. ──•◈•─────•◈•─
የዕለቱ ጥቅስ
──•◈•─────•◈•─
“የዘንባባ ዛፍ ዝንጣፊ ይዘው ሊቀበሉት ወጡና፦ ሆሣዕና፤ በጌታ ስም የሚመጣ የእስራኤል ንጉሥ የተባረከ ነው እያሉ ጮኹ።”
ዮሐንስ 12፥13
ወደ ቻናሉ ለመ🀄️ላ🀄️ል፦ @Holy_scriptures

❤2
#ሆሣዕና
"ሆሣዕና በአርያም እያሉ ይጮኹ ነበር"
ማቴ ፳፩፥፱
🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿
ዛሬ "ሆሳዕና" ነው:: ለትንሣኤ በዓል አንድ ሳምንት ቀረው::
#ሆሳዕና ቃሉ ከሁለት አረማይክ ቃላት የተሰራ ሲሆን ትርጉም «እባክህ እርዳ፣ አሁን አድን» ማለት ነው። እብራይስጡም ይህንኑ ቃል ወርሶ «הושענא » ሆሻአና ሲል ይገኛል። አዎ «አሁን አድን፣ እባክህ እርዳን» ብሎ የአዳም ዘር ያጣውን ልጅነትና የደረሰበትን ሞት ለመላቀቅ የሚያሰማው የጩኸት ድምጽ ነው፣ «ሆሳዕና»!!!
ዳዊት ነቢይ በመንፈስ ቅዱስ ተመልክቶ ማዳኑን ሲጣራና አሁን ናልን ሲል ከዘመናት በፊት አድምጠነዋል። የውስጥ ዓይኖቹ ሩቅ አይተዋል። ማዳኑንም ሽተው እንዲህ ሲል ዘምሮለታል።
«አቤቱ፥ እባክህ፥ አሁን አድን አቤቱ፥ እባክህ፥ አሁን አቅና» መዝ ፻፲፰፥፳፭
አዎ፣ ንጉሥ ክርስቶስ ከዘጠና ዘጠኙ በጎች መካከል የጠፋውን አንዱን በግ ፍለጋ ንጉሥ ሆኖ ሳለ እንደንጉሥ ያይደለ በአህያ፣ ለዚያውም በውርንጫ ተቀምጦ «የአሁን አድን (ሆሳዕና)» ጩኸት ሊመልስ በጽዮን ከተማ ይመጣል፤ ይህንንም ዘካርያስ ከዘመረው ዘመናት ተቆጥረው ነበር።
«አንቺ የጽዮን ልጅ ሆይ፥ እጅግ ደስ ይበልሽ አንቺ የኢየሩሳሌም ልጅ ሆይ፥ እልል በዪ እነሆ፥ ንጉሥሽ ጻድቅና አዳኝ ነው ትሑትም ሆኖ በአህያም፥ በአህያይቱ ግልገል በውርጫይቱ ላይ ተቀምጦ ወደ አንቺ ይመጣል» ዘካ ፱፥፱
ሰማያዊ ንጉሥ ክርስቶስ ከቅድስት ድንግል ማርያም ያለዘርዓ ብእሲ ከስጋችን ተዛምዶ ማዳኑን ሲጠብቁ፤ ከሩቅ አይተው ሲጣሩ፣ ሲዘምሩለትና አንድ ቀን ማዳኑ እንደሚሆን ተስፋ ሲያደርጉት የነበረው ሰዓቱ ደርሶ በመካከላቸው ሲገኝ ይጠብቁት የነበረው ዓይነት ሳይሆን ውበት የሌለውን ንጉሥ ለመቀበል የገዛ ወገኖቹ ተቸግረው ነበር።
አዎ፣ የደም ግባት ብቻ ሳይሆን የንጉሥ ወግ የሌለው፣ በአህያ ለዚያውም በውርንጫ የሚመጣ ንጉሥ እንዴት ይቀበሉት?
አባቶቻቸው ለዘመናት «ሆሳዕና፣ ማዳንህ አሁን ይሁን» ያሉለትና የዘመሩለት በዕለተ ቀጠሮው ማዳኑን ሊያሳይ ከጽዮን ደጃፍ ቀርቦ ሳለ የማያውቁት፣ ያልሰሙት፣ ትንቢቱን ያላነበቡት «ሆሳዕና» ሲሉ ትልልቆቹ ዕብራውያን ግን ዝም አሉ፣ ዝም በሉም አሉ!
«ነገር ግን የካህናት አለቆችና ጻፎች ያደረገውን ድንቃ ድንቅ በመቅደስም፣ ሆሣዕና ለዳዊት ልጅ እያሉ የሚጮኹትን ልጆች ባዩ ጊዜ፥ ተቈጥተው፣ እነዚህ የሚሉትን አትሰማምን? አሉት»
የማዳኑ ጌታም፣
«እሰማለሁ፤ ከሕፃናትና ከሚጠቡት አፍ ምስጋናን ለራስህ አዘጋጀህ የሚለውን ቃል ከቶ አላነበባችሁምን? አላቸው» ማቴ ፳፩፥፲፭-፲፮
ኢየሱስ ክርስቶስ የእነዚህን ሕፃናት ዝማሬና ምስጋናን የሰማው ከቤተ ፋጌ ወደ ኢየሩሳሌም ማዳኑን ሊፈጽም በመጣ ጊዜ ነበር። ቤተ ፋጌ ከኢየሩሳሌም ከተማ ምሥራቃዊ አቅጣጫ በቢታንያና በደብረ ዘይት ተራራ መካከል የምትገኝ መንደር ነበረች።
ጌታ ኢየሱስም ከኢያሪኰ ከተማ ወደኢየሩሳሌም ሲወጣ ካረፈባት ከቤተ ፋጌ መንደር ሁለቱን ደቀ መዛሙርት ልኰ ውርንጫይቱን ከታሰረችበት ፈትተው እንዲያመጡለት አዟል።
«ወደ ኢየሩሳሌምም ቀርበው ወደ ደብረ ዘይት ወደ ቤተ ፋጌ ሲደርሱ፥ ያንጊዜ ኢየሱስ ከደቀ መዛሙርቱ ሁለት ላከ፥ እንዲህም አላቸው፦ በፊታችሁ ወዳለችው መንደር ሂዱ፥ በዚያን ጊዜም የታሰረችን አህያ ውርንጫም ከእርስዋ ጋር ታገኛላችሁ፤ ፈትታችሁ አምጡልኝ» ማቴ ፳፩፥፪
ያን ጊዜም በቀደምት አበው የተነገረው ትንቢትና ዝማሬ ፍጻሜ አገኘ ማለት ነው።
«የሚቀድሙትም ሕዝብ የሚከተሉትም። ሆሣዕና ለዳዊት ልጅ በጌታ ስም የሚመጣ የተባረከ ነው፤ ሆሣዕና በአርያም እያሉ ይጮኹ ነበር» ማቴ ፳፩፥፱
ይሁን እንጂ ኢየሩሳሌም ለሆሳዕና አልተዘጋጀችም ነበር። ይልቁንም ቤተ መቅደሱ አካባቢ ስለማዳኑ ዝማሬ በማቅረብ ፋንታ የጦፈ የንግድ ገበያ ደርቶበት ነበር። ቤተመቅደሱ የጸሎት ሥፍራ መሆኑ ቀርቶ የሻጮችና የለዋጮች መድረክ ሆኖ ነበር። ያኔ ማዳኑ የቀረበላት ኢየሩሳሌም በመቅደሱ በራፍ ስትሸጥ፣ ስትለውጥ መድኃኒቱን ሆሳዕና እያለች መቀበልን እንዳልቻለች ሁሉ የዛሬዋ ቤተክርስቲያንስ ንግድና ሸቀጥ የሌለበትን «ሆሳዕና» እያከበረች ነው ወይ? ብለን ብንጠይቅ ራስን ማታለል ካልተጨመረበት በስተቀር፣ መሸጥ መሸቀጡ የሌለበትን «ሆሳዕና» የሚያከብር የለም ነው መልሱ። ዐውደ ምሕረቱ ሱቅ በደረቴ ያልሆነበትን ሥፍራ ማግኘት ከባድ ነው።
ኢየሱስ ማዳኑን ከመፈጸሙ በፊት እነዚህን ነጋዴዎች አስወግዷል። ገበታቸውን ገልብጧል። እየገረፈ አስወጥቷል። የወንበዴዎች ዋሻ የሆነውን የጸሎት ቤት ጠራርጓል። ዛሬስ ቤቱ ስንት ወንበዴ መሽጎበት ይሆን? ወንበዴዎቹ ይዘምራሉ፣ ሆሳዕና ይላሉ፣ የዘንባባ ዝንጣፊ ይይዛሉ፣ በጣታቸው፣ በግንባራቸው ያስራሉ። ወንበዴዎች ናቸው ተብለው እንዳይርቋቸው የአምልኰ መልክ አላቸው። ቤተመቅደሱን የወንበዴዎች ዋሻ አደረጋችሁ ያለው በግብር ውንብድና በመልክ ግን አገልጋይ ይመስሉ የነበሩትን የመቅደሱን ሰዎች ነበር። ዛሬም እንደዚያው!!
በእድሜአችን ስንት «ሆሳዕና በአርያም» አሳለፍን? ማዳኑ በተደረገለት ማንነታችን ውስጥ ስንት ፍሬ አፈራን? የተራበው ኢየሱስ ከእኛ የሚፈልገውን ፍሬ ይዘናል? ወይስ ፍሬ አልባ ሆነን ለቁጣ የተዘጋጀን እንሆን? «ሆሳዕና በአርያም» ማለቱ ብቻውን አያድንም፣ ማዳኑንም አያመጣም። የወንበዴ ዋሻ ማንነታችንን እናጽዳ። ከዚህ ዓለም ሽቃጭና ልዋጭ ማስመሰያ ማንነት እንውጣ! በጎ ፍሬ እንዲያፈራ ለተላከው የወይኑ ባለቤት ወራሽ እንገዛ! ያኔ «ሆሳዕና በአርያም» ስንል ማዳኑ ፈጥኖ ይሆንልናል።
አዎ ሆሳዕና በአርያም! በዚህም በወዲያኛውም! ሆሳዕና በአርያም።ሃሌ ሉያ!!!!!!!!
ምንጭ:- ደጀ ብርሃን

🔥6👍5
Victorious Christian life
Nigusse Denano
#መጻሕፍትን_በድምጽ
ርዕስ፦ አሸናፊው የክርስቲያን ኑሮ
የመጽሐፈ ኢያሱ ጥናት
ጸሐፊ፦ ዶ/ር አሳን ሬድፓዝ
ትርጉም፦ ዋቅጅራ ጎባ
ክፍል-14
ይቀጥላል...
ወደ ቻናሉ ለመ🀄️ላ🀄️ል፦ @Holy_scriptures
ርዕስ፦ አሸናፊው የክርስቲያን ኑሮ
የመጽሐፈ ኢያሱ ጥናት
ጸሐፊ፦ ዶ/ር አሳን ሬድፓዝ
ትርጉም፦ ዋቅጅራ ጎባ
ክፍል-14
ይቀጥላል...
ወደ ቻናሉ ለመ🀄️ላ🀄️ል፦ @Holy_scriptures
👍2❤1
#ሰኞ፣ ከሆሣዕና ማግሥት ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ከቢታንያ ወደ ኢየሩሳሌም ሲገባ ሁለት ነገሮችን አድርጓል፡፡ አንደኛ ከቅጠል በስተቀር ፍሬ ያልተገኘባትን ዕፀ በለስ ረግሟል፡፡ ሁለተኛ ወደ ቤተ መቅደስ ገብቶ የሚሸጡትን፣ የሚገዙትንና የሚለውጡትን አስወጥቷል፡፡ (ማቴ.21÷12-17፤ ማር.11÷17፤ ሉቃ.19÷45-46፡፡)
ወደ ቻናሉ ለመ🀄️ላ🀄️ል፦ @Holy_scriptures
ወደ ቻናሉ ለመ🀄️ላ🀄️ል፦ @Holy_scriptures
👍4
. ──•◈•─────•◈•─
የዕለቱ ጥቅስ
──•◈•─────•◈•─
“ይህስ ስሜ የተጠራበት ቤት በዓይናችሁ የሌቦች ዋሻ ሆኖአልን? እነሆ፥ እኔ አይቻለሁ፥ ይላል እግዚአብሔር።”
ኤርምያስ 7፥11

❤8
#ሰኞ
👉 በለሷ የሚጠበቅባትን አልያዘችም (ከፍሬ ጎድላ ተገኝታለች)።
👉 ቤተመቅደሱ የማይጠበቅበትን ይዟል (ሻጭ፣ ገዢ እና ለዋጭ) ።
በቅዱስ ሉቃስ ወንጌል ላይ እንደተገለጸው ይህ ምሳሌ አለ "ለአንድ ሰው በወይኑ አትክልት የተተከለች በለስ ነበረችው ፍሬም ሊፈልግባት ወጥቶ ምንም አላገኘም፡፡" ሉቃ 13፥6 በማለት በበለስ ስለተመሰለ የሰው ልጅ ሕይወት በማሰብ እንዲመለስ ንስሐ እንዲገባ በሕይወትም እንዲኖር እግዚአብሔር ማሳሰቡን ይናገራል፡፡ ንስሐ አልገባም አልመለስም ያለም በለሷ እንደጠወለገችና እንደተቆረጠች ሁሉ ፍሬ ባለማፍራታቸው እንደሚቆረጡ እንዲሁም ወደ እሳት እንደሚጣሉ መጽሐፍ ቅዱስ በግልጽ ያስረዳል፡፡ ፍሬ አልባ እንዳንሆን ጌታ ሲመጣም እንዳናፍር የመጽሐፉን ቃል ልንጠብቅና ልንፈጽም ይገባናል፡፡ በዚህ የሕማማት የመጀመሪያ ቀን ዕለተ ሰኞ የምናስበው የምንዘክረው የሰው ልጅ ሕይወት በከንቱ በቸልተኝነት እንዳይደክም እንዳይጠወልግ፣ እንዳይደርቅ ወደ እሳትም እንዳይጣል ማድረግ ይገባናል፡፡ ለዚህም ፍቱን መፍትሄ የሚጠበቅብንን ፍሬ ማፍራት ነው። ፍሬ ማፍራት መብት ሳይሆን ግዴታ ነው!
ጌታችንና መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ወደ ቤተ መቅደስ ግብቶ ከበለሲቷ ተቃራኒ በሆነ ሁኔታ መቅደሱ ሞልቶ ነበር። በምን ከተባለ በጸሎት ሳይሆን በሽያጭ! የጸሎት ቤት መሆን ሲገባው የወንበዶች ዋሻ ነበር የሆነው። እና ጌታችን የቤቱ ቅናት ስለሚበላው እርምጃ ወሰደ። ማን ላይ?
👉የሚሸጥ (ማቴ.21፥12)
👉የሚገዛ [ብዙ ጊዜ ይህን "የሚገዙትን" የሚለውን አናስተውለውም] (ማቴ.21፥12)
👉የገንዘብ ለዋጮች (ማቴ.21፥12)
ዛሬ የእግዚአብሔር ቤተሰቦች ጌታችን ወደ መቅደስ ሕይወታችን ቢመጣ ምን ያገኝ ይሆን? በወንበዶች የታጨቀ መቅደስ ወይስ ፍሬ ማፍራት ሲገባው ያለ ፍሬ የከረመን በለስ? የእግዚአብሔር ቃል ግን ለንስሐ የሚገባ ፍሬ አድርጉ ይለናል። ማቴ 3፥8
ማቴዎስ 21
¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯
¹² ኢየሱስም ወደ መቅደስ ገባና በመቅደስ የሚሸጡትንና የሚገዙትን ሁሉ አወጣ፥ የገንዘብ ለዋጮችንም ገበታዎች የርግብ ሻጮችንም ወንበሮች ገለበጠና፦
¹³ ቤቴ የጸሎት ቤት ትባላለች ተብሎ ተጽፎአል፥ እናንተ ግን የወንበዶች ዋሻ አደረጋችኋት አላቸው።
¹⁴ በመቅደስም ዕውሮችና አንካሶች ወደ እርሱ ቀረቡና ፈወሳቸው።
¹⁵ ነገር ግን የካህናት አለቆችና ጻፎች ያደረገውን ድንቃ ድንቅ በመቅደስም፦ ሆሣዕና ለዳዊት ልጅ እያሉ የሚጮኹትን ልጆች ባዩ ጊዜ፥ ተቈጥተው፦
¹⁶ እነዚህ የሚሉትን አትሰማምን? አሉት። ኢየሱስም፦ እሰማለሁ፤ ከሕፃናትና ከሚጠቡት አፍ ምስጋናን ለራስህ አዘጋጀህ የሚለውን ቃል ከቶ አላነበባችሁምን? አላቸው።
¹⁷ ትቶአቸውም ከከተማ ወደ ቢታንያ ወጣ በዚያም አደረ።

👍6❤4
Victorious Christian Life
Nigusse Denano
#መጻሕፍትን_በድምጽ
ርዕስ፦ አሸናፊው የክርስቲያን ኑሮ
የመጽሐፈ ኢያሱ ጥናት
ጸሐፊ፦ ዶ/ር አሳን ሬድፓዝ
ትርጉም፦ ዋቅጅራ ጎባ
ክፍል-15
ይቀጥላል...
ወደ ቻናሉ ለመ🀄️ላ🀄️ል፦ @Holy_scriptures
ርዕስ፦ አሸናፊው የክርስቲያን ኑሮ
የመጽሐፈ ኢያሱ ጥናት
ጸሐፊ፦ ዶ/ር አሳን ሬድፓዝ
ትርጉም፦ ዋቅጅራ ጎባ
ክፍል-15
ይቀጥላል...
ወደ ቻናሉ ለመ🀄️ላ🀄️ል፦ @Holy_scriptures
❤2👍1
#ማክሰኞ ኢየሱስ ለመጨረሻ ጊዜ በቤተ መቅድስ ያስተማረበት ቀን ነው።
ጌታ ከቃሉ ስንት ጊዜ አስተማረን? ምን ያህልስ ወደ ተግባር ለወጥነው? ወይስ እንደ ፈሪሳውያን በራሱ መጽሐፍ ላይ ጌታችንን እየተከራከርነውና አልፎ ተርፎም ከሕይወታችን ልናስወጣው እየከጀልን ይሆን? የማንስ ጽሕፈት በላያችን ይታያል?
ወደ ቻናሉ ለመ🀄️ላ🀄️ል፦ @Holy_scriptures
ጌታ ከቃሉ ስንት ጊዜ አስተማረን? ምን ያህልስ ወደ ተግባር ለወጥነው? ወይስ እንደ ፈሪሳውያን በራሱ መጽሐፍ ላይ ጌታችንን እየተከራከርነውና አልፎ ተርፎም ከሕይወታችን ልናስወጣው እየከጀልን ይሆን? የማንስ ጽሕፈት በላያችን ይታያል?
ወደ ቻናሉ ለመ🀄️ላ🀄️ል፦ @Holy_scriptures
❤17👍1👏1
. ──•◈•─────•◈•─
የዕለቱ ጥቅስ
──•◈•─────•◈•─
“ለሚወጣ ሁሉ በክርስቶስም ትምህርት ለማይኖር ሰው አምላክ የለውም፤ በክርስቶስ ትምህርት ለሚኖር አብና ወልድ አሉት።”
2ኛ ዮሐንስ 1፥9

👍5
#ማክሰኞ
ለመሆኑ ጌታችንና መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ምን አስተማረ? ወይም ምን ተማሩ አለ?
👉“እንግዲህ ከነዚህ ከሁሉ ካነሱት ትእዛዛት አንዲቱን የሚሽር ለሰውም እንዲሁ የሚያስተምር ማንም ሰው በመንግሥተ ሰማያት ከሁሉ ታናሽ ይባላል፤ የሚያደርግ ግን የሚያስተምርም ማንም ቢሆን እርሱ በመንግሥተ ሰማያት ታላቅ ይባላል።”
ማቴዎስ 5፥19
👉“ነገር ግን ሄዳችሁ፦ ምሕረትን እወዳለሁ መሥዋዕትንም አይደለም ያለው ምን እንደ ሆነ ተማሩ፤ ኃጢአተኞችን ወደ ንስሐ እንጂ ጻድቃንን ልጠራ አልመጣሁምና አላቸው።”
ማቴዎስ 9፥13
👉“የሰው ልጅ ብዙ መከራ ሊቀበል፥ ከሽማግሌዎችም ከካህናት አለቆችም ከጻፎችም ሊጣል፥ ሊገደልም ከሦስት ቀንም በኋላ ሊነሣ እንዲገባው ያስተምራቸው ጀመር፤ ቃሉንም ገልጦ ይናገር ነበር።”
ማርቆስ 8፥31
👉“ቀንበሬን በላያችሁ ተሸከሙ ከእኔም ተማሩ፥ እኔ የዋህ በልቤም ትሑት ነኝና፥ ለነፍሳችሁም ዕረፍት ታገኛላችሁ፤”
ማቴዎስ 11፥29
👉“ሲያስተምርም እንዲህ አለ፦ ረጃጅም ልብስ ለብሰው መዞርን፥ በገበያም ሰላምታን፥ በምኵራብም የከበሬታን ወንበር፥ በግብርም የከበሬታን ስፍራ ከሚወዱ ከጻፎች ተጠበቁ፤”
ማርቆስ 12፥38-39
👉“ምሳሌውንም ከበለስ ተማሩ፤ ጫፍዋ ሲለሰልስ ቅጠልዋም ሲያቈጠቍጥ፥ ያን ጊዜ በጋ እንደ ቀረበ ታውቃላችሁ፤”
ማቴዎስ 24፥32
👉 “እንግዲህ ሂዱና አሕዛብን ሁሉ በአብ በወልድና በመንፈስ ቅዱስ ስም እያጠመቃችኋቸው፥ ያዘዝኋችሁንም ሁሉ እንዲጠብቁ እያስተማራችኋቸው ደቀ መዛሙርት አድርጓቸው፤ እነሆም እኔ እስከ ዓለም ፍጻሜ ድረስ ሁልጊዜ ከእናንተ ጋር ነኝ።”
ማቴዎስ 28፥19-20
👉“ኢየሱስም በእርሱ ያመኑትን አይሁድ እንዲህ አላቸው፤ “በትምህርቴ ብትጸኑ እናንተ በእውነት ደቀ መዛሙርቴ ናችሁ፤”
ዮሐንስ 8፥31 (አዲሱ መ.ት)

👍8
victorious christian life
Nigusse Denano
#መጻሕፍትን_በድምጽ
ርዕስ፦ አሸናፊው የክርስቲያን ኑሮ
የመጽሐፈ ኢያሱ ጥናት
ጸሐፊ፦ ዶ/ር አሳን ሬድፓዝ
ትርጉም፦ ዋቅጅራ ጎባ
ክፍል-16
ይቀጥላል...
ወደ ቻናሉ ለመ🀄️ላ🀄️ል፦ @Holy_scriptures
ርዕስ፦ አሸናፊው የክርስቲያን ኑሮ
የመጽሐፈ ኢያሱ ጥናት
ጸሐፊ፦ ዶ/ር አሳን ሬድፓዝ
ትርጉም፦ ዋቅጅራ ጎባ
ክፍል-16
ይቀጥላል...
ወደ ቻናሉ ለመ🀄️ላ🀄️ል፦ @Holy_scriptures
ጥበቡ የምድረ በዳው እረኛ.pdf
9.9 MB
ርዕስ፦ ጥበቡ የምድረ በዳው እረኛ
የዶክተር ጥበቡ ኃይለሥላሴ የሕይወትና የአገልግሎት ታሪክ
ጸሐፊ፦ ሊሻን አጎናፍር
ኤዲተር፦ ወንድዬ ዓሊ
ወደ ቻናሉ ለመ🀄️ላ🀄️ል፦ @Holy_scriptures
የዶክተር ጥበቡ ኃይለሥላሴ የሕይወትና የአገልግሎት ታሪክ
ጸሐፊ፦ ሊሻን አጎናፍር
ኤዲተር፦ ወንድዬ ዓሊ
ወደ ቻናሉ ለመ🀄️ላ🀄️ል፦ @Holy_scriptures
❤7👍2👏1
#ረቡዕ የአስቆሮቱ ይሁዳ ኢየሱስን የካደበት ቀንና ማርያም (በማርቆስ ስሟ አልተጠቀሰም) በኢየሱስ እግር ስር ሽቶ ያፈሰሰችበትና በጸጉሯ ያበሰችበት ቀን ነው።
“እርሱም በቢታንያ በለምጻሙ በስምዖን ቤት በነበረ ጊዜ፥ በማዕድ ተቀምጦ ሳለ፥ አንዲት ሴት ዋጋው እጅግ የከበረ ጥሩ ናርዶስ ሽቱ የመላበት የአልባስጥሮስ ቢልቃጥ ይዛ መጣች፤ ቢልቃጡንም ሰብራ በራሱ ላይ አፈሰሰችው።”
(ማርቆስ 14፥3)
ወደ ቻናሉ ለመ🀄️ላ🀄️ል፦ @Holy_scriptures
“እርሱም በቢታንያ በለምጻሙ በስምዖን ቤት በነበረ ጊዜ፥ በማዕድ ተቀምጦ ሳለ፥ አንዲት ሴት ዋጋው እጅግ የከበረ ጥሩ ናርዶስ ሽቱ የመላበት የአልባስጥሮስ ቢልቃጥ ይዛ መጣች፤ ቢልቃጡንም ሰብራ በራሱ ላይ አፈሰሰችው።”
(ማርቆስ 14፥3)
ወደ ቻናሉ ለመ🀄️ላ🀄️ል፦ @Holy_scriptures
❤11👍2🔥2
. ──•◈•─────•◈•─
የዕለቱ ጥቅስ
──•◈•─────•◈•─
“ስለዚህ እንደ ቆመ የሚመስለው እንዳይወድቅ ይጠንቀቅ።”
1ኛ ቆሮንቶስ 10፥12
ወደ ቻናሉ ለመ🀄️ላ🀄️ል፦ @Holy_scriptures
የዕለቱ ጥቅስ
──•◈•─────•◈•─
“ስለዚህ እንደ ቆመ የሚመስለው እንዳይወድቅ ይጠንቀቅ።”
1ኛ ቆሮንቶስ 10፥12
ወደ ቻናሉ ለመ🀄️ላ🀄️ል፦ @Holy_scriptures
❤7
#ረቡዕ የአስቆሮቱ ይሁዳ ኢየሱስን የካደበት ቀንና ማርያም (በማርቆስ ስሟ አልተጠቀሰም) በኢየሱስ እግር ስር ሽቶ ያፈሰሰችበትና በጸጉሯ ያበሰችበት ቀን ነው። (ማር. 14 ) በዚህ ቀን አንድ ነገር ማስተዋል አለብን ብዙ ጊዜ ከኢየሱስ ጋር የተጓዙ ሰዎች ትጥቃቸው መፈታት የጀመረበትና እውነተኛ ማንነታቸው የተገለጠበት ቀን ነበር። ከዚህ በፊት በርትተው ይጓዙ የነበሩ ሁሉ የሥጋ ድካም በብርቱ መገዳደር እና መጣል የጀመራቸው ጊዜ ነበር። አንዳዶች ወድቀው ሲነሱ አንዱ እስከወዲያኛው ወደቀ። በነገራችን ላይ የዚህን የሥጋን ከመንፈስ ጋር ለማበር መቸገር መፍትሄ ከአንድ ቀን በኋላ በጌቴሴማኒ ሹክ ብሏቸዋል። እንዲህ በማለት፦ “ወደ ፈተና እንዳትገቡ ትጉና ጸልዩ፤ መንፈስስ ተዘጋጅታለች ሥጋ ግን ደካማ ነው አለው።” (ማቴዎስ 26፥41)
ወደ ረቡዕ ቀን ስንመለስ ይሁዳ እንዲህ አይነት ሰው ነበር፦
"ይህንም የተናገረ ሌባ ስለ ነበረ ነው እንጂ ለድሆች ተገድዶላቸው አይደለም፤ ከረጢትም ይዞ በውስጡ ከሚገባው ይወስድ ስለ ነበረ ነው።" (ዮሐ. 12፡6) በሌላ በኩል ደግሞ በምን ሰዓት ምን ማድረግ እንዳለባት የምታውቅን ሴት እንመለከታለን። ኢየሱስ ከሞተ በኋላ ለአካሉ ሽቶ ለመቀባት አስበው የሄዱ ቢኖሩም ትንሣኤው ቀድሟቸው ሳይሳካላቸው ተመልሰዋል። መቅደላዊት ማርያም ግን መችና የት ኢየሱስን ማግኘት እንደሚቻል የምታውቅ ሴት ነበረች። እናም የዛሬው ቀን ከኢየሱስ ጋር ለዘለአለሙ ለመጓዝ ኃይል እንድናገኝ፣ ከእርሱ አሳብና አጀንዳ ጋር ደግሞ ተባብረን እንድንጓዝ ጌታ ይርዳን!
“እርሱም በቢታንያ በለምጻሙ በስምዖን ቤት በነበረ ጊዜ፥ በማዕድ ተቀምጦ ሳለ፥ አንዲት ሴት ዋጋው እጅግ የከበረ ጥሩ ናርዶስ ሽቱ የመላበት የአልባስጥሮስ ቢልቃጥ ይዛ መጣች፤ ቢልቃጡንም ሰብራ በራሱ ላይ አፈሰሰችው።”
ማርቆስ 14፥3
“ከአሥራ ሁለቱም አንዱ የአስቆሮቱ ይሁዳ አሳልፎ ሊሰጠው ወደ ካህናት አለቆች ሄደ።”
ማርቆስ 14፥10

❤7👍2
victorious christian life
Nigusse Denano
#መጻሕፍትን_በድምጽ
ርዕስ፦ አሸናፊው የክርስቲያን ኑሮ
የመጽሐፈ ኢያሱ ጥናት
ጸሐፊ፦ ዶ/ር አሳን ሬድፓዝ
ትርጉም፦ ዋቅጅራ ጎባ
ክፍል-17
ይቀጥላል...
ወደ ቻናሉ ለመ🀄️ላ🀄️ል፦ @Holy_scriptures
ርዕስ፦ አሸናፊው የክርስቲያን ኑሮ
የመጽሐፈ ኢያሱ ጥናት
ጸሐፊ፦ ዶ/ር አሳን ሬድፓዝ
ትርጉም፦ ዋቅጅራ ጎባ
ክፍል-17
ይቀጥላል...
ወደ ቻናሉ ለመ🀄️ላ🀄️ል፦ @Holy_scriptures
#ሐሙስ ጌታችንና መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ከመሞቱ በፊት ከደቀ መዛሙርቱ ጋር የመጨረሻውን እራት የበላበትንና በእውነት ለእርሱ ተከታይ ለሆኑት ብርቱና መሰረታዊ ትምህርት፣ ምክር፣ ተግጻጽ ሲያስፈልግም በተግባር የተደገፈ ትምህርት ያስተላለፈበት እንዲሁም አሁን በመንግስቱ ላሉ በኋላም ለሚመጡ የጸለየው አስደናቂ ጸሎት የጸለየበት፣ የደቀ መዛሙርቱ ድካም. . . ወዘተ የሐሙስ ቀን ሁነቶች ናቸው። ሌላ የሚገርም ነገር ቢኖር ኢየሱስን ከመከራሁ እንዲቀርና እርሱን ለመርዳት ተማሪዎቹ በስጋ ቢጣጣሩም ፍቅራቸውን በመሃላ ለማጽናት ቢሞክሩም በኋላ እየሸሹና እየከዱ መገኘታቸው ነው። ለካ እውነተኛ ማንነት በወቅታዊ ስሜት ሳይሆን በፈተና ወቅት የሚገለጥ ነው! የዮሐንስ ወንጌልን ከምዕራፍ 13-18።
“እውነተኛ አምላክ ብቻ የሆንህ አንተን የላክኸውንም ኢየሱስ ክርስቶስን ያውቁ ዘንድ ይህች የዘላለም ሕይወት ናት።”
(ዮሐንስ 17፥3)
🔜 ስለጌታ እራት ዛሬ ይጠብቁን።
ወደ ቻናሉ ለመ🀄️ላ🀄️ል፦ @Holy_scriptures
“እውነተኛ አምላክ ብቻ የሆንህ አንተን የላክኸውንም ኢየሱስ ክርስቶስን ያውቁ ዘንድ ይህች የዘላለም ሕይወት ናት።”
(ዮሐንስ 17፥3)
🔜 ስለጌታ እራት ዛሬ ይጠብቁን።
ወደ ቻናሉ ለመ🀄️ላ🀄️ል፦ @Holy_scriptures
👍10🥰2❤1
. ──•◈•─────•◈•─
የዕለቱ ጥቅስ
──•◈•─────•◈•─
“ኢየሱስም ከፋሲካ በዓል በፊት፥ ከዚህ ዓለም ወደ አብ የሚሄድበት ሰዓት እንደ ደረሰ አውቆ፥ በዚህ ዓለም ያሉትን ወገኖቹን የወደዳቸውን እስከ መጨረሻ ወደዳቸው።”
ዮሐንስ 13፥1

👍3❤2