ቅዱሳት መጻሕፍት
7.45K subscribers
1.35K photos
61 videos
332 files
796 links
በዚህ ቻናል

👉ቅዱሳት መጻሕፍት ይጠናሉ::
👉መጽሐፍ ቅዱሳዊ ትምህርቶች ይቀርባሉ::
👉 ለቅዱሳት መጽሐፍት ጥናት የሚያግዙ መጻሕፍት ይለቀቃሉ።

⭐️⭐️⭐️⭐️⭐️

@Holy_scriptures
Download Telegram
#እራሳችንን_እንመርምር

ከታላቁ ድነታችን ጀምሮ አንዳንድ በሕይወት ከከበቡንና ካስቸገሩን ሁኔታዎች እግዚአብሔር በቸርነቱ ታድጎን ካወጣን በኋላ በተአምራቱና ድንቁ ተገርመን እርሱን ስናወራው እንከርማለን። ግን ከዚያ በዘለለ ምን ማድረግ እንችላለን? የተደረገው ተአምር እንድንደሰት እና እንድንገረም ብቻ ነው?

“ታንኳዎችንም ወደ ምድር አድርሰው ሁሉን ትተው ተከተሉት።”
ሉቃስ 5፥11



ወደ ቻናሉ ለመ🀄️🀄️ል፦ @Holy_scriptures
👍62🙏2
.    ==❀❀❀===❀❀❀==      
              የዕለቱ ጥቅስ 
     ==❀❀❀===❀❀❀==
“ኢየሱስም አዘነላቸውና ዓይኖቻቸውን ዳሰሰ፥ ወዲያውም አዩና ተከተሉት።”
ማቴዎስ 20፥34



ወደ ቻናሉ ለመ🀄️🀄️ል፦ @Holy_scriptures
5👍2🙏2
ዓላማ መር ህይወት- ቀን 26_Purpose driven Life - Day 26_ alama mer hiywot…
PETERiCH (I am empty without Jesus)
#መጻሕፍትን_በድምጽ

👉ርዕስ፦ ዓላማ መር ሕይወት
✍️ጸሐፊ፦ ሪክ ዋረን
🗣ትርጉም፦ ኢቫንጀሊካል ቴዎሎጂካል ኮሌጅ
🗒ክፍል፦ 26 (በፈተና ውስጥ ማደግ)


ይቀጥላል...


ወደ ቻናሉ ለመ🀄️🀄️ል፦ @Holy_scriptures
👍5
#የእግዚአብሔር_ቃል_ምን_ይላል?


ገላትያ 2
¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯
¹⁵ እኛ በፍጥረት አይሁድ ነን ኃጢአተኞችም የሆኑ አሕዛብ አይደለንም፤
¹⁶ ነገር ግን ሰው በኢየሱስ ክርስቶስ በማመን እንዲጸድቅ እንጂ በሕግ ሥራ እንዳይሆን አውቀን፥ ሥጋን የለበሰ ሁሉ በሕግ ሥራ ስለማይጸድቅ፥ እኛ ራሳችን በሕግ ሥራ ሳይሆን በክርስቶስ እምነት እንጸድቅ ዘንድ በክርስቶስ ኢየሱስ አምነናል።
¹⁷ ነገር ግን በክርስቶስ ልንጸድቅ የምንፈልግ ስንሆን ራሳችን ደግሞ ኃጢአተኞች ሆነን ከተገኘን፥ እንግዲያስ ክርስቶስ የኃጢአት አገልጋይ ነዋ? አይደለም።
¹⁸ ያፈረስሁትን ይህን እንደ ገና የማንጽ ከሆንሁ ራሴ ሕግ ተላላፊ እንድሆን አስረዳለሁና።
¹⁹ እኔ ለእግዚአብሔር ሕያው ሆኜ እኖር ዘንድ በሕግ በኩል ለሕግ ሞቼ ነበርና።
²⁰ ከክርስቶስ ጋር ተሰቅዬአለሁ፤ እኔም አሁን ሕያው ሆኜ አልኖርም ክርስቶስ ግን በእኔ ይኖራል፤ አሁንም በሥጋ የምኖርበት ኑሮ በወደደኝና ስለ እኔ ራሱን በሰጠው በእግዚአብሔር ልጅ ላይ ባለ እምነት የምኖረው ነው።
²¹ የእግዚአብሔርን ጸጋ አልጥልም፤ ጽድቅስ በሕግ በኩል ከሆነ እንኪያስ ክርስቶስ በከንቱ ሞተ።



ወደ ቻናሉ ለመ🀄️🀄️ል፦ @Holy_scriptures
5👍3
ቅዱሳት መጻሕፍት
እንዴት እንሙት? እንዴት እንኑር?                    በጋሽ ንጉሤ ቡልቻ በምድር ላይ ረጅም ዕድሜ አልኖረም፤ የኖረበት ጥቂት ዕድሜ ግን እስከ ዛሬ ያላባራ የለውጥ፣ የተሐድሶ፣ የፍስሓ፣ የጸጋ ሞገድ አስነሥቷል። ‘ከኖርኩ አይቀር እንደ እርሱ ልኑር’ የሚያሰኝ ትርጉም ያለው ሕይወት ኖረ። ኢየሱስ ክርስቶስ እንዴት እንደሚኖር ብቻ ሳይሆን እንዴት እንደሚሞትም አሳየን። ከኑሮው ለመቅዳት የምንሻማ…
የቀጠለ...


እንዴት እንሙት? እንዴት እንኑር?



                   በጋሽ ንጉሤ ቡልቻ



#ሦስተኛ_ትምህርት

ኢየሱስ ክርስቶስ የሞቱን እውነት አስቀድሞ ቢረዳም እጅ አጣጥፎ፣ ጉልበቱን ኮርትሞ በሰቀቀንና በድንጋጤ ሞትን አልተጠባበቀም። እስከ መጨረሻ ትንፋሹ ሕቅታ ድረስ በጎ እየሠራ፣ የያዙትን ወታደሮች እየፈወሰ፣ ለሰቀሉት ምሕረት እየለመነ፣ ከአባቱ ጋር በጸሎት እየተነጋገረ “ተፈጸመ” ብሎ ነፍሱን ሰጠ።

እስክንሞት ድረስ ቦዝነን እንዳንቀመጥ፣ ከበጎ ሥራ እንዳንታክት፣ ከጸሎት እንዳናፈገፍግ፣ ‘ወይኔ ጉዴ’ እያልን በሰቀቀን እንዳናልቅ አስተማረን። እያንዳንዷን ሰዓት በዘላለም መዝገብ ውስጥ የሚገባ የሰላምና የፍቅር ዘር እየዘራን እንሙት (ያው መሞታችን አይቀርም ብዬ ነው)። የምንወድዳቸውን በጣም እንውደዳቸው፤ ለሚጠሉን እንጸልይላቸው፤ ለአገርና ለሕዝብ መልካሙን ሁሉ እንመኝ፤ እንናገር፤ እንባርክ። እንደዚያ ሀኬተኛ ባሪያ መክሊታችንን ቀብረን የቁጥጥሩን ቀን በድንጋጤ አንጠብቅ። በተሰጠን ትንሽ ትንፋሽ እንኳ በመክሊታችን እየነገድን እንሙት።

#አራተኛ_ትምህርት

ለሞቱ ቀን ተማሪዎችን እያዘጋጃቸው ሳለ፣ ጌታችን ከደቀ መዛሙርቱ ጋር መዝሙር ዘመረ (ማቴ 26፥30)። ምን እንደ ዘመሩ ባይጻፍልንም፣ የእኔ ግምት የፋሲካ ሰሞን ስለ ነበረ እስራኤል ከግብፅ ባርነት ነጻ የወጣበትን፣ የእግዚአብሔርን ትድግናና ግርማ የሚናገር የነጻነትና የምስጋና መዝሙር ሳይሆን አይቀርም። በሞት ሰሞን መዝሙር አልተከለከለም። የሚሠራውን የሚያውቀውና የፍጥረት ሁሉ ገዥ የሆነውን፣ የነፍስ ሁሉ ባለቤት የሆነውን ጌታ እያመሰገንነው እንሙት።

ሌላም ብዙ ትምህርት አለው። ለምሳሌ፣ በመስቀል ላይ እየሞተ ሳለ ስለ ወላጅ እናቱ አስቦ ለዮሐንስ ዐደራ መስጠቱ ትልቅ የኀላፊነት አብነት ነው።

የመጨረሻው እራት ከደቀ መዛሙርቱ ጋር ሲበላ፣ ህብስቱንና ወይኑን ሲሰጣቸው “በእግዚአብሔር መንግሥት ከእናንተ ጋር አዲሷን ወይን እስክንጠጣ ከዚህ በኋላ አልጠጣውም” ማለቱ የትንሣኤንና የዳግም ምፅዐቱን ተስፋ የሚያለመልም የተረጋጋ ንግግር ነው። ከዚህ ሕይወት በኋላ ሌላ የከበረ ሕይወት አለ፤ ይህንን እየተናገረ የሞተ ሰው ነበረ።

ሁሉን ትምህርት ዘርዝረን አንጨርስም ...

ነገር ግን ይህ አስገራሚ ሞት የሞተው ትሑቱ ኢየሱስ የገሃነም ኀይሎች ሊቋቋሙት በማይችሉት ታላቅ ኀይል ከሙታን ተለይቶ ተነሣ። በእርሱ የምናምን የሁላችንን ዕንባ የሚያብስ፣ ነፍሳችንን የሚመልስ፣ የመጽናናት ብሥራት ሰጠን። እና ወዳጆቼ እንደ ጳውሎስ፣ “ለእኔ ሕይወት ክርስቶስ ሞትም ጥቅም ነው” የማለት ጸጋ ያድለን።


ምንጭ:- hintset.org



ወደ ቻናሉ ለመ🀄️🀄️ል፦ @Holy_scriptures
👍73🙏1
.    ==❀❀❀===❀❀❀==      
              የዕለቱ ጥቅስ 
     ==❀❀❀===❀❀❀==
“አፉንና ምላሱን የሚጠብቅ ነፍሱን ከመከራ ይጠብቃል።”
ምሳሌ 21፥23



ወደ ቻናሉ ለመ🀄️🀄️ል፦ @Holy_scriptures
👍8🥰1
ዓላማ መር ህይወት- ቀን 27_Purpose driven Life - Day 27_ alama mer hiywot…
PETERiCH (I am empty without Jesus)
#መጻሕፍትን_በድምጽ

👉ርዕስ፦ ዓላማ መር ሕይወት
✍️ጸሐፊ፦ ሪክ ዋረን
🗣ትርጉም፦ ኢቫንጀሊካል ቴዎሎጂካል ኮሌጅ
🗒ክፍል፦ 27 (ፈተናን ማሸነፍ)


ይቀጥላል...


ወደ ቻናሉ ለመ🀄️🀄️ል፦ @Holy_scriptures
👍61🙏1
ወደ ቻናሉ ለመ🀄️🀄️ል፦ @Holy_scriptures
ዋና ዋና የመጽሐፍ ቅዱስ ጭብጦች.pdf
9.8 MB
👉ርዕስ፦ ዋና ዋና የመጽሐፍ ቅዱስ ጭብጦች
✍️ጸሐፊ፦ ዶ/ር ሉዊስ ስፔሪ ቼፈር
🗣ተርጓሚ፦ ተክሉ መንገሻ
✏️ኤዲተር፦ ገበየሁ አየለ


ወደ ቻናሉ ለመ🀄️🀄️ል፦ @Holy_scriptures
9👍2
.    ==❀❀❀===❀❀❀==      
              የዕለቱ ጥቅስ 
     ==❀❀❀===❀❀❀==
“እግዚአብሔርን የምትወዱ፥ ክፋትን ጥሉ፤ እግዚአብሔር የቅዱሳኑን ነፍሶች ይጠብቃል፥ ከኃጥኣንም እጅ ያድናቸዋል።”
            መዝሙር 97፥10



ወደ ቻናሉ ለመ🀄️🀄️ል፦ @Holy_scriptures
👍84
ዓላማ መር ህይወት- ቀን 28_Purpose driven Life - Day 28_ alama mer hiywet…
PETERiCH (I am empty without Jesus)
#መጻሕፍትን_በድምጽ

👉ርዕስ፦ ዓላማ መር ሕይወት
✍️ጸሐፊ፦ ሪክ ዋረን
🗣ትርጉም፦ ኢቫንጀሊካል ቴዎሎጂካል ኮሌጅ
🗒ክፍል፦ 28 (ጊዜ ይወስዳል)


ይቀጥላል...


ወደ ቻናሉ ለመ🀄️🀄️ል፦ @Holy_scriptures
👍3
ቅዱሳት መጻሕፍት
#እምነት ለምን እንመን?                    ክፍል-5 ለምን እግዚአብሔርን እና ቅዱሳት መጻሕፍትን እንመን? 👉እግዚአብሔር የሕይወት ሁሉ ፈጣሪ እና ደጋፊ ነው፣ እርሱም ሁሉን ቻይ፣ ሁሉን የሚያውቅ እና በሁሉም ቦታ የሚገኝ የዘላለም አምላክ ነው። በእግዚአብሔር መታመን ማለት በአስቸጋሪ ሁኔታዎች ውስጥም ቢሆን በጥበቡ፣ በፍቅሩ እና በሉዓላዊነቱ መታመን ማለት ነው። በፍጹም ልብህ በእግዚአብሔር…
#እምነት


                   ክፍል-6


እምነት መሠረቱ ምንድነው? የምናምነው እግዚአብሔርን ወይስ እንዲሆንልን የምንፈልገውን ነገር?


እምነቱ መሠረቱ እግዚአብሔር እና የእግዚአብሔር  ቃል ነው። ከዚህ ውጪ የሆነ "እምነት" የሚባለው ነገር ክርስቲያናዊ እምነት አይደለም! ቅዱሳት መጻሕፍትም ይህን እውነት ሳይሸፋፍኑ እንዲህ ይነግሩናል፦

“በእግዚአብሔር የታመነ እምነቱም እግዚአብሔር የሆነ ሰው ቡሩክ ነው።”
          ኤርምያስ 17፥7

“ቃልን የሚያዳምጥ መልካም ነገርን ያገኛል፤ በእግዚአብሔር የታመነ ምስጉን ነው።”
           ምሳሌ 16፥20

የምናምነው እግዚአብሔርን ወይስ እንዲያደረግልን የምንፈልገውን ነገር?

እውነተኛ አማኝ የሚያምነው እንዲደረግለት የሚፈልገውን ነገር ሳይሆን እግዚአብሔር ራሱን ነው። ኃይል ስልጣንና ጉልበት ያለው ሁሉን ቻዩ እግዚአብሔር ጋር ነው። በቻይነቱ እንተማመናለን እንጂ "ነገሮች እንዲህ መሆን አለባቸው!" ብለን እምነታችንን እነርሱ ላይ አንጥልም። ምክንያቱም እነርሱ ምን አቅም አላቸውና? ሁሉን ቻዩ እግዚአብሔር ሲያንቀሳቅስ ነው ነገሮች የሚንቀሳቀሱት።

“ሁሉን ታደርግ ዘንድ ቻይ እንደ ሆንህ፥ አሳብህም ይከለከል ዘንድ ከቶ እንደማይቻል አወቅሁ።”
           ኢዮብ 42፥2

“ለእግዚአብሔርም ክብር እየሰጠ፥ የሰጠውንም ተስፋ ደግሞ ሊፈጽም እንዲችል አጥብቆ እየተረዳ፥ በእምነት በረታ እንጂ በአለማመን ምክንያት በእግዚአብሔር ተስፋ ቃል አልተጠራጠረም።”
          ሮሜ 4፥20-21


እግዚአብሔርን እንዴት እንመን?

1. ቃሉን በመስማት

“እንግዲያስ እምነት ከመስማት ነው መስማትም በእግዚአብሔር ቃል ነው።”
            ሮሜ 10፥17



ይቀጥላል...


ወደ ቻናሉ ለመ🀄️🀄️ል፦ @Holy_scriptures
👍63😁1
በቅዱሳት መጻሕፍት ውስጥ ሐዋርያው ቅዱስ ጳውሎስ ወንጌል በመስበክ እና በማስተማር ከሌሎች ቦታዎች ይልቅ ረጅም ጊዜ የተቀመጠው የት ከተማ ነው?
Anonymous Quiz
33%
ሀ. ቆሮንቶስ
47%
ለ. ኤፌሶን
4%
ሐ. ፊልጵስዩስ
9%
መ. ተሰሎንቄ
7%
ሠ. ኢየሩሳሌም
7
.    ==❀❀❀===❀❀❀==      
              የዕለቱ ጥቅስ 
     ==❀❀❀===❀❀❀==
“ነገር ግን ጽና፥ እጅግ በርታ፤ ባሪያዬ ሙሴ ያዘዘህን ሕግ ሁሉ ጠብቅ፥ አድርገውም፤ በምትሄድበትም ሁሉ እንዲከናወንልህ ወደ ቀኝም ወደ ግራም አትበል።”
ኢያሱ 1፥7



ወደ ቻናሉ ለመ🀄️🀄️ል፦ @Holy_scriptures
👍61
Audio
#መጻሕፍትን_በድምጽ

👉ርዕስ፦ ዓላማ መር ሕይወት
✍️ጸሐፊ፦ ሪክ ዋረን
🗣ትርጉም፦ ኢቫንጀሊካል ቴዎሎጂካል ኮሌጅ
🗒ክፍል፦ 29 (የተሰጠህን ሥራ መቀበል)


ይቀጥላል...


ወደ ቻናሉ ለመ🀄️🀄️ል፦ @Holy_scriptures
እግዚአብሔር በየቀኑ በሕይወታቸው ውስጥ የሚያደርገውን በጎነት የማናስተውል ብዙ ነን። ከእንቅልፋችን በሰላምና ጤና ነቅተን የማለዳዋን ፀሓይ ለማየት ስለመታደላችን ምስጋና ስናቀርብ አንታይም። በመሰለን መንገድ ያልተከናወነ ነገር ብንቀበልም፥ መብታችን እንጂ ቸርነት አይመስለንም። በሕይወት መኖር እንደ ቀልድ ይታለፋል። ስፍር ቍጥር የሌላቸው ቅጽበታዊ ዕለታዊና የዘመናችን ሙሉ የበጎነት ስጦታዎቹ በቸልታ ተወርውረው ይኖራሉ። እኛ ሰዎች እንገርማለን እኮ። እናሳዝንማለን።

የገዛ ምራቁ ትን ብሎት ሕይወቱን በሰከንዶች ውስጥ ሊያጣ የሚችል ሰው በሕይወት መቈየት የቻለው በእግዚአብሔር ምሕረት መኾኑን ይዘነጋል። ፍጥረት ሕግና ሥርዐት ጠብቆ የሚኖረው በጌታ ነው። ምድር በአምላካዊ ቸርነት ተጠብቃ ሕይወት ያብብባታል። ሥጋት በወጠረው ዓለም ውስጥ በሰላም ወጥተን መግባት መቻላችን ትርጕሙ የሚገባን አገር ምድሩ ሲታመስ መኾን የለበትም።

ከስንት አስፈሪ ነገሮች ተረፍን? ስንቱን የሞት ሸለቆዎች በምሕረቱ ተሻገርን? ስንት ጊዜ ወድቀን ስንት ጊዜ በቸርነቱ ተደግፈን ተነሣን? ዛሬስ ቢኾን ከእጆቹ ምን ተቀብለናል? ወዳጃችን፥ "ነፍሴ ሆይ፥ ውለታውን አትርሺ" ማለቱ ቁምነገረኝነት ያለው ሰው በመኾኑ ነው። ጌታችን ማዳኑ ዛሬም አዲስ ነው።


መጋቢ ሰሎሞን አበበ ገብረ መድኅን



ወደ ቻናሉ ለመ🀄️🀄️ል፦ @Holy_scriptures
🙏92👍1😁1
.    ==❀❀❀===❀❀❀==      
              የዕለቱ ጥቅስ 
     ==❀❀❀===❀❀❀==
“እናንተንም ነውርና ነቀፋ የሌላችሁና ቅዱሳን አድርጎ በእርሱ ፊት ያቀርባችሁ ዘንድ፥ በፊት የተለያችሁትን ክፉ ሥራችሁንም በማድረግ በአሳባችሁ ጠላቶች የነበራችሁትን አሁን በሥጋው ሰውነት በሞቱ በኩል አስታረቃችሁ።”
ቆላስይስ 1፥21-22




ወደ ቻናሉ ለመ🀄️🀄️ል፦ @Holy_scriptures
8
ዓላማ መር ህይወት- ቀን 30_Purpose driven Life - Day 30_ alama mer hiywet…
PETERiCH (I am empty without Jesus)
#መጻሕፍትን_በድምጽ

👉ርዕስ፦ ዓላማ መር ሕይወት
✍️ጸሐፊ፦ ሪክ ዋረን
🗣ትርጉም፦ ኢቫንጀሊካል ቴዎሎጂካል ኮሌጅ
🗒ክፍል፦ 30 (የተበጀኸው እግዚአብሔርን ለማገልገል ነው)


ይቀጥላል...


ወደ ቻናሉ ለመ🀄️🀄️ል፦ @Holy_scriptures
👍4
ቅዱሳት መጻሕፍት
#እምነት                    ክፍል-6 እምነት መሠረቱ ምንድነው? የምናምነው እግዚአብሔርን ወይስ እንዲሆንልን የምንፈልገውን ነገር? እምነቱ መሠረቱ እግዚአብሔር እና የእግዚአብሔር  ቃል ነው። ከዚህ ውጪ የሆነ "እምነት" የሚባለው ነገር ክርስቲያናዊ እምነት አይደለም! ቅዱሳት መጻሕፍትም ይህን እውነት ሳይሸፋፍኑ እንዲህ ይነግሩናል፦ “በእግዚአብሔር የታመነ እምነቱም እግዚአብሔር የሆነ…
#እምነት


                   ክፍል-7


እግዚአብሔርን እንዴት እንመን? ወይንም ለማመን ምን እናድርግ?

2. በፍጹም ልብ እግዚአብሔርን መፈለግ

“እናንተ ትሹኛላችሁ፥ በፍጹም ልባችሁም ከሻችሁኝ ታገኙኛላችሁ።”
        ኤርምያስ 29፥13

3. በቅዱሳት መጻሕፍት ተአማኒነት ላይ ማመን

“የእግዚአብሔር ሰው ፍጹምና ለበጎ ሥራ ሁሉ የተዘጋጀ ይሆን ዘንድ፥ የእግዚአብሔር መንፈስ ያለበት መጽሐፍ ሁሉ ለትምህርትና ለተግሣጽ ልብንም ለማቅናት በጽድቅም ላለው ምክር ደግሞ ይጠቅማል።”
        2ኛ ጢሞቴዎስ 3፥16-17

4. ኢየሱስ ክርስቶስን የእግዚአብሔር ልጅ ነው ብሎ ማመን

“በእርሱ የሚያምን ሁሉ የዘላለም ሕይወት እንዲኖረው እንጂ እንዳይጠፋ እግዚአብሔር አንድያ ልጁን እስኪሰጥ ድረስ ዓለሙን እንዲሁ ወዶአልና።”
         ዮሐንስ 3፥16

5. እምነትንና ጥበብን እንዲሰጠን እግዚአብሔርን መለመን

"ከእናንተ ግን ማንም ጥበብ ቢጎድለው፥ ሳይነቅፍ በልግስና ለሁሉ የሚሰጠውን እግዚአብሔርን ይለምን፥ ለእርሱም ይሰጠዋል። ነገር ግን በምንም ሳይጠራጠር በእምነት ይለምን፤ የሚጠራጠር ሰው በነፋስ የተገፋና የተነቃነቀ የባሕርን ማዕበል ይመስላልና።"
             ያዕቆብ 1፥5-6

6. የእግዚአብሔርን ቃል መታዘዝ

“እምነት ከሥራው ጋር አብሮ ያደርግ እንደ ነበረ፥ በሥራም እምነት እንደ ተፈጸመ ትመለከታለህን?”
         ያዕቆብ 2፥22

7. በእግዚአብሔር ተስፋዎች ማመን

“አቤቱ፥ አንተ ተስፋዬ ነህና፥ እግዚአብሔር ሆይ፥ ከታናሽነቴ ጀምረህ መታመኛዬ ነህና።”
         መዝሙር 71፥5

8. ከሌሎች አማኞች ጋር ሕብረት ማድረግ

"የተስፋን ቃል የሰጠው የታመነ ነውና እንዳይነቃነቅ የተስፋችንን ምስክርነት እንጠብቅ፤ ለፍቅርና ለመልካምም ሥራ እንድንነቃቃ እርስ በርሳችን እንተያይ፤ በአንዳንዶችም ዘንድ ልማድ እንደ ሆነው፥ መሰብሰባችንን አንተው እርስ በርሳችን እንመካከር እንጂ፤ ይልቁንም ቀኑ ሲቀርብ እያያችሁ አብልጣችሁ ይህን አድርጉ።"
            ዕብራውያን 10፥23-25


ይቀጥላል...



ወደ ቻናሉ ለመ🀄️🀄️ል፦ @Holy_scriptures
👍63
.    ==❀❀❀===❀❀❀==      
              የዕለቱ ጥቅስ 
     ==❀❀❀===❀❀❀==
“በቸርነትህ የተቤዠሃቸውን ሕዝብህን መራህ፤ በኃይልህ ወደ ቅዱስ ማደሪያህ አገባሃቸው።”
ዘጸአት 15፥13



ወደ ቻናሉ ለመ🀄️🀄️ል፦ @Holy_scriptures
👍72🥰2
ዓላማ መር ህይወት- ቀን 31_Purpose driven Life - Day 31_ alama mer hiywet…
PETERiCH (I am empty without Jesus)
#መጻሕፍትን_በድምጽ

👉ርዕስ፦ ዓላማ መር ሕይወት
✍️ጸሐፊ፦ ሪክ ዋረን
🗣ትርጉም፦ ኢቫንጀሊካል ቴዎሎጂካል ኮሌጅ
🗒ክፍል፦ 31 (ቅርጽህን መረዳት)


ይቀጥላል...


ወደ ቻናሉ ለመ🀄️🀄️ል፦ @Holy_scriptures
👍3