#የእግዚአብሔር_ቃል_ምን_ይላል?
መዝሙር 25
¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯
¹ አቤቱ፥ ወደ አንተ ነፍሴን አነሣለሁ።
² አምላኬ፥ አንተን ታመንሁ፤ አልፈር፥ ጠላቶቼ በእኔ አይሣቁብኝ።
³ አንተን ተስፋ የሚያደርጉ አያፍሩም፤ በከንቱ የሚገበዙ ያፍራሉ።
⁴ አቤቱ፥ መንገድህን አመልክተኝ፥ ፍለጋህንም አስተምረኝ።
⁵ አንተ የመድኃኒቴ አምላክ ነህና በእውነትህ ምራኝ፥ አስተምረኝም፤ ቀኑን ሁሉ አንተን ተስፋ አድርጌአለሁ።
⁶ አቤቱ፥ ምሕረትህንና ቸርነትህን አስብ፥ ከጥንት ጀምሮ ናቸውና።
⁷ የልጅነቴን ኃጢአትና መተላለፍ አታስብብኝ፤ አቤቱ፥ ስለ ቸርነትህ ብዛት እንደ ምሕረትህ አስበኝ።
⁸ እግዚአብሔር ቸር ቅንም ነው፤ ስለዚህ ኃጢአተኞችን በመንገድ ይመራቸዋል።
⁹ ገሮችን በፍርድ ይመራል፥ ለገሮችም መንገድን ያስተምራቸዋል።
¹⁰ የእግዚአብሔር መንገድ ሁሉ ቸርነትና እውነት ነው። ቃል ኪዳኑንና ምስክሩን ለሚጠብቁ።
¹¹ አቤቱ፥ ኃጢአቴ እጅግ ነውና ስለ ስምህ ይቅር በለኝ።
¹² እግዚአብሔርን የሚፈራ ሰው ማን ነው? በሚመርጠው መንገድ ያስተምረዋል።
¹³ ነፍሱ በመልካም ታድራለች፥ ዘሩም ምድርን ይወርሳል።
¹⁴ እግዚአብሔር ለሚፈሩት ኃይላቸው ነው፥ ቃል ኪዳኑንም ያስታውቃቸዋል።
¹⁵ እርሱ እግሮቼን ከወጥመድ ያወጣቸዋልና ዓይኖቼ ሁልጊዜ ወደ እግዚአብሔር ናቸው።
¹⁶ እኔ ብቻዬንና ችግረኛ ነኝና ፊትህን ወደ እኔ አድርግ ማረኝም።
¹⁷ የልቤ ችግር ብዙ ነው፤ ከጭንቀቴ አውጣኝ።
¹⁸ ድካሜንና መከራዬን እይ፥ ኃጢአቴንም ሁሉ ይቅር በለኝ።
¹⁹ ጠላቶቼ እንደ በዙ እይ፥ የግፍም ጥል ጠልተውኛል።
²⁰ ነፍሴን ጠብቅና አድነኝ፤ አንተን ታምኛለሁና አልፈር።
²¹ አንተን ተስፋ አድርጌአለሁና የውሃትና ቅንነት ይጠብቁኝ።
²² አቤቱ፥ እስራኤልን ከመከራው ሁሉ አድነው።
ወደ ቻናሉ ለመ🀄️ላ🀄️ል፦ @Holy_scriptures

👍5❤4
. ──•◈•─────•◈•─
የዕለቱ ጥቅስ
──•◈•─────•◈•─
“ሰው ሆይ፥ መልካሙን ነግሮሃል፤ እግዚአብሔርም ከአንተ ዘንድ የሚሻው ምንድር ነው? ፍርድን ታደርግ ዘንድ፥ ምሕረትንም ትወድድ ዘንድ፥ ከአምላክህም ጋር በትሕትና ትሄድ ዘንድ አይደለምን?”
ሚክያስ 6፥8

❤7
#እራሳችንን_እንመርምር
መንፈሣችንን መቆጣጠር ላይ እንዴት ነን? መንፈሣችን ቅጥር ከሌለው የክርስትና ሕይወታችን ተጠብቆ ለጌታ ቀን የምንበቃውስ በየትኛው መንገድ ነው?
“ቅጥር እንደሌላት እንደ ፈረሰች ከተማ፥ መንፈሱን የማይከለክል ሰው እንዲሁ ነው።”
ምሳሌ 25፥28

👍1🙏1
. ──•◈•─────•◈•─
የዕለቱ ጥቅስ
──•◈•─────•◈•─
“እግዚአብሔር የላከው የእግዚአብሔርን ቃል ይናገራልና፤ እግዚአብሔር መንፈሱን ሰፍሮ አይሰጥምና።”
ዮሐንስ 3፥34

👍2
#መጻሕፍትን_በድምጽ
📔ርዕስ፦ የመጽሐፍ ቅዱስ አስተምህሮ
👤ጸሐፊ፦ ዶ/ር ቻርልስ ሲ.ራይሪ
🗣ተርጓሚ፦ ሲሳይ ደሳለኝ
ወደ ቻናሉ ለመ🀄️ላ🀄️ል፦ @Holy_scriptures
📔ርዕስ፦ የመጽሐፍ ቅዱስ አስተምህሮ
👤ጸሐፊ፦ ዶ/ር ቻርልስ ሲ.ራይሪ
🗣ተርጓሚ፦ ሲሳይ ደሳለኝ
ወደ ቻናሉ ለመ🀄️ላ🀄️ል፦ @Holy_scriptures
👍4
ቅዱሳት መጻሕፍት
#እምነት ክፍል-8 በቅዱሳት መጻሕፍት መሠረት እምነታችንን ለመጠበቅ ምን እናድረግ? 1. ጸሎት እና በእግዚአብሔር ላይ መደገፍ “እኔ ግን እምነትህ እንዳይጠፋ ስለ አንተ ጸለይሁ፤ አንተም በተመለስህ ጊዜ ወንድሞችህን አበርታ።”” ሉቃስ 22፥32 (አዲሱ መ.ት) ኢየሱስ እምነታችንን ለመጠበቅ ጸሎት አስፈላጊ እንደሆነ ያስተምራል። በጸሎት የእግዚአብሔርን…
#እምነት
ክፍል-9
እምነት እና ሥራ
በመጽሐፍ ቅዱስ መሠረት ሰው የሚድነው ወይም የሚጸድቀው በእምነት እንጂ በሥራ እንዳልሆነ እርግጥ ነው፤ ይህ በእምነት የመጽደቅ ጉዳይም በሰው ዘንድ ሳይሆን በእግዚአብሔር ዘንድ የሚታየው ነው፡፡
በሮሜ 4፥1‐8 የምናገኘው የእግዚአብሔር ቃል ይህን የሚያረጋግጥ ነው፤ በቊ.1 ላይ «በሥጋ አባታችን የሆነ አብርሃም ምን አገኘ እንላለን? አብርሃም በሥራ ጸድቆ ቢሆን የሚመካበት አለውና፤ ነገር ግን በእግዚአብሔር ዘንድ አይደለም» ይላል፤ «በእግዚአብሔር ዘንድ አይደለም» የሚለው ይህ ቃል በእግዚአብሔር ዘንድ በሥራ መጽደቅ እንደሌለ የሚገልጽ ነው፡፡
በዚህ ክፍል ሰው ያለ ሥራ በእምነት እንደሚጸድቅ ለማሳየት ሁለት ሰዎች በምሳሌነት ተጠቅሰዋል፤ እነርሱም አብርሃምና ዳዊት ናቸው፡፡ እነዚህ ሁለት ሰዎች በአንድነት መጠቀሳቸው በመጽሐፍ ቅዱስ የተለመደ ሲሆን (ማቴ.1፥1፤ የሐ.ሥ.13፥26‐36) ይህንንም ታላቅ ርእሰ ጉዳይ ለማብራራት አብረው መጠቀሳቸው ወሳኝ ነው፡፡ አብርሃም የነበረው ሕግ ከመሰጠቱ በፊት ሲሆን ዳዊት ደግሞ በሕጉ ዘመን የነበረ ሰው ነው፤ ከሁለቱም ሰዎች አንጻር ሲታይ ግን በእግዚአብሔር ዘንድ ጽድቅ የሚቈጠረው በሥራ ሳይሆን በእምነት እንደሆነ ተብራርቷል፡፡
በቊ.3 ላይ አብርሃምን በተመለከተ ሲገልጽ «መጽሐፍስ ምን አለ? አብርሃም እግዚአብሔርን አመነ ጽድቅም ሆኖ ተቈጠረለት፤ ለሚሠራ ደመወዝ እንደ ዕዳ ነው እንጂ እንደ ጸጋ አይቈጠርለትም፤ ነገር ግን ለማይሠራ ኃጢአተኛውን በሚያጸድቅ ለሚያምን ሰው እምነቱ ጽድቅ ሆኖ ይቈጠርለታል» ይላል፡፡ በዚህም ቃል ውስጥ አብርሃም ጽድቅን ያገኘው እግዚአብሔርን ስላመነ ተቈጥሮለት እንጂ ጽድቅ ሠርቶ እንዳልሆነ እንገነዘባለን፡፡ ይህም ለሚያምን ሰው ሁሉ እግዚአብሔር የሚያደርገው መሆኑ ተገልጿል፡፡ በመቀጠል ደግሞ ዳዊት ይህን ጉዳይ በተመለከተ የተናገረው ተጠቅሷል፡፡ ይኸውም «እንደዚህም ደግሞ እግዚአብሔር ያለ ሥራ ጽድቅን ስለሚቈጥርለት ሰው ብፅዕና ይናገራል እንዲህ ሲል፤ ‘ዓመፃቸው የተሰረየላቸው ኃጢአታቸውም የተከደነላቸው ብፁዓን ናቸው፤ ጌታ ኃጢአቱን የማይቈጥርበት ሰው ብፁዕ ነው»(ቊ.6‐8)፤ በአብርሃም ሕይወት እንዳየነው እግዚአብሔር ሊቈጠርልን የማይገባውን ጽድቅ በእምነት ሲቈጥርልን እናያለን፤ በዚህ ዳዊት በተናገረው ቃል ውስጥ ደግሞ እግዚአብሔር ሊቈጥርብን የሚገባውን ኃጢአት ባለመቊጠር ጸጋውን ሲያሳይ እንመለከታለን፡፡ ይህም «እግዚአብሔር ያለ ሥራ ጽድቅን ስለሚቈጥርለት ሰው ብፅዕና» የተነገረ መሆኑ ተገልጿል፡፡ ስለዚህ በሮሜ 4 ውስጥ የተሰጠው ትምህርት ሰው በእግዚአብሔር ዘንድ የሚጸድቀው ያለ ሥራ በእምነት መሆኑን የሚያሳይ ነው፤ ይህ እምነት በሥራ ሊገለጥ የሚችል እውነተኛ መሆኑን እግዚአብሔር ማወቅ ይችላልና፡፡
በያዕ.2 ውስጥ የምናገኘው ትምህርት ግን ጽድቅ ወይም መዳን በሰው ዘንድ የሚታየው ወይም የሚረጋገጠው በእምነት ብቻ ሳይሆን በሥራም እንደሆነ የሚገልጽ ነው፡፡ በሰው ዘንድ የአንድ ሰው እምነት እውነተኛ እምነት መሆኑ ሊታይ የሚችለው በሥራ ነው፤ በቊ.14 ላይ «ወንድሞች ሆይ እምነት አለኝ የሚል ሥራ ግን የሌለው ሰው ቢኖር ምን ይጠቅመዋል፤ እምነቱስ ሊያድነው ይችላልን?» በማለት ያዕቆብ ጥያቄ ያነሳል፤ እዚህ ላይ «እምነት አለኝ» የሚለው ያ ሰው ራሱ ነው፡፡
ይቀጥላል...
ምንጭ፦ 1bible.page

👍9❤2🔥1😁1
. ──•◈•─────•◈•─
የዕለቱ ጥቅስ
──•◈•─────•◈•─
“ተመልሶ ይምረናል፤ ክፋታችንንም ይጠቀጥቃል፥ ኃጢአታችንንም በባሕሩ ጥልቅ ይጥለዋል።”
ሚክያስ 7፥19

❤7🙏2
Audio
#መጻሕፍትን_በድምጽ
📔ርዕስ፦ የመጽሐፍ ቅዱስ አስተምህሮ
👤ጸሐፊ፦ ዶ/ር ቻርልስ ሲ.ራይሪ
🗣ተርጓሚ፦ ሲሳይ ደሳለኝ
👉መግቢያ
ይቀጥላል...
ወደ ቻናሉ ለመ🀄️ላ🀄️ል፦ @Holy_scriptures
📔ርዕስ፦ የመጽሐፍ ቅዱስ አስተምህሮ
👤ጸሐፊ፦ ዶ/ር ቻርልስ ሲ.ራይሪ
🗣ተርጓሚ፦ ሲሳይ ደሳለኝ
👉መግቢያ
ይቀጥላል...
ወደ ቻናሉ ለመ🀄️ላ🀄️ል፦ @Holy_scriptures
👍8❤1
ክርስቲያናዊ ዓቅብተ እምነት – CHRISTIAN APOLOGETICS
ክፍል-1
መግቢያ
“ዳሩ ግን ጌታን እርሱም ክርስቶስ በልባችሁ ቀድሱት። በእናንተ ስላለ ተስፋ ምክንያትን ለሚጠይቁዋችሁ ሁሉ መልስ ለመስጠት ዘወትር የተዘጋጃችሁ ሁኑ፥ ነገር ግን በየዋህነትና በፍርሃት ይሁን።” 1ጴጥ. 3፥15
የክርስቶስ ቤተ ክርስቲያን ያለ ተግዳሮት የኖረችበት ዘመን የለም፡፡ በየዘመናቱ የነበሩት ተግዳሮቶች አንድ መልክ ባይኖራቸውም ነገር ግን አንድ ዓላማና ግብ ያላቸው ሆነው እናገኛቸዋለን፡፡ እርሱም ቤተ ክርስቲያንን ማዳክም ብሎም ማጥፋት ነው፡፡ ነገር ግን በተለያዩ ዘመናት የኖሩት ክርስቲያኖች መሠረታዊውን የክርስትና አስተምሕሮ ከውስጣዊና ውጫዊ ተግዳሮቶች ተከላክሎ በማቆየቱ ረገድ በመንፈስ ቅዱስ እርዳታ ከፍተኛውን ሚና ተጫውተዋል፡፡
የምንኖረው መንፈሳዊ ውጊያ ባለበት ዓለም ውስጥ ነው፡፡ ውጊያው ደግሞ የሚደረገው በሰዎች አዕምሮ ውስጥ ነው፡፡ ይህንን ውጊያ ለማሸነፍ የተዘጋጀንና የታጠቅን መሆን ያስፈልገናል፡፡ የዚህ ጽሑፍ ዓላማ ስለ ክርስቲያናዊ ዓቅብተ እምነት ታሪካዊ አመጣጥና መጽሐፍ ቅዱሳዊነት መሠረታዊ ግንዛቤን ማስጨበጥ ነው። መጽሐፍ ቅዱስ 1ቆሮ 10፥4-6 ላይ በተናገረው መሠረት በእግዚአብሔር ሐሳብ ላይ የሚነሳውን ከፍ ያለውን የሰውን ሐሳብ በማፍረስ አዕምሮን ሁሉ ለክርስቶስ እንዴት መማረክ እንደምንችል ክርስቲያናዊውን መንገድ ያመላክታል፡፡ አንባቢያንም ስለ ክርስቲያናዊ ዓቅብተ እምነት የበለጠ ጥናት እንዲያደርጉ እንደሚያነሳሳና አቅጣጫን እንደሚጠቁም ይታመናል።
1.የክርስቲያናዊ ዓቅብተ እምነት ትርጉምና ታሪክ
1.1. ትርጉም
“አፖሎጀቲክስ” የሚለው የእንግሊዘኛ ቃል አፖሎጊያ ከሚል የግሪክ ቃል የመጣ ሲሆን ትርጓሜውም “በመከላከል መናገር” እንደ ማለት ነው፡፡ በጥንታዊቷ ግሪክ የሕግ ስርኣት ውስጥ ሁለት ቁልፍ የሆኑ ቃላት ጥቅም ላይ ይውሉ ነበር፤ የከሳሽ ወገን ንግግር “ካታጎሪያ” በመባል የሚታወቅ ሲሆን የተከሳሽ ወገን ምላሽ ደግሞ “አፖሎጊያ” በመባል ይታወቃል፡፡ “አፖሎጊያ’ የሚለው ቃል በአዲስ ኪዳን ውስጥ በተደጋጋሚ ተጠቅሷል። በሐዋርያት ሥራ 26፥2 ላይ ሐዋርው ጳውሎስ ተከሶ በፊስጦስና አግሪጳ ፊት በቀረበ ጊዜ ተጠቅሞበታል፤ እንዲሁም በፊልጵስዩስ 1፥7፣ 1፥16 እና 1ጴጥሮስ 3፥15 ላይ እናገኘዋለን፡፡
ዓቅብተ እምነት ከነገረ መለኮት የጥናት ዘርፎች መካከል አንዱ ሲሆን መረጃዎችን በተቀናበረ ሁኔታ በመጠቀም ለሃይማኖታዊ አስተምህሮ ጥብቅና መቆም ነው፡፡ የአንድ ሃይማኖት አስተምህሮ ትክክል መሆኑንና እምነቱን መምረጥ ከሰው አመክንዮአዊ አስተሳሰብ ጋር የማይጣረስ መሆኑን ለማሳየት የሚደረግ ጥረትም ነው፡፡ ስለዚህ ዓቅብተ እምነት ሰዎች አስተሳሰባቸውን እንዲለውጡ የማሳመን ሥራ ነው፡፡ ክርስቲያናዊ ዓቅብተ እምነት ክርስቲያናዊ ሥነ መለኮት (Christian Theology)፣ ተፈጥሯዊ ሥነ መለኮት (Natural Theology) እና ፍልስፍናን በማጣመር ክርስቲያናዊውን አስተምህሮ ከውጪያዊ ጥቃቶችና የተሳሳቱ ትርጓሜዎች ለመከላከል ይጥራል፣ እንዲሁም የሌሎች ንፅረተ ዓለማት አስተምሕሮዎችን ይመረምራል፡፡
ይቀጥላል...
ምንጭ:- ewnetlehulu.org

👍5
. ──•◈•─────•◈•─
የዕለቱ ጥቅስ
──•◈•─────•◈•─
“ምድርም በእግዚአብሔር ፊት ተበላሸች፤ ምድርም ግፍን ተሞላች።”
ዘፍጥረት 6፥11

👍5😢1
Audio
#መጻሕፍትን_በድምጽ
📔ርዕስ፦ የመጽሐፍ ቅዱስ አስተምህሮ
👤ጸሐፊ፦ ዶ/ር ቻርልስ ሲ.ራይሪ
🗣ተርጓሚ፦ ሲሳይ ደሳለኝ
👉ክፍል-1
ይቀጥላል...
ወደ ቻናሉ ለመ🀄️ላ🀄️ል፦ @Holy_scriptures
📔ርዕስ፦ የመጽሐፍ ቅዱስ አስተምህሮ
👤ጸሐፊ፦ ዶ/ር ቻርልስ ሲ.ራይሪ
🗣ተርጓሚ፦ ሲሳይ ደሳለኝ
👉ክፍል-1
ይቀጥላል...
ወደ ቻናሉ ለመ🀄️ላ🀄️ል፦ @Holy_scriptures
👍5
ንስር
ንስር የአእዋፍ ንጉስ በመባል የሚታወቅ የወፍ ዘር ነው ታላላቅ ነገስታት ንስርን ለተለያዩ ነገሮች መግለጫነት እንደ ምሳሌ ተጠቅመዋል ለነጻነት ለሥልጣን ለግርማና ለመሳሰሉት በዚህ ጹሑፍ ግን የምናተኩረው አስገራሚ የሆነ መመሳሰል በንስር ባሕሪና በክርስቲያን ሕይወት ውስጥ መኖሩን ነው በዚህች አጭር ጹሑፍ ውስጥ አምስት ነጥቦችን ብቻ እንመልከታለን፡፡
1. ንስር ስፍራውን አይለቅም
የተለያ አዕዋፍና አራዊት ከአየር ንብረት ለውጥ ጋር በተዛመደ መልኩ ጎጆዋቸውንና ስፍራቸውን በመተው ወደሌላ ቦታ ይሰደዳሉ ይህም ፍልሰት በመባል ይታወቃል ኀይለኛ ፍልሰት በመባል ይታወቃል ኃይለኛ የክረምት ወቅት ሲመጣ ብዙዎቹ ወደ ሌላ አካባቢ እስከ እረጅም እርቀት ድረስ በመጓዝ ሀገር ሁሉ አቋርጠው ይሰደዳሉ ንስር ግን እንደዚህ አይደለም ክረምት አልፎ በጋም እንደሚመጣ ያውቃል በመሆኑም በብዙ ድካምና ጥረት የሠራውን ጎጆውን ጥሎ አይሸሽም እንደምንም ብሎ በጎጆው ውስጥ በመሆን ያን የክረምትን ወራት ያሳልፋል ንስር የክረምት ወራት ያሳልፋል ንስር ክርስቲያኖችም እንደዚህ ናቸው ወጀብ አውሎ ንፋስ ስለበዛባቸው ብቻ እግዚአብሔርን ካስቀመጣቸው ቦታና ከሰጣቸው ስፍራ ተነስተው አይሄዱም ጌታ ወጀቡን ጸጥ በማድረግ እንደሚያሻግራቸው ያውቃሉ በሆኑም በስፍራቸው ጸንተው ይቆያሉ(ናሆም 1፡3)
2. የንስር ጠላት
ንሰር አንድ ጠላት ብቻ አለው ያም እባብ ነው ንስር ቤቱን የሚሰራው ከፍ ባለ አለት ላይ ስለሆነ ከእባብ ሌላ ምንም ሊደርስበት አይችልም እባብ ግን ተስታኮ ወደ ጎጆው ሊያመራና የንስርን እንቁላሎች ወይም ጫጩቶችን ሊጎዳ ይችላል ከዚህም የተነሳ ሴቷ ንስር እንቁላሎች ወይም ጫቹቶችን ሊጎዳ ይችላል ከዚህም የተነሳ ሴቷ ንስር እንቁላሎችዋንም ሆነ ጫጩቶቿን በትጋት ነው የምትጠብቀው እባቡ ወደ ጎጆዋ ሲመጣ በከፍተኛ ፍጥነት በአፏ እና በጥፍሮቿ ትይዘውና ወደላይ ትበራለች ከዚያም አለት ፈልጋ በአለቱ ላይ እባቡን ትለቀዋለች እባቡም በአለቱ ላይ ተፈጥፍጦ ይሞታል የክርስቲያን ጠላት የቀደመው እባብ የተባለው ዲያብሎስን ነው ራእይ 12፡9 ክርስቲያንም ዲያብሎስን የሚቀጠቅጠው በአለቱ በክርስቶስ ነው በክርስቶስ ዲያብሎስ ድል ተነስቷልና
3. ንስር ሲታመም
ንስር አንዳንድ ጊዜ ይታመማል በተለይ የተበከለ ምግብ ከበላ ይታመማል በሚታመምበትም ጊዜ ተዘርግቶ በደረቱ ይተኛና ዓይኑን ወደ ፀሐይ ቀና በማድረግ ፀሐይን በቀጥታ በዓይኖቹ ይመለከታል ፈውስንም ከፀሐይ ብርሃን ያገኛል ንስር የተለየ ዓይን ስላለው ፀሐይን በቀጥታ አይቶ ሳይታወር የሚቀር የተለየ ፍጥረት ቢሆን ነው የዓይኑ አፈጣጠር የተለየ እስከ 40 ኪ.ሜ ድረስም አሻግሮ ማየት ይችላል ንስር ክርስቲያኖችንም በሕይወታቸው ችግር ሲገጥማቸው ድካም ሲይዛቸውና ፈተና ሲያንገላታቸው በቀጥታ ወደ ክርስቶስ በመመልከትና እርሱን ደጅ በመጥናት እንደ ፀሐይ ከሚያበራው ፊቱ ፈውስን ብርታትና ኃይልን ይቀበላሉ ንስር አንዳንድ ጊዜ ካልተፈወሰ እዚያው ፀሐይን እያየ ሞቶ ይቀራል ክርስቲያን የመጣው ቢመጣ ጌታውን እያየ ይሞታታል እንጂ ጌታውን ትቶ አይሄድም ሮሜ 8፡38-39 ንስር እስከ 40 ኪሜ ድረስ ከርቀት አሻግሮ እንደሚያይ ሁሉ ንስር አስቀድሞ ከርቀት የሚያዩበትና የሚያስተውሉበትን መንፈስ ከጌታ ተቀብለዋል፡፡
4. ንስር በማለዳ
ንስር በማለዳ ተነስቶ ሁልጊዜ ከአፉ በሚወጣ ፈሳሽ ቅባት መሰል ነገር የክንፎቹን ላባዎች ይቀባል ይህም ቀን በሚበርበት ጊዜ ክንፎቹን የንፋሱን ግፊት ለመቋቋም ጥንካሬ እንዲያገኙ ያደርጋቸዋል ይህንንም ተግባር ባለማቋረጥ በማለዳ ተነስቶ ያደርጋል ንስር ክርስቲያኖችም ዕለት ዕለት በማለዳ በመንቃት በጸሎት ቃሉን በማንበብ ለየዕለቱ ፈተናን ውጣ ውረድ የሚያስፈልጋቸውን ኃይልና ብረታት ከጌታ ይቀበላሉ ይህንን ያልተለማመዱ ክርስቲያኖች ግን ብዙ ጊዜ ሽንፈት ቢገጥማቸው አያስደንቅም ንስር ክርስቲያኖች ግን እንደዚህ አይደሉም ከእንቅልፍ ይልቅ የጌታቸውን ፊት ይናፍቃሉ በማለዳም ወደእርሱ ይገሰግሳሉ ፊቱንም ይፈልጋሉ ጌታም ፊቱን በላያቸው ላይ ያበራል የቀኑንም ክፋት ሁሉ በድል ይወጣሉ፡፡
5. የንስር ፍቅር
ንስር ለጫጩቶቿ የምታደርገው ፍቅር በጣም አስደናቂ ነው ጫጩቶቿ በሚፈለፍሉበት ጊዜ የጎጆው እንጨት እንዳይጎረብጣቸው በደረቷ አካባቢ የሚገኘውን ስስ የገላዋን ክፍል በመንጨት ትጎዘጉዝላቸዋለች ጫጩቶቿም በምቾት ደስ ብሏቸው አካሏ ቁራጭ ላይ ይተኛሉ ይሞቃቸዋልም የክርስቶስ የሆኑትም ተመሳሳይ ፍቅር ለሌሎች እንዲያሳዩ ይጠበቅባቸዋል ለአዳዲሶችም የምናሳየው እንክብካቤ ፍቅርን የተላበሰ ሊሆን ይገባል፡፡
"እግዚአብሔርን በመተማመን የሚጠባበቁ ግን ኃይላቸውን ያድሳሉ እንደ ንስር በክንፍ ይወጣሉ ይሮጣሉ አይታክቱም ይሄዳሉ አይደክሙም"
(ኢሳ 40፡31)
ምንጭ፦ ትርጉም ተድላ ሲማ፣ ብርሃን መፅሔት፣ 1989 ቁጥር 29

👍21🔥6❤1👏1
. ──•◈•─────•◈•─
የዕለቱ ጥቅስ
──•◈•─────•◈•─
“ንስር ጫጩቶቹን እንደሚያወጣ፥ በእነርሱም ላይ እንደሚሰፍፍ፥ ክንፎቹን ዘርግቶ ወሰዳቸው፥ በክንፎቹም አዘላቸው።”
ዘዳግም 32፥11

❤9
Audio
#መጻሕፍትን_በድምጽ
📔ርዕስ፦ የመጽሐፍ ቅዱስ አስተምህሮ
👤ጸሐፊ፦ ዶ/ር ቻርልስ ሲ.ራይሪ
🗣ተርጓሚ፦ ሲሳይ ደሳለኝ
👉ክፍል-2
ይቀጥላል...
ወደ ቻናሉ ለመ🀄️ላ🀄️ል፦ @Holy_scriptures
📔ርዕስ፦ የመጽሐፍ ቅዱስ አስተምህሮ
👤ጸሐፊ፦ ዶ/ር ቻርልስ ሲ.ራይሪ
🗣ተርጓሚ፦ ሲሳይ ደሳለኝ
👉ክፍል-2
ይቀጥላል...
ወደ ቻናሉ ለመ🀄️ላ🀄️ል፦ @Holy_scriptures
👍3❤1
የጸሎት ሦስቱ ሂደቶች
1. “ነፍሴ አንተን ተጠማች” (መዝሙር 63፥1)
2. “ነፍሴ በኋላህ ተከታተለች” (መዝሙር 63፥8)
3. “ነፍሴ በቅቤና በስብ እንደሚጠግቡ ትጠግባለች” (መዝሙር 63፥5)
ከላይ ያሉት ጥቅሶች ከመዝመረ ዳዊት ምዕራፍ 63 ላይ የተወሰዱ ሲሆን በከፊልም ቢሆን የጸሎትን ደረጃ ያሳያሉ ብዬ አስባለሁ፡፡ ጸሎት ወደ ውስጠኛው የእግዚአብሔር ማደሪያ የሚደረግ ግሥገሣ እንደ ሆነ ‹‹አምላኬ አምላኬ ወደ አንተ እገሠግሣለሁ›› (መዝ 63፥1) የሚለው ቃል ያመለክተናል፡፡ጉዞ መነሻ እንዳለው ሁሉ ጸሎታችንም ከውጨኛው የጸሎት አደባባይ ወደ ውስጠኛው የጸሎት አደባባይ ያነጣጠረ ነው፡፡ለዚህም ነው ዳዊት ‹‹ኃይልህንና ክብርህን አይ ዘንድ እንዲሁ በመቅደስህ ውስጥ ተመለከትሁ››(መዝ 63፥2) ብሎ የሚናገረው፡፡
ከላይ የጠቀስኩትን ክፍል ስናነብ የምንገነዘበው ነገር አለ፡፡ እሱም ጸሎታችን እየጠለቀ በሄደ ቁጥር፣ የእግዚአብሔርን ኃይልህንና ክብር የማየት በረከታችን እየጨመረ እንደሚሄድ ነው፡፡ ለዚህ ነው በግልብ (superficial) ጸሎት ‹‹ነፍሴ በቅቤና በስብ እንደሚጠግቡ ትጠግባለች›› (መዝ 63፥5) ማለት የማንችለው፡፡
‹‹እገሠግሣለሁ›› (ቁ.1) ስንልም የጸሎት ርምጃችን ጽናት፣ትግዕስት፣ ንቁነት ወዘተ እንደ ግብዓት እንደሚያስፈልጉት መገንዘብ ይኖርብናል፡፡ ብዙ ጊዜ ለጸሎት ስንደረደርና ለመገሥገሥ ስናስብ ‹‹ነፍሴ አንተን ተጠማች፤ሥጋዬ አንተን እንዴት ናፈቀች›› (መዝ 63፥1) የሚል መንፈስን ይዘን ነው የምንቀርበው፤ በተጓዳኝ ተግዳሮቶቻችን እያሰብን፤ ሕመማችን እያሰብን፤ ፈተናዎቻችን እያሰብን፣ መከራዎቻችን እያሰብን ወዘተ፡፡ባለፉት የጸሎት ጊዜያት የነበሩንን ግሩም ልምምዶች እያሰብንም አምላካችን አሁንም እንዲደግመው በመማጸን በፊቱ እንሆናለን፡፡
ጸሎትን ስንጀምር የመጸለይ ፍላጎታችን እጅግ ዝቅ ያለ ስለሚሆን፣ ቶሎ እንድናቋርጥ ፈተናዎች ይመጣሉ፡፡ ድካም ይጫጫነናል፤ አእምሮአችን ይበታተናል ሌላም ሌላም፡፡ ነገር ግን በጽናት ይህንን ተግዳሮት አሸንፈን ከዘለቅን፣ የእግዚአብሔር ሕልውና የሚታወቀን ደረጃ ውስጥ እንገባለን፡፡በዚህ ደረጃ ላይ ሆነን ነው ‹‹ነፍሴ በኋላህ ተከታተለች››(መዝ 63፥8) የምንለው፡፡ በዚህ ደረጃ ላይ ሆነን ነው ‹‹ሳበን ካንተም በኋላ እንሮጣለን…..ከወይን ጠጅ ይልቅ ፍቅርህን እናስባለን››(መኃልይ 1፥4) የምንለው፡፡ በዚህ ጊዜ ትንሽ ትንሽ ዝማሬና ምሥጋናም ያምረናል፤ ጸሎታችንንም ሳናቋርጥ መቀጠል ያምረናል፡፡ቢሆንም ብዙ ሰዎች በሚገባ የጸለዩ ስለሚመስላቸው እዚህ ደረጃ ላይ ያቋርጣሉ፡፡እንዳውም ስለነበራቸው ድንቅ የጸሎት ጊዜም ለሰዎች ሊመሰክሩም ይችላሉ ብዬም አስባለሁ፡፡ይህንን ደረጃ ስናልፍ ሦስተኛው ደረጃ ውስጥ እንገባለን፡፡
ሦስተኛው የጸሎት ደረጃ፣ ከጌታ ጋር እጅግ አስደናቂ ሕብረት የምናደርግበት የጸሎት ደረጃ ሲሆን፣እውነተኛ የሕይወት ለውጥ(transformation) ለማየት መልካም ዕድሎችን ይፈጥርልናል፡፡ በዚህ የጸሎት ደረጃ አዘውትረን ስናሳልፍ ነው ‹‹ነፍሴ በቅቤና በስብ እንደሚጠግቡ ትጠግባለች፤ ከንፈሮቼም ስምህን በደስታ ያመሰግናሉ››(መዝ 63፥5)ብለን በእውነት እና በድፍረት መናገር የምንችለው፡፡ይህ ደረጃ ‹‹መንፈስ ራሱ በማይነገር መቃተት የሚማልድበት››(ሮሜ 8፥27) የጸሎት ደረጃ ነው፤ እንደ እግዚአብሔር ፈቃድም የምንጸልይበት፡፡እንባ ቋንቋችን ይሆናል፡፡ይሄ ደረጃ ሲጠልቅ፣ ዝምታ ይበዛል፡፡እውነተኛ ንሥሓ ከአንደበታችን ይወጣል፡፡የከረምንበትን መንፈሳዊ ሕይወት በመንፈስ ስለምናየው ከልብ እናዝናለን፡፡ከጌታ ጋር ያለ ግብዝነት ለመራመድ የምንወስንበት ጊዜም ይሆናል፡፡ይህ ዓይነት ጸሎት በሕይወታችን ሲበዛ ነው፣መንፈሳዊ ለውጦችና ፍሬዎች የሚበዙት፡፡
ጌታ ሆይ እባክህ ወደ ጠለቀ ጸሎት ሳበን!
ምንጭ:- Divine Wisdom4

❤13👍4🙏1💯1
. ──•◈•─────•◈•─
የዕለቱ ጥቅስ
──•◈•─────•◈•─
“እርሱ ለዘመንህ የሚያስተማምን መሠረት፣ የድነት፣ የዕውቀትና የጥበብ መዝገብ ይሆናል፤ እግዚአብሔርንም መፍራት የዚህ ሀብት ቍልፍ ነው።”
ኢሳይያስ 33፥6 (አዲሱ መ.ት)

❤8
Audio
#መጻሕፍትን_በድምጽ
📔ርዕስ፦ የመጽሐፍ ቅዱስ አስተምህሮ
👤ጸሐፊ፦ ዶ/ር ቻርልስ ሲ.ራይሪ
🗣ተርጓሚ፦ ሲሳይ ደሳለኝ
👉ክፍል-3
ይቀጥላል...
ወደ ቻናሉ ለመ🀄️ላ🀄️ል፦ @Holy_scriptures
📔ርዕስ፦ የመጽሐፍ ቅዱስ አስተምህሮ
👤ጸሐፊ፦ ዶ/ር ቻርልስ ሲ.ራይሪ
🗣ተርጓሚ፦ ሲሳይ ደሳለኝ
👉ክፍል-3
ይቀጥላል...
ወደ ቻናሉ ለመ🀄️ላ🀄️ል፦ @Holy_scriptures
👍3
አምልኮ
አምልኮ የሚለው ቃል በመሰረቱ በዕብራይስጥ አቦዳ (Aboda) በግሪክ ፕሮስኪኒስ (Proskneo) የሚለው ሲሆን ለአንድ ጌታ ብቻ የተገዛ ባሪያ ሊያቀርበው የሚገባ ፍጹምና ሁለንተናዊ አገልግሎት ነው። አምልኮ፣ ስግደትን፣ ውዳሴን፣ አክብሮትን ዝማሬን፣ ፀሎትን፣ መስዋዕትን፣ መልካም ስራን፣ ፈሪሃ እግዚአብሔርን፣ ፍቅርን፣ ሕይወትን አጠቃሎ ለእግዚአብሔር አምላክ ብቻ መስጠት ማለት ነው። ስለዚህ አምልኮ ለአምላክህ ብቻ የሚገባና የሚሰጥ አገልግሎት ወይም መሰጠት ነው።
በመጽሐፍ ቅዱስ አምላክ የሚለው ቃል የሚያመለክተው፦
ሀ. እግዚአብሔርን (ዘፀ 20፥2)
ለ. ጣዖትን (ዘዳ 4፥28)
ሐ. ሰይጣንን (2ቆሮ 4፥4)
መ. የሰውን ቀዳሚ ምኞት (ፊል 3፥19)
የአምልኮ ትርጉም፦
የተስተካከለ የሕይወት አቅጣጫ ወይም ለእግዚአብሔር ሙሉ ለሙሉ የመገዛት ሕይወት ነው።
ሀ. አገልግሎት ነው (ኢያሱ 24፥15)
ለ. መልካም ምግባር እና ንጹሕ ሕይወት ነው (ያዕ 1፥26፤ ሮሜ 12፥11)
ሐ. ለእግዚአብሔር ታላቅነት በመንፈስ እና በእውነት መስገድ ነው (ያዕ 4፥19፣24)
መ. እግዚአብሔር ከሰጠን ገንዘብ እና ንብረት ውስጥ መልሰን ለእርሱ መስጠት ነው (ምሳሌ 3፥9)
ምንጭ:- wongelcenter.com

👍8❤4👏1
. ──•◈•─────•◈•─
የዕለቱ ጥቅስ
──•◈•─────•◈•─
“እኛኮ ትርፍ ለማግኘት ብለን የእግዚአብሔርን ቃል ቀላቅለው እንደሚሸቃቅጡት እንደ ብዙዎቹ አይደለንም፤ ነገር ግን ከእግዚአብሔር እንደተላኩ ሰዎች በክርስቶስ ሆነን በእግዚአብሔር ፊት በቅንነት እንናገራለን።”
2ኛ ቆሮንቶስ 2፥17 (አዲሱ መ.ት)

❤8👍2