ቅዱሳት መጻሕፍት
7.45K subscribers
1.36K photos
61 videos
332 files
801 links
በዚህ ቻናል

👉ቅዱሳት መጻሕፍት ይጠናሉ::
👉መጽሐፍ ቅዱሳዊ ትምህርቶች ይቀርባሉ::
👉 ለቅዱሳት መጽሐፍት ጥናት የሚያግዙ መጻሕፍት ይለቀቃሉ።

⭐️⭐️⭐️⭐️⭐️

@Holy_scriptures
Download Telegram
#የእግዚአብሔር_ቃል_ምን_ይላል?


ሮሜ 8
¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯
¹ እንግዲህ በክርስቶስ ኢየሱስ ላሉት አሁን ኵነኔ የለባቸውም።
² በክርስቶስ ኢየሱስ ያለው የሕይወት መንፈስ ሕግ ከኃጢአትና ከሞት ሕግ አርነት አውጥቶኛልና።
³-⁴ ከሥጋ የተነሣ ስለ ደከመ ለሕግ ያልተቻለውን፥ እግዚአብሔር የገዛ ልጁን በኃጢአተኛ ሥጋ ምሳሌ በኃጢአትም ምክንያት ልኮ አድርጎአልና፤ እንደ መንፈስ ፈቃድ እንጂ እንደ ሥጋ ፈቃድ በማንመላለስ በእኛ የሕግ ትእዛዝ ይፈጸም ዘንድ ኃጢአትን በሥጋ ኰነነ።
⁵ እንደ ሥጋ ፈቃድ የሚኖሩ የሥጋን ነገር ያስባሉና፥ እንደ መንፈስ ፈቃድ የሚኖሩ ግን የመንፈስን ነገር ያስባሉ።
⁶ ስለ ሥጋ ማሰብ ሞት ነውና፥ ስለ መንፈስ ማሰብ ግን ሕይወትና ሰላም ነው።
⁷ ስለ ሥጋ ማሰብ በእግዚአብሔር ዘንድ ጥል ነውና፤ ለእግዚአብሔር ሕግ አይገዛምና፥ መገዛትም ተስኖታል፤
⁸ በሥጋ ያሉትም እግዚአብሔርን ደስ ሊያሰኙት አይችሉም።
⁹ እናንተ ግን የእግዚአብሔር መንፈስ በእናንተ ዘንድ ቢኖር፥ በመንፈስ እንጂ በሥጋ አይደላችሁም። የክርስቶስ መንፈስ የሌለው ከሆነ ግን ይኸው የእርሱ ወገን አይደለም።
¹⁰ ክርስቶስ በእናንተ ውስጥ ቢሆን ሰውነታችሁ በኃጢአት ምክንያት የሞተ ነው፥ መንፈሳችሁ ግን በጽድቅ ምክንያት ሕያው ነው።
¹¹ ነገር ግን ኢየሱስን ከሙታን ያስነሣው የእርሱ መንፈስ በእናንተ ዘንድ ቢኖር፥ ክርስቶስ ኢየሱስን ከሙታን ያስነሣው እርሱ በእናንተ በሚኖረው በመንፈሱ፥ ለሚሞተው ሰውነታችሁ ደግሞ ሕይወትን ይሰጠዋል።



ወደ ቻናሉ ለመ🀄️🀄️ል፦ @Holy_scriptures
3👍1
.       ──•◈•─────•◈•─
                          የዕለቱ ጥቅስ
        ──•◈•─────•◈•─
“ነገር ግን፦ ቃሌን ስሙ፥ እኔም አምላክ እሆናችኋለሁ እናንተም ሕዝብ ትሆኑኛላችሁ፤ መልካምም ይሆንላችሁ ዘንድ ባዘዝኋችሁ መንገድ ሁሉ ሂዱ ብዬ በዚህ ነገር አዘዝኋቸው።”
ኤርምያስ 7፥23



ወደ ቻናሉ ለመ🀄️🀄️ል፦ @Holy_scriptures
🔥4👍1
የካታኮቡ ሰማእታት ክፍል አሥር catacombs part 10
ታላቁ ተስፋ - Great Hope - Official
#መጻሕፍትን_በድምጽ

👉ርዕስ፦ የካታኮምቡ ሰማዕት
🗣ትርጉም፦ በአማረ ማሞ
መካነ ኢየሱስ ሥነ ጽሑፍ ክፍል።
📻ክፍል-10

ይቀጥላል...



ወደ ቻናሉ ለመ🀄️🀄️ል፦ @Holy_scriptures
👍2🔥2
#ከተማ_ወይም_ቦታ_በቅዱሳት_መጻሕፍት


#ደማስቆ


ሁለት ሺህ ዓመት ከክርስቶስ ልደት በፊት የተሠራ እስከ ዛሬ ድረስ የሶርያ መናገሻ ከተማ የሆነ። «ቅን» የተባለው ጥንታዊ መንገድ እስከ አሁን ይገኝበታል፤ ሐ.ሥ. 9፥11። በአቅራቢያው አባናና ፋርፋ የተባሉ ሁለት ወንዞች ይፈሳሉ፤ 2ነገ. 5፥12። ከምሥራቅ ወደ ታላቁ ባሕር፥ ከሰሜንም ወደ ግብጽ የሚሄዱ መንገዶች የሚገናኙበት ስለሆነ፥ ብዙ ነጋዴዎች የሚመላለሱበት መናኸሪያ ከተማ ነበር።
አብርሃም በአቅራቢያው ይኖር ነበር፣ ዘፍ. 14፥15። እነዳዊት የደማስቆን ሰዎች ድል ነሡ፤ 2ሳሙ. 8፥5:6። በእስራኤል ታሪክ ውስጥ ስማቸው ተጽፎ የምናገኛቸው የሶርያ ገዥዎች የሚከተሉት ናቸው ፦

👉ሬዞን (1ነገ. 11፥23-25)፥
👉ወልደ አዴር (1ነገ. 15፥18)፥
👉አዛሄል (2ነገ. 13፥22)፥
👉ወልደ አዴር 2ኛ (2ነገ. 13፥24)፥
👉ረአሶን (2ነገ. 16፥5፤ ኢሳ. 7፥1)።

ጳውሎስ ወደ ደማስቆ ሲሄድ ሳለ ክርስቶስ ተገለጠለት፤ ወንጌልን ማስተማር በደማስቆ ጀመረ፤ ሐ.ሥ. 9። በ628 ዓ.ም. የእስልምና ሃይማኖት ተከታዮች ከተማውን ማረኩና የእስልምና ትምህርት ማስፋፊያ አደረጉት።



ምንጭ፦ የመጽሐፍ ቅዱስ መዝገበ ቃላት፤ ገጽ 227-228



ወደ ቻናሉ ለመ🀄️🀄️ል፦ @Holy_scriptures
5👍1
.       ──•◈•─────•◈•─
                          የዕለቱ ጥቅስ
        ──•◈•─────•◈•─
“ድሆችን እናስብ ዘንድ ብቻ ለመኑን፥ ይህንም ደግሞ ላደርግ ተጋሁ።”
ገላትያ 2፥10



ወደ ቻናሉ ለመ🀄️🀄️ል፦ @Holy_scriptures
👍21
Audio
#መጻሕፍትን_በድምጽ

👉ርዕስ፦ የካታኮምቡ ሰማዕት
🗣ትርጉም፦ በአማረ ማሞ
መካነ ኢየሱስ ሥነ ጽሑፍ ክፍል።
📻ክፍል-11

ይቀጥላል...



ወደ ቻናሉ ለመ🀄️🀄️ል፦ @Holy_scriptures
3👍3
ወደ ቻናሉ ለመ🀄️🀄️ል፦ @Holy_scriptures
ንቃ.pdf
6.1 MB
ርዕስ፦ ንቃ
ከአስመሳይ ሃይማኖተኞች ተጠንቀቁ
2ኛ ጴጥሮስ፣ 2ኛ እና 3ኛ ዮሐንስና ይሁዳ መልእክቶች
ጸሐፊ፦ ዋረን ደብልዩ ዌርዝቢ
ትርጉም፦ መስፍን ታዬ



ወደ ቻናሉ ለመ🀄️🀄️ል፦ @Holy_scriptures
10👏1🙏1
.       ──•◈•─────•◈•─
                          የዕለቱ ጥቅስ
        ──•◈•─────•◈•─
“የእስራኤል ቅዱስ፥ ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላልና፦ በመመለስና በማረፍ ትድናላችሁ፤ በጸጥታና በመታመን ኃይል ይሆንላችኋል፤ እናንተም እንቢ አላችሁ፥”
ኢሳይያስ 30፥15



ወደ ቻናሉ ለመ🀄️🀄️ል፦ @Holy_scriptures
7👍2🙏2
የጸጋ ስጦታዎች ውጤታማ አሠራር እንዴት ሊሆን ይገባል?


                      ክፍል-1


                               በመርዕድ ለማ

በዚህ ክፍል የጸጋ ስጦታዎች አሠራር እንዴት እንደ ሆነ እናያለን። ጽሑፉ፦ መንፈሳዊ ልምምዶች፣ ሚዛናዊነት ወይስ አክራሪነት?፣ ጌታ ወይስ ስጦታው? በሚሉ ሦስት ዐበይት ክፍሎች ቀርቧል። በጽሑፉ ማጠቃለያም ፍቅር ከጸጋ ስጦታዎች ጋር ያለውን ትስስርና ተዛምዶ እንመለከታለን።

መንፈሳዊ ልምምዶች

መንፈሳዊ ልምምዶችን በሁለት መልኩ ማየት እንችላለን። የመጀመሪያው፣ ልምምዶችን ማክረር ነው። መንፈሳዊ ልምምድ በራሱ እራሱን የቻለ አገልግሎት ወይም ውጤት አይደለም። የአገልግሎት መድረኮች የተለያዩ መንፈሳዊ ልምምዶች ጎልተው ይታዩባቸዋል። ማሸብሸብ፣ እጅን ዘርግቶ መጸለይ፣ ዝግ ብሎ መናገር፣ ጮኾ መናገር፣ ወዘተ። እነኚህን የመሳሰሉ ልምምዶች ሊኖሩ ይችላሉ። ቁም ነገሩና ዋነኛው ጉዳይ “በሰዎች ሕይወት ውስጥ ምን ሆነ? ተፈወሱ? በመንፈስ ቅዱስ ተሞሉ? ሕይወታቸው ተለወጠ? በምናስተናግደው ሕዝብ ሕይወት ውስጥ ምንድነው የሚታየው? ለውጡ፣ ፍሬው እንዴት ነው?” የሚለው ነው። አለበለዚያ የልምምድ አገልጋዮች ብቻ ሆነን እንቀራለን። የብዙዎች አገልግሎት ውጤት አልባ የሚሆነው የሰዎችን ልምምድ ስለሚኮርጁ ነው። እግዚአብሔር እያንዳንዳችንን እንዳለን ሆነን እንድናመልከውና እንድናገለግለው ይፈልጋል። እኛው በእኛነታችን ሆነን ብናገለግለው ለሰዎች ውብና ማራኪ እንሆናለን። ምክንያቱም እግዚአብሔር እኔን አንተን ወይም አንቺን የመሰለ ሌላ ሰው አልፈጠረምና።

ቀጥሎ፣ የልምምድ ተቃዋሚዎች ጉዳይ ነው። እነኚህ በጣም ወግ አጥባቂ ስለሆኑ አንድ ጊዜ የጨበጡትን ነገር እድሜ ዘመናቸውን መልቀቅ አይፈልጉም። ለልምምዱማ እነርሱም የራሳቸው ልምምድ አላቸው። ዳሩ ግን ካወቅሁት ሌላ ነገር እንዴት? ለምን? የሚል ግትርነት ያስቸግራቸዋል። መሠረታዊ የሆነው የእግዚአብሔር ቃል አይለወጥ እንጂ አሠራሮችና ልምምዶችን ወጥ ይሁኑ አንበል። የጌታ ኢየሱስን የፈውስ አገልግሎት ስንመለከት እጁን ጭኖ ፈውሶአል፤ በቃል ብቻ ፈውሶአል፤ የዕውሩን ዓይን ጭቃ በመቀባት ፈውሶአል። የእግዚአብሔር ኃይል ትናንት በሠራበት መንገድ ብቻ አልነበረም በሚቀጥለው ቀን ሲሠራ የታየው። ሐዋርያው ጳውሎስም እጁን በመጫን ፈውሶአል፤ በለበሰው ጨርቅ አማካይነት ፈውሶአል። እነ ጴጥሮስ ጥላቸው እንኳ ሳይቀር ፈውሶአል። በብሉይ ኪዳን ኤልሳዕ በሞተው በሱነማዪቱ ልጅ ላይ ተዘርግቶበት ወደ ሕይወት መልሶታል። እስቲ በተለያዩ ጊዜአት እናንተም የተለማመዳችሁትን ልምምድ አስታውሱ። በዘመናችን እጅ በመጫን ሌሎች የመውደቃቸው ነገር አጠያያቂ ሆኗል። ምናልባት በኛም አገር የመንፈስ ቅዱስ መነቃቃት ሲጀምርና ለመንፈስ ቅዱስ ሙላት ስንጸልይላቸው፣ ከመንቀጥቀጥ፣ ከመጮኽም አልፈው የወደቁ ብዙዎች ናቸው። መውደቁ ብቻውን አገልግሎት መሆን አይችልም። ዳሩ ግን መንፈስ ቅዱስ በተለየ መንገድ ሲመጣ ልንወድቅ እንችላለን። የእጅ መጫን መነሻ አሳባችንን እንፈትሸው። ለመንፈሳዊ በረከት፣ ለመንፈስ ቅዱስ ሙላት፣ ለፈውስ ወይስ ሰዎችን ለመጣል? የእጅ መጫን ዓላማችን ትክክለኛ ከሆነ ምናለ ይውደቁ። እኛንም የመንፈስ ቅዱስ ኃይል ከጣለን እንውደቅ። በነጆን ዌስሊና ጆናታን ኤድዋርድስ አገልግሎት ብዙ ሰዎች ራሳቸውን መቆጣጠር አቅቷቸው ይወድቁ ነበር። ነገር ግን አሁንም ደግሜ እላለሁ፣ መውደቅ እራሱ ብቻውን አገልግሎት አይደለም። ስሚዝ ዊግልስወርዝ የሚባል ታላቅ የእምነት ሰው የታመሙ ሰዎችን የታመሙበትን ሥፍራ በቦክስ በመምታት ፈውሶአል። እሱ ይህን ስላደረገ እኛም እንድርግ ብንል ያለ ጥርጥር በወንጀል ተከሰን ፍርድ ቤት ልንቀርብ እንችላለን። ስለዚህ መንፈስ ቅዱስን እናድምጠው፤ አገልግሎታችንም ይሠምራል።

ሚዛናዊነት ወይስ አክራሪነት?

ሐዋርያው ጳውሎስ በ1ኛ ተሰሎንቄ 5፡19-22 ባለው ክፍል ሲናገር “መንፈስን አታጥፉ፤ ትንቢትን አትናቁ፤ ሁሉን ፈትኑ መልካሙንም ያዙ፤ ከማናቸውም ዓይነት ክፉ ነገር ራቁ” ይላል። በዚህ ክፍል ለሚዛናዊነት የሚረዱን አምስት ሃሳቦችን እናያለን።

1. መንፈስን አታጥፉ፦

በብሉይ ኪዳን ለካህናት ከተሰጣቸው የአገልግሎት ድርሻ አንዱ ዘወትር በመሠዊያ ላይ እሳት እንዲነድ ማድረግ፣ እንዳይጠፋ መጠበቅ ነበር። መንፈስ ቅዱስ በእሳት ይመሰላል። ይህ እሳት የሆነው የእግዚአብሔር መንፈስ ከቤተክርስቲያናችንና ከግል ሕይወታችን ከጠፋ አገልግሎታችን ሁሉ ይጠፋል። ስለዚህ ዘወትር በመንፈስ ቅዱስ ጋር እንሥራ፤ በመንፈስ ቅዱስ እንመራ። በተለያዩ ችግሮች ምክንያት መንፈሱን አናዳፍነው። ይህም ሐዋርያው ጳውሎስ ጢሞቴዎስን እንዳሳሰበው ማለት ነው። “ስለዚህ ምክንያት፣ እሳት እንደሚያቀጣጥል ሰው፣ እጆቼን በመጫኔ በአንተ ላይ ያለውን የእግዚአብሔርን ስጦታ እንድታነሳሳ አሳስብሃለሁ።” (2ኛ ጢሞቴዎስ 1፡6)

2. ትንቢትን አትናቁ፦

የትንቢት አገልግሎት በሐዲስ ኪዳን ቤተክርስቲያን በጣም የታወቀ አገልግሎት ነው። ደግሞም ሐዋርያው ጳውሎስ ይህን ስጦታ ለማግኘት ፈልጉ ይላል። አንዳንድ ጊዜ በስመ ትንቢት ቤተክርስቲያን ችግር ሊገጥማት ይችላል። እውነተኞች ትንቢት ተናጋሪዎች እንደ መኖራቸው ሁሉ ሐሰተኞች ነቢያትም ይኖራሉ። ታዲያ ባንዳንድ በተሳሳተ ትንቢት ሳቢያ በሚመጣ ችግር “ከዛሬ ጀምሮ ትንቢት የሚባል ነገር አያስፈልገንም” በማለት ቤተክርስቲያን ይህንንም ጸጋ እንዳትጥለው ጥንቃቄ ያስፈልጋል።


ይቀጥላል...


ምንጭ:- shalomgospel.com




ወደ ቻናሉ ለመ🀄️🀄️ል፦ @Holy_scriptures
👍74🙏1
.       ──•◈•─────•◈•─
                          የዕለቱ ጥቅስ
        ──•◈•─────•◈•─
“የወንጌልም እውነት በእናንተ ዘንድ ጸንቶ እንዲኖር ለአንድ ሰዓት እንኳ ለቅቀን አልተገዛንላቸውም።”
ገላትያ 2፥5


ወደ ቻናሉ ለመ🀄️🀄️ል፦ @Holy_scriptures
5
Audio
👉ርዕስ፦ ፍትሕ
በባይብል ፕሮጀክት፣ በአማርኛ ቋንቋ የተዘጋጀ


ወደ ቻናሉ ለመ🀄️🀄️ል፦ @Holy_scriptures
2👍1
.       ──•◈•─────•◈•─
                          የዕለቱ ጥቅስ
        ──•◈•─────•◈•─
“ልቡ ጠቢብ፥ ኃይሉም ታላቅ ነው፤ ደፍሮትስ በደኅና የሄደ ማን ነው?”
ኢዮብ 9፥4



ወደ ቻናሉ ለመ🀄️🀄️ል፦ @Holy_scriptures
3👍2
#እራሳችንን_እንመርምር


በአንድ ክርስቲያን ዘንድ የአፍ እና የልብ መለያየትን የመሰለ መጥፎ ነገር የለም። ሁለቱም በአንድነት ሲያብሩ ማየት ትልቅ ነገር ነው። ሁለቱም በአንድነት ቆመው በእግዚአብሔር ዓይን እርሱ ደስ ሲያሰኙ ማየት ደግሞ የስኬት ስኬት ነው። ለመሆኑ ወደዚህ ስኬት ደርሰናል?


“አቤቱ፥ ረድኤቴ መድኃኒቴም፥ የአፌ ቃልና የልቤ አሳብ በፊትህ ያማረ ይሁን።”
መዝሙር 19፥14




ወደ ቻናሉ ለመ🀄️🀄️ል፦ @Holy_scriptures
👍6🔥2
.       ──•◈•─────•◈•─
                          የዕለቱ ጥቅስ
        ──•◈•─────•◈•─
“ልጄ ሆይ፥ ልብህ ጠቢብ ቢሆን ልቤ ደግሞ ደስ ይለዋል፤”
ምሳሌ 23፥15



ወደ ቻናሉ ለመ🀄️🀄️ል፦ @Holy_scriptures
6👍1
ወደ ቻናሉ ለመ🀄️🀄️ል፦ @Holy_scriptures
3👍2
ስልታዊ ነገረ መለኮት.pdf
21.6 MB
ርዕስ፦ ስልታዊ ነገረ መለኮት ቅጽ-1
ጸሐፊ፦ ዌይን ግሩደም
ትርጉም፦ ተስፋዬ መስፍን፣ ደርበው አዱኛ፣ ፍስሐ ፈይሳ፣ ምኒልክ አስፋው፣ ጌታቸው ወ/አማኑኤል፣ ሚናስ ብሩክ
አርትኦት፦ ንጉሤ ቡልቻ፣ ፍስሐአምላክ እንየው

የመጽሐፍ ቅዱስ አስተምህሮ መግቢያ


ወደ ቻናሉ ለመ🀄️🀄️ል፦ @Holy_scriptures
9👍2
የአትናቴዎስ የሃይማኖት መግለጫ


1. ለመዳን የሚፈልግ ሁሉ ከሁሉም ነገር አስቀድሞ የሁሉ የሆነች የቤተ ክርስቲያን ሃይማኖትን እውነተኛ አድርጎ ሊቀበል ያስፈልገዋል።
2. ንጹሕና ሙሉ አድርጎ ያልጠበቀው ሁሉ ያለ ጥርጥር የዘላለም ጥፋት ይደርስበታል።
3. በሦስትነቱ አንድነቱን፥ በአንድነቱም ሦስትነቱን አምነን አንድ አምላክን እናመልካለን። ይህም እውነተኛ የክርስትና ሃይማኖት ነው።
4. ይህንንም የምናደርገው አካላቱን ሳንደባልቅ መለኮታዊ ህልውናውንም ሳንከፍል ነው።
5. ምክንያቱም የአብ አካል ለብቻው የወልድ ለብቻው፥ የመንፈስ ቅዱስም ለብቻው ስለሆነ ነው።
6. ሆኖም የአብ፥ የወልድና የመንፈስ ቅዱ መለኮት አንድ ነው፥ ክብሩ ሥልጣኑም እኩል ሆኖ ይኖራል።
7. ወልድ በህልውናው እንደ አብ ነው፥ መንፈስ ቅዱስም እንደዚሁ ነው።
8. አብ አልተፈጠረም፥ ወልድ አልተፈጠረም፥ መንፈስ ቅዱስም አልተፈጠረም።
9. አብ ወሰን የለውም፥ ወልድ ወሰን የለውም፥ መንፈስ ቅዱም ወሰን የለውም።
10. አብ ዘላለማዊ ነው፥ ወልድ ዘላለማዊ ነው፥ መንፈስ ቅዱስም ዘላለማዊ ነው።
11. ቢሆነም ዘላለማዊ የሚሆን አንድ እንጂ ሦስት አይደሉም።
12. ያልተፈጠረና ወሰን የሌለው ሦስት እንዳልሆነ እንደዚሁም ያልተፈጠረና ወሰን የሌለው አንድ ነው።
13. እንዲሁም አብ ሁሉን የሚችል ነው፥ ወልድ ሁሉን የሚችል ነው፥ መንፈስ ቅዱስም ሁሉን የሚችል ነው።
14. ቢሆንም፥ ሁሉን የሚችል አንድ አንጂ ሦስት አይደሉም።
15. ስለዚህ አብ አምላክ ነው፥ ወልድ አምላክ ነው፥ መንፈስ ቅዱስም አምላክ ነው።
16. ሆኖም አንድ አምላክ እንጂ ሦስት አማልክት አይደሉም።
17. ስለዚህ አብ ጌታ ነው፥ ወልድ ጌታ ነው፥ መንፈስ ቅዱስም ጌታ ነው።
18. ሆኖም አንድ ጌታ እንጂ ሦስት ጌቶች አይደሉም።
19. ምክንያቱም የክርስትና እምነት እውነተኛነት እያንዳንዱ አካል አምላክና ጌታ መሆኑን እንድናምን እንደሚያስገድደን ሁሉ የክርስትና ሃይማኖት ሦስት አማልክት ወይም ሦስት ጌቶች እንዳንል ይከለክለናል።
20. አብ በማንም አልተሠራም፥ አልተፈጠረም፥ አልተወለደምም።
21. ወልድ ከአብ ተወለደ እንጂ አልተሠራም አልተፈጠረምም።
22. መንፈስ ቅዱስ አልተሠራም፥ አልተፈጠረም፥ አልተወለደምም፥ ነገር ግን ከአብ የሚሠርጽ ነው።
23. ስለዚህ አብ አንድ ስለሆነ ሦስት አብ አይደለም፥ ወልድም አንድ አንጂ ሦስት ወልድ አይደለም፥ መንፈስ ቅዱስም አንድ እንጂ ሦስት አይደለም።
24. ከሦቱ አካላት አንዱ ከሌላው ቀዳሚነት ወይም ደኃሪነት የለውም፤ አንዱም ከሌላው የሚበልጥ ወይም የሚያንስ አይደለም።
25. ስለሆነም፥ ሦስቱ አካላት በእኩልነትና በዘላለማዊነት አንድ ናቸው። ከዚህ የተነሣም ከፍ ብሎ እንደተጠቀሰው ሦስቱ አካላት በአንድ መለኮት አንድ አምላክም በሦስት አካላት ይመለካል።
26. ለመዳን የሚፈልግ ሁሉ ስለ ሥላሴ እንደዚህ ማሰብ ይገባዋል።
27. ከዚህም ሌላ የዘላለምን ደኅንነት ለማግኘት የጌታችንን የኢየሱስ ክርስቶስን በሥጋ መገለጽ በእውነት ማመን አስፈላጊ ነው።
28. ምክንያቱም ትክክለኛው እምነት ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ የእግዚአብሔር ልጅ አምላክም ሰውም መሆኑን አምነን ማስታወቅ ነው።
29. እርሱም ከዘመናት አስቀድሞ ከአብ የተወለደ አምላክ ከእናቱም በሥጋ በዓለም የተወለደ ሰው ነው።
30. የሚያስብ ነፍስ ያለችውና የሰውን ሥጋ የለበሰ ፍጹም አምላክ ፍጹም ሰው ነው።
31. በአምላክነቱ ከአብ ጋር የተካከለ፥ በሰውነቱም ከአብ ያነሰ ነው።
32. አምላክም ሰውም ቢሆንም አንድ ክርስቶስ እንጂ ሁለት ክርስቶስ አይደለም።
33. አንድ ነው ስንል ግን የሰውን ሥጋ ለበሰ እንጂ መለኮት ወደ ሥጋ አልተለወጠም።
34. በእርግጥ አንድ የሆነውም በባሕርያት መደባለቅ ሳይን በአካል አንድ በመሆኑ ነው።
35. ምክንያቱም የሚያስብ ነፍስና ሥጋ አንድ ሰው እንደሆኑ ሁሉ አምላክና ሰው በክርስቶስ አንድ ናቸው።
36. እርሱም ለደህንነታችን ሲል መከራ የተቀበለ፥ ወደ ሲኦል የወረደ፥ ከሙታን የተነሣ፤
37. ወደ ሰማይ የወጣ፥ በአብ ቀኝ የተቀመጠ፥ በሕያዋንና በሙታንም ሊፈርድ ከዚያ የሚመለስ ነው።
38. በመምጣቱ ጊዜም ሰዎች ሁሉ በሥጋ ተነስተው ስለ ሥራቸው መልስ ይሰጣሉ።
39. መልካም የሠሩ ወደ ዘላለም ሕይወት ክፉ የሠሩም ወደ ዘላለም እሳት ይገባሉ።
40. ይህ እውነትኛው የክርስትና እምነት ነው። ይህን የማያምንና አጥብቆ የማይዝ ሊድን አይችልም።




ወደ ቻናሉ ለመ🀄️🀄️ል፦ @Holy_scriptures
👍122🙏2🔥1
.       ──•◈•─────•◈•─
                          የዕለቱ ጥቅስ
        ──•◈•─────•◈•─
“አባቶቻችንም ሁሉ እንደነበሩ እኛ በፊትህ ስደተኞችና መጻተኞች ነን፤ ዘመናችንም በምድር ላይ እንደ ጥላ ናት፥ አትጸናም።”
1 ዜና 29፥15



ወደ ቻናሉ ለመ🀄️🀄️ል፦ @Holy_scriptures
👍62
ቅዱሳት መጻሕፍት
የጸጋ ስጦታዎች ውጤታማ አሠራር እንዴት ሊሆን ይገባል?                       ክፍል-1                                በመርዕድ ለማ በዚህ ክፍል የጸጋ ስጦታዎች አሠራር እንዴት እንደ ሆነ እናያለን። ጽሑፉ፦ መንፈሳዊ ልምምዶች፣ ሚዛናዊነት ወይስ አክራሪነት?፣ ጌታ ወይስ ስጦታው? በሚሉ ሦስት ዐበይት ክፍሎች ቀርቧል። በጽሑፉ ማጠቃለያም ፍቅር ከጸጋ ስጦታዎች ጋር ያለውን…
የጸጋ ስጦታዎች ውጤታማ አሠራር እንዴት ሊሆን ይገባል?


                      ክፍል-2


                               በመርዕድ ለማ


3. ሁሉን ፈትኑ፦

መቼም የሰማነውንና ያገኘነውን ሁሉ አግበስብሶ መቀበል ጤናማ ሕይወታችንን ያውካል። ያለንበት ዓለም በብዙ ዓይነት የመናፍስት አሠራር የተሞላ ነው። የእግዚአብሔር መንፈስ አለ፤ የሰይጣን መንፈስ አለ፤ የሰውም መንፈስ አለ። በምንሰማውና በምናየው ነገር አድናቆት ውስጥ ከመግባታችን በፊት ነገሩ ምን ይሆን? ብሎ የነገሩን ትክክለኛነት ለማረጋገጥ እንሞክር። ከእግዚአብሔር ቃል ጋር እንዲሁም በውስጣችን ካለው መንፈስ ጋር እናመሳክረው።

4. መልካሙን ያዙ፦

እግዚአብሔር እኛን ሲፈጥረን ተንቀሳቃሽ አሻንጉሊቶች አድርጎ አልሠራንም፤ የራሳችን ፈቃድ፣ ስሜትና ፍላጎት ያለን አድርጎ ነው። ደግሞም መልካሙን ከክፉው ለይተን እንድናውቅ አድርጎ አዘጋጅቶናል። እንዲሁም በልጁ በኢየሱስ ክርስቶስ አዲስ ፍጥረት ካደረገን በኋላ መንፈሱን በውስጣችን አስቀምጧል። ይህም መንፈስ የሚመራን ነው። በዚህም በእግዚአብሔር መንፈስ መሪነት መልካሙን ከክፉው ለይተን ከተረዳን፣ ክፉውን በመጣል መልካሙን በመያዝ መጽናት ይኖርብናል። “በእግዚአብሔር መንፈስ የሚመሩ ሁሉ እነዚህ የእግዚአብሔር ልጆች ናቸውና።” [ሮሜ 8፡14]

5. ከማናቸውም ዓይነት ክፉ ነገር ራቁ፦

እኛ የእግዚአብሔር ሰዎች ማንኛውንም ዓይነት ክፉ ነገር መጥላት ብቻ ሳይሆን ከዚያ መራቅ ግዴታችን ነው። ሐዋርያው ጳውሎስ በሮሜ 12፥9 ላይ “ክፉውን ነገር ተጸየፉት” ይላል። አንድ የተጸየፍነውን ነገር በዓይናችንም እንኳ ልናየው አንፈልግም። በአእምሮአችንም ልናሰላስለው አንወድም። ክፉውን ነገር ተጸየፉት ካለ በኋላ ከበጎ ነገር ጋር ተባበሩ ይላል። ስለዚህ ምንጊዜም ለበጎ ነገር ፈቃደኞችና ተባባሪዎች መሆን ይኖርብናል።

ጌታ ወይስ ስጦታው?

ሁላችንም ከፍተኛ ጥንቃቄ የምናደርግበት ጉዳይ እንዳለ ለማሳሰብ እወዳለሁ። ዛሬ መንፈስ ቅዱስ የሚሠራበት ወቅት እንደ መሆኑ መጠን ሰዎች መንፈሳዊ ጥማታቸውን ለማርካት ከአንዱ ቤተክርስቲያን ወደ ሌላው ሲሄዱ ያታያሉ። የተጠማነው ማንን ነው? ጌታን ነው ወይስ መንፈሳዊ ነገር? የመጀመሪያው ጥማታችንና ፍላጎታችን ጌታ ይሁን፤ ያኔ እንረካለን። “ማንም የተጠማ ቢኖት ወደ እኔ ይምጣና ይጠጣ” አለ ጌታ [ዮሐንስ 7፥37]

ለኃጢአተኞች፣ ለበሽተኞች ለተለያዩ ነፍሳት የሚሰበከው ምንድነው? ስብከታችን የሚያተኩረው ምን ላይ ነው? በጌታ ኢየሱስ ላይ መሆን ይገባዋል። ምክንያቱም የፈውስ፣ የመገለጥ፣ የተዓምራቶችና የድንቆች ሁሉ ምንጭ እራሱ ጌታ ኢየሱስ ስለሆነ። አገልጋዮች ምዕመናንን ልባቸውም ዓይናቸውም ከእኛ ላይ ተነሥቶ በክርስቶስ ላይ እንዲያርፍ እናድርግ። ይህን ብናደርግ ታማኝነታችን ይገለጻል። እንደገናም ትሕትና ነው። ሌላ ቀርቶ አንዳንድ በሽተኞች ወደ ቤተክርስቲያን ሲመጡ ፈውስን የሚቀበሉበትን መንገድ አዘጋጅተው ይመጣሉ። እግዚአብሔር ዛሬ በመገለጥ ተናገረኝ ይላሉ። ፈውስ በመገለጥ ብቻ አይመጣም። ምናልባትም ፈውስ ከሚመጣባቸው መንገዶች አንዱ ሊሆን ይችላል። ፈውስ በእግዚአብሔር፣ በእጅ በመጫን፣ በአምልኮ ውስጥ በመሆን ይመጣል። በፈለገው መንገድ ይምጣ ነገር ግን እኛ ባዶ ሆነን ጌታን እንፈልግ። የመንፈስ ቅዱስ ሥራ ጌታ ኢየሱስን ማክበር ነው። “የምነግራችሁ ገና ብዙ አለኝ፤ ነገር ግን አሁን ልትሸከሙት አትችሉም። ግን የእውነት መንፈስ በመጣ ጊዜ ወደ እውነት ሁሉ ይመራችኋል፤ የሚሰማውን ሁሉ ይናገራል እንጂ ከራሱ አይነግርምና፤ የሚመጣውንም ይነግራችኋል፣ እርሱ ያከብረኛል፣ ለእኔ ካለኝ ወስዶ ይነግራችኋል።” [ዮሐንስ 16፥14] እዚህ ላይ የምንመለከተው መንፈስ ቅዱስ ተጠሪነቱ ለራሱ ሳይሆን ለጌታ ኢየሱስ ነው። ስለዚህ ማንኛውም መንፈሳዊ አገልግሎቶች፣ የጸጋ ስጦታዎች፣ ልምምዶቻችን ሁሉ ለጌታ ክብር መዋል አለባቸው። እርሱ ኢየሱስ ክርስቶስ ጌታ እንደ ሆነ ማሳየትና መግለጥ ይኖርባቸዋል።


ይቀጥላል...


ምንጭ:- shalomgospel.com




ወደ ቻናሉ ለመ🀄️🀄️ል፦ @Holy_scriptures
6👍3