ቅዱሳት መጻሕፍት
7.45K subscribers
1.35K photos
61 videos
332 files
796 links
በዚህ ቻናል

👉ቅዱሳት መጻሕፍት ይጠናሉ::
👉መጽሐፍ ቅዱሳዊ ትምህርቶች ይቀርባሉ::
👉 ለቅዱሳት መጽሐፍት ጥናት የሚያግዙ መጻሕፍት ይለቀቃሉ።

⭐️⭐️⭐️⭐️⭐️

@Holy_scriptures
Download Telegram
በቅዱሳት መጻሕፍት ውስጥ ሐዋርያው ቅዱስ ጳውሎስ ወንጌል በመስበክ እና በማስተማር ከሌሎች ቦታዎች ይልቅ ረጅም ጊዜ የተቀመጠው የት ከተማ ነው?
Anonymous Quiz
33%
ሀ. ቆሮንቶስ
47%
ለ. ኤፌሶን
4%
ሐ. ፊልጵስዩስ
9%
መ. ተሰሎንቄ
7%
ሠ. ኢየሩሳሌም
7
.    ==❀❀❀===❀❀❀==      
              የዕለቱ ጥቅስ 
     ==❀❀❀===❀❀❀==
“ነገር ግን ጽና፥ እጅግ በርታ፤ ባሪያዬ ሙሴ ያዘዘህን ሕግ ሁሉ ጠብቅ፥ አድርገውም፤ በምትሄድበትም ሁሉ እንዲከናወንልህ ወደ ቀኝም ወደ ግራም አትበል።”
ኢያሱ 1፥7



ወደ ቻናሉ ለመ🀄️🀄️ል፦ @Holy_scriptures
👍61
Audio
#መጻሕፍትን_በድምጽ

👉ርዕስ፦ ዓላማ መር ሕይወት
✍️ጸሐፊ፦ ሪክ ዋረን
🗣ትርጉም፦ ኢቫንጀሊካል ቴዎሎጂካል ኮሌጅ
🗒ክፍል፦ 29 (የተሰጠህን ሥራ መቀበል)


ይቀጥላል...


ወደ ቻናሉ ለመ🀄️🀄️ል፦ @Holy_scriptures
እግዚአብሔር በየቀኑ በሕይወታቸው ውስጥ የሚያደርገውን በጎነት የማናስተውል ብዙ ነን። ከእንቅልፋችን በሰላምና ጤና ነቅተን የማለዳዋን ፀሓይ ለማየት ስለመታደላችን ምስጋና ስናቀርብ አንታይም። በመሰለን መንገድ ያልተከናወነ ነገር ብንቀበልም፥ መብታችን እንጂ ቸርነት አይመስለንም። በሕይወት መኖር እንደ ቀልድ ይታለፋል። ስፍር ቍጥር የሌላቸው ቅጽበታዊ ዕለታዊና የዘመናችን ሙሉ የበጎነት ስጦታዎቹ በቸልታ ተወርውረው ይኖራሉ። እኛ ሰዎች እንገርማለን እኮ። እናሳዝንማለን።

የገዛ ምራቁ ትን ብሎት ሕይወቱን በሰከንዶች ውስጥ ሊያጣ የሚችል ሰው በሕይወት መቈየት የቻለው በእግዚአብሔር ምሕረት መኾኑን ይዘነጋል። ፍጥረት ሕግና ሥርዐት ጠብቆ የሚኖረው በጌታ ነው። ምድር በአምላካዊ ቸርነት ተጠብቃ ሕይወት ያብብባታል። ሥጋት በወጠረው ዓለም ውስጥ በሰላም ወጥተን መግባት መቻላችን ትርጕሙ የሚገባን አገር ምድሩ ሲታመስ መኾን የለበትም።

ከስንት አስፈሪ ነገሮች ተረፍን? ስንቱን የሞት ሸለቆዎች በምሕረቱ ተሻገርን? ስንት ጊዜ ወድቀን ስንት ጊዜ በቸርነቱ ተደግፈን ተነሣን? ዛሬስ ቢኾን ከእጆቹ ምን ተቀብለናል? ወዳጃችን፥ "ነፍሴ ሆይ፥ ውለታውን አትርሺ" ማለቱ ቁምነገረኝነት ያለው ሰው በመኾኑ ነው። ጌታችን ማዳኑ ዛሬም አዲስ ነው።


መጋቢ ሰሎሞን አበበ ገብረ መድኅን



ወደ ቻናሉ ለመ🀄️🀄️ል፦ @Holy_scriptures
🙏92👍1😁1
.    ==❀❀❀===❀❀❀==      
              የዕለቱ ጥቅስ 
     ==❀❀❀===❀❀❀==
“እናንተንም ነውርና ነቀፋ የሌላችሁና ቅዱሳን አድርጎ በእርሱ ፊት ያቀርባችሁ ዘንድ፥ በፊት የተለያችሁትን ክፉ ሥራችሁንም በማድረግ በአሳባችሁ ጠላቶች የነበራችሁትን አሁን በሥጋው ሰውነት በሞቱ በኩል አስታረቃችሁ።”
ቆላስይስ 1፥21-22




ወደ ቻናሉ ለመ🀄️🀄️ል፦ @Holy_scriptures
8
ዓላማ መር ህይወት- ቀን 30_Purpose driven Life - Day 30_ alama mer hiywet…
PETERiCH (I am empty without Jesus)
#መጻሕፍትን_በድምጽ

👉ርዕስ፦ ዓላማ መር ሕይወት
✍️ጸሐፊ፦ ሪክ ዋረን
🗣ትርጉም፦ ኢቫንጀሊካል ቴዎሎጂካል ኮሌጅ
🗒ክፍል፦ 30 (የተበጀኸው እግዚአብሔርን ለማገልገል ነው)


ይቀጥላል...


ወደ ቻናሉ ለመ🀄️🀄️ል፦ @Holy_scriptures
👍4
ቅዱሳት መጻሕፍት
#እምነት                    ክፍል-6 እምነት መሠረቱ ምንድነው? የምናምነው እግዚአብሔርን ወይስ እንዲሆንልን የምንፈልገውን ነገር? እምነቱ መሠረቱ እግዚአብሔር እና የእግዚአብሔር  ቃል ነው። ከዚህ ውጪ የሆነ "እምነት" የሚባለው ነገር ክርስቲያናዊ እምነት አይደለም! ቅዱሳት መጻሕፍትም ይህን እውነት ሳይሸፋፍኑ እንዲህ ይነግሩናል፦ “በእግዚአብሔር የታመነ እምነቱም እግዚአብሔር የሆነ…
#እምነት


                   ክፍል-7


እግዚአብሔርን እንዴት እንመን? ወይንም ለማመን ምን እናድርግ?

2. በፍጹም ልብ እግዚአብሔርን መፈለግ

“እናንተ ትሹኛላችሁ፥ በፍጹም ልባችሁም ከሻችሁኝ ታገኙኛላችሁ።”
        ኤርምያስ 29፥13

3. በቅዱሳት መጻሕፍት ተአማኒነት ላይ ማመን

“የእግዚአብሔር ሰው ፍጹምና ለበጎ ሥራ ሁሉ የተዘጋጀ ይሆን ዘንድ፥ የእግዚአብሔር መንፈስ ያለበት መጽሐፍ ሁሉ ለትምህርትና ለተግሣጽ ልብንም ለማቅናት በጽድቅም ላለው ምክር ደግሞ ይጠቅማል።”
        2ኛ ጢሞቴዎስ 3፥16-17

4. ኢየሱስ ክርስቶስን የእግዚአብሔር ልጅ ነው ብሎ ማመን

“በእርሱ የሚያምን ሁሉ የዘላለም ሕይወት እንዲኖረው እንጂ እንዳይጠፋ እግዚአብሔር አንድያ ልጁን እስኪሰጥ ድረስ ዓለሙን እንዲሁ ወዶአልና።”
         ዮሐንስ 3፥16

5. እምነትንና ጥበብን እንዲሰጠን እግዚአብሔርን መለመን

"ከእናንተ ግን ማንም ጥበብ ቢጎድለው፥ ሳይነቅፍ በልግስና ለሁሉ የሚሰጠውን እግዚአብሔርን ይለምን፥ ለእርሱም ይሰጠዋል። ነገር ግን በምንም ሳይጠራጠር በእምነት ይለምን፤ የሚጠራጠር ሰው በነፋስ የተገፋና የተነቃነቀ የባሕርን ማዕበል ይመስላልና።"
             ያዕቆብ 1፥5-6

6. የእግዚአብሔርን ቃል መታዘዝ

“እምነት ከሥራው ጋር አብሮ ያደርግ እንደ ነበረ፥ በሥራም እምነት እንደ ተፈጸመ ትመለከታለህን?”
         ያዕቆብ 2፥22

7. በእግዚአብሔር ተስፋዎች ማመን

“አቤቱ፥ አንተ ተስፋዬ ነህና፥ እግዚአብሔር ሆይ፥ ከታናሽነቴ ጀምረህ መታመኛዬ ነህና።”
         መዝሙር 71፥5

8. ከሌሎች አማኞች ጋር ሕብረት ማድረግ

"የተስፋን ቃል የሰጠው የታመነ ነውና እንዳይነቃነቅ የተስፋችንን ምስክርነት እንጠብቅ፤ ለፍቅርና ለመልካምም ሥራ እንድንነቃቃ እርስ በርሳችን እንተያይ፤ በአንዳንዶችም ዘንድ ልማድ እንደ ሆነው፥ መሰብሰባችንን አንተው እርስ በርሳችን እንመካከር እንጂ፤ ይልቁንም ቀኑ ሲቀርብ እያያችሁ አብልጣችሁ ይህን አድርጉ።"
            ዕብራውያን 10፥23-25


ይቀጥላል...



ወደ ቻናሉ ለመ🀄️🀄️ል፦ @Holy_scriptures
👍63
.    ==❀❀❀===❀❀❀==      
              የዕለቱ ጥቅስ 
     ==❀❀❀===❀❀❀==
“በቸርነትህ የተቤዠሃቸውን ሕዝብህን መራህ፤ በኃይልህ ወደ ቅዱስ ማደሪያህ አገባሃቸው።”
ዘጸአት 15፥13



ወደ ቻናሉ ለመ🀄️🀄️ል፦ @Holy_scriptures
👍72🥰2
ዓላማ መር ህይወት- ቀን 31_Purpose driven Life - Day 31_ alama mer hiywet…
PETERiCH (I am empty without Jesus)
#መጻሕፍትን_በድምጽ

👉ርዕስ፦ ዓላማ መር ሕይወት
✍️ጸሐፊ፦ ሪክ ዋረን
🗣ትርጉም፦ ኢቫንጀሊካል ቴዎሎጂካል ኮሌጅ
🗒ክፍል፦ 31 (ቅርጽህን መረዳት)


ይቀጥላል...


ወደ ቻናሉ ለመ🀄️🀄️ል፦ @Holy_scriptures
👍3
ግርዶሽ ወይስ ነጸብራቅ?


                      ወ/ዊ ያሬድ ጥላሁን

ፊደል ላልቆጠረ፣ አስኳላ ላልደፈረ ገጠሬ “ጨረቃ እኮ የራሷ ብርሃን የላትም!” ቢባል አሻፈረኝ ሊል፣ ከባሰም ቆመጥ ሊያነሳ ይችላል። ታዲያ ማን ይፈርድበታል? በጨቅላነቱ “ጨረቃ ድንብል ቦቃ . . .” እያለ የዘመረላትን፣ በወጣትነቱ ምሽቱን ያደመቀችለትን፣ በውድቅት ጨለማውን ያፈካችለትን ጨረቃ የራሷ ብርሃን የላትም ቢባል እንዴት ሊዋጥለት ይችላል? እውነቱ ግን ያ ነው። ጨረቃ ለራሷ በቆፈን የተቆራመደች ቀዝቃዛ ፈለክ (ፕላኔት) እንደሆነች ለዘመናት ያጠኗት ይመሰክራሉ።

ምድር በምትገኝበት የሕዋ ንፍቀ ክበብ ብቸኛዋ የብርሃን ምንጭ ፀሐይ ናት። ምድር በራሷ ዛቢያ በምታደርገው ዙረት ሳቢያ ቀንና ሌሊት ይፈራረቃሉ። ጀርባችንን ለፀሐይ ስንሰጥ ይጨልምብናል። በምሽት የፀሐይን ብርሃን በቀጥታ ማግኘት ባንችልም በተዘዋዋሪ እናገኛታለን። ጨረቃ የፀሐይን ብርሃን ተቀብላ በማንፀባረቅ እኛን የምድሮቹን ታገለግላለች።

ሆኖም ጨረቃ በዘመናት ውስጥ አልፎ አልፎ የሚከሰት አንድ ጣጣ አላት። ከፀሐይ ብርሃን ተቀብላ ሌሊታችንን ማፍካቷን ትተውና በፀሐይና በምድር መካከል ተደንቅራ የፀሐይን ብርሃን በመጋረድ ቀናችንን ታጨልማለች። ይህንንም የፀሐይ ግርዶሽ ወይም "ኤክሊፕስ" ብለን እንጠራዋለን።

ይህ ተፈጥሯዊ ክስተት ለእኛ በኢየሱስ ክርስቶስ ለምናምንና ሕያው እግዚአብሔርን ለምናገለግል ትልቅ መልዕክት አለው። ጨረቃ የራሷ ብርሃን እንደሌላት ሁሉ ማንኛውም አገልጋይ የራሱ የሆነ አንዳች ነገር የለውም። የእኔ ጸጋ፣ የእኔ ቅባት፣ የእኔ ቤተክርስቲያን፣ የእኔ ሕዝብ የሚባል ነገር የለም። የተጠራነው ተግተን ፊቱን እየፈለግን ከእርሱ የተቀበልነውን ብርሃን በጨለማ እንድናበራና ክብሩን እንድናፀባርቅ ብቻ ነው።

ጌታ ኢየሱስ ክርስቶስ እንኳ የአባቱን ፈቃድ ሊፈጽም በሥጋ በመጣ ጊዜ ያደረገው ይህንን ነው። የእግዚአብሔርን ክብር በጨለማ ላሉ በማንፀባረቅ የማይታየውን እግዚአብሔርን በቃሉና በሥራው ተረከው። ለዚህ አይደል የዕብራውያን መልዕክት ጸሐፊ፦

“እርሱም የክብሩ መንፀባርቅና የባሕሪው ምሳሌ ሆኖ ሁሉን በሥልጣኑ ቃል እየደገፈ ኃጢአታችንን በራሱ ካነጻ በኋላ በሰማያት በግርማው ቀኝ ተቀመጠ” (ዕብ. 1፥2) የሚለን።

እኛም የተጠራነው የክርስቶስን ብርሃን ተቀብለን እንድናፀባርቅ እንጂ ክርስቶስን ጋርደን ራሳችንን አግንነን፣ እንዳልተቀበለ ኮርተን፣ ሁሉን ለራሳችን አጋብሰን ጭላንጭሉንም እንድናደበዝዝ አይደለም። ቅዱስ ቃሉ

“እኛ ግን በመጋረጃ በማይከደን ፊት የጌታን ክብር እንደ መስታወት እያብለጨለጭን መንፈስ ከሚሆን ጌታ ዘንድ እንደሚደረግ ያን መልክ እንመስል ዘንድ ከክብር ወደ ክብር እንለወጣለን” (2 ቆሮ. 3፥18)

እንደሚል ለማንፀባረቅ ተጠርተናል። ሆኖም በዘመናችን ነፀብራቅ ሳይሆን ግርዶሽ እየበዛ ያለ ይመስላል። አገልጋዮች በጨለማ ያሉ ሰዎች የማይታየውን የእግዚአብሔርን ብርሃን እንዲያዩ ከማገዝ ይልቅ በእግዚአብሔርና በሰው መካከል ገብተው እኔን እዩኝ ካሉ እንኳን ጨለማ ሊያበሩ ቀኑን ያጨልማሉ። ያኔ ነው መንፈሳዊ ኤክሊፕስ ወይም የእግዚአብሔር ግርዶሽ የሚከሰተው። መጋረድ የሉሲፈር እንጂ የክርስቶስም ሆነ የእውነተኛ ተከታዮቹ ተግባር አይደለም። አገልጋዮች ከዚህ ክፋት ለመመለስና ንስሐ ለመግባት ካልወደዱ አልፎ አልፎ በተፈጥሮ እንደሚከሰተው ጨረቃም በተራዋ በምድር ተከልላ ደም እንደምትለብስ የሚጋርዱ ሁሉ የመጋረድ እጣ ፈንታ ይደርስባቸዋል። በፍርድም ሥር ይወድቃሉ።


ምንጭ፦ www.semayawithought.org



ወደ ቻናሉ ለመ🀄️🀄️ል፦ @Holy_scriptures
👍166
.    ==❀❀❀===❀❀❀==      
              የዕለቱ ጥቅስ 
     ==❀❀❀===❀❀❀==
“እናንተ ግብዞች ጻፎችና ፈሪሳውያን፥ ከአዝሙድና ከእንስላል ከከሙንም አሥራት ስለምታወጡ፥ ፍርድንና ምሕረትን ታማኝነትንም፥ በሕግ ያለውን ዋና ነገር ስለምትተዉ፥ ወዮላችሁ፤ ሌላውን ሳትተዉ ይህን ልታደርጉ ይገባችሁ ነበር።”
ማቴዎስ 23፥23



ወደ ቻናሉ ለመ🀄️🀄️ል፦ @Holy_scriptures
🔥3👍1
ዓላማ መር ህይወት- ቀን 32_Purpose driven Life - Day 32_ alama mer hiywet…
PETERiCH (I am empty without Jesus)
#መጻሕፍትን_በድምጽ

👉ርዕስ፦ ዓላማ መር ሕይወት
✍️ጸሐፊ፦ ሪክ ዋረን
🗣ትርጉም፦ ኢቫንጀሊካል ቴዎሎጂካል ኮሌጅ
🗒ክፍል፦ 32 (እግዚአብሔር በሰጠን መጠቀም)


ይቀጥላል...


ወደ ቻናሉ ለመ🀄️🀄️ል፦ @Holy_scriptures
.    ==❀❀❀===❀❀❀==      
              የዕለቱ ጥቅስ 
     ==❀❀❀===❀❀❀==
“ሙሴም የግብፆችን ጥበብ ሁሉ ተማረ፥ በቃሉና በሥራውም የበረታ ሆነ።”
            ሐዋርያት 7፥22



ወደ ቻናሉ ለመ🀄️🀄️ል፦ @Holy_scriptures
6👍1
ዓላማ መር ህይወት- ቀን 33_Purpose driven Life - Day 33_ alama mer hiywet…
PETERiCH (I am empty without Jesus)
#መጻሕፍትን_በድምጽ

👉ርዕስ፦ ዓላማ መር ሕይወት
✍️ጸሐፊ፦ ሪክ ዋረን
🗣ትርጉም፦ ኢቫንጀሊካል ቴዎሎጂካል ኮሌጅ
🗒ክፍል፦ 33 (የእውነተኛ አገልጋዮች ፍሬ)


ይቀጥላል...


ወደ ቻናሉ ለመ🀄️🀄️ል፦ @Holy_scriptures
👍2
ወደ ቻናሉ ለመ🀄️🀄️ል፦ @Holy_scriptures
👍3
እግዚአብሔርን መምሰል.pdf
3.2 MB
👉ርዕስ፦ እግዚአብሔርን መምሰል
ጸሐፊ፦ ወንጌላዊ ያሬድ ጥላሁን



ወደ ቻናሉ ለመ🀄️🀄️ል፦ @Holy_scriptures
👍1
.    ==❀❀❀===❀❀❀==      
              የዕለቱ ጥቅስ 
     ==❀❀❀===❀❀❀==
“እግዚአብሔር በተስፋ ለሚጠብቁት ለምትሻውም ነፍስ መልካም ነው።”
ሰቆ. 3፥25


ወደ ቻናሉ ለመ🀄️🀄️ል፦ @Holy_scriptures
🥰42👍1🔥1
ዓላማ መር ህይወት- ቀን 34_Purpose driven Life - Day 34_ alama mer hiywet…
PETERiCH (I am empty without Jesus)
#መጻሕፍትን_በድምጽ

👉ርዕስ፦ ዓላማ መር ሕይወት
✍️ጸሐፊ፦ ሪክ ዋረን
🗣ትርጉም፦ ኢቫንጀሊካል ቴዎሎጂካል ኮሌጅ
🗒ክፍል፦ 34 (እንደ አገልጋይ ማሰብ)


ይቀጥላል...


ወደ ቻናሉ ለመ🀄️🀄️ል፦ @Holy_scriptures
👍3
#ከተማ_ወይም_ቦታ_በቅዱሳት_መጻሕፍት


#ለኪሶ

ለኪሶ በዕብራይስጥ መጽሐፍ ቅዱስ (ብሉይ ኪዳን) ውስጥ በተደጋጋሚ የምትጠቀስ ጥንታዊት ከተማ ናት። በጥንቷ ይሁዳ በሸፌላ ግዛት የምትገኝ ጉልህ የከነዓናውያን እና በኋላም የእስራኤል ከተማ ነበረች። ላኪሶ ብዙውን ጊዜ ከወታደራዊ ዘመቻዎች ጋር የተቆራኘች ሲሆን እስራኤላውያን ከነዓንን በወረሩበት ወቅት እንዲሁም በአሦራውያን እና በባቢሎናውያን ወረራ ወቅት ተጠቅሷል።

ለላኪሽ መጽሐፍ ቅዱሳዊ ማጣቀሻዎች


ከነዓንን ድል ማድረግ፡- ለኪሶ በመጀመሪያ የተጠቀሰችው እስራኤላውያን ከነዓንን በወረሩበት ጊዜ ከተቆጣጠሩት ከተሞች አንዷ ነች (ኢያሱ 10፥3-5፣ 31-32)። የላኪሶ ንጉሥ ኢያሱን ለመውጋት ከአሞራውያን ነገሥታት ጥምረት ፈጥረው ተዋጉ ነገር ግን ተሸነፉ።

የሮብዓም ምሽግ፡- በ2ኛ ዜና 11፥9 ላይ ለኪሶ በይሁዳ ንጉሥ በሮብዓም ከተመሸጉ ከተሞች አንዷ ሆና ተዘርዝራለች።

የአሦር ከበባ፡- ለኪሶ በ701 ዓመተ ዓለም በይሁዳ ላይ ባካሄደው የአሦር ንጉሥ ሰናክሬም ዘመቻ አውድ ውስጥ በዋነኝነት ተጠቅሳለች። የሌኪሶን ከበባ በ2ኛ ነገሥት 18፥13-17 እና 2ኛ ዜና 32፥9 ላይ ተጠቅሳለች። በነነዌ በሚገኘው የሰናክሬም ቤተ መንግስት የላኪሽ አርኪኦሎጂያዊ ማስረጃዎች ይህንን ክስተት ያረጋግጣሉ።

የባቢሎናውያን ወረራ፡- በ586 ከክርስቶስ ልደት በፊት ኢየሩሳሌም ከመፍረሷ በፊት በባቢሎናውያን እጅ ከወደቁ የመጨረሻዎቹ የተመሸጉ ከተሞች መካከል ላኪሶ በኤርምያስ 34፥7 ላይ ተጠቅሳለች።


ምንጭ፦ Ussishkin, D. (2004). The renewed archaeological excavations at Lachish (1973–1994). Tel Aviv: Emery and Claire Yass Publications in Archaeology.



ወደ ቻናሉ ለመ🀄️🀄️ል፦ @Holy_scriptures
👍4
በቅዱሳት መጻሕፍት ውስጥ ይሁዳ በባቢሎን ሲማረክ በስንት ዙር ነው ምርኮኞች ወደ ባቢሎን የተጋዙት?
Anonymous Quiz
3%
ሀ. በአንድ
32%
ለ. በሁለት
54%
ሐ. በሦስት
10%
መ. በአራት
🔥6🥰1
.    ==❀❀❀===❀❀❀==      
              የዕለቱ ጥቅስ 
     ==❀❀❀===❀❀❀==
“እነሆ፥ የእኅትሽ የሰዶም ኃጢአት ይህ ነበረ፤ ትዕቢት እንጀራን መጥገብ መዝለልና ሥራ መፍታት በእርስዋና በሴቶች ልጆችዋ ነበረ፥ የችግረኛውንና የድሀውንም እጅ አላጸናችም።”
ሕዝቅኤል 16፥49



ወደ ቻናሉ ለመ🀄️🀄️ል፦ @Holy_scriptures
👍63🔥1