ቅዱሳት መጻሕፍት
7.45K subscribers
1.35K photos
61 videos
332 files
798 links
በዚህ ቻናል

👉ቅዱሳት መጻሕፍት ይጠናሉ::
👉መጽሐፍ ቅዱሳዊ ትምህርቶች ይቀርባሉ::
👉 ለቅዱሳት መጽሐፍት ጥናት የሚያግዙ መጻሕፍት ይለቀቃሉ።

⭐️⭐️⭐️⭐️⭐️

@Holy_scriptures
Download Telegram
ጥበቡ የምድረ በዳው እረኛ.pdf
9.9 MB
ርዕስ፦ ጥበቡ የምድረ በዳው እረኛ
የዶክተር ጥበቡ ኃይለሥላሴ የሕይወትና የአገልግሎት ታሪክ
ጸሐፊ፦ ሊሻን አጎናፍር
ኤዲተር፦ ወንድዬ ዓሊ

ወደ ቻናሉ ለመ🀄️🀄️ል፦ @Holy_scriptures
7👍2👏1
#ረቡዕ የአስቆሮቱ ይሁዳ ኢየሱስን የካደበት ቀንና ማርያም (በማርቆስ ስሟ አልተጠቀሰም) በኢየሱስ እግር ስር ሽቶ ያፈሰሰችበትና በጸጉሯ ያበሰችበት ቀን ነው።

“እርሱም በቢታንያ በለምጻሙ በስምዖን ቤት በነበረ ጊዜ፥ በማዕድ ተቀምጦ ሳለ፥ አንዲት ሴት ዋጋው እጅግ የከበረ ጥሩ ናርዶስ ሽቱ የመላበት የአልባስጥሮስ ቢልቃጥ ይዛ መጣች፤ ቢልቃጡንም ሰብራ በራሱ ላይ አፈሰሰችው።”
      (ማርቆስ 14፥3)



ወደ ቻናሉ ለመ🀄️🀄️ል፦ @Holy_scriptures
11👍2🔥2
.       ──•◈•─────•◈•─
                          የዕለቱ ጥቅስ
        ──•◈•─────•◈•─
“ስለዚህ እንደ ቆመ የሚመስለው እንዳይወድቅ ይጠንቀቅ።”
1ኛ ቆሮንቶስ 10፥12



ወደ ቻናሉ ለመ🀄️🀄️ል፦ @Holy_scriptures
7
#ረቡዕ የአስቆሮቱ ይሁዳ ኢየሱስን የካደበት ቀንና ማርያም (በማርቆስ ስሟ አልተጠቀሰም) በኢየሱስ እግር ስር ሽቶ ያፈሰሰችበትና በጸጉሯ ያበሰችበት ቀን ነው። (ማር. 14 ) በዚህ ቀን አንድ ነገር ማስተዋል አለብን ብዙ ጊዜ ከኢየሱስ ጋር የተጓዙ ሰዎች ትጥቃቸው መፈታት የጀመረበትና እውነተኛ ማንነታቸው የተገለጠበት ቀን ነበር። ከዚህ በፊት በርትተው ይጓዙ የነበሩ ሁሉ የሥጋ ድካም በብርቱ መገዳደር እና መጣል የጀመራቸው ጊዜ ነበር። አንዳዶች ወድቀው ሲነሱ አንዱ እስከወዲያኛው ወደቀ። በነገራችን ላይ የዚህን የሥጋን ከመንፈስ ጋር ለማበር መቸገር መፍትሄ ከአንድ ቀን በኋላ በጌቴሴማኒ ሹክ ብሏቸዋል። እንዲህ በማለት፦ “ወደ ፈተና እንዳትገቡ ትጉና ጸልዩ፤ መንፈስስ ተዘጋጅታለች ሥጋ ግን ደካማ ነው አለው።” (ማቴዎስ 26፥41)

ወደ ረቡዕ ቀን ስንመለስ ይሁዳ እንዲህ አይነት ሰው ነበር፦
"ይህንም የተናገረ ሌባ ስለ ነበረ ነው እንጂ ለድሆች ተገድዶላቸው አይደለም፤ ከረጢትም ይዞ በውስጡ ከሚገባው ይወስድ ስለ ነበረ ነው።" (ዮሐ. 12፡6) በሌላ በኩል ደግሞ በምን ሰዓት ምን ማድረግ እንዳለባት የምታውቅን ሴት እንመለከታለን። ኢየሱስ ከሞተ በኋላ ለአካሉ ሽቶ ለመቀባት አስበው የሄዱ ቢኖሩም ትንሣኤው ቀድሟቸው ሳይሳካላቸው ተመልሰዋል። መቅደላዊት ማርያም ግን መችና የት ኢየሱስን ማግኘት እንደሚቻል የምታውቅ ሴት ነበረች። እናም የዛሬው ቀን ከኢየሱስ ጋር ለዘለአለሙ ለመጓዝ ኃይል እንድናገኝ፣ ከእርሱ አሳብና አጀንዳ ጋር ደግሞ ተባብረን እንድንጓዝ ጌታ ይርዳን!

“እርሱም በቢታንያ በለምጻሙ በስምዖን ቤት በነበረ ጊዜ፥ በማዕድ ተቀምጦ ሳለ፥ አንዲት ሴት ዋጋው እጅግ የከበረ ጥሩ ናርዶስ ሽቱ የመላበት የአልባስጥሮስ ቢልቃጥ ይዛ መጣች፤ ቢልቃጡንም ሰብራ በራሱ ላይ አፈሰሰችው።”
ማርቆስ 14፥3

“ከአሥራ ሁለቱም አንዱ የአስቆሮቱ ይሁዳ አሳልፎ ሊሰጠው ወደ ካህናት አለቆች ሄደ።”
ማርቆስ 14፥10


ወደ ቻናሉ ለመ🀄️🀄️ል፦ @Holy_scriptures
7👍2
victorious christian life
Nigusse Denano
#መጻሕፍትን_በድምጽ

ርዕስ፦ አሸናፊው የክርስቲያን ኑሮ
የመጽሐፈ ኢያሱ ጥናት
ጸሐፊ፦ ዶ/ር አሳን ሬድፓዝ
ትርጉም፦ ዋቅጅራ ጎባ
ክፍል-17

ይቀጥላል...



ወደ ቻናሉ ለመ🀄️🀄️ል፦ @Holy_scriptures
#ሐሙስ ጌታችንና መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ከመሞቱ በፊት ከደቀ መዛሙርቱ ጋር የመጨረሻውን እራት የበላበትንና በእውነት ለእርሱ ተከታይ ለሆኑት ብርቱና መሰረታዊ ትምህርት፣ ምክር፣ ተግጻጽ ሲያስፈልግም በተግባር የተደገፈ ትምህርት ያስተላለፈበት እንዲሁም አሁን በመንግስቱ ላሉ በኋላም ለሚመጡ የጸለየው አስደናቂ ጸሎት የጸለየበት፣ የደቀ መዛሙርቱ ድካም. . . ወዘተ የሐሙስ ቀን ሁነቶች ናቸው። ሌላ የሚገርም ነገር ቢኖር ኢየሱስን ከመከራሁ እንዲቀርና እርሱን ለመርዳት ተማሪዎቹ በስጋ ቢጣጣሩም ፍቅራቸውን በመሃላ ለማጽናት ቢሞክሩም በኋላ እየሸሹና እየከዱ መገኘታቸው ነው። ለካ እውነተኛ ማንነት በወቅታዊ ስሜት ሳይሆን በፈተና ወቅት የሚገለጥ ነው! የዮሐንስ ወንጌልን ከምዕራፍ 13-18።

“እውነተኛ አምላክ ብቻ የሆንህ አንተን የላክኸውንም ኢየሱስ ክርስቶስን ያውቁ ዘንድ ይህች የዘላለም ሕይወት ናት።”
(ዮሐንስ 17፥3)

🔜 ስለጌታ እራት ዛሬ ይጠብቁን።



ወደ ቻናሉ ለመ🀄️🀄️ል፦ @Holy_scriptures
👍10🥰21
.       ──•◈•─────•◈•─
                          የዕለቱ ጥቅስ
        ──•◈•─────•◈•─
“ኢየሱስም ከፋሲካ በዓል በፊት፥ ከዚህ ዓለም ወደ አብ የሚሄድበት ሰዓት እንደ ደረሰ አውቆ፥ በዚህ ዓለም ያሉትን ወገኖቹን የወደዳቸውን እስከ መጨረሻ ወደዳቸው።”
ዮሐንስ 13፥1



ወደ ቻናሉ ለመ🀄️🀄️ል፦ @Holy_scriptures
👍32
ለክርስቲያኑ የጌታ እራት ትርጉሙ እንዴትነው? 


ሦስት የተያያዙ ሃሳቦች ለሃላፊ ጊዜ ፣ ለአሁን ጊዜና ለወደፊት ጊዜ ሊጠቅሙ የሚችሉ ሲሆኑ እነርሱም ተያይዘው ያሉና  የተገናኙም ናቸው::

#1ኛ  የጌታ እራት የጌታን መታሰቢያ ጊዜ የምናስታውስበት ነው ጌታም እንዲህ ሲል ትዕዛዝ ሰጥቷል<< Do this in remembrance of me  >> የሉቃስ ወንጌል 22፥19 ፤ 1ኛ ቆሮንቶስ 11፥24-25 ይህ ለመኖርያችን ዋጋ ለመክፈል በአዕምሮ ወይም በሥጋ የምንጨነቅበት ሳይሆን ግሩምና ድንቅ የሆነውን የጌታን የማዳን ሕይወትና አገልግሎት ለማስታወስ ነው ይህ የጌታ እራት ጥልቅ የሆነውን ምሥጋናና አድናቆት ኢየሱስ ክርስቶስ ለእኛ ስላደረገልን ለመግለጽ ትልቅ በዓል ወይንም በእንግሊዘኛው Occasion ነው::

በአይሁድ የፋሲካ እራት ጊዜ የዕብራውያን ከግብጽ ባርነት ነጻ መውጣት የታወጀ አንድ ደረጃም ወደፊት የሄደ ነበረ በዘጸአት 12፥26 እና 27 ላይ እንዲህ የሚል ቃል ተጽፎ እናገኛለን "እንዲህም ይሆናል፤ ልጆቻችሁ፦ ይህ አምልኮ ለእናንተ ምንድር ነው ?  ባሉአችሁ ጊዜ፥ እናንተ፦ በግብፅ አገር በእስራኤል ልጆች ቤቶች ላይ አልፎ ግብፃዊያንን በመታ ጊዜ፥ ቤቶቻችንን ያዳነ የእግዚአብሔር የማለፉ መሥዋዕት ይህች ናት ትሉአቸዋላችሁ::" ይለናል በመሆኑም በዚህ በአዲስ ኪዳኑየጌታ እራት ደግሞ ክርስቲያኑ ከኃጢአት ነጻ መውጣቱን ፣ ከሞት ሥቃይ መከራ በአካልና በአዕምሮም ሳይቀር ፋሲካችን በሆነው ክርስቶስ እንደገናም ነጻ መውጣቱንና መላቀቁንምጭምር ያውጃል(1ኛ ቆሮንቶስ 5 ፥ 7 ፤ 1ኛ ቆሮንቶስ 11 ፥ 26 )


#2ኛ  ሁለተኛው የጌታ እራት ጊዜ ፦ብርታት የማግኘት ፣ ጉልበት የማግኘት ፣ የመታደስ ጊዜ ፣ የመተሳሰርና የቁርባን ጊዜ  ነው:: እንደ ተሳትፎአችን መጠን የኢየሱስ ሞትና ትንሣኤ ትርፉ ሕይወትን መስጠት ነው( ሮሜ 5 ፥ 10 ፤ 1ኛ ቆሮንቶስ 10 ፥ 16 ) ስለዚህ በክርስቶስ ትንሣኤ ባለ መንፈስ ውስጥ ሥልጣንን አግኝተን እንመገባለን እናድጋለን:: ጆን ዊስሊ ይህንን ጥንካሬ ያውቃል በአማካኝ በየአራት ወይም አምስት ቀን በረጅም ጊዜና ፍሬያማ ሥራው ወይንም የሕይወት ታሪኩ ቁርባኑን ይወስዳል:: 


#3ኛ ሦስተኛውና የመጨረሻው የጌታ እራት ጊዜ ቃልኪዳንን የማደስ እና ተስፋ የማድረግ ጊዜ ነው ነገር ግን ራሳችንን ቃል በቃል ማረጋገጥና የጥራት ሙከራ ወይንም ፈተና ማድረግ አለብን የጌታን እራት ተካፍለን የምንበላበት አኳኋን ዋጋ ያለውነው( 1ኛ ቆሮንቶስ 11 ፥ 28 እና 29 ) እንደገናም የእርሱ ሕዝቦች ሙሉ በሆነ የመታደስ ተስፋ ለክርስቶስ የተሰጠንበትን እናድሳለን እርሱ እስኪመጣ ድረስ ( 1ኛ ቆሮንቶስ 11 ፥ 26 ) ክርስቶስ ከተመለሰ በኋላ በእርሱ መንግሥት ውስጥ በእርሱ አካላዊ መገኘት ከእርሱ ጋር ተካፍለን እንበላለን ( የማቴዎስ ወንጌል 26 ፥ 29 )


ምንጭ:- yonasgetaneh.blogspot.com



ወደ ቻናሉ ለመ🀄️🀄️ል፦ @Holy_scriptures
5👍4
victorious christian life
Nigusse Denano
#መጻሕፍትን_በድምጽ

ርዕስ፦ አሸናፊው የክርስቲያን ኑሮ
የመጽሐፈ ኢያሱ ጥናት
ጸሐፊ፦ ዶ/ር አሳን ሬድፓዝ
ትርጉም፦ ዋቅጅራ ጎባ
ክፍል-18

ይቀጥላል...



ወደ ቻናሉ ለመ🀄️🀄️ል፦ @Holy_scriptures
1👍1
#የእግዚአብሔር_ቃል_ምን_ይላል?


ዮሐንስ 17
¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯
¹-² ኢየሱስም ይህን ተናግሮ ወደ ሰማይ ዓይኖቹን አነሣና እንዲህ አለ፦ አባት ሆይ፥ ሰዓቱ ደርሶአል፤ ልጅህ ያከብርህ ዘንድ፥ በሥጋም ሁሉ ላይ ሥልጣን እንደ ሰጠኸው፥ ለሰጠኸው ሁሉ የዘላለምን ሕይወት ይሰጣቸው ዘንድ ልጅህን አክብረው።
³ እውነተኛ አምላክ ብቻ የሆንህ አንተን የላክኸውንም ኢየሱስ ክርስቶስን ያውቁ ዘንድ ይህች የዘላለም ሕይወት ናት።
⁴ እኔ ላደርገው የሰጠኸኝን ሥራ ፈጽሜ በምድር አከበርሁህ፤
⁵ አሁንም፥ አባት ሆይ፥ ዓለም ሳይፈጠር በአንተ ዘንድ በነበረኝ ክብር አንተ በራስህ ዘንድ አክብረኝ።
⁶ ከዓለም ለሰጠኸኝ ሰዎች ስምህን ገለጥሁላቸው። የአንተ ነበሩ ለእኔም ሰጠሃቸው፤ ቃልህንም ጠብቀዋል።
⁷ የሰጠኸኝ ሁሉ ከአንተ እንደ ሆነ አሁን ያውቃሉ፤
⁸ የሰጠኸኝን ቃል ሰጥቻቸዋለሁና፤ እነርሱም ተቀበሉት፥ ከአንተም ዘንድ እንደ ወጣሁ በእውነት አወቁ፥ አንተም እንደ ላክኸኝ አመኑ።
⁹ እኔ ስለ እነዚህ እለምናለሁ፤ ስለ ዓለም አልለምንም ስለ ሰጠኸኝ እንጂ፤ የአንተ ናቸውና፤
¹⁰ የእኔም የሆነ ሁሉ የአንተ ነው የአንተውም የእኔ ነው፤ እኔም ስለ እነርሱ ከብሬአለሁ።
¹¹ ከዚህም በኋላ በዓለም አይደለሁም፥ እነርሱም በዓለም ናቸው፥ እኔም ወደ አንተ እመጣለሁ። ቅዱስ አባት ሆይ፥ እነዚህን የሰጠኸኝን እንደ እኛ አንድ እንዲሆኑ በስምህ ጠብቃቸው።
¹² ከእነርሱ ጋር በዓለም ሳለሁ የሰጠኸኝን በስምህ እኔ እጠብቃቸው ነበር፤ ጠበቅኋቸውም መጽሐፉም እንዲፈጸም ከጥፋት ልጅ በቀር ከእነርሱ ማንም አልጠፋም።
¹³ አሁንም ወደ አንተ እመጣለሁ፤ በእነርሱም ዘንድ ደስታዬ የተፈጸመ እንዲሆንላቸው ይህን በዓለም እናገራለሁ።
¹⁴ እኔ ቃልህን ሰጥቻቸዋለሁ፤ እኔም ከዓለም እንዳይደለሁ ከዓለም አይደሉምና ዓለም ጠላቸው።
¹⁵ ከክፉ እንድትጠብቃቸው እንጂ ከዓለም እንድታወጣቸው አልለምንም።
¹⁶ እኔ ከዓለም እንዳይደለሁ ከዓለም አይደሉም።
¹⁷ በእውነትህ ቀድሳቸው፤ ቃልህ እውነት ነው።
¹⁸ ወደ ዓለም እንደ ላክኸኝ እንዲሁ እኔ ወደ ዓለም ላክኋቸው፤
¹⁹ እነርሱም ደግሞ በእውነት የተቀደሱ እንዲሆኑ እኔ ራሴን ስለ እነርሱ እቀድሳለሁ።
²⁰-²¹ ሁሉም አንድ ይሆኑ ዘንድ፥ ከቃላቸው የተነሣ በእኔ ስለሚያምኑ ደግሞ እንጂ ስለ እነዚህ ብቻ አልለምንም፤ አንተ እንደ ላክኸኝ ዓለም ያምን ዘንድ፥ አንተ፥ አባት ሆይ፥ በእኔ እንዳለህ እኔም በአንተ፥ እነርሱ ደግሞ በእኛ አንድ ይሆኑ ዘንድ እለምናለሁ።
²²-²³ እኛም አንድ እንደ ሆንን አንድ ይሆኑ ዘንድ፤ እኔም በእነርሱ አንተም በእኔ ስትሆን፥ በአንድ ፍጹማን እንዲሆኑ፥ የሰጠኸኝን ክብር እኔ ሰጥቻቸዋለሁ፤ እንዲሁም ዓለም አንተ እንደ ላክኸኝ በወደድኸኝም መጠን እነርሱን እንደ ወደድሃቸው ያውቃል።
²⁴ አባት ሆይ፥ ዓለም ሳይፈጠር ስለ ወደድኸኝ የሰጠኸኝን ክብሬን እንዲያዩ እኔ ባለሁበት የሰጠኸኝ እነርሱ ደግሞ ከእኔ ጋር ይሆኑ ዘንድ እወዳለሁ።
²⁵ ጻድቅ አባት ሆይ፥ ዓለም አላወቀህም፥ እኔ ግን አወቅሁህ እነዚህም አንተ እንደ ላክኸኝ አወቁ፤
²⁶ እኔንም የወደድህባት ፍቅር በእነርሱ እንድትሆን እኔም በእነርሱ፥ ስምህን አስታወቅኋቸው አስታውቃቸውማለሁ።




ወደ ቻናሉ ለመ🀄️🀄️ል፦ @Holy_scriptures
👍8
#አርብ ፀሐይ ብርሃኗን የከለከለችበት፣ እግዚኣብሔር ለኃጢኣት ያለውን ታላቅ ቁጣ በብርቱ የገለጠበት፣ በሌላ በኩል ሰማይ ከምድር እንዲታረቅ፣ በሰው መካከል ልዩነት እንዳይኖር የጥል ግድግዳ እንዲፈርስ የመጨረሻ ዋጋ የተከፈለበት፣ እግዚአብሔር ሰውን እንደሚወድ በደም እየጻፈ ያስረዳበት፣ በዓለም የሃይማኖት ይሁን በሌላው ታሪክ በማይታወቅ መልኩ አምላክ(የሚመለከው) እንዲያመልኩት ለተጠሩት ሰዎች የሞተበት፣ የተሰዋበት፣ መዳናቸውን ለመፈጸም የተዋረደበት ቃላት ሊገልጡት የማይችሉት ፍቅር የተብራራበት ቀን ነው። ካህን ሞተ! ካህን ደም ይዞ ገባ! ካህን አዳነን! የአለምን የጊዜ አቆጣጠር/ ስርዓት ከዓመተ ዓለም ወደ ዓመተ ምሕረት የተለወጠበት የዓለም ዳግመኛ የውልደት ቀንም ነው። የዓለማችን ታላቁ አዋጅ "τελέω"/ "ተፈፀመ" የታወጀበትም ነው።

የአምላክ የናዝሬቱ ኢየሱስ ጣር የበዛበት የሰው ፌዝና ዛቻ እንዲሁም አለማወቅ የበረታበት አስጨናቂም ቀን ነው አርብ።

"ኢየሱስም ሆምጣጤውን ከተቀበለ በኋላ። ተፈጸመ አለ፥ ራሱንም አዘንብሎ ነፍሱን አሳልፎ ሰጠ።" (ዮሐ. 19፡30)

🔜 ለመሆኑ ኢየሱስ ይህን ታላቅ ስቃይ
ተሸክሞ ለምን ሞተ? በቀጣይ
ጹሑፍ ይህንን እንመለከታለን።



ወደ ቻናሉ ለመ🀄️🀄️ል፦ @Holy_scriptures
13👍3
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
ወደ ቻናሉ ለመ🀄️🀄️ል፦ @Holy_scriptures
5👍1👎1
.       ──•◈•─────•◈•─
                          የዕለቱ ጥቅስ
        ──•◈•─────•◈•─
“ኢየሱስም ሆምጣጤውን ከተቀበለ በኋላ፦ ተፈጸመ አለ፥ ራሱንም አዘንብሎ ነፍሱን አሳልፎ ሰጠ።”
ዮሐንስ 19፥30



ወደ ቻናሉ ለመ🀄️🀄️ል፦ @Holy_scriptures
👍61😁1
ኢየሱስ ክርስቶስ ለምን ሞተ?
          


“እኔ ደግሞ የተቀበልሁትን ከሁሉ በፊት አሳልፌ ሰጠኋችሁ እንዲህ ብዬ፦ መጽሐፍ እንደሚል ክርስቶስ ስለ ኃጢአታችን ሞተ፥ ተቀበረም፥”
  (1ኛ ቆሮንቶስ 15፥3)


“በሕይወትም ያሉት ስለ እነርሱ ለሞተውና ለተነሣው እንጂ ወደ ፊት ለራሳቸው እንዳይኖሩ ስለ ሁሉ ሞተ።”
       (2ኛ ቆሮ 5፥15)


“ክፉ ከሆነ ከአሁኑ ዓለም ያድነን ዘንድ እንደ አምላካችንና እንደ አባታችን ፈቃድ ስለ ኃጢአታችን ራሱን ሰጠ።”
       (ገላትያ 1፥4)


"እርሱ ሰላማችን ነውና፤ ሁለቱን ያዋሐደ በአዋጅ የተነገሩትንም የትእዛዛትን ሕግ ሽሮ በመካከል ያለውን የጥል ግድግዳን በሥጋው ያፈረሰ፤ ይህም ከሁለታቸው አንድን አዲስን ሰው በራሱ ይፈጥር ዘንድ ሰላምንም ያደርግ ዘንድ፥ ጥልንም በመስቀሉ ገድሎ በእርሱ ሁለታቸውን በአንድ አካል ከእግዚአብሔር ጋር ያስታርቅ ዘንድ ነው።"
(ኤፌሶን 2፥14-16)


“በውኃ መታጠብና ከቃሉ ጋር አንጽቶ እንዲቀድሳት ስለ እርስዋ ራሱን አሳልፎ ሰጠ፤”
     (ኤፌሶን 5፥25-26)


“በእኛ ላይ የነበረውን የሚቃወመንንም በትእዛዛት የተጻፈውን የዕዳ ጽሕፈት ደመሰሰው፤ እርሱንም በመስቀል ጠርቆ ከመንገድ አስወግዶታል፤”
(ቆላስይስ 2፥14)


“የምንነቃም ብንሆን፥ የምናንቀላፋም ብንሆን፥ ከእርሱ ጋር አብረን በሕይወት እንኖር ዘንድ ስለ እኛ ሞተ።”
      (1ኛ ተሰሎንቄ 5፥10)


“ለኃጢአት ሞተን ለጽድቅ እንድንኖር፥ እርሱ ራሱ በሥጋው ኃጢአታችንን በእንጨት ላይ ተሸከመ”
       (1ኛ ጴጥሮስ 2፥24)


“መድኃኒታችንም ከዓመፅ ሁሉ እንዲቤዠን፥ መልካሙንም ለማድረግ የሚቀናውን ገንዘቡም የሚሆነውን ሕዝብ ለራሱ እንዲያነጻ፥ ስለ እኛ ነፍሱን ሰጥቶአል።”
      (ቲቶ 2፥14)


“በዚህም ፈቃድ የኢየሱስ ክርስቶስን ሥጋ አንድ ጊዜ ፈጽሞ በማቅረብ ተቀድሰናል።”
     (ዕብራውያን 10፥10)



ወደ ቻናሉ ለመ🀄️🀄️ል፦ @Holy_scriptures
👍5🥰4❤‍🔥2👎1
#ፋሲካ
#ትንሣኤ

ተፈጸመ! “Tetelestai” (τετέλεσται)



"ተቴሌስታይ" (በግሪክኛ፦ τετέλεσται) ኢየሱስ ክርስቶስ በመስቀል ላይ የተናገረው በዮሐንስ ወንጌል ውስጥ የሚገኝ ቃል ነው። "ተፈጸመ" ተብሎም ይተረጎማል። ይህ ኃይለ ቃል የሚያመለክተው የኢየሱስን ተልእኮ ማጠናቀቅን በተለይ ለሰው ልጆች ኃጢአት የማስተሰረያ መስዋዕት መሆኑን ነው።

መንፈሳዊ እና ሥነ-መለኮታዊ ትርጉም፡-

በጥንታዊ ግሪክ “ቴቴሌስታይ” በተለያዩ የዕለት ተዕለት ሁኔታዎች ውስጥ ጥቅም ላይ ውሏል።

👉አካውንቲንግ (ሒሳብ)፦ ዕዳ ሙሉ በሙሉ መከፈሉን ለማሳየት ደረሰኝ ላይ ይጻፋል።
👉ወታደራዊ፦ ተልዕኮ መፈጸሙን ለማወጅ።
👉ዳኝነት(ሕግ)፦ ቅጣቱ ተፈጽሟል።
👉ሃይማኖታዊ፡- መስዋዕቱ ተቀባይነት ያለው እና የተሟላ መሆኑን ለማመልከት ካህናቱ ይጠቀሙበት ነበር።

ስለዚህ ጌታችን እና መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ “ተቴሌስታይ” ሲል፡-

👉የኃጢአት ዋጋ ሙሉ በሙሉ ተከፍሏል።
👉የመዳን ተልእኮ ተጠናቀቀ።
👉የብሉይ ኪዳን ትንቢቶች ተፈጽመዋል።
👉የመሥዋዕቱ ሥራ ተጠናቀቀ እና በእግዚአብሔር ዘንድ ፍጹም ተቀባይነት ያለው ሆነ ማለቱ ነው።


ምንጭ፦
👉Strong, J. (1995). The New Strong’s Exhaustive Concordance of the Bible. Thomas Nelson.
👉Thayer, J. H. (1889). Thayer’s Greek-English Lexicon of the New Testament. Hendrickson Publishers.



ወደ ቻናሉ ለመ🀄️🀄️ል፦ @Holy_scriptures
9👍2
#ቅዳሜ የደቀ መዛሙርቱ ክህደት ወደ ጸጸት፣ ፍርሃትና ጥርጣሬ የተሸጋገረበት ነው። በደቀ መዛሙርቱ ዘንድ ስሜት የቃሉን እውነትና ተስፋ አይሎ የተገኘበትም ነው። የካህናት አለቆችና ፈሪሳዊያን በበኩላቸው ለወሰዱት እርምጃ እንከን እስከማይገኝ ድረስ ጥንቃቄያቸውን አብዝተው የጨመሩበትም ነው።

የሚገርመው የጌታ የመነሳቱ አይቀሬነት ትልቅ ጉዳይ ሆኖ በደቀ መዛሙርቱ ዘንድ መወራት ሲገባው ወሬ እና አጀንዳ ሆኖ የሰነበተው በፈሪሳዊያን ዘንድ መሆኑ ነው። ለምን? የደቀመዛሙርቱን ዓይን ምን ጋረደው? በነገራችን ላይ በአይሁድ ባህል መሰረት የአርብ ምሽት የመዘጋጀት ቀን በመባል ትታወቃለች። ማቴ. 27፥62-66 ይመልከቱ።         

"እንግዲህ ደቀ መዛሙርቱ መጥተው በሌሊት እንዳይሰርቁት ለሕዝቡም። ከሙታን ተነሣ እንዳይሉ፥ የኋለኛይቱ ስሕተት ከፊተኛይቱ ይልቅ የከፋች ትሆናለችና መቃብሩ እስከ ሦስተኛ ቀን ድረስ እንዲጠበቅ እዘዝ አሉት።"
(ማቴ. 27፡64)

🔜 ኢየሱስ ምን ቀን ነው የተቀበረው? ከተቀበረ በኋላ የት ነበር? ሦስት ቀን ሙሉ ነው የተቀበረው ወይስ እንዴት ቢቀበር ነው ሦስት ቀን የተባለው? በቀጣይ ጹሑፍ ይህንን እንመለከታለን።



ወደ ቻናሉ ለመ🀄️🀄️ል፦ @Holy_scriptures
👍103
.       ──•◈•─────•◈•─
                          የዕለቱ ጥቅስ
        ──•◈•─────•◈•─
“ነፍሴን በሲኦል አትተዋትምና፥ ቅዱስህንም መበስበስን ያይ ዘንድ አትተወውም።”
መዝሙር 16፥10



ወደ ቻናሉ ለመ🀄️🀄️ል፦ @Holy_scriptures
🥰52
ኢየሱስ በየትኛው ቀን ነው የተሰቀለው?  . . . ከሞተ በኋላስ የት ነበር?



ወደ ቀኑ ስንመጣ፥ በወንጌላት ውስጥ ቀኑ የትኛው መሆኑ አልተጻፈም። ጥያቄውን ከሁለት አንጻር መመልከት እንችላለን።

1. በአይሁድ አንድ ሙሉ ቀንም የቀን ሽራፊም እንደ ቀን ነው የሚቆጠረው። ዐርብ፥ ቅዳሜ፥ እሑድ ሙሉም ጎዶሎም ሆነውም እንደ ሦስት ቀን ይቆጠራሉ።

2. ሁለተኛው፥ በወንጌላት ውስጥ ቀኑ የትኛው መሆኑ አልተጻፈም ብያለሁ። ጸሎተ ኀሙስ፥ ስቅለተ ዕርብ የምንለው ከትውፊት እንጂ ቀኑ ይህ ነው ተብሎ አልተጻፈልንም። የመዘጋጀት ቀን መሆኑ፥ ሉቃ. 23፥54፤ የሰንበት ዋዜማ መሆኑ፥ ማር. 15፥42 በዮሐ. 19፥31 የማዘጋጀት ቀን መሆኑ ተጽፎልናል። ዮሐንስ ስለዚያ ቀን ሲናገር ከዚያም የበለጠ ብሎአል፤ አይሁድም የማዘጋጀት ቀን ስለ ሆነ ያ ሰንበት ትልቅ ነበረና ሥጋቸው በሰንበት በመስቀል ላይ እንዳይኖር፥ ጭናቸውን ሰብረው እንዲያወርዱአቸው ጲላጦስን ለመኑት። ብሎአል። ἦν γὰρ μεγάλη ἡ ἡμέρα ἐκείνη τοῦ σαββάτου•  ነበረና ትልቅ ቀን ያ ሰንበት።
የአይሁድ ፋሲካ በአዲሱ ዓመታቸው የመጀመሪያ ወር 14ኛ ቀን ነው የሚከበረው፤ ዘሌ. 23፥5፤ ዕዝ. 6፥19፤ ሕዝ. 45፥21።በተለያዩ ምክንያቶች በቀኑ ማክበር ያልቻለ እንዲያውም በሁለተኛ ወር በአሥራ አራተኛው ቀን ያከብረዋል፤ ዘኁ. 9፥1-14፤ 2ዜና 30፥1-18። የአይሁድ ወር ጨረቃዊ ወር ነውና ይህ ቀን ሁሌም በአንድ ቀን ላይ አያርፍም። ፀሐያዊ ወርም እንኳ ቢሆን በአንድ ቀን አያርፍም። ስለዚህ የአይሁድ ፋሲካ የግድ በአንድ ቀን እንደሚያርፍ አድርገን መጠበቅ የለብንም። ፋሲካ የበዓል ቀን እንጂ የሰንበት ቀን አይደለም።

ሌላው፥ ትልቅ ሰንበት ወይም ታላቅ ሰንበት የተባለ ሰንበት በብሉይ ኪዳን አንድ ብቻ ሆኖ ተጠቅሶአል። የተለመደው የአይሁድ ሰንበት ቅዳሜ ስለሆነና ቀናቸው የሚጀምረው ከምሽት ጀምሮ ስለሆነ፥ ስቅለት ዐርብ እንደሆነ መውሰዱ አግባብ ነው። ሰንበት ማለት ትርጉሙ ማረፍ ነው። ሰባተኛው ቀን ስለሆነም ሰባት ማለትም ነው። ከሰባት ይልቅ ግን ትርጉሙ ማረፍ ወይም ከሥራ መታገድ ነው። አይሁድ ከሰባት ቀናት በአንዱ ማረፍን ያርፋሉ። በአይሁድ ከሰባቱ ቀናት ሌላ ሰንበት የተባለ ቀንም አለ። በሰባት ዓመት የሚከበር የዓመት ሰንበትም አለ። በዚህኛው ሰው ብቻ ሳይሆን ምድሪቱም ሰንበት አድርጋ ታርፋለች አትታረስም። በ50ኛው ዓመት የሚከበር የኢዮቤልዩ ዓመትም አለ። ስለ ተለየ የሰንበት ቀን በዘሌ. 16 እናገኛለን። ይህ ሰንበት የስርየት ቀን የተባለው ቀን ነው። ቀኑ በሰንበት (ወይም ሰባተኛ) ቀን ዐረፈም አላረፈም ሰንበት ይባላል። ከሳምንቱ በየትኛውም ቀን ቢያርፍ ሰንበት ይባላል። ይህኛው ቀን የሚውለው ሰባተኛው ወር እና አሥረኛው ቀን ነው፤ ዘሌ. 16፥29-31። ይህ ቀን በዓመት አንዴ ሊቀ ካህናቱ ወደ ቅድስተ ቅዱሳን የሚገባበት ቀን ነው። ያ ቀን የተለየ ሕዝባዊ ወይም ብሔራዊ የስርየት ቀን ነው።

አንዳንድ የመጽሐፍ ቅዱስ ሊቃውንት ያ የስቅለት ዕለት ከዚያ ቀን ጋር የተቆራኘ እንደሆነ ያስባሉ። ቀኑ שַׁבָּתוֹן שַׁבָּת ሻባት ሻባቶውን ተብሎአል፤ ሰንበተ ሰንበት ማለት ነው። በዘሌ. 16፥31 ታላቅ ሰንበት ይሆንላችኋል፥ ራሳችሁንም ታዋርዳላችሁ የዘላለም ሥርዓት ነው። የተባለው ቀን ነው። ይህ ቀን ሁሌም ሰባተኛ ወር አሥረኛ ቀን ስለሆነ ሰኞ ወይም ረቡዕ፥ ወይም ቅዳሜም ሊውል ይችላል። ይሁን እንጂ ይህ ትልቅ ሰንበት የፋሲካ ሰንበት ሊሆን አይችልም። ፋሲካ በሰባተኛው ሳይሆን በአንደኛው ወር ነው የሚከበረውና።

እንግዲህ ኢየሱስ የተሰቀለው የፋሲካ ቀን፥ ልብ እንበል ፋሲካ የምንለው በጉ የሚታረድበት ቀን ነው፤ በተለምዶ ስቅለተ ዓርብ እንበል እንጂ ፋሲካ ዓርብ ነው መባል የነበረበት። ይህ ቀን ታዲያ የግድ ዐርብ ነው ማለት አይደለም። ረቡዕ ወይም ኀሙስም ሊሆን ይችላል። ከሆነ ሦስት ቀንና ሦስት ሌሊት ከዚህ አንጻርም ሲታይ ስሌቱ ትክክል ሊመጣ ይችላል።

ኢየሱስ ከሞተ በኋላ የት ነበር የቆየው?

ኢየሱስ ወደ ሲዖል ወረደ፤ በዚያም ተሰቃየ፤ አጋንንት ሲሳለቁበት፥ ሲጫወቱበት ቆይተው በዚያ ዳግም ተወልዶ በሦስተኛው ቀን ተነሣ ብለው ኑፋቄ የሚያስተምሩ አሉ። በአጋንንት መሰቃየቱና ዳግም መወለዱን እንተወው፤ የራሳቸው እኩይ ፈጠራ ስለሆነ። ወደ ሲዖል መውረዱን ከወዴት አገኛችሁት ብለን እንጠይቅና ከዚያ ለመልሳቸው ምላሽ መስጠት ይቻላል። በብሉይ ኪዳን ቋንቋ ሲዖል (שְׁאוֹל ሽዖውል) የኃጢአተኞች የስቃይ ፍጻሜ ስፍራ ከመሆን ጋር፥ መቃብር ከማለት ጋርም አንድ ነው። ለምሳሌ፥ ያዕቆብ፥ ሽምግልናዬን በኅዘን ወደ መቃብር ታወርዱታላችሁ። ሲል (ዘፍ. 42፥38) ወደ ሲዖል ወረደ ማለት አይደለም፤ ሞቶ ተቀበረ እንጂ። ኢየሱስም ሞቶ ተቀበረ እንጂ ወደ ሲዖል ወረደ ተብሎ አልተጻፈም።

ይህንን ጥያቄ በሉቃ. 23፥43 ከተጻፈው መመለስ ይቻላል። ኢየሱስ አብረውት ተሰቅለው ከነበሩት አንዱ ለተናገረው ሲመልስ፥ ኢየሱስም፦ እውነት እልሃለሁ፥ ዛሬ ከእኔ ጋር በገነት ትሆናለህ አለው። ተብሎ ተጽፎአል። ኢየሱስ በገነት እንደሚሆን ከተናገረና እነዚህ በሲዖል ሦስት ቀን ቆየ ካሉ ማንን እንስማ? አሳቾቹን ከሰማን ሲዖል ማለት እና ገነት ማለት አንድ ናቸው ማለት ነው።


ምንጭ፦ ከፌስቡክ (ዘላለም መንግሥቱ)



ወደ ቻናሉ ለመ🀄️🀄️ል፦ @Holy_scriptures
👍115
Media is too big
VIEW IN TELEGRAM
#ትንሣኤ

“እንደ ተናገረ ተነሥቶአልና በዚህ የለም፤ የተኛበትን ስፍራ ኑና እዩ።”
ማቴዎስ 28፥6


ወደ ቻናሉ ለመ🀄️🀄️ል፦ @Holy_scriptures
.       ──•◈•─────•◈•─
                          የዕለቱ ጥቅስ
        ──•◈•─────•◈•─
“እርሱ ግን፦ አትደንግጡ፤ የተሰቀለውን የናዝሬቱን ኢየሱስን ትፈልጋላችሁ፤ ተነሥቶአል፥ በዚህ የለም፤ እነሆ እርሱን ያኖሩበት ስፍራ።”
ማርቆስ 16፥6



ወደ ቻናሉ ለመ🀄️🀄️ል፦ @Holy_scriptures
👍51
#ትንሣኤ


መጽሐፍ እንደሚል ጌታችንና መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ስለ ኃጢአታችን ሞተ ተቀበረም፥ መጽሐፍም እንደሚል በሦስተኛው ቀን ከሙታን በኃይል ተነሣ! ሞት ይይዘው ዘንድ አልቻለም። ከዚያስ የእኛ ድርሻ ምን መሆን አለበት?

፩. የተናገረውን ማሰብ
፪. መጽሐፍንና ኢየሱስ ክርስቶስ የተናገረውን ቃል ማመን

ደቀ መዛሙርቱ ያደረጉት ይሄን ነበር።

“ስለዚህ ከሙታን ከተነሣ በኋላ ደቀ መዛሙርቱ ይህን እንደ ተናገረ አሰቡና መጽሐፍንና ኢየሱስ የተናገረውን ቃል አመኑ።”
           ዮሐንስ 2፥22


"እኔ ደግሞ የተቀበልሁትን ከሁሉ በፊት አሳልፌ ሰጠኋችሁ እንዲህ ብዬ፦ መጽሐፍ እንደሚል ክርስቶስ ስለ ኃጢአታችን ሞተ፥ ተቀበረም፥ መጽሐፍም እንደሚል በሦስተኛው ቀን ተነሣ፥"
          1ኛ ቆሮንቶስ 15፥3-4            


ሌላው የጌታችን እና የመድኃኒታችን የኢየሱስ ክርስቶስ ትንሣኤ በየትኛውም ሁኔታ ፍትህና ፍርድ ለተዛባባችሁ ትክክለኛ ፍርድ እና ፍትህ እንዳለ ማሳያ ነው። እስቲ አስቡት #ትንሣኤ ባይኖር የተዳፈነው፣ የተቀበረው እንዴት ይገለጣል? ክብር ለትንሣኤው ጀግና ይሁን እንጂ!


“ቀን ቀጥሮአልና፥ በዚያም ቀን ባዘጋጀው ሰው እጅ በዓለሙ ላይ በጽድቅ ሊፈርድ አለው፤ ስለዚህም እርሱን ከሙታን በማስነሣቱ ሁሉን አረጋግጦአል።”
                 ሐዋርያት 17፥31



ወደ ቻናሉ ለመ🀄️🀄️ል፦ @Holy_scriptures
9👍4