ቅዱሳት መጻሕፍት
7.44K subscribers
1.35K photos
61 videos
331 files
795 links
በዚህ ቻናል

👉ቅዱሳት መጻሕፍት ይጠናሉ::
👉መጽሐፍ ቅዱሳዊ ትምህርቶች ይቀርባሉ::
👉 ለቅዱሳት መጽሐፍት ጥናት የሚያግዙ መጻሕፍት ይለቀቃሉ።

⭐️⭐️⭐️⭐️⭐️

@Holy_scriptures
Download Telegram
ዓላማ መር ህይወት- ቀን 5_Purpose driven Life - Day 5 _ alama mer hiywet…
PETERiCH (I am empty without Jesus)
#መጻሕፍትን_በድምጽ

👉ርዕስ፦ ዓላማ መር ሕይወት
✍️ጸሐፊ፦ ሪክ ዋረን
🗣ትርጉም፦ ኢቫንጀሊካል ቴዎሎጂካል ኮሌጅ
🗒ክፍል፦ 5 (ሕይወትን ከእግዚአብሔር ዕይታ አንጻር መልእክት)


ይቀጥላል...


ወደ ቻናሉ ለመ🀄️🀄️ል፦ @Holy_scriptures
👍43
የቀጠለ...

⏱️ቢዚ - ቢዚ፤ ለሁሉ ጊዜ አለው ወይስ አለን?



                    በጋሽ ንጉሤ ቡልቻ


ይረዳን እንደ ሆነ እስቲ መላ ልምታ፡፡ በጎ ትብብራችሁን ስጡኝና ይህን ጥያቄ በጥሞና መልሱልኝ “ለመሞት አንድ ወር ቀርቶሃል የምትሠራውን ሁሉ በነዚህ ሠላሳ ቀናት ጨርስ” ብትባሉ ቀኖቹንና ሌሊቶቹን ምን ታደርጉባቸው ነበር?
 
ብጣሽ ወረቀት አውጡና የምታደርጓቸውን ነገሮች በቅደም ተከተል ጻፉዋቸው፡፡ ልምምዱ ምናልባት ዋና የምትሉትን ዋና ካልሆኑት ለመለየት ይረዳችሁ ይሆናል፡፡
 
የሕይወታችሁ ዋና ዓላማ ምንድን ነው? የደም ግፊታችሁን እየጨመረ፣ ናላችሁን እያዞረ፣ ትንፋሽ አሳጥቶ የሚያስሮጣችሁን ነገር ሁሉ ከዚህ ዋና ዓላማ አንጻር ፈትሹት፡፡ ወደ ዓላማው የሚፈስ ነባር ወንዝ ነው ወይስ በየመስኩ የፈነዳ መድረሻው ያልታወቀ የውሃ ምንጭ? የክርስቶስ ተከታይ ዋና ዓላማ ምንድን ነው የተባለ እንደሆነ ሐዋርያው ጳውሎስ ባጭሩና በግልጽ ከተናገረው ከዚህ ጥቅስ የተሻለ መግለጫ አላገኘሁም፡፡ “አንዱ ስለ ሁሉ ሞተ፣ እንግዲያውስ ሁሉ ሞቱ በሕይወትም ያሉትም ስለ እነርሱ ለሞተውና ለተነሣው እንጂ ወደ ፊት ለራሳቸው እንዳይኖሩ ስለ ሁሉ ሞተ፡፡” 2ኛ ቆሮ 5፡13
 
የክርስቶስ ተከታይ ግለ ሰብም ሆነ ማኅበረ ሰብ የሕይወት ዓላማው ንድፍ ተሠርቶለት አልቋል፡፡ የምንሠራው ሁሉ የምናስበው ሁሉ የዚህ ዋና ንድፍ (Master Plan) አካል ካልሆነ ሕገ ወጥ ግንባታ ነው፤ ለፍቶ መና ነው፡፡ እያንዳንዱዋ የእንቅስቃሴ ቅንጣት መፈተሸ ዋጋዋም መተመን አለባት፡፡ መሮጥ ብቻውን ዋጋ ቢስ ነው፤ ሕይወት መሮጫ ግብ ይሻል፤ ግቡም በአንጻሩ የመገስገሻ መስመር አለው፡፡ ሐዋርያው ትንፋሽ ሊሰበስብ ሲቃረብ ሩጫ ጨረስኩ ሳይሆን ‹‹ሩጫውን ጨረስኩ›› ማለቱ የተሰመረ መንገድ፣ የሚደረስበት ግብ መኖሩን  ሲያመለክተን ነው፡፡
 
የቢዚነት ጉዳይ ግን ከዓላማ አንጻር ብቻ ሳይሆን በጊዜ አስተዳደር አንጻርም ሊታይ ይገባል፡፡ ጊዜ ከፈጣሪ የተሰጠን ሀብት ነው፡፡ ጊዜ ሀብት ከሆነ እንግዲያው እያንዳንዳችን “መጋቤ ጊዜያት” ሆነን በዚህ ሀብት ላይ ተሹመናል፡፡ የጊዜ መጋቢነት እንዴት ይከወን ስንል ባለ ሙያዎች ከሚመክሩን መካከል ሦስቱን ብቻ ልጥቀስ፡-
 
ጊዜዬ የት ጠፋ? ምን አደረግሁት? እያልክ የምትጠይቅ ከሆነ ሥራዬ ብለህ የዕለት ዕለት እንቅስቃሴህን ለተከታታይ ሰባት ቀናት ያደረግከውን ነገር ስም እየሰጠህ ልትጽፈው ትችላለህ፡፡ ከሳምንቱ በኋላ የጊዜ አጠቃቀምህን በዐይነቱ ስትሰድረው ጊዜህ ምን ላይ እንደዋለ የጊዜ ምጋቤ ባህርይህን ትረዳዋለህ፡፡ ያኔ ያላግባብ የባከነ ወይም በቂ ጊዜ ያልተሰጠው ምን እንደሆነ ግልጽ ይሆናል፡፡
 
ይህ የጊዜ ውሎ ግምጋሜ ወደ ሁለተኛው ዋና ነገር ይመራሃል ይህም ጊዜህን የሚሰርቁ የጊዜ መንታፊዎቸን ለይቶ ማወቅ ነው፡፡ ከታወቁት የጊዜ መንታፊዎች መካከል፡-

👉መወላወል (የቱን ላንሳ የቱን ልጣል)
👉ዝርክርክነት (ካርዱን የት ነበር ያደረግኩት)
👉መግቻ የሌላቸው የስልክ ጥሪዎች
👉ነገ ይደርሳል እያሉ መሳነፍ
👉ተራ/ወረፋ ጥበቃ
👉ጥድፊያ (ጥድፊያ ሲበዛ ፍጥነት ይቀንሳል ይባላል)
👉ድንገት የሚከሰቱ መስተጓጉሎች ይገኙበታል፡፡

እነዚህን የጊዜ ሌቦች እንዴት ነቅተህ እንደምትጠብቅ ከራስህ ጋር ተመካከር፡፡
 
ሦስተኛው ርምጃ ለሕይወትህ ዓላማ መሳካት የሚረዳ ከአንተ ባህርይና ሁናቴ ጋር የሚጣጣም የጊዜ ሰሌዳ መንደፍ ነው፡፡ የጊዜ መርሃ ግብር እንደሚያወጡት ቀላልነት ሳያዛንፉ መከተሉ ቀላል አይደለም፡፡ ላወጣኸው የጊዜ ሰሌዳ መገዛት ቢያቅትህ እንደገና መከለስና ማሻሻል ምንም ነውር የለበትም፡፡
 
ይህን ሁሉ ስታደርግ ልብ ማለት የሚገባህ ሕይወት ሥራ ብቻ÷ የግል ኑሮ ብቻ እንዳይደለ መገንዘብ ነው፡፡ የሥራና የዕረፍትን ሚዛን፣ የግልና የማኅበር ኑሮን ሚዛን፣ የዕለቱንና የዘላለሙን ሚዛን የሚጠብቅ የሕይወት ስልት መቀየስ ሁሉ ጎናዊ ስምረት እንዲኖረን ይረዳል፡፡
 
ወገኖቼ ጤናችን እስኪዛባ ደስታችን እስኪጠፋ ቢዚ ከሆንን እየቆየ ወደ ክስመት (burn out) ልንሄድ እንችላለን፡፡ በእምነት እጦት ሰበብ ሩጫ ያበዙትን ሕዝበ እስራኤል እግዚአብሔር እንደገሰጻቸውና እንደመከራቸው እኛንም ያስጠነቅቀናል፡፡
 
“የእስራኤል ቅዱስ ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላልና በመመለስና በማረፍ ትድናላችሁ፣ በፀጥታና በመታመን ኃይል ይሆንላችኋል፡፡”
(ኢሳ 30፡15)

ቁምላቸው ፈንታሁን ወደ አማርኛ ተርጉሞት በቃለ እግዚአብሔር አንባቢዎች ማኅበር በኩል ከታተመው መጽሐፍ ይህን አስተዋይ ጸሎት ልብ እንድንለው አብረንም እንድንጸልየው እጋብዛለሁ፡፡
 
ሰከን አርገኝ ጌታ!
ለአእምሮዬ ፀጥታ ለግሰህ፣ የልቤን ድውድውታ ቀንሰው፡፡
በጊዜ ውስጥ የዘላለምን አፅናፍ ራእይ ስጠኝና ጥድፊያዬ ልጓም ይበጅለት፡፡
በቀናት ዑደት ቱማታና ግርግር መካከል፣
የዘላለም ዓለም ኮረብቶች ግርማዊ አርምሞ በኔ ላይ ያርብብ፡፡
የሠራ አካላቴ ውጥረት በትውስታዬ በሚኖሩ
ዘማሪ ጅረቶች የሚያሳርፍ ሙዚቃ ይርገብ፡፡
የእንቅልፍን አስማታዊ አዳሽ ኃይል እንድገነዘብ እርዳኝ፡፡
ጥበብን አካፍለኝና የደቂቃ እርፍቶች በየመካከሉ እየወሰድኩ፡-
አበቦችን ልመልከት፣ ከወዳጅ ጋር ልጫወት፣
በጫካው መካከል ልመላለስ፣ ሸረሪት ድሯን ስትሸምን ልያት
ህፃኗን በፈገግታ ልቀበላት፣ እንባዎቿንም ላብስላት፡፡
ሩጫ ሁልጊዜ ለፈጣኖች እንዳይደለ፣
የኑሮ ሁለንተና ፍጥነት እየጨመሩ መኖጥ እንዳይደለ በየዕለቱ አስታውሰኝ፡፡
ቀና ብዬ ደመኖቹንና ሰማዩን
እንዲሁም ያዘመመን ዛፍ ልመልከታቸው፣
ዛፉ ዛሬ ይህን አክሎ ያደረገው፣ የበረታው በሕይወት ሰጪ ፀሐይህ ሙቀት
በዝግታ በማደጉ መሆኑን ልገንዘብ፡፡
ሰከን አርገኝ ጌታ ከአንተ ጋር ኅብረት በማድረግ በጥልቅ እኔነቴ የሚያሹኝን ሰላምና እረፍት ልጎናጸፍ፡፡


ምንጭ :- semayawithought.com




ወደ ቻናሉ ለመ🀄️🀄️ል፦ @Holy_scriptures
👍72🙏2💯1
በቅዱሳት መጻሕፍት ውስጥ ጌታችን እና መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ እራሱን በተደጋጋሚ "እኔ...ነኝ" እያለ የገለጸበት መጽሐፍ የቱ ነው?
Anonymous Quiz
11%
ሀ. ማቴዎስ
5%
ለ. ማርቆስ
4%
ሐ. ሉቃስ
80%
መ. ዮሐንስ
11
.    ==❀❀❀===❀❀❀==      
              የዕለቱ ጥቅስ 
     ==❀❀❀===❀❀❀==
“እናንተ ግን፥ ወንድሞች ሆይ፥ መልካም ሥራን ለመሥራት አትታክቱ።”
2ኛ ተሰሎንቄ 3፥13



ወደ ቻናሉ ለመ🀄️🀄️ል፦ @Holy_scriptures
👍111
ዓላማ መር ህይወት- ቀን 6_Purpose driven Life - Day 6_ alama mer hiywet…
PETERiCH (I am empty without Jesus)
#መጻሕፍትን_በድምጽ

👉ርዕስ፦ ዓላማ መር ሕይወት
✍️ጸሐፊ፦ ሪክ ዋረን
🗣ትርጉም፦ ኢቫንጀሊካል ቴዎሎጂካል ኮሌጅ
🗒ክፍል፦ 6 (ሕይወት ጊዜያዊ ሥራ ነው)


ይቀጥላል...


ወደ ቻናሉ ለመ🀄️🀄️ል፦ @Holy_scriptures
2👍2
#የእግዚአብሔር_ቃል_ምን_ይላል


ዘዳግም 34
¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯
⁹ ሙሴም እጆቹን ስለ ጫነበት የነዌ ልጅ ኢያሱ የጥበብን መንፈስ ተሞላ፤ የእስራኤልም ልጆች ታዘዙለት፥ እግዚአብሔርም ሙሴን እንዳዘዘው አደረጉ።
¹⁰ እግዚአብሔርን ፊት ለፊት እንዳወቀው እንደ ሙሴ ያለ ነቢይ ከዚያ ወዲህ በእስራኤል ዘንድ አልተነሣም፤
¹¹ በግብፅ ምድር በፈርዖንና በባሪያዎቹ ሁሉ ላይ በምድሪቱም ሁሉ ላይ ምልክትንና ድንቅን ያደርግ ዘንድ እግዚአብሔር እንደ ላከው ያለ፥
¹² በእስራኤል ሁሉ ፊት በጸናች እጅ ሁሉና በታላቅ ማስደንገጥ ሁሉ እንዳደረገው እንደ ሙሴ ያለ አልተነሣም።



ወደ ቻናሉ ለመ🀄️🀄️ል፦ @Holy_scriptures
🙏8👍21
.    ==❀❀❀===❀❀❀==      
              የዕለቱ ጥቅስ 
     ==❀❀❀===❀❀❀==
“ጌታን ኢየሱስ ክርስቶስን የማይወድ ቢኖር የተረገመ ይሁን። ጌታችን ሆይ፥ ና።”
1ኛ ቆሮንቶስ 16፥22



ወደ ቻናሉ ለመ🀄️🀄️ል፦ @Holy_scriptures
👍9👏2
ዓላማ መር ህይወት- ቀን 7_Purpose driven Life - Day 7 _ alama mer hiywet…
PETERiCH (I am empty without Jesus)
#መጻሕፍትን_በድምጽ

👉ርዕስ፦ ዓላማ መር ሕይወት
✍️ጸሐፊ፦ ሪክ ዋረን
🗣ትርጉም፦ ኢቫንጀሊካል ቴዎሎጂካል ኮሌጅ
🗒ክፍል፦ 7 (የሁሉም ነገር ምክንያት)


ይቀጥላል...


ወደ ቻናሉ ለመ🀄️🀄️ል፦ @Holy_scriptures
4👍2
ወደ ቻናሉ ለመ🀄️🀄️ል፦ @Holy_scriptures
👍1
ክርስቶስ የሚሠራት ቤተ ክርስቲያን.pdf
3.1 MB
👉ርዕስ፦ ክርስቶስ የሚሠራት ቤተ ክርስቲያን
✍️ጸሐፊ፦ ዶክተር ዓለሙ ቢፍቱ


ወደ ቻናሉ ለመ🀄️🀄️ል፦ @Holy_scriptures
👍61
በቅዱሳት መጻሕፍት ውስጥ “...እሳትን እሰድዳለሁ፥ ... አዳራሾች ትበላለች።” በሚለው ዓረፍተ ነገር የሚታወቀው መጽሐፍ የቱ ነው?
Anonymous Quiz
24%
ሀ. ኢሳይያስ
7%
ለ. ዮናስ
32%
ሐ. አሞጽ
7%
መ. ናሆም
19%
ሠ. ኤርምያስ
10%
ረ. ሕዝቅኤል
4👍2
.    ==❀❀❀===❀❀❀==      
              የዕለቱ ጥቅስ 
     ==❀❀❀===❀❀❀==
“አንተም ከሕዝቡ ሁሉ አዋቂዎችን፥ እግዚአብሔርን የሚፈሩትን፥ የታመኑ፥ የግፍንም ረብ የሚጠሉትን ሰዎች ምረጥ፤ ከእነርሱም የሺህ አለቆችን፥ የመቶ አለቆችን፥ የአምሳ አለቆችን፥ የአሥርም አለቆችን ሹምላቸው።”
ዘጸአት 18፥21



ወደ ቻናሉ ለመ🀄️🀄️ል፦ @Holy_scriptures
👍4🔥2
Audio
#መጻሕፍትን_በድምጽ

👉ርዕስ፦ ዓላማ መር ሕይወት
✍️ጸሐፊ፦ ሪክ ዋረን
🗣ትርጉም፦ ኢቫንጀሊካል ቴዎሎጂካል ኮሌጅ
🗒ክፍል፦ 8 (ለእግዚአብሔር ደስታ የታቀድህ ነህ)


ይቀጥላል...


ወደ ቻናሉ ለመ🀄️🀄️ል፦ @Holy_scriptures
👍21
ቅዱሳት መጻሕፍት
#እምነት ውድ የቻናላችን ቤተሰቦች ጌታ ቢፈቃድ በቅርብ ቀን ". . . ነገር ግን የሰው ልጅ በመጣ ጊዜ በምድር እምነትን ያገኝ ይሆንን?” ሉቃስ 18፥8 በሚል ርዕስ ተከታታይ ትምህርት እንጀምራል። በዚህም መሠረት ስለእምነት ሊነሱ ይገባል የምትሉትን አሳቦች በአሳብ መስጫው ላይ በነጻነት እንድታሰፍሩልን ስንል እንጠይቃለን። ጸልዩልን! ወደ ቻናሉ ለመ🀄️🀄️ል፦ @Holy_scriptures
#እምነት

እምነት


                   ክፍል-1


በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ያለው "እምነት" ትርጉም

በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ "እምነት" የሚለው ቃል በእግዚአብሔር መታመንን፣ ማመንን እና መደገፍን ያመለክታል። በእግዚአብሔር ተስፋዎች፣ ባህሪ እና ሃይል ላይ ጽኑ እምነትን የሚያስተላልፍ በብሉይም ሆነ በአዲስ ኪዳን ውስጥ ማዕከላዊ ጽንሰ-ሀሳብ ነው።

በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ "እምነት" ስንት ጊዜ ተጠቀሰ?

"እምነት" የሚለው ቃል በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ብዙ ጊዜ ተጠቅሷል፣ ነገር ግን ትክክለኛው ቁጥሩ እንደ መጽሐፍ ቅዱስ ትርጉሙ ይለያያል።

ለምሳሌ፦

👉KJV፦ 247 ጊዜ
👉NIV፦ 458 ጊዜ
👉ESV፦ 378 ጊዜ

በዕብራይስጥ (ብሉይ ኪዳን) የ"እምነት" ትርጉም

በዕብራይስጥ "እምነት"  የሚለው ቃል "ኢሙናህ (אֱמוּנָה)" ሲሆን ትርጉሙም በዋናነት ታማኝነት፣ ጽናት እና . . . ወ.ዘ.ተ ማለት እንጂ በአሁን ጊዜ "እምነት" ብለን እንደምንጠራው ብቻ አይደለም። የመተማመን እና አስተማማኝነት ሀሳብንም ያስተላልፋል።

“እነሆ፥ ነፍሱ ኰርታለች፥ በውስጡም ቅን አይደለችም፤ ጻድቅ ግን በእምነቱ (ኤሙና) በሕይወት ይኖራል።”
        ዕንባቆም 2፥4

በግሪክ (አዲስ ኪዳን) የ"እምነት" ትርጉም

እምነት ለሚለው የግሪክ ቃል "ፒስቲስ (πίστις)" ሲሆን ትርጉሙም በእግዚአብሔር እውነት እና ተስፋዎች ላይ መደገፍ፣ የሙጥኝ እና መጣበቅ ማለት ነው። በአዲስ ኪዳን አማኙ ከእግዚአብሔር እና ከኢየሱስ ክርስቶስ ጋር ያለውን ግንኙነት ለመግለጽ በሰፊው ጥቅም ላይ ውሏል።

“እምነትም (ጲስጢስ) ተስፋ ስለምናደርገው ነገር የሚያስረግጥ፥ የማናየውንም ነገር የሚያስረዳ ነው።”
         

ይቀጥላል...


ምንጭ፦ Harris, R. L., Archer, G. L., & Waltke, B. K. (1980). Theological Wordbook of the Old Testament (Vol. 1). Moody Press.

Balz, H. R., & Schneider, G. (1990). Exegetical Dictionary of the New Testament (Vol. 3). Eerdmans.




ወደ ቻናሉ ለመ🀄️🀄️ል፦ @Holy_scriptures
👍108🔥3
.    ==❀❀❀===❀❀❀==      
              የዕለቱ ጥቅስ 
     ==❀❀❀===❀❀❀==
“ጽድቅንና ፍርድን በማድረግ የእግዚአብሔርን መንገድ ይጠብቁ ዘንድ ልጆቹንና ከእርሱ በኋላ ቤቱን እንዲያዝዝ አውቃለሁና፤ ይህም እግዚአብሔር በአብርሃም ላይ የተናገረውን ነገር ሁሉ ያመጣ ዘንድ ነው።”
ዘፍጥረት 18፥19



ወደ ቻናሉ ለመ🀄️🀄️ል፦ @Holy_scriptures
Audio
#መጻሕፍትን_በድምጽ

👉ርዕስ፦ ዓላማ መር ሕይወት
✍️ጸሐፊ፦ ሪክ ዋረን
🗣ትርጉም፦ ኢቫንጀሊካል ቴዎሎጂካል ኮሌጅ
🗒ክፍል፦ 9 (እግዚአብሔርን ፈገግ የሚያሰኘው ነገር ምንድነው?)


ይቀጥላል...


ወደ ቻናሉ ለመ🀄️🀄️ል፦ @Holy_scriptures
👍51
የሕሊና ዓይነቶች 


በቅዱሳት መጻሕፍት በተለይም በአዲስ ኪዳን ይባስ ብሎም ደግሞ በሐዋርያው ቅዱስ ጳውሎስ ትምህርት "#ሕሊና" የሚለው አሳብ ተደጋግሞ ይነሳል። ለምሳሌ ሐዋርያው እንዲህ ይላል፦

“ስለዚህ እኔ ደግሞ በእግዚአብሔርና በሰው ፊት ሁልጊዜ ነውር የሌለባት ሕሊና ትኖረኝ ዘንድ እተጋለሁ።”
           ሐዋርያት 24፥16

ከታች ከተዘረዘሩት ለአንድ ክርስቲያን የሚያስፈልገውና የግሉ ሊያደርገው ሊጋደልበት የሚገባው የቱ ነው? ለምን?

1. ክፉ ሕሊና

ክፉ ሕሊና ተበላሽቶ ወደ ሥነ ምግባር ዝቅጠት የሚመራ ነው። ይህ ሕሊና የእግዚአብሔርን ፈቃድ የሚጻረር እና የኃጢያት ባህሪን የሚያበረታታ ነው። (ዕብ. 10፥22)

2. የረከሰ ሕሊና

የረከሰ ሕሊና በኃጢአት የረከሰና ግልጽ የሆነ የሞራል ልዩነት ማድረግ የማይችል ነው። ትክክል እና
ስህተት መካከል ወደ ግራ መጋባት ይመራል። (ቲቶ. 1፥15) 

3. የደነዘዘ ሕሊና

የደነዘዘ ሕሊና ማለት በድግግሞሽ ኃጢአት የተዳከመ ወይም የደነደነ ነው። ከጊዜ በኋላ
ሰውየው ለጥፋተኝነት ወይም ለጥፋተኝነት ግድየለሽ ይሆናል። ኃጢአትን እንደ ስህተት አይገነዘብም። (1ኛ ጢሞ. 
4፥2) 

4. ደካማ ሕሊና

ደካማ ሕሊና የሚያመለክተው ኃጢአት በሌለበት አካባቢም እንኳ በቀላሉ ሊኮነን የሚችል ያልበሰለ
ወይም ከልክ ያለፈ ስስ ሕሊና ነው። ይህ ሊሆን የሚችለው አንድ ሰው በተፈጥሮ ኃጢአተኛ ያልሆኑ የሥነ ምግባር ጉዳዮች ላይ እርግጠኛ ካልሆነ ነው። (1ኛ ቆሮ. 8፥7)

5. ንጹሕ ሕሊና

ንፁህ ህሊና ማለት ከጥፋተኝነት እና ከነቀፋ በጸዳ መልኩ በእግዚአብሔርና በሰው ፊት መኖር ፣ በታማኝነት እና በመታዘዝ መመላለስ ማለት ነው። (ሐዋ. 24፥16)

6. በጎ ሕሊና

በጎ ሕሊና ከእግዚአብሔር እውነት ጋር የሚስማማ እና ወደ ጽድቅ ሕይወት የሚመራ ነው። ግለሰቡ
ይቅርታን እንዲጠይቅ እና የሞራል ህይወት እንዲጠብቅ የሚገፋፋው ለኃጢያት እና የጥፋተኝነትን ድንበር በማወቅ ለእነዚህ ነገሮች ንቁ የሆነ ነው። (1 ጢሞ. 1፥19)




ወደ ቻናሉ ለመ🀄️🀄️ል፦ @Holy_scriptures
👍137
.    ==❀❀❀===❀❀❀==      
              የዕለቱ ጥቅስ 
     ==❀❀❀===❀❀❀==
“ቃልህ ተገኝቶአል እኔም በልቼዋለሁ አቤቱ፥ የሠራዊት አምላክ ሆይ፥ በስምህ ተጠርቻለሁና ቃልህ ሐሤትና የልብ ደስታ ሆነኝ።”
ኤርምያስ 15፥16



ወደ ቻናሉ ለመ🀄️🀄️ል፦ @Holy_scriptures
7
Audio
#መጻሕፍትን_በድምጽ

👉ርዕስ፦ ዓላማ መር ሕይወት
✍️ጸሐፊ፦ ሪክ ዋረን
🗣ትርጉም፦ ኢቫንጀሊካል ቴዎሎጂካል ኮሌጅ
🗒ክፍል፦ 10 (የአምልኮ ልብ)


ይቀጥላል...


ወደ ቻናሉ ለመ🀄️🀄️ል፦ @Holy_scriptures
👍71🥰1
#እምነት

እምነት


                   ክፍል-2

አሁን ስለእምነት ባነሳነው ትምህርት ሁለተኛ ክፍል ላይ እንገኛለን። በመጀመሪያው ክፍል ላይ "እምነት" የሚለው ቃል በብሉይ እና በአዲስ ኪዳን፣ በዕብራይስጥ እና በግሪክ ቋንቋ በአጠቃላይ የትኛውን አሳብ እንደሚሸከም አጠር ባለ መልኩ አይተናል። ከዚህ ክፍል ጀምሮ የጥናታችን መሪ ጥቅስ ከሆነው በመነሳት "እምነት" የሚለውን መጽሐፍ ቅዱሳዊ አሳብ በጥልቀት እንመለከተዋለን። እስቲ እንጀምር።

ሉቃስ ምዕራፍ 18 ሲጀምር ጌታችን እና መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ እንዴት መጸለይ እንደሚገባን በምሳሌ ሲያስረዳን እንዲህ ሲል ይጀምራል፦

“ሳይታክቱም ዘወትር ሊጸልዩ እንዲገባቸው የሚል ምሳሌን ነገራቸው፥”
ሉቃስ 18፥1

ምሳሌውን ሲጨርስ ደግሞ አንድ የሚያሳስበውን አሳብ በጥያቄ መልክ በማንሳት ያጠቃልላል እንዲህ ሲል፦

“. . . ነገር ግን የሰው ልጅ በመጣ ጊዜ በምድር እምነትን ያገኝ ይሆንን?”
ሉቃስ 18፥8

". . . ይሁንና፥ እኔ ተመልሼ በምመጣበት ጊዜ በእምነት ጸንተው የሚኖሩ ሰዎች አገኝ ይሆን?”
ሉቃስ 18፥8 (ሕያው ቃል)

እና የጌታችንን ጥያቄ ጆሮ ዳባ ልበስ ብለን ካለፍን አጉል የዋህነት እና ስንፍና ተጠናወተን ከማለት ውጪ ምን ይባላል?

የኢየሱስ ጥያቄ ምናልባት የመምጫው ጊዜ እየተቃረበ ሲመጣ፣ በቤተ ክርስቲያን ውስጥ ብዙዎች ከእውነተኛው እምነት ወደ ኋላ እስከሚሉ ድረስ ክፋት እያየለ እንደሚሄድ ያመለክታል (ማቴ 24፥11-13፣24፤ 1ጢሞ)፡፡ ምን ይሄ ብቻ ጌታችን እና መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ወደ መስቀል ሞት ከመሄዱ በፊት ሐዋርያት ከእርሱ እንደማይለዩ ሲምሉና ሲገዘቱ እርሱ ከዲያቢሎስ ጋር ግብግብ የገጠመበትንና ዲያቢሎስም ትኩረት ያደረገበትን አንድ ትልቅ የክርስቲያን ሀብት እንዲህ በማለት ገልጾታል፦

"ጌታም፦ ስምዖን ስምዖን ሆይ፥ እነሆ፥ ሰይጣን እንደ ስንዴ ሊያበጥራችሁ ለመነ፤ እኔ ግን እምነትህ እንዳይጠፋ ስለ አንተ አማለድሁ፤ አንተም በተመለስህ ጊዜ ወንድሞችህን አጽና አለ።"
ሉቃስ 22፥31-32

ኢየሱስ ተመልሶ ሲመጣ እየተሰደዱና እየተገደሉ ነገር ግን፥ ሳያሰልሱና ሳያቋርጡ የሚጸልዩ ሰዎችን ያገኝ ይሆን? በመጨረሻው ዘመን ማለትም ክርስቶስ ተመልሶ ከመምጣቱ በፊት፥ ስደትና መከራ በሰዎች ሁሉ ላይ ይመጣል። «በዚያን ጊዜ ብዙዎች ሃይማኖታቸውን በመካድ ይሰናከላሉ» (ማቴ. 24፥10)። ታዲያ ክርስቶስ ታማኝ ሆነው የሚቆዩ ሰዎችን ያገኝ ይሆን?

የጌታችንን ጥያቄ ልብ ብለን ልንጠይቅ ይገባል። አልፎ ተርፎም እያንዳንዱ አማኝ እራሱን የሚከተለውን ጥያቄ መጠየቅ አለበት እምነቴ ጽኑ ነውን፣ ፍትሕ እንዲሰፍንና የእርሱ ጽድቅ ሙሉ በሙሉ ለዘላለም እንዲያሸንፍ፣ በመጸለይና ወደ እግዚአብሔር በመጮኸ እየተጋሁ ነኝን? ወይስ ስለ ክርስቶስ መመለስና ስለ ዘላለማዊ መንግሥቱ ናፍቆትና ጕጕት እስከማይኖረኝ ድረስ ሐሳቤ በዚህ ዓለም የኑሮ ጕዳይ ተይዞአል?” (ራእ 19—22)። የዚህ ትምህርትም ዓላማ ራስን ለመመርመር እድል ለመስጠት ነው። ለዚህም እንዲያመቸን የእውነተኛ እምነት ምንነት፣ ባህሪያት፣ በእምነት እንዴት ማደግ እንደምንችል ወይንም ደግሞ እምነታችንን እንዴት ማሳደግ እንደምንችል. . . ወ.ዘ.ተ በአሁኑ ዘመን "እምነት" የሚባለው ነገር ከቅዱሳት መጻሕፍት አንጻር እንፈትሻለን። በእያንዳንዱ ትምህርት ላይም አስተያየት እና ጥያቄ ይበረታታል። ውይይት ማድረግም እንዲሁ የተፈቀደና የሚበረታታ ነው።


ይቀጥላል...


ምንጭ፦ ምሉእ ሕይወት፤ ገጽ 1575፣ የአዲስ ኪዳን ማብራሪያ፤ ገጽ 216




ወደ ቻናሉ ለመ🀄️🀄️ል፦ @Holy_scriptures
👍8👏1
.    ==❀❀❀===❀❀❀==      
              የዕለቱ ጥቅስ 
     ==❀❀❀===❀❀❀==
“የጌታውንም ፈቃድ አውቆ ያልተዘጋጀ እንደ ፈቃዱም ያላደረገ ያ ባሪያ እጅግ ይገረፋል፤”
ሉቃስ 12፥47



ወደ ቻናሉ ለመ🀄️🀄️ል፦ @Holy_scriptures
👍41