ቅዱሳት መጻሕፍት
7.45K subscribers
1.35K photos
61 videos
332 files
798 links
በዚህ ቻናል

👉ቅዱሳት መጻሕፍት ይጠናሉ::
👉መጽሐፍ ቅዱሳዊ ትምህርቶች ይቀርባሉ::
👉 ለቅዱሳት መጽሐፍት ጥናት የሚያግዙ መጻሕፍት ይለቀቃሉ።

⭐️⭐️⭐️⭐️⭐️

@Holy_scriptures
Download Telegram
#ሰኞ፣ ከሆሣዕና ማግሥት ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ከቢታንያ ወደ ኢየሩሳሌም ሲገባ ሁለት ነገሮችን አድርጓል፡፡ አንደኛ ከቅጠል በስተቀር ፍሬ ያልተገኘባትን ዕፀ በለስ ረግሟል፡፡ ሁለተኛ ወደ ቤተ መቅደስ ገብቶ የሚሸጡትን፣ የሚገዙትንና የሚለውጡትን አስወጥቷል፡፡ (ማቴ.21÷12-17፤ ማር.11÷17፤ ሉቃ.19÷45-46፡፡)



ወደ ቻናሉ ለመ🀄️🀄️ል፦ @Holy_scriptures
👍4
.       ──•◈•─────•◈•─
                          የዕለቱ ጥቅስ
        ──•◈•─────•◈•─
“ይህስ ስሜ የተጠራበት ቤት በዓይናችሁ የሌቦች ዋሻ ሆኖአልን? እነሆ፥ እኔ አይቻለሁ፥ ይላል እግዚአብሔር።”
ኤርምያስ 7፥11



ወደ ቻናሉ ለመ🀄️🀄️ል፦ @Holy_scriptures
8
#ሰኞ

👉 በለሷ የሚጠበቅባትን አልያዘችም (ከፍሬ ጎድላ ተገኝታለች)።
👉 ቤተመቅደሱ የማይጠበቅበትን ይዟል (ሻጭ፣ ገዢ እና ለዋጭ) ።

በቅዱስ ሉቃስ ወንጌል ላይ እንደተገለጸው ይህ ምሳሌ አለ "ለአንድ ሰው በወይኑ አትክልት የተተከለች በለስ ነበረችው ፍሬም ሊፈልግባት ወጥቶ ምንም አላገኘም፡፡" ሉቃ 13፥6 በማለት በበለስ ስለተመሰለ የሰው ልጅ ሕይወት በማሰብ እንዲመለስ ንስሐ እንዲገባ በሕይወትም እንዲኖር እግዚአብሔር ማሳሰቡን ይናገራል፡፡ ንስሐ አልገባም አልመለስም ያለም በለሷ እንደጠወለገችና እንደተቆረጠች ሁሉ ፍሬ ባለማፍራታቸው እንደሚቆረጡ እንዲሁም ወደ እሳት እንደሚጣሉ መጽሐፍ ቅዱስ በግልጽ ያስረዳል፡፡ ፍሬ አልባ እንዳንሆን ጌታ ሲመጣም እንዳናፍር የመጽሐፉን ቃል ልንጠብቅና ልንፈጽም ይገባናል፡፡ በዚህ የሕማማት የመጀመሪያ ቀን ዕለተ ሰኞ የምናስበው የምንዘክረው የሰው ልጅ ሕይወት በከንቱ በቸልተኝነት እንዳይደክም እንዳይጠወልግ፣ እንዳይደርቅ ወደ እሳትም እንዳይጣል ማድረግ ይገባናል፡፡ ለዚህም ፍቱን መፍትሄ የሚጠበቅብንን ፍሬ ማፍራት ነው። ፍሬ ማፍራት መብት ሳይሆን ግዴታ ነው!

ጌታችንና መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ወደ ቤተ መቅደስ ግብቶ ከበለሲቷ ተቃራኒ በሆነ ሁኔታ መቅደሱ ሞልቶ ነበር። በምን ከተባለ በጸሎት ሳይሆን በሽያጭ! የጸሎት ቤት መሆን ሲገባው የወንበዶች ዋሻ ነበር የሆነው። እና ጌታችን የቤቱ ቅናት ስለሚበላው እርምጃ ወሰደ። ማን ላይ?
👉የሚሸጥ (ማቴ.21፥12)
👉የሚገዛ [ብዙ ጊዜ ይህን "የሚገዙትን" የሚለውን አናስተውለውም] (ማቴ.21፥12)
👉የገንዘብ ለዋጮች (ማቴ.21፥12)

ዛሬ የእግዚአብሔር ቤተሰቦች ጌታችን ወደ መቅደስ ሕይወታችን ቢመጣ ምን ያገኝ ይሆን? በወንበዶች የታጨቀ መቅደስ ወይስ ፍሬ ማፍራት ሲገባው ያለ ፍሬ የከረመን በለስ? የእግዚአብሔር ቃል ግን ለንስሐ የሚገባ ፍሬ አድርጉ ይለናል። ማቴ 3፥8

ማቴዎስ 21
¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯
¹² ኢየሱስም ወደ መቅደስ ገባና በመቅደስ የሚሸጡትንና የሚገዙትን ሁሉ አወጣ፥ የገንዘብ ለዋጮችንም ገበታዎች የርግብ ሻጮችንም ወንበሮች ገለበጠና፦
¹³ ቤቴ የጸሎት ቤት ትባላለች ተብሎ ተጽፎአል፥ እናንተ ግን የወንበዶች ዋሻ አደረጋችኋት አላቸው።
¹⁴ በመቅደስም ዕውሮችና አንካሶች ወደ እርሱ ቀረቡና ፈወሳቸው።
¹⁵ ነገር ግን የካህናት አለቆችና ጻፎች ያደረገውን ድንቃ ድንቅ በመቅደስም፦ ሆሣዕና ለዳዊት ልጅ እያሉ የሚጮኹትን ልጆች ባዩ ጊዜ፥ ተቈጥተው፦
¹⁶ እነዚህ የሚሉትን አትሰማምን? አሉት። ኢየሱስም፦ እሰማለሁ፤ ከሕፃናትና ከሚጠቡት አፍ ምስጋናን ለራስህ አዘጋጀህ የሚለውን ቃል ከቶ አላነበባችሁምን? አላቸው።
¹⁷ ትቶአቸውም ከከተማ ወደ ቢታንያ ወጣ በዚያም አደረ።


ወደ ቻናሉ ለመ🀄️🀄️ል፦ @Holy_scriptures
👍64
Victorious Christian Life
Nigusse Denano
#መጻሕፍትን_በድምጽ

ርዕስ፦ አሸናፊው የክርስቲያን ኑሮ
የመጽሐፈ ኢያሱ ጥናት
ጸሐፊ፦ ዶ/ር አሳን ሬድፓዝ
ትርጉም፦ ዋቅጅራ ጎባ
ክፍል-15

ይቀጥላል...



ወደ ቻናሉ ለመ🀄️🀄️ል፦ @Holy_scriptures
2👍1
#ማክሰኞ ኢየሱስ ለመጨረሻ ጊዜ በቤተ መቅድስ ያስተማረበት ቀን ነው።

ጌታ ከቃሉ ስንት ጊዜ አስተማረን? ምን ያህልስ ወደ ተግባር ለወጥነው? ወይስ እንደ ፈሪሳውያን በራሱ መጽሐፍ ላይ ጌታችንን እየተከራከርነውና አልፎ ተርፎም ከሕይወታችን ልናስወጣው እየከጀልን ይሆን? የማንስ ጽሕፈት በላያችን ይታያል?



ወደ ቻናሉ ለመ🀄️🀄️ል፦ @Holy_scriptures
17👍1👏1
.       ──•◈•─────•◈•─
                          የዕለቱ ጥቅስ
        ──•◈•─────•◈•─
“ለሚወጣ ሁሉ በክርስቶስም ትምህርት ለማይኖር ሰው አምላክ የለውም፤ በክርስቶስ ትምህርት ለሚኖር አብና ወልድ አሉት።”
2ኛ ዮሐንስ 1፥9



ወደ ቻናሉ ለመ🀄️🀄️ል፦ @Holy_scriptures
👍5
#ማክሰኞ

ለመሆኑ ጌታችንና መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ምን አስተማረ? ወይም ምን ተማሩ አለ?

👉“እንግዲህ ከነዚህ ከሁሉ ካነሱት ትእዛዛት አንዲቱን የሚሽር ለሰውም እንዲሁ የሚያስተምር ማንም ሰው በመንግሥተ ሰማያት ከሁሉ ታናሽ ይባላል፤ የሚያደርግ ግን የሚያስተምርም ማንም ቢሆን እርሱ በመንግሥተ ሰማያት ታላቅ ይባላል።”
        ማቴዎስ 5፥19


👉“ነገር ግን ሄዳችሁ፦ ምሕረትን እወዳለሁ መሥዋዕትንም አይደለም ያለው ምን እንደ ሆነ ተማሩ፤ ኃጢአተኞችን ወደ ንስሐ እንጂ ጻድቃንን ልጠራ አልመጣሁምና አላቸው።”
ማቴዎስ 9፥13

👉“የሰው ልጅ ብዙ መከራ ሊቀበል፥ ከሽማግሌዎችም ከካህናት አለቆችም ከጻፎችም ሊጣል፥ ሊገደልም ከሦስት ቀንም በኋላ ሊነሣ እንዲገባው ያስተምራቸው ጀመር፤ ቃሉንም ገልጦ ይናገር ነበር።”
         ማርቆስ 8፥31

👉“ቀንበሬን በላያችሁ ተሸከሙ ከእኔም ተማሩ፥ እኔ የዋህ በልቤም ትሑት ነኝና፥ ለነፍሳችሁም ዕረፍት ታገኛላችሁ፤”
          ማቴዎስ 11፥29

👉“ሲያስተምርም እንዲህ አለ፦ ረጃጅም ልብስ ለብሰው መዞርን፥ በገበያም ሰላምታን፥ በምኵራብም የከበሬታን ወንበር፥ በግብርም የከበሬታን ስፍራ ከሚወዱ ከጻፎች ተጠበቁ፤”
         ማርቆስ 12፥38-39

👉“ምሳሌውንም ከበለስ ተማሩ፤ ጫፍዋ ሲለሰልስ ቅጠልዋም ሲያቈጠቍጥ፥ ያን ጊዜ በጋ እንደ ቀረበ ታውቃላችሁ፤”
ማቴዎስ 24፥32

👉 “እንግዲህ ሂዱና አሕዛብን ሁሉ በአብ በወልድና በመንፈስ ቅዱስ ስም እያጠመቃችኋቸው፥ ያዘዝኋችሁንም ሁሉ እንዲጠብቁ እያስተማራችኋቸው ደቀ መዛሙርት አድርጓቸው፤ እነሆም እኔ እስከ ዓለም ፍጻሜ ድረስ ሁልጊዜ ከእናንተ ጋር ነኝ።”
      ማቴዎስ 28፥19-20


👉“ኢየሱስም በእርሱ ያመኑትን አይሁድ እንዲህ አላቸው፤ “በትምህርቴ ብትጸኑ እናንተ በእውነት ደቀ መዛሙርቴ ናችሁ፤”
ዮሐንስ 8፥31 (አዲሱ መ.ት)



ወደ ቻናሉ ለመ🀄️🀄️ል፦ @Holy_scriptures
👍8
victorious christian life
Nigusse Denano
#መጻሕፍትን_በድምጽ

ርዕስ፦ አሸናፊው የክርስቲያን ኑሮ
የመጽሐፈ ኢያሱ ጥናት
ጸሐፊ፦ ዶ/ር አሳን ሬድፓዝ
ትርጉም፦ ዋቅጅራ ጎባ
ክፍል-16

ይቀጥላል...



ወደ ቻናሉ ለመ🀄️🀄️ል፦ @Holy_scriptures
ወደ ቻናሉ ለመ🀄️🀄️ል፦ @Holy_scriptures
4
ጥበቡ የምድረ በዳው እረኛ.pdf
9.9 MB
ርዕስ፦ ጥበቡ የምድረ በዳው እረኛ
የዶክተር ጥበቡ ኃይለሥላሴ የሕይወትና የአገልግሎት ታሪክ
ጸሐፊ፦ ሊሻን አጎናፍር
ኤዲተር፦ ወንድዬ ዓሊ

ወደ ቻናሉ ለመ🀄️🀄️ል፦ @Holy_scriptures
7👍2👏1
#ረቡዕ የአስቆሮቱ ይሁዳ ኢየሱስን የካደበት ቀንና ማርያም (በማርቆስ ስሟ አልተጠቀሰም) በኢየሱስ እግር ስር ሽቶ ያፈሰሰችበትና በጸጉሯ ያበሰችበት ቀን ነው።

“እርሱም በቢታንያ በለምጻሙ በስምዖን ቤት በነበረ ጊዜ፥ በማዕድ ተቀምጦ ሳለ፥ አንዲት ሴት ዋጋው እጅግ የከበረ ጥሩ ናርዶስ ሽቱ የመላበት የአልባስጥሮስ ቢልቃጥ ይዛ መጣች፤ ቢልቃጡንም ሰብራ በራሱ ላይ አፈሰሰችው።”
      (ማርቆስ 14፥3)



ወደ ቻናሉ ለመ🀄️🀄️ል፦ @Holy_scriptures
11👍2🔥2
.       ──•◈•─────•◈•─
                          የዕለቱ ጥቅስ
        ──•◈•─────•◈•─
“ስለዚህ እንደ ቆመ የሚመስለው እንዳይወድቅ ይጠንቀቅ።”
1ኛ ቆሮንቶስ 10፥12



ወደ ቻናሉ ለመ🀄️🀄️ል፦ @Holy_scriptures
7
#ረቡዕ የአስቆሮቱ ይሁዳ ኢየሱስን የካደበት ቀንና ማርያም (በማርቆስ ስሟ አልተጠቀሰም) በኢየሱስ እግር ስር ሽቶ ያፈሰሰችበትና በጸጉሯ ያበሰችበት ቀን ነው። (ማር. 14 ) በዚህ ቀን አንድ ነገር ማስተዋል አለብን ብዙ ጊዜ ከኢየሱስ ጋር የተጓዙ ሰዎች ትጥቃቸው መፈታት የጀመረበትና እውነተኛ ማንነታቸው የተገለጠበት ቀን ነበር። ከዚህ በፊት በርትተው ይጓዙ የነበሩ ሁሉ የሥጋ ድካም በብርቱ መገዳደር እና መጣል የጀመራቸው ጊዜ ነበር። አንዳዶች ወድቀው ሲነሱ አንዱ እስከወዲያኛው ወደቀ። በነገራችን ላይ የዚህን የሥጋን ከመንፈስ ጋር ለማበር መቸገር መፍትሄ ከአንድ ቀን በኋላ በጌቴሴማኒ ሹክ ብሏቸዋል። እንዲህ በማለት፦ “ወደ ፈተና እንዳትገቡ ትጉና ጸልዩ፤ መንፈስስ ተዘጋጅታለች ሥጋ ግን ደካማ ነው አለው።” (ማቴዎስ 26፥41)

ወደ ረቡዕ ቀን ስንመለስ ይሁዳ እንዲህ አይነት ሰው ነበር፦
"ይህንም የተናገረ ሌባ ስለ ነበረ ነው እንጂ ለድሆች ተገድዶላቸው አይደለም፤ ከረጢትም ይዞ በውስጡ ከሚገባው ይወስድ ስለ ነበረ ነው።" (ዮሐ. 12፡6) በሌላ በኩል ደግሞ በምን ሰዓት ምን ማድረግ እንዳለባት የምታውቅን ሴት እንመለከታለን። ኢየሱስ ከሞተ በኋላ ለአካሉ ሽቶ ለመቀባት አስበው የሄዱ ቢኖሩም ትንሣኤው ቀድሟቸው ሳይሳካላቸው ተመልሰዋል። መቅደላዊት ማርያም ግን መችና የት ኢየሱስን ማግኘት እንደሚቻል የምታውቅ ሴት ነበረች። እናም የዛሬው ቀን ከኢየሱስ ጋር ለዘለአለሙ ለመጓዝ ኃይል እንድናገኝ፣ ከእርሱ አሳብና አጀንዳ ጋር ደግሞ ተባብረን እንድንጓዝ ጌታ ይርዳን!

“እርሱም በቢታንያ በለምጻሙ በስምዖን ቤት በነበረ ጊዜ፥ በማዕድ ተቀምጦ ሳለ፥ አንዲት ሴት ዋጋው እጅግ የከበረ ጥሩ ናርዶስ ሽቱ የመላበት የአልባስጥሮስ ቢልቃጥ ይዛ መጣች፤ ቢልቃጡንም ሰብራ በራሱ ላይ አፈሰሰችው።”
ማርቆስ 14፥3

“ከአሥራ ሁለቱም አንዱ የአስቆሮቱ ይሁዳ አሳልፎ ሊሰጠው ወደ ካህናት አለቆች ሄደ።”
ማርቆስ 14፥10


ወደ ቻናሉ ለመ🀄️🀄️ል፦ @Holy_scriptures
7👍2
victorious christian life
Nigusse Denano
#መጻሕፍትን_በድምጽ

ርዕስ፦ አሸናፊው የክርስቲያን ኑሮ
የመጽሐፈ ኢያሱ ጥናት
ጸሐፊ፦ ዶ/ር አሳን ሬድፓዝ
ትርጉም፦ ዋቅጅራ ጎባ
ክፍል-17

ይቀጥላል...



ወደ ቻናሉ ለመ🀄️🀄️ል፦ @Holy_scriptures
#ሐሙስ ጌታችንና መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ከመሞቱ በፊት ከደቀ መዛሙርቱ ጋር የመጨረሻውን እራት የበላበትንና በእውነት ለእርሱ ተከታይ ለሆኑት ብርቱና መሰረታዊ ትምህርት፣ ምክር፣ ተግጻጽ ሲያስፈልግም በተግባር የተደገፈ ትምህርት ያስተላለፈበት እንዲሁም አሁን በመንግስቱ ላሉ በኋላም ለሚመጡ የጸለየው አስደናቂ ጸሎት የጸለየበት፣ የደቀ መዛሙርቱ ድካም. . . ወዘተ የሐሙስ ቀን ሁነቶች ናቸው። ሌላ የሚገርም ነገር ቢኖር ኢየሱስን ከመከራሁ እንዲቀርና እርሱን ለመርዳት ተማሪዎቹ በስጋ ቢጣጣሩም ፍቅራቸውን በመሃላ ለማጽናት ቢሞክሩም በኋላ እየሸሹና እየከዱ መገኘታቸው ነው። ለካ እውነተኛ ማንነት በወቅታዊ ስሜት ሳይሆን በፈተና ወቅት የሚገለጥ ነው! የዮሐንስ ወንጌልን ከምዕራፍ 13-18።

“እውነተኛ አምላክ ብቻ የሆንህ አንተን የላክኸውንም ኢየሱስ ክርስቶስን ያውቁ ዘንድ ይህች የዘላለም ሕይወት ናት።”
(ዮሐንስ 17፥3)

🔜 ስለጌታ እራት ዛሬ ይጠብቁን።



ወደ ቻናሉ ለመ🀄️🀄️ል፦ @Holy_scriptures
👍10🥰21
.       ──•◈•─────•◈•─
                          የዕለቱ ጥቅስ
        ──•◈•─────•◈•─
“ኢየሱስም ከፋሲካ በዓል በፊት፥ ከዚህ ዓለም ወደ አብ የሚሄድበት ሰዓት እንደ ደረሰ አውቆ፥ በዚህ ዓለም ያሉትን ወገኖቹን የወደዳቸውን እስከ መጨረሻ ወደዳቸው።”
ዮሐንስ 13፥1



ወደ ቻናሉ ለመ🀄️🀄️ል፦ @Holy_scriptures
👍32
ለክርስቲያኑ የጌታ እራት ትርጉሙ እንዴትነው? 


ሦስት የተያያዙ ሃሳቦች ለሃላፊ ጊዜ ፣ ለአሁን ጊዜና ለወደፊት ጊዜ ሊጠቅሙ የሚችሉ ሲሆኑ እነርሱም ተያይዘው ያሉና  የተገናኙም ናቸው::

#1ኛ  የጌታ እራት የጌታን መታሰቢያ ጊዜ የምናስታውስበት ነው ጌታም እንዲህ ሲል ትዕዛዝ ሰጥቷል<< Do this in remembrance of me  >> የሉቃስ ወንጌል 22፥19 ፤ 1ኛ ቆሮንቶስ 11፥24-25 ይህ ለመኖርያችን ዋጋ ለመክፈል በአዕምሮ ወይም በሥጋ የምንጨነቅበት ሳይሆን ግሩምና ድንቅ የሆነውን የጌታን የማዳን ሕይወትና አገልግሎት ለማስታወስ ነው ይህ የጌታ እራት ጥልቅ የሆነውን ምሥጋናና አድናቆት ኢየሱስ ክርስቶስ ለእኛ ስላደረገልን ለመግለጽ ትልቅ በዓል ወይንም በእንግሊዘኛው Occasion ነው::

በአይሁድ የፋሲካ እራት ጊዜ የዕብራውያን ከግብጽ ባርነት ነጻ መውጣት የታወጀ አንድ ደረጃም ወደፊት የሄደ ነበረ በዘጸአት 12፥26 እና 27 ላይ እንዲህ የሚል ቃል ተጽፎ እናገኛለን "እንዲህም ይሆናል፤ ልጆቻችሁ፦ ይህ አምልኮ ለእናንተ ምንድር ነው ?  ባሉአችሁ ጊዜ፥ እናንተ፦ በግብፅ አገር በእስራኤል ልጆች ቤቶች ላይ አልፎ ግብፃዊያንን በመታ ጊዜ፥ ቤቶቻችንን ያዳነ የእግዚአብሔር የማለፉ መሥዋዕት ይህች ናት ትሉአቸዋላችሁ::" ይለናል በመሆኑም በዚህ በአዲስ ኪዳኑየጌታ እራት ደግሞ ክርስቲያኑ ከኃጢአት ነጻ መውጣቱን ፣ ከሞት ሥቃይ መከራ በአካልና በአዕምሮም ሳይቀር ፋሲካችን በሆነው ክርስቶስ እንደገናም ነጻ መውጣቱንና መላቀቁንምጭምር ያውጃል(1ኛ ቆሮንቶስ 5 ፥ 7 ፤ 1ኛ ቆሮንቶስ 11 ፥ 26 )


#2ኛ  ሁለተኛው የጌታ እራት ጊዜ ፦ብርታት የማግኘት ፣ ጉልበት የማግኘት ፣ የመታደስ ጊዜ ፣ የመተሳሰርና የቁርባን ጊዜ  ነው:: እንደ ተሳትፎአችን መጠን የኢየሱስ ሞትና ትንሣኤ ትርፉ ሕይወትን መስጠት ነው( ሮሜ 5 ፥ 10 ፤ 1ኛ ቆሮንቶስ 10 ፥ 16 ) ስለዚህ በክርስቶስ ትንሣኤ ባለ መንፈስ ውስጥ ሥልጣንን አግኝተን እንመገባለን እናድጋለን:: ጆን ዊስሊ ይህንን ጥንካሬ ያውቃል በአማካኝ በየአራት ወይም አምስት ቀን በረጅም ጊዜና ፍሬያማ ሥራው ወይንም የሕይወት ታሪኩ ቁርባኑን ይወስዳል:: 


#3ኛ ሦስተኛውና የመጨረሻው የጌታ እራት ጊዜ ቃልኪዳንን የማደስ እና ተስፋ የማድረግ ጊዜ ነው ነገር ግን ራሳችንን ቃል በቃል ማረጋገጥና የጥራት ሙከራ ወይንም ፈተና ማድረግ አለብን የጌታን እራት ተካፍለን የምንበላበት አኳኋን ዋጋ ያለውነው( 1ኛ ቆሮንቶስ 11 ፥ 28 እና 29 ) እንደገናም የእርሱ ሕዝቦች ሙሉ በሆነ የመታደስ ተስፋ ለክርስቶስ የተሰጠንበትን እናድሳለን እርሱ እስኪመጣ ድረስ ( 1ኛ ቆሮንቶስ 11 ፥ 26 ) ክርስቶስ ከተመለሰ በኋላ በእርሱ መንግሥት ውስጥ በእርሱ አካላዊ መገኘት ከእርሱ ጋር ተካፍለን እንበላለን ( የማቴዎስ ወንጌል 26 ፥ 29 )


ምንጭ:- yonasgetaneh.blogspot.com



ወደ ቻናሉ ለመ🀄️🀄️ል፦ @Holy_scriptures
5👍4
victorious christian life
Nigusse Denano
#መጻሕፍትን_በድምጽ

ርዕስ፦ አሸናፊው የክርስቲያን ኑሮ
የመጽሐፈ ኢያሱ ጥናት
ጸሐፊ፦ ዶ/ር አሳን ሬድፓዝ
ትርጉም፦ ዋቅጅራ ጎባ
ክፍል-18

ይቀጥላል...



ወደ ቻናሉ ለመ🀄️🀄️ል፦ @Holy_scriptures
1👍1
#የእግዚአብሔር_ቃል_ምን_ይላል?


ዮሐንስ 17
¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯
¹-² ኢየሱስም ይህን ተናግሮ ወደ ሰማይ ዓይኖቹን አነሣና እንዲህ አለ፦ አባት ሆይ፥ ሰዓቱ ደርሶአል፤ ልጅህ ያከብርህ ዘንድ፥ በሥጋም ሁሉ ላይ ሥልጣን እንደ ሰጠኸው፥ ለሰጠኸው ሁሉ የዘላለምን ሕይወት ይሰጣቸው ዘንድ ልጅህን አክብረው።
³ እውነተኛ አምላክ ብቻ የሆንህ አንተን የላክኸውንም ኢየሱስ ክርስቶስን ያውቁ ዘንድ ይህች የዘላለም ሕይወት ናት።
⁴ እኔ ላደርገው የሰጠኸኝን ሥራ ፈጽሜ በምድር አከበርሁህ፤
⁵ አሁንም፥ አባት ሆይ፥ ዓለም ሳይፈጠር በአንተ ዘንድ በነበረኝ ክብር አንተ በራስህ ዘንድ አክብረኝ።
⁶ ከዓለም ለሰጠኸኝ ሰዎች ስምህን ገለጥሁላቸው። የአንተ ነበሩ ለእኔም ሰጠሃቸው፤ ቃልህንም ጠብቀዋል።
⁷ የሰጠኸኝ ሁሉ ከአንተ እንደ ሆነ አሁን ያውቃሉ፤
⁸ የሰጠኸኝን ቃል ሰጥቻቸዋለሁና፤ እነርሱም ተቀበሉት፥ ከአንተም ዘንድ እንደ ወጣሁ በእውነት አወቁ፥ አንተም እንደ ላክኸኝ አመኑ።
⁹ እኔ ስለ እነዚህ እለምናለሁ፤ ስለ ዓለም አልለምንም ስለ ሰጠኸኝ እንጂ፤ የአንተ ናቸውና፤
¹⁰ የእኔም የሆነ ሁሉ የአንተ ነው የአንተውም የእኔ ነው፤ እኔም ስለ እነርሱ ከብሬአለሁ።
¹¹ ከዚህም በኋላ በዓለም አይደለሁም፥ እነርሱም በዓለም ናቸው፥ እኔም ወደ አንተ እመጣለሁ። ቅዱስ አባት ሆይ፥ እነዚህን የሰጠኸኝን እንደ እኛ አንድ እንዲሆኑ በስምህ ጠብቃቸው።
¹² ከእነርሱ ጋር በዓለም ሳለሁ የሰጠኸኝን በስምህ እኔ እጠብቃቸው ነበር፤ ጠበቅኋቸውም መጽሐፉም እንዲፈጸም ከጥፋት ልጅ በቀር ከእነርሱ ማንም አልጠፋም።
¹³ አሁንም ወደ አንተ እመጣለሁ፤ በእነርሱም ዘንድ ደስታዬ የተፈጸመ እንዲሆንላቸው ይህን በዓለም እናገራለሁ።
¹⁴ እኔ ቃልህን ሰጥቻቸዋለሁ፤ እኔም ከዓለም እንዳይደለሁ ከዓለም አይደሉምና ዓለም ጠላቸው።
¹⁵ ከክፉ እንድትጠብቃቸው እንጂ ከዓለም እንድታወጣቸው አልለምንም።
¹⁶ እኔ ከዓለም እንዳይደለሁ ከዓለም አይደሉም።
¹⁷ በእውነትህ ቀድሳቸው፤ ቃልህ እውነት ነው።
¹⁸ ወደ ዓለም እንደ ላክኸኝ እንዲሁ እኔ ወደ ዓለም ላክኋቸው፤
¹⁹ እነርሱም ደግሞ በእውነት የተቀደሱ እንዲሆኑ እኔ ራሴን ስለ እነርሱ እቀድሳለሁ።
²⁰-²¹ ሁሉም አንድ ይሆኑ ዘንድ፥ ከቃላቸው የተነሣ በእኔ ስለሚያምኑ ደግሞ እንጂ ስለ እነዚህ ብቻ አልለምንም፤ አንተ እንደ ላክኸኝ ዓለም ያምን ዘንድ፥ አንተ፥ አባት ሆይ፥ በእኔ እንዳለህ እኔም በአንተ፥ እነርሱ ደግሞ በእኛ አንድ ይሆኑ ዘንድ እለምናለሁ።
²²-²³ እኛም አንድ እንደ ሆንን አንድ ይሆኑ ዘንድ፤ እኔም በእነርሱ አንተም በእኔ ስትሆን፥ በአንድ ፍጹማን እንዲሆኑ፥ የሰጠኸኝን ክብር እኔ ሰጥቻቸዋለሁ፤ እንዲሁም ዓለም አንተ እንደ ላክኸኝ በወደድኸኝም መጠን እነርሱን እንደ ወደድሃቸው ያውቃል።
²⁴ አባት ሆይ፥ ዓለም ሳይፈጠር ስለ ወደድኸኝ የሰጠኸኝን ክብሬን እንዲያዩ እኔ ባለሁበት የሰጠኸኝ እነርሱ ደግሞ ከእኔ ጋር ይሆኑ ዘንድ እወዳለሁ።
²⁵ ጻድቅ አባት ሆይ፥ ዓለም አላወቀህም፥ እኔ ግን አወቅሁህ እነዚህም አንተ እንደ ላክኸኝ አወቁ፤
²⁶ እኔንም የወደድህባት ፍቅር በእነርሱ እንድትሆን እኔም በእነርሱ፥ ስምህን አስታወቅኋቸው አስታውቃቸውማለሁ።




ወደ ቻናሉ ለመ🀄️🀄️ል፦ @Holy_scriptures
👍8
#አርብ ፀሐይ ብርሃኗን የከለከለችበት፣ እግዚኣብሔር ለኃጢኣት ያለውን ታላቅ ቁጣ በብርቱ የገለጠበት፣ በሌላ በኩል ሰማይ ከምድር እንዲታረቅ፣ በሰው መካከል ልዩነት እንዳይኖር የጥል ግድግዳ እንዲፈርስ የመጨረሻ ዋጋ የተከፈለበት፣ እግዚአብሔር ሰውን እንደሚወድ በደም እየጻፈ ያስረዳበት፣ በዓለም የሃይማኖት ይሁን በሌላው ታሪክ በማይታወቅ መልኩ አምላክ(የሚመለከው) እንዲያመልኩት ለተጠሩት ሰዎች የሞተበት፣ የተሰዋበት፣ መዳናቸውን ለመፈጸም የተዋረደበት ቃላት ሊገልጡት የማይችሉት ፍቅር የተብራራበት ቀን ነው። ካህን ሞተ! ካህን ደም ይዞ ገባ! ካህን አዳነን! የአለምን የጊዜ አቆጣጠር/ ስርዓት ከዓመተ ዓለም ወደ ዓመተ ምሕረት የተለወጠበት የዓለም ዳግመኛ የውልደት ቀንም ነው። የዓለማችን ታላቁ አዋጅ "τελέω"/ "ተፈፀመ" የታወጀበትም ነው።

የአምላክ የናዝሬቱ ኢየሱስ ጣር የበዛበት የሰው ፌዝና ዛቻ እንዲሁም አለማወቅ የበረታበት አስጨናቂም ቀን ነው አርብ።

"ኢየሱስም ሆምጣጤውን ከተቀበለ በኋላ። ተፈጸመ አለ፥ ራሱንም አዘንብሎ ነፍሱን አሳልፎ ሰጠ።" (ዮሐ. 19፡30)

🔜 ለመሆኑ ኢየሱስ ይህን ታላቅ ስቃይ
ተሸክሞ ለምን ሞተ? በቀጣይ
ጹሑፍ ይህንን እንመለከታለን።



ወደ ቻናሉ ለመ🀄️🀄️ል፦ @Holy_scriptures
13👍3
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
ወደ ቻናሉ ለመ🀄️🀄️ል፦ @Holy_scriptures
5👍1👎1