. ──•◈•─────•◈•─
የዕለቱ ጥቅስ
──•◈•─────•◈•─
“ኖኅ ግን በእግዚአብሔር ፊት ሞገስን አገኘ።”
ዘፍጥረት 6፥8
ወደ ቻናሉ ለመ🀄️ላ🀄️ል፦ @Holy_scriptures
የዕለቱ ጥቅስ
──•◈•─────•◈•─
“ኖኅ ግን በእግዚአብሔር ፊት ሞገስን አገኘ።”
ዘፍጥረት 6፥8
ወደ ቻናሉ ለመ🀄️ላ🀄️ል፦ @Holy_scriptures
🔥11👍4
Audio
#መጻሕፍትን_በድምጽ
👉ርዕስ፦ የካታኮምቡ ሰማዕት
🗣ትርጉም፦ በአማረ ማሞ
መካነ ኢየሱስ ሥነ ጽሑፍ ክፍል።
📻ክፍል-8
ይቀጥላል...
ወደ ቻናሉ ለመ🀄️ላ🀄️ል፦ @Holy_scriptures
👉ርዕስ፦ የካታኮምቡ ሰማዕት
🗣ትርጉም፦ በአማረ ማሞ
መካነ ኢየሱስ ሥነ ጽሑፍ ክፍል።
📻ክፍል-8
ይቀጥላል...
ወደ ቻናሉ ለመ🀄️ላ🀄️ል፦ @Holy_scriptures
ቅዱሳት መጻሕፍት
#መጻሕፍትን_እንመርምር የኢየሱስ ክርስቶስ ትንሣኤ የአካል ወይስ የመንፈስ? ክፍል-፬ "ለዘብተኛ አቋም" አላቸው በመባል የሚታወቁት ሰዱቃውያን በሙታን ትንሣኤ አያምኑም ነበር (ማቴዎስ 22÷23):: በአንጻሩ ደግሞ ፈሪሳውያን በሙታን ትንሣኤ ያምናሉ (ሐዋርያት ሥራ 23÷8)፡፡ ሰዱቃውያን ትንሣኤ ሙታን ላለመኖሩ እንደ ምክንያት ያቀረቡት ጒዳይ ስለማግባትና ስለመጋባት…
#መጻሕፍትን_እንመርምር
የኢየሱስ ክርስቶስ ትንሣኤ የአካል ወይስ የመንፈስ?
ክፍል-፭
2. የሐዋርያው ጳውሎስ አስተምህሮ
ሐዋርያው ጳውሎስ እጅግ ጥንታዊ ነው የሚባለውን የቤተ ክርስቲያን የእምነት መግለጫ ጠቅሶ በጻፈበት ክፍል ላይ፣ የክርስቶስን ሞት ከገለጸ በኋላ የሃይማኖት መግለጫው እንዲህ ያላል፣ “ቅዱሳት መጻሕፈት እንደሚሉት ክርስቶስ ስለ ኀጢአታችን ሞተ፤ ተቀበረ፤ በቅዱሳት መጻሕፍት እንደ ተጻፈውም በሦስተኛው ቀን ተነሣ” (1ቆሮንቶስ 15÷3-4)፡፡ ከዚህ ክፍል በግልጽ የምንማረው እውነት፣ ሞቶ የተቀበረው አካል ከሙታን እንደ ተነሣ ነው፡፡ ይህም የሞተው፣ የተቀበረውና ሞትን ድል አድርጎ የተነሣው አካል አንድ መሆኑን አመላካች ነው፡፡ በዚሁ ምዕራፍ ሐዋርያው የስንዴ ቅንጣትን በምሳሌነት በመጠቀም አራት ጊዜ የተዘራው የስንዴ ቅንጣት እንደ በቀለ ይገልጻል፣ “…ይዘራል ይነሣል ይዘራል ይነሣል ይዘራል ይነሣል ይዘራል…ይነሣል” (1ቆሮንቶስ 15÷42-44)። ልክ እንደዚሁ ሁሉ ሞቶ የተቀበረው የክርስቶስ አካል በትንሣኤ እንደ ተነሣ የሚያስተምር ነው፡፡
ክርስቶስ ዳግም ተመልሶ ሲመጣ፣ “ክቡር ሥጋውን እንዲመስል የተዋረደውን ሥጋችንን ይለውጣል” (ፊልጵስዩስ 3÷21) የሚለው የሐዋርያው አነጋገር የተዋረደው የእኛ ሥጋ ልክ እንደ እርሱ ሥጋ እንደሚለወጥ ሲገልጽ፣ እርሱ ራሱ “በተለወጠ ሥጋ” እንዳለ የሚያስተምር ነው፡፡ በዚህ ክፍል የቅዱሳኑንም ሆነ የክርስቶስን አካል ለማመልከት ጥቅም ላይ የዋለውና የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ ቅጆች “ሥጋ” ብለው የተረጐሙት “ሶማ” የሚለው የሐዲስ ኪዳን ግሪክ፣ ዘወትር የሚጨበጠውን የሚዳሰሰውን አካል የሚያመለክት ነው፡፡ የክርስቶስ ትንሣኤ በመንፈስ ቢሆን ኖሮ፣ ሐዋርያው “ሥጋ” ከሚለው ቃል ይልቅ መንፈስ የሚለውን ቃል ይጠቀም ነበር፡፡ የጻድቃን ዕጣ ፈንታቸው በትንሣኤ ሥጋ ከሙታን መነሣት ከሆነ፣ ክርስቶስም ከሙታን የተነሣው በትንሣኤ ሥጋ ነው ማለት ነው፡፡ ጻድቃን ከመሞት ወደ አለመሞት የመለወጣቸው ሂደት ቊሳዊ እንደ ሆነው ሁሉ፣ የክርስቶስም ትንሣኤ በቊሳዊ አካል እንደ ሆነ በንጽጽር የሚያሳይ ነው::
ሐዋርያው፣ “ኢየሱስን ከሙታን ያስነሣው የእርሱ መንፈስ በእናንተ የሚኖር ከሆነ፣ ክርስቶስን ከሙታን ያስነሣው፣ በውስጣችሁ በሚኖረው በመንፈሱ ሟች ለሆነው ሰውነታችሁ ሕይወትን ይሰጣል” (ሮሜ 8÷11) በዚህ ክፍል ሐዋርያው በክርስቶስ አካል ላይ መታደስ እንደ ተካሄደ እንጂ፣ አካሉ በመቃብር እንዳልቀረ ታሳቢ ያደረገ ንግግር ነው::
ሐዋርያው ጳውሎስ በቈላስይስ 2፥9፣ “የመለኮት ሙላት ሁሉ በአካል በእርሱ ይኖራልና" ሲል “ይኖራል” (ካቶይኬ) የሚለውን ቃል የተጠቀመው የአሁን ጊዜ ግሥ ነው፤ ይህም አምላክ የመሆን ባሕርዩ (“የመለኮት ሙላት” “ቴዎቴቶስ” ) በሰውነቱ/በሥጋው (“ሶማቲኮስ”) የሚኖረው፣ ሐዋርያው ይህን መልእክት እስከሚጽፍበት ጊዜ ድረስ ኢየሱስ አካል/ሥጋ እንዳለው የሚያሳይ ነው፡፡
ሉቃስ፣ በሐዋርያት ሥራ መጽሐፉ ላይ ባቀረበው ዘገባ ጳውሎስ፣ የኢየሱስ ክርስቶስ ሥጋ እንደ ንጉሥ ዳዊት ሥጋ በመቃብር ውስጥ እንዳልበሰበሰ፣ ነገር ግን እግዚአብሔር የሞትን ጣር አጥፍቶ አንዳስነሣው ገልጾአል (ሐዋርያት ሥራ 13÷34-37)፡፡ በተጨማሪም ይህ የክርስቶስ ኢየሱስ የአካል ትንሣኤ የትንቢት ፍጻሜ እንደ ሆነ ተገልጾአል (መዝሙር 16÷10)። የክርስቶስ አካል ከንጉሥ ዳዊት አካል ጋር ተነጻጽሮ መቅረቡ እንዲሁም የንጉሥ ዳዊት መቃብር ዛሬም ድረስ እንዳለና የኢየሱስ መቃብር ግን ባዶ መሆኑ፣ የአካል ትንሣኤን አያመለክትም ብሎ ማሰብ እጅግ ሲበዛ አስቸጋሪ ነው፡፡
በአንደኛ ቆሮንቶስ ምዕራፍ ዐሥራ አምስት በዝርዝር የቀረበው መረጃ የኢየሱስ ክርስቶስ ትንሣኤ የአካል መሆኑን በግልጽ የሚያስተምር ነው:: ዋና የሚባሉትን ነጥቦች እንመልከት
ይቀጥላል...
ምንጭ፦ ዶ/ር ተስፋዬ ሮበሌ፤ በሥጋ ትንሣኤ አምናለሁ! የአስተምህሮተ ትንሣኤ መጽሐፍ ቅዱሳዊ፣ ታሪካዊና ሥነ አመክንዮአዊ ትንታኔ፤ ከምእራፍ ሰባት የተወሰደ

❤7👍2
. ──•◈•─────•◈•─
የዕለቱ ጥቅስ
──•◈•─────•◈•─
“ኢየሱስም ከዚያ አልፎ በመቅረጫው ተቀምጦ የነበረ ማቴዎስ የሚባል አንድ ሰው አየና፦ ተከተለኝ አለው። ተነሥቶም ተከተለው።”
ማቴዎስ 9፥9

👍7
Audio
#መጻሕፍትን_በድምጽ
👉ርዕስ፦ የካታኮምቡ ሰማዕት
🗣ትርጉም፦ በአማረ ማሞ
መካነ ኢየሱስ ሥነ ጽሑፍ ክፍል።
📻ክፍል-9
ይቀጥላል...
ወደ ቻናሉ ለመ🀄️ላ🀄️ል፦ @Holy_scriptures
👉ርዕስ፦ የካታኮምቡ ሰማዕት
🗣ትርጉም፦ በአማረ ማሞ
መካነ ኢየሱስ ሥነ ጽሑፍ ክፍል።
📻ክፍል-9
ይቀጥላል...
ወደ ቻናሉ ለመ🀄️ላ🀄️ል፦ @Holy_scriptures
#የእግዚአብሔር_ቃል_ምን_ይላል?
ሮሜ 8
¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯
¹ እንግዲህ በክርስቶስ ኢየሱስ ላሉት አሁን ኵነኔ የለባቸውም።
² በክርስቶስ ኢየሱስ ያለው የሕይወት መንፈስ ሕግ ከኃጢአትና ከሞት ሕግ አርነት አውጥቶኛልና።
³-⁴ ከሥጋ የተነሣ ስለ ደከመ ለሕግ ያልተቻለውን፥ እግዚአብሔር የገዛ ልጁን በኃጢአተኛ ሥጋ ምሳሌ በኃጢአትም ምክንያት ልኮ አድርጎአልና፤ እንደ መንፈስ ፈቃድ እንጂ እንደ ሥጋ ፈቃድ በማንመላለስ በእኛ የሕግ ትእዛዝ ይፈጸም ዘንድ ኃጢአትን በሥጋ ኰነነ።
⁵ እንደ ሥጋ ፈቃድ የሚኖሩ የሥጋን ነገር ያስባሉና፥ እንደ መንፈስ ፈቃድ የሚኖሩ ግን የመንፈስን ነገር ያስባሉ።
⁶ ስለ ሥጋ ማሰብ ሞት ነውና፥ ስለ መንፈስ ማሰብ ግን ሕይወትና ሰላም ነው።
⁷ ስለ ሥጋ ማሰብ በእግዚአብሔር ዘንድ ጥል ነውና፤ ለእግዚአብሔር ሕግ አይገዛምና፥ መገዛትም ተስኖታል፤
⁸ በሥጋ ያሉትም እግዚአብሔርን ደስ ሊያሰኙት አይችሉም።
⁹ እናንተ ግን የእግዚአብሔር መንፈስ በእናንተ ዘንድ ቢኖር፥ በመንፈስ እንጂ በሥጋ አይደላችሁም። የክርስቶስ መንፈስ የሌለው ከሆነ ግን ይኸው የእርሱ ወገን አይደለም።
¹⁰ ክርስቶስ በእናንተ ውስጥ ቢሆን ሰውነታችሁ በኃጢአት ምክንያት የሞተ ነው፥ መንፈሳችሁ ግን በጽድቅ ምክንያት ሕያው ነው።
¹¹ ነገር ግን ኢየሱስን ከሙታን ያስነሣው የእርሱ መንፈስ በእናንተ ዘንድ ቢኖር፥ ክርስቶስ ኢየሱስን ከሙታን ያስነሣው እርሱ በእናንተ በሚኖረው በመንፈሱ፥ ለሚሞተው ሰውነታችሁ ደግሞ ሕይወትን ይሰጠዋል።

❤3👍1
. ──•◈•─────•◈•─
የዕለቱ ጥቅስ
──•◈•─────•◈•─
“ነገር ግን፦ ቃሌን ስሙ፥ እኔም አምላክ እሆናችኋለሁ እናንተም ሕዝብ ትሆኑኛላችሁ፤ መልካምም ይሆንላችሁ ዘንድ ባዘዝኋችሁ መንገድ ሁሉ ሂዱ ብዬ በዚህ ነገር አዘዝኋቸው።”
ኤርምያስ 7፥23

🔥4👍1
የካታኮቡ ሰማእታት ክፍል አሥር catacombs part 10
ታላቁ ተስፋ - Great Hope - Official
#መጻሕፍትን_በድምጽ
👉ርዕስ፦ የካታኮምቡ ሰማዕት
🗣ትርጉም፦ በአማረ ማሞ
መካነ ኢየሱስ ሥነ ጽሑፍ ክፍል።
📻ክፍል-10
ይቀጥላል...
ወደ ቻናሉ ለመ🀄️ላ🀄️ል፦ @Holy_scriptures
👉ርዕስ፦ የካታኮምቡ ሰማዕት
🗣ትርጉም፦ በአማረ ማሞ
መካነ ኢየሱስ ሥነ ጽሑፍ ክፍል።
📻ክፍል-10
ይቀጥላል...
ወደ ቻናሉ ለመ🀄️ላ🀄️ል፦ @Holy_scriptures
👍2🔥2
#ከተማ_ወይም_ቦታ_በቅዱሳት_መጻሕፍት
#ደማስቆ
ሁለት ሺህ ዓመት ከክርስቶስ ልደት በፊት የተሠራ እስከ ዛሬ ድረስ የሶርያ መናገሻ ከተማ የሆነ። «ቅን» የተባለው ጥንታዊ መንገድ እስከ አሁን ይገኝበታል፤ ሐ.ሥ. 9፥11። በአቅራቢያው አባናና ፋርፋ የተባሉ ሁለት ወንዞች ይፈሳሉ፤ 2ነገ. 5፥12። ከምሥራቅ ወደ ታላቁ ባሕር፥ ከሰሜንም ወደ ግብጽ የሚሄዱ መንገዶች የሚገናኙበት ስለሆነ፥ ብዙ ነጋዴዎች የሚመላለሱበት መናኸሪያ ከተማ ነበር።
አብርሃም በአቅራቢያው ይኖር ነበር፣ ዘፍ. 14፥15። እነዳዊት የደማስቆን ሰዎች ድል ነሡ፤ 2ሳሙ. 8፥5:6። በእስራኤል ታሪክ ውስጥ ስማቸው ተጽፎ የምናገኛቸው የሶርያ ገዥዎች የሚከተሉት ናቸው ፦
👉ሬዞን (1ነገ. 11፥23-25)፥
👉ወልደ አዴር (1ነገ. 15፥18)፥
👉አዛሄል (2ነገ. 13፥22)፥
👉ወልደ አዴር 2ኛ (2ነገ. 13፥24)፥
👉ረአሶን (2ነገ. 16፥5፤ ኢሳ. 7፥1)።
ጳውሎስ ወደ ደማስቆ ሲሄድ ሳለ ክርስቶስ ተገለጠለት፤ ወንጌልን ማስተማር በደማስቆ ጀመረ፤ ሐ.ሥ. 9። በ628 ዓ.ም. የእስልምና ሃይማኖት ተከታዮች ከተማውን ማረኩና የእስልምና ትምህርት ማስፋፊያ አደረጉት።
ምንጭ፦ የመጽሐፍ ቅዱስ መዝገበ ቃላት፤ ገጽ 227-228

❤5👍1
. ──•◈•─────•◈•─
የዕለቱ ጥቅስ
──•◈•─────•◈•─
“ድሆችን እናስብ ዘንድ ብቻ ለመኑን፥ ይህንም ደግሞ ላደርግ ተጋሁ።”
ገላትያ 2፥10

👍2❤1
Audio
#መጻሕፍትን_በድምጽ
👉ርዕስ፦ የካታኮምቡ ሰማዕት
🗣ትርጉም፦ በአማረ ማሞ
መካነ ኢየሱስ ሥነ ጽሑፍ ክፍል።
📻ክፍል-11
ይቀጥላል...
ወደ ቻናሉ ለመ🀄️ላ🀄️ል፦ @Holy_scriptures
👉ርዕስ፦ የካታኮምቡ ሰማዕት
🗣ትርጉም፦ በአማረ ማሞ
መካነ ኢየሱስ ሥነ ጽሑፍ ክፍል።
📻ክፍል-11
ይቀጥላል...
ወደ ቻናሉ ለመ🀄️ላ🀄️ል፦ @Holy_scriptures
❤3👍3
ንቃ.pdf
6.1 MB
ርዕስ፦ ንቃ
ከአስመሳይ ሃይማኖተኞች ተጠንቀቁ
2ኛ ጴጥሮስ፣ 2ኛ እና 3ኛ ዮሐንስና ይሁዳ መልእክቶች
ጸሐፊ፦ ዋረን ደብልዩ ዌርዝቢ
ትርጉም፦ መስፍን ታዬ
ወደ ቻናሉ ለመ🀄️ላ🀄️ል፦ @Holy_scriptures
ከአስመሳይ ሃይማኖተኞች ተጠንቀቁ
2ኛ ጴጥሮስ፣ 2ኛ እና 3ኛ ዮሐንስና ይሁዳ መልእክቶች
ጸሐፊ፦ ዋረን ደብልዩ ዌርዝቢ
ትርጉም፦ መስፍን ታዬ
ወደ ቻናሉ ለመ🀄️ላ🀄️ል፦ @Holy_scriptures
❤10👏1🙏1
. ──•◈•─────•◈•─
የዕለቱ ጥቅስ
──•◈•─────•◈•─
“የእስራኤል ቅዱስ፥ ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላልና፦ በመመለስና በማረፍ ትድናላችሁ፤ በጸጥታና በመታመን ኃይል ይሆንላችኋል፤ እናንተም እንቢ አላችሁ፥”
ኢሳይያስ 30፥15

❤7👍2🙏2
የጸጋ ስጦታዎች ውጤታማ አሠራር እንዴት ሊሆን ይገባል?
ክፍል-1
በመርዕድ ለማ
በዚህ ክፍል የጸጋ ስጦታዎች አሠራር እንዴት እንደ ሆነ እናያለን። ጽሑፉ፦ መንፈሳዊ ልምምዶች፣ ሚዛናዊነት ወይስ አክራሪነት?፣ ጌታ ወይስ ስጦታው? በሚሉ ሦስት ዐበይት ክፍሎች ቀርቧል። በጽሑፉ ማጠቃለያም ፍቅር ከጸጋ ስጦታዎች ጋር ያለውን ትስስርና ተዛምዶ እንመለከታለን።
መንፈሳዊ ልምምዶች
መንፈሳዊ ልምምዶችን በሁለት መልኩ ማየት እንችላለን። የመጀመሪያው፣ ልምምዶችን ማክረር ነው። መንፈሳዊ ልምምድ በራሱ እራሱን የቻለ አገልግሎት ወይም ውጤት አይደለም። የአገልግሎት መድረኮች የተለያዩ መንፈሳዊ ልምምዶች ጎልተው ይታዩባቸዋል። ማሸብሸብ፣ እጅን ዘርግቶ መጸለይ፣ ዝግ ብሎ መናገር፣ ጮኾ መናገር፣ ወዘተ። እነኚህን የመሳሰሉ ልምምዶች ሊኖሩ ይችላሉ። ቁም ነገሩና ዋነኛው ጉዳይ “በሰዎች ሕይወት ውስጥ ምን ሆነ? ተፈወሱ? በመንፈስ ቅዱስ ተሞሉ? ሕይወታቸው ተለወጠ? በምናስተናግደው ሕዝብ ሕይወት ውስጥ ምንድነው የሚታየው? ለውጡ፣ ፍሬው እንዴት ነው?” የሚለው ነው። አለበለዚያ የልምምድ አገልጋዮች ብቻ ሆነን እንቀራለን። የብዙዎች አገልግሎት ውጤት አልባ የሚሆነው የሰዎችን ልምምድ ስለሚኮርጁ ነው። እግዚአብሔር እያንዳንዳችንን እንዳለን ሆነን እንድናመልከውና እንድናገለግለው ይፈልጋል። እኛው በእኛነታችን ሆነን ብናገለግለው ለሰዎች ውብና ማራኪ እንሆናለን። ምክንያቱም እግዚአብሔር እኔን አንተን ወይም አንቺን የመሰለ ሌላ ሰው አልፈጠረምና።
ቀጥሎ፣ የልምምድ ተቃዋሚዎች ጉዳይ ነው። እነኚህ በጣም ወግ አጥባቂ ስለሆኑ አንድ ጊዜ የጨበጡትን ነገር እድሜ ዘመናቸውን መልቀቅ አይፈልጉም። ለልምምዱማ እነርሱም የራሳቸው ልምምድ አላቸው። ዳሩ ግን ካወቅሁት ሌላ ነገር እንዴት? ለምን? የሚል ግትርነት ያስቸግራቸዋል። መሠረታዊ የሆነው የእግዚአብሔር ቃል አይለወጥ እንጂ አሠራሮችና ልምምዶችን ወጥ ይሁኑ አንበል። የጌታ ኢየሱስን የፈውስ አገልግሎት ስንመለከት እጁን ጭኖ ፈውሶአል፤ በቃል ብቻ ፈውሶአል፤ የዕውሩን ዓይን ጭቃ በመቀባት ፈውሶአል። የእግዚአብሔር ኃይል ትናንት በሠራበት መንገድ ብቻ አልነበረም በሚቀጥለው ቀን ሲሠራ የታየው። ሐዋርያው ጳውሎስም እጁን በመጫን ፈውሶአል፤ በለበሰው ጨርቅ አማካይነት ፈውሶአል። እነ ጴጥሮስ ጥላቸው እንኳ ሳይቀር ፈውሶአል። በብሉይ ኪዳን ኤልሳዕ በሞተው በሱነማዪቱ ልጅ ላይ ተዘርግቶበት ወደ ሕይወት መልሶታል። እስቲ በተለያዩ ጊዜአት እናንተም የተለማመዳችሁትን ልምምድ አስታውሱ። በዘመናችን እጅ በመጫን ሌሎች የመውደቃቸው ነገር አጠያያቂ ሆኗል። ምናልባት በኛም አገር የመንፈስ ቅዱስ መነቃቃት ሲጀምርና ለመንፈስ ቅዱስ ሙላት ስንጸልይላቸው፣ ከመንቀጥቀጥ፣ ከመጮኽም አልፈው የወደቁ ብዙዎች ናቸው። መውደቁ ብቻውን አገልግሎት መሆን አይችልም። ዳሩ ግን መንፈስ ቅዱስ በተለየ መንገድ ሲመጣ ልንወድቅ እንችላለን። የእጅ መጫን መነሻ አሳባችንን እንፈትሸው። ለመንፈሳዊ በረከት፣ ለመንፈስ ቅዱስ ሙላት፣ ለፈውስ ወይስ ሰዎችን ለመጣል? የእጅ መጫን ዓላማችን ትክክለኛ ከሆነ ምናለ ይውደቁ። እኛንም የመንፈስ ቅዱስ ኃይል ከጣለን እንውደቅ። በነጆን ዌስሊና ጆናታን ኤድዋርድስ አገልግሎት ብዙ ሰዎች ራሳቸውን መቆጣጠር አቅቷቸው ይወድቁ ነበር። ነገር ግን አሁንም ደግሜ እላለሁ፣ መውደቅ እራሱ ብቻውን አገልግሎት አይደለም። ስሚዝ ዊግልስወርዝ የሚባል ታላቅ የእምነት ሰው የታመሙ ሰዎችን የታመሙበትን ሥፍራ በቦክስ በመምታት ፈውሶአል። እሱ ይህን ስላደረገ እኛም እንድርግ ብንል ያለ ጥርጥር በወንጀል ተከሰን ፍርድ ቤት ልንቀርብ እንችላለን። ስለዚህ መንፈስ ቅዱስን እናድምጠው፤ አገልግሎታችንም ይሠምራል።
ሚዛናዊነት ወይስ አክራሪነት?
ሐዋርያው ጳውሎስ በ1ኛ ተሰሎንቄ 5፡19-22 ባለው ክፍል ሲናገር “መንፈስን አታጥፉ፤ ትንቢትን አትናቁ፤ ሁሉን ፈትኑ መልካሙንም ያዙ፤ ከማናቸውም ዓይነት ክፉ ነገር ራቁ” ይላል። በዚህ ክፍል ለሚዛናዊነት የሚረዱን አምስት ሃሳቦችን እናያለን።
1. መንፈስን አታጥፉ፦
በብሉይ ኪዳን ለካህናት ከተሰጣቸው የአገልግሎት ድርሻ አንዱ ዘወትር በመሠዊያ ላይ እሳት እንዲነድ ማድረግ፣ እንዳይጠፋ መጠበቅ ነበር። መንፈስ ቅዱስ በእሳት ይመሰላል። ይህ እሳት የሆነው የእግዚአብሔር መንፈስ ከቤተክርስቲያናችንና ከግል ሕይወታችን ከጠፋ አገልግሎታችን ሁሉ ይጠፋል። ስለዚህ ዘወትር በመንፈስ ቅዱስ ጋር እንሥራ፤ በመንፈስ ቅዱስ እንመራ። በተለያዩ ችግሮች ምክንያት መንፈሱን አናዳፍነው። ይህም ሐዋርያው ጳውሎስ ጢሞቴዎስን እንዳሳሰበው ማለት ነው። “ስለዚህ ምክንያት፣ እሳት እንደሚያቀጣጥል ሰው፣ እጆቼን በመጫኔ በአንተ ላይ ያለውን የእግዚአብሔርን ስጦታ እንድታነሳሳ አሳስብሃለሁ።” (2ኛ ጢሞቴዎስ 1፡6)
2. ትንቢትን አትናቁ፦
የትንቢት አገልግሎት በሐዲስ ኪዳን ቤተክርስቲያን በጣም የታወቀ አገልግሎት ነው። ደግሞም ሐዋርያው ጳውሎስ ይህን ስጦታ ለማግኘት ፈልጉ ይላል። አንዳንድ ጊዜ በስመ ትንቢት ቤተክርስቲያን ችግር ሊገጥማት ይችላል። እውነተኞች ትንቢት ተናጋሪዎች እንደ መኖራቸው ሁሉ ሐሰተኞች ነቢያትም ይኖራሉ። ታዲያ ባንዳንድ በተሳሳተ ትንቢት ሳቢያ በሚመጣ ችግር “ከዛሬ ጀምሮ ትንቢት የሚባል ነገር አያስፈልገንም” በማለት ቤተክርስቲያን ይህንንም ጸጋ እንዳትጥለው ጥንቃቄ ያስፈልጋል።
ይቀጥላል...
ምንጭ:- shalomgospel.com

👍7❤4🙏1
. ──•◈•─────•◈•─
የዕለቱ ጥቅስ
──•◈•─────•◈•─
“የወንጌልም እውነት በእናንተ ዘንድ ጸንቶ እንዲኖር ለአንድ ሰዓት እንኳ ለቅቀን አልተገዛንላቸውም።”
ገላትያ 2፥5

❤5
Audio
❤2👍1
. ──•◈•─────•◈•─
የዕለቱ ጥቅስ
──•◈•─────•◈•─
“ልቡ ጠቢብ፥ ኃይሉም ታላቅ ነው፤ ደፍሮትስ በደኅና የሄደ ማን ነው?”
ኢዮብ 9፥4

❤3👍2
#እራሳችንን_እንመርምር
በአንድ ክርስቲያን ዘንድ የአፍ እና የልብ መለያየትን የመሰለ መጥፎ ነገር የለም። ሁለቱም በአንድነት ሲያብሩ ማየት ትልቅ ነገር ነው። ሁለቱም በአንድነት ቆመው በእግዚአብሔር ዓይን እርሱ ደስ ሲያሰኙ ማየት ደግሞ የስኬት ስኬት ነው። ለመሆኑ ወደዚህ ስኬት ደርሰናል?
“አቤቱ፥ ረድኤቴ መድኃኒቴም፥ የአፌ ቃልና የልቤ አሳብ በፊትህ ያማረ ይሁን።”
መዝሙር 19፥14

👍6🔥2
. ──•◈•─────•◈•─
የዕለቱ ጥቅስ
──•◈•─────•◈•─
“ልጄ ሆይ፥ ልብህ ጠቢብ ቢሆን ልቤ ደግሞ ደስ ይለዋል፤”
ምሳሌ 23፥15
ወደ ቻናሉ ለመ🀄️ላ🀄️ል፦ @Holy_scriptures
የዕለቱ ጥቅስ
──•◈•─────•◈•─
“ልጄ ሆይ፥ ልብህ ጠቢብ ቢሆን ልቤ ደግሞ ደስ ይለዋል፤”
ምሳሌ 23፥15
ወደ ቻናሉ ለመ🀄️ላ🀄️ል፦ @Holy_scriptures
❤6👍1