ቅዱሳት መጻሕፍት
7.45K subscribers
1.35K photos
61 videos
332 files
795 links
በዚህ ቻናል

👉ቅዱሳት መጻሕፍት ይጠናሉ::
👉መጽሐፍ ቅዱሳዊ ትምህርቶች ይቀርባሉ::
👉 ለቅዱሳት መጽሐፍት ጥናት የሚያግዙ መጻሕፍት ይለቀቃሉ።

⭐️⭐️⭐️⭐️⭐️

@Holy_scriptures
Download Telegram
.    ==❀❀❀===❀❀❀==      
              የዕለቱ ጥቅስ 
     ==❀❀❀===❀❀❀==
“ከሰማርያም ካፈለሱአቸው ካህናት አንዱ መጥቶ በቤቴል ተቀመጠ፥ እግዚአብሔርንም እንዴት እንዲፈሩት ያስተምራቸው ነበር።”
2ኛ ነገሥት 17፥28




ወደ ቻናሉ ለመ🀄️🀄️ል፦ @Holy_scriptures
👍2
ዓላማ መር ህይወት- ቀን 20_Purpose driven Life - Day 20_ alama mer hiywot…
PETERiCH (I am empty without Jesus)
#መጻሕፍትን_በድምጽ

👉ርዕስ፦ ዓላማ መር ሕይወት
✍️ጸሐፊ፦ ሪክ ዋረን
🗣ትርጉም፦ ኢቫንጀሊካል ቴዎሎጂካል ኮሌጅ
🗒ክፍል፦ 20 (የፈረሰ ኅብረት ማደስ)


ይቀጥላል...


ወደ ቻናሉ ለመ🀄️🀄️ል፦ @Holy_scriptures
👍4
ቅዱሳት መጻሕፍት
#የሮሜ_መልእክት_ጥናት ሮሜ 10 ¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯ ⁵ ሙሴ ከሕግ የሆነውን ጽድቅ የሚያደርገው ሰው በእርሱ በሕይወት እንዲኖር ጽፎአልና። ⁶ ከእምነት የሆነ ጽድቅ ግን እንዲህ ይላል፦ በልብህ፦ ማን ወደ ሰማይ ይወጣል? አትበል፤ ይህ ክርስቶስን ለማውረድ ነው፤ ⁷ ወይም፦ በልብህ፦ ወደ ጥልቁ ማን ይወርዳል? አትበል፤ ይህ ክርስቶስን ከሙታን ለማውጣት ነው። ⁸ ነገር ግን ምን ይላል? በአፍህ በልብህም ሆኖ…
#የሮሜ_መልእክት_ጥናት



ሮሜ 10፥5-9


ጳውሎስ የሙሴን ትምህርት እየጠቀሰ በመጀመሪያ በሕግ ስለሚገኘው ጽድቅ በመግለጥ ያስረዳል። እግዚአብሔር ሙሴን እንዲህ አለው፥ «እነዚህን ነገሮች የሚያደርግ ሰው ይህም የሕግን ትእዛዛት የሚፈጽም፥ በእነርሱ ይኖራል» (ዘሌ. 18፥5) የአይሁድ ሕግ «ሕይወትን» (ወይም ደኅንነትን) ሊሰጥ ይችላል፤ ይህም የሚሆነው የሕግን መሰናዶ አሟልቶ ለመፈጸም ለሚችል ለማንኛውም ሰው ነው። ነገር ግን ይህን ለማድረግ የሚችል ማንም ሰው ስለሌለ ሕግ ማንንም ሰው ሊያድን አልቻለም። ጳውሎስ አሁን ደግሞ በእምነት ስለሚገኘው ጽድቅ ያስረዳል። ይህም ጽድቅ በመሠረቱ የደኅንነት መንገድ ነው። ይህን ጽድቅ ለማግኘት ወደ ሰማይ መውጣት አያስፈልገንም (ዘዳ. 30፥11-12)። ምክንያቱም ክርስቶስ አስቀድሞ ከሰማይ ወደ እኛ አምጥቶልናል። ክርስቶስን ለማውረድ ወደ ሰማይ መውጣት አያስፈልገንም፣ እርሱ ራሱ አስቀድሞ ወርዶአል። ደግሞም ይህን ጽድቅ ማለትም ክርስቶስን ለማግኘት ወደ ጥልቅ (ወደ ሲዖል) መውረድ አያስፈልገንም (ዘዳ. 30፥13)። ክርስቶስ አስቀድሞ ከሞት ተነሥቶአል፤ አስቀድሞ ከመቃብር ወጥቶአል።

ታዲያ በሕግ የሚገኘው ጽድቅ (ቁ. 5) የሚለን ምንድን ነው? እርሱ የሚለን ሰዎችን የደኅንነትን መንገድ የሚያሳየው የእምነት ቃል መጥቶ ቀርቦአል ነው (ዘዳ. 30፥14)። መቅረብ ብቻ ሳይሆን በልባችንም ውስጥ ገብቷል። ይህ የእምነት ቃል ወይም የደኅንነት መንገድ ምንድን ነው? «ኢየሱስ ጌታ ነው ብለህ በአፍህ ብትመሰክር፥ እግዚአብሔር ከሞት እንዳስነሣው በልብህ ብታምን ትድናለህ» የሚለው ነው። የድነት መሠረታዊ እውነቶች በዚህ ስፍራ በአጭሩ ተገልጸዋል፡፡ በክርስቶስ ጌትነትና በአካላዊ ትንሣኤው ላይ ባለ እምነት ዙሪያ የሚሽከረከሩ ናቸው። እምነት ከልብ ነው፤ ልብም ፍልቅ ስሜትን፣ አእምሮንና ፈቃድን ያጠቃልላል፤ የሰውንም ሁለንተና ይይዛል፡፡ እምነት በቃልና በተግባር ኢየሱስ ጌታ እንደ ሆነ በአደባባይ መግለጥ አለበት።

ኢየሱስ ክርስቶስ በአዲስ ኪዳን "አዳኝ” ተብሎ የተጠራው 16 ጊዜ ሲሆን፣ ጌታ በመባል ደግሞ ከ450 ጊዜ በላይ ተጠርቷል:: ዛሬ በአንዳንድ የወንጌል አማኞች ዘንድ ኢየሱስ የአንድ ሰው የሕይወቱ ጌታ ሳይሆን አዳኝ ሊሆን ይችላል በማለት የሚሰጠው ትምህርት በአዲስ ኪዳን የትም ቦታ የሚገኝ አይደለም:: ማንም ሰው ኢየሱስን የሕይወቱ ጌታ አድርጎ ካልተቀበለው አዳኙ ሊሆን አይችልም፤ ይህም በሐዋርያት ትምህርት ውስጥ ዋና አስተምህሮት ነበር (ሐሥ 2፥36-40)፡፡

ጌታ (በግሪክ “ኪሪዮስ”) “ኪሪዮስ”) ማለት ኀይል፣ ኣገዛዝ፣ ሥልጣንና የጌትነት መብት ያለው ማለት ነው:: “ኢየሱስ ጌታ ነው” ብሎ መመስከር ኢየሱስ ከእግዚአብሔር አብ ጋር አኩል እንደሆነና (ቊ 13፤ ዮሐ 20፥28፤ ሐሥ 2፥36፤ ዕብ 1፥10) ኀይል (ራእ 5፥12)፣ አምልኮ (ፊል 2፥10-11)፣ መታመን (ዮሐ 14፥1፡ ዕብ 2፥13)፣ ታዛዥነት (ዕብ 5፥9) እና ወደ እርሱም መጸለይ (ሐሥ 7፥59-60፣ 2ቆሮ 12፡8) እንደሚገባው ማወጅ ነው፡፡

የአዲስ ኪዳን ክርስቲያኖች ኢየሱስን ጌታ” ብለው ሲጠሩ አፋዊ ሳይሆን፡ ክርስቶስንና ቃሉን የሕይወታቸው ሁሉ ጌታ ያደረጉበት (ሉቃ 6፥46-49፡ ዮሓ 15፥14) ጥልቅ የሆነ እውነተኛ የልብ ሐሳብ መግለጫ ነው (ከጴጥ 3፥15 ጋር ያነጻጽሩ)፡፡ ኢየሱስ በቤትና በቤተክርስቲያን በመንፈሳዊ ጉዳዮች ላይ ጌታ መሆን አለበት። በተጨማሪም የአእምሮ፣ የገንዘብ፣ የትምህርት፣ የመዝናኛ ሁኔታዎችና በአጠቃላይ የሥራ መስኮች ሁሉ ማለትም በሕይወት ገጠመኞች ሁሉ ላይ ጌታ መሆን አለበት (12፥1-2፤ 1ቆሮ 10፥31)



ይቀጥላል. . .


ምንጭ፦ የአዲስ ኪዳን ማብራሪያ፤ ገጽ  375፣ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ከማጥኛ ጽሑፍ ጋር፤ ገጽ 1722-1723፣ ምሉእ ሕይወት፤ ገጽ 1760




ወደ ቻናሉ ለመ🀄️🀄️ል፦ @Holy_scriptures
👍7
.    ==❀❀❀===❀❀❀==      
              የዕለቱ ጥቅስ 
     ==❀❀❀===❀❀❀==
“ጥበብ ዓይነተኛ ነገር ናትና ጥበብን አግኝ፤ ከሀብትህም ሁሉ ማስተዋልን አትርፍ።”
ምሳሌ 4፥7



ወደ ቻናሉ ለመ🀄️🀄️ል፦ @Holy_scriptures
6👍1
ዓላማ መር ህይወት- ቀን 21_Purpose driven Life - Day 21_ alama mer hiywot…
PETERiCH (I am empty without Jesus)
#መጻሕፍትን_በድምጽ

👉ርዕስ፦ ዓላማ መር ሕይወት
✍️ጸሐፊ፦ ሪክ ዋረን
🗣ትርጉም፦ ኢቫንጀሊካል ቴዎሎጂካል ኮሌጅ
🗒ክፍል፦ 21 (ቤተ-ክርስቲያንህን መጠበቅ)


ይቀጥላል...


ወደ ቻናሉ ለመ🀄️🀄️ል፦ @Holy_scriptures
👍4
ወደ ቻናሉ ለመ🀄️🀄️ል፦ @Holy_scriptures
👍1
ሥላሴ በተዋሕዶ.pdf
17.4 MB
👉ርዕስ፦ ሥላሴ በተዋሕዶ
✍️ጸሐፊ፦ ከመሠረት ስብሐት ለአብ
🖨አሳታሚ፦ መካነ ኢየሱስ ሰሚናሪ



ወደ ቻናሉ ለመ🀄️🀄️ል፦ @Holy_scriptures
👍61
.    ==❀❀❀===❀❀❀==      
              የዕለቱ ጥቅስ 
     ==❀❀❀===❀❀❀==
“እግዚአብሔርም ለእስራኤል ቤት እንዲህ ይላልና፦ እኔን ፈልጉ፥ በሕይወትም ትኖራላችሁ፤”
አሞጽ 5፥4



ወደ ቻናሉ ለመ🀄️🀄️ል፦ @Holy_scriptures
🙏21🔥1
ዓላማ መር ህይወት- ቀን 22_Purpose driven Life - Day 22_ alama mer hiywot…
PETERiCH (I am empty without Jesus)
#መጻሕፍትን_በድምጽ

👉ርዕስ፦ ዓላማ መር ሕይወት
✍️ጸሐፊ፦ ሪክ ዋረን
🗣ትርጉም፦ ኢቫንጀሊካል ቴዎሎጂካል ኮሌጅ
🗒ክፍል፦ 22 (ክርስቶስን ለመምሰል ተፈጥረሃል)


ይቀጥላል...


ወደ ቻናሉ ለመ🀄️🀄️ል፦ @Holy_scriptures
በቅዱሳት መጻሕፍት ውስጥ "የእግዚአብሔር ልጅ" ማን ነው?


በመጽሐፍ ቅዱስ "የእግዚአብሔር ልጅ/ልጆች" ትርጓሜ


በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ በተለያዩ ስፍራዎች የቀረቡትን ማስረጃዎች በማጤን “የእግዚአብሔር ልጅ” የሚለው ሐረግ ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን ትርጕሞች እንደሚይዝ መረዳት ይቻላል፤

1. የእግዚአብሔርን የፍጥረት ባለቤትነት ማሳያ ነው።

“በውኑ ለዝናብ አባት አለውን? ወይስ የጠልን ነጠብጣብ የወለደ ማን ነው” ከሚለው መረዳት እንደሚቻለው (ኢዮብ 38፥28)፤ የእግዚአብሔር አባትነት እርሱ የፍጥረት ሁሉ ባለቤት መሆኑን የሚያሳይ ዘይቤአዊ አገላለጥ ነው። “የእኛ ዘር ከሌሎች ይበልጣል” በሚል ስሜት የተዋጡት አቴናውያን፣ “እኛም ደግሞ ልጆቹ ነን” በማለት የተናገሩትን ከፈላስፎቻቸው በመውሰድ ሰውን ሁሉ የሚመለከት አድርጎ ሐዋርያው ጳውሎስ ያቀረበው ለዚህ ይመስላል (የሐዋ. 17፥28፤ አ.መ.ት)። የሉቃስ ወንጌል አዳምን “የእግዚአብሔር ልጅ” ማለቱ ምናልባት በዚህ አግባብ የሚታይ ነው (3፥38)። እግዚአብሔር የፍጥረት ሁሉ ፈጣሪ በመሆኑ የፍጥረት ሁሉ አባት ነው። ነገር ግን ሰዎች ሁሉ የእግዚአብሔር ልጆች ስለ መሆናቸው መጽሐፍ ቅዱስ እምብዛም የሚናገረው ነገር የለውም።

2. መላእክትን ወይም ሰማያውያን ፍጥረታትን ያመለክታል፤

የእግዚአብሔር ልጆች ተብለዋልና ( 2፥1፤ 38፥7፤ መዝ. 29፥1፤ 82፥6፤ 89፥6)።

3. እስራኤል የእግዚአብሔር መሆኗን ያመለክታል።

እስራኤል ከምድር ሁሉ ለይቶ የመረጣት በመሆኗ ለእግዚአብሔር የመጀመሪያ ልጅ ናት፤ በዚህ ረገድ እግዚአብሔር ከእርሷ በፊት ልጅ አልነበረውም። ይህንንም ሙሴ በፈርዖን ፊት ቆሞ፣ “እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፡- እስራኤል የበኵር ልጄ ነው” በማለት እንዲናገር አድርጎታል (ዘጸ. 4፥22-23)። “እኔ ለእስራኤል አባት ነኝና፤ ኤፍሬምም በኵሬ ነውና” በማለትም ተጽፏል (ኤር. 31፥9)። ይህ ከእግዚአብሔር የድነት ዕቅድና ከእስራኤል ተልእኮ ጋር ይያያዛል።

እስራኤላውያን በኪዳን ሕዝብነታቸው፣ “እናንተ የአምላካችሁ የእግዚአብሔር ልጆች ናችሁ” ተብለዋል (ዘዳ. 14፥1)። በዚህ አገባቡ፣ የእግዚአብሔር ልጅ ማለት የእግዚአብሔር መሆንን እና የእግዚአብሔር ቤተ ሰብነትን ያሳያል። አማኞች የአብርሃም ልጆች የሆኑበትና የእግዚአብሔር የተቀበሉበት አግባብም ይኸው ነው (ሮሜ 9፥6-8 እና 24-31 እንዲሁም 11፥7-26ን ይመለከቷል።)

4. ጻድቃንን ይኸውም የእግዚአብሔር ጠባያት የሚታዩባቸው ሰዎችንም ያመለክታል።

ጠላቶቻቸውን የሚወድዱና መልካም የሚያደርጉ (ሉቃ. 6፥35)፣ የሚያስተራርቁ (ማቴ. 5፥9)፣ ጽድቅን የሚያደርጉ (1ዮሐ. 3፥10) “የእግዚአብሔር ልጆች” ናቸው።

5. ከዳዊት ሥርወ መንግሥት የሚመጣ ንጉሥ የእግዚአብሔር ልጅ ተብሏል።

ዳዊት፣ "ከልጆቼ ሁሉ በእግዚአብሔር መንግሥት ዙፋን ላይ ተቀምጦ በእስራኤል ላይ ይነግሥ ዘንድ ልጄን ሰሎሞንን መርጦታል። እርሱም፦ ልጅ ይሆነኝ ዘንድ መርጬዋለሁና፥ እኔም አባት እሆነዋለሁና … አለኝ” ሲል የተናገረው ይህንኑ ነው (1ዜና 28፥5-7)።

6. በመጨረሻም፣ “የእግዚአብሔር ልጅ” ወልድ ማለት ነው::

መለኮትነትን ያሳያል። “ከቶውንም እግዚአብሔርን ያየ ማንም የለም፤ ነገር ግን በአብ ዕቅፍ ያለው አንድያ ልጁ የሆነው አምላክ እርሱ ተረከው” (ዮሐ. 1፥18፤ አ.መ.ት)፣ እንዲሁም “ራሱን ከእግዚአብሔር ጋር አስተካክሎ እግዚአብሔር አባቴ ነው ስላለ ሊገድሉት አብዝተው ይፈልጉት ነበር” (ዮሐ. 5፥18) የተባለው ለዚህ ነው።



ምንጭ፦ የእግዚአብሔር ልጅ፤ ጳውሎስ ፈቃዱ፤ ገጽ 255-256




ወደ ቻናሉ ለመ🀄️🀄️ል፦ @Holy_scriptures
👍9
.    ==❀❀❀===❀❀❀==      
              የዕለቱ ጥቅስ 
     ==❀❀❀===❀❀❀==
“ችግረኞች ይበላሉ፥ ይጠግቡማል፤ እግዚአብሔርንም የሚሹት ያመሰግኑታል፤ ልባቸውም ለዘላለም ሕያው ይሆናል።”
መዝሙር 22፥26



ወደ ቻናሉ ለመ🀄️🀄️ል፦ @Holy_scriptures
👍54
ዓላማ መር ህይወት- ቀን 23_Purpose driven Life - Day 23_ alama mer hiywot…
PETERiCH (I am empty without Jesus)
#መጻሕፍትን_በድምጽ

👉ርዕስ፦ ዓላማ መር ሕይወት
✍️ጸሐፊ፦ ሪክ ዋረን
🗣ትርጉም፦ ኢቫንጀሊካል ቴዎሎጂካል ኮሌጅ
🗒ክፍል፦ 23 (እድገታችን)


ይቀጥላል...


ወደ ቻናሉ ለመ🀄️🀄️ል፦ @Holy_scriptures
👍3
ቅዱሳት መጻሕፍት
#እምነት ማንን እንመን?                    ክፍል-4 ቅዱሳት መጻሕፍት በማን ላይ ማመን ወይም መታመን እንዳለብን በተለይም በእምነት አውድ ላይ ሰፊ መመሪያ ይሰጣሉ። ከዚህ በታች በመጽሐፍ ቅዱስ መሠረት ማንን ማመን እንዳለብን ዝርዝር ማብራሪያ፣ ከተወሰኑ ጥቅሶች እና መርሆች ጋር። 1. ከምንም በላይ በእግዚአብሔር እግዚአብሔር ሉዓላዊ፣ ታማኝ እና የማይለወጥ በመሆኑ የመጨረሻው ለማመን…
#እምነት

ለምን እንመን?


                   ክፍል-5


ለምን እግዚአብሔርን እና ቅዱሳት መጻሕፍትን እንመን?

👉እግዚአብሔር የሕይወት ሁሉ ፈጣሪ እና ደጋፊ ነው፣ እርሱም ሁሉን ቻይ፣ ሁሉን የሚያውቅ እና በሁሉም ቦታ የሚገኝ የዘላለም አምላክ ነው። በእግዚአብሔር መታመን ማለት በአስቸጋሪ ሁኔታዎች ውስጥም ቢሆን በጥበቡ፣ በፍቅሩ እና በሉዓላዊነቱ መታመን ማለት ነው።

በፍጹም ልብህ በእግዚአብሔር ታመን፥ በራስህም ማስተዋል አትደገፍ፤ በመንገድህ ሁሉ እርሱን እወቅ፥ እርሱም ጎዳናህን ያቀናልሃል።
               ምሳሌ 3፥5-6


👉ኢየሱስ የእግዚአብሔር ልጅ እና የሰው ልጆች ሁሉ አዳኝ ነው። በህይወቱ፣ በሞቱ እና በትንሳኤው፣ ኢየሱስ ድነትን እና ከእግዚአብሔር ጋር እርቅን አውጇል። በኢየሱስ መታመን ማለት የከፈለውን መስዋዕትነት መቀበል እና ትምህርቱን መከተል ማለት ነው።

“በእርሱ የሚያምን ሁሉ የዘላለም ሕይወት እንዲኖረው እንጂ እንዳይጠፋ እግዚአብሔር አንድያ ልጁን እስኪሰጥ ድረስ ዓለሙን እንዲሁ ወዶአልና።”
            ዮሐንስ 3፥16

መንፈስ ቅዱስ በአማኞች ሕይወት ውስጥ የእግዚአብሔር መገኘት፣ እየመራቸው፣ የሚያጽናናቸው እና እንደ እግዚአብሔር ፈቃድ እንዲኖሩ የሚያስችላቸው ነው። በመንፈስ ቅዱስ መታመን ማለት በዕለት ተዕለት ሕይወት ውስጥ በእሱ መመሪያ እና ጥንካሬ መታመን ማለት ነው።

“አብ በስሜ የሚልከው ግን መንፈስ ቅዱስ የሆነው አጽናኝ እርሱ ሁሉን ያስተምራችኋል እኔም የነገርኋችሁን ሁሉ ያሳስባችኋል።”
              ዮሐንስ 14፥26


👉መጽሐፍ ቅዱስ እግዚአብሔርን ደስ የሚያሰኝ  ሕይወት እንድንመራ እውነትን፣ ጥበብንና ትምህርትን የሚሰጥ በመንፈስ አነሳሽነት የተጻፈ ቃል ነው። በመጽሐፍ ቅዱስ መታመን ማለት ሥልጣን ያለው እና ለእምነት እና ለተግባር ወይንም ለኑሮ በቂ እንደሆነ ማመን ማለት ነው።

“የእግዚአብሔር ሰው ፍጹምና ለበጎ ሥራ ሁሉ የተዘጋጀ ይሆን ዘንድ፥ የእግዚአብሔር መንፈስ ያለበት መጽሐፍ ሁሉ ለትምህርትና ለተግሣጽ ልብንም ለማቅናት በጽድቅም ላለው ምክር ደግሞ ይጠቅማል።”
           2ኛ ጢሞቴዎስ 3፥16-17


ይቀጥላል...


ወደ ቻናሉ ለመ🀄️🀄️ል፦ @Holy_scriptures
7👍7👏1
.    ==❀❀❀===❀❀❀==      
              የዕለቱ ጥቅስ 
     ==❀❀❀===❀❀❀==
“ልጆችም ስለ ሆናችሁ እግዚአብሔር አባ አባት ብሎ የሚጮኽ የልጁን መንፈስ በልባችሁ ውስጥ ላከ።”
ገላትያ 4፥6



ወደ ቻናሉ ለመ🀄️🀄️ል፦ @Holy_scriptures
👍61
ዓላማ መር ህይወት- ቀን 24_Purpose driven Life - Day 24_ alama mer hiywot…
PETERiCH (I am empty without Jesus)
#መጻሕፍትን_በድምጽ

👉ርዕስ፦ ዓላማ መር ሕይወት
✍️ጸሐፊ፦ ሪክ ዋረን
🗣ትርጉም፦ ኢቫንጀሊካል ቴዎሎጂካል ኮሌጅ
🗒ክፍል፦ 24 (በእውነት መለወጥ)


ይቀጥላል...


ወደ ቻናሉ ለመ🀄️🀄️ል፦ @Holy_scriptures
እንዴት እንሙት? እንዴት እንኑር?


                   በጋሽ ንጉሤ ቡልቻ


በምድር ላይ ረጅም ዕድሜ አልኖረም፤ የኖረበት ጥቂት ዕድሜ ግን እስከ ዛሬ ያላባራ የለውጥ፣ የተሐድሶ፣ የፍስሓ፣ የጸጋ ሞገድ አስነሥቷል። ‘ከኖርኩ አይቀር እንደ እርሱ ልኑር’ የሚያሰኝ ትርጉም ያለው ሕይወት ኖረ። ኢየሱስ ክርስቶስ እንዴት እንደሚኖር ብቻ ሳይሆን እንዴት እንደሚሞትም አሳየን። ከኑሮው ለመቅዳት የምንሻማ ሁሉ ከሞቱም ለመማር ብንዘጋጅ እጅግ እንጠቀማለን።

እውነቱን ለመናገር መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ለመሞት የመጣ ነዋሪ ነበር። “በሥጋና በደም የተካፈለው” (ሰው ሆኖ የተወለደው) በሞቱ አማካይነት በሞት ላይ ሥልጣን ያለውን ዲያብሎስን ለመሻር ነው። እና በመሞት አሸነፈው፤ በንጹሕ ሞት ድል ነሣው፤ ታይቶ በማይታወቅ ዐይነት መሥዋዕታዊ ሞት ሞትንና አለቃውን ቀጣቸው። ቅርንጫፉን በመቁረጥ ሳይሆን፣ የሞትን ሥሩን በጥሶ አመከነው። የሞት መነሻ ሥሩ ኀጢአት ነበረና የኀጢአትን ሰንኮፍ ሲነቅል ሞት ተልፈሰፈሰ። የእግዚአብሔር ስም ይመስገን። ይህ ሟች ልዩ ሟች ነው። ማንም ይሞታል በኀጢአቱ፣ በአዳምነቱ፤ ይህኛው ግን ያለ ኀጢአት ሞቶ ኀጢአተኛኞች ሟቾችን አጸደቀ። አቤት ጥበቡ!

ይህስ ይሁን፣ ታዲያ ትምህርቱ ምንድን ነው? ከአሟሟቱ ምን እንማራለን?

የወንጌላቱ ትራኬ በሕይወት ታሪክ አጻጻፍ ደንብ ሲቃኝ አድልዎ ያሳያል። ስለ ሕይወቱ፣ ስለ አገልግሎቱ፣ ስለ ትምህርቱ፣ ከጻፉት ጋር በማይመጣጠን መንገድ ስለ ሞቱ የጻፉት ይበልጣል። ምናልባት የመጽሐፋቸውን እርቦ ያህል የጻፉት ስለዚህ ሰው የመጨረሻ ሳምንት ሳይሆን አይቀርም። በከንቱ አላደረጉትም፤ ሞቱ ግዙፍ ሞት ነበርና።

#የመጀመሪያው_ትምህርት

ኢየሱስ ክርስቶስ ኑሮው የተለካ ዐጭር ጊዜ እንደ ነበረ ዐውቆ፣ ይህንኑ እየተናገረ፣ በዚሁ ዕይታ ይኖር የነበረ ሰው ነበር። በታላቅ መረጋጋት ውስጥ ሆኖ እያለ አንዳች የተልእኮ ጥድፊያ ደግሞ ይጎተጉተው እንደ ነበር ያስታውቃል። “…ገና ጥቂት ጊዜ ከእናንተ ጋር እቆያለሁ፤ ወደ ላከኝም እሄዳለሁ። ትፈልጉኛላችሁ አታገኙኝምም…” ዮሐ 7፥33-34፤ “ቀን ሳለ የላከኝን ሥራ ላደርግ ይገባኛል” (ዮሐ 9፥4)፤ ለመሞት ተዘጋጅቶ በተልእኮ ልቡና ውስጥ ይኖር ነበር።

የእኛስ እድሜ ልክ የለሽ ነው እንዴ? ‘ሌሎች ሊሞቱ ይችላሉ፤ እኔ እንኳ ሳልቆይ አልቀርም’ ማለት ከፍተኛ ሽንገላ አይደለምን? የሞትን እውነታ ገፋ ገፋ ማድረግ ሰብአዊ ጨዋታ ሳይሆን አይቀርም። የምር ስንነጋገር ግን ይህን ዐረፍተ ነገር እንኳ አንብበን ሳንጨርስ ሕይወት ልትቋረጥ እንደምትችል አንዘነጋውም። እንግዲያው አንዱ የጌታ ትምህርት ሕይወት ጥቂት ጊዜ ታይቶ እንደሚጠፋ እንፋሎት መሆኑን ተገንዝቦ በተልእኮ ልቡና እንዲሁም በሥራ ትጋት መኖር ነው። ሕይወት ከቸሩ ጌታ የተሰጠችን ጥሪት ናት። ሙዐለ ሕይወት ትርፋማ እንዲሆን ሳንጨነቅ፣ በብርቱ ትጋት እንድንሠራ ያሻል።

#ሁለተኛው_ትምህርት

ጌታችን ሞትን እንደ ክብር መሸጋገሪያ መንገድ አድርጎ የቆጠረበት አተያይ ነው። የሞቱ ጊዜ ደረሰ ማለት ለጌታችን የክብሩ ጊዜ ደረሰ የማለት ያህል ነበር። አሟሟቱ ላይ ላዩን ሲያዩት የታላቅ ውርደት ይመስል ነበር። በሐሰተኛ ምስክሮች ተከስሶ፣ በቅርብ ጓደኞቹ ተከድቶ፣ አጠገቡ በነበረ ተማሪው በገንዘብ ተሸጦ፣ በወታደሮች ጥፊና ድብደባ፣ በጅራፍ ግርፊያና በስላቅ እየተነዳ፣ እርቃኑን በእንጨት መስቀል ላይ ተሰቅሎ፣ ዐላፊ አግዳሚ እያላገጠበት የሞተውን ሞት እንዴት ነው የክብር መንገድ የሚለው?

ነገሩ እንዲህ ነው፤ መሬት ሲሳለቅበት ሰማይ ያጨበጭብለት ነበር፤ ጲላጦስ እንዲሰቀል ሲፈርድበት አባቱ ትንሣኤውን ያዘጋጅለት ነበር፤ ብቻውን ቀርቶ እየጮኸ ሲሞት ለአእላፍ አማኞቹ የሰማይ በር ያስከፍት ነበር። ሞቱ ታላቅ ዐላማ ስለ ነበረው ጻድቅ አምላክ ያከበረው ሞት ነበረ። አባቱን እስከ መጨረሻው ሰዓት ድረስ ታዝዞ፣ የሰውን ልጅ እስከ መጨረሻው ድረስ ወድዶ ስለ ሞተ ታላቅ ክብር ተጎናጸፈ። “... በዚህ ምክንያት እግዚአብሔር ያለ ልክ ከፍ ከፍ አደረገው” ብሎ ይለናል ሐዋርያው ጳውሎስ (ፊል 2፥9)። እንግዲያው ለእኛ ለምናምነው ሁሉ የመታዘዝና የፍቅር አርኣያ ሆነልን፤ የክብርን መንገድ አሳየን። እና እኛ ከመሞታችን በፊት በዚህ በጠረገልን መንገድ ስንጓዝ፣ በሕመም ብንሞት፣ በአደጋ፣ በእርጅና በሌላ በማናቸውም “አሰቃቂ” ይሁን “ለስላሳ” አሟሟት ብንሞት ግሥገሳችን ወደ ክብር እንደ ሆነ እንድናስብ ያሻል። ‘ጎሽ፤ አንተ ታማኝ ባሪያ እንኳን ደኅና መጣህ!’ ወደሚለን ቸር አባት እየቀረብን መሆናችንን እናስብ።


ይቀጥላል. . .


ምንጭ:- hintset.org



ወደ ቻናሉ ለመ🀄️🀄️ል፦ @Holy_scriptures
👍76👏1
በቅዱሳት መጻሕፍት ውስጥ ዳዊት ከንጉሥ ሳኦል ፊት በሸሸ ጊዜ የት ነበር የተሸሸገው?
Anonymous Quiz
18%
ሀ. ሞዓብ ምድር
60%
ለ. ዓዶላም ዋሻ
5%
ሐ. ቤተልሔም
18%
መ. ኬብሮን
👍2
.    ==❀❀❀===❀❀❀==      
              የዕለቱ ጥቅስ 
     ==❀❀❀===❀❀❀==
“ለሥራ ከመትጋት አትለግሙ፤ በመንፈስ የምትቃጠሉ ሁኑ፤ ለጌታ ተገዙ፤”
ሮሜ 12፥11



ወደ ቻናሉ ለመ🀄️🀄️ል፦ @Holy_scriptures
👍7
ዓላማ መር ህይወት- ቀን 25_Purpose driven Life - Day 25_ alama mer hiywot…
PETERiCH (I am empty without Jesus)
#መጻሕፍትን_በድምጽ

👉ርዕስ፦ ዓላማ መር ሕይወት
✍️ጸሐፊ፦ ሪክ ዋረን
🗣ትርጉም፦ ኢቫንጀሊካል ቴዎሎጂካል ኮሌጅ
🗒ክፍል፦ 25 (በችግር መለወጥ)


ይቀጥላል...


ወደ ቻናሉ ለመ🀄️🀄️ል፦ @Holy_scriptures
3👍2
#እራሳችንን_እንመርምር

ከታላቁ ድነታችን ጀምሮ አንዳንድ በሕይወት ከከበቡንና ካስቸገሩን ሁኔታዎች እግዚአብሔር በቸርነቱ ታድጎን ካወጣን በኋላ በተአምራቱና ድንቁ ተገርመን እርሱን ስናወራው እንከርማለን። ግን ከዚያ በዘለለ ምን ማድረግ እንችላለን? የተደረገው ተአምር እንድንደሰት እና እንድንገረም ብቻ ነው?

“ታንኳዎችንም ወደ ምድር አድርሰው ሁሉን ትተው ተከተሉት።”
ሉቃስ 5፥11



ወደ ቻናሉ ለመ🀄️🀄️ል፦ @Holy_scriptures
👍62🙏2
.    ==❀❀❀===❀❀❀==      
              የዕለቱ ጥቅስ 
     ==❀❀❀===❀❀❀==
“ኢየሱስም አዘነላቸውና ዓይኖቻቸውን ዳሰሰ፥ ወዲያውም አዩና ተከተሉት።”
ማቴዎስ 20፥34



ወደ ቻናሉ ለመ🀄️🀄️ል፦ @Holy_scriptures
5👍2🙏2