ቅዱሳት መጻሕፍት
7.44K subscribers
1.35K photos
61 videos
331 files
795 links
በዚህ ቻናል

👉ቅዱሳት መጻሕፍት ይጠናሉ::
👉መጽሐፍ ቅዱሳዊ ትምህርቶች ይቀርባሉ::
👉 ለቅዱሳት መጽሐፍት ጥናት የሚያግዙ መጻሕፍት ይለቀቃሉ።

⭐️⭐️⭐️⭐️⭐️

@Holy_scriptures
Download Telegram
.    ==❀❀❀===❀❀❀==      
              የዕለቱ ጥቅስ 
     ==❀❀❀===❀❀❀==
“የደመና ዓምድ በቀን፥ የእሳት ዓምድ በሌሊት ከሕዝቡ ፊት ከቶ ፈቀቅ አላለም።”
ዘጸአት 13፥22



ወደ ቻናሉ ለመ🀄️🀄️ል፦ @Holy_scriptures
🔥6
#እራሳችንን_እንመርምር


እኔምለው ግን እግዚአብሔር አንድ በአንድ ነገሮችን መቼም ቢሆን የትም የተሰሩትን፣ በማንም ይሁን በየትኛው ሁኔታ፣ መልካም ቢሆን ክፉ ለፍርድ እንደሚያመጣ በእርግጥ አስበን እናውቃለን? የእግዚአብሔር ዝምታ ፍርድ አልባ ነው ብለን እንድናስበው አድርጎን እንዳይሆን እፈራለሁ። የክፉ ምክር ሰምተን እና የዓለምን መለኪያ ተውሰን ፍርድ እያከማቸን ይሆን ወይስ እግዚአብሔርን በመፍራት ላይ እንገኛለን?

"የነገሩን ሁሉ ፍጻሜ እንስማ፤ ይህ የሰው ሁለንተናው ነውና፤ እግዚአብሔርን ፍራ፥ ትእዛዙንም ጠብቅ። እግዚአብሔር ሥራን ሁሉ የተሰወረውንም ነገር ሁሉ፥ መልካምም ቢሆን ክፉም ቢሆን፥ ወደ ፍርድ ያመጣዋልና።"
መክብብ 12፥13-14



ወደ ቻናሉ ለመ🀄️🀄️ል፦ @Holy_scriptures
👍82👏1
.    ==❀❀❀===❀❀❀==      
              የዕለቱ ጥቅስ 
     ==❀❀❀===❀❀❀==
“እኔም በልቤ፦ በዚያ ለነገር ሁሉና ለሥራ ሁሉ ጊዜ አለውና በጻድቅና በኃጢአተኛ ላይ እግዚአብሔር ይፈርዳል አልሁ።”
መክብብ 3፥17



ወደ ቻናሉ ለመ🀄️🀄️ል፦ @Holy_scriptures
8👍1
#የእግዚአብሔር_ቃል_ምን_ይላል?


2ኛ ነገሥት 8
¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯
⁷ ኤልሳዕም ወደ ደማስቆ መጣ፤ የሶርያም ንጉሥ ወልደ አዴር ታምሞ ነበር፤ ወሬኞችም፦ የእግዚአብሔር ሰው ወደዚህ መጥቶአል ብለው ነገሩት።
⁸ ንጉሡም አዛሄልን፦ ገጸ በረከት በእጅህ ወስደህ የእግዚአብሔርን ሰው ልትገናኝ ሂድ፤ በእርሱም አፍ፦ ከዚህ በሽታ እድናለሁን? ብለህ እግዚአብሔርን ጠይቅ አለው።
⁹ አዛሄልም ሊገናኘው ሄደ፥ ከእርሱም ጋር ከደማስቆ መልካሙን ነገር ሁሉ የአርባ ግመል ጭነት ገጸ በረከት ወሰደ፤ መጥቶም በፊቱ ቆመና፦ ልጅህ የሶርያ ንጉሥ ወልደ አዴር፦ ከዚህ በሽታ እድናለሁን? ሲል ወደ አንተ ልኮኛል አለ።
¹⁰ ኤልሳዕም፦ ሂድ፥ መዳንስ ትድናለህ በለው፤ ነገር ግን እንዲሞት እግዚአብሔር አሳይቶኛል አለው።
¹¹ እስኪያፍርም ድረስ ትኵር ብሎ ተመለከተው፤ የእግዚአብሔርም ሰው አነባ።
¹² አዛሄልም፦ ጌታዬ ለምን ያነባል? አለ። እርሱም፦ በእስራኤል ልጆች ላይ የምታደርገውን ክፋት ስለማውቅ ነው፤ ምሽጎቻቸውን በእሳት ታቃጥላለህ፥ ጕልማሶቻቸውንም በሰይፍ ትገድላለህ፥ ሕፃናቶቻቸውንም ትፈጠፍጣለህ፥ እርጉዞቻቸውንም ትቀድዳለህ አለው።
¹³ አዛሄልም፦ ይህን ታላቅ ነገር አደርግ ዘንድ እኔ ውሻ ባሪያህ ምንድር ነኝ? አለ። ኤልሳዕም፦ አንተ በሶርያ ላይ ንጉሥ እንድትሆን እግዚአብሔር አሳይቶኛል አለው።
¹⁴ ከኤልሳዕም ርቆ ወደ ጌታው መጣ፤ እርሱም፦ ኤልሳዕ ምን አለህ? አለው።
¹⁵ እርሱም፦ እንድትፈወስ ነገረኝ አለው። በነጋውም ለሐፍ ወስዶ በውኃ ነከረው በፊቱም ላይ ሸፈነው፥ ሞተም። አዛሄልም በፋንታው ነገሠ።




ወደ ቻናሉ ለመ🀄️🀄️ል፦ @Holy_scriptures
👍6
.    ==❀❀❀===❀❀❀==      
              የዕለቱ ጥቅስ 
     ==❀❀❀===❀❀❀==
“የእስራኤል ልጆች ማኅበር ሁሉ በሴሎ ተሰበሰቡ፥ በዚያም የመገናኛውን ድንኳን ተከሉ፤ ምድሩም ጸጥ ብሎ ተገዛላቸው።”
ኢያሱ 18፥1



ወደ ቻናሉ ለመ🀄️🀄️ል፦ @Holy_scriptures
👍112👎1
ቅዱሳት መጻሕፍት
#ጥምቀት                     ክፍል-፰ ፕሮቴስታንት ፕሮቴስታንት ስለ ጥምቀት ያለው አመለካከት በሰፊው ይለያያል፡- ሉተራኒዝም፦ ሉተራውያን ጥምቀት የጸጋ መቀበያ መንገድ እንደሆነ ያምናሉ እናም ለድነት አስፈላጊ ነው፣ ነገር ግን እምነትን የእግዚአብሔርን ጸጋ የመቀበያ ዋና መሳሪያ እንደሆነም ያምናሉ። ካልቪኒዝም፦ ጥምቀት እንደ እግዚአብሔር ቃል ኪዳን ምልክት እና ማኅተም ነው የሚታየው…
#ጥምቀት


                    ክፍል-፱
           (የመጨረሻ ክፍል)


በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ “ጥምቀት ያድናል” ሲባል ምን ማለት ነው?

“ጥምቀት ያድናል” የሚለው ሐረግ በዋነኝነት የተወሰደው ከ1ኛ ጴጥሮስ 3፡21 ሲሆን እሱም እንዲህ ይላል።

“ይህም ውኃ ደግሞ ማለት ጥምቀት ምሳሌው ሆኖ አሁን ያድነናል፥ የሰውነትን እድፍ ማስወገድ አይደለም፥ ለእግዚአብሔር የበጎ ሕሊና ልመና ነው እንጂ፥ ይህም በኢየሱስ ክርስቶስ ትንሣኤ ነው፤”
      1ኛ ጴጥሮስ 3፥21

ይህ ቁጥር የሚያመለክተው ጥምቀት አካላዊ ብቻ ሳይሆን ከደህንነት ጋር በተያያዘ መንፈሳዊ ጠቀሜታ እንዳለው ነው። ሆኖም፣ የተለያዩ ክርስቲያናዊ ወጎች ይህንን ጽንሰ ሐሳብ በተለያየ መንገድ ይተረጉማሉ።

የ"ጥምቀት ያድናል" የቤተክርስቲያን የተለያዩ ትርጓሜዎች

1. የሮማ ካቶሊክ ቤተ ክርስቲያን

የካቶሊክ ቤተ ክርስቲያን ጥምቀት ለመዳን አስፈላጊ እንደሆነ ታስተምራለች ምክንያቱም የመጀመሪያውን ኃጢአት አስወግዶ ሰውን ወደ ቤተክርስቲያን ስለሚያመጣ። ይህ እምነት በዮሐንስ 3፥5 ላይ የተመሰረተ ሲሆን ኢየሱስ “... እውነት እውነት እልሃለሁ፥ ሰው ከውኃና ከመንፈስ ካልተወለደ በቀር ወደ እግዚአብሔር መንግሥት ሊገባ አይችልም።”

2. የምስራቅ ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን

ከካቶሊክ እምነት ጋር በሚመሳሰል መልኩ የኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን ጥምቀትን ለድነት አስፈላጊ እንደሆነ አድርገው ይመለከታሉ። ይህም ሂደት ሰውን ወደ ክርስቶስ አካል ይጨምራል።

3. የሉተራን ቤተ ክርስቲያን

ሉተራውያን በጥምቀት እንደገና መወለድን ያምናሉ። ማለትም ጥምቀት የእግዚአብሔርን ጸጋ እና ይቅርታ ያስተላልፋል። የሐዋርያት ሥራ 2፥38ን በመጥቀስ ጴጥሮስ “...ንስሐ ግቡ፥ ኃጢአታችሁም ይሰረይ ዘንድ እያንዳንዳችሁ በኢየሱስ ክርስቶስ ስም ተጠመቁ፤ የመንፈስ ቅዱስንም ስጦታ ትቀበላላችሁ።” ሲል ተናግሯል። ነገር ግን፣ እምነት ለመዳን አስፈላጊ መሆኑንም አፅንዖት ይሰጣሉ።

4. የተሐድሶ እና የፕሪስባይቴሪያን አብያተ ክርስቲያናት

የተሐድሶ ወጎች ጥምቀትን እንደ እግዚአብሔር ቃል ኪዳን ምልክት እና ማኅተም ይመለከቱታል፣ ልክ እንደ ብሉይ ኪዳን መገረዝ። ጥምቀት እራሱ እንደሚያድን አያምኑም ይልቁንም አስቀድሞ በእምነት የተቀበለውን የድነት ውስጣዊ ጸጋ ያሳያል።

5. ባፕቲስት እና ወንጌላውያን አብያተ ክርስቲያናት

ባፕቲስት እና ብዙ ወንጌላውያን አብያተ ክርስቲያናት ጥምቀት እራሱ ያድናል የሚለውን ሃሳብ አይቀበሉም። መዳን በእምነት ብቻ እንደሆነ ያምናሉ (ኤፌሶን 2፥8-9) እና ጥምቀት የውስጣዊ እምነት ውጫዊ መግለጫ እንደሆነ ያምናሉ። የመታዘዝ ተግባር ነው ነገር ግን ለመዳን አስፈላጊ አይደለም (ሮሜ 10፥9)።



ምንጭ፦ Catechism of the Catholic Church. (1994). Libreria Editrice Vaticana.
Calvin, J. (1559). Institutes of the Christian religion.
Holy Bible, New International Version. (2011). Zondervan.
Luther, M. (1529). Luther’s Small Catechism.
Ware, T. (1993). The Orthodox Church. Penguin Books.



ወደ ቻናሉ ለመ🀄️🀄️ል፦ @Holy_scriptures
👍43
#እንወያይ

ጥምቀት በእናንተ አባል በሆናችሁበት አጥቢያ ወይንም ቤተ እምነት እንዴት ይታያል? እናንተስ እንዴት ታያላችሁ? የተለያዩ አብያተ ክርስቲያናት ዘንድ ያለው የጥምቀት አስተምህሮ ልዩነት ወደ አንድ ሊመጣ ይችላል ብላችሁ ታምናላችሁ? ወደ አንድ ለመምጣት የማይችል ከሆነ ለምን?


ወደ ቻናሉ ለመ🀄️🀄️ል፦ @Holy_scriptures
👏3👍21
.    ==❀❀❀===❀❀❀==      
              የዕለቱ ጥቅስ 
     ==❀❀❀===❀❀❀==
“በነጻነት ሕግ ፍርድን ይቀበሉ ዘንድ እንዳላቸው ሰዎች እንዲህ ተናገሩ፥ እንዲህም አድርጉ።”
ያዕቆብ 2፥12



ወደ ቻናሉ ለመ🀄️🀄️ል፦ @Holy_scriptures
👍7
ወደ ቻናሉ ለመ🀄️🀄️ል፦ @Holy_scriptures
🔥31👍1👏1
ዓላማ መር ህይወት- መግቢያ_ Purpose driven Life - Introduction _ alama mer…
PETERiCH (I am empty without Jesus)
#መጻሕፍትን_በድምጽ

👉ርዕስ፦ ዓላማ መር ሕይወት
✍️ጸሐፊ፦ ሪክ ዋረን
🗣ትርጉም፦ ኢቫንጀሊካል ቴዎሎጂካል ኮሌጅ
🚪 መግቢያ


ወደ ቻናሉ ለመ🀄️🀄️ል፦ @Holy_scriptures
👏5🔥2
ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በሕይወት ቅድሚያ ሊያገኙና ሊከተሉ ስለሚያስፈልጉ ነገሮች ምን አለ?


ጌታችን እና መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በዚህ ምድር ስንኖር "life priority order" ወይንም በሕይወት ቅድሚያ ስለሚያስፈልጉ እና ስለሚከተሉ ነገሮች በማቴዎስ 6፥25-34 አብራርቶልናል።

1. እግዚአብሔር ወይንም የእግዚአብሔር መንግሥት (ቁ. 33)
2. ነፍስ (ቁ. 25)
3. ምግብ (ቁ. 25)
4. ሰውነት (ቁ. 25)
5. ልብስ (ቁ. 25)

ከላይ በቅደም ተከተል የተጠቀሱት ቦታቸው የሚዛነፍ ከሆነ ሕይወት ሚዛኗን ስታ አማኝን ለጭንቀት ይዳርጉታል። ይባስ ካለ ደግሞ ዓለሙን አትርፎ ነፍሱን ወደ ማጉደል አዘቅት ይከተዋል።

“ስለዚህ እላችኋለሁ፥ ስለ ነፍሳችሁ በምትበሉትና በምትጠጡት፥ ወይም ስለ ሰውነታችሁ በምትለብሱት አትጨነቁ፤ ነፍስ ከመብል ሰውነትም ከልብስ አይበልጥምን?”
ማቴዎስ 6፥25


“ነገር ግን አስቀድማችሁ የእግዚአብሔርን መንግሥት ጽድቁንም ፈልጉ፥ ይህም ሁሉ ይጨመርላችኋል።”
ማቴዎስ 6፥33



ወደ ቻናሉ ለመ🀄️🀄️ል፦ @Holy_scriptures
🙏8👍61
.    ==❀❀❀===❀❀❀==      
              የዕለቱ ጥቅስ 
     ==❀❀❀===❀❀❀==
“ወደ ዘላለም ሕይወት የሚወስደውን የጌታችንን የኢየሱስ ክርስቶስን ምሕረት ስትጠባበቁ በእግዚአብሔር ፍቅር ራሳችሁን ጠብቁ።”
ይሁዳ 1፥21




ወደ ቻናሉ ለመ🀄️🀄️ል፦ @Holy_scriptures
🥰6👍41
ዓላማ መር ህይወት- ቀን 1_Purpose driven Life - Day 1 _ alama mer hiywet…
PETERiCH (I am empty without Jesus)
#መጻሕፍትን_በድምጽ

👉ርዕስ፦ ዓላማ መር ሕይወት
✍️ጸሐፊ፦ ሪክ ዋረን
🗣ትርጉም፦ ኢቫንጀሊካል ቴዎሎጂካል ኮሌጅ
🗒ክፍል፦ 1


ይቀጥላል...


ወደ ቻናሉ ለመ🀄️🀄️ል፦ @Holy_scriptures
👍81🔥1
#የሮሜ_መልእክት_ጥናት


ሮሜ 10
¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯
⁵ ሙሴ ከሕግ የሆነውን ጽድቅ የሚያደርገው ሰው በእርሱ በሕይወት እንዲኖር ጽፎአልና።
⁶ ከእምነት የሆነ ጽድቅ ግን እንዲህ ይላል፦ በልብህ፦ ማን ወደ ሰማይ ይወጣል? አትበል፤ ይህ ክርስቶስን ለማውረድ ነው፤
⁷ ወይም፦ በልብህ፦ ወደ ጥልቁ ማን ይወርዳል? አትበል፤ ይህ ክርስቶስን ከሙታን ለማውጣት ነው።
⁸ ነገር ግን ምን ይላል? በአፍህ በልብህም ሆኖ ቃሉ ቀርቦልሃል፤ ይህም የምንሰብከው የእምነት ቃል ነው።
⁹ ኢየሱስ ጌታ እንደ ሆነ በአፍህ ብትመሰክር እግዚአብሔርም ከሙታን እንዳስነሣው በልብህ ብታምን ትድናለህና፤
¹⁰ ሰው በልቡ አምኖ ይጸድቃልና በአፉም መስክሮ ይድናልና።
¹¹ መጽሐፍ፦ በእርሱ የሚያምን ሁሉ አያፍርም ይላልና።
¹² በአይሁዳዊና በግሪክ ሰው መካከል ልዩነት የለምና፤ አንዱ ጌታ የሁሉ ጌታ ነውና፥ ለሚጠሩትም ሁሉ ባለ ጠጋ ነው፤
¹³ የጌታን ስም የሚጠራ ሁሉ ይድናልና።


ሮሜ 10 (አዲሱ መ.ት)
¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯
⁵ ሙሴ በሕግ በኩል የሆነውን ጽድቅ ሲገልጽ፣ “እነዚህን የሚፈጽም ሰው በእነርሱ ይኖራል” ይላል።
⁶ ከእምነት የሆነው ጽድቅ ግን እንዲህ ይላል፤ “ ‘በልብህ ማን ወደ ሰማይ ይወጣል?’ አትበል”፤ ይህ ክርስቶስን ለማውረድ ነው፤
⁷ “ወይም ‘ወደ ጥልቁስ ማን ይወርዳል?’ አትበል”፤ ይህም ክርስቶስን ከሙታን ለማውጣት ነው።
⁸ ነገር ግን ምን ይላል? “ቃሉ በአጠገብህ ነው፤ በአፍህና በልብህም ውስጥ ነው፤” የምንሰብከውም የእምነት ቃል ይህ ነው፤
⁹ “ኢየሱስ ጌታ ነው” ብለህ በአፍህ ብትመሰክር፣ እግዚአብሔርም ከሙታን እንዳስነሣው በልብህ ብታምን፣ ትድናለህ።
¹⁰ የምትጸድቀው በልብህ አምነህ ነው፤ የምትድነውም በአፍህ መስክረህ ነውና።
¹¹ መጽሐፍ እንደሚለው፣ “በእርሱ የሚያምን ሁሉ አያፍርም።”
¹² በአይሁድና በአሕዛብ መካከል ልዩነት የለም፤ አንዱ ጌታ የሁሉ ጌታ ነውና፤ የሚለምኑትንም አብዝቶ ይባርካል፤
¹³ “የጌታን ስም የሚጠራ ሁሉ ይድናልና።”


ሮሜ 10 (ሕያው ቃል)
¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯
⁵ ሕግን በመጠበቅ ስለ መጽደቅ ሙሴ፥ «አንድ ሰው ሕግ የሚያዘውን ሁሉ መጠበቅ ከቻለ ፥ ሕግ ራሱ ሕይወት ይሰጠዋል» ሲል ጽፎአል።
⁶ በእምነት የሚገኘው ጽድቅ ግን፥ «ክርስቶስን ወደ ምድር ለማውረድ ወደ ሰማይ መውጣት አያስፈልግህም።
⁷ ወይም ወደ ሲኦል ወርደህ ክርስቶስን ከሙታን መካከል ማስነሣት የለብህም» ይላል።
⁸ ነገር ግን መጽደቅ ስለሚቻልበት መንገድ እንዲህ ይላል። «የእግዚአብሔር ቃል በአጠገብህ ይገኛል ፤ በአፍህና በልብህም ውስጥ ነው።» ይህም የእግዚአብሔር ቃል እኛ የምናስተምራችሁ የእምነት ቃል ነው።
⁹ ኢየሱስ ጌታ እንደሆነ በአፋችሁ ብትመሰክሩ፥ እግዚአብሔርም ከሞት እንዳስነሣው በልባችሁ ብታምኑ ትድናላችሁ።
¹⁰ ምክንያቱም ሰው በልቡ አምኖ ይጸድቃል። ስለ እምነቱም በመመስከሩ ይድናል።
¹¹ ይህ እውነት መሆኑን ለማረጋገጥ እንዲህ የሚል ቃል በመጽሐፍ ተጽፎ ይገኛል ፤ «በእርሱ የሚያምን ሁሉ አያፍርም።»
¹² ይህ ቃል የተጻፈው በአይሁድና በአሕዛብ መካከል ምንም ልዩነት ሳይደረግ ለሁሉ ነው። የሁሉም ጌታ የሆነው ኢየሱስ፥ ለሚለምኑት ሁሉ በረከቱን የሚሰጥ ባለጸጋ አምላክ ነው።
¹³ በቅዱሳት መጻሕፍት ፥ «የጌታን ስም የሚጠራ ሁሉ ይድናል» ተብሏል።



ወደ ቻናሉ ለመ🀄️🀄️ል፦ @Holy_scriptures
👍32
በቅዱሳት መጻሕፍት ከብሉይ ኪዳን ነቢያት መካከል “... ጻድቅ ግን በእምነቱ በሕይወት ይኖራል።” በሚለው የሚታወቀው ነቢይ የቱ ነው?
Anonymous Quiz
19%
ሀ. ኢሳይያስ
12%
ለ. ኤርምያስ
9%
ሐ. ሕዝቅኤል
54%
መ. ዕንባቆም
6%
ሠ. ኤልያስ
👍7
.    ==❀❀❀===❀❀❀==      
              የዕለቱ ጥቅስ 
     ==❀❀❀===❀❀❀==
“መድኃኒታችንም ከዓመፅ ሁሉ እንዲቤዠን፥ መልካሙንም ለማድረግ የሚቀናውን ገንዘቡም የሚሆነውን ሕዝብ ለራሱ እንዲያነጻ፥ ስለ እኛ ነፍሱን ሰጥቶአል።”
ቲቶ 2፥14



ወደ ቻናሉ ለመ🀄️🀄️ል፦ @Holy_scriptures
7👍1😁1
ዓላማ መር ህይወት- ቀን 2_Purpose driven Life - Day 2 _ alama mer hiywet…
PETERiCH (I am empty without Jesus)
#መጻሕፍትን_በድምጽ

👉ርዕስ፦ ዓላማ መር ሕይወት
✍️ጸሐፊ፦ ሪክ ዋረን
🗣ትርጉም፦ ኢቫንጀሊካል ቴዎሎጂካል ኮሌጅ
🗒ክፍል፦ 2 (አጋጣሚ አይደለህም)


ይቀጥላል...


ወደ ቻናሉ ለመ🀄️🀄️ል፦ @Holy_scriptures
3👍2
ወደ ቻናሉ ለመ🀄️🀄️ል፦ @Holy_scriptures
👍1
ዓላማ መር ሕይወት.pdf
11.2 MB
👉ርዕስ፦ ዓላማ መር ሕይወት
ጸሐፊ፦ ሪክ ዋረን
🗣ትርጉም፦ ኢቫንጄሊካል ቲዎሎጂካል ኮሌጅ


ወደ ቻናሉ ለመ🀄️🀄️ል፦ @Holy_scriptures
3
ከቅዱሳት መጻሕፍት መካከል በአዲስ ኪዳን የሐዋርያው ቅዱስ ጳውሎስን በጣም ስሜታዊ እና ግላዊ ጹሑፍ የያዘው መጽሐፍ የትኛው ነው?
Anonymous Quiz
35%
ሀ. 2ኛ ጢሞቴዎስ
25%
ለ. ገላትያ
30%
ሐ. 2ኛ ቆሮንቶስ
11%
መ. ሮሜ
4👍4
.    ==❀❀❀===❀❀❀==      
              የዕለቱ ጥቅስ 
     ==❀❀❀===❀❀❀==
“የመንፈስ ፍሬ ግን ፍቅር፥ ደስታ፥ ሰላም፥ ትዕግሥት፥ ቸርነት፥ በጎነት፥ እምነት፥ የውሃት፥ ራስን መግዛት ነው።”
ገላትያ 5፥22



ወደ ቻናሉ ለመ🀄️🀄️ል፦ @Holy_scriptures
👍14