምህሮ
👤ጸሐፊ፦ ዶ/ር ቻርልስ ሲ.ራይሪ
🗣ተርጓሚ፦ ሲሳይ ደሳለኝ
👉ክፍል-9 (የመጨረሻ ክፍል)


ወደ ቻናሉ ለመ🀄️🀄️ል፦ @Holy_scriptures
የአማኝ ሕይወት በእድገት መቀጠል ሲገባው ለምን ወደ ኋላ ይላል?

በመንፈሳዊ ሕይወት ውስጥ ከማደግ ይልቅ ወደ ኋላ ማፈግፈግ ብዙ ጊዜ ይስተዋላል። ከእነዚህ ምክንያቶች ውስጥ ዛሬ አንዱን እንመለከታለን።

1. "ተንኰልን የሙጥኝ " ብሎ ሲይዝ

2. "ሊመለስም እንቢ" ሲል

“እንግዲህ ይህ የኢየሩሳሌም ሕዝብ ዘወትር ስለ ምን ወደ ኋላው ይመለሳል? ተንኰልን ይዞአል ሊመለስም እንቢ ብሎአል።”
(ኤርምያስ 8፥5)

“ታዲያ፣ ይህ ሕዝብ ለምን ፊቱን አዙሮ ወደ ኋላ ይሄዳል? ለምንስ ኢየሩሳሌም ዘወትር ወደ ኋላ ትመለሳለች? ተንኰልን የሙጥኝ ብለው ይዘዋል፤ ሊመለሱም ፈቃደኛ አይደሉም።”
ኤርምያስ 8፥5 (አዲሱ መ.ት)


"እንግዲህ ክፋትን ሁሉ ተንኰልንም ሁሉ ግብዝነትንም ቅንዓትንም ሐሜትንም ሁሉ አስወግዳችሁ፥ ጌታ ቸር መሆኑን ቀምሳችሁ እንደ ሆነ፥ ለመዳን በእርሱ እንድታድጉ አሁን እንደ ተወለዱ ሕፃናት ተንኰል የሌለበትን የቃልን ወተት ተመኙ።"
(1ኛ ጴጥሮስ 2፥1-3)

ለመሆኑ "ተንኮል" ማለት ምን ማለት ነው? እስቲ በዚህ ነገር በአሳብ መስጫው ላይ አሳብ ስጡበት፤ ተወያዩበትም።



ወደ ቻናሉ ለመ🀄️🀄️ል፦ @Holy_scriptures
13👍3
.       ──•◈•─────•◈•─
                          የዕለቱ ጥቅስ
        ──•◈•─────•◈•─
“ጌታ ኢየሱስም ከእነርሱ ጋር ከተናገረ በኋላ ወደ ሰማይ ዐረገ በእግዚአብሔርም ቀኝ ተቀመጠ።”
ማርቆስ 16፥19



ወደ ቻናሉ ለመ🀄️🀄️ል፦ @Holy_scriptures
9👍3
ዛሬ የጌታችን እና የመድኃኒታችን የኢየሱስ ክርስቶስ ዕርገት የሚከበርበት ቀን ነው። ከትንሣኤ በኋላ 40 ቀን መሆኑ ነው። ምድራዊ ተልእኮውን ጨርሶ ወደ አብ ያረገበት የክብር ጊዜ ነው። ዕርገቱ የስንብት አይደለም፣ ነገር ግን የተስፋው ቃል ማለትም ስፍራ ሊያዘጋጅልን እንደሚሄድ (ዮሐ. 14፥2-3) እና መንፈስ ቅዱስ ኃይል እንዲሰጠንና እንዲመራን እንደሚልክ የተናገረበትም ነው። ዕርገቱ ክርስቶስ በክብር እንደሚነግሥ፣ ስለ እኛ እንደሚማልድ ያሳስበናል፣ እናም ዜግነታችን በሰማይ መሆኑን ያረጋግጥልናል። ደቀ መዛሙርቱ ቆመው ሰማዩን እየተመለከቱ ሳለ የመላእክት መልእክት አሁንም ያስተጋባል። “... ወደ ሰማይ እየተመለከታችሁ ስለ ምን ቆማችኋል?” (ሐዋርያት 1፥11) አዎ፣ በፍርሃት ቀና ብለን ብቻ ሳይሆን በተልእኮ ወደ ፊት እንሂድ እስከ ምድር ዳርቻ ድረስ ምስክሮቹ እንሁን!



ወደ ቻናሉ ለመ🀄️🀄️ል፦ @Holy_scriptures
🔥104
ቅዱሳት መጻሕፍት
#በዓለ_ኀምሳ #ጰራቅሊጦስ የቀጠለ... ለ. መንፈስ ቅዱስ የእግዚአብሔርን መልእክት ለሕዝቡ ለመንገር ይሠራ ነበር፡፡ ለምሳሌ በምድረ በዳ እስራኤላውያንን ይመራ የነበረው መንፈስ ቅዱስ ነው (ነህ 9፥20)፡፡ የእስራኤል መዘምራን መዝሙራቸውን በዘመሩ ጊዜ፣ የዘመሩት በጌታ መንፈስ ነው (2ሳሙ 23፥2፤ ከሐሥ1፥16፣20)፡፡ እንደዚሁም ነቢያት ቃሉን ለሕዝቡ ለመንገር በእግዚአብሔር መንፈስ ይመሩ…
#በዓለ_ኀምሳ
#ጰራቅሊጦስ

የቀጠለ...


ሠ. መንፈስ ቅዱስ አንድን ሰው ቀጥተኛ በሆነው የጽድቅ አኗኗር ለመምራት ፍላጎት እንዳለው በብሉይ ኪዳን ላይ ተስተውሎአል፤

ከዚህ ሐሳብ ጋር በተያያዘ መልኩም ዳዊት በአንዳንድ መዝሙሮቹ ላይ መስክሮአል (መዝ 51፥10-13፣ 143፥10)። የእግዚአብሔር ሕዝብ እግዚአብሔርን በመስማት ፈንታ የግላቸውን መንገድ የሚከተሉ ከሆነ፣ በትክክል ሲታይ የመንፈስ ቅዱስን መንገድ አንከተልም እያሉ ነው (ዘፍ 16፥2)፡፡ በእግዚአብሔር መንፈስ እየተመሩ ያልኖሩት፣ የእግዚአብሔርን ፍርድ በተለያየ መልኩ ሳይቀበሉ አልቀረም (ዘኊ 14፥29፤ ዘዳ1፥26)፡፡

ረ. በብሉይ ኪዳን ዘመን፣ መንፈስ ቅዱስ ለአገልግሎት ለማብቃት ወይም ትንቢት እንዲናገሩ ለማድረግ የመጣው በጣት በሚቈጠሩ ሰዎች ላይ መሆኑን ማስተዋል ተገቢ ነው

ለእስራኤል ሕዝብ ሁሉ የሆነ የመንፈስ ቅዱስ መውረድ አልነበረም (ከኢዮኤል 2፥28-29፤ ከሐሥ 2፥4፡16-18)፤ እስከ ታላቁ የጰንጠቆስጤ ዕለት ድረስ፣ ሰፋ ባለ መልኩ የመንፈስ ቅዱስ መውረድ አልተከሠተም ነበር (ሐሥ 2)።

2. በአዲስ ኪዳን መንፈስ ቅዱስ ራሱን የገለጠበት ሥራ፡፡

ሀ. መንፈስ ቅዱስ ስለ በደል የሚወቅስ (ዮሐ 16፥7-8)፣

ስለ ኢየሱስ ያለውን እውነት የሚገልጥ (ዮሐ 14፥16፡26)፣ አዲስ ልደትን የሚሰጥ (ዮሐ 3፥3-6)፣ ወደ ክርስቶስ አካል ውስጥ እንድንገባ የሚያደርግ የድነት ኀይል ነው። በክርስቶስ አምነን ስንለወጥ መንፈስ ቅዱስን እንቀበላለን (ዮሐ 3፥3-6፤ 20፥22)፤ የመለኮታዊ ባሕርይ ተካፋይም እንሆናለን (2ጴጥ 1፥4)።

ለ. መንፈስ ቅዱስ መቀደስን የሚያመጣ ኀይል ነው፡፡

በክርስቶስ አምነው በሚለወጡበት ጊዜ አማኞች የመንፈስ ቅዱስ ማደሪያ ይሆናሉ፤ ከዚያም በእርሱ የመቀደስ ተግባር ሥር ይሆናሉ (ሮሜ 8፥9፤ 1ቆሮ 6፡19)፡፡ መንፈስ ቅዱስ በውስጣችን ሲኖር፣ የሚሠራውን ሥራ ልብ በሉ፡፡ እርሱ ይቀድሰናል፣ ይኸውም ያነጻናል፤ ከኀጢአት ባርነት ነጻ በማውጣትም (ሮሜ 8፥24፣ ገላ 5፥16-17፤ 2ተሰ 2፥13) በቅዱስ ኑሮ እንድንመራ ያደፋፍረናል ማለት ነው፡፡ የእግዚአብሔር ልጆች እንደ ሆንን ይነግረናል (ሮሜ 8፥6)፣ እግዚአብሔርን በምናመልክበት ጊዜ (ሐሥ 10፥46) እና በጸሎት ሕይወታችን ያግዘናል፤ ወደ እግዚአብሔርም በምንጮኸበት ጊዜ ይማልድልናል (ሮሜ 8፥26-27)። ክርስቶስን እናከብር ዘንድ የክርስቶስ የሆኑትን የጸጋ ባሕርያት በውስጣችን ይፈጥርልናል (ገላ 5፥22-23፤ 1ጴጥ 1፥2)። እርሱ ኢየሱስን ለእኛ በመግለጥ፣ ከኢየሱስ ጋር የቀረበ ኅብረትና አንድነት እንዲኖረን በማድረግ (ዮሐ 14፥16-18፤ 16፥14)፡፡ ወደ እውነት ሁሉ የሚመራን መለኮታዊ አስተማሪያችን ነው (ዮሐ 16፥13፤ 14፥26፤ 1ቆሮ 2፥9-16)፡፡ ባለማቋረጥ የእግዚአብሔርን ፍቅር ወደ እኛ ያስተላልፋል (ሮሜ 5፥5)፡ ደስታን መጽናናትንና ርዳታን ይሰጠናል (ዮሐ 14፥16፤ 1ተሰ 1፥6)፡፡


ይቀጥላል...



ምንጭ፦ ምሉእ ሕይወት፤ ገጽ 1314-1315፣ 1679-80




ወደ ቻናሉ ለመ🀄️🀄️ል፦ @Holy_scriptures
6👍4