ቅዱሳት መጻሕፍት
7.45K subscribers
1.35K photos
61 videos
331 files
795 links
በዚህ ቻናል

👉ቅዱሳት መጻሕፍት ይጠናሉ::
👉መጽሐፍ ቅዱሳዊ ትምህርቶች ይቀርባሉ::
👉 ለቅዱሳት መጽሐፍት ጥናት የሚያግዙ መጻሕፍት ይለቀቃሉ።

⭐️⭐️⭐️⭐️⭐️

@Holy_scriptures
Download Telegram
Audio
#መጻሕፍትን_በድምጽ

👉ርዕስ፦ ዓላማ መር ሕይወት
✍️ጸሐፊ፦ ሪክ ዋረን
🗣ትርጉም፦ ኢቫንጀሊካል ቴዎሎጂካል ኮሌጅ
🗒ክፍል፦ 12 (ከእግዚአብሔር ጋር ወዳጅነትህን ማሳደግ)


ይቀጥላል...


ወደ ቻናሉ ለመ🀄️🀄️ል፦ @Holy_scriptures
👍2
ዐብይ ጾም የሚጀምረው መቼ ነው? ጾሙስ ስንት ቀን ነው?


ጾም ነገ ይገባል፤ ዐቢይ ጾም የሚጀምረው ግን በሚቀጥለው ሰኞ ዕለት ነው። (ዝርዝሩን ዝቅ ብዬ አስረዳለሁ።) የካቶሊክ፣ የአንግሊካን፣ የምስራቅ ኦርቶዶክስ እና የተለያዩ የፕሮቴስታንት አብያተ ክርስቲያናት ይህን የ40 ቀናት ጾም (Lent) ያካሄዳሉ። (የኢትዮጵያ ፕሬቴስታንቶች ግን ከኦርቶዶክሳዊነት ጋር የተለያዩ መሆናቸው እንዲያሳይላቸው ነው መሰለኝ ይህን ትውፊት አይከተሉም።) የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤ/ክ ይህን “ጾመ አርብዓ” (ሁዳዴ) እንዲጾሙ ታዛለች፤ ይህንን ቤተ ክርስቲያኒቱ ሕጓ አድርጋ በተቀበለችው መጽሐፈ ሲኖዶስ (ዘሐዋርያት ተደንግጓል)። 40 ቀናት የተመረጡት ጌታ "በገዳመ ቆሮንቶስ" ለአርባ ቀናት መጾሙንና በብሉይ ኪዳንም ሙሴና ኤልያስ የጾሙት በመሆኑ ነው። የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤ/ክ ጾም በተግባር ሲታይ ግን የአርባ ቀን ጾም ሳይሆን፣ የ54 ቀናት ነው። (አንዳንዶች 55 ያደርጉታል።) ለምን?

ፕሮፌሰር ጌታቸው ኃይሌ በግለ ታሪካቸው እንዳሰፈሩት ከሆነ፣ ይህ የሆነበት ምክንያት በ40 ቀናቱ ጾም ላይ “ሁለት ባለሰባት ቀን ጾሞች፣ አንዱ ጾመ አርባ ከመጀመሩ በፊት፣ አንዱ ካለቀ በኋላ ተጨምረው፣ እነዚህ ሦስት ጾሞች ተርታውን ስለሚመጡ ነው። ከጾመ አርባ በፊት የሚመጣው (የመጀመሪያው) ጾም “ጾመ ሕርቃል” ይባላል። ጾመ ሕርቃልና ጾመ አርባ እንዳለቁ የሚመጣው (የመጨረሻው) ጾም ደግሞ “ጾመ ሕማማት” ይባላል። ሦስቱ ጾሞች በተለያየ ጊዜ ከመምጣት ይልቅ ተከታትለው የመጡት በአበው ውሳኔ እንጂ፣ ታሪካቸው ተከታታይ ሆኖ አይደለም። ጾመ አርባ የሚጾመው የጌታን ጾም ለማስታወስና ከጌታ ጋር ተባባሪ ለመሆን ነው፤ ጾመ ሕማማት የሚጾመውና የሚሰገደው የጌታን ሥቃይ ለማስታወስና ስርየት ኀጢአት ለማግኘት ነው። ጾመ ሕርቃል የሚጾመው ሕርቃል ላፈረሰው መሐላ ፍዳ ለመክፈል ነው።”

ሕርቃል ማነው?

ሕርቃል (Heraclius) ከ610-641 ባይዛንታይንን የገዛ ንጉሠ ነገሥት ነው። ዋና ከተማው ቁስጥንጥንያ ነበረች። በግዛቱም ውስጥ ኦርቶዶክሳውያን፣ ካቶሊኮች እና አይሁድ ነበሩ። እነዚህም ሦስት ወገኖች በየጊዜው ጠብ የሚፈጥሩና አዲስ ወራሪ በመጣ ቁጥር ከመካከላቸው አንዱ ወራሪውን አስቀድሞ በመቀበል ሌሎቹን ለማስመታት የሚጥሩ ነበሩ። ሕርቃል በፊት የነበረው ንጉሥ ፎቃ በሚገዛበት ጊዜ የፋርስ ንጉሥ ቁስጥንጥንያን ከብቦ ማስጨነቅ ጀመሩ። ያኔ ክርስቲያኖቹ የፋሲካን በዓል በሚያደርጉበት ጊዜ በየአገሩ ያሉ አይሁድ ተጠራርተው ወረሯቸውና አብያተ ክርስቲያናትን ዘረፉ። መዘበሩ።

ወዲያው ሕርቃል የጦር መኮንን ነበረና የፋርስን ንጉሥ አሸንፎ ሕዝቡን ነጻ ሲያወጣ የቁስጥንጥንያ ነዋሪዎች የገዛ ንጉሣቸውን ገድለው እርሱን አነገሡት። እርሱም ከአገር አገር በውጊያ እየዞረ ኢየሩሳሌም ሲደርስ በዚያን ወቅት አይሁድም ብዙ እጅ መንሻ አመጡለትና እንዳይገድላቸው ቃል አስገቡት፤ አይሁድ ያደረጉት የማያውቀው ሕርቃልም ቃል ኪዳን ገባላቸው። ኢየሩሳሌም ሲገባ ደግሞ የክርስቲያኖቹ ካህናት በዝማሬ ተቀበሉት። የፈራረሱትን አብያተ ክርስቲያናት ያየው ሕርቃል የሆነውን ነገር ቢጠይቅ የአይሁድን ክፋት አጫወቱትና እንዲበቀልላቸው ጥያቄ አቀረቡለት።

እርሱ ግን ለአይሁድ ቃል ኪዳን እንደገባላቸውና ቃል ኪዳኑን ቢያፈርስ እግዚአብሔር እንደሚቀጣው ነገራቸው። ካህናቱ ግን “አይሁድን ተበቀልልን እንጂ ቃል ኪዳኑ አያሳስብህ፤ ንስሓ እንዲሆንህ እኛ ክርስቲያኖቹ ዓለም እስክታልፍ ድረስ ስላንተ በየዓመቱ አንድ ሳምንት እንጾምልሃለን” አሉት። በዚያ ጊዜ ሠራዊቱ አይሁድን እንዲገድሏቸው ትእዛዝ ሰጠ። ብዙዎቹን ፈጇቸው። እነዚያም ኤጴስ ቆጶሳት ስለ ሕርቃል መሓላ መጣስ በየዓመቱ አንድ ሳምንት የንስሓ ጾም እንዲጾሙ ለክርስቲያኖች ሁሉ ላኩባቸው።

እናም “ጾመ ሕርቃል” የንሥሐ ጾም ነው። Encyclopaedia Aethiopica ይህን አሳምሮ ይገልጸዋል፤ “Heraclius was also the Emperor whose repentance for the massacre of Jews in Jerusalem in 630/31 became the alleged reason for adding an (eighth) extra week to the Lent.” በማለት። ጾሙ ራሱን የቻለ ሳምንት ስላስፈለገው፣ በሰባቱ ሳምንታት ጾም ላይ ተጨምሮ ጾሙን የስምንት ሳምንታት አድርጎታል። “ፍትሐ ነገሥት ንባቡና ትርጓሜው” የሚለውን ኦርቶዶክሳዊ መጽሐፍም፣ “ከዐቢይ ጾም አስቀድማ የምትሆን የሕርቃል ጾም ናት” ይላል (ገጽ 150)።

እናላችሁ የዚህ ሳምንት ጾም ከዐቢይ ጾም ቀድማ የምትመጣ ጾመ ሕርቃል ናት። ጾመ ሕርቃልን ፍትሓ ነግሥቱ ቢጠቅሰውም ዝርዝሩን አይናገርም። ትርጓሜ ፍትሐ ነገሥትም መንፈሳዊ አንድምታው ላይ ያተኩራል እንጂ ታሪኩን አይናገርም፤ እንደ ፕሮፌሰር ጌታቸው አገላለጽ። እሳቸውም ታሪኩን ያገኙት አባቶች ወደ ግዕዝ ከተተረጎመው የጊዮርጊስ ወልደ ዓሚድ የዓለም ታሪክ መጽሐፍ ላይ ነው። ስለዚህም አብዛኛው ጿሚ የዐቢይ ጾምን የመጀመሪያ ሳምንት ጾም ታሪክ ሳያውቅ ነው የሚጾመው። ለኢትዮጵያ ጾሙን የሰጠችው የግብፅ ቤ/ክ ታሪኩ በሕይወት ያሉ ወገኖችን የሚያቃቅር ሆኖ ስላገኘችው ታሪኩን መካድ ወይም ለጾሙ ሌላ ምክንያት መስጠትን የተሻለ ሆና ያገኘችው ይመስላል። በእኔ ውስን ንባብ መሠረት የግብፅ ኦርቶዶክስ ቤት ክርስቲያን የዚህን ሳምንት ጾም “የዝግጅት ሳምንት” በሚል ስያሜ ነው የምትጾመው፤ የዐቢይ ጾም ዝግጅት መሆኑ ነው። በተለያዩ አጋጣሚዎች እንደ ታዘብሁት ከሆነ ደግሞ በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ አማኞች ዘንድ ግን ይህ ታሪክ በቅጡ የሚታወቅ አይመስለኝም።

ጾመ ሕርቃል የአንድ ሳምንት ጾም ነው፤ ከዚያ የ40 ቀን ዐቢይ ጾም ይቀጥላል። ከዚያም የጌታን ሕማማት መነሻው የሚያደርገው የሐዋርያት ጾም ለአንድ ሳምንት ይቀጥላል። ስለዚህ 7 + 40 + 7 = 54። ከዚያም ይፈሰካል!

ዛሬ ዛሬ ዐቢይ ጾምን የሚጾሙ ጥቂት ወንጌላውያን ክርስቲያኖችን ዐውቃለሁ፤ እኔም ስተባበራቸው ነበር። ታዲያ ከአርባው ቀን በፊት (በዚህ ሳምንት) የሚካሄደውን “ጾመ ሕርቃል” መጾም አለባቸው? ይህስ ምን ያህል መጽሐፍ ቅዱሳዊ ነው?


ምንጭ፦ @PaulosFekadu



ወደ ቻናሉ ለመ🀄️🀄️ል፦ @Holy_scriptures
👍83
በቅዱሳት መጻሕፍት ውስጥ ለአርባ ቀንና ለአርባ ሌሊት የጾመው ሰው ማን ነው?
Anonymous Quiz
19%
ሀ. ሙሴ
2%
ለ. ኤልያስ
37%
ሐ. ጌታችን እና መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ
42%
መ. ሁሉም
👍8🙏2
.    ==❀❀❀===❀❀❀==      
              የዕለቱ ጥቅስ 
     ==❀❀❀===❀❀❀==
“ኢዮሣፍጥም ፈራ፥ እግዚአብሔርንም ሊፈልግ ፊቱን አቀና፤ በይሁዳም ሁሉ ጾም አወጀ።”
2 ዜና 20፥3



ወደ ቻናሉ ለመ🀄️🀄️ል፦ @Holy_scriptures
8👍1👏1
Audio
#መጻሕፍትን_በድምጽ

👉ርዕስ፦ ዓላማ መር ሕይወት
✍️ጸሐፊ፦ ሪክ ዋረን
🗣ትርጉም፦ ኢቫንጀሊካል ቴዎሎጂካል ኮሌጅ
🗒ክፍል፦ 13 (እግዚአብሔርን የሚያስደስት አምልኮ)


ይቀጥላል...


ወደ ቻናሉ ለመ🀄️🀄️ል፦ @Holy_scriptures
👍4
ከአፍታ ቆይታ በኋላ... #እግዚአብሔር_የመረጠው_ጾም በሚል ርዕስ ይጠብቁን።



ወደ ቻናሉ ለመ🀄️🀄️ል፦ @Holy_scriptures
👍4
#እግዚአብሔር_የመረጠው_ጾም


እግዚአብሔር የመረጠው ጾም፦ በቅዱሳት መጻሕፍት እይታ

ጾም በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ በግለሰቦች እና በማህበረሰቦች ለተለያዩ ዓላማዎች የሚተገበር፣ ንስሐ መግባትን፣ መለኮታዊ መመሪያን መፈለግ እና ለእግዚአብሔር መሰጠትን የሚያሳይ ማዕከላዊ መንፈሳዊ ትምህርት ወይንም ልምምድ ነው። ይሁን እንጂ መጽሐፍ ቅዱስ ጾም በሁለት ይከፍለዋል ሥርዓታዊ ጾም እና እግዚአብሔር በእውነት የሚፈልገው ወይንም የመረጠው በማለት። “እግዚአብሔር የመረጠው ጾም” ጽንሰ-ሐሳብ ከየትኛውም ክፍል ይልቅ በኢሳይያስ 58 ላይ በተሻለ ሁኔታ ተብራርቷል፣ እግዚአብሔር እስራኤልን ስለማስመሰል ጾማቸው ገሠጻቸው እና እርሱን ደስ የሚያሰኘውን የጾም ባህሪያት ደግሞ ገለጸላቸው። ይህ ምንባብ ጾምን ከመጽሐፍ ቅዱሳዊ አንፃር ለመረዳት ሥነ-መለኮታዊ እና ሥነ-ምግባራዊ ምልከታን ያቀርባል።

የላይ ላዩ ጾም በእግዚአብሔር ከተመረጠው ጾም ጋር ሲነጻጸር (ኢሳይያስ 58፥1-12)

በኢሳይያስ 58 ላይ፣ እስራኤላውያን እግዚአብሔር ለምን ጾማቸውን እንደማይቀበል በማሰብ ብስጭታቸውን ገልጸዋል (ኢሳ 58፥3)። እግዚአብሔር ምላሹን የሰጣቸው ግብዝነታቸውን በማጋለጥ፣ በግፍ እና ራስ ወዳድነት. . . ሳያስወግዱ እንደሚጾሙ ጠቁሟል። ሕዝቡ በውጫዊ የአምልኮ ሥርዓቶች የእግዚአብሔርን ሞገስ ፈለጉ ነገር ግን ልባቸውን እና ተግባራቸውን ከእሱ ፈቃድ ጋር ማስማማት አልቻሉም።

የሚከተለው አንቀጽ ተገቢ ያልሆነውን ጾም እግዚአብሔርን ከሚያስደስተው የጾም ዓይነት ጋር ያነጻጽራል።


"እኔስ የመረጥሁት ጾም ይህ አይደለምን? የበደልን እስራት ትፈቱ ዘንድ፥ የቀንበርንስ ጠፍር ትለቅቁ ዘንድ፥ የተገፉትንስ አርነት ትሰድዱ ዘንድ፥ ቀንበሩንስ ሁሉ ትሰብሩ ዘንድ አይደለምን? እንጀራህንስ ለተራበ ትቈርስ ዘንድ፥ ስደተኞቹን ድሆች ወደ ቤትህ ታገባ ዘንድ፥ የተራቈተውንስ ብታይ ታለብሰው ዘንድ፥ ከሥጋ ዘምድህ እንዳትሸሽግ አይደለምን?"
ኢሳይያስ 58፥6-7


ይቀጥላል...



ወደ ቻናሉ ለመ🀄️🀄️ል፦ @Holy_scriptures
👍93
#የእግዚአብሔር_ቃል_ምን_ይላል?


ኢሳይያስ 58
¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯
¹ በኃይልህ ጩኽ፥ አትቈጥብ፥ ድምፅህን እንደ መለከት አንሣ፥ ለሕዝቤ መተላለፋቸውን ለያዕቆብ ቤትም ኃጢአታቸውን ንገር።
² ነገር ግን ዕለት ዕለት ይሹኛል መንገዴንም ያውቁ ዘንድ ይወድዳሉ፤ ጽድቅን እንዳደረጉ የአምላካቸውንም ፍርድ እንዳልተዉ ሕዝብ እውነተኛውን ፍርድ ይለምኑኛል፥ ወደ እግዚአብሔርም ለመቅረብ ይወድዳሉ።
³ ስለ ምን ጾምን፥ አንተም አልተመለከትኸንም? ሰውነታችንንስ ስለ ምን አዋረድን፥ አንተም አላወቅህም? ይላሉ። እነሆ፥ በጾማችሁ ቀን ፈቃዳችሁን ታደርጋላችሁ፥ ሠራተኞቻችሁንም ሁሉ ታስጨንቃላችሁ።
⁴ እነሆ፥ ለጥልና ለክርክር ትጾማላችሁ በግፍ ጡጫም ትማታላችሁ፤ ድምፃችሁንም ወደ ላይ ታሰሙ ዘንድ ዛሬ እንደምትጾሙት አትጾሙም።
⁵ እኔ የመረጥሁት ጾም ይህ ነውን? ሰውስ ነፍሱን የሚያዋርደው እንደዚህ ባለ ቀን ነውን? በውኑ ራሱን እንደ እንግጫ ዝቅ ያደርግ ዘንድ ማቅንና አመድንም በበታቹ ያነጥፍ ዘንድ ነውን? በውኑ ይህን ጾም፥ በእግዚአብሔርም ዘንድ የተወደደ ቀን ትለዋለህን?
⁶ እኔስ የመረጥሁት ጾም ይህ አይደለምን? የበደልን እስራት ትፈቱ ዘንድ፥ የቀንበርንስ ጠፍር ትለቅቁ ዘንድ፥ የተገፉትንስ አርነት ትሰድዱ ዘንድ፥ ቀንበሩንስ ሁሉ ትሰብሩ ዘንድ አይደለምን?
⁷ እንጀራህንስ ለተራበ ትቈርስ ዘንድ፥ ስደተኞቹን ድሆች ወደ ቤትህ ታገባ ዘንድ፥ የተራቈተውንስ ብታይ ታለብሰው ዘንድ፥ ከሥጋ ዘምድህ እንዳትሸሽግ አይደለምን?
⁸ የዚያን ጊዜ ብርሃንህ እንደ ንጋት ይበራል፥ ፈውስህም ፈጥኖ ይበቅላል፥ ጽድቅህም በፊትህ ይሄዳል፥ የእግዚአብሔርም ክብር በኋላህ ሆኖ ይጠብቅሃል።
⁹ የዚያን ጊዜ ትጠራለህ እግዚአብሔርም ይሰማሃል፤ ትጮኻለህ እርሱም፦ እነሆኝ ይላል። ከመካከልህ ቀንበርን ብታርቅ፥ ጣትህንም መጥቀስ ብትተው፥
¹⁰ ባታንጐራጕርም፥ ነፍስህንም ለተራበ ብታፈስስ፥ የተጨነቀውንም ነፍስ ብታጠግብ፥ ብርሃንህ በጨለማ ይወጣል ጨለማህም እንደ ቀትር ይሆናል።
¹¹ እግዚአብሔርም ሁልጊዜ ይመራሃል፤ ነፍስህንም በመልካም ነገር ያጠግባል አጥንትህንም ያጠናል፤ አንተም እንደሚጠጣ ገነት፥ ውኃውም እንደማያቋርጥ ምንጭ ትሆናለህ።
¹² ከዱሮ ዘመን የፈረሱት ስፍራዎች ይሠራሉ፥ የብዙ ትውልድም መሠረት ይታነጻል፤ አንተም፦ ሰባራውን ጠጋኝ፥ የመኖሪያ መንገድን አዳሽ ትባላለህ።
¹³ ፈቃድህን በተቀደሰው ቀኔ ከማድረግ እግርህን ከሰንበት ብትመልስ፥ ሰንበትንም ደስታ፥ እግዚአብሔርም የቀደሰውን ክቡር ብትለው፥ የገዛ መንገድህንም ከማድረግ ፈቃድህንም ከማግኘት ከንቱ ነገርንም ከመናገር ተከልክለህ ብታከብረው፥
¹⁴ በዚያን ጊዜ በእግዚአብሔር ደስ ይልሃል፥ በምድርም ከፍታዎች ላይ አወጣሃለሁ፥ የአባትህንም የያዕቆብን ርስት አበላሃለሁ፤ የእግዚአብሔር አፍ ተናግሮአልና።




ወደ ቻናሉ ለመ🀄️🀄️ል፦ @Holy_scriptures
👍12
.    ==❀❀❀===❀❀❀==      
              የዕለቱ ጥቅስ 
     ==❀❀❀===❀❀❀==
“ለሰልፍም ኃይልን ታስታጥቀኛለህ፤ በላዬ የቆሙትን በበታቼ ታስገዛቸዋለህ።”
2ኛ ሳሙኤል 22፥40



ወደ ቻናሉ ለመ🀄️🀄️ል፦ @Holy_scriptures
👍6
Audio
#መጻሕፍትን_በድምጽ

👉ርዕስ፦ ዓላማ መር ሕይወት
✍️ጸሐፊ፦ ሪክ ዋረን
🗣ትርጉም፦ ኢቫንጀሊካል ቴዎሎጂካል ኮሌጅ
🗒ክፍል፦ 14 (እግዚአብሔር የራቀ ሲመስል)


ይቀጥላል...


ወደ ቻናሉ ለመ🀄️🀄️ል፦ @Holy_scriptures
👍2
#እምነት

የእምነት እሳቤ በአዲስ ኪዳን


                   ክፍል-3

የአዲስ ኪዳን የእምነት እሳቤ አራት ዐበይት ፍሬ ሐሳቦችን ያጠቃልላል፤

1. እምነት ማለት የተሰቀለውንና ከሞት የተነሣውን ክርስቶስን እንደግል አዳኛችንና ጌታችን አድርጎ ከልብ ማመንና በእርሱም መደገፍ ማለት ነው።

“ጻድቅ በእምነት ይኖራል ተብሎ እንደ ተጻፈ የእግዚአብሔር ጽድቅ ከእምነት ወደ እምነት በእርሱ ይገለጣልና።”
ሮሜ 1፥17

በአዲስ ኪዳን ለተገለጠው ኢየሱስ ክርስቶስ ፈቃዳችንንና ሁለንተናችንን በማስገዛት በሙሉ ልባችን ማመንን ያካትታል (ሮሜ 6፥17፣ ኤፌ 6፥6፤ ዕብ 10፥22)።

2. እምነት በእውነተኛ ጸጸት በክርስቶስ በኩል ከኀጢአት ወደ እግዚአብሔር መመለስ ማለት ነው(ሐሥ 17፥30፤ 2ቆሮ 7፥10)። ለድነት የሚያበቃ እምነት ሁልጊዜ የንስሓ እምነት ነው (ሐሥ 2፥37-38፤ ማቴ 3፥2)።

3. እምነት እግዚአብሔርን በማመን፣ ለእርሱ ምስጋናን በማቅረብ፣ በመንፈስ ቅዱስ ዳግም ልደትን በማግኘት በሚነሣሣ የኑሮ ዘይቤ ለኢየሱስ ክርስቶስና ለቃሉ መታዘዝን ያካትታል (ዮሐ 3፥3-6፤ 14፥15:21-24፤ ዕብ 5፥8-9) ስለዚህ እምነትና መታዘዝ የማይነጣጠሉ ናቸው።

“በእርሱም ስለ ስሙ በአሕዛብ ሁሉ መካከል ከእምነት የሚነሣ መታዘዝ እንዲገኝ ጸጋንና ሐዋርያነትን ተቀበልን፤”
ሮሜ 1፥5

“እንግዲህ እንደ ወንጌሌ ስለ ኢየሱስ ክርስቶስም እንደ ተሰበከ፥ ከዘላለም ዘመንም የተሰወረው አሁን ግን የታየው በነቢያትም መጻሕፍት የዘላለም እግዚአብሔር እንደ አዘዘ ለእምነት መታዘዝ ይሆን ዘንድ ለአሕዛብ ሁሉ የታወቀው ምሥጢር እንደ ተገለጠ መጠን ሊያበረታችሁ ለሚችለው፥”
ሮሜ 16፥25-26

ራስን ለቅድስና ላይሰጡ ድነት አለኝ ማለት ተገቢ አይደለም፡፡

4. እምነት፤ ራስን በፍቅር፣ በምስጋናና በታማኝነት በመግለጽ ለጌታ ለኢየሱስ ክርስቶስ ከልብ የሆነ መሰጠትና ቁርኝትን ያካትታል፡፡ እምነት በጥልቀት ሲታይ ከፍቅር የሚለይ አይደለም፡፡ እምነት በክርስቶስ ላይ ባተኮረ፣ በግል መሥዋዕትነትና ራስን በመስጠት ተግባር ላይ የተመሠረተ ነው (ማቴ 22፥37፤ ዮሐ 21፥15-17፡ ሐሥ 8፥37፤ ሮሜ 6፥17፤ ገላ 2፥20፤ ኤፌ 6፥6)።

“እርሱንም ሳታዩት ትወዱታላችሁ፤ አሁንም ምንም ባታዩት በእርሱ አምናችሁ፥ የእምነታችሁን ፍፃሜ እርሱም የነፍሳችሁን መዳን እየተቀበላችሁ፥ በማይነገርና ክብር በሞላበት ሐሤት ደስ ይላችኋል።”
1ኛ ጴጥሮስ 1፥8-9



ይቀጥላል...



ምንጭ፦ ምሉእ ሕይወት፤ ገጽ 1746




ወደ ቻናሉ ለመ🀄️🀄️ል፦ @Holy_scriptures
👍6🔥3
በቅዱሳት መጻሕፍት ውስጥ የይስሐቅ ልጅ ያዕቆብ ስንት ልጆች ነበሩት?
Anonymous Quiz
64%
ሀ. 12
33%
ለ. 13
3%
ሐ. 14
0%
መ. 15
👍3
.    ==❀❀❀===❀❀❀==      
              የዕለቱ ጥቅስ 
     ==❀❀❀===❀❀❀==
“ሳሙኤል ግን ገና እግዚአብሔርን አላወቀም ነበር፥ የእግዚአብሔርም ቃል ገና አልተገለጠለትም ነበር።”
1ኛ ሳሙኤል 3፥7



ወደ ቻናሉ ለመ🀄️🀄️ል፦ @Holy_scriptures
👍5
Audio
#መጻሕፍትን_በድምጽ

👉ርዕስ፦ ዓላማ መር ሕይወት
✍️ጸሐፊ፦ ሪክ ዋረን
🗣ትርጉም፦ ኢቫንጀሊካል ቴዎሎጂካል ኮሌጅ
🗒ክፍል፦ 15 (ለእግዚአብሔር ቤተሰብነት ተበጅተሃል)


ይቀጥላል...


ወደ ቻናሉ ለመ🀄️🀄️ል፦ @Holy_scriptures
👍8
ቅዱሳት መጻሕፍት
#እግዚአብሔር_የመረጠው_ጾም እግዚአብሔር የመረጠው ጾም፦ በቅዱሳት መጻሕፍት እይታ ጾም በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ በግለሰቦች እና በማህበረሰቦች ለተለያዩ ዓላማዎች የሚተገበር፣ ንስሐ መግባትን፣ መለኮታዊ መመሪያን መፈለግ እና ለእግዚአብሔር መሰጠትን የሚያሳይ ማዕከላዊ መንፈሳዊ ትምህርት ወይንም ልምምድ ነው። ይሁን እንጂ መጽሐፍ ቅዱስ ጾም በሁለት ይከፍለዋል ሥርዓታዊ ጾም እና እግዚአብሔር በእውነት የሚፈልገው…
#እግዚአብሔር_የመረጠው_ጾም


በኢሳይያስ 58 መሠረት እግዚአብሔር በመረጠው ጾም ሲጾም ምን በረከቶች አሉት

👉ፈውስ እና ጽድቅ

“የዚያን ጊዜ ብርሃንህ እንደ ንጋት ይበራል፥ ፈውስህም ፈጥኖ ይበቅላል፥ ጽድቅህም በፊትህ ይሄዳል፥ የእግዚአብሔርም ክብር በኋላህ ሆኖ ይጠብቅሃል።”
           ኢሳይያስ 58፥8

👉የጸሎት መልስ

“የዚያን ጊዜ ትጠራለህ እግዚአብሔርም ይሰማሃል፤ ትጮኻለህ እርሱም፦ እነሆኝ ይላል። ከመካከልህ ቀንበርን ብታርቅ፥ ጣትህንም መጥቀስ ብትተው፥”
           ኢሳይያስ 58፥9

👉መለኮታዊ መመሪያ እና ጥንካሬ

“እግዚአብሔርም ሁልጊዜ ይመራሃል፤ ነፍስህንም በመልካም ነገር ያጠግባል አጥንትህንም ያጠናል፤ አንተም እንደሚጠጣ ገነት፥ ውኃውም እንደማያቋርጥ ምንጭ ትሆናለህ።”
         ኢሳይያስ 58፥11

👉ተሐድሶ እና ፍሬያማነት

“እግዚአብሔርም ሁልጊዜ ይመራሃል፤ ነፍስህንም በመልካም ነገር ያጠግባል አጥንትህንም ያጠናል፤ አንተም እንደሚጠጣ ገነት፥ ውኃውም እንደማያቋርጥ ምንጭ ትሆናለህ።”
          ኢሳይያስ 58፥11

እነዚህ ተስፋዎች ጾም ራስን መካድ ብቻ ሳይሆን መለወጥ እና መለኮታዊ ሞገስ መሆኑን ያጎላሉ።

ጾም በክርስቲያናዊ ሕይወት ውስጥ ያለው ሚና

በአዲስ ኪዳን ውስጥ፣ ጾም የእግዚአብሔርን ፈቃድ በመፈለግ፣ ስለሌሎች በመማለድ እና ለአገልግሎት በመዘጋጀት ወሳኝ ሚና መጫወቱን ቅዱሳት መጻሕፍት በስፋት ይገልጽልናል (ሐዋ. 13፥2-3፤ የሐዋርያት ሥራ 14፥23)። የጥንቷ ቤተ ክርስቲያን ጠቃሚ ውሳኔዎችን ከማድረጓ በፊት ትጾማለች፣ ትጸልይ ነበር፣ ይህም ጾም ከምግብ መከልከል ብቻ ሳይሆን ወደ እግዚአብሔር መቅረብና ለእግዚአብሔር ሥራ መሰማራትን እንደሆነ አሳይታለች።

ጳውሎስ ስለ ጾም አስተምሯል ዓላማው ራስን ለማጽደቅ ሳይሆን ለመንፈሳዊ ዲሲፒሊን ነው (1 ቆሮንቶስ 7፥ 5)። ጾም በጸሎት፣ በስግደት፣ በመታዘዝ ሲታጀብ ወደ ለውጥና መታደስ ይመራል።



ምንጭ፦
Piper, J. (1997). A Hunger for God: Desiring God Through Fasting and Prayer. Crossway.
Whitney, D. S. (1991). Spiritual Disciplines for the Christian Life. NavPress.



ወደ ቻናሉ ለመ🀄️🀄️ል፦ @Holy_scriptures
👍43🔥1
#እግዚአብሔር_የመረጠው_ጾም

"ትጾማለህ? የተራቡትን አብላ፣ የተጠሙትን አጠጣ፣ የታመመን ጠይቅ፣ የታሰሩትን አትርሳ፣ ለተሰቃዩት እራራላቸው፣ ያዘኑትንና የሚያለቅሱትን አጽናና፣ መሐሪ፣ ትሁት፣ ቸር፣ ረጋ ያልክ፣ ታጋሽ፣ አዛኝ፣ ይቅር ባይ ሁን። አምላክ ጾምህን ተቀብሎ የንስሐን ፍሬ አብዝቶ እንዲሰጥህ አክባሪ፣ እውነተኛ እና ትጉህ ሁን።"
ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ


                    

ወደ ቻናሉ ለመ🀄️🀄️ል፦ @Holy_scriptures
👍6🥰2
.    ==❀❀❀===❀❀❀==      
              የዕለቱ ጥቅስ 
     ==❀❀❀===❀❀❀==
“እርሱም የላከውን እናንተ አታምኑምና በእናንተ ዘንድ የሚኖር ቃሉ የላችሁም።”
ዮሐንስ 5፥38

               

ወደ ቻናሉ ለመ🀄️🀄️ል፦ @Holy_scriptures
👍61
ዓላማ መር ህይወት- ቀን 16_Purpose driven Life - Day 16_ alama mer hiywot…
PETERiCH (I am empty without Jesus)
#መጻሕፍትን_በድምጽ

👉ርዕስ፦ ዓላማ መር ሕይወት
✍️ጸሐፊ፦ ሪክ ዋረን
🗣ትርጉም፦ ኢቫንጀሊካል ቴዎሎጂካል ኮሌጅ
🗒ክፍል፦ 16 (ዋናው ነገር)


ይቀጥላል...


ወደ ቻናሉ ለመ🀄️🀄️ል፦ @Holy_scriptures
ወደ ቻናሉ ለመ🀄️🀄️ል፦ @Holy_scriptures
👍4
የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት ዘዴ.pdf
826 KB
👉ርዕስ፦ የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት ዘዴ

ከኢንተርናሽናል ኮርስፖንዳንስ ኢንስቲትዩት ጋር በመተባበር በዶሮቲ ጆንስ ተዘጋጅቶ በ"ሥነ መለኮት በቤቴ" አማካኝነት ከእንግሊዘኛ ወደ አማርኛ የተመለሰ የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት ዘዴ የመማርያ መጽሐፍ።


ወደ ቻናሉ ለመ🀄️🀄️ል፦ @Holy_scriptures
10
.    ==❀❀❀===❀❀❀==      
              የዕለቱ ጥቅስ 
     ==❀❀❀===❀❀❀==
“በይሁዳም ሁሉና በገሊላ በሰማርያም የነበሩት አብያተ ክርስቲያናት በሰላም ኖሩ ታነጹም፤ በእግዚአብሔርም ፍርሃትና በመንፈስ ቅዱስ መጽናናት እየሄዱ ይበዙ ነበር።”
ሐዋርያት 9፥31

      

ወደ ቻናሉ ለመ🀄️🀄️ል፦ @Holy_scriptures
👍42