ቅዱሳት መጻሕፍት
7.46K subscribers
1.35K photos
61 videos
332 files
799 links
በዚህ ቻናል

👉ቅዱሳት መጻሕፍት ይጠናሉ::
👉መጽሐፍ ቅዱሳዊ ትምህርቶች ይቀርባሉ::
👉 ለቅዱሳት መጽሐፍት ጥናት የሚያግዙ መጻሕፍት ይለቀቃሉ።

⭐️⭐️⭐️⭐️⭐️

@Holy_scriptures
Download Telegram
.       ──•◈•─────•◈•─
                          የዕለቱ ጥቅስ
        ──•◈•─────•◈•─
“በወንጌል እንደምሰብከው፥ ከሙታን የተነሣውን፥ ከዳዊት ዘርም የሆነውን ኢየሱስ ክርስቶስን አስብ፤”
2ኛ ጢሞቴዎስ 2፥8



ወደ ቻናሉ ለመ🀄️🀄️ል፦ @Holy_scriptures
9👍2
#መጻሕፍትን_እንመርምር

የኢየሱስ ክርስቶስ ትንሣኤ የአካል ወይስ የመንፈስ?


                        ክፍል-፩

            
                                           ከዶ/ር ተስፋዬ ሮበሌ

ይህ ዶ/ር ተስፋዬ ሮበሌ፣ “በሥጋ ትንሣኤ አምናለሁ! የአስተምህሮተ ትንሣኤ መጽሐፍ ቅዱሳዊ፣ ታሪካዊና ሥነ አመክንዮአዊ ትንታኔ” በሚል ርእስ ካዘጋጀው መጽሐፍ፣ ከምዕራፍ ሰባት በቀጥታ የተወሰደ ነው፡፡ በሙታን ትንሣኤ ላይ ሰፊ ማብራሪያ ከፈለጉ ይህን መጽሐፍ እንዲያነቡ እናበረታታለን፡፡

መናፍቃዊ የሆኑ ሃይማኖታዊ ድርጅቶች የኢየሱስ ክርስቶስን ትንሣኤ እናምናለን ይበሉ እንጂ፣ ትንሣኤው ግዘፋዊ/ቊሳዊ ሳይሆን በመንፈስ ነው የሚል አቋም አላቸው:: ከላይ ባየናቸው ምዕራፎች፣ መቃብሩ ባዶ ነው፣ ደቀ መዛሙርቱም የትንሣኤውን ጌታ በዐይነ ሥጋቸው አይተውታል ወዘተ በሚል ያቀርብናቸው እጅግ በርካታ ማስረጃዎች ትንሣኤው በመንፈስ ሳይሆን በአካል መሆኑን በግምት ውስጥ ያስገቡ ናቸው:: ይህ በሆነበት ሁኔታ፣ መናፍቃን በተለይ ደግሞ የይሖዋ ምስክሮች ቃለ እግዚአብሔር ብቻ ሳይሆን፣ ታሪክ ራሱ ርእሰ ጒዳዩን በግልጽና በስፋት የሚያስተምርበት ሁኔታ እያለ ትንሣኤው የመንፈስ ነው ማለታቸው ስሕተት ነው:: ከዚህ በመቀጠል ይህን ጒዳይ በስፋት ለመመርመር እንሞክራለን፡፡

“ኢየሱስ ክርስቶስ ትንሣኤ የአካል ወይስ የመንፈስ?" የሚለው ርእሰ ጒዳይ ለትንሣኤ ሙታን አስተምህሮ እጅግ መሠረታዊው ትምህርት ነው፡፡ ርእሰ ጒዳዩን በጥልቀት መመርመር ይቻለን ዘንድ፣ በቤተ ክርስቲያን ታሪክ ትንሣኤ ሙታንን አስመልክቶ የቀረቡትንና ሊቀርቡ የሚችሉትን አማራጭ ትንተናዎች ከተመለከትን በኋላ ትንሣኤው የአካል ነው ወይስ የመንፈስ የሚለውን ጒዳይ በስፋት እንመረምራለን:—

፩ አካለ ተንሥአት(Bodily Resuscitation)፦

ይህ ንድፈ ሐሳብ የኢየሱስ ሞት አካላዊ ሞት እንደ ሞተ፣ አካላዊ በሆነ ሁኔታም ከሙታን እንደ ተነሣ ያምናል፡፡ ከዚህም የተነሣ የኢየሱስ ክርስቶስ መቃብር ባዶ እንደ ሆነ ይቀበላል፡፡ የኢየሱስ ክርስቶስ የቅድመ ትንሣኤ ግብረ አካል አንዳችም ለውጥ ወይም ተሐድሶ ሳይካሄድበት እርሱ ራሱ ከሙታን ተነሥቶአል። ስለዚህ ትንሣኤው የቆመውን ሕይወት ቀጣይ ከማድረግ ውጪ አንዳችም ተሐድሶ አላመጣም የሚል አመለካከት ነው፡፡

፪ አካለ ትንሣኤ/ተሐድሶ(Bodily Transformation)

ይህ ንድፈ ሐሳብ የኢየሱስ ሞት አካላዊ ሞት እንደ ሞተና አካላዊ በሆነ ሁኔታ ከሙታን እንደ ተነሣ ያምናል፡፡ ከዚህም የተነሣ የኢየሱስ ክርስቶስ መቃብር ባዶ እንደ ሆነ ይቀበላል፡፡ የኢየሱስ ክርስቶስ የቅድመ ትንሣኤ ግብረ አካል ቊሳዊ ቢሆንም እንኳ፣ ተሐድሶ ስለተደረገበት፣ “የከበረ አካል” ሆኖ እርሱ ራሱ ከሙታን ተነሥቶአል፡፡ የትንሣኤው አካል፣ በቅድመ ትንሣኤ የነበረው አካል ይታይበት የነበረው ተፈጥሮአዊ ባሕርይ አይታይበትም (ለምሳሌ:— መድከም፣ ማርጀት፣ መሞት)።

፫ የመንፈስ ትንሣኤ (Spiritual Resurrection)

ይህ ንድፈ ሐሳብ ደግሞ፣ ኢየሱስ በእውነት እንደ ሞተ የሚቀበል ቢሆንም፣ ከትንሣኤው በኋላ ግን ኢየሱስ ክርስቶስ ዳግም ሰው አልሆነም፤ እንደ መላእክ መንፈሳዊ ፍጥረት ሆኖ ከሙታን ተነሥቶአል፡፡ ባልታወቀ ምክንያት መቃብሩ ባዶ ቢሆንም ኢየሱስ መንፈስ ሆኖ እንጂ፣ በአካለ ሆኖ እንጂ፣ በአካለ ሥጋ ከሙታን አልተነሣም:: ስለዚህ በሞተው ኢየሱስና በተነሣው ኢየሱስ መካከል የነፍስ ወይም የመንፈስ ወይም ደግሞ የአካል አንድነት የለም:: እንደዚህ አመለካከት በሞተው ኢየሱስና በተነሣው ኢየሱስ መካከል ያለው አንድነትም ሆነ ልዩነት በውል ኢየሱስ መካከል ያለው አይታወቅም፡፡ ይህ ዐይነቱ አመለካከት ያላቸው የይሖዋ ምስክሮችና “የመጠበቂያ ግንብ የመጽሐፍ ቅዱስና የትራክት ማኅበር” በመባል የሚታወቀው ሃይማኖታዊ ድርጅታቸው ነው፡፡ እንደ ይሖዋ ምስክሮች ትምህርት የሞተው ኢየሱስ ሰው ሲሆን፣ ከሙታን የተነሣው ደግሞ ሊቀ መላእክ ሚካኤል ነው፡፡ እንደ ድርጅቱ ትምህርት፣ በኢየሱስ ሰብአዊ ሕይወት ውስጥ ሊቀ መላእክ ሚካኤል ያልነበረ ሲሆን፣ ከትንሣኤው በኋላ ግን፣ ኢየሱስ ሊቀ መላእክ ሚካኤል ሆኖ ከሙታን ተነሥቶአል፡፡ እንዲያውም ድርጅቱ ኢየሱስ በምድር ላይ ለሰላሳ ሦስት ዓመት ከመንፈቅ ይሖዋ አምላክን በትጋት ስላገለገለ፣ ይሖዋ አምላክ ለሚካኤል ያለመሞትን (ኢመዋቲነትን) ሸልሞታል የሚል ትምህርት አለው:: ነገር ግን ኢየሱስ ሚካኤል ካልነበረ ወይም በኢየሱስ ውስጥ ሚካኤልነት ከሌለ፣ ኢየሱስ የሚባለው ግለሰብ ሰላሳ ሦስት ዓመት ከመንፈቅ አምላክን አገልግሎ ሳለ፣ በእርሱ ፈንታ ሚካኤል ኢመዋቲነትን በአምላክ እንዴት ሊሸለም ቻለ ለሚለው ጥያቄ ድርጅቱ የሚሰጠው አንዳችም ማብራሪያ የለም፡፡


ይቀጥላል...



ምንጭ፦ ዶ/ር ተስፋዬ ሮበሌ፤ በሥጋ ትንሣኤ አምናለሁ! የአስተምህሮተ ትንሣኤ መጽሐፍ ቅዱሳዊ፣ ታሪካዊና ሥነ አመክንዮአዊ ትንታኔ፤ ከምእራፍ ሰባት የተወሰደ


ወደ ቻናሉ ለመ🀄️🀄️ል፦ @Holy_scriptures
👍43
.       ──•◈•─────•◈•─
                          የዕለቱ ጥቅስ
        ──•◈•─────•◈•─
“አሁን ግን እናንተ በፊት ርቃችሁ የነበራችሁ በክርስቶስ ኢየሱስ ሆናችሁ በክርስቶስ ደም ቀርባችኋል።”
ኤፌሶን 2፥13



ወደ ቻናሉ ለመ🀄️🀄️ል፦ @Holy_scriptures
👍4
ቅድስና Holiness
BibleProject - Amharic / አማርኛ
👉ርዕስ፦ ቅድስና
በባይብል ፕሮጀክት፣ በአማርኛ ቋንቋ የተዘጋጀ


ወደ ቻናሉ ለመ🀄️🀄️ል፦ @Holy_scriptures
6
#መጻሕፍትን_እንመርምር

የኢየሱስ ክርስቶስ ትንሣኤ የአካል ወይስ የመንፈስ?


                        ክፍል-፪


፬ ምናባዊ ትንሣኤ ንድፈ ሐሳብ(Reductive Resurrection Theories)፦

ይህ ንድፈ ሐሳብ ኢየሱስ በትክክል እንደ ሞተና በትክክል ከሙታን እንደ ተነሣ አያምንም:: ስለዚህ መቃብሩ ባዶ ነበር ወይስ አልነበረም የሚለው ጒዳይ ከርእሰ ጒዳዩ ጋር ተያያዥነት የለውም ባይ ነው፡፡ በትክክል ያልሞተ ነገር ከሙታን ተነሥቶአል ማለት ትርጒም ስለሌለው፡፡ ኢየሱስ ከሙታን ተነሥቶአል የሚባለው ጒዳይ ሊተነተን የሚችለው የሚገባው ሥነ ልቡናዊ በሆነ መልኩ ነው። ይኸውም በደቀ መዛሙርቱ በነበራቸው ውስጣዊ የአእምሮ ሁኔታ ነው:: ኢየሱስ ታየን ወይም ተገለጠልን የሚለው የደቀ መዛሙርቱ ዐዋጅ፣ ራእያዊ አልያም ቅዥት (hallucination) ነው፡፡ እንደዚህ አመለካከት “ኢየሱስ ከሞት ተነሥቶአል” ማለት “የክርስቶስ መስቀል የማዳን ኀይል አለው” ወይም የእምነቴ ማዕከል ኢየሱስ ነው ከማለት ውጪ አንዳችም ትርጒም የለውም፡፡ ይህ ማለት ደግሞ ኢየሱስ ከሙታን ተነሥቶአል የሚለው ጒዳይ የሚብራራው መንፈሳዊ የሆነ ትርጒም ተሰጥቶት እንጂ፣ በቀጥታ ትርጒሙ አይደለም፡፡ በአጠቃላይ እንደዚህ አመለካከት የሞተ ሰው ከሙታን ተነሥቶአል የሚለውን ጒዳይ አይቀበልም፡፡

አካለ ትንሥአት ንድፈ ሐሳብ መጽሐፍ ቅዱሳዊ ያልሆነ አስተምህሮ ያለመሆኑ ብቻ ሳይሆን፣ ይህን አስተምህሮ የሚደግፍ አንዳችም ምሁር እንዲሁም ሃይማኖታዊ እንቅስቃሴ የለም:: የኢየሱስ ክርስቶስ ትንሣኤ፣ ይህ ንድፈ ሐሳብ እንደሚያስተምረው ትምህርት ከሆነ፣ ክርስቶስ ዳግም የመሞት ዕጣ ፈንታ አለው:: ነገር ግን ቃለ እግዚአብሔር የኢየሱስ የትንሣኤ አካል እንደማይሞት መጽሐፍ ቅዱስ በግልጽ ያስተምራል (1ቆሮንቶስ 15÷54-55፤ ዕብራውያን 2÷14)። አካለ ትንሥአት ንድፈ ሐሳብ ትምህርት ከሙታን ተነሥተው ዳግም እንደ ሞቱት ሰዎች (እንደ አልዓዛር፣ እንደ እያሪኦስ ልጅ፣ እንዲሁም በናይን ትኖር እንደ ነበረው መበለት) እንጂ፣ በከበረ ሁኔታ ለአንዴና ለዘላለም ሞትን ድል አድርጎ የተነሣውን ኢየሱስ ክርስቶስን የሚያመለከት አይደለም (ክርስቶስ ዳግም አይሞትምና)። በአጠቃላይ የአካል ትንሣኤ አስተምህሮና አካለ ትንሥአት ንድፈ ሐሳብ የትንሣኤው አካል ቊሳዊ ነው በሚለው ጒዳይ ላይ ተመሳሳይ አቋም ቢጋሩም፣ የትንሣኤ አካል እንደ ቅድመ ትንሣኤ አካል ሟች ነው የሚለውን የአካለ ትንሥአትን ንድፈ ሐሳብ አስተምህሮ፣ የአካል ትንሣኤ ትምህርት አይቀበልም፡፡

ትንሣኤው መንፈሳዊ ነው በሚለው አቋማቸው በስፋት የሚታወቁት የይሖዋ ምስክሮች ሲሆኑ፣ ድርጅታቸው አስተምህሮውን ለመደገፍ የሚያቀርባቸውን መጽሐፍ ቅዱሳዊ ማስረጃዎች
አንድ በአንድ እየነቀስን በማውጣት፣ የክርስቶስ ትንሣኤ የአካል ሳይሆን የመንፈስ ነው ወደሚለው ድምዳሜ ሊያደርሱ ይችላሉን የሚለውን ጒዳይ በስፋት ለመመርመር ሙከራ እናደርጋለን፡፡

ይህ ጹሑፍ የኢየሱስ ክርስቶስ ትንሣኤ የአካል ትንሣኤ ነው፣ የሚለው አስተምህሮ የክርስቶስ ቤተ ክርስቲያን ለሁለት ሺህ ዓመት ስታስተምረው የነበረና አሁንም በማስተማር ላይ የምትገኘው ትምህርት መሆኑን ቃለ እግዚአብሔርን፣ ታሪክንና ሥነ አመክንዮን በመጥቀስ ሰፊ ትንታኔ ለማቅረብ ጥረት ያደርጋል፡፡

የአካል ትንሣኤ አስተምህሮ የሚከተሉትን ሁለት መሠረተ ነጥቦች ማዕከል ያደረገ ትምህርት ነው፡፡


ይቀጥላል...



ምንጭ፦ ዶ/ር ተስፋዬ ሮበሌ፤ በሥጋ ትንሣኤ አምናለሁ! የአስተምህሮተ ትንሣኤ መጽሐፍ ቅዱሳዊ፣ ታሪካዊና ሥነ አመክንዮአዊ ትንታኔ፤ ከምእራፍ ሰባት የተወሰደ



ወደ ቻናሉ ለመ🀄️🀄️ል፦ @Holy_scriptures
👍9
.       ──•◈•─────•◈•─
                          የዕለቱ ጥቅስ
        ──•◈•─────•◈•─
“ነገር ግን ጌታን ኢየሱስ ክርስቶስን ልበሱት፤ ምኞቱንም እንዲፈጽም ለሥጋ አታስቡ።”
ሮሜ 13፥14



ወደ ቻናሉ ለመ🀄️🀄️ል፦ @Holy_scriptures
👏21👍1
#መጻሕፍትን_በድምጽ

👉ርዕስ፦ የካታኮምቡ ሰማዕት
🗣ትርጉም፦ በአማረ ማሞ
መካነ ኢየሱስ ሥነ ጽሑፍ ክፍል።

በቀጣይ የምንሰማው መጽሐፍ "የካታኮምቡ ሰማዕት" የሚለውን ነው።



ወደ ቻናሉ ለመ🀄️🀄️ል፦ @Holy_scriptures
6👍4🥰1
#እራሳችንን_እንመርምር


እምነታችንን እንዳናጠፋ እና በእምነት ነገር እንዳንጠፋ የሕሊናችንን ጤንነት እና ንጽሕና ምን ያህል ጠብቀነዋል?

“እምነትና በጎ ሕሊና ይኑርህ፥ አንዳንዶች ሕሊናን ጥለው፥ መርከብ አለ መሪ እንደሚጠፋ፥ በእምነት ነገር ጠፍተዋልና፤”
1ኛ ጢሞቴዎስ 1፥19




ወደ ቻናሉ ለመ🀄️🀄️ል፦ @Holy_scriptures
👍21
.       ──•◈•─────•◈•─
                          የዕለቱ ጥቅስ
        ──•◈•─────•◈•─
“ከስምንት ቀን በኋላም ደቀ መዛሙርቱ ደግመው በውስጥ ነበሩ፥ ቶማስም ከእነርሱ ጋር ነበረ። ደጆች ተዘግተው ሳሉ ኢየሱስ መጣ፤ በመካከላቸውም ቆሞ፦ ሰላም ለእናንተ ይሁን አላቸው።”
ዮሐንስ 20፥26



ወደ ቻናሉ ለመ🀄️🀄️ል፦ @Holy_scriptures
6👍3
ዳግማዊ ትንሣኤ ምንድነው?


ከትንሣኤ ዕለት ቀጥሎ ያለው ሰንበት #ዳግማዊ_ትንሳኤ በመባል ይታወቃል። ይህ እለት በዚህ ስም ሊጠራ የቻለበት ምክንያት ጌታችን አምላካችንና መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በዋናው የትንሣኤ ቀን በእለተ ፋሲካ ለቅዱሳን ሐዋርያት በዝግ በር ገብቶ በመካከላቸው ተገኝቶ «ሰላም ለሁላችሁ ይሁን» ብሎ ትንሣኤውን ሲገልጽላቸው ሐዋርያው ቶማስ አልተገኘም ነበር፡፡እናም በኋላ ከሔደበት ሲመጣ ወንድሞቹ ጌታችን መነሣቱን እንደተገለጸላቸው በደስታ ሲነግሩት ቅር ተሰኝቶ «በኋላ እናንተ ዓየን ብላችሁ ልትመሰክሩ፣ ልታስተምሩ፣ እኔ ግን 'ሰምቼአለሁ' ብዬ ልመሰክር፣ ላስተምር? አይሆንም እኔም ካላየሁ አላምንም» በማለቱ የሰውን ሁሉ፤ ይልቁንም የመረጣቸው ወዳጆቹን የልብ ሐሳብ ምክንያቱን ለይቶ የሚያውቀው፣ ቸርነቱ ወሰን የሌለው የባሕርይ አምላክ መድኃኒዓለም ክርስቶስ ልክ እንደመጀመሪያው ትንሣኤ ዕለት ሐዋርያት በአንድነት በተዘጋ ቤት እንዳሉ በሩን ሳይከፍት ገብቶ «ሰላም ለሁላችን ይሁን» በማለት በመካከላቸው ቆመ፤ ቶማስንም «ያመንክ እንጂ ተጠራጣሪ አትሁን እነሆ የተቸነከሩ እጆቼንና እግሮቼን፣ የተወጋ ጐኔንም ናና እይ» ብሎ አሳየው፡፡ እርሱም ምልክቱን በማየቱ በመዳሰሱ ትንሣኤውንና አምላክነቱን እንደፍላጎቱ በመረዳቱ «ጌታዬ አምላኬ ብሎ መስክሮ» አመነ፡፡

👉እንግዲህ ይህ የትንሣኤው ምስጢር ለሁለተኛ ጊዜ ለሐዋርያት የተገለጠበት ዕለት ስለሆነ «ዳግም ትንሣኤ» ተብሎ ሰንበቱ ይጠራበታል፤ ይከበርበታል፡፡ ዮሐ. 20፥24-30




ወደ ቻናሉ ለመ🀄️🀄️ል፦ @Holy_scriptures
👍10🤔1
የካታኮቦ ሰማእታት ክፍል 1Catacombs part 1
ታላቁ ተስፋ - Great Hope - Official
#መጻሕፍትን_በድምጽ

👉ርዕስ፦ የካታኮምቡ ሰማዕት
🗣ትርጉም፦ በአማረ ማሞ
መካነ ኢየሱስ ሥነ ጽሑፍ ክፍል።
📻ክፍል-1

ይቀጥላል...



ወደ ቻናሉ ለመ🀄️🀄️ል፦ @Holy_scriptures
👍62
.       ──•◈•─────•◈•─
                          የዕለቱ ጥቅስ
        ──•◈•─────•◈•─
“ወደ ሰፊ ስፍራም አወጣኝ፤ ወድዶኛልና አዳነኝ።”
2ኛ ሳሙኤል 22፥20



ወደ ቻናሉ ለመ🀄️🀄️ል፦ @Holy_scriptures
👍61
Audio
#መጻሕፍትን_በድምጽ

👉ርዕስ፦ የካታኮምቡ ሰማዕት
🗣ትርጉም፦ በአማረ ማሞ
መካነ ኢየሱስ ሥነ ጽሑፍ ክፍል።
📻ክፍል-2

ይቀጥላል...



ወደ ቻናሉ ለመ🀄️🀄️ል፦ @Holy_scriptures
6🔥1
#መጻሕፍትን_እንመርምር

የኢየሱስ ክርስቶስ ትንሣኤ የአካል ወይስ የመንፈስ?


                        ክፍል-፫


(1) በሞተው ሰውና ከሙታን በተነሣው ሰው መካከል ልዩነት የለም፡፡

ከሞት የሚነሣው የሞተው ሰው ራሱ ነው (የሞተው አካል ከሞት የሚነሣው አካል አያቋርጤ ነው:: ለምሳሌ— ኢየሱስ ከትንሣኤውም በኋላ ራሱን፣ “እኔው ራሴው ነኝ” (ሉቃስ 24÷39) ብሏል። አስታውሴው፣ ጠባዩ፣ አካላዊ ቅርጹ (ለምሳሌ ከትንሣኤ በፊት በአካሉ ላይ የነበረው ጠባሳ/ዕትራት ከትንሣኤውም በኋላ አብሮት ነበር) ወዘተ አልተቀየረም፡፡

(2) ቅድመ ትንሣኤና ድኅረ ትንሣኤ ያለው አካል ቊሳዊ ይዘቱም ሆነ አያቋርጤነቱን በጠበቀ መልኩ ዕድሳት ይደረግለታል

(ለምሳሌ የሚከተሉትን ክፍሎች ይመለከቷል ሮሜ 8÷11፤ 1ቆሮንቶስ 15÷53፤ ፊልጵስዩስ 3÷20- 21)።

“አንተ ሞኝ የምትዘራው ካልሞተ ሕይወት አያገኝም፡፡ የምትዘራውም የስንዴ ወይም የሌላ ዐይነት ዘር ቅንጣት ብቻ እንጂ ወደ ፊት የምታገኘውን አካል አይደለም፡፡ እግዚአብሔር ግን እንደ ፈቀደ አካልን ይሰጠዋል፤ ለእያንዳንዱም የዘር ዐይነት የራሱን አካል ይሰጠዋል” (1ቆሮንቶስ 15÷36-38)፣

ሐዋርያው ጳውሎስ በዚህ ክፍል የስንዴን ቅንጣት በመውሰድ የሚያስተምረው ትምህርት፣ ቅድመ ትንሣኤና ድኅረ ትንሣኤ አካል ቊሳዊ አያቋርጤነት እንዳለው የተዘራውን ዐይነት ዘር ከተዘራው ዘር ላይ እንደሚበቅል ነው:: አንዱ በሌላው እንደሚተካ ወይም አንዱ በሌላው እንደሚቀየር ሳይሆን፣ ይኸው አካል በትንሣኤ ሂደት ውስጥ እንደሚታደስ ነው:: ቅድመ ትንሣኤ አካል ይበሰብሳል፣ ይሞታል፣ ክብር የሌለው እንዲሁም ፍጥረታዊ ሲሆን ድኅረ ትንሣኤ አካል ግን የማይበሰብስ፣ ክብርንና ኀይልን የተሞላ እንዲሁም መንፈሳዊ ነው (1ቆሮንቶስ 15÷42-44)፡፡

“በሥጋ ትንሣኤ አምናለሁ!”

ኢየሱስ ክርስቶስ ከሙታን የተነሣው በአካለ ሥጋ መሆኑን የሚየስተምሩትን የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍሎች በጥሙና እንመልከት:—

1. ትንሣኤ የሚለው ቃል ቊሳዊ የሆነ አካልን ብቻ የሚያመለክት ነው

የሐዲስ ኪዳንን የትንሣኤ ትምህርት በጠለለ መልኩ ለመረዳት አይሁዶች ስለ ሙታን ትንሣኤ ያላቸውን ትምህርት በትክክል ማወቅ ያስፈልጋል፡፡ ምክንያቱም ከሉቃስ በስተቀር ሁሉም የሐዲስ ኪዳን ጸሓፍያን አይሁዶች ስለሆኑ (ቈላስይስ 4÷11:14) እንዲሁም ሐዲስ ኪዳን ስለ ትንሣኤ ሙታን የሚያስተምረው ትምህርት፣ ከብሉያት አስተምህሮ ጋር ተያያዥነት ያለው ስለሆነ፡፡


ይቀጥላል...



ምንጭ፦ ዶ/ር ተስፋዬ ሮበሌ፤ በሥጋ ትንሣኤ አምናለሁ! የአስተምህሮተ ትንሣኤ መጽሐፍ ቅዱሳዊ፣ ታሪካዊና ሥነ አመክንዮአዊ ትንታኔ፤ ከምእራፍ ሰባት የተወሰደ



ወደ ቻናሉ ለመ🀄️🀄️ል፦ @Holy_scriptures
5👍3
.       ──•◈•─────•◈•─
                          የዕለቱ ጥቅስ
        ──•◈•─────•◈•─
“ሞትን ለዘላለም ይውጣል፥ ጌታ እግዚአብሔርም ከፊት ሁሉ እንባን ያብሳል፥ የሕዝቡን ስድብ ከምድር ሁሉ ላይ ያስወግዳል፤ እግዚአብሔር ተናግሮአልና።”
ኢሳይያስ 25፥8



ወደ ቻናሉ ለመ🀄️🀄️ል፦ @Holy_scriptures
2👏1
Audio
#መጻሕፍትን_በድምጽ

👉ርዕስ፦ የካታኮምቡ ሰማዕት
🗣ትርጉም፦ በአማረ ማሞ
መካነ ኢየሱስ ሥነ ጽሑፍ ክፍል።
📻ክፍል-3

ይቀጥላል...



ወደ ቻናሉ ለመ🀄️🀄️ል፦ @Holy_scriptures
🔥1
ወደ ቻናሉ ለመ🀄️🀄️ል፦ @Holy_scriptures
🥰3
የካታኮንቡ ሰማዕት.pdf
30.5 MB
👉ርዕስ፦ የካታኮምቡ ሰማዕት
🗣ትርጉም፦ በአማረ ማሞ
መካነ ኢየሱስ ሥነ ጽሑፍ ክፍል።



ወደ ቻናሉ ለመ🀄️🀄️ል፦ @Holy_scriptures
👍51🔥1
.       ──•◈•─────•◈•─
                          የዕለቱ ጥቅስ
        ──•◈•─────•◈•─
“የክርስቶስ ኢየሱስም የሆኑቱ ሥጋን ከክፉ መሻቱና ከምኞቱ ጋር ሰቀሉ።”
ገላትያ 5፥24



ወደ ቻናሉ ለመ🀄️🀄️ል፦ @Holy_scriptures
12👍1
የካታኮምቦ ሰማዕታት ክፍል 4 Catacombs part 4
ታላቁ ተስፋ - Great Hope - Official
#መጻሕፍትን_በድምጽ

👉ርዕስ፦ የካታኮምቡ ሰማዕት
🗣ትርጉም፦ በአማረ ማሞ
መካነ ኢየሱስ ሥነ ጽሑፍ ክፍል።
📻ክፍል-4

ይቀጥላል...



ወደ ቻናሉ ለመ🀄️🀄️ል፦ @Holy_scriptures
2🥰2👍1