#የእግዚአብሔር_ቃል_ምን_ይላል?
አሞጽ 7
¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯
¹² አሜስያስም አሞጽን፦ ባለ ራእዩ ሆይ፥ ሂድ ወደ ይሁዳም ምድር ሽሽ፥ በዚያም እንጀራን ብላ፥
¹³ በዚያም ትንቢትን ተናገር፤ ነገር ግን ቤቴል የንጉሥ መቅደስና የመንግሥት ቤት ናትና ከእንግዲህ ወዲህ በዚህ ደግሞ ትንቢት አትናገር አለው።
¹⁴ አሞጽም መልሶ አሜስያስን አለው፦ እኔ ላም ጠባቂና ወርካ ለቃሚ ነኝ እንጂ ነቢይ ወይም የነቢይ ልጅ አይደለሁም፤
¹⁵ እግዚአብሔርም በጎቹን ከመከተል ወሰደኝ፥ እግዚአብሔርም፦ ሂድ፥ ለሕዝቤም ለእስራኤል ትንቢት ተናገር አለኝ።
¹⁶ አሁንም የእግዚአብሔርን ቃል ስማ፤ አንተ። በእስራኤል ላይ ትንቢት አትናገር፥ በይስሐቅም ቤት ላይ አትስበክ ብለሃል፤
¹⁷ ስለዚህ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ ሚስትህ በከተማይቱ ውስጥ ጋለሞታ ትሆናለች፥ ወንዶችና ሴቶች ልጆችህም በሰይፍ ይወድቃሉ፥ ምድርህም በገመድ ትከፈላለች፤ አንተም በረከሰች ምድር ትሞታለህ፥ እስራኤልም ከምድሩ ተማርኮ ይሄዳል።
ወደ ቻናሉ ለመ🀄️ላ🀄️ል፦ @Holy_scriptures

🙏2👍1
. ──•◈•─────•◈•─
የዕለቱ ጥቅስ
──•◈•─────•◈•─
“ነገር ግን ስሜን ለምትፈሩት ለእናንተ የጽድቅ ፀሐይ ትወጣላችኋለች፥ ፈውስም በክንፎችዋ ውስጥ ይሆናል፤ እናንተም ትወጣላችሁ፥ እንደ ሰባም እምቦሳ ትፈነጫላችሁ።”
ሚልክያስ 4፥2

🥰2❤1
Victorious Christian life
Nigusse Denano
#መጻሕፍትን_በድምጽ
ርዕስ፦ አሸናፊው የክርስቲያን ኑሮ
የመጽሐፈ ኢያሱ ጥናት
ጸሐፊ፦ ዶ/ር አሳን ሬድፓዝ
ትርጉም፦ ዋቅጅራ ጎባ
ክፍል-12
ይቀጥላል...
ወደ ቻናሉ ለመ🀄️ላ🀄️ል፦ @Holy_scriptures
ርዕስ፦ አሸናፊው የክርስቲያን ኑሮ
የመጽሐፈ ኢያሱ ጥናት
ጸሐፊ፦ ዶ/ር አሳን ሬድፓዝ
ትርጉም፦ ዋቅጅራ ጎባ
ክፍል-12
ይቀጥላል...
ወደ ቻናሉ ለመ🀄️ላ🀄️ል፦ @Holy_scriptures
👍4
ቅዱሳት መጻሕፍት
#ትንሣኤ የቀጠለ... ትንሣኤ በብሉይ ኪዳን የትንሣኤ አሳብ በአዲስ ኪዳን ብቻ የተከሰተ ዱብ እዳ ነገር አይደለም። በብሉይ ኪዳን በአጠቃላይ የተስማማ የትንሣኤ ሥነ-መለኮት ሲኖር (ኢዮብ 19፥25–27፤ መዝ. 49፥15፤ 73፥23–28፤ ኢሳ 25፥8፤ 26፥19፤ ሕዝ 37፥1– 14፤ ሆሴ 13፥14፤ ዳን 12፥1–4 ወዘተ)፣ በመዝሙር 16፥10 እና መዝሙር 22 እና ኢሳይያስ 53፥10–11 እና ዳንኤል…
#ትንሣኤ
ትንሳኤ በመዝሙረ ዳዊት
ሌሎች በጉልህ ትንሣኤን አመላካች የብሉይ ኪዳን ክፍሎች፦
“ሙታንህ ሕያዋን ይሆናሉ፥ ሬሳዎችም ይነሣሉ። በምድር የምትኖሩ ሆይ፥ ጠልህ የብርሃን ጠል ነውና፥ ምድርም ሙታንን ታወጣለችና ንቁ ዘምሩም።”
ኢሳይያስ 26፥19
"ስለዚህ ትንቢት ተናገር እንዲህም በላቸው፦ ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ ሕዝቤ ሆይ፥ እነሆ፥ መቃብራችሁን እከፍታለሁ ከመቃብራችሁም አወጣችኋለሁ፥ ወደ እስራኤልም ምድር አገባችኋለሁ። ሕዝቤ ሆይ፥ መቃብራችሁን በከፈትሁ ጊዜ ከመቃብራችሁም ባወጣኋችሁ ጊዜ፥ እኔ እግዚአብሔር እንደ ሆንሁ ታውቃላችሁ። መንፈሴንም በውስጣችሁ አሳድራለሁ፥ እናንተም በሕይወት ትኖራላችሁ፥ በገዛ ምድራችሁም አኖራችኋለሁ፤ እኔም እግዚአብሔር እንደ ተናገርሁ እንዳደረግሁም ታውቃላችሁ፥ ይላል እግዚአብሔር።"
ሕዝቅኤል 37፥12-14
ይቀጥላል...
ምንጭ፦ https://owlcation.com/humanities/How-Does-is-the-Doctrine-of-Resurrection-Developed-from-the-Old-Testament-to-the-New-Testament፣
ወደ ቻናሉ ለመ🀄️ላ🀄️ል፦ @Holy_scriptures
ትንሳኤ በመዝሙረ ዳዊት
ጥቂት የነገረ መለኮት ሊቃውንት መዝሙረ ዳዊትን ስለ ትንሣኤ በሚገባ ለመረዳት እንደ ማስረጃ ቢጠቅሱም ዶ/ር ስቴፈን ሪድ ለመዝሙረኛው “ከሞት በኋላ ስላለው ሕይወት ያለው ፍላጎት በአንጻራዊ ሁኔታ ሲታይ አነስተኛ ነው” ብለዋል። አንዳንድ መዝሙረኞች ሕመምና ጭቆና ያጋጠሟቸውን ነገሮች እንደ ሞቱ አድርገው ይገልጹና አምላክ እንዴት እንደሚያስነሣቸው ይናገሩ ይሆናል። የሚናገሩት ከሞት በኋላ ስላለው ትንሣኤ አይደለም። ብዙ የመጀመሪያ አንባቢዎች እንደ 1 ሳሙኤል 2፥6 እና ኢሳ 26፥19 ያሉትን ምንባቦች የተረዱት በዚህ መንገድ ነው። የመዝሙር 16፥9-11 የመጀመሪያ አንባቢ (በአዲስ ኪዳን ለሚያምኑ መሲሐዊ አንድምታ ያላቸው ጥቅሶች) እነዚህን ጥቅሶች እንደ ሞት ከሚመስለው አካላዊ ወይም ስሜታዊ ሥቃይ መለኮታዊ መዳን አድርገው ሳይገነዘቡት አልቀረም። በዚያ ቀን ሕመሞች በጣም ገዳይ ሊሆኑ ስለሚችሉ፣ መዝሙረኞቹ አምላክ ከሞት ደጃፍ ስለነጠቀቸው ማመስገናቸው ትክክል ይሆን ነበር። ለምሳሌ መዝሙረ ዳዊት 116፥8-9 “ነፍሴን ከሞት፥ ዓይኔንም ከእንባ፥ እግሬንም ከመሰናከል አድኖአልና።በሕያዋን አገር በእግዚአብሔር ፊት እሄዳለሁ” ይላል። ትንሳኤ በመክብብ
መክብብ ከሞት በኋላ ስለሚሆነው ነገር የጥንት ሰዎች ያላቸውን አንዳንድ አሻሚ አሳቦችን ይይዛል። መክብብ 3፥19-21 የሰዎችንና የእንስሳትን እጣ ፈንታ በማነጻጸር በቁጥር 20 ላይ “ሁሉ ወደ አንድ ቦታ ይሄዳል፤ ሁሉ ከአፈር ነው ሁሉም ወደ አፈር ይመለሳል።” በማለት አንድ ናቸው ሲል ደምድሟል። በሪድ መሠረት፣ “እዚህ ምንም የትንሣኤ ተስፋ ያለ አይመስልም”። መክብብ 12፥7 “አፈርም ወደ ነበረበት ምድር ሳይመለስ፥ ነፍስም ወደ ሰጠው ወደ እግዚአብሔር ሳይመለስ ፈጣሪህን አስብ።” በማለት የበለጠ ተስፋ የሚሰጥ ይመስላል። ቆሄሌት የሰው መንፈስ ወደ እግዚአብሔር እንደሚመለስ ቢናገርም፣ መንፈስ ወደ ፈጣሪው ከተመለሰ በኋላ ምን እንደ ሆነ ለእነዚህ ጥንት ሰዎች ግልጽ አልነበረም። ቫንሆዘር እንዳሉት፣ “ትንሣኤ ማለት አሁን ካለው አካል ጋር ወደሚመሳሰል አካል መመለስ ወይም ወደ ሌላ ነገር መለወጥ (አብረቅራቂ ኮከብ፣ ለምሳሌ) በአይሁድ አስተሳሰብ ግልጽ አይደለም”። የመጀመሪያ አንባቢዎች፣ ከክርስቶስ ትንሳኤ አንፃር የተረዳውን የዘመናችን አንባቢ ጋር ሲነጻጸሩ በዚህ ቁጥር ላይ ብዙ ተስፋ አያገኙም።ትንሳኤ በዳንኤል
በዳንኤል ዘመን፣ ተራማጅ የመገለጥ ቁርጥራጮች መሰባሰብ ጀመሩ። ዳንኤል ለእግዚአብሔር ሕዝብም ሆነ ለሌላው የሰው ልጅ የትንሣኤን የመጀመሪያ ቃል ተናግሯል፡- “በምድርም ትቢያ ውስጥ ካንቀላፉቱ ብዙዎች ይነቃሉ፤ እኵሌቶቹ ወደ ዘላለም ሕይወት፥ እኵሌቶቹም ወደ እፍረትና ወደ ዘላለም ጕስቍልና።” (12፥2) የብሉይ ኪዳን የትንሣኤ ማጣቀሻዎች እጅግ በጣም አስደናቂ እና ከአዲስ ኪዳን ማጣቀሻዎች ባነሰ ድግግሞሽ የተከሰቱ መሆናቸውን ልብ ሊባል ይገባል። ብዙ የብሉይ ኪዳን ትንሣኤዎች ፅንሰ-ሀሳቡን በዘፍጥረት 2፥7 “ከምድር አፈር” ጋር ማገናኘታቸው ጠቃሚ ነው። ሌሎች በጉልህ ትንሣኤን አመላካች የብሉይ ኪዳን ክፍሎች፦
“ሙታንህ ሕያዋን ይሆናሉ፥ ሬሳዎችም ይነሣሉ። በምድር የምትኖሩ ሆይ፥ ጠልህ የብርሃን ጠል ነውና፥ ምድርም ሙታንን ታወጣለችና ንቁ ዘምሩም።”
ኢሳይያስ 26፥19
"ስለዚህ ትንቢት ተናገር እንዲህም በላቸው፦ ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ ሕዝቤ ሆይ፥ እነሆ፥ መቃብራችሁን እከፍታለሁ ከመቃብራችሁም አወጣችኋለሁ፥ ወደ እስራኤልም ምድር አገባችኋለሁ። ሕዝቤ ሆይ፥ መቃብራችሁን በከፈትሁ ጊዜ ከመቃብራችሁም ባወጣኋችሁ ጊዜ፥ እኔ እግዚአብሔር እንደ ሆንሁ ታውቃላችሁ። መንፈሴንም በውስጣችሁ አሳድራለሁ፥ እናንተም በሕይወት ትኖራላችሁ፥ በገዛ ምድራችሁም አኖራችኋለሁ፤ እኔም እግዚአብሔር እንደ ተናገርሁ እንዳደረግሁም ታውቃላችሁ፥ ይላል እግዚአብሔር።"
ሕዝቅኤል 37፥12-14
ይቀጥላል...
ምንጭ፦ https://owlcation.com/humanities/How-Does-is-the-Doctrine-of-Resurrection-Developed-from-the-Old-Testament-to-the-New-Testament፣
ወደ ቻናሉ ለመ🀄️ላ🀄️ል፦ @Holy_scriptures
Owlcation
How Is the Doctrine of Resurrection Developed From the Old Testament to the New Testament?
This article contains a brief exploration of the doctrine of the resurrection.
👍6
. ──•◈•─────•◈•─
የዕለቱ ጥቅስ
──•◈•─────•◈•─
“የዋሆች ብፁዓን ናቸው፥ ምድርን ይወርሳሉና።”
ማቴዎስ 5፥5
ወደ ቻናሉ ለመ🀄️ላ🀄️ል፦ @Holy_scriptures
የዕለቱ ጥቅስ
──•◈•─────•◈•─
“የዋሆች ብፁዓን ናቸው፥ ምድርን ይወርሳሉና።”
ማቴዎስ 5፥5
ወደ ቻናሉ ለመ🀄️ላ🀄️ል፦ @Holy_scriptures
🔥3
Victorious christian life
Nigusse Denano
#መጻሕፍትን_በድምጽ
ርዕስ፦ አሸናፊው የክርስቲያን ኑሮ
የመጽሐፈ ኢያሱ ጥናት
ጸሐፊ፦ ዶ/ር አሳን ሬድፓዝ
ትርጉም፦ ዋቅጅራ ጎባ
ክፍል-13
ይቀጥላል...
ወደ ቻናሉ ለመ🀄️ላ🀄️ል፦ @Holy_scriptures
ርዕስ፦ አሸናፊው የክርስቲያን ኑሮ
የመጽሐፈ ኢያሱ ጥናት
ጸሐፊ፦ ዶ/ር አሳን ሬድፓዝ
ትርጉም፦ ዋቅጅራ ጎባ
ክፍል-13
ይቀጥላል...
ወደ ቻናሉ ለመ🀄️ላ🀄️ል፦ @Holy_scriptures
👍3
#እራሳችንን_እንመርምር
ጌታችን እና መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ እንዲህ አለ፦ “...ጽድቃችሁ ከጻፎችና ከፈሪሳውያን ጽድቅ ካልበለጠ፥ ወደ መንግሥተ ሰማያት ከቶ አትገቡም።” (ማቴዎስ 5፥20)
ታዲያ እኛ የግል ጽድቅ አለን ወይ? ቢኖረንስ የመርገም ጨርቅ አይደለም? እሺ ምኑን ነው ታዲያ ጌታ ከፈሪሳውያን እንዲበልጥ የጠየቀን?

👍1
. ──•◈•─────•◈•─
የዕለቱ ጥቅስ
──•◈•─────•◈•─
“የዘንባባ ዛፍ ዝንጣፊ ይዘው ሊቀበሉት ወጡና፦ ሆሣዕና፤ በጌታ ስም የሚመጣ የእስራኤል ንጉሥ የተባረከ ነው እያሉ ጮኹ።”
ዮሐንስ 12፥13

❤2
#ሆሣዕና
"ሆሣዕና በአርያም እያሉ ይጮኹ ነበር"
ማቴ ፳፩፥፱
🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿
ዛሬ "ሆሳዕና" ነው:: ለትንሣኤ በዓል አንድ ሳምንት ቀረው::
#ሆሳዕና ቃሉ ከሁለት አረማይክ ቃላት የተሰራ ሲሆን ትርጉም «እባክህ እርዳ፣ አሁን አድን» ማለት ነው። እብራይስጡም ይህንኑ ቃል ወርሶ «הושענא » ሆሻአና ሲል ይገኛል። አዎ «አሁን አድን፣ እባክህ እርዳን» ብሎ የአዳም ዘር ያጣውን ልጅነትና የደረሰበትን ሞት ለመላቀቅ የሚያሰማው የጩኸት ድምጽ ነው፣ «ሆሳዕና»!!!
ዳዊት ነቢይ በመንፈስ ቅዱስ ተመልክቶ ማዳኑን ሲጣራና አሁን ናልን ሲል ከዘመናት በፊት አድምጠነዋል። የውስጥ ዓይኖቹ ሩቅ አይተዋል። ማዳኑንም ሽተው እንዲህ ሲል ዘምሮለታል።
«አቤቱ፥ እባክህ፥ አሁን አድን አቤቱ፥ እባክህ፥ አሁን አቅና» መዝ ፻፲፰፥፳፭
አዎ፣ ንጉሥ ክርስቶስ ከዘጠና ዘጠኙ በጎች መካከል የጠፋውን አንዱን በግ ፍለጋ ንጉሥ ሆኖ ሳለ እንደንጉሥ ያይደለ በአህያ፣ ለዚያውም በውርንጫ ተቀምጦ «የአሁን አድን (ሆሳዕና)» ጩኸት ሊመልስ በጽዮን ከተማ ይመጣል፤ ይህንንም ዘካርያስ ከዘመረው ዘመናት ተቆጥረው ነበር።
«አንቺ የጽዮን ልጅ ሆይ፥ እጅግ ደስ ይበልሽ አንቺ የኢየሩሳሌም ልጅ ሆይ፥ እልል በዪ እነሆ፥ ንጉሥሽ ጻድቅና አዳኝ ነው ትሑትም ሆኖ በአህያም፥ በአህያይቱ ግልገል በውርጫይቱ ላይ ተቀምጦ ወደ አንቺ ይመጣል» ዘካ ፱፥፱
ሰማያዊ ንጉሥ ክርስቶስ ከቅድስት ድንግል ማርያም ያለዘርዓ ብእሲ ከስጋችን ተዛምዶ ማዳኑን ሲጠብቁ፤ ከሩቅ አይተው ሲጣሩ፣ ሲዘምሩለትና አንድ ቀን ማዳኑ እንደሚሆን ተስፋ ሲያደርጉት የነበረው ሰዓቱ ደርሶ በመካከላቸው ሲገኝ ይጠብቁት የነበረው ዓይነት ሳይሆን ውበት የሌለውን ንጉሥ ለመቀበል የገዛ ወገኖቹ ተቸግረው ነበር።
አዎ፣ የደም ግባት ብቻ ሳይሆን የንጉሥ ወግ የሌለው፣ በአህያ ለዚያውም በውርንጫ የሚመጣ ንጉሥ እንዴት ይቀበሉት?
አባቶቻቸው ለዘመናት «ሆሳዕና፣ ማዳንህ አሁን ይሁን» ያሉለትና የዘመሩለት በዕለተ ቀጠሮው ማዳኑን ሊያሳይ ከጽዮን ደጃፍ ቀርቦ ሳለ የማያውቁት፣ ያልሰሙት፣ ትንቢቱን ያላነበቡት «ሆሳዕና» ሲሉ ትልልቆቹ ዕብራውያን ግን ዝም አሉ፣ ዝም በሉም አሉ!
«ነገር ግን የካህናት አለቆችና ጻፎች ያደረገውን ድንቃ ድንቅ በመቅደስም፣ ሆሣዕና ለዳዊት ልጅ እያሉ የሚጮኹትን ልጆች ባዩ ጊዜ፥ ተቈጥተው፣ እነዚህ የሚሉትን አትሰማምን? አሉት»
የማዳኑ ጌታም፣
«እሰማለሁ፤ ከሕፃናትና ከሚጠቡት አፍ ምስጋናን ለራስህ አዘጋጀህ የሚለውን ቃል ከቶ አላነበባችሁምን? አላቸው» ማቴ ፳፩፥፲፭-፲፮
ኢየሱስ ክርስቶስ የእነዚህን ሕፃናት ዝማሬና ምስጋናን የሰማው ከቤተ ፋጌ ወደ ኢየሩሳሌም ማዳኑን ሊፈጽም በመጣ ጊዜ ነበር። ቤተ ፋጌ ከኢየሩሳሌም ከተማ ምሥራቃዊ አቅጣጫ በቢታንያና በደብረ ዘይት ተራራ መካከል የምትገኝ መንደር ነበረች።
ጌታ ኢየሱስም ከኢያሪኰ ከተማ ወደኢየሩሳሌም ሲወጣ ካረፈባት ከቤተ ፋጌ መንደር ሁለቱን ደቀ መዛሙርት ልኰ ውርንጫይቱን ከታሰረችበት ፈትተው እንዲያመጡለት አዟል።
«ወደ ኢየሩሳሌምም ቀርበው ወደ ደብረ ዘይት ወደ ቤተ ፋጌ ሲደርሱ፥ ያንጊዜ ኢየሱስ ከደቀ መዛሙርቱ ሁለት ላከ፥ እንዲህም አላቸው፦ በፊታችሁ ወዳለችው መንደር ሂዱ፥ በዚያን ጊዜም የታሰረችን አህያ ውርንጫም ከእርስዋ ጋር ታገኛላችሁ፤ ፈትታችሁ አምጡልኝ» ማቴ ፳፩፥፪
ያን ጊዜም በቀደምት አበው የተነገረው ትንቢትና ዝማሬ ፍጻሜ አገኘ ማለት ነው።
«የሚቀድሙትም ሕዝብ የሚከተሉትም። ሆሣዕና ለዳዊት ልጅ በጌታ ስም የሚመጣ የተባረከ ነው፤ ሆሣዕና በአርያም እያሉ ይጮኹ ነበር» ማቴ ፳፩፥፱
ይሁን እንጂ ኢየሩሳሌም ለሆሳዕና አልተዘጋጀችም ነበር። ይልቁንም ቤተ መቅደሱ አካባቢ ስለማዳኑ ዝማሬ በማቅረብ ፋንታ የጦፈ የንግድ ገበያ ደርቶበት ነበር። ቤተመቅደሱ የጸሎት ሥፍራ መሆኑ ቀርቶ የሻጮችና የለዋጮች መድረክ ሆኖ ነበር። ያኔ ማዳኑ የቀረበላት ኢየሩሳሌም በመቅደሱ በራፍ ስትሸጥ፣ ስትለውጥ መድኃኒቱን ሆሳዕና እያለች መቀበልን እንዳልቻለች ሁሉ የዛሬዋ ቤተክርስቲያንስ ንግድና ሸቀጥ የሌለበትን «ሆሳዕና» እያከበረች ነው ወይ? ብለን ብንጠይቅ ራስን ማታለል ካልተጨመረበት በስተቀር፣ መሸጥ መሸቀጡ የሌለበትን «ሆሳዕና» የሚያከብር የለም ነው መልሱ። ዐውደ ምሕረቱ ሱቅ በደረቴ ያልሆነበትን ሥፍራ ማግኘት ከባድ ነው።
ኢየሱስ ማዳኑን ከመፈጸሙ በፊት እነዚህን ነጋዴዎች አስወግዷል። ገበታቸውን ገልብጧል። እየገረፈ አስወጥቷል። የወንበዴዎች ዋሻ የሆነውን የጸሎት ቤት ጠራርጓል። ዛሬስ ቤቱ ስንት ወንበዴ መሽጎበት ይሆን? ወንበዴዎቹ ይዘምራሉ፣ ሆሳዕና ይላሉ፣ የዘንባባ ዝንጣፊ ይይዛሉ፣ በጣታቸው፣ በግንባራቸው ያስራሉ። ወንበዴዎች ናቸው ተብለው እንዳይርቋቸው የአምልኰ መልክ አላቸው። ቤተመቅደሱን የወንበዴዎች ዋሻ አደረጋችሁ ያለው በግብር ውንብድና በመልክ ግን አገልጋይ ይመስሉ የነበሩትን የመቅደሱን ሰዎች ነበር። ዛሬም እንደዚያው!!
በእድሜአችን ስንት «ሆሳዕና በአርያም» አሳለፍን? ማዳኑ በተደረገለት ማንነታችን ውስጥ ስንት ፍሬ አፈራን? የተራበው ኢየሱስ ከእኛ የሚፈልገውን ፍሬ ይዘናል? ወይስ ፍሬ አልባ ሆነን ለቁጣ የተዘጋጀን እንሆን? «ሆሳዕና በአርያም» ማለቱ ብቻውን አያድንም፣ ማዳኑንም አያመጣም። የወንበዴ ዋሻ ማንነታችንን እናጽዳ። ከዚህ ዓለም ሽቃጭና ልዋጭ ማስመሰያ ማንነት እንውጣ! በጎ ፍሬ እንዲያፈራ ለተላከው የወይኑ ባለቤት ወራሽ እንገዛ! ያኔ «ሆሳዕና በአርያም» ስንል ማዳኑ ፈጥኖ ይሆንልናል።
አዎ ሆሳዕና በአርያም! በዚህም በወዲያኛውም! ሆሳዕና በአርያም።ሃሌ ሉያ!!!!!!!!
ምንጭ:- ደጀ ብርሃን

🔥6👍5
Victorious Christian life
Nigusse Denano
#መጻሕፍትን_በድምጽ
ርዕስ፦ አሸናፊው የክርስቲያን ኑሮ
የመጽሐፈ ኢያሱ ጥናት
ጸሐፊ፦ ዶ/ር አሳን ሬድፓዝ
ትርጉም፦ ዋቅጅራ ጎባ
ክፍል-14
ይቀጥላል...
ወደ ቻናሉ ለመ🀄️ላ🀄️ል፦ @Holy_scriptures
ርዕስ፦ አሸናፊው የክርስቲያን ኑሮ
የመጽሐፈ ኢያሱ ጥናት
ጸሐፊ፦ ዶ/ር አሳን ሬድፓዝ
ትርጉም፦ ዋቅጅራ ጎባ
ክፍል-14
ይቀጥላል...
ወደ ቻናሉ ለመ🀄️ላ🀄️ል፦ @Holy_scriptures
👍2❤1
#ሰኞ፣ ከሆሣዕና ማግሥት ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ከቢታንያ ወደ ኢየሩሳሌም ሲገባ ሁለት ነገሮችን አድርጓል፡፡ አንደኛ ከቅጠል በስተቀር ፍሬ ያልተገኘባትን ዕፀ በለስ ረግሟል፡፡ ሁለተኛ ወደ ቤተ መቅደስ ገብቶ የሚሸጡትን፣ የሚገዙትንና የሚለውጡትን አስወጥቷል፡፡ (ማቴ.21÷12-17፤ ማር.11÷17፤ ሉቃ.19÷45-46፡፡)
ወደ ቻናሉ ለመ🀄️ላ🀄️ል፦ @Holy_scriptures
ወደ ቻናሉ ለመ🀄️ላ🀄️ል፦ @Holy_scriptures
👍4
. ──•◈•─────•◈•─
የዕለቱ ጥቅስ
──•◈•─────•◈•─
“ይህስ ስሜ የተጠራበት ቤት በዓይናችሁ የሌቦች ዋሻ ሆኖአልን? እነሆ፥ እኔ አይቻለሁ፥ ይላል እግዚአብሔር።”
ኤርምያስ 7፥11

❤8
#ሰኞ
👉 በለሷ የሚጠበቅባትን አልያዘችም (ከፍሬ ጎድላ ተገኝታለች)።
👉 ቤተመቅደሱ የማይጠበቅበትን ይዟል (ሻጭ፣ ገዢ እና ለዋጭ) ።
በቅዱስ ሉቃስ ወንጌል ላይ እንደተገለጸው ይህ ምሳሌ አለ "ለአንድ ሰው በወይኑ አትክልት የተተከለች በለስ ነበረችው ፍሬም ሊፈልግባት ወጥቶ ምንም አላገኘም፡፡" ሉቃ 13፥6 በማለት በበለስ ስለተመሰለ የሰው ልጅ ሕይወት በማሰብ እንዲመለስ ንስሐ እንዲገባ በሕይወትም እንዲኖር እግዚአብሔር ማሳሰቡን ይናገራል፡፡ ንስሐ አልገባም አልመለስም ያለም በለሷ እንደጠወለገችና እንደተቆረጠች ሁሉ ፍሬ ባለማፍራታቸው እንደሚቆረጡ እንዲሁም ወደ እሳት እንደሚጣሉ መጽሐፍ ቅዱስ በግልጽ ያስረዳል፡፡ ፍሬ አልባ እንዳንሆን ጌታ ሲመጣም እንዳናፍር የመጽሐፉን ቃል ልንጠብቅና ልንፈጽም ይገባናል፡፡ በዚህ የሕማማት የመጀመሪያ ቀን ዕለተ ሰኞ የምናስበው የምንዘክረው የሰው ልጅ ሕይወት በከንቱ በቸልተኝነት እንዳይደክም እንዳይጠወልግ፣ እንዳይደርቅ ወደ እሳትም እንዳይጣል ማድረግ ይገባናል፡፡ ለዚህም ፍቱን መፍትሄ የሚጠበቅብንን ፍሬ ማፍራት ነው። ፍሬ ማፍራት መብት ሳይሆን ግዴታ ነው!
ጌታችንና መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ወደ ቤተ መቅደስ ግብቶ ከበለሲቷ ተቃራኒ በሆነ ሁኔታ መቅደሱ ሞልቶ ነበር። በምን ከተባለ በጸሎት ሳይሆን በሽያጭ! የጸሎት ቤት መሆን ሲገባው የወንበዶች ዋሻ ነበር የሆነው። እና ጌታችን የቤቱ ቅናት ስለሚበላው እርምጃ ወሰደ። ማን ላይ?
👉የሚሸጥ (ማቴ.21፥12)
👉የሚገዛ [ብዙ ጊዜ ይህን "የሚገዙትን" የሚለውን አናስተውለውም] (ማቴ.21፥12)
👉የገንዘብ ለዋጮች (ማቴ.21፥12)
ዛሬ የእግዚአብሔር ቤተሰቦች ጌታችን ወደ መቅደስ ሕይወታችን ቢመጣ ምን ያገኝ ይሆን? በወንበዶች የታጨቀ መቅደስ ወይስ ፍሬ ማፍራት ሲገባው ያለ ፍሬ የከረመን በለስ? የእግዚአብሔር ቃል ግን ለንስሐ የሚገባ ፍሬ አድርጉ ይለናል። ማቴ 3፥8
ማቴዎስ 21
¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯
¹² ኢየሱስም ወደ መቅደስ ገባና በመቅደስ የሚሸጡትንና የሚገዙትን ሁሉ አወጣ፥ የገንዘብ ለዋጮችንም ገበታዎች የርግብ ሻጮችንም ወንበሮች ገለበጠና፦
¹³ ቤቴ የጸሎት ቤት ትባላለች ተብሎ ተጽፎአል፥ እናንተ ግን የወንበዶች ዋሻ አደረጋችኋት አላቸው።
¹⁴ በመቅደስም ዕውሮችና አንካሶች ወደ እርሱ ቀረቡና ፈወሳቸው።
¹⁵ ነገር ግን የካህናት አለቆችና ጻፎች ያደረገውን ድንቃ ድንቅ በመቅደስም፦ ሆሣዕና ለዳዊት ልጅ እያሉ የሚጮኹትን ልጆች ባዩ ጊዜ፥ ተቈጥተው፦
¹⁶ እነዚህ የሚሉትን አትሰማምን? አሉት። ኢየሱስም፦ እሰማለሁ፤ ከሕፃናትና ከሚጠቡት አፍ ምስጋናን ለራስህ አዘጋጀህ የሚለውን ቃል ከቶ አላነበባችሁምን? አላቸው።
¹⁷ ትቶአቸውም ከከተማ ወደ ቢታንያ ወጣ በዚያም አደረ።

👍6❤4
Victorious Christian Life
Nigusse Denano
#መጻሕፍትን_በድምጽ
ርዕስ፦ አሸናፊው የክርስቲያን ኑሮ
የመጽሐፈ ኢያሱ ጥናት
ጸሐፊ፦ ዶ/ር አሳን ሬድፓዝ
ትርጉም፦ ዋቅጅራ ጎባ
ክፍል-15
ይቀጥላል...
ወደ ቻናሉ ለመ🀄️ላ🀄️ል፦ @Holy_scriptures
ርዕስ፦ አሸናፊው የክርስቲያን ኑሮ
የመጽሐፈ ኢያሱ ጥናት
ጸሐፊ፦ ዶ/ር አሳን ሬድፓዝ
ትርጉም፦ ዋቅጅራ ጎባ
ክፍል-15
ይቀጥላል...
ወደ ቻናሉ ለመ🀄️ላ🀄️ል፦ @Holy_scriptures
❤2👍1
#ማክሰኞ ኢየሱስ ለመጨረሻ ጊዜ በቤተ መቅድስ ያስተማረበት ቀን ነው።
ጌታ ከቃሉ ስንት ጊዜ አስተማረን? ምን ያህልስ ወደ ተግባር ለወጥነው? ወይስ እንደ ፈሪሳውያን በራሱ መጽሐፍ ላይ ጌታችንን እየተከራከርነውና አልፎ ተርፎም ከሕይወታችን ልናስወጣው እየከጀልን ይሆን? የማንስ ጽሕፈት በላያችን ይታያል?
ወደ ቻናሉ ለመ🀄️ላ🀄️ል፦ @Holy_scriptures
ጌታ ከቃሉ ስንት ጊዜ አስተማረን? ምን ያህልስ ወደ ተግባር ለወጥነው? ወይስ እንደ ፈሪሳውያን በራሱ መጽሐፍ ላይ ጌታችንን እየተከራከርነውና አልፎ ተርፎም ከሕይወታችን ልናስወጣው እየከጀልን ይሆን? የማንስ ጽሕፈት በላያችን ይታያል?
ወደ ቻናሉ ለመ🀄️ላ🀄️ል፦ @Holy_scriptures
❤17👍1👏1
. ──•◈•─────•◈•─
የዕለቱ ጥቅስ
──•◈•─────•◈•─
“ለሚወጣ ሁሉ በክርስቶስም ትምህርት ለማይኖር ሰው አምላክ የለውም፤ በክርስቶስ ትምህርት ለሚኖር አብና ወልድ አሉት።”
2ኛ ዮሐንስ 1፥9
ወደ ቻናሉ ለመ🀄️ላ🀄️ል፦ @Holy_scriptures
የዕለቱ ጥቅስ
──•◈•─────•◈•─
“ለሚወጣ ሁሉ በክርስቶስም ትምህርት ለማይኖር ሰው አምላክ የለውም፤ በክርስቶስ ትምህርት ለሚኖር አብና ወልድ አሉት።”
2ኛ ዮሐንስ 1፥9
ወደ ቻናሉ ለመ🀄️ላ🀄️ል፦ @Holy_scriptures
👍5
#ማክሰኞ
ለመሆኑ ጌታችንና መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ምን አስተማረ? ወይም ምን ተማሩ አለ?
👉“እንግዲህ ከነዚህ ከሁሉ ካነሱት ትእዛዛት አንዲቱን የሚሽር ለሰውም እንዲሁ የሚያስተምር ማንም ሰው በመንግሥተ ሰማያት ከሁሉ ታናሽ ይባላል፤ የሚያደርግ ግን የሚያስተምርም ማንም ቢሆን እርሱ በመንግሥተ ሰማያት ታላቅ ይባላል።”
ማቴዎስ 5፥19
👉“ነገር ግን ሄዳችሁ፦ ምሕረትን እወዳለሁ መሥዋዕትንም አይደለም ያለው ምን እንደ ሆነ ተማሩ፤ ኃጢአተኞችን ወደ ንስሐ እንጂ ጻድቃንን ልጠራ አልመጣሁምና አላቸው።”
ማቴዎስ 9፥13
👉“የሰው ልጅ ብዙ መከራ ሊቀበል፥ ከሽማግሌዎችም ከካህናት አለቆችም ከጻፎችም ሊጣል፥ ሊገደልም ከሦስት ቀንም በኋላ ሊነሣ እንዲገባው ያስተምራቸው ጀመር፤ ቃሉንም ገልጦ ይናገር ነበር።”
ማርቆስ 8፥31
👉“ቀንበሬን በላያችሁ ተሸከሙ ከእኔም ተማሩ፥ እኔ የዋህ በልቤም ትሑት ነኝና፥ ለነፍሳችሁም ዕረፍት ታገኛላችሁ፤”
ማቴዎስ 11፥29
👉“ሲያስተምርም እንዲህ አለ፦ ረጃጅም ልብስ ለብሰው መዞርን፥ በገበያም ሰላምታን፥ በምኵራብም የከበሬታን ወንበር፥ በግብርም የከበሬታን ስፍራ ከሚወዱ ከጻፎች ተጠበቁ፤”
ማርቆስ 12፥38-39
👉“ምሳሌውንም ከበለስ ተማሩ፤ ጫፍዋ ሲለሰልስ ቅጠልዋም ሲያቈጠቍጥ፥ ያን ጊዜ በጋ እንደ ቀረበ ታውቃላችሁ፤”
ማቴዎስ 24፥32
👉 “እንግዲህ ሂዱና አሕዛብን ሁሉ በአብ በወልድና በመንፈስ ቅዱስ ስም እያጠመቃችኋቸው፥ ያዘዝኋችሁንም ሁሉ እንዲጠብቁ እያስተማራችኋቸው ደቀ መዛሙርት አድርጓቸው፤ እነሆም እኔ እስከ ዓለም ፍጻሜ ድረስ ሁልጊዜ ከእናንተ ጋር ነኝ።”
ማቴዎስ 28፥19-20
👉“ኢየሱስም በእርሱ ያመኑትን አይሁድ እንዲህ አላቸው፤ “በትምህርቴ ብትጸኑ እናንተ በእውነት ደቀ መዛሙርቴ ናችሁ፤”
ዮሐንስ 8፥31 (አዲሱ መ.ት)

👍8