ቅዱሳት መጻሕፍት
7.45K subscribers
1.35K photos
61 videos
332 files
797 links
በዚህ ቻናል

👉ቅዱሳት መጻሕፍት ይጠናሉ::
👉መጽሐፍ ቅዱሳዊ ትምህርቶች ይቀርባሉ::
👉 ለቅዱሳት መጽሐፍት ጥናት የሚያግዙ መጻሕፍት ይለቀቃሉ።

⭐️⭐️⭐️⭐️⭐️

@Holy_scriptures
Download Telegram
መንፈስ ቅዱስ.pdf
9.1 MB
👉ርዕስ፦ መንፈስ ቅዱስ
ጸሐፊ፦ ቢሊ ግሬሃም
🗣ትርጉም፦ ግርማዊ
✏️እርማት፦ ወንድዬ ዓሊ


ወደ ቻናሉ ለመ🀄️🀄️ል፦ @Holy_scriptures
11🔥3
.       ──•◈•─────•◈•─
                          የዕለቱ ጥቅስ
        ──•◈•─────•◈•─
“እግዚአብሔር ፈራጃችን ነው፥ እግዚአብሔር ሕግን ሰጪያችን ነው፥ እግዚአብሔር ንጉሣችን ነው፤ እርሱ ያድነናል።”
ኢሳይያስ 33፥22



ወደ ቻናሉ ለመ🀄️🀄️ል፦ @Holy_scriptures
👍84
ቅዱሳት መጻሕፍት
ትንሣኤ ሙታን                             ወ/ዊ ያሬድ ጥላሁን                  ክፍል-3    ሞት፡- የሰውን ልጅ ሁሉ ያንበረከከ፣ ጀግኖችን ያልፈራ፣ ነገሥታትን ያላፈረ፣ አዛውንትን ያላከበረ የሰው ጠላት ከሞት በላይ ማን ይኖር ይሆን!? በኃጢአት በኩል ወደ ዓለም ገብቶ በሥጋ ሁሉ ላይ የነገሠ፣ ከአዳም አንስቶ እስከ ሙሴ ከሕግ በፊትም ሆነ ከሕግ በኃላ የተንሰራፋ፣ የሰውን…
ትንሣኤ ሙታን


                            ወ/ዊ ያሬድ ጥላሁን


                 ክፍል-4

ተስፋ፡- ጌታ ኢየሱስ ከሙታን እንደተነሣ ምንም ያህል አስቀድሞ፣ ደጋግሞ የነገራቸው ቢሆንም ትንሣኤን ለማመን ልባቸው የዘገየውን ደቀመዛሙርቱን ለማስረዳት ያደረገው ነገር ቢኖር መጽሐፍትን ያስተውሉ ዘንድ አዕምሯቸውን መክፈት ነው። ይህም ትንሣኤው አስቀድሞ የተሰጠ መለኮታዊ ተስፋ መሆኑኑ ያረጋግጥልናል።

እግዚአብሔር የተስፋ አምላክ ነው። ታዲያ ተስፋ መስጠት የጀመረው የተስፋው ወራሽ የሆነው ሰው ከተፈጠረ በኃላ ብቻ አልነበረም። ሐዋርያው ጳውሎስ በመንፈስ ቅዱስ መረዳት ወደ ዘላለም መጥቆ ዐለም ሳይፈጠር ስለተከናወነ አንድ ተግባር ይተርክልናል፡-

“ስለዚህም ሕይወት የማይዋሽ እግዚአብሔር ከዘላለም ዘመናት በፊት ተስፋን ሰጠ” ቲቶ 1፥2

“በክርስቶስ ኢየሱስ እንደሚሆን የሕይወት ተስፋ በእግዚአብሔር ፈቃድ የኢየሱስ ክርስቶስ ሐዋርያ የሆነ ጳውሎስ” 2ጢሞ. 1፥1

“… ይህም ፀጋ ከዘላለም ዘመናት በፊት በክርስቶስ ኢየሱስ ተሰጠን፣ አሁን ግን በመድኃኒታችን በኢየሱስ ክርስቶስ መገለጥ ታይቷል። እርሱ ሞትን ሽሯልና … በወንጌል ሕይወትንና አለመጥፋትን ወደ ብርሃን አውጥቷል” 2ጢሞ. 1፥9-11
 
ይህ የዘላለም ተስፋ ነው በዘመናት ውስጥ ከእግዚአብሔር ዘንድ ለአባቶች የተሰጠው። ተስፋው በሙሉ ከትንሳኤ ጋር የተያያዘ ነው። እግዚአብሔር በዘመናት ውስጥ ከተለያዩ ሰዎች ጋር ኪዳን የገባ ቢሆንም “ቅዱስ” ተብሎ የተጠራ ኪዳን እግዚአብሔር ከአብርሃምና ከዳዊት ጋር የገባው “የተስፋ ኪዳን” ነው። ተስፋችን ስንሞት ሥጋችን ወደ አፈር፣ ነፍሳችን ወደ እግዚአብሔር ሄዳ በዚያ ለዘላለም መኖራችን አይደለም። በፍፁም አይደለ! ምንም እንክዋ ነፍሳችን ከሥጋችን ከምትለይበት አንስቶ ጌታ ዳግመኛ እስኪመጣና የአካል ትንሣኤ እስኪሆን ድረስ ሕያው የሆነች ነፍሳችን በጌታ ዘንድ የምትቆይ ቢሆንም ያ ተስፋችን አይደለም። እዚያም ሆነን በናፍቆት የምንጠብቀው ተስፋ የሥጋ ትንሣኤን ይመሥለኛል። ለዚህ አይደል የጌታን ዳግም መምጣት ሲያወሳ ጳውሎስ “የተባረከው ተስፋችን የታላቁ የአምላካችንና የመድኃኒታችን የኢየሱስ ክርስቶስ መገለጥ” ቲቶ 2፥11-13 በማለት የሚጠራው? ስለዚህ እኛም መገለጡን ከሚጠባበቁ አዕላፋት ቅዱሳን ጋር ተጨምረን “ማራናታ፡- አሜን ጌታ ኢየሱስ ሆይ ቶሎ ና!” እንበል። በቅድስና በመኖር ወንጌልንም በማሰራጨት መምጣቱን እናፋጥን። 



ምንጭ:- semayawithought.com



ወደ ቻናሉ ለመ🀄️🀄️ል፦ @Holy_scriptures
👍8
በቤተክርስቲያን ታሪክ የተካሄደው የኤፌሶን ጉባኤ (431) የትኛውን ኑፋቄ አውግዟል?
Anonymous Quiz
28%
ሀ. ኖስትሲዝም
32%
ለ. ንስጥሮሳዊነት
32%
ሐ. አርዮሳዊነት
8%
መ. ሴባልዮሳዊነት
.       ──•◈•─────•◈•─
                          የዕለቱ ጥቅስ
        ──•◈•─────•◈•─
“እግዚአብሔርም እነዚያን የአገር ከተሞች ባጠፋ ጊዜ አብርሃምን አሰበው፤ ሎጥ ተቀምጦበት የነበረውንም ከተማ ባጠፋ ጊዜ ከዚያ ጥፋት መካከል ሎጥን አወጣው።”
ዘፍጥረት 19፥29



ወደ ቻናሉ ለመ🀄️🀄️ል፦ @Holy_scriptures
8👍6
ቅዱሳት መጻሕፍት
#እምነት                    ክፍል-7 እግዚአብሔርን እንዴት እንመን? ወይንም ለማመን ምን እናድርግ? 2. በፍጹም ልብ እግዚአብሔርን መፈለግ “እናንተ ትሹኛላችሁ፥ በፍጹም ልባችሁም ከሻችሁኝ ታገኙኛላችሁ።”         ኤርምያስ 29፥13 3. በቅዱሳት መጻሕፍት ተአማኒነት ላይ ማመን “የእግዚአብሔር ሰው ፍጹምና ለበጎ ሥራ ሁሉ የተዘጋጀ ይሆን ዘንድ፥ የእግዚአብሔር መንፈስ ያለበት…
#እምነት


                   ክፍል-8


በቅዱሳት መጻሕፍት መሠረት እምነታችንን ለመጠበቅ ምን እናድረግ?


1. ጸሎት እና በእግዚአብሔር ላይ መደገፍ

“እኔ ግን እምነትህ እንዳይጠፋ ስለ አንተ ጸለይሁ፤ አንተም በተመለስህ ጊዜ ወንድሞችህን አበርታ።””
         ሉቃስ 22፥32 (አዲሱ መ.ት)

ኢየሱስ እምነታችንን ለመጠበቅ ጸሎት አስፈላጊ እንደሆነ ያስተምራል። በጸሎት የእግዚአብሔርን ብርታት መፈለግ እንዳለብን በማሳየት በግል ለጴጥሮስ አማለደ።

2. በእግዚአብሔር ቃል መበርታት

“እንግዲያስ እምነት ከመስማት ነው መስማትም በእግዚአብሔር ቃል ነው።”
             ሮሜ 10፥17

ቅዱሳት መጻሕፍትን አዘውትሮ ማጥናት እና ማሰላሰል እምነታችንን ያጠናክራል እናም ከጥርጣሬ ይጠብቀናል (መዝ. 119፡105)።

3. በፈተና ውስጥ መጽናት

“ወንድሞቼ ሆይ፥ የእምነታችሁ መፈተን ትዕግሥትን እንዲያደርግላችሁ አውቃችሁ፥ ልዩ ልዩ ፈተና ሲደርስባችሁ እንደ ሙሉ ደስታ ቍጠሩት”
            ያዕቆብ 1፥2-3

4. ከቅዱሳን ጋር ሕብረት ማድረግ

"ለፍቅርና ለመልካምም ሥራ እንድንነቃቃ እርስ በርሳችን እንተያይ፤ በአንዳንዶችም ዘንድ ልማድ እንደ ሆነው፥ መሰብሰባችንን አንተው እርስ በርሳችን እንመካከር እንጂ፤ ይልቁንም ቀኑ ሲቀርብ እያያችሁ አብልጣችሁ ይህን አድርጉ።
            ዕብራውያን 10፥24-25

በአማኞች ማህበረሰብ ውስጥ መሆን እምነትን በጋራ ለመበረታታት ይረዳል።

“በሐዋርያትም ትምህርትና በኅብረት እንጀራውንም በመቍረስ በየጸሎቱም ይተጉ ነበር።”
                 ሐዋርያት 2፥42

5. ከኃጢአትና ከፈተና መጠበቅ

"በመጠን ኑሩ ንቁም፥ ባላጋራችሁ ዲያብሎስ የሚውጠውን ፈልጎ እንደሚያገሣ አንበሳ ይዞራልና፤ በዓለም ያሉት ወንድሞቻችሁ ያን መከራ በሙሉ እንዲቀበሉ እያወቃችሁ በእምነት ጸንታችሁ ተቃወሙት።"
              1ኛ ጴጥሮስ 5፥8-9

እምነትን ለመጠበቅ ንቁ መሆን እና ኃጢአትን መቃወም አስፈላጊ ነው (ኤፌሶን 6፥10-11)።

6. በመንፈስ ቅዱስ ላይ መደገፍ

"እናንተ ግን፥ ወዳጆች ሆይ፥ ከሁሉ ይልቅ በተቀደሰ ሃይማኖታችሁ ራሳችሁን ለማነጽ እየተጋችሁ በመንፈስ ቅዱስም እየጸለያችሁ፥ ወደ ዘላለም ሕይወት የሚወስደውን የጌታችንን የኢየሱስ ክርስቶስን ምሕረት ስትጠባበቁ በእግዚአብሔር ፍቅር ራሳችሁን ጠብቁ።"
               ይሁዳ 1፥20-21

መንፈስ ቅዱስ አማኞችን በእምነት ያጠነክራል እና ይመራል (ዮሐ. 14፡26)።


ይቀጥላል...


ወደ ቻናሉ ለመ🀄️🀄️ል፦ @Holy_scriptures
👍171
.       ──•◈•─────•◈•─
                          የዕለቱ ጥቅስ
        ──•◈•─────•◈•─
“ስለ ሥጋችሁ ድካም እንደ ሰው ልማድ እላለሁ። ብልቶቻችሁ ዓመፃ ሊያደርጉ ለርኵስነትና ለዓመፃ ባሪያዎች አድርጋችሁ እንዳቀረባችሁ፥ እንደዚሁ ብልቶቻችሁ ሊቀደሱ ለጽድቅ ባሪያዎች አድርጋችሁ አሁን አቅርቡ።”
ሮሜ 6፥19



ወደ ቻናሉ ለመ🀄️🀄️ል፦ @Holy_scriptures
7👍3
መንፈስ ቅዱስ Holy Spirit
BibleProject - Amharic / አማርኛ
👉ርዕስ፦ መንፈስ ቅዱስ
በባይብል ፕሮጀክት፣ በአማርኛ ቋንቋ የተዘጋጀ


ወደ ቻናሉ ለመ🀄️🀄️ል፦ @Holy_scriptures
👍32
.       ──•◈•─────•◈•─
                          የዕለቱ ጥቅስ
        ──•◈•─────•◈•─
“ለሰው ፊትም ሳያደላ በእያንዳንዱ ላይ እንደ ሥራው የሚፈርደውን አባት ብላችሁ ብትጠሩ በእንግድነታችሁ ዘመን በፍርሃት ኑሩ።”
1ኛ ጴጥሮስ 1፥17



ወደ ቻናሉ ለመ🀄️🀄️ል፦ @Holy_scriptures
👍6
#እራሳችንን_እንመርምር

የእምነታችን ፍጻሜ ምንድነው? አማኝ ነን፣ ክርስቲያን፣ መንፈሳዊ ሰው ተባልን። እሺ፣ ፍጻሜው ምንድነው? ግቡስ? ለምን አመንን? ለምንስ ዋጋ እንከፍላለን?

“የእምነታችሁን ፍጻሜ እርሱም የነፍሳችሁን ድነት እየተቀበላችሁ ነውና።”
1ኛ ጴጥሮስ 1፥9 (አዲሱ መ.ት)

“እኛ ግን ነፍሳቸውን ሊያድኑ ከሚያምኑቱ ነን እንጂ ወደ ጥፋት ከሚያፈገፍጉ አይደለንም።”
ዕብራውያን 10፥39



ወደ ቻናሉ ለመ🀄️🀄️ል፦ @Holy_scriptures
👍42
በቅዱሳት መጻሕፍት ውስጥ ሐዋርያው ጴጥሮስ 1ኛ ጴጥሮስ መልእክት ሲጽፍ በመጻፍ የተባበረው ማን ነው?
Anonymous Quiz
29%
ሀ. እራሱ ነው የጻፈው ማንም አልተባበረውም
18%
ለ. ማርቆስ
43%
ሐ. ስልዋኖስ(ሲላስ)
6%
መ. ሉቃስ
4%
ሠ. ጢሞቴዎስ
👍72
.       ──•◈•─────•◈•─
                          የዕለቱ ጥቅስ
        ──•◈•─────•◈•─
“ንቁ፥ በሃይማኖት ቁሙ፥ ጎልምሱ ጠንክሩ።”
1ኛ ቆሮንቶስ 16፥13



ወደ ቻናሉ ለመ🀄️🀄️ል፦ @Holy_scriptures
🙏61
#መጻሕፍትን_በድምጽ

በቀጣይ
👉ርዕስ፦ አሸናፊው የክርስቲያን ኑሮ
የመጽሐፈ ኢያሱ ጥናት
ጸሐፊ፦ ዶ/ር አሳን ሬድፓዝ
🗣ትርጉም፦ ዋቅጅራ ጎባ

ወደ ቻናሉ ለመ🀄️🀄️ል፦ @Holy_scriptures
7👍1
የጥንት ቤተክርስቲያን ጉባዔዎች


ክፍል-፩


ቤተክርስቲያን በየወቅቱ ለሚደርስባት ውስጣዊ ችግር ማለት የአስተምህሮ ዝንፈት እና የሐሰት ትምህርትና አስተማሪዎች ሾልኮ መግባት በተደራጀ መልኩ መልስ ስትሰጥ ኖራለች። ምክንያቱንም አንድ ጊዜ በጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ፈጽሞ ለተሰጠን ሃይማኖት ጥንቃቄ ስለሚያስፈልግና አንዴ ከተዛነፈ ለመመለስ ስለሚያስቸግር ሳይቃጠል በቅጠል ስትል ኖራለች። ለዚህም ጥሩ ምሳሌ በሐዋርያት ሥራ ላይ ያለችዋ የመጀመሪያዋ ቤተክርስቲያን ለተከሰተባት ችግር ምን አይነት መፍትሄ እንደሰጠች ምሳሌነት እንመልከት። ከዚያም የጥንት ቤተክርስቲያን አባቶች ይህን ፈለግ በመከተል የተሳበሰቡበትን ዋና ዋና ጉባኤዎች በተከታታይ ክፍል እንመለከታለን

የሐዋርያት ሥራዋ ቤተክርስቲያን

ለምን ተሰበሰቡ?

“አንዳንዶችም ከይሁዳ ወረዱና፦ እንደ ሙሴ ሥርዓት ካልተገረዛችሁ ትድኑ ዘንድ አትችሉም ብለው ወንድሞችን ያስተምሩ ነበር።”
ሐዋርያት 15፥1
“ሐዋርያትና ሽማግሌዎችም ስለዚህ ነገር ለመማከር ተሰበሰቡ።”
ሐዋርያት 15፥6

ምን ወሰኑ?
"እንዲህም ጽፈው በእነርሱ እጅ ላኩ። ሐዋርያትና ሽማግሌዎች ወንድሞችም በአንጾኪያና በሶርያ በኪልቅያም ለሚኖሩ ከአሕዛብ ወገን ለሆኑ ወንድሞች ሰላምታ ያቀርባሉ። ያላዘዝናቸው ሰዎች ከእኛ ወጥተው፦ ትገረዙ ዘንድና ሕግን ትጠብቁ ዘንድ ይገባችኋል ብለው ልባችሁን እያወኩ በቃል እንዳናወጡአችሁ ስለ ሰማን፥ ስለ ጌታችን ስለ ኢየሱስ ክርስቶስ ስም ነፍሳቸውን ከሰጡት ከምንወዳቸው ከበርናባስና ከጳውሎስ ጋር የተመረጡትን ሰዎች ወደ እናንተ እንልክ ዘንድ በአንድ ልብ ሆነን ፈቀድን። ራሳቸውም ደግሞ በቃላቸው ያንኑ ይነግሩአችሁ ዘንድ ይሁዳንና ሲላስን ልከናል። ለጣዖት ከተሠዋ፥ ከደምም፥ ከታነቀም፥ ከዝሙትም ትርቁ ዘንድ ከዚህ ከሚያስፈልገው በቀር ሌላ ሸክም እንዳንጭንባችሁ እኛና መንፈስ ቅዱስ ፈቅደናልና፤ ከዚህም ሁሉ ራሳችሁን ብትጠብቁ በመልካም ትኖራላችሁ። ጤና ይስጣችሁ።"
ሐዋርያት 15፥23-29

የጥንት ቤተ ክርስቲያን ጉባኤዎች እነሆ፦

1. የኒቂያ የመጀመሪያው ጉባኤ (325 ዓ.ም.)

የኢየሱስ ክርስቶስ አምላክነት ጥያቄ ያነሳውን የአርዮስን ምንፍቅና ለመፍታት በንጉሠ ነገሥት ቆስጠንጢኖስ ቀዳማዊ የኒቂያ ጉባኤ ተጀመረ።

ቁልፍ ውጤት፦ ጉባኤው የኒቂያን የሃይማኖት መግለጫ አወጣ፣ ኢየሱስም እንደ አብ “አንድ አካል” (ሆሞኡሲዮስ/ "homoousios") መሆኑን በማረጋገጥ አርዮሳዊነት ውድቅ አደረገ።
ጉባዔው ውሳኔ ለመስጠት እስከ ሁለት ወር የፈጀ ሲሆን እስከ 318 ጳጳሳት ተሳትፈውበታል።

2. የቁስጥንጥንያ ጉባኤ (381 ዓ.ም.)

ዓላማው የኒቂያን ጉባዔ ውሳኔ ለማጽናት እና የቀሩትን የአርዮስን ትምህርት ያመጣውን ተፅዕኖዎች ለመፍታት በአፄ ቴዎዶስዮስ ቀዳማዊ የተጠራ ጉባኤ ነበር።

ቁልፍ ውሳኔዎች፡-

የኒቂያን የሃይማኖት መግለጫ አስፋፍቷል። መንፈስ ቅዱስን እንደ መለኮት እና ከአብና ከወልድ ጋር እኩል መሆኑን አውጇል። አርዮሳዊነትን፣ አፖሊናሪያኒዝም እና መቄዶኒያኒዝምን አውግዟል።
ተፅዕኖው፦ የጠነከረ የሥላሴ ሥነ-መለኮት እና የኒቂያ ጉባኤ ውሳኔ አጠናክሯል።


ይቀጥላል...


ምንጭ፦
👉Stevenson, J., & Frend, W. H. C. (2013). A new Eusebius: Documents illustrating the history of the Church to AD 337. SPCK
👉Gonzalez, J. L. (2010). The Story of Christianity: Volume 1, The Early Church to the Reformation. HarperOne.
👉Schaff, P. (1885). History of the Christian Church, Volume III: Nicene and Post-Nicene Christianity. Charles Scribner’s Sons.



ወደ ቻናሉ ለመ🀄️🀄️ል፦ @Holy_scriptures
12👍10🔥1
.       ──•◈•─────•◈•─
                          የዕለቱ ጥቅስ
        ──•◈•─────•◈•─
“ነገር ግን በጌታችንና በመድኃኒታችን በኢየሱስ ክርስቶስ ጸጋና እውቀት እደጉ። ለእርሱ አሁንም እስከ ዘላለምም ቀን ድረስ ክብር ይሁን፤ አሜን።”
2ኛ ጴጥሮስ 3፥18



ወደ ቻናሉ ለመ🀄️🀄️ል፦ @Holy_scriptures
👍62
Victorious Chrstian Life
Nigusse Denano
#መጻሕፍትን_በድምጽ

ርዕስ፦ አሸናፊው የክርስቲያን ኑሮ
የመጽሐፈ ኢያሱ ጥናት
ጸሐፊ፦ ዶ/ር አሳን ሬድፓዝ
ትርጉም፦ ዋቅጅራ ጎባ
ክፍል-1

ይቀጥላል...



ወደ ቻናሉ ለመ🀄️🀄️ል፦ @Holy_scriptures
👍6
ወደ ቻናሉ ለመ🀄️🀄️ል፦ @Holy_scriptures
1👍1
አሸናፊው የክርስቲያን ኑሮ.pdf
6.3 MB
👉ርዕስ፦ አሸናፊው የክርስቲያን ኑሮ
የመጽሐፈ ኢያሱ ጥናት
ጸሐፊ፦ ዶ/ር አሳን ሬድፓዝ
🗣ትርጉም፦ ዋቅጅራ ጎባ


ወደ ቻናሉ ለመ🀄️🀄️ል፦ @Holy_scriptures
👍11🙏4
.       ──•◈•─────•◈•─
                          የዕለቱ ጥቅስ
        ──•◈•─────•◈•─
“ጌታ ሆይ፥ ስለ ኃጢአታችንና ስለ አባቶቻችን በደል ኢየሩሳሌምና ሕዝብህ በዙሪያችን ላሉት ሁሉ መሰደቢያ ሆነዋልና እንደ ጽድቅህ ሁሉ ቍጣህና መዓትህ ከከተማህ ከኢየሩሳሌም ከቅዱስ ተራራህ እንዲመለስ እለምንሃለሁ።”
ዳንኤል 9፥16



ወደ ቻናሉ ለመ🀄️🀄️ል፦ @Holy_scriptures
2👍2
Victorious Chrstian Life
Nigusse Denano
#መጻሕፍትን_በድምጽ

ርዕስ፦ አሸናፊው የክርስቲያን ኑሮ
የመጽሐፈ ኢያሱ ጥናት
ጸሐፊ፦ ዶ/ር አሳን ሬድፓዝ
ትርጉም፦ ዋቅጅራ ጎባ
ክፍል-2

ይቀጥላል...



ወደ ቻናሉ ለመ🀄️🀄️ል፦ @Holy_scriptures
👍3