. ──•◈•─────•◈•─
የዕለቱ ጥቅስ
──•◈•─────•◈•─
“እርሱ ለዘመንህ የሚያስተማምን መሠረት፣ የድነት፣ የዕውቀትና የጥበብ መዝገብ ይሆናል፤ እግዚአብሔርንም መፍራት የዚህ ሀብት ቍልፍ ነው።”
ኢሳይያስ 33፥6 (አዲሱ መ.ት)
ወደ ቻናሉ ለመ🀄️ላ🀄️ል፦ @Holy_scriptures

❤8
Audio
#መጻሕፍትን_በድምጽ
📔ርዕስ፦ የመጽሐፍ ቅዱስ አስተምህሮ
👤ጸሐፊ፦ ዶ/ር ቻርልስ ሲ.ራይሪ
🗣ተርጓሚ፦ ሲሳይ ደሳለኝ
👉ክፍል-3
ይቀጥላል...
ወደ ቻናሉ ለመ🀄️ላ🀄️ል፦ @Holy_scriptures
📔ርዕስ፦ የመጽሐፍ ቅዱስ አስተምህሮ
👤ጸሐፊ፦ ዶ/ር ቻርልስ ሲ.ራይሪ
🗣ተርጓሚ፦ ሲሳይ ደሳለኝ
👉ክፍል-3
ይቀጥላል...
ወደ ቻናሉ ለመ🀄️ላ🀄️ል፦ @Holy_scriptures
👍3
አምልኮ
አምልኮ የሚለው ቃል በመሰረቱ በዕብራይስጥ አቦዳ (Aboda) በግሪክ ፕሮስኪኒስ (Proskneo) የሚለው ሲሆን ለአንድ ጌታ ብቻ የተገዛ ባሪያ ሊያቀርበው የሚገባ ፍጹምና ሁለንተናዊ አገልግሎት ነው። አምልኮ፣ ስግደትን፣ ውዳሴን፣ አክብሮትን ዝማሬን፣ ፀሎትን፣ መስዋዕትን፣ መልካም ስራን፣ ፈሪሃ እግዚአብሔርን፣ ፍቅርን፣ ሕይወትን አጠቃሎ ለእግዚአብሔር አምላክ ብቻ መስጠት ማለት ነው። ስለዚህ አምልኮ ለአምላክህ ብቻ የሚገባና የሚሰጥ አገልግሎት ወይም መሰጠት ነው።
በመጽሐፍ ቅዱስ አምላክ የሚለው ቃል የሚያመለክተው፦
ሀ. እግዚአብሔርን (ዘፀ 20፥2)
ለ. ጣዖትን (ዘዳ 4፥28)
ሐ. ሰይጣንን (2ቆሮ 4፥4)
መ. የሰውን ቀዳሚ ምኞት (ፊል 3፥19)
የአምልኮ ትርጉም፦
የተስተካከለ የሕይወት አቅጣጫ ወይም ለእግዚአብሔር ሙሉ ለሙሉ የመገዛት ሕይወት ነው።
ሀ. አገልግሎት ነው (ኢያሱ 24፥15)
ለ. መልካም ምግባር እና ንጹሕ ሕይወት ነው (ያዕ 1፥26፤ ሮሜ 12፥11)
ሐ. ለእግዚአብሔር ታላቅነት በመንፈስ እና በእውነት መስገድ ነው (ያዕ 4፥19፣24)
መ. እግዚአብሔር ከሰጠን ገንዘብ እና ንብረት ውስጥ መልሰን ለእርሱ መስጠት ነው (ምሳሌ 3፥9)
ምንጭ:- wongelcenter.com

👍8❤4👏1
. ──•◈•─────•◈•─
የዕለቱ ጥቅስ
──•◈•─────•◈•─
“እኛኮ ትርፍ ለማግኘት ብለን የእግዚአብሔርን ቃል ቀላቅለው እንደሚሸቃቅጡት እንደ ብዙዎቹ አይደለንም፤ ነገር ግን ከእግዚአብሔር እንደተላኩ ሰዎች በክርስቶስ ሆነን በእግዚአብሔር ፊት በቅንነት እንናገራለን።”
2ኛ ቆሮንቶስ 2፥17 (አዲሱ መ.ት)

❤8👍2
Audio
👍4❤2
Audio
#መጻሕፍትን_በድምጽ
📔ርዕስ፦ የመጽሐፍ ቅዱስ አስተምህሮ
👤ጸሐፊ፦ ዶ/ር ቻርልስ ሲ.ራይሪ
🗣ተርጓሚ፦ ሲሳይ ደሳለኝ
👉ክፍል-4
ይቀጥላል...
ወደ ቻናሉ ለመ🀄️ላ🀄️ል፦ @Holy_scriptures
📔ርዕስ፦ የመጽሐፍ ቅዱስ አስተምህሮ
👤ጸሐፊ፦ ዶ/ር ቻርልስ ሲ.ራይሪ
🗣ተርጓሚ፦ ሲሳይ ደሳለኝ
👉ክፍል-4
ይቀጥላል...
ወደ ቻናሉ ለመ🀄️ላ🀄️ል፦ @Holy_scriptures
👍4
The-Wiersbe-Bible-Commentary-Old-Testament.pdf
9.1 MB
THE WIERSBE BIBLE COMMENTARY: OLD TESTAMENT.
Published by David C. Cook. 4050 Lee Vance View.
Colorado Springs, CO 80918 U.S.A..
ወደ ቻናሉ ለመ🀄️ላ🀄️ል፦ @Holy_scriptures
Published by David C. Cook. 4050 Lee Vance View.
Colorado Springs, CO 80918 U.S.A..
ወደ ቻናሉ ለመ🀄️ላ🀄️ል፦ @Holy_scriptures
❤6👍2
. ──•◈•─────•◈•─
የዕለቱ ጥቅስ
──•◈•─────•◈•─
“ከክፉ የጎልማሳነት ምኞት ግን ሽሽ፥ በንጹሕም ልብ ጌታን ከሚጠሩ ጋር ጽድቅን እምነትን ፍቅርን ሰላምን አጥብቀህ ተከተል።”
2ኛ ጢሞቴዎስ 2፥22

❤9👏1
Audio
#መጻሕፍትን_በድምጽ
📔ርዕስ፦ የመጽሐፍ ቅዱስ አስተምህሮ
👤ጸሐፊ፦ ዶ/ር ቻርልስ ሲ.ራይሪ
🗣ተርጓሚ፦ ሲሳይ ደሳለኝ
👉ክፍል-5
ይቀጥላል...
ወደ ቻናሉ ለመ🀄️ላ🀄️ል፦ @Holy_scriptures
📔ርዕስ፦ የመጽሐፍ ቅዱስ አስተምህሮ
👤ጸሐፊ፦ ዶ/ር ቻርልስ ሲ.ራይሪ
🗣ተርጓሚ፦ ሲሳይ ደሳለኝ
👉ክፍል-5
ይቀጥላል...
ወደ ቻናሉ ለመ🀄️ላ🀄️ል፦ @Holy_scriptures
🥰3❤1👏1
በቅዱሳት መጻሕፍት ውስጥ ካሉ ነቢያት መካከል ከሚከተሉት ስም እና የስም ፍቺ ጥምረት ትክክል ያልሆነው የቱ ነው?
Anonymous Quiz
25%
ሀ. ናሆም --❯ እግዚአብሔር ያጽናናል
20%
ለ. ኢሳይያስ --❯ እግዚአብሔር ያድናል
24%
ሐ. አብድዩ --❯ የእግዚአብሔር አገልጋይ
32%
መ. ኤርምያስ --❯ የእግዚአብሔር መልእክተኛ
#እራሳችንን_እንመርምር
የሰው ልጅ በምድር ላይ ሲመላለስ ይልቁን ክርስቲያን ለሽያጭ፣ ለድርድር ወይንም ለጥቅም ከማስቀመጥ ይልቅ ዋጋ የሚከፍልላቸው እና የሚከፍልባቸው ብዙ ነገሮች አሉ። ከእነዚህም መካከል እውነት አንዷ ናት! መንፈሳዊ ነገር፣ የወንጌል ነገር ለራስ ጥቅም በገበያ ወጥተው አይቸረቸሩም። ስንት ጊዜ ኑሮን ለማሸነፍ ይሁን በሌላ ሰበብ እውነትን በርዘናት፣ ደልዘናት፣ ሸቅጠናት. . . ለገበያ እንዳሰጣናት ፈጣሪ ይወቀው! ግን እሷን ሽጠን የት ለመድረስ? ምን ለመሆን?
“እውነትን ግዛ አትሽጣትም፥ ጥበብን ተግሣጽን ማስተዋልንም።”
ምሳሌ 23፥23
“እኛኮ ትርፍ ለማግኘት ብለን የእግዚአብሔርን ቃል ቀላቅለው እንደሚሸቃቅጡት እንደ ብዙዎቹ አይደለንም፤ ነገር ግን ከእግዚአብሔር እንደተላኩ ሰዎች በክርስቶስ ሆነን በእግዚአብሔር ፊት በቅንነት እንናገራለን።”
2ኛ ቆሮንቶስ 2፥17 (አዲሱ መ.ት)
ወደ ቻናሉ ለመ🀄️ላ🀄️ል፦ @Holy_scriptures
የሰው ልጅ በምድር ላይ ሲመላለስ ይልቁን ክርስቲያን ለሽያጭ፣ ለድርድር ወይንም ለጥቅም ከማስቀመጥ ይልቅ ዋጋ የሚከፍልላቸው እና የሚከፍልባቸው ብዙ ነገሮች አሉ። ከእነዚህም መካከል እውነት አንዷ ናት! መንፈሳዊ ነገር፣ የወንጌል ነገር ለራስ ጥቅም በገበያ ወጥተው አይቸረቸሩም። ስንት ጊዜ ኑሮን ለማሸነፍ ይሁን በሌላ ሰበብ እውነትን በርዘናት፣ ደልዘናት፣ ሸቅጠናት. . . ለገበያ እንዳሰጣናት ፈጣሪ ይወቀው! ግን እሷን ሽጠን የት ለመድረስ? ምን ለመሆን?
“እውነትን ግዛ አትሽጣትም፥ ጥበብን ተግሣጽን ማስተዋልንም።”
ምሳሌ 23፥23
“እኛኮ ትርፍ ለማግኘት ብለን የእግዚአብሔርን ቃል ቀላቅለው እንደሚሸቃቅጡት እንደ ብዙዎቹ አይደለንም፤ ነገር ግን ከእግዚአብሔር እንደተላኩ ሰዎች በክርስቶስ ሆነን በእግዚአብሔር ፊት በቅንነት እንናገራለን።”
2ኛ ቆሮንቶስ 2፥17 (አዲሱ መ.ት)
ወደ ቻናሉ ለመ🀄️ላ🀄️ል፦ @Holy_scriptures
❤2👍1
. ──•◈•─────•◈•─
የዕለቱ ጥቅስ
──•◈•─────•◈•─
“ጨው መልካም ነው፤ ጨው ግን አልጫ ቢሆን በምን ታጣፍጡታላችሁ? በነፍሳችሁ ጨው ይኑርባችሁ፥ እርስ በርሳችሁም ተስማሙ።”
ማርቆስ 9፥50

❤4👍2🙏2
Audio
#መጻሕፍትን_በድምጽ
📔ርዕስ፦ የመጽሐፍ ቅዱስ አስተምህሮ
👤ጸሐፊ፦ ዶ/ር ቻርልስ ሲ.ራይሪ
🗣ተርጓሚ፦ ሲሳይ ደሳለኝ
👉ክፍል-6
ይቀጥላል...
ወደ ቻናሉ ለመ🀄️ላ🀄️ል፦ @Holy_scriptures
📔ርዕስ፦ የመጽሐፍ ቅዱስ አስተምህሮ
👤ጸሐፊ፦ ዶ/ር ቻርልስ ሲ.ራይሪ
🗣ተርጓሚ፦ ሲሳይ ደሳለኝ
👉ክፍል-6
ይቀጥላል...
ወደ ቻናሉ ለመ🀄️ላ🀄️ል፦ @Holy_scriptures
👍3
#በዓለ_ኀምሳ
#ጰራቅሊጦስ
ጴንጤቆስጤ! የጴንጠቆስጤ ቀን የዋለው ከኢየሱስ ትንሣኤ በኋላ በሃምሣኛው ቀን ነው። በግሪክ ጴንጠቆስጤ ማለት «ሃምሣኛ» ማለት ነው። በብሉይ ኪዳን መሠረት ጴንጠቆስጤ የሚውለው የአይሁድ ፋሲካ በዓል ከሆነ በኋላ በሚቀጥለው እሑድ በሃምሳኛው ቀን ሲሆን (ዘሌ. 23፥15) ይኸው ቀን ደግሞ ክርስቲያኖች ትንሣኤን ካከበሩ በሃምሳኛው ቀን መሆኑ ነው። በዓለ ኀምሳ (ጴንጤቆስጤ)፣ የሰባቱ ሱባዔ በዓል (ዘዳ 16፥10)፣ የመከር በዓል (ዘጸ 23፥16)፤ የበኩራት ቀንም(ዘኁ 28፥26) ይባላል። አይሁዶች የመከር በዓልን የሚያከብሩት በጴንጠቆስጤ ዕለት ነበር (ዘጸ. 34፥22፤ ዘዳ. 16፥9–10)። በተመሳሳይ ሁኔታ ጰንጠቆስጤ ለቤተ ክርስቲያን በዓለም ውስጥ ያሉ ነፍሳት የእግዚኣብሔር መከር በመሆን የሚሰበሰቡበት ጅማሬ ነው፡፡
አይሁዶች የጴንጠቆስጤ ዕለትን የሚያከብሩበት ሁለተኛ ምክንያትም አላቸው። ይኸውም እግዚአብሔር ሕጉን የሰጣቸው በዚያ ቀን እንደሆነ ስለሚያምኑ ነው። ስለዚህም በዚያን ቀን እግዚአብሔር ለደቀ መዛሙርቱ ለመጀመሪያ ጊዜ የመንፈስ ቅዱስን ጥምቀት መስጠቱ በጣም ተስማሚ ነበር ማለት ነው።
በቀጣይ ጌታ ቢፈቅድ መንፈስ ቅዱስ ማን ነው? ምን ሊሰራ መጣ ወይም ዋና ሥራው ምንድን ነው? የሚለውን እንመለከታለን።
ይቀጥላል...
ምንጭ፦ የአዲስ ኪዳን ማብራሪያ፤ ገጽ 292፣ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ከማጥኛ ጽሑፍ ጋር፤ ገጽ 1646፣ ምሉእ ሕይወት፤ ገጽ 1668

❤6🥰5👍2🔥2👏1
. ──•◈•─────•◈•─
የዕለቱ ጥቅስ
──•◈•─────•◈•─
“እግዚአብሔርንም መፍራት ባስተማረ በዘካርያስ ዘመን እግዚአብሔርን ይፈልግ ዘንድ ልብ አደረገ እግዚአብሔርንም በፈለገ ጊዜ እግዚአብሔር ነገሩን አከናወነለት።”
2 ዜና 26፥5
ወደ ቻናሉ ለመ🀄️ላ🀄️ል፦ @Holy_scriptures
የዕለቱ ጥቅስ
──•◈•─────•◈•─
“እግዚአብሔርንም መፍራት ባስተማረ በዘካርያስ ዘመን እግዚአብሔርን ይፈልግ ዘንድ ልብ አደረገ እግዚአብሔርንም በፈለገ ጊዜ እግዚአብሔር ነገሩን አከናወነለት።”
2 ዜና 26፥5
ወደ ቻናሉ ለመ🀄️ላ🀄️ል፦ @Holy_scriptures
❤7
Audio
#መጻሕፍትን_በድምጽ
📔ርዕስ፦ የመጽሐፍ ቅዱስ አስተምህሮ
👤ጸሐፊ፦ ዶ/ር ቻርልስ ሲ.ራይሪ
🗣ተርጓሚ፦ ሲሳይ ደሳለኝ
👉ክፍል-7
ይቀጥላል...
ወደ ቻናሉ ለመ🀄️ላ🀄️ል፦ @Holy_scriptures
📔ርዕስ፦ የመጽሐፍ ቅዱስ አስተምህሮ
👤ጸሐፊ፦ ዶ/ር ቻርልስ ሲ.ራይሪ
🗣ተርጓሚ፦ ሲሳይ ደሳለኝ
👉ክፍል-7
ይቀጥላል...
ወደ ቻናሉ ለመ🀄️ላ🀄️ል፦ @Holy_scriptures
👍1
ቅዱሳት መጻሕፍት
#መጻሕፍትን_እንመርምር የኢየሱስ ክርስቶስ ትንሣኤ የአካል ወይስ የመንፈስ? ክፍል-፮ ሀ. “ከእናንተ አንዳንዶቹ ትንሣኤ ሙታን የለም እንዴት ይላሉ?” (ቊጥር 12) ጳውሎስ ይህን መልእክት የጻፈው ከአቴና ትንሽ ኪሎ ሜትር ወረድ ብላ በምትገኘው ቆሮንቶስ ነው:: በዚያ የሞቱ ሰዎች ዳግም ሕይወት…
#መጻሕፍትን_እንመርምር
የኢየሱስ ክርስቶስ ትንሣኤ የአካል ወይስ የመንፈስ?
ክፍል-፯
መ. “እንዲሁ ደግሞ፣ ፊተኛው ሰው አዳም ሕያው ነፍስ ሆነ ተብሎ ተጽፎአል፤ ኋለኛው አዳም ሕይወትን የሚሰጥ መንፈስ ሆነ” (ቊጥር 45)
በዚህ ክፍል ላይ የተነጻጸሩት ነፍስ (ግሪክ “ሱቼ” ) እና መንፈስ (ግሪክ “ኒውማ”) መፈታት ያለባቸው ከቊጥር 44 አንጻር ነው:: ስለዚህ በቊጥር 44 ላይ ያለው ንጽጽር በሚሞተው አካል (ለኀጢአትና ለውጤቱ ሰለባ የሆነው) እንዲሁም በትንሣኤ አካል (ከኀጢአት ተጽእኖ ውጪ የሆነው) መካከል ነው:: በቊጥር 45 ላይም የምናገኘው ንጽጽር ይኸው ነው፡፡ አካል በሚፈጠርበት ጊዜ ኀጢአተኛ ስላልነበር የኀጢአትም ጥቃት አልደረሰበትም:: ነገር ግን በኀጢአት በመውደቁ ምክንያት ተበላሸ፣ ረከሰ፣ ደከመ፣ ሞተ፡፡
ሠ. “የፊተኛው ሰው ከመሬት መሬታዊ ነው፤ ሁለተኛው ሰው ከሰማይ ነው” (ቊጥር 47)
ይህ ክፍል ኢየሱስን ሰው ይለዋል። ለኀጢአት ክፍያ ኢየሱስ ሰብአዊነቱን ትቶአል ከሚለው የይሖዋ ምስክሮች ትምህርት በቀጥታ ይጣረሳል፡፡ የትንሣኤ አካል ዐፈር ብቻ አይደለም፤ ነገር ግን ለሕይወት ብቁ እንዲሆን የተለወጠ ነው (ቊጥር 48)።
ረ “ሥጋና ደም የእግዚአብሔርን መንግሥት ሊወርሱ አይችሉም፤ የሚበሰብሰውም የማይበሰብሰውን አይወርስም” (ቊጥር 50)
የይሖዋ ምስክሮች አብዛኛውን ጊዜ የመጀመሪያውን ዐረፍተ ነገር ብቻ መጥቀስ ይወዳሉ፡፡ ነገር ግን ተከታዩ ዐረፍተ ነገር የክፍሉን ሐሳብ በተሟላ መልኩ ይገልጻል። የሚሞተው አካላችን ችግሩ ቊሳዊ አካል መሆኑ ሳይሆን፣ ስለተበላሸ፣ የሚበሰብስ ስለሆነ ነው:: በመጽሐፍ ቅዱስ፣ “ሥጋና ደም” የሚለውን አገላለጽ በምድር ብቻ የተወሰነ መሆንን፣ ድካምን የሚገልጽ ሥዕላዊ ቋንቋ ነው (ማቴዎስ 16÷17፤ ገላትያ 1÷16፤ ኤፌሶን 6÷12፤ ዕብራውያን 2÷14)።
የእግዚአብሔርን መንግሥት ያለመውረሳችን ምክንያቱ በኀጢአት መውደቃችን ነው (1ቆሮንቶስ 6÷9-10፤ ገላትያ 5÷12)። ስለዚህ የእግዚአብሔርን መንግሥት ለመውረስ ቊሳዊ አካልን መተው ሳይሆን (1ቆሮንቶስ 15÷50) የተበላሸውን ሁኔታችንን የሚያድስና የሚያስተካክል የመንፈስ ቅዱስ ሰማያዊ ሕይወት ማግኘት ነው (1ጴጥሮስ 1÷4)::
ሰ. “ሙታን የማይበሰብሱ ሆነው ይነሣሉ፤ እኛም እንለወጣለን፡፡ ይህ የሚበሰብሰው የማይበሰብሰውን ሊለብስ ይህም የሚሞተው የማይሞተውን ሊለብስ ይገባዋል” (ቊጥር 52-53)
ጳውሎስ በዚህ ክፍል እያጠናከረ ያለው ትምህርት፣ ሥጋና ደም የእግዚአብሔርን መንግሥት ሊወርስ መለወጥ የግድ እንደሚያስፈልገው ነው። እሱን በማጥፋት መንፈሳዊ በሆነው አካል መቀየር አስፈላጊ አይደለም፡፡ ይህ የተበላሸ፣ ሟች የሆነው ሰብአዊነት የማይሞተውንና የማይበሰብሰውን መልበስ ያስፈልገዋል፡፡ አሁን ያለን ይህ አካላችን ቀጣይነት ይኖረዋል፤ ነገር ግን የሚበሰብሰው ክፍል ሊለወጥ ይገባዋል፡፡
ሸ. “በዚያን ጊዜ ሞት ድል በመንሣት ተዋጠ ተብሎ የተጻፈው ቃል ይፈጸማል” (ቊጥር 54)
ትንሣኤ ሞትን ድል የሚያደርገው የሚሞተው አካል በሕይወት ሲታደስ ብቻ ነው::
ይቀጥላል...
ምንጭ፦ ዶ/ር ተስፋዬ ሮበሌ፤ በሥጋ ትንሣኤ አምናለሁ! የአስተምህሮተ ትንሣኤ መጽሐፍ ቅዱሳዊ፣ ታሪካዊና ሥነ አመክንዮአዊ ትንታኔ፤ ከምእራፍ ሰባት የተወሰደ

❤3👏2👍1
ቅዱሳት መጻሕፍት
#በዓለ_ኀምሳ #ጰራቅሊጦስ ጴንጤቆስጤ! የጴንጠቆስጤ ቀን የዋለው ከኢየሱስ ትንሣኤ በኋላ በሃምሣኛው ቀን ነው። በግሪክ ጴንጠቆስጤ ማለት «ሃምሣኛ» ማለት ነው። በብሉይ ኪዳን መሠረት ጴንጠቆስጤ የሚውለው የአይሁድ ፋሲካ በዓል ከሆነ በኋላ በሚቀጥለው እሑድ በሃምሳኛው ቀን ሲሆን (ዘሌ. 23፥15) ይኸው ቀን ደግሞ ክርስቲያኖች ትንሣኤን ካከበሩ በሃምሳኛው ቀን መሆኑ ነው። በዓለ ኀምሳ (ጴንጤቆስጤ)፣…
#
በእግዚአብሔር ቤዛነትን የመስጠት ዐላማ ውስጥ መንፈስ ቅዱስ የሚሠራውን አስፈላጊ ሥራ አማኞች መረዳት ይኖርባቸዋል፡፡ ያለ መንፈስ ቅዱስ ኀይል ፍጥረት፣ ፍጥረተ ዓለም እንዲሁም የሰው ዘር (ዘፍ 1:2፤ ኢዮ 33:4) አይኖርም ነበር:: ያለመንፈስ ቅዱስም መጽሐፍ ቅዱስ (2ጴጥ 1፥21)፣ አዲስ ኪዳን (ዮሐ 14፥26፤ 15፡26-27፤ (ቆሮ 2፡10-14)፣ ወንጌልን ለማወጅ የሚያስችል ኀይል (ሐሥ 1፥8) አይኖርም፡፡ ያለ መንፈስ ቅዱስ እምነት፣ አዲስ ልደት፣ ቅድስና እውን አይሆንም እንዲሁም ክርስቲያኖች በዓለም ውስጥ አይኖሩም ነበር፡፡
የመንፈስ ቅዱስ አካል፣ በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ መንፈስ ቅዱስ የራሱ የሆነ የግል ማንነት እንዳለው ተገልጾአል (2ቆሮ 3፥17-18፤ ዕብ 9፥14፤ 1ጴጥ 1፥2)። እርሱ ልክ እንደ እግዚአብሔር አብና እንደ እግዚአብሔር ወልድ መለኮታዊ ማንነት አለው፡፡ ስለዚህ መንፈስ ቅዱስ ስሜት አነሣሽ ወይም ኀይል ብቻ አይደለም:: የራሱ የሆነ ባሕርይ አለው፤ ያስባል (ሮሜ 8፥27)፤ ስሜት አለው (ሮሜ 15፥30)፣ ፈቃድ አለው (1ቆሮ 12፥11) እንዲሁም ኅብረትን የመውደድና በኅብረትም ደስ የመሰኘት ችሎታ አለው፡፡ አማኞች ከኢየሱስ ጋር ወደ ቀረበ ሀልዎትና ኅብረት ውስጥ ይገቡ ዘንድ መንፈስ ቅዱስ በእግዚአብሔር አብ ተልኮአል (ዮሐ 14፥16-18፥26)፡፡ ከእነዚህ እውነቶች አንጻር መንፈስ ቅዱስን እንደ አንድ አካል በመቊጠርና በልባችን ውስጥ የሚኖር ዘላለማዊ ሕያው አምላክ እንደ ሆነ በማሰብ አምልኮአችን፤ ፍቅራችንና መገዛታችን ለእርሱ እንደሚገባው ሆኖ መቅረብ ይኖርበታል (ማር 1፥11)፡፡
የመንፈስ ቅዱስ ሥራ፤
1. በብሉይ ኪዳን መንፈስ ቅዱስ ራሱን የገለጠበት ሥራ፡፡
የቃሉ ምንነት፣ “መንፈስ” የሚለው የዕብራይስጥ አቻ ቃል፣ “ሩሕ” የሚል ነው፣ ይህም ቃል አንዳንድ ጊዜ፣ "ነፋስ” ወይም “ትንፋሽ" ተብሎ ይተረጐማል፡፡ ስለዚህ ብሉይ ኪዳን የእግዚአብሔር ትንፋሽ ወይም ከእግዚአብሔር የሆነ ነፋስ ሲል (ለምሳሌ ዘፍ 2፥7፤ ሕዝ 37፥9-10፡14) የሚያመለክተው የእግዚአብሔርን መንፈስ ሥራ ሊሆን ይችላል፡፡
መጽሐፍ ቅዱስ በብሉይ ኪዳን ዘመን የነበረውን ልዩ ልዩ የመንፈስ ቅዱስን ሥራ ይገልጻል፤
ሀ. ፍጥረት በተፈጠረበት ጊዜ መንፈስ ቅዱስ የፈጣሪነት ተግባሩን አከናውኖአል፡፡
የመጽሐፍ ቅዱስ ሁለተኛው ጥቅስ፣ ለዓለም መልክና ቅርጽ በመስጠት ለእግዚአብሔር ፈጣሪ ቃል ለማዘጋጀት፣ “የእግዚአብሔር መንፈስ በውሆች ላይ ይረብብ ነበር” (ዘፍ 1፥2) ይላል፡፡ የእግዚአብሔር ቃልና (ይኸውም ከሥላሴ ሁለተኛው አካል) የእግዚአብሔር መንፈስ ሁለቱም፣ ፍጥረት ሲፈጠር ፈጣሪዎች ነበሩ (ኢዮ 26፥13፤ መዝ 33፥6)። በተጨማሪም መንፈስ ቅዱስ የሕይወት ፈጣሪ ነው፣ እግዚአብሔር አዳምን በፈጠረ ጊዜ፣ የሕይወትን እስትንፋስ ወደ እርሱ እፍ ያለበት ያለጥርጥር መንፈሱ ነበር (ዘፍ 2፥7፤ ከኢዮ 27፥3)፤ መንፈስ ቅዱስም ለእግዚአብሔር ፍጥረት ሁሉ ሕይወትን በመስጠት ረገድ ዛሬም ቢሆን እንደ ቀጠለ ነው (ኢዮ 33፥4፤ መዝ 104፥30)።
ይቀጥላል...
ምንጭ፦ lsj.gr/wiki/paracletus፣ ምሉእ ሕይወት፤ ገጽ 1314፣ 1679
ወደ ቻናሉ ለመ🀄️ላ🀄️ል፦ @Holy_scriptures
ጰራቅሊጦስ
የቀጠለ...
በቅዱሳት መጸሕፍት መንፈስ ቅዱስ ጰራቅሊጦስ ተብሎ ተገልጿል። ጰራቅሊጦስ (ግሪክ፡ παράκλητος፣ ላቲን፡ ጰራቅሊጦስ) ጠበቃ ወይም ረዳት ማለት ነው። በክርስትና ውስጥ፣ “ጰራቅሊጦስ” የሚለው ቃል በአብዛኛው የሚያመለክተው መንፈስ ቅዱስን ነው። ጰራቅሊጦስ የመጣው ከኮይኔ የግሪክ ቃል ነው παράκλητος (paráklētos)። ይህ ስያሜ የሁለት ጥምር ቃል ውህደት ነው። “ፓራ” (በጎን/ጎን) እና “ካሌይን” ("to call" ወይም ለመጥራት)። በመጀመሪያ በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ በዮሐንስ 14፡16 ይገኛል። በአጠቃላይ በአዲስ ኪዳን 5 ጊዜ የተጠቀሰ ሲሆን 4 ጊዜ በዮሐንስ ወንጌል(14፥16፤ 14፥26፤ 15፥26፤ 16፥7) አንድ ጊዜ ደግሞ በ1ኛ ዮሐንስ መልእክት (2፥1) ውስጥ ይገኛል። በ1ኛ ዮሐንስ ያለው ቃል የሚናገረው ስለጌታችን እና መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ነው።በእግዚአብሔር ቤዛነትን የመስጠት ዐላማ ውስጥ መንፈስ ቅዱስ የሚሠራውን አስፈላጊ ሥራ አማኞች መረዳት ይኖርባቸዋል፡፡ ያለ መንፈስ ቅዱስ ኀይል ፍጥረት፣ ፍጥረተ ዓለም እንዲሁም የሰው ዘር (ዘፍ 1:2፤ ኢዮ 33:4) አይኖርም ነበር:: ያለመንፈስ ቅዱስም መጽሐፍ ቅዱስ (2ጴጥ 1፥21)፣ አዲስ ኪዳን (ዮሐ 14፥26፤ 15፡26-27፤ (ቆሮ 2፡10-14)፣ ወንጌልን ለማወጅ የሚያስችል ኀይል (ሐሥ 1፥8) አይኖርም፡፡ ያለ መንፈስ ቅዱስ እምነት፣ አዲስ ልደት፣ ቅድስና እውን አይሆንም እንዲሁም ክርስቲያኖች በዓለም ውስጥ አይኖሩም ነበር፡፡

🔥3❤2👍2