ቅዱሳት መጻሕፍት
7.45K subscribers
1.35K photos
61 videos
332 files
796 links
በዚህ ቻናል

👉ቅዱሳት መጻሕፍት ይጠናሉ::
👉መጽሐፍ ቅዱሳዊ ትምህርቶች ይቀርባሉ::
👉 ለቅዱሳት መጽሐፍት ጥናት የሚያግዙ መጻሕፍት ይለቀቃሉ።

⭐️⭐️⭐️⭐️⭐️

@Holy_scriptures
Download Telegram
.    ==❀❀❀===❀❀❀==      
              የዕለቱ ጥቅስ 
     ==❀❀❀===❀❀❀==
“እናንተ ግብዞች ጻፎችና ፈሪሳውያን፥ ከአዝሙድና ከእንስላል ከከሙንም አሥራት ስለምታወጡ፥ ፍርድንና ምሕረትን ታማኝነትንም፥ በሕግ ያለውን ዋና ነገር ስለምትተዉ፥ ወዮላችሁ፤ ሌላውን ሳትተዉ ይህን ልታደርጉ ይገባችሁ ነበር።”
ማቴዎስ 23፥23



ወደ ቻናሉ ለመ🀄️🀄️ል፦ @Holy_scriptures
🔥3👍1
ዓላማ መር ህይወት- ቀን 32_Purpose driven Life - Day 32_ alama mer hiywet…
PETERiCH (I am empty without Jesus)
#መጻሕፍትን_በድምጽ

👉ርዕስ፦ ዓላማ መር ሕይወት
✍️ጸሐፊ፦ ሪክ ዋረን
🗣ትርጉም፦ ኢቫንጀሊካል ቴዎሎጂካል ኮሌጅ
🗒ክፍል፦ 32 (እግዚአብሔር በሰጠን መጠቀም)


ይቀጥላል...


ወደ ቻናሉ ለመ🀄️🀄️ል፦ @Holy_scriptures
.    ==❀❀❀===❀❀❀==      
              የዕለቱ ጥቅስ 
     ==❀❀❀===❀❀❀==
“ሙሴም የግብፆችን ጥበብ ሁሉ ተማረ፥ በቃሉና በሥራውም የበረታ ሆነ።”
            ሐዋርያት 7፥22



ወደ ቻናሉ ለመ🀄️🀄️ል፦ @Holy_scriptures
6👍1
ዓላማ መር ህይወት- ቀን 33_Purpose driven Life - Day 33_ alama mer hiywet…
PETERiCH (I am empty without Jesus)
#መጻሕፍትን_በድምጽ

👉ርዕስ፦ ዓላማ መር ሕይወት
✍️ጸሐፊ፦ ሪክ ዋረን
🗣ትርጉም፦ ኢቫንጀሊካል ቴዎሎጂካል ኮሌጅ
🗒ክፍል፦ 33 (የእውነተኛ አገልጋዮች ፍሬ)


ይቀጥላል...


ወደ ቻናሉ ለመ🀄️🀄️ል፦ @Holy_scriptures
👍2
ወደ ቻናሉ ለመ🀄️🀄️ል፦ @Holy_scriptures
👍3
እግዚአብሔርን መምሰል.pdf
3.2 MB
👉ርዕስ፦ እግዚአብሔርን መምሰል
ጸሐፊ፦ ወንጌላዊ ያሬድ ጥላሁን



ወደ ቻናሉ ለመ🀄️🀄️ል፦ @Holy_scriptures
👍1
.    ==❀❀❀===❀❀❀==      
              የዕለቱ ጥቅስ 
     ==❀❀❀===❀❀❀==
“እግዚአብሔር በተስፋ ለሚጠብቁት ለምትሻውም ነፍስ መልካም ነው።”
ሰቆ. 3፥25


ወደ ቻናሉ ለመ🀄️🀄️ል፦ @Holy_scriptures
🥰42👍1🔥1
ዓላማ መር ህይወት- ቀን 34_Purpose driven Life - Day 34_ alama mer hiywet…
PETERiCH (I am empty without Jesus)
#መጻሕፍትን_በድምጽ

👉ርዕስ፦ ዓላማ መር ሕይወት
✍️ጸሐፊ፦ ሪክ ዋረን
🗣ትርጉም፦ ኢቫንጀሊካል ቴዎሎጂካል ኮሌጅ
🗒ክፍል፦ 34 (እንደ አገልጋይ ማሰብ)


ይቀጥላል...


ወደ ቻናሉ ለመ🀄️🀄️ል፦ @Holy_scriptures
👍3
#ከተማ_ወይም_ቦታ_በቅዱሳት_መጻሕፍት


#ለኪሶ

ለኪሶ በዕብራይስጥ መጽሐፍ ቅዱስ (ብሉይ ኪዳን) ውስጥ በተደጋጋሚ የምትጠቀስ ጥንታዊት ከተማ ናት። በጥንቷ ይሁዳ በሸፌላ ግዛት የምትገኝ ጉልህ የከነዓናውያን እና በኋላም የእስራኤል ከተማ ነበረች። ላኪሶ ብዙውን ጊዜ ከወታደራዊ ዘመቻዎች ጋር የተቆራኘች ሲሆን እስራኤላውያን ከነዓንን በወረሩበት ወቅት እንዲሁም በአሦራውያን እና በባቢሎናውያን ወረራ ወቅት ተጠቅሷል።

ለላኪሽ መጽሐፍ ቅዱሳዊ ማጣቀሻዎች


ከነዓንን ድል ማድረግ፡- ለኪሶ በመጀመሪያ የተጠቀሰችው እስራኤላውያን ከነዓንን በወረሩበት ጊዜ ከተቆጣጠሩት ከተሞች አንዷ ነች (ኢያሱ 10፥3-5፣ 31-32)። የላኪሶ ንጉሥ ኢያሱን ለመውጋት ከአሞራውያን ነገሥታት ጥምረት ፈጥረው ተዋጉ ነገር ግን ተሸነፉ።

የሮብዓም ምሽግ፡- በ2ኛ ዜና 11፥9 ላይ ለኪሶ በይሁዳ ንጉሥ በሮብዓም ከተመሸጉ ከተሞች አንዷ ሆና ተዘርዝራለች።

የአሦር ከበባ፡- ለኪሶ በ701 ዓመተ ዓለም በይሁዳ ላይ ባካሄደው የአሦር ንጉሥ ሰናክሬም ዘመቻ አውድ ውስጥ በዋነኝነት ተጠቅሳለች። የሌኪሶን ከበባ በ2ኛ ነገሥት 18፥13-17 እና 2ኛ ዜና 32፥9 ላይ ተጠቅሳለች። በነነዌ በሚገኘው የሰናክሬም ቤተ መንግስት የላኪሽ አርኪኦሎጂያዊ ማስረጃዎች ይህንን ክስተት ያረጋግጣሉ።

የባቢሎናውያን ወረራ፡- በ586 ከክርስቶስ ልደት በፊት ኢየሩሳሌም ከመፍረሷ በፊት በባቢሎናውያን እጅ ከወደቁ የመጨረሻዎቹ የተመሸጉ ከተሞች መካከል ላኪሶ በኤርምያስ 34፥7 ላይ ተጠቅሳለች።


ምንጭ፦ Ussishkin, D. (2004). The renewed archaeological excavations at Lachish (1973–1994). Tel Aviv: Emery and Claire Yass Publications in Archaeology.



ወደ ቻናሉ ለመ🀄️🀄️ል፦ @Holy_scriptures
👍4
በቅዱሳት መጻሕፍት ውስጥ ይሁዳ በባቢሎን ሲማረክ በስንት ዙር ነው ምርኮኞች ወደ ባቢሎን የተጋዙት?
Anonymous Quiz
3%
ሀ. በአንድ
32%
ለ. በሁለት
54%
ሐ. በሦስት
10%
መ. በአራት
🔥6🥰1
.    ==❀❀❀===❀❀❀==      
              የዕለቱ ጥቅስ 
     ==❀❀❀===❀❀❀==
“እነሆ፥ የእኅትሽ የሰዶም ኃጢአት ይህ ነበረ፤ ትዕቢት እንጀራን መጥገብ መዝለልና ሥራ መፍታት በእርስዋና በሴቶች ልጆችዋ ነበረ፥ የችግረኛውንና የድሀውንም እጅ አላጸናችም።”
ሕዝቅኤል 16፥49



ወደ ቻናሉ ለመ🀄️🀄️ል፦ @Holy_scriptures
👍63🔥1
ዓላማ መር ህይወት- ቀን 35_Purpose driven Life - Day 35_ alama mer hiywet…
PETERiCH (I am empty without Jesus)
#መጻሕፍትን_በድምጽ

👉ርዕስ፦ ዓላማ መር ሕይወት
✍️ጸሐፊ፦ ሪክ ዋረን
🗣ትርጉም፦ ኢቫንጀሊካል ቴዎሎጂካል ኮሌጅ
🗒ክፍል፦ 35 (የእግዚአብሔር ኃይል በድካም ውስጥ)


ይቀጥላል...


ወደ ቻናሉ ለመ🀄️🀄️ል፦ @Holy_scriptures
ትንሣኤ ሙታን


                 ወ/ዊ ያሬድ ጥላሁን


           ክፍል-1

የክርስትና እምነት ምንድነው? ይህ ጥያቄ በአንደኛው ክፍለ ዘመን ለሚኖር ሰው ቢቀርብለት፣ ያለምንም ማመንታት “የትንሣኤ እንቅስቃሴ ነው!” ሊል እንደሚችል መገመት አያስቸግርም። ለዚህም በርካታ ማረጋገጫዎች አሉ። ከብዙዎቹ ጥቂቶቹን ላንሳ፡ -

የትንሣኤው ምሥክሮች፡ - ጌታ ኢየሱስ አገልግሎቱን የጀመረው ምሥክሮቹ የሚሆኑትን የዛሬ ደቀመዛሙርት የነገዎቹንም ሐዋርያት በመጥራት ነበር። የኃይማኖት መናኽሪያ ከሆነችው ኢየሩሳሌም ርቆ መልካም ነገር ሊወጣባት ይችላል ተብላ በማትገመተው የገሊላዋ ናዝሬት ሰዎችን መጥራት ጀመረ። ያልተማሩ ማንበብና መጻፍ የማያውቁ አሣ አጥማጆችና ቀራጮችን ሰብሰበ። በርግጥ እንኳን ሌላው ሰው፣ ራሳቸውም ቢሆኑ የተጠሩበትን ዓላማ በጊዜው አልተረዱም። የወንጌላውያኑን ትረካ በትዕግሥትና በጥሞና ስንከታተል ግን የተጠሩበት ዓላማ ፍንትው ብሎ ይታየናል። ይኽውም የትንሣኤው ምሥክሮች እንዲሆኑ ነው።

መወለዱ ምሥክር አላስፈለገውም፣ ምክንያቱም ሰው ሁሉ ይወለዳል፣ በሰዎች መሃል መኖሩ የመወለዱ ማርጋገጫ ነው። መጠመቁ ምሥክር አላስፈለገውም፣ ማንም ሰው ይጠመቃላ! ሞቱም ቢሆን ምሥክር አላስፈለገውም፣ የተሰቀለውና የሞተው በሰው ሁሉ ፊት ነዋ! ካህናት ነበሩ፣ ፈሪሳውያን ነበሩ፣ ጻህፍት ነበሩ፣ ወዳጆቹ ነበሩ፣ የሮማ ወታደሮች ነበሩ፣ ምኑ ቅጡ በኢየሩሳሌም የሚኖሩ ሁሉ የሞቱን ዜና ሰምቷል፣ ደግሞም ሰው ሁሉ ይሞታል! ስለዚህ ምሥክር አላስፈለገውም። ነገር ግን በአካል ከሙታን መነሳቱ ምስክሮች አስፍልገውታል። ምክንያቱም የሞተ ሰው ተነስቶ አያውቅም፣ የኢየሱስ ትንሳኤ ከሞት መንቃትና ነፍስ መዝራት ሳይሆን ሙሉ በሙሉ በተለወጠና ልዕለ ተፈጥሮአዊ በሆነ የሕይወት ኃይል ነው የተነሳው። ተነስቶም አርባ ቀናት በብዙ ማስረጃ የታየው ለእነዚሁ ለመረጣቸው ምሥክሮቹ ነው። ምንም እንኩዋ ምሥክሮቹ አብና መንፈስ ቅዱስ፣ የነብያት ድምፆች የሆኑት ቅዱሳት መጻህፍት ጭምር ቢሆኑም የሐዋርያቱ ምሥክርነት ግን ድርሻው የማይናቅ ነው፣ ለሰው ልጅ ቅርብ ናቸዋ!   

“ሐዋርያትም የጌታን የኢየሱስ ክርስቶስን ትንሣኤ በታላቅ ኃይል ይመሰክሩ ነበር፤ በሁሉም ላይ ታላቅ ጸጋ ነበረባቸው።”
ሐዋርያት 4፥33

“ከኤፊቆሮስ ወገንና ኢስጦኢኮችም ከተባሉት ፈላስፎች አንዳንዶቹ ከእርሱ ጋር ተገናኙ። አንዳንዶቹም፦ ይህ ለፍላፊ ምን ሊናገር ይወዳል? አሉ፤ ሌሎችም የኢየሱስንና የትንሣኤውን ወንጌል ስለ ሰበከላቸው፦ አዲሶችን አማልክት የሚያወራ ይመስላል አሉ።”
ሐዋርያት 17፥18


ይቀጥላል...


ምንጭ:- semayawithought.com



ወደ ቻናሉ ለመ🀄️🀄️ል፦ @Holy_scriptures
👍122
. ──•◈•─────•◈•─
የዕለቱ ጥቅስ
──•◈•─────•◈•─
“ይህም ዳንኤል በዳርዮስ መንግሥትና በፋርሳዊው በቂሮስ መንግሥት ኑሮው ተቃናለት።”
ዳንኤል 6፥28



ወደ ቻናሉ ለመ🀄️🀄️ል፦ @Holy_scriptures
👍6😁1
ዓላማ መር ህይወት- ቀን 36_Purpose driven Life - Day 36_ alama mer hiywot…
PETERiCH (I am empty without Jesus)
#መጻሕፍትን_በድምጽ

👉ርዕስ፦ ዓላማ መር ሕይወት
✍️ጸሐፊ፦ ሪክ ዋረን
🗣ትርጉም፦ ኢቫንጀሊካል ቴዎሎጂካል ኮሌጅ
🗒ክፍል፦ 36 (የተሠራኸው ለተልዕኮ ነው)


ይቀጥላል...


ወደ ቻናሉ ለመ🀄️🀄️ል፦ @Holy_scriptures
👍1
የስደት መንገድ The Way of the Exile
BibleProject - Amharic / አማርኛ
👉ርዕስ፦ የግዞት(የስደት) መንገድ
በባይብል ፕሮጀክት፣ በአማርኛ ቋንቋ የተዘጋጀ


ወደ ቻናሉ ለመ🀄️🀄️ል፦ @Holy_scriptures
👍1
#የእግዚአብሔር_ቃል_ምን_ይላል?


ሉቃስ 11
¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯
⁹ እኔም እላችኋለሁ፦ ለምኑ፥ ይሰጣችሁማል፤ ፈልጉ፥ ታገኙማላችሁ፤ መዝጊያን አንኳኩ፥ ይከፈትላችሁማል።
¹⁰ የሚለምን ሁሉ ይቀበላልና፥ የሚፈልግም ያገኛል፥ መዝጊያውንም ለሚያንኳኳው ይከፈትለታል።
¹¹ አባት ከሆናችሁ ከእናንተ ከማንኛችሁም ልጁ እንጀራ ቢለምነው፥ እርሱም ድንጋይ ይሰጠዋልን? ዓሣ ደግሞ ቢለምነው በዓሣ ፋንታ እባብ ይሰጠዋልን?
¹² ወይስ እንቍላል ቢለምነው ጊንጥ ይሰጠዋልን?
¹³ እንኪያስ እናንተ ክፉዎች ስትሆኑ ለልጆቻችሁ መልካም ስጦታ መስጠት ካወቃችሁ፥ በሰማይ ያለው አባት ለሚለምኑት እንዴት አብልጦ መንፈስ ቅዱስን ይሰጣቸው?



ወደ ቻናሉ ለመ🀄️🀄️ል፦ @Holy_scriptures
16👍2
.       ──•◈•─────•◈•─
                          የዕለቱ ጥቅስ
        ──•◈•─────•◈•─
“ብቻ የአምላክህን የእግዚአብሔርን ሕግ ትጠብቅ ዘንድ እግዚአብሔር ጥበብንና ማስተዋልን ይስጥህ፥ በእስራኤልም ላይ ያሠልጥንህ።”
1 ዜና 22፥12



ወደ ቻናሉ ለመ🀄️🀄️ል፦ @Holy_scriptures
5👍1
ዓላማ መር ህይወት- ቀን 37_Purpose driven Life - Day 37_ alama mer hiywet…
PETERiCH (I am empty without Jesus)
#መጻሕፍትን_በድምጽ

👉ርዕስ፦ ዓላማ መር ሕይወት
✍️ጸሐፊ፦ ሪክ ዋረን
🗣ትርጉም፦ ኢቫንጀሊካል ቴዎሎጂካል ኮሌጅ
🗒ክፍል፦ 37 (የሕይወት መልዕክትህን ማካፈል)


ይቀጥላል...


ወደ ቻናሉ ለመ🀄️🀄️ል፦ @Holy_scriptures
1👍1
ቅዱሳት መጻሕፍት
ትንሣኤ ሙታን                  ወ/ዊ ያሬድ ጥላሁን            ክፍል-1 የክርስትና እምነት ምንድነው? ይህ ጥያቄ በአንደኛው ክፍለ ዘመን ለሚኖር ሰው ቢቀርብለት፣ ያለምንም ማመንታት “የትንሣኤ እንቅስቃሴ ነው!” ሊል እንደሚችል መገመት አያስቸግርም። ለዚህም በርካታ ማረጋገጫዎች አሉ። ከብዙዎቹ ጥቂቶቹን ላንሳ፡ - የትንሣኤው ምሥክሮች፡ - ጌታ ኢየሱስ አገልግሎቱን የጀመረው…
ትንሣኤ ሙታን


                            ወ/ዊ ያሬድ ጥላሁን


                 ክፍል-2


እምነት፡-  ሐዋርያቱ ከሥፍራ ሥፍራ እየተዘዋወሩ ወንጌልን ሰበኩ። ለመሆኑ የሰበኩት የምሥራች ወንጌል ምንድን ነበር? ስለ ሰው ልጆች ኃጢአት የተሰዋው መሢሁ ኢየሱስ ከሙታን መነሳቱ ነው። ስለዚህ ያወጁት ትንሳኤውን ነው። ሉቃስ በሐዋ. 4፥33  “ሐዋርያትም የጌታን የኢየሱስ ክርስቶስ ትንሳኤ በታላቅ ኃይል ይመሠክሩ ነበር፣ በሁሉም ላይ ታላቅ ፀጋ ነበረባቸው” ይለናል። የኢየሩሳሌም ሐዋርያት ሆኑ የአሕዛብ ሐዋርያ ሊሆን የተሾመው ጳውሎስ ከትንሣኤው ውጪ የሰበኩት ወንጌል የለም። የተሰበከላቸውም ሰዎች እንዲያምኑ የተጠየቁት ሌላ ሳይሆን ስለ በደላችው የሞተው ኢየሱስ ከሙታን መነሣቱን ነው። እንደ ሮሜ መልዕክት ከሆነ መጽደቅም ሆነ መዳን የሚገኝው ሰው የኢየሱስ ክርስቶስን ትንሣኤ ሲያምን ብቻ ነው። ለዚህም ይህን ክፍል እንደ ዋቢ መመልከት ይበቃል። “ኢየሱስ ጌታ እንደሆነ በአፍህ ብትመሠክር፣ እግዚአብሔርም ከሙታን እንዳነሣው በልብህ ብታምን ትድናለህ” ሮሜ 10፥9። ስለዚህ በአዲስ ኪዳን የሚሠበከውም ትንሣኤ፣ የሚታመነውም ትንሳኤ ነው። አብርሃም የእምነት አባት ነው። “የእምነት አባት” ምን ማለት ነው? እግዚአብሔር የአብርሃምን እምነት ደረጃና ልክ አድርጎ መድቦታል። የሚቀበለው፣ የሚያከብረውና በምላሹም ጽድቅን የሚያጎናፅፈው እምነት የአብርሃም ዓይነት እምነት ነው። የአብርሃም እምነት ምን ነበር? ትንሳኤ ነበር። እግዚአብሔር ለሙታን ሕይወትን ይሰጣል፣ የሞቱትን ያስነሣል ብሎ አመነና እምነቱ ጽድቅ ሆኖ ተቆጠረለት። አብርሃም ትንሳኤን በጥቂቱም ቢሆን የተለማመደው በራሱ ሰውነትና በሚስቱ በሣራ ሰውነት ላይ ነው። “የመቶ ዓመትም ሽማግሌ ስለሆነ እንደ ሙት የሆነውን የራሱን ሥጋና የሣራን ማህፀን ሙት መሆኑን በእምነቱ ሳይደክም ተመለከተ . . . ስለዚህም ደግሞ ጽድቅ ሆኖ ተቆጠረለት” ሮሜ 4፡19፣22። ስለዚህ ማንም ‘እግዚአብሔር ሙታንን ያሥነሣል፣ ኢየሱስንም ከሙታን አስነሥቶታል’ ብሎ ቢያምን በእርግጥ የአብርሃም ልጅ ሆኗል፣ እግዚአብሔርም እምነቱን ጽድቅ አድርጎ ቆጥሮለታል። ለዚህ ነው ‘የአዲስ ኪዳን እምነት የትንሣኤ እምነት ነው’ የምንለው።

 
የእግዚአብሔር ማንነት፡- እግዚአብሔር ሁሉን ቻይ ነው። ነገር ግን መታወቅም ሆነ መታመን የሚፈልገው በአንድ ነገር ነው። “ለሙታን ሕይወትን የሚሰጥ፣ የሌለውንም እንዳለ አድርጎ የሚጠራ አምላክ” ሆኖ። [ሮሜ 4፡17] ለምን? እግዚአብሔር የሕይወት መንፈስ ነዋ! እርሱ ራሱ የዘላለም ሕይወት ነው። የማይሞት፣ የማይጠፋ፣ የማያልፍ የሕይወት ኃይል! ይህ ሕይወት የሕብረት ሕይወት ነው፤ ከአንድ በላይ የሆኑ አካላት በአንድ ጊዜ ሊካፈሉ የሚችሉት አስገራሚ ሕይወት። እግዚአብሔር በፀጋው ባለጠግነት ይህን ሕይወት ከሰው ልጅ ጋር ሊካፈለው  ወደደ። ትንሣኤን ከሥላሴ አንፃር ብናየው፣ ኢየሱስን ከሙታን ያስነሳው ማነው? ለሚለው ጥያቄ የተለያዩ መልሶች እናገኛለን። መጽሐፍ ቅዱስ እግዚአብሔር አብ እንዳስነሣው ይነግረናል፣ ነገር ግን አንድ ሥፍራ ጌታ ራሱ “ነፍሴን ደግሞ አነሣት ዘንድ አኖራለሁና፣ ስለዚህ አብ ይወደኛል። እኔ በፈቃዴ አኖራታለሁ እንጂ ከእኔ ማንም አይወስዳትም። ላኖራት ሥልጣን አለኝ ደግሞም ላነሣት ሥልጣን አለኝ፣ ይህችን ትዕዛዝ ከአባቴ ተቀበልሁ” ዮሐ. 10፡18  ሲል እናነባለን። በሌሎች ክፍሎች ደግሞ መንፈስ ቅዱስ እንዳስነሳው እናነባለን። እነዚህን ክፍሎች ስንገጣጥማቸው የምናገኝው ሥዕል አብ፣ ወልድ፣ መንፈስ ቅዱስ አንድ አምላክ ሙታንን የሚያነሣ የትንሣኤ አምላክ መሆኑን ነው።   

ይቀጥላል... 


ምንጭ:- semayawithought.com



ወደ ቻናሉ ለመ🀄️🀄️ል፦ @Holy_scriptures
👍123