ቅዱሳት መጻሕፍት
7.45K subscribers
1.36K photos
61 videos
332 files
801 links
በዚህ ቻናል

👉ቅዱሳት መጻሕፍት ይጠናሉ::
👉መጽሐፍ ቅዱሳዊ ትምህርቶች ይቀርባሉ::
👉 ለቅዱሳት መጽሐፍት ጥናት የሚያግዙ መጻሕፍት ይለቀቃሉ።

⭐️⭐️⭐️⭐️⭐️

@Holy_scriptures
Download Telegram
የአትናቴዎስ የሃይማኖት መግለጫ


1. ለመዳን የሚፈልግ ሁሉ ከሁሉም ነገር አስቀድሞ የሁሉ የሆነች የቤተ ክርስቲያን ሃይማኖትን እውነተኛ አድርጎ ሊቀበል ያስፈልገዋል።
2. ንጹሕና ሙሉ አድርጎ ያልጠበቀው ሁሉ ያለ ጥርጥር የዘላለም ጥፋት ይደርስበታል።
3. በሦስትነቱ አንድነቱን፥ በአንድነቱም ሦስትነቱን አምነን አንድ አምላክን እናመልካለን። ይህም እውነተኛ የክርስትና ሃይማኖት ነው።
4. ይህንንም የምናደርገው አካላቱን ሳንደባልቅ መለኮታዊ ህልውናውንም ሳንከፍል ነው።
5. ምክንያቱም የአብ አካል ለብቻው የወልድ ለብቻው፥ የመንፈስ ቅዱስም ለብቻው ስለሆነ ነው።
6. ሆኖም የአብ፥ የወልድና የመንፈስ ቅዱ መለኮት አንድ ነው፥ ክብሩ ሥልጣኑም እኩል ሆኖ ይኖራል።
7. ወልድ በህልውናው እንደ አብ ነው፥ መንፈስ ቅዱስም እንደዚሁ ነው።
8. አብ አልተፈጠረም፥ ወልድ አልተፈጠረም፥ መንፈስ ቅዱስም አልተፈጠረም።
9. አብ ወሰን የለውም፥ ወልድ ወሰን የለውም፥ መንፈስ ቅዱም ወሰን የለውም።
10. አብ ዘላለማዊ ነው፥ ወልድ ዘላለማዊ ነው፥ መንፈስ ቅዱስም ዘላለማዊ ነው።
11. ቢሆነም ዘላለማዊ የሚሆን አንድ እንጂ ሦስት አይደሉም።
12. ያልተፈጠረና ወሰን የሌለው ሦስት እንዳልሆነ እንደዚሁም ያልተፈጠረና ወሰን የሌለው አንድ ነው።
13. እንዲሁም አብ ሁሉን የሚችል ነው፥ ወልድ ሁሉን የሚችል ነው፥ መንፈስ ቅዱስም ሁሉን የሚችል ነው።
14. ቢሆንም፥ ሁሉን የሚችል አንድ አንጂ ሦስት አይደሉም።
15. ስለዚህ አብ አምላክ ነው፥ ወልድ አምላክ ነው፥ መንፈስ ቅዱስም አምላክ ነው።
16. ሆኖም አንድ አምላክ እንጂ ሦስት አማልክት አይደሉም።
17. ስለዚህ አብ ጌታ ነው፥ ወልድ ጌታ ነው፥ መንፈስ ቅዱስም ጌታ ነው።
18. ሆኖም አንድ ጌታ እንጂ ሦስት ጌቶች አይደሉም።
19. ምክንያቱም የክርስትና እምነት እውነተኛነት እያንዳንዱ አካል አምላክና ጌታ መሆኑን እንድናምን እንደሚያስገድደን ሁሉ የክርስትና ሃይማኖት ሦስት አማልክት ወይም ሦስት ጌቶች እንዳንል ይከለክለናል።
20. አብ በማንም አልተሠራም፥ አልተፈጠረም፥ አልተወለደምም።
21. ወልድ ከአብ ተወለደ እንጂ አልተሠራም አልተፈጠረምም።
22. መንፈስ ቅዱስ አልተሠራም፥ አልተፈጠረም፥ አልተወለደምም፥ ነገር ግን ከአብ የሚሠርጽ ነው።
23. ስለዚህ አብ አንድ ስለሆነ ሦስት አብ አይደለም፥ ወልድም አንድ አንጂ ሦስት ወልድ አይደለም፥ መንፈስ ቅዱስም አንድ እንጂ ሦስት አይደለም።
24. ከሦቱ አካላት አንዱ ከሌላው ቀዳሚነት ወይም ደኃሪነት የለውም፤ አንዱም ከሌላው የሚበልጥ ወይም የሚያንስ አይደለም።
25. ስለሆነም፥ ሦስቱ አካላት በእኩልነትና በዘላለማዊነት አንድ ናቸው። ከዚህ የተነሣም ከፍ ብሎ እንደተጠቀሰው ሦስቱ አካላት በአንድ መለኮት አንድ አምላክም በሦስት አካላት ይመለካል።
26. ለመዳን የሚፈልግ ሁሉ ስለ ሥላሴ እንደዚህ ማሰብ ይገባዋል።
27. ከዚህም ሌላ የዘላለምን ደኅንነት ለማግኘት የጌታችንን የኢየሱስ ክርስቶስን በሥጋ መገለጽ በእውነት ማመን አስፈላጊ ነው።
28. ምክንያቱም ትክክለኛው እምነት ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ የእግዚአብሔር ልጅ አምላክም ሰውም መሆኑን አምነን ማስታወቅ ነው።
29. እርሱም ከዘመናት አስቀድሞ ከአብ የተወለደ አምላክ ከእናቱም በሥጋ በዓለም የተወለደ ሰው ነው።
30. የሚያስብ ነፍስ ያለችውና የሰውን ሥጋ የለበሰ ፍጹም አምላክ ፍጹም ሰው ነው።
31. በአምላክነቱ ከአብ ጋር የተካከለ፥ በሰውነቱም ከአብ ያነሰ ነው።
32. አምላክም ሰውም ቢሆንም አንድ ክርስቶስ እንጂ ሁለት ክርስቶስ አይደለም።
33. አንድ ነው ስንል ግን የሰውን ሥጋ ለበሰ እንጂ መለኮት ወደ ሥጋ አልተለወጠም።
34. በእርግጥ አንድ የሆነውም በባሕርያት መደባለቅ ሳይን በአካል አንድ በመሆኑ ነው።
35. ምክንያቱም የሚያስብ ነፍስና ሥጋ አንድ ሰው እንደሆኑ ሁሉ አምላክና ሰው በክርስቶስ አንድ ናቸው።
36. እርሱም ለደህንነታችን ሲል መከራ የተቀበለ፥ ወደ ሲኦል የወረደ፥ ከሙታን የተነሣ፤
37. ወደ ሰማይ የወጣ፥ በአብ ቀኝ የተቀመጠ፥ በሕያዋንና በሙታንም ሊፈርድ ከዚያ የሚመለስ ነው።
38. በመምጣቱ ጊዜም ሰዎች ሁሉ በሥጋ ተነስተው ስለ ሥራቸው መልስ ይሰጣሉ።
39. መልካም የሠሩ ወደ ዘላለም ሕይወት ክፉ የሠሩም ወደ ዘላለም እሳት ይገባሉ።
40. ይህ እውነትኛው የክርስትና እምነት ነው። ይህን የማያምንና አጥብቆ የማይዝ ሊድን አይችልም።




ወደ ቻናሉ ለመ🀄️🀄️ል፦ @Holy_scriptures
👍122🙏2🔥1
.       ──•◈•─────•◈•─
                          የዕለቱ ጥቅስ
        ──•◈•─────•◈•─
“አባቶቻችንም ሁሉ እንደነበሩ እኛ በፊትህ ስደተኞችና መጻተኞች ነን፤ ዘመናችንም በምድር ላይ እንደ ጥላ ናት፥ አትጸናም።”
1 ዜና 29፥15



ወደ ቻናሉ ለመ🀄️🀄️ል፦ @Holy_scriptures
👍62
ቅዱሳት መጻሕፍት
የጸጋ ስጦታዎች ውጤታማ አሠራር እንዴት ሊሆን ይገባል?                       ክፍል-1                                በመርዕድ ለማ በዚህ ክፍል የጸጋ ስጦታዎች አሠራር እንዴት እንደ ሆነ እናያለን። ጽሑፉ፦ መንፈሳዊ ልምምዶች፣ ሚዛናዊነት ወይስ አክራሪነት?፣ ጌታ ወይስ ስጦታው? በሚሉ ሦስት ዐበይት ክፍሎች ቀርቧል። በጽሑፉ ማጠቃለያም ፍቅር ከጸጋ ስጦታዎች ጋር ያለውን…
የጸጋ ስጦታዎች ውጤታማ አሠራር እንዴት ሊሆን ይገባል?


                      ክፍል-2


                               በመርዕድ ለማ


3. ሁሉን ፈትኑ፦

መቼም የሰማነውንና ያገኘነውን ሁሉ አግበስብሶ መቀበል ጤናማ ሕይወታችንን ያውካል። ያለንበት ዓለም በብዙ ዓይነት የመናፍስት አሠራር የተሞላ ነው። የእግዚአብሔር መንፈስ አለ፤ የሰይጣን መንፈስ አለ፤ የሰውም መንፈስ አለ። በምንሰማውና በምናየው ነገር አድናቆት ውስጥ ከመግባታችን በፊት ነገሩ ምን ይሆን? ብሎ የነገሩን ትክክለኛነት ለማረጋገጥ እንሞክር። ከእግዚአብሔር ቃል ጋር እንዲሁም በውስጣችን ካለው መንፈስ ጋር እናመሳክረው።

4. መልካሙን ያዙ፦

እግዚአብሔር እኛን ሲፈጥረን ተንቀሳቃሽ አሻንጉሊቶች አድርጎ አልሠራንም፤ የራሳችን ፈቃድ፣ ስሜትና ፍላጎት ያለን አድርጎ ነው። ደግሞም መልካሙን ከክፉው ለይተን እንድናውቅ አድርጎ አዘጋጅቶናል። እንዲሁም በልጁ በኢየሱስ ክርስቶስ አዲስ ፍጥረት ካደረገን በኋላ መንፈሱን በውስጣችን አስቀምጧል። ይህም መንፈስ የሚመራን ነው። በዚህም በእግዚአብሔር መንፈስ መሪነት መልካሙን ከክፉው ለይተን ከተረዳን፣ ክፉውን በመጣል መልካሙን በመያዝ መጽናት ይኖርብናል። “በእግዚአብሔር መንፈስ የሚመሩ ሁሉ እነዚህ የእግዚአብሔር ልጆች ናቸውና።” [ሮሜ 8፡14]

5. ከማናቸውም ዓይነት ክፉ ነገር ራቁ፦

እኛ የእግዚአብሔር ሰዎች ማንኛውንም ዓይነት ክፉ ነገር መጥላት ብቻ ሳይሆን ከዚያ መራቅ ግዴታችን ነው። ሐዋርያው ጳውሎስ በሮሜ 12፥9 ላይ “ክፉውን ነገር ተጸየፉት” ይላል። አንድ የተጸየፍነውን ነገር በዓይናችንም እንኳ ልናየው አንፈልግም። በአእምሮአችንም ልናሰላስለው አንወድም። ክፉውን ነገር ተጸየፉት ካለ በኋላ ከበጎ ነገር ጋር ተባበሩ ይላል። ስለዚህ ምንጊዜም ለበጎ ነገር ፈቃደኞችና ተባባሪዎች መሆን ይኖርብናል።

ጌታ ወይስ ስጦታው?

ሁላችንም ከፍተኛ ጥንቃቄ የምናደርግበት ጉዳይ እንዳለ ለማሳሰብ እወዳለሁ። ዛሬ መንፈስ ቅዱስ የሚሠራበት ወቅት እንደ መሆኑ መጠን ሰዎች መንፈሳዊ ጥማታቸውን ለማርካት ከአንዱ ቤተክርስቲያን ወደ ሌላው ሲሄዱ ያታያሉ። የተጠማነው ማንን ነው? ጌታን ነው ወይስ መንፈሳዊ ነገር? የመጀመሪያው ጥማታችንና ፍላጎታችን ጌታ ይሁን፤ ያኔ እንረካለን። “ማንም የተጠማ ቢኖት ወደ እኔ ይምጣና ይጠጣ” አለ ጌታ [ዮሐንስ 7፥37]

ለኃጢአተኞች፣ ለበሽተኞች ለተለያዩ ነፍሳት የሚሰበከው ምንድነው? ስብከታችን የሚያተኩረው ምን ላይ ነው? በጌታ ኢየሱስ ላይ መሆን ይገባዋል። ምክንያቱም የፈውስ፣ የመገለጥ፣ የተዓምራቶችና የድንቆች ሁሉ ምንጭ እራሱ ጌታ ኢየሱስ ስለሆነ። አገልጋዮች ምዕመናንን ልባቸውም ዓይናቸውም ከእኛ ላይ ተነሥቶ በክርስቶስ ላይ እንዲያርፍ እናድርግ። ይህን ብናደርግ ታማኝነታችን ይገለጻል። እንደገናም ትሕትና ነው። ሌላ ቀርቶ አንዳንድ በሽተኞች ወደ ቤተክርስቲያን ሲመጡ ፈውስን የሚቀበሉበትን መንገድ አዘጋጅተው ይመጣሉ። እግዚአብሔር ዛሬ በመገለጥ ተናገረኝ ይላሉ። ፈውስ በመገለጥ ብቻ አይመጣም። ምናልባትም ፈውስ ከሚመጣባቸው መንገዶች አንዱ ሊሆን ይችላል። ፈውስ በእግዚአብሔር፣ በእጅ በመጫን፣ በአምልኮ ውስጥ በመሆን ይመጣል። በፈለገው መንገድ ይምጣ ነገር ግን እኛ ባዶ ሆነን ጌታን እንፈልግ። የመንፈስ ቅዱስ ሥራ ጌታ ኢየሱስን ማክበር ነው። “የምነግራችሁ ገና ብዙ አለኝ፤ ነገር ግን አሁን ልትሸከሙት አትችሉም። ግን የእውነት መንፈስ በመጣ ጊዜ ወደ እውነት ሁሉ ይመራችኋል፤ የሚሰማውን ሁሉ ይናገራል እንጂ ከራሱ አይነግርምና፤ የሚመጣውንም ይነግራችኋል፣ እርሱ ያከብረኛል፣ ለእኔ ካለኝ ወስዶ ይነግራችኋል።” [ዮሐንስ 16፥14] እዚህ ላይ የምንመለከተው መንፈስ ቅዱስ ተጠሪነቱ ለራሱ ሳይሆን ለጌታ ኢየሱስ ነው። ስለዚህ ማንኛውም መንፈሳዊ አገልግሎቶች፣ የጸጋ ስጦታዎች፣ ልምምዶቻችን ሁሉ ለጌታ ክብር መዋል አለባቸው። እርሱ ኢየሱስ ክርስቶስ ጌታ እንደ ሆነ ማሳየትና መግለጥ ይኖርባቸዋል።


ይቀጥላል...


ምንጭ:- shalomgospel.com




ወደ ቻናሉ ለመ🀄️🀄️ል፦ @Holy_scriptures
6👍3
Audio
#መጻሕፍትን_በድምጽ

👉ርዕስ፦ የካታኮምቡ ሰማዕት
🗣ትርጉም፦ በአማረ ማሞ
መካነ ኢየሱስ ሥነ ጽሑፍ ክፍል።
📻ሙሉ ትረካ
⏱️አጠቃላይ የሚፈጀው ሰዓት፦ 3:49:45



ወደ ቻናሉ ለመ🀄️🀄️ል፦ @Holy_scriptures
👍5
የኒቅያ የሃይማኖት መግለጫ


ሁሉን በሚችል ሰማይንና ምድርን፣ የሚታየውንና የማይታየውን በፈጠረ አንድ አምላክ በሚሆን በእግዚአብሔር አብ አምናለሁ። እርሱ ብቻ የአብ ልጅ በሚሆን፣ ዓለም ሳይፈጠር ከአብ በተወለደ፣ ከአምላክ በተገኘ አምላክ፣ ከብርሃን በተገኘ ብርሃን፣ ከእውነተኛ አምላክ በተገኘ እውነተኛ አምላክ፣ በህልውናው ከአብ ጋር አንድ የሆነ፣ በተፈጠረ ሳይሆን በተወለደ፣ ሁሉ በእርሱ በሆነ፣ ስለ እኛ ስለ ሰዎች ስለ ደህንነታችንም ከሰማይ በወረደ፣ በመንፈስ ቅዱስ ከድንግል ማርያም ሥጋ ነስቶ ሰው በሆነ፣ በጴንጤናዊው በጲላጦስ ዘመን ስለ እኛ በተሰቀለ፣ መከራ በተቀበለ፣ በሞተ፣ በተቀበረም፣ በቅዱሳት መጻሕፍትም እንደተጻፈ በሦስተኛው ቀን ከሙታን ተለይቶ በተነሣ፣ ወደ ሰማይም በወጣ፣ በአብ ቀኝ በተቀመጠ፣ በሕያዋንና በሙታንም ሊፈርድ ዳግመኛ በክብር በሚመጣ፣ ለመንግሥቱም ፍጻሜ በሌለው በአንድ ጌታ በኢየሱስ ክርስቶስ አምናለሁ። ከአብና ከወልድ ጋር በሚሰገድለትና በሚከበር፣ ከአብ በሚሠርጽ፣ በነቢያት በተናገረ፣ የሕይወት ጌታና ሰጪ በሆነ፣ በመንፈስ ቅዱስም አምናለሁ። የሁሉም በሆነች በአንዲት ቅድስት የሐዋርያት ቤተ ክርስቲያንም አምናለሁ። ለኃጢአት ማስተስረያ በአንዲት ጥምቀትም አምናለሁ። የሙታንን ትንሣኤና ገና የሚመጣውን ዓለም ሕይወትም እጠባበቃለሁ። አሜን



ወደ ቻናሉ ለመ🀄️🀄️ል፦ @Holy_scriptures
16👍2🥰1🙏1
.       ──•◈•─────•◈•─
                          የዕለቱ ጥቅስ
        ──•◈•─────•◈•─
“ዮቶርም እግዚአብሔር ለእስራኤል ስላደረገው ቸርነት ሁሉ፥ ከግብፃውያንም እጅ ስላዳናቸው ደስ አለው።”
ዘጸአት 18፥9



ወደ ቻናሉ ለመ🀄️🀄️ል፦ @Holy_scriptures
9
ቅዱሳት መጻሕፍት
የጸጋ ስጦታዎች ውጤታማ አሠራር እንዴት ሊሆን ይገባል?                       ክፍል-2                                በመርዕድ ለማ 3. ሁሉን ፈትኑ፦ መቼም የሰማነውንና ያገኘነውን ሁሉ አግበስብሶ መቀበል ጤናማ ሕይወታችንን ያውካል። ያለንበት ዓለም በብዙ ዓይነት የመናፍስት አሠራር የተሞላ ነው። የእግዚአብሔር መንፈስ አለ፤ የሰይጣን መንፈስ አለ፤ የሰውም መንፈስ…
የጸጋ ስጦታዎች ውጤታማ አሠራር እንዴት ሊሆን ይገባል?


                      ክፍል-3
              (የመጨረሻ ክፍል)


                               በመርዕድ ለማ


የጸጋ ስጦታዎችና ፍቅር

ሐዋርያው ጳውሎስ ስለ መንፈስ ቅዱስ ሥራና ስጦታዎች በሰፊው የተናገረበት ክፍል ለቆሮንቶስ ሰዎች የጻፈው የመጀመሪያው መልእክቱ ነው። በዚሁ መልእክት በ12ኛው ምዕራፍ ላይ የጸጋ ስጦታዎችን ምንነትና የስጦታዎቹ ምንጭ ማን እንደሆነ የተናገረበት ክፍል ነው። በምዕራፍ 14 ላይ ደግሞ በማህበር፣ በጉባዔ ውስጥ እንዴት መጠቀም እንደሚኖርብን የተናገረበት ክፍል ነው። ምዕራፍ 13 ስጦታዎች አመርቂና ውጤታማ መሆን የሚችሉት በፍቅር ስንጠቀምባቸው ብቻ ነው በማለት ያስረዳል፤ ምዕራፍ 13 ስለ ፍቅር በስፋት የሚናገርበት ምዕራፍ ነው። ከቁጥር 1-3 ካለፍቅር የጸጋ ስጦታዎች ጠቃሚነት እንደሌላቸው ተገልጦአል፤ ከቁጥር 4-7 ደግሞ የፍቅርን የተለያዩ መግለጫዎች እንመለከታለን። ከቁጥር 8-13 የጸጋ ስጦታዎች እስከ ተወሰነ ጊዜ ድረስ ብቻ እንደሚሠሩና እምነት፣ ተስፋ፣ ፍቅር ጸንተው እንደሚኖሩ ገልጦ ከሦስቱም የሚበልጠው ፍቅር እንደ ሆነ ተናግሯል። ብዙውን ጊዜ በዚሁ በምዕራፍ 13 ላይ የተገለጸውን ፍቅር ሰዎች በተሳሳተ መልኩ ይጠቀሙበታል።

አንዳንዶቹ የጸጋ ስጦታንና የመንፈስ ቅዱስን አገልግሎት ላለማጉላት የፈለጉ ሰዎች፦ ፍቅር ነው እንጂ የጸጋ ስጦታ ጠቃሚ አይደለም በማለት ለጸጋ ስጦታዎች ሥፍራ እንዳይሰጡና የመንፈስ ቅዱስን እሳት ለማዳፈኛ ሲጠቀሙበት ይታያል። ይህ ትልቁ ስሕተት ነው። አንድን እውነት ሌላውን እውነት ለማጥፊያ መጠቀም በእግዚአብሔር ዘንድ የሚያስጠይቅ ስለሆነ እንጠንቀቅ። ሌሎች ደግሞ ከመጠን ባለፈ መልኩ የጸጋ ስጦታዎችን ብቻ በመግለጥ ስጦታዎችን ካለፍቅር የሚጠቀሙና የሚያስተምሩ አሉ። እነርሱም የትም አይደርሱም። ያለፍቅር ሁሉ ከንቱ ነውና። ከቁጥር 4-7 ባለው ክፍል 15 የተለያዩ የፍቅርን ባሕርያት እንመለከታለን።

ፍቅር ይታገሳል፦ አገልጋዮች ሰዎች አገልግሎታችንን ባይረዱ ችግር ቢገጥመን በዚህም ብንፈተን በትዕግስት እግዚአብሔርን መጠበቅ ፍቅር ነው።

ፍቅር ቸርነትን ያደርጋል፦ አገልግሎታችን እኛው ለኛው መሆን የለበትም፣ ለሌሎች ሰዎች ጥቅምና መታነጽ ምክንያት መሆን አለበት። ስለዚህ ለሌሎች ቸርነት ማድረግና ርህራሄን ማሳየት ፍቅር ነው።

ፍቅር አይቀናም፦ አገልጋዮች በምናገለግለው የጸጋ አገልግሎት ወደ ቅናት ውስጥ ከገባን ጸጋችንን በተሳሳተ መንገድ ተጠቅመንበታል ማለት ነው። ስለዚህ ከቅናት ነጻ መሆን አለብን።

ፍቅር አይመካም፣ አይታበይም፦ ትምክህተኛነት እግዚአብሔርን ያለማወቅ ነው። ማንም ሰው ትምክህቱ በእግዚአብሔር ላይ እንዲሆን የእግዚአብሔር ቃል ያዛል። “ጠቢብ በጥበቡ አይመካ፣ ኃያልም በኃይሉ አይመካ፤ ባለጠጋም በብልጥግናው አይመካ፤ ነገር ግን የሚመካው፣ ምሕረትንና ፍርድን ጽድቅንም በምድር ላይ የማደርግ እኔ እግዚአብሔር መሆኔን በማወቁና በማስተዋሉ በዚህ ይመካ፤ ደስ የሚያሰኙኝ እነዚህ ናቸውና፣ ይላል እግዚአብሔር።” [ኤርምያስ 9፥23-24]

ፍቅር የማይገባውን አያደርግም፦ አንድ አገልጋይ በአነጋገሩ፣ በአሳቡ፣ በሚያደርገው ነገር ሁሉ ጠንቃቃና አስተዋይ ሊሆን ይገባዋል። ሰዎች በጸጋ ስጦታዎች የምናገለግላቸውን አገልግሎቶች ብቻ ሳይሆን ጠቅላላ ሕይወታችንንም ይከታተላሉ። ስለዚህ ጨዋና የተከበረ ጭምትና ነውር የሌለበት ከክፋትም የራቅን ልንሆን ይገባል።

ፍቅር የራሱን አይፈልግም፦ ከአገልግሎታችን ጋር በተያያዘ መልኩ የተለያዩ ፈተናዎችና ችግሮች ሲገጥሙን፣ ለምን ተነካሁ? በማለት የያዝነውን አደራ መጣል የፍቅር ጉድለት ነው። አገልጋይ ሳይነካ ማገልገል ጨርሶ አይችልም።

ፍቅር አይበሳጭም፦ አገልጋይ ከተበሳጨ በጸጋ አያድግም። ዘወትር በቅርብ ያለውን ብቻ ስለሚያይ በርቀት ያለውን የእግዚአብሔርን አሳብ አይረዳም። ስለዚህ በሆነው ባልሆነው መበሳጨት በአንድ አገልጋይ የሚታይ የፍቅር ጉድለት ነው።

ፍቅር በደልን አይቆጥርም፦ አገልግሎታችን ከተለያዩ ሰዎች ጋር የተያያዘ ነው። በመሆኑም ከሰዎች ጋር እስከ ተያያዘ ድረስ ደግሞ ሰዎችን መጉዳትና በሰዎችም መጎዳት ሊያጋጥም ይችላል። ጎዳንም ተጎዳንም ዘወትር ይቅር ለማለትና በይቅርታ ለማስተካከል ዝግጁ መሆን ይኖርብናል። ይኸን ብናደርግ የፍቅር ሰዎች ሆነናል ማለት ነው።

ፍቅር ከእውነት ጋር ደስ ይለዋል እንጂ ስለ አመጻ ደስ አይለውም፦ የፍቅር ሰው የሌሎች ሰዎች አገልግሎትና የመንፈሳዊ ሕይወት እድገት ያስደስተዋል። እንዲሁም ውድቀታቸውንና ችግራቸውን በራሱ እንደ ደረሰ አድርጎ ይቆጥረዋል፤ ይሰማዋል።

ፍቅር ሁሉን ይታገሳል፦ የሌሎችን ሰዎች ስሕተት ለማጋለጥ አይቸኩልም፤ ወይም ትክክለኛነቱንና ሀቀኛነቱን ለማሳየት አይጥርም። በሚቃወሙትና በሚተቹት ሰዎች ሁሉ ፊት እራሱን ይገዛል። ሁሉን ያምናል፣ የፍቅር ሰው በሚሰማውና በሚያየው ነገር ልቡ አያፈገፍግም፤ ዳሩ ግን በአምላኩ ይታመናል።

ፍቅር ሁሉን ተስፋ ያደርጋል፦ በፍቅር የሚያገለግል ሰው ዛሬ በጨለማ ያለ ቢመስለውም የነገው ብርሃን እንደሚሆንለት በአምላኩ ተስፋ ያደርጋል። በሙሉ ተስፋም ይወጣል ይገባልም።

ፍቅር በሁሉ ይጸናል፦ አንድ የጌታ አገልጋይ ብዙ ሰልፍና ጦር የሚገጥመው ሰው ነው። ከወጀቡና ከማዕበሉ የተነሳ ሥፍራውን በመልቀቅ የሚሸሽ ሳይሆን በአምላኩ ተማምኖ ተደግፎ ቀጥ ብሎ የሚቆም መሆን አለበት። እንግዲያስ እውነትን በፍቅር እየገለጥን ከጌታ የተቀበልነውን አገልግሎት በፍቅር መጠቀም እንድንችል እግዚአብሔር ይርዳን። አሜን።



ምንጭ:- shalomgospel.com



ወደ ቻናሉ ለመ🀄️🀄️ል፦ @Holy_scriptures
4👍3
.       ──•◈•─────•◈•─
                          የዕለቱ ጥቅስ
        ──•◈•─────•◈•─
“ፊተኛ ኑሮአችሁን እያሰባችሁ እንደሚያታልል ምኞት የሚጠፋውን አሮጌውን ሰው አስወግዱ፥”
ኤፌሶን 4፥22


ወደ ቻናሉ ለመ🀄️🀄️ል፦ @Holy_scriptures
8
"ጌታው በስብከትህ ውስጥ ክርስቶስ የለም? እንዲያ ከሆነ ወደ ቤትህ ተመለስ፤ የሚረባ ነገር መስበክ እስክትጀምር ድረስ መልሰህ መቼም አትስበክ።"
ቻርለስ ስፐርጅን



ወደ ቻናሉ ለመ🀄️🀄️ል፦ @Holy_scriptures
👍102
.       ──•◈•─────•◈•─
                          የዕለቱ ጥቅስ
        ──•◈•─────•◈•─
“በልቤ ስላላችሁ፣ ስለ ሁላችሁ እንዲህ ማሰቤ ተገቢ ነው፤ በእስራቴም ሆነ ለወንጌል ስመክትና ሳጸናው ሁላችሁም ከእኔ ጋር የእግዚአብሔር ጸጋ ተካፋዮች ናችሁና።”
ፊልጵስዩስ 1፥7 (አዲሱ መ.ት)



ወደ ቻናሉ ለመ🀄️🀄️ል፦ @Holy_scriptures
5🔥1
ቅዱሳት መጻሕፍት
#መጻሕፍትን_እንመርምር የኢየሱስ ክርስቶስ ትንሣኤ የአካል ወይስ የመንፈስ?                         ክፍል-፭                                                        2. የሐዋርያው ጳውሎስ አስተምህሮ ሐዋርያው ጳውሎስ እጅግ ጥንታዊ ነው የሚባለውን የቤተ ክርስቲያን የእምነት መግለጫ ጠቅሶ በጻፈበት ክፍል ላይ፣ የክርስቶስን ሞት ከገለጸ በኋላ የሃይማኖት…
#መጻሕፍትን_እንመርምር

የኢየሱስ ክርስቶስ ትንሣኤ የአካል ወይስ የመንፈስ?


                        ክፍል-፮
                                         

ሀ. “ከእናንተ አንዳንዶቹ ትንሣኤ ሙታን የለም እንዴት ይላሉ?” (ቊጥር 12)

ጳውሎስ ይህን መልእክት የጻፈው ከአቴና ትንሽ ኪሎ ሜትር ወረድ ብላ በምትገኘው ቆሮንቶስ ነው:: በዚያ የሞቱ ሰዎች ዳግም ሕይወት ያገኛሉ የሚለው ትምህርት ተረት ነበር (ሐዋርያት ሥራ 17÷32)፡፡ አንድ ግሪካዊ ወደ ፊት ሕይወት በመንፈሳዊው ዓለም ውስጥ ይቀጥላል የሚለው ትምህርት የሚቀበለው እንጂ የሚሰናከልበት ጒዳይ አይደለም፤ ግሪካውያንን የሚያሰናክላቸው የአካል ትንሣኤ ወይም በዚሁ አካል ዳግም ሕይወት ያገኛል የሚለው ትምህርት ነው።

ለ. “የምትዘራው የሚሆነውን አካል አይደለም” (ቊጥር 37)

የዘር ፍሬ ከሚበቅለው ፍሬ እንደሚለይ የትንሣኤም አካል ከሚሞተው አካል የተለየ ነው:: ነገር ግን በተዘራው ማለትም በሞተው ዘርና በበቀለው ዘር መካከል በክፍለ ህዋስ ወይም በመሠረታዊ ተፈጥሮአቸውም ሆነ በታሪካቸው ልዩነት እንደሌላቸው ሁሉ የትንሣኤ አካል ከሞተው አካል ያለው አንድነት እንደዚሁ ነው::

ሐ. “የሙታን ትንሣኤ ደግሞ እንዲሁ ነው፡፡ በመበስበስ ይዘራል፣ ባለመበስበስ ይነሣል፤ በውርደት ይዘራል፣ በክብር ይነሣል፤ በድካም ይዘራል፤ በኀይል ይነሣል፤ ፍጥረታዊ አካል ይዘራል፣ መንፈሳዊ አካል ይነሣል፡፡ ፍጥረታዊ አካል ካለ መንፈሳዊ አካል ደግሞ አለ” (ቊጥር 42-44)

በክፍሉ አራት ጥንድ ነገሮች አብረው ተነጻጽረዋል፡፡ በመበስበስ፣ ባለመበስበስ፤ በውርደት፣ በክብር፤ በድካም፣ በኀይል፤ ፍጥረታዊ፣ መንፈሳዊ፡፡ በመጀመሪያዎቹ ሦስት ጥንዶች ስለሚሞተው አካል የተሰጡት አሉታዊ ገለጻዎች ናቸው። መበስበስ፣ ውርደት፣ ድካም ከመጀመሪያው አካል የተገኙ አሉታዊ ውርሶች ናቸው:: በመጀመሪያዎቹ ሦስት ጥንዶች ውስጥ ስለ ትንሣኤ አካል የቀረቡት ገለጻዎች የሚጠቁሙት አሉታዊ የሆኑት የውድቀት ውጤቶች እንደሚለወጡ ነው:: በክፍሉ ላይ የቀረቡት የጳውሎስ ማስረጃዎች የሐሳብ ፍሰታቸው ወጥነት ያለው ነው:: አራተኛው ጥንድ እንደ ላይኞቹ ሦስቱ አብረው በንጽጽር የቀረበ ነው:: ይኸውም ለውድቀት መንሥኤ ስለሆነው አካልና ከውድቀት ለመነሣት ምክንያት ስለሆነው አካል ነው፡፡

“ፍጥረታዊ አካል” የተባለው የኀጢአት አሉታዊ ውጤት የሆነው ነው፡፡ በኦሪት ዘፍጥረት መጽሐፍ ላይ እግዚአብሔር አምላክ አዳምን ከምድር ዐፈር እንዳበጀው፣ ይህንንም አካል፣ “መልካም ነው” እንዳለ እንመለከታለን (ዘፍጥረት 1÷26-31)።

አንደኛ ቆሮንቶስ 2፥14-15 ስለ መንፈሳዊ ሰው ይናገራል:: “መንፈሳዊ ሰው” ማለት ግን ቊሳዊ አካል የሌለው መንፈስ ብቻ የሆነ ማለት አይደለም፡፡ ነገር ግን በመንፈስ ቅዱስ ቊጥጥር ሥር ያለ ማለት ነው:: በአጠቃላይ “ፍጥረታዊ አካል” በእግዚአብሔር ቢፈጠርም፣ እግዚአብሔር በመጀመሪያ “መልካም ነው” ቢለውም እንኳ፣ በኀጢአት አማካይነት ግን ይህ አካል ተበላሽቶአል፡፡


ይቀጥላል...



ምንጭ፦ ዶ/ር ተስፋዬ ሮበሌ፤ በሥጋ ትንሣኤ አምናለሁ! የአስተምህሮተ ትንሣኤ መጽሐፍ ቅዱሳዊ፣ ታሪካዊና ሥነ አመክንዮአዊ ትንታኔ፤ ከምእራፍ ሰባት የተወሰደ




ወደ ቻናሉ ለመ🀄️🀄️ል፦ @Holy_scriptures
👍83
.       ──•◈•─────•◈•─
                          የዕለቱ ጥቅስ
        ──•◈•─────•◈•─
“ሕዝቤ ሰንፈዋልና አላወቁኝም ሰነፎች ልጆች ናቸው፥ ማስተዋልም የላቸውም፤ ክፉ ነገርን ለማድረግ ብልሃተኞች ናቸው፥ በጎ ነገርን ማድረግ ግን አያውቁም።”
ኤርምያስ 4፥22



ወደ ቻናሉ ለመ🀄️🀄️ል፦ @Holy_scriptures
4😢3👍1
#የእግዚአብሔር_ቃል_ምን_ይላል?


መዝሙር 25
¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯
¹ አቤቱ፥ ወደ አንተ ነፍሴን አነሣለሁ።
² አምላኬ፥ አንተን ታመንሁ፤ አልፈር፥ ጠላቶቼ በእኔ አይሣቁብኝ።
³ አንተን ተስፋ የሚያደርጉ አያፍሩም፤ በከንቱ የሚገበዙ ያፍራሉ።
⁴ አቤቱ፥ መንገድህን አመልክተኝ፥ ፍለጋህንም አስተምረኝ።
⁵ አንተ የመድኃኒቴ አምላክ ነህና በእውነትህ ምራኝ፥ አስተምረኝም፤ ቀኑን ሁሉ አንተን ተስፋ አድርጌአለሁ።
⁶ አቤቱ፥ ምሕረትህንና ቸርነትህን አስብ፥ ከጥንት ጀምሮ ናቸውና።
⁷ የልጅነቴን ኃጢአትና መተላለፍ አታስብብኝ፤ አቤቱ፥ ስለ ቸርነትህ ብዛት እንደ ምሕረትህ አስበኝ።
⁸ እግዚአብሔር ቸር ቅንም ነው፤ ስለዚህ ኃጢአተኞችን በመንገድ ይመራቸዋል።
⁹ ገሮችን በፍርድ ይመራል፥ ለገሮችም መንገድን ያስተምራቸዋል።
¹⁰ የእግዚአብሔር መንገድ ሁሉ ቸርነትና እውነት ነው። ቃል ኪዳኑንና ምስክሩን ለሚጠብቁ።
¹¹ አቤቱ፥ ኃጢአቴ እጅግ ነውና ስለ ስምህ ይቅር በለኝ።
¹² እግዚአብሔርን የሚፈራ ሰው ማን ነው? በሚመርጠው መንገድ ያስተምረዋል።
¹³ ነፍሱ በመልካም ታድራለች፥ ዘሩም ምድርን ይወርሳል።
¹⁴ እግዚአብሔር ለሚፈሩት ኃይላቸው ነው፥ ቃል ኪዳኑንም ያስታውቃቸዋል።
¹⁵ እርሱ እግሮቼን ከወጥመድ ያወጣቸዋልና ዓይኖቼ ሁልጊዜ ወደ እግዚአብሔር ናቸው።
¹⁶ እኔ ብቻዬንና ችግረኛ ነኝና ፊትህን ወደ እኔ አድርግ ማረኝም።
¹⁷ የልቤ ችግር ብዙ ነው፤ ከጭንቀቴ አውጣኝ።
¹⁸ ድካሜንና መከራዬን እይ፥ ኃጢአቴንም ሁሉ ይቅር በለኝ።
¹⁹ ጠላቶቼ እንደ በዙ እይ፥ የግፍም ጥል ጠልተውኛል።
²⁰ ነፍሴን ጠብቅና አድነኝ፤ አንተን ታምኛለሁና አልፈር።
²¹ አንተን ተስፋ አድርጌአለሁና የውሃትና ቅንነት ይጠብቁኝ።
²² አቤቱ፥ እስራኤልን ከመከራው ሁሉ አድነው።




ወደ ቻናሉ ለመ🀄️🀄️ል፦ @Holy_scriptures
👍54
.       ──•◈•─────•◈•─
                          የዕለቱ ጥቅስ
        ──•◈•─────•◈•─
“ሰው ሆይ፥ መልካሙን ነግሮሃል፤ እግዚአብሔርም ከአንተ ዘንድ የሚሻው ምንድር ነው? ፍርድን ታደርግ ዘንድ፥ ምሕረትንም ትወድድ ዘንድ፥ ከአምላክህም ጋር በትሕትና ትሄድ ዘንድ አይደለምን?”
ሚክያስ 6፥8



ወደ ቻናሉ ለመ🀄️🀄️ል፦ @Holy_scriptures
7
#እራሳችንን_እንመርምር


መንፈሣችንን መቆጣጠር ላይ እንዴት ነን? መንፈሣችን ቅጥር ከሌለው የክርስትና ሕይወታችን ተጠብቆ ለጌታ ቀን የምንበቃውስ በየትኛው መንገድ ነው?

“ቅጥር እንደሌላት እንደ ፈረሰች ከተማ፥ መንፈሱን የማይከለክል ሰው እንዲሁ ነው።”
ምሳሌ 25፥28



ወደ ቻናሉ ለመ🀄️🀄️ል፦ @Holy_scriptures
👍1🙏1
.       ──•◈•─────•◈•─
                          የዕለቱ ጥቅስ
        ──•◈•─────•◈•─
“እግዚአብሔር የላከው የእግዚአብሔርን ቃል ይናገራልና፤ እግዚአብሔር መንፈሱን ሰፍሮ አይሰጥምና።”
ዮሐንስ 3፥34



ወደ ቻናሉ ለመ🀄️🀄️ል፦ @Holy_scriptures
👍2
#መጻሕፍትን_በድምጽ

📔ርዕስ፦ የመጽሐፍ ቅዱስ አስተምህሮ
👤ጸሐፊ፦ ዶ/ር ቻርልስ ሲ.ራይሪ
🗣ተርጓሚ፦ ሲሳይ ደሳለኝ



ወደ ቻናሉ ለመ🀄️🀄️ል፦ @Holy_scriptures
👍4
ቅዱሳት መጻሕፍት
#እምነት                    ክፍል-8 በቅዱሳት መጻሕፍት መሠረት እምነታችንን ለመጠበቅ ምን እናድረግ? 1. ጸሎት እና በእግዚአብሔር ላይ መደገፍ “እኔ ግን እምነትህ እንዳይጠፋ ስለ አንተ ጸለይሁ፤ አንተም በተመለስህ ጊዜ ወንድሞችህን አበርታ።””          ሉቃስ 22፥32 (አዲሱ መ.ት) ኢየሱስ እምነታችንን ለመጠበቅ ጸሎት አስፈላጊ እንደሆነ ያስተምራል። በጸሎት የእግዚአብሔርን…
#እምነት


                 ክፍል-9


እምነት እና ሥራ


በመጽሐፍ ቅዱስ መሠረት ሰው የሚድነው ወይም የሚጸድቀው በእምነት እንጂ በሥራ እንዳልሆነ እርግጥ ነው፤ ይህ በእምነት የመጽደቅ ጉዳይም በሰው ዘንድ ሳይሆን በእግዚአብሔር ዘንድ የሚታየው ነው፡፡

በሮሜ 4፥1‐8 የምናገኘው የእግዚአብሔር ቃል ይህን የሚያረጋግጥ ነው፤ በቊ.1 ላይ «በሥጋ አባታችን የሆነ አብርሃም ምን አገኘ እንላለን? አብርሃም በሥራ ጸድቆ ቢሆን የሚመካበት አለውና፤ ነገር ግን በእግዚአብሔር ዘንድ አይደለም» ይላል፤ «በእግዚአብሔር ዘንድ አይደለም» የሚለው ይህ ቃል በእግዚአብሔር ዘንድ በሥራ መጽደቅ እንደሌለ የሚገልጽ ነው፡፡

በዚህ ክፍል ሰው ያለ ሥራ በእምነት እንደሚጸድቅ ለማሳየት ሁለት ሰዎች በምሳሌነት ተጠቅሰዋል፤ እነርሱም አብርሃምና ዳዊት ናቸው፡፡ እነዚህ ሁለት ሰዎች በአንድነት መጠቀሳቸው በመጽሐፍ ቅዱስ የተለመደ ሲሆን (ማቴ.1፥1፤ የሐ.ሥ.13፥26‐36) ይህንንም ታላቅ ርእሰ ጉዳይ ለማብራራት አብረው መጠቀሳቸው ወሳኝ ነው፡፡ አብርሃም የነበረው ሕግ ከመሰጠቱ በፊት ሲሆን ዳዊት ደግሞ በሕጉ ዘመን የነበረ ሰው ነው፤ ከሁለቱም ሰዎች አንጻር ሲታይ ግን በእግዚአብሔር ዘንድ ጽድቅ የሚቈጠረው በሥራ ሳይሆን በእምነት እንደሆነ ተብራርቷል፡፡

በቊ.3 ላይ አብርሃምን በተመለከተ ሲገልጽ «መጽሐፍስ ምን አለ? አብርሃም እግዚአብሔርን አመነ ጽድቅም ሆኖ ተቈጠረለት፤ ለሚሠራ ደመወዝ እንደ ዕዳ ነው እንጂ እንደ ጸጋ አይቈጠርለትም፤ ነገር ግን ለማይሠራ ኃጢአተኛውን በሚያጸድቅ ለሚያምን ሰው እምነቱ ጽድቅ ሆኖ ይቈጠርለታል» ይላል፡፡ በዚህም ቃል ውስጥ አብርሃም ጽድቅን ያገኘው እግዚአብሔርን ስላመነ ተቈጥሮለት እንጂ ጽድቅ ሠርቶ እንዳልሆነ እንገነዘባለን፡፡ ይህም ለሚያምን ሰው ሁሉ እግዚአብሔር የሚያደርገው መሆኑ ተገልጿል፡፡ በመቀጠል ደግሞ ዳዊት ይህን ጉዳይ በተመለከተ የተናገረው ተጠቅሷል፡፡ ይኸውም «እንደዚህም ደግሞ እግዚአብሔር ያለ ሥራ ጽድቅን ስለሚቈጥርለት ሰው ብፅዕና ይናገራል እንዲህ ሲል፤ ‘ዓመፃቸው የተሰረየላቸው ኃጢአታቸውም የተከደነላቸው ብፁዓን ናቸው፤ ጌታ ኃጢአቱን የማይቈጥርበት ሰው ብፁዕ ነው»(ቊ.6‐8)፤ በአብርሃም ሕይወት እንዳየነው እግዚአብሔር ሊቈጠርልን የማይገባውን ጽድቅ በእምነት ሲቈጥርልን እናያለን፤ በዚህ ዳዊት በተናገረው ቃል ውስጥ ደግሞ እግዚአብሔር ሊቈጥርብን የሚገባውን ኃጢአት ባለመቊጠር ጸጋውን ሲያሳይ እንመለከታለን፡፡ ይህም «እግዚአብሔር ያለ ሥራ ጽድቅን ስለሚቈጥርለት ሰው ብፅዕና» የተነገረ መሆኑ ተገልጿል፡፡ ስለዚህ በሮሜ 4 ውስጥ የተሰጠው ትምህርት ሰው በእግዚአብሔር ዘንድ የሚጸድቀው ያለ ሥራ በእምነት መሆኑን የሚያሳይ ነው፤ ይህ እምነት በሥራ ሊገለጥ የሚችል እውነተኛ መሆኑን እግዚአብሔር ማወቅ ይችላልና፡፡

በያዕ.2 ውስጥ የምናገኘው ትምህርት ግን ጽድቅ ወይም መዳን በሰው ዘንድ የሚታየው ወይም የሚረጋገጠው በእምነት ብቻ ሳይሆን በሥራም እንደሆነ የሚገልጽ ነው፡፡ በሰው ዘንድ የአንድ ሰው እምነት እውነተኛ እምነት መሆኑ ሊታይ የሚችለው በሥራ ነው፤ በቊ.14 ላይ «ወንድሞች ሆይ እምነት አለኝ የሚል ሥራ ግን የሌለው ሰው ቢኖር ምን ይጠቅመዋል፤ እምነቱስ ሊያድነው ይችላልን?» በማለት ያዕቆብ ጥያቄ ያነሳል፤ እዚህ ላይ «እምነት አለኝ» የሚለው ያ ሰው ራሱ ነው፡፡


ይቀጥላል...


ምንጭ፦ 1bible.page



ወደ ቻናሉ ለመ🀄️🀄️ል፦ @Holy_scriptures
👍92🔥1😁1
.       ──•◈•─────•◈•─
                          የዕለቱ ጥቅስ
        ──•◈•─────•◈•─
“ተመልሶ ይምረናል፤ ክፋታችንንም ይጠቀጥቃል፥ ኃጢአታችንንም በባሕሩ ጥልቅ ይጥለዋል።”
ሚክያስ 7፥19



ወደ ቻናሉ ለመ🀄️🀄️ል፦ @Holy_scriptures
7🙏2
Audio
#መጻሕፍትን_በድምጽ

📔ርዕስ፦ የመጽሐፍ ቅዱስ አስተምህሮ
👤ጸሐፊ፦ ዶ/ር ቻርልስ ሲ.ራይሪ
🗣ተርጓሚ፦ ሲሳይ ደሳለኝ
👉መግቢያ

ይቀጥላል...


ወደ ቻናሉ ለመ🀄️🀄️ል፦ @Holy_scriptures
👍81
ክርስቲያናዊ ዓቅብተ እምነት – CHRISTIAN APOLOGETICS



ክፍል-1


መግቢያ

“ዳሩ ግን ጌታን እርሱም ክርስቶስ በልባችሁ ቀድሱት። በእናንተ ስላለ ተስፋ ምክንያትን ለሚጠይቁዋችሁ ሁሉ መልስ ለመስጠት ዘወትር የተዘጋጃችሁ ሁኑ፥ ነገር ግን በየዋህነትና በፍርሃት ይሁን።” 1ጴጥ. 3፥15

የክርስቶስ ቤተ ክርስቲያን ያለ ተግዳሮት የኖረችበት ዘመን የለም፡፡ በየዘመናቱ የነበሩት ተግዳሮቶች አንድ መልክ ባይኖራቸውም ነገር ግን አንድ ዓላማና ግብ ያላቸው ሆነው እናገኛቸዋለን፡፡ እርሱም ቤተ ክርስቲያንን ማዳክም ብሎም ማጥፋት ነው፡፡ ነገር ግን በተለያዩ ዘመናት የኖሩት ክርስቲያኖች መሠረታዊውን የክርስትና አስተምሕሮ ከውስጣዊና ውጫዊ ተግዳሮቶች ተከላክሎ በማቆየቱ ረገድ በመንፈስ ቅዱስ እርዳታ ከፍተኛውን ሚና ተጫውተዋል፡፡

የምንኖረው መንፈሳዊ ውጊያ ባለበት ዓለም ውስጥ ነው፡፡ ውጊያው ደግሞ የሚደረገው በሰዎች አዕምሮ ውስጥ ነው፡፡ ይህንን ውጊያ ለማሸነፍ የተዘጋጀንና የታጠቅን መሆን ያስፈልገናል፡፡ የዚህ ጽሑፍ ዓላማ ስለ ክርስቲያናዊ ዓቅብተ እምነት ታሪካዊ አመጣጥና መጽሐፍ ቅዱሳዊነት መሠረታዊ ግንዛቤን ማስጨበጥ ነው። መጽሐፍ ቅዱስ 1ቆሮ 10፥4-6 ላይ በተናገረው መሠረት በእግዚአብሔር ሐሳብ ላይ የሚነሳውን ከፍ ያለውን የሰውን ሐሳብ በማፍረስ አዕምሮን ሁሉ ለክርስቶስ እንዴት መማረክ እንደምንችል ክርስቲያናዊውን መንገድ ያመላክታል፡፡ አንባቢያንም ስለ ክርስቲያናዊ ዓቅብተ እምነት የበለጠ ጥናት እንዲያደርጉ እንደሚያነሳሳና አቅጣጫን እንደሚጠቁም ይታመናል።

1.የክርስቲያናዊ ዓቅብተ እምነት ትርጉምና ታሪክ

1.1. ትርጉም

“አፖሎጀቲክስ” የሚለው የእንግሊዘኛ ቃል አፖሎጊያ ከሚል የግሪክ ቃል የመጣ ሲሆን ትርጓሜውም “በመከላከል መናገር” እንደ ማለት ነው፡፡ በጥንታዊቷ ግሪክ የሕግ ስርኣት ውስጥ ሁለት ቁልፍ የሆኑ ቃላት ጥቅም ላይ ይውሉ ነበር፤ የከሳሽ ወገን ንግግር “ካታጎሪያ” በመባል የሚታወቅ ሲሆን የተከሳሽ ወገን ምላሽ ደግሞ “አፖሎጊያ” በመባል ይታወቃል፡፡ “አፖሎጊያ’ የሚለው ቃል በአዲስ ኪዳን ውስጥ በተደጋጋሚ ተጠቅሷል። በሐዋርያት ሥራ 26፥2 ላይ ሐዋርው ጳውሎስ ተከሶ በፊስጦስና አግሪጳ ፊት በቀረበ ጊዜ ተጠቅሞበታል፤ እንዲሁም በፊልጵስዩስ 1፥7፣ 1፥16 እና 1ጴጥሮስ 3፥15 ላይ እናገኘዋለን፡፡

ዓቅብተ እምነት ከነገረ መለኮት የጥናት ዘርፎች መካከል አንዱ ሲሆን መረጃዎችን በተቀናበረ ሁኔታ በመጠቀም ለሃይማኖታዊ አስተምህሮ ጥብቅና መቆም ነው፡፡ የአንድ ሃይማኖት አስተምህሮ ትክክል መሆኑንና እምነቱን መምረጥ ከሰው አመክንዮአዊ አስተሳሰብ ጋር የማይጣረስ መሆኑን ለማሳየት የሚደረግ ጥረትም ነው፡፡ ስለዚህ ዓቅብተ እምነት ሰዎች አስተሳሰባቸውን እንዲለውጡ የማሳመን ሥራ ነው፡፡ ክርስቲያናዊ ዓቅብተ እምነት ክርስቲያናዊ ሥነ መለኮት (Christian Theology)፣ ተፈጥሯዊ ሥነ መለኮት (Natural Theology) እና ፍልስፍናን በማጣመር ክርስቲያናዊውን አስተምህሮ ከውጪያዊ ጥቃቶችና የተሳሳቱ ትርጓሜዎች ለመከላከል ይጥራል፣ እንዲሁም የሌሎች ንፅረተ ዓለማት አስተምሕሮዎችን ይመረምራል፡፡


ይቀጥላል...


ምንጭ:- ewnetlehulu.org




ወደ ቻናሉ ለመ🀄️🀄️ል፦ @Holy_scriptures
👍5