#እራሳችንን_እንመርምር
እምነታችንን እንዳናጠፋ እና በእምነት ነገር እንዳንጠፋ የሕሊናችንን ጤንነት እና ንጽሕና ምን ያህል ጠብቀነዋል?
“እምነትና በጎ ሕሊና ይኑርህ፥ አንዳንዶች ሕሊናን ጥለው፥ መርከብ አለ መሪ እንደሚጠፋ፥ በእምነት ነገር ጠፍተዋልና፤”
1ኛ ጢሞቴዎስ 1፥19
ወደ ቻናሉ ለመ🀄️ላ🀄️ል፦ @Holy_scriptures

👍2❤1
. ──•◈•─────•◈•─
የዕለቱ ጥቅስ
──•◈•─────•◈•─
“ከስምንት ቀን በኋላም ደቀ መዛሙርቱ ደግመው በውስጥ ነበሩ፥ ቶማስም ከእነርሱ ጋር ነበረ። ደጆች ተዘግተው ሳሉ ኢየሱስ መጣ፤ በመካከላቸውም ቆሞ፦ ሰላም ለእናንተ ይሁን አላቸው።”
ዮሐንስ 20፥26

❤6👍3
ዳግማዊ ትንሣኤ ምንድነው?
ከትንሣኤ ዕለት ቀጥሎ ያለው ሰንበት #ዳግማዊ_ትንሳኤ በመባል ይታወቃል። ይህ እለት በዚህ ስም ሊጠራ የቻለበት ምክንያት ጌታችን አምላካችንና መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በዋናው የትንሣኤ ቀን በእለተ ፋሲካ ለቅዱሳን ሐዋርያት በዝግ በር ገብቶ በመካከላቸው ተገኝቶ «ሰላም ለሁላችሁ ይሁን» ብሎ ትንሣኤውን ሲገልጽላቸው ሐዋርያው ቶማስ አልተገኘም ነበር፡፡እናም በኋላ ከሔደበት ሲመጣ ወንድሞቹ ጌታችን መነሣቱን እንደተገለጸላቸው በደስታ ሲነግሩት ቅር ተሰኝቶ «በኋላ እናንተ ዓየን ብላችሁ ልትመሰክሩ፣ ልታስተምሩ፣ እኔ ግን 'ሰምቼአለሁ' ብዬ ልመሰክር፣ ላስተምር? አይሆንም እኔም ካላየሁ አላምንም» በማለቱ የሰውን ሁሉ፤ ይልቁንም የመረጣቸው ወዳጆቹን የልብ ሐሳብ ምክንያቱን ለይቶ የሚያውቀው፣ ቸርነቱ ወሰን የሌለው የባሕርይ አምላክ መድኃኒዓለም ክርስቶስ ልክ እንደመጀመሪያው ትንሣኤ ዕለት ሐዋርያት በአንድነት በተዘጋ ቤት እንዳሉ በሩን ሳይከፍት ገብቶ «ሰላም ለሁላችን ይሁን» በማለት በመካከላቸው ቆመ፤ ቶማስንም «ያመንክ እንጂ ተጠራጣሪ አትሁን እነሆ የተቸነከሩ እጆቼንና እግሮቼን፣ የተወጋ ጐኔንም ናና እይ» ብሎ አሳየው፡፡ እርሱም ምልክቱን በማየቱ በመዳሰሱ ትንሣኤውንና አምላክነቱን እንደፍላጎቱ በመረዳቱ «ጌታዬ አምላኬ ብሎ መስክሮ» አመነ፡፡
👉እንግዲህ ይህ የትንሣኤው ምስጢር ለሁለተኛ ጊዜ ለሐዋርያት የተገለጠበት ዕለት ስለሆነ «ዳግም ትንሣኤ» ተብሎ ሰንበቱ ይጠራበታል፤ ይከበርበታል፡፡ ዮሐ. 20፥24-30

👍10🤔1
የካታኮቦ ሰማእታት ክፍል 1Catacombs part 1
ታላቁ ተስፋ - Great Hope - Official
#መጻሕፍትን_በድምጽ
👉ርዕስ፦ የካታኮምቡ ሰማዕት
🗣ትርጉም፦ በአማረ ማሞ
መካነ ኢየሱስ ሥነ ጽሑፍ ክፍል።
📻ክፍል-1
ይቀጥላል...
ወደ ቻናሉ ለመ🀄️ላ🀄️ል፦ @Holy_scriptures
👉ርዕስ፦ የካታኮምቡ ሰማዕት
🗣ትርጉም፦ በአማረ ማሞ
መካነ ኢየሱስ ሥነ ጽሑፍ ክፍል።
📻ክፍል-1
ይቀጥላል...
ወደ ቻናሉ ለመ🀄️ላ🀄️ል፦ @Holy_scriptures
👍6❤2
. ──•◈•─────•◈•─
የዕለቱ ጥቅስ
──•◈•─────•◈•─
“ወደ ሰፊ ስፍራም አወጣኝ፤ ወድዶኛልና አዳነኝ።”
2ኛ ሳሙኤል 22፥20
ወደ ቻናሉ ለመ🀄️ላ🀄️ል፦ @Holy_scriptures
የዕለቱ ጥቅስ
──•◈•─────•◈•─
“ወደ ሰፊ ስፍራም አወጣኝ፤ ወድዶኛልና አዳነኝ።”
2ኛ ሳሙኤል 22፥20
ወደ ቻናሉ ለመ🀄️ላ🀄️ል፦ @Holy_scriptures
👍6❤1
Audio
#መጻሕፍትን_በድምጽ
👉ርዕስ፦ የካታኮምቡ ሰማዕት
🗣ትርጉም፦ በአማረ ማሞ
መካነ ኢየሱስ ሥነ ጽሑፍ ክፍል።
📻ክፍል-2
ይቀጥላል...
ወደ ቻናሉ ለመ🀄️ላ🀄️ል፦ @Holy_scriptures
👉ርዕስ፦ የካታኮምቡ ሰማዕት
🗣ትርጉም፦ በአማረ ማሞ
መካነ ኢየሱስ ሥነ ጽሑፍ ክፍል።
📻ክፍል-2
ይቀጥላል...
ወደ ቻናሉ ለመ🀄️ላ🀄️ል፦ @Holy_scriptures
❤6🔥1
#መጻሕፍትን_እንመርምር
የኢየሱስ ክርስቶስ ትንሣኤ የአካል ወይስ የመንፈስ?
ክፍል-፫
(1) በሞተው ሰውና ከሙታን በተነሣው ሰው መካከል ልዩነት የለም፡፡
ከሞት የሚነሣው የሞተው ሰው ራሱ ነው (የሞተው አካል ከሞት የሚነሣው አካል አያቋርጤ ነው:: ለምሳሌ— ኢየሱስ ከትንሣኤውም በኋላ ራሱን፣ “እኔው ራሴው ነኝ” (ሉቃስ 24÷39) ብሏል። አስታውሴው፣ ጠባዩ፣ አካላዊ ቅርጹ (ለምሳሌ ከትንሣኤ በፊት በአካሉ ላይ የነበረው ጠባሳ/ዕትራት ከትንሣኤውም በኋላ አብሮት ነበር) ወዘተ አልተቀየረም፡፡
(2) ቅድመ ትንሣኤና ድኅረ ትንሣኤ ያለው አካል ቊሳዊ ይዘቱም ሆነ አያቋርጤነቱን በጠበቀ መልኩ ዕድሳት ይደረግለታል
(ለምሳሌ የሚከተሉትን ክፍሎች ይመለከቷል ሮሜ 8÷11፤ 1ቆሮንቶስ 15÷53፤ ፊልጵስዩስ 3÷20- 21)።
“አንተ ሞኝ የምትዘራው ካልሞተ ሕይወት አያገኝም፡፡ የምትዘራውም የስንዴ ወይም የሌላ ዐይነት ዘር ቅንጣት ብቻ እንጂ ወደ ፊት የምታገኘውን አካል አይደለም፡፡ እግዚአብሔር ግን እንደ ፈቀደ አካልን ይሰጠዋል፤ ለእያንዳንዱም የዘር ዐይነት የራሱን አካል ይሰጠዋል” (1ቆሮንቶስ 15÷36-38)፣
ሐዋርያው ጳውሎስ በዚህ ክፍል የስንዴን ቅንጣት በመውሰድ የሚያስተምረው ትምህርት፣ ቅድመ ትንሣኤና ድኅረ ትንሣኤ አካል ቊሳዊ አያቋርጤነት እንዳለው የተዘራውን ዐይነት ዘር ከተዘራው ዘር ላይ እንደሚበቅል ነው:: አንዱ በሌላው እንደሚተካ ወይም አንዱ በሌላው እንደሚቀየር ሳይሆን፣ ይኸው አካል በትንሣኤ ሂደት ውስጥ እንደሚታደስ ነው:: ቅድመ ትንሣኤ አካል ይበሰብሳል፣ ይሞታል፣ ክብር የሌለው እንዲሁም ፍጥረታዊ ሲሆን ድኅረ ትንሣኤ አካል ግን የማይበሰብስ፣ ክብርንና ኀይልን የተሞላ እንዲሁም መንፈሳዊ ነው (1ቆሮንቶስ 15÷42-44)፡፡
“በሥጋ ትንሣኤ አምናለሁ!”
ኢየሱስ ክርስቶስ ከሙታን የተነሣው በአካለ ሥጋ መሆኑን የሚየስተምሩትን የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍሎች በጥሙና እንመልከት:—
1. ትንሣኤ የሚለው ቃል ቊሳዊ የሆነ አካልን ብቻ የሚያመለክት ነው
የሐዲስ ኪዳንን የትንሣኤ ትምህርት በጠለለ መልኩ ለመረዳት አይሁዶች ስለ ሙታን ትንሣኤ ያላቸውን ትምህርት በትክክል ማወቅ ያስፈልጋል፡፡ ምክንያቱም ከሉቃስ በስተቀር ሁሉም የሐዲስ ኪዳን ጸሓፍያን አይሁዶች ስለሆኑ (ቈላስይስ 4÷11:14) እንዲሁም ሐዲስ ኪዳን ስለ ትንሣኤ ሙታን የሚያስተምረው ትምህርት፣ ከብሉያት አስተምህሮ ጋር ተያያዥነት ያለው ስለሆነ፡፡
ይቀጥላል...
ምንጭ፦ ዶ/ር ተስፋዬ ሮበሌ፤ በሥጋ ትንሣኤ አምናለሁ! የአስተምህሮተ ትንሣኤ መጽሐፍ ቅዱሳዊ፣ ታሪካዊና ሥነ አመክንዮአዊ ትንታኔ፤ ከምእራፍ ሰባት የተወሰደ

❤5👍3
. ──•◈•─────•◈•─
የዕለቱ ጥቅስ
──•◈•─────•◈•─
“ሞትን ለዘላለም ይውጣል፥ ጌታ እግዚአብሔርም ከፊት ሁሉ እንባን ያብሳል፥ የሕዝቡን ስድብ ከምድር ሁሉ ላይ ያስወግዳል፤ እግዚአብሔር ተናግሮአልና።”
ኢሳይያስ 25፥8

❤2👏1
Audio
#መጻሕፍትን_በድምጽ
👉ርዕስ፦ የካታኮምቡ ሰማዕት
🗣ትርጉም፦ በአማረ ማሞ
መካነ ኢየሱስ ሥነ ጽሑፍ ክፍል።
📻ክፍል-3
ይቀጥላል...
ወደ ቻናሉ ለመ🀄️ላ🀄️ል፦ @Holy_scriptures
👉ርዕስ፦ የካታኮምቡ ሰማዕት
🗣ትርጉም፦ በአማረ ማሞ
መካነ ኢየሱስ ሥነ ጽሑፍ ክፍል።
📻ክፍል-3
ይቀጥላል...
ወደ ቻናሉ ለመ🀄️ላ🀄️ል፦ @Holy_scriptures
🔥1
የካታኮንቡ ሰማዕት.pdf
30.5 MB
👍5❤1🔥1
. ──•◈•─────•◈•─
የዕለቱ ጥቅስ
──•◈•─────•◈•─
“የክርስቶስ ኢየሱስም የሆኑቱ ሥጋን ከክፉ መሻቱና ከምኞቱ ጋር ሰቀሉ።”
ገላትያ 5፥24
ወደ ቻናሉ ለመ🀄️ላ🀄️ል፦ @Holy_scriptures
የዕለቱ ጥቅስ
──•◈•─────•◈•─
“የክርስቶስ ኢየሱስም የሆኑቱ ሥጋን ከክፉ መሻቱና ከምኞቱ ጋር ሰቀሉ።”
ገላትያ 5፥24
ወደ ቻናሉ ለመ🀄️ላ🀄️ል፦ @Holy_scriptures
❤12👍1
የካታኮምቦ ሰማዕታት ክፍል 4 Catacombs part 4
ታላቁ ተስፋ - Great Hope - Official
#መጻሕፍትን_በድምጽ
👉ርዕስ፦ የካታኮምቡ ሰማዕት
🗣ትርጉም፦ በአማረ ማሞ
መካነ ኢየሱስ ሥነ ጽሑፍ ክፍል።
📻ክፍል-4
ይቀጥላል...
ወደ ቻናሉ ለመ🀄️ላ🀄️ል፦ @Holy_scriptures
👉ርዕስ፦ የካታኮምቡ ሰማዕት
🗣ትርጉም፦ በአማረ ማሞ
መካነ ኢየሱስ ሥነ ጽሑፍ ክፍል።
📻ክፍል-4
ይቀጥላል...
ወደ ቻናሉ ለመ🀄️ላ🀄️ል፦ @Holy_scriptures
❤2🥰2👍1
ቅዱሳት መጻሕፍት
የጥንት ቤተክርስቲያን ጉባዔዎች ክፍል-፫ የኬልቄዶን ጉባዔ 451 በ451 ዓ.ም የተካሄደው የኬልቄዶን ጉባኤ የቤተክርስቲያን አራተኛው ጉባኤ ሲሆን በክርስትና ታሪክ ውስጥ ትልቅ ቦታ ከሚሰጣቸው ጉባኤዎች አንዱ ተደርጎ ይወሰዳል። ነገረ ክርስቶሳዊ አስተምህሮ በመቅረጽ እና የጥንቷ ቤተክርስቲያንን ያከፋፈሉትን ስነ-መለኮታዊ አለመግባባቶችን ለመፍታት ማዕከላዊ ሚና ተጫውቷል። ታሪካዊ…
የጥንት ቤተክርስቲያን ጉባዔዎች
ክፍል-፬
ከኬልቄዶን ጉባኤ (451 ዓ.ም.) ከተካሄደ በኋላ፣ በርካታ ዋና ዋና የቤተክርስቲያን ጉባዔዎች ተካሂደዋል። ነገር ግን፣ እነዚህ ሁሉ ጉባኤዎች በሁሉም አብያተ ክርስቲያናት ዘንድ ተቀባይነት አላገኙም። ለዚህም ዋናው ምክንያት በተለይም ከኬልቄዶን በኋላ በተፈጠሩ ጥልቅ ሥነ-መለኮታዊ አለመግባባቶች እና ፖለቲካዊ ልዩነቶች የተነሳ ነው።
ከኬልቄዶን ጉባኤ በኋላ ያሉ ቁልፍ ክስተቶች፡-
1. የምስራቅ ኦርቶዶክስ አብያተ ክርስቲያናት ጋር በኬልቄዶን ጉባዔ ውሳኔ አለመስማማት
ይህ ጉባዔ በብዙ የምስራቅ አብያተ ክርስቲያናት ውድቅ ተደርጓል፣ በተለይም በግብፅ፣ በሶሪያ እና በአርሜኒያ። እነዚህ አብያተ ክርስቲያናት ከጊዜ በኋላ የምስራቅ ኦርቶዶክስ አብያተ ክርስቲያናት በመባል ይታወቃሉ። ይህም ጉልህ እና ዘላቂ የሆነ መከፋፈል አስከትሏል።
2. የኬልቄዶንያ እና የኬልቄዶንያ ያልሆኑ ካምፖች ምስረታ፡-
የኬልቄዶን ጉባዔ ውሳኔ በምዕራቡ ቤተ ክርስቲያን (ሮምን ጨምሮ) እና በባይዛንታይን (ምሥራቃዊ ኦርቶዶክስ) ቤተ ክርስቲያን ጸንቷል። ሆኖም፣ የኬልቄዶንያ ያልሆኑ አብያተ ክርስቲያናት ራሳቸውን ችለው ቀጥለዋል፣ እያንዳንዱም የየራሱን ወጎች፣ ተዋረዶች እና ሥነ-መለኮታዊ ማዕቀፎችን እያዳበረ ቀጥለዋል።
3. የኮፕቲክ ኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን መነሳት እና ሌሎች፦
የአሌክሳንደሪያ ኮፕቲክ(የግብፅ) ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን፣ የሶርያ ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን እና የአርመን ሐዋርያዊት ቤተ ክርስቲያን ኬልቄዶንን ያልተቀበሉት ዋና ዋና አብያተ ክርስቲያናት ናቸው። በአካባቢያቸውም ሀይማኖታዊ እና ሀገራዊ ተቋማት ሆኑ።
4. በምስራቅ-ምእራብ ቤተክርስቲያን ላይ ያመጣው ተጽእኖ፦
በኬልቄዶን የተጀመረው መከፋፈል በክርስትና ውስጥ የአስተምህሮ፣ የፖለቲካ እና የባህል መለያየት እንዲጨምር አስተዋጽኦ አድርጓል፣ ይህም ከጊዜ በኋላ በ1054 ዓ.ም በምስራቅ ኦርቶዶክስ እና በሮማ ካቶሊካዊነት መካከል በተከሰተው መለያየት ተጠናቀቀ።
ምንጭ፦ Chadwick, H. (1993). The early Church (Revised ed.). Penguin Books.
Pelikan, J. (1971). The Christian tradition: A history of the development of doctrine, Volume 1: The emergence of the Catholic tradition (100-600). University of Chicago Press.
Meyendorff, J. (1989). Imperial unity and Christian divisions: The Church 450–680 A.D. St. Vladimir's Seminary Press.

👍10❤4👏1😢1
. ──•◈•─────•◈•─
የዕለቱ ጥቅስ
──•◈•─────•◈•─
“የቀረውንም ነገር ሳልቆጥር፥ ዕለት ዕለት የሚከብድብኝ የአብያተ ክርስቲያናት ሁሉ አሳብ ነው።”
2ኛ ቆሮ 11፥28

👍7❤1
Audio
#መጻሕፍትን_በድምጽ
👉ርዕስ፦ የካታኮምቡ ሰማዕት
🗣ትርጉም፦ በአማረ ማሞ
መካነ ኢየሱስ ሥነ ጽሑፍ ክፍል።
📻ክፍል-5
ይቀጥላል...
ወደ ቻናሉ ለመ🀄️ላ🀄️ል፦ @Holy_scriptures
👉ርዕስ፦ የካታኮምቡ ሰማዕት
🗣ትርጉም፦ በአማረ ማሞ
መካነ ኢየሱስ ሥነ ጽሑፍ ክፍል።
📻ክፍል-5
ይቀጥላል...
ወደ ቻናሉ ለመ🀄️ላ🀄️ል፦ @Holy_scriptures
🥰3👍1
. ──•◈•─────•◈•─
የዕለቱ ጥቅስ
──•◈•─────•◈•─
“እግዚአብሔር ሁሉን ይምር ዘንድ ሁሉን በአለመታዘዝ ዘግቶታልና።”
ሮሜ 11፥32

📻ክፍል-6
ይቀጥላል...
ወደ ቻናሉ ለመ🀄️ላ🀄️ል፦ @Holy_scriptures
👉ርዕስ፦ የካታኮምቡ ሰማዕት
🗣ትርጉም፦ በአማረ ማሞ
መካነ ኢየሱስ ሥነ ጽሑፍ ክፍል።
📻ክፍል-6
ይቀጥላል...
ወደ ቻናሉ ለመ🀄️ላ🀄️ል፦ @Holy_scriptures
❤3
ቅዱሳት መጻሕፍት
#መጻሕፍትን_እንመርምር የኢየሱስ ክርስቶስ ትንሣኤ የአካል ወይስ የመንፈስ? ክፍል-፫ (1) በሞተው ሰውና ከሙታን በተነሣው ሰው መካከል ልዩነት የለም፡፡ ከሞት የሚነሣው የሞተው ሰው ራሱ ነው (የሞተው አካል ከሞት የሚነሣው አካል አያቋርጤ ነው:: ለምሳሌ— ኢየሱስ ከትንሣኤውም በኋላ ራሱን፣ “እኔው ራሴው ነኝ” (ሉቃስ 24÷39) ብሏል። አስታውሴው፣ ጠባዩ፣…
#መጻሕፍትን_እንመርምር
የኢየሱስ ክርስቶስ ትንሣኤ የአካል ወይስ የመንፈስ?
ክፍል-፬
"ለዘብተኛ አቋም" አላቸው በመባል የሚታወቁት ሰዱቃውያን በሙታን ትንሣኤ አያምኑም ነበር (ማቴዎስ 22÷23):: በአንጻሩ ደግሞ ፈሪሳውያን በሙታን ትንሣኤ ያምናሉ (ሐዋርያት ሥራ 23÷8)፡፡ ሰዱቃውያን ትንሣኤ ሙታን ላለመኖሩ እንደ ምክንያት ያቀረቡት ጒዳይ ስለማግባትና ስለመጋባት ነበር፤ ይህም ትንሣኤ ሙታን የአካል እንደ ሆነ ታሳቢ ያደረገ ንግግር መሆኑ ብቻ ሳይሆን ኢየሱስም የመለሰው መልስ ትንሣኤ ሙታን የአካል እንደ ሆነ ነገር ግን ከትንሣኤ በኋላ ማግባትና መጋባት እንደማይኖር የሚያስረዳ ነው (ማቴዎስ 22÷28)። ከግማሽ በላይ የሚሆኑት የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት የተጻፉት ቀድሞ ፈሪሳዊ በነበሩ ሰዎች ነው:: አይሁዶች በተለይ ደግሞ ፈሪሳውያን ሰው የተፈጠረው ከምድር ዐፈር እንደ ሆነ (ዘፍጥረት 2÷7)፣ ወደ ዐፈርም እንደሚመለስ (መክብብ 12÷7)፣ በትንሣኤም ቀን ወደ ዐፈርነት ከተለወጠው አካሉ በእግዚአብሔር ኪነ ጥበብ ሕያው ሆኖ ከሙታን እንደሚነሣ (ዘዳግም 32÷39፤ 1ሳሙኤል 2፥6፤ ኢዮብ 19÷25-27፤ መዝሙር 49÷14-15) ያምናሉ፡፡
የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት አስተምህሮ ንጉሥ ዳዊት የእግዚአብሔር ቅዱስ የሆነው ኢየሱስ መበስበስን እንማያይ ተንብዮ ነበር (መዝሙር 16÷10):: ጴጥሮስ የንጉሥ ዳዊትን ትንቢት በተመለከተ እንዲህ በሏል፣ "ይህንን አስቀድሞ በማየቱ እርሱ በሲኦል እንደማይቀርና ሥጋውም እንማይበሰብስ ስለ ክርስቶስ ትንሣኤ ተነገረ" (ሐዋርያት ሥራ 2÷31):: በዚህ ቦታ “ሥጋ” ተብሎ የተተረጐመው የግሪክ ቃል (ሳርክ) ሊበሰብስ እንደሚችል ነገር ግን በእግዚአብሔር ከሃሌ ኲሉነት በመስበስን ሳያይ እንደማይበሰብስ ሆነ ከሙታን እንደ ተነሣ ያስተምራል:: ሐዋርያው ጳውሎስም ይህን የዳዊት ትንቢት በመጥቀስ ኢየሱስ፣ “እንዳልበሰበሰና እግዚአብሔርም ከሙታን እንዳስነሣው ለማረጋገጥ ...ቅዱስህ መበስበስን እንዲያይ አትፈቅድም' ይላል” (ሐዋርያት ሥራ 13፥34:35)።
ኢየሱስ ሰዱቃውያን በሙታን ትንሣኤ ባለማመናቸው፣ “ቅዱሳት መጻሕፍትንና የእግዚአብሔርን ኀይል ስለማታውቁ ትስታላችሁ” (ማቴዎስ 23÷29) ሲል ተናግሯቸዋል: እንዲሁም ዘፀአት 3፥6:15 በመጥቀስ፣ “እኔ የአብርሃም አምላክ፣ የይስሐቅ አምላክ፣ የያዕቀብ አምላክ ነኝ፡፡ እግዚአብሔር የሕያዋን እንጂ የሙታን አምላክ አይደለም” (ማቴዎስ 23÷32) ሲል አስተምሯል፡፡
ነቢዩ ኢሳይያስ፣ “ነገር ግን ሙታን ሕያዋን ይሆናሉ፤ በድናቸውም ይነሣል፡፡ እናንት በዐፈር ውስጥ የምትኖሩ፣ ተነሡ፤ በደስታም ዘመሩ፡፡ ጠልህ እንደ ንጋት ጠል ነው፤ ምድር ሙታንን ትወልዳለች” (ኢሳይያስ 26÷19) የሚለው ትምህርቱ የሞተው አካል እንደሚነሣ ይህም የሙታን ትንሣኤ የአካል እንደ ሆነ የሚያስተምር ነው፡፡
ዳንኤል፣ “በምድር ዐፈር ውስጥ ካንቀላፉት ብዙዎች ይነቃሉ፤ አንዳንዶቹ ለዘላለም ሕይወት፣ ሌሎቹም ለውርደትና ለዘላለም ጒስቊልና ይነሣሉ” (ዳንኤል 12፥2) የሚለው ትንቢቱ ትንሣኤ ሙታን የአካል እንደ ሆነ የሚያስተምር ነው:: በተመሳሳይ መልኩ ኢየሱስ ትንሣኤ ሙታን ከሚያገኙ ሰዎች ግማሹ ወደ ዘላለም ሕይወት ግማሾቹ ደግሞ ወደ ዘላለም ሞት እንደሚሄዱ አስተምሮአል (ዮሐንስ 5÷28)፡፡
ማርያምና ማርታ ወንድማቸው አልዓዛር በትንሣኤ ቀን እንደሚነሣ ተስፋ እንደሚያደርጉ በተጨማሪ ኢየሱስ በትንሣኤ ቀን ብቻ ሳይሆን ዛሬም ሙታንን የማስነሣት ኀይል ከገለጸ በኋላ አልዓዛርን ከሙታን ማስነሣቱ ትንሣኤ ሙታን የአካል እንደ ሆነ በግልጽ የሚያስተምር ነው (ዮሐንስ 11÷38-44)፡፡
ከእነዚህም ሆኑ ከእነዚህ ጋር ተዛማጅነት ካላቸው የብሉይና የሐዲስ ኪዳን ምንባባት በግልጽ የምንረዳው እውነት፣ ብሉያትም ሆኑ ሐዲሳት ስለ ትንሣኤ የሚያስተምሩት ትምህርት ተደጋጋፊ እንዲሁም እርስ በእርሱ የሚጣጣም መሆኑን ነው፡፡ ይኸውም መጽሐፍ ቅዱስ ትንሣኤ የሚለውን ቃል የሚጠቀመው ቊሳዊ አካል ከሙታን መነሣቱን ለማመልከት ብቻ ነው:: ዕብራውያን በተለይ ፈሪሳውያን የጻድቃን የወደፊት ሁኔታ አስመልክቶ የተለያየ አመለካከት ቢኖራቸውም፣ ሁሉም ግን ትንሣኤን ቊሳዊ አካል በጊዜዩዊነትም ሆነ በቋሚነት ከመነሣት ጋር ብቻ ነበር የሚያያይዙት፡፡
ምንም እንኳ ኢየሱስ ክርስቶስ በፈሪሳውያን ግብዝነት ደስተኛ ባይሆንም፣ ሰዱቃውያን የሙታን ትንሣኤ ባለመቀበላቸው ቢነቅፋቸውም፣ ትንሣኤ በሚለው የቃል ፍቺ ላይ ግን ተመሳሳይ አቋም ነበራቸው (ማቴዎስ 22÷23-32)፡፡ ጳውሎስ ቀድሞውኑ ፈሪሳዊ ስለነበር ሥቃይ የደረሰብኝ በሙታን ትንሣኤ በማመኔ ነው ብሎ ነበር (ሐዋርያት ሥራ 23÷6-8)፡፡
በአጠቃላይ ትንሣኤ የሚለው ቃል ያለው ትርጒም የሞተ ሰው አካል በቋሚነትም ሆነ በጊዜያዊነት ሕይወት ማግኘት ማለት ነው፡፡

👍4
በቅዱሳት መጻሕፍት ውስጥ "የትንሣኤ ምዕራፍ" በመባል የሚታወቀው ምዕራፍ የቱ ነው?
Anonymous Quiz
36%
ሀ. ዮሐንስ ወንጌል፣ ምዕራፍ 20
24%
ለ. ሉቃስ ወንጌል፣ ምዕራፍ 24
33%
ሐ. 1 ቆሮንቶስ፣ ምዕራፍ 15
7%
መ. የዮሐንስ ራእይ፣ ምዕራፍ 20
🥰4👍2
. ──•◈•─────•◈•─
የዕለቱ ጥቅስ
──•◈•─────•◈•─
“ሕፃንነትና ጕብዝና ከንቱዎች ናቸውና ከልብህ ኀዘንን አርቅ፥ ከሰውነትህም ክፉን ነገር አስወግድ።”
መክብብ 11፥10

❤4👍1