ቅዱሳት መጻሕፍት
7.45K subscribers
1.35K photos
61 videos
332 files
795 links
በዚህ ቻናል

👉ቅዱሳት መጻሕፍት ይጠናሉ::
👉መጽሐፍ ቅዱሳዊ ትምህርቶች ይቀርባሉ::
👉 ለቅዱሳት መጽሐፍት ጥናት የሚያግዙ መጻሕፍት ይለቀቃሉ።

⭐️⭐️⭐️⭐️⭐️

@Holy_scriptures
Download Telegram
ወደ ቻናሉ ለመ🀄️🀄️ል፦ @Holy_scriptures
👍1
የውኃ ጥምቀት.pdf
664.8 KB
👉ርዕስ፦ የውኃ ጥምቀት
ጸሐፊ፦ ቲም ፌሎስ
🗣ትርጉም፦ ግርማዊ
📝እርማት፦ ይግረም ረታ



ወደ ቻናሉ ለመ🀄️🀄️ል፦ @Holy_scriptures
👍42
ምስጢረ ጥምቀት.pdf
620.9 KB
👉ርዕስ፦ ምስጢረ ጥምቀት
የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን አስተምህሮ



ወደ ቻናሉ ለመ🀄️🀄️ል፦ @Holy_scriptures
👍3
.    ==❀❀❀===❀❀❀==      
              የዕለቱ ጥቅስ 
     ==❀❀❀===❀❀❀==
“እንዲሁ ዳግመኛ ለኢየሩሳሌምና ለይሁዳ ቤት በዚህ ወራት በጎነትን አደርግ ዘንድ አስቤአለሁ አትፍሩ።”
ዘካርያስ 8፥15



ወደ ቻናሉ ለመ🀄️🀄️ል፦ @Holy_scriptures
👍31
Audio
#መጻሕፍትን_በድምጽ

👉ርዕስ፦ እፎይታ
✍️ጸሐፊ፦ ወ/ዊ ያሬድ ጥላሁን
🔊ክፍል፦ 13


ይቀጥላል...


ወደ ቻናሉ ለመ🀄️🀄️ል፦ @Holy_scriptures
👍4
#ሄኖን


#ከተማ_ወይም_ቦታ_በቅዱሳት_መጻሕፍት


ሄኖን፤ ምንጮች ማለት ነው። ከዮርዳኖስ በስተ ምዕራብ ከስካይቶፖሊስ (ቤተ ሳን) በስተ ደቡብ በኩል ዐሥራ ሦስት ኪሎ ሜትር ያህል ርቀት ላይ የሚገኝ ስፍራ ሳይሆን አይቀርም፡፡ ወንዝ አቅራቢያ ከቤትሳን ወደ ደቡብ ያለ ቦታ።  መጥምቁ ዮሐንስ ብዙ ገሊላውያንን በዚህ ቦታ አጥምቋል፤ ዮሐ. 3፥23።



ምንጭ፦ የመጽሐፍ ቅዱስ መዝገበ ቃላት፤ ገጽ 13፣ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ከማጥኛ ጽሑፍ ጋር፤ ገጽ 1593



ወደ ቻናሉ ለመ🀄️🀄️ል፦ @Holy_scriptures
👍6👎1
.    ==❀❀❀===❀❀❀==      
              የዕለቱ ጥቅስ 
     ==❀❀❀===❀❀❀==
“እርሱም የላከውን እናንተ አታምኑምና በእናንተ ዘንድ የሚኖር ቃሉ የላችሁም።”
ዮሐንስ 5፥38



ወደ ቻናሉ ለመ🀄️🀄️ል፦ @Holy_scriptures
👍3
እፎይ-ታ ቀዳማይ | ክፍል 14 | ራስን መተዋወቅ
Evangelist Yared Tilahun
#መጻሕፍትን_በድምጽ

👉ርዕስ፦ እፎይታ
✍️ጸሐፊ፦ ወ/ዊ ያሬድ ጥላሁን
🔊ክፍል፦ 14


ይቀጥላል...


ወደ ቻናሉ ለመ🀄️🀄️ል፦ @Holy_scriptures
1👍1
ቅዱሳት መጻሕፍት
#ጥምቀት               ክፍል-፪ የጥምቀት ዓይነቶች 1.የአካል ጥምቀት "…እኛ ሁላችን በአንድ መንፈስ አንድ አካል እንድንሆን ተጠምቀናልና…" (1ኛ ቆሮ.1፥13)፡፡ አጥማቂ መንፈስ ቅዱስ ሲሆን መጠመቂያው የክርስቶስ አካል ነው፡፡ "…ከክርስቶስ ኢየሱስ ጋር አንድ እንሆን ዘንድ የተጠመቅን ሁላችን …" (ሮሜ.6፥2) ሲል ይህንን ጥምቀት ያመለክታል፡፡ ለመዳን ብቸኛው አስፈላጊ ጥመምቀት…
#ጥምቀት


                                     ክፍል-፫


ጥምቀት በማን ስም?


ሰዎች ኢየሱስን ለመቀበል እንዲዘጋጁ መጥምቁ ዮሐንስ የንስሐ ጥምቀትን ይሰብክ ነበር። ኢየሱስ አማኞችን በመንፈስ ቅዱስና በእሳት አጥምቋል (ማቴ. 3፥11፤ ማር. 1፥8)። በአዲስ ኪዳን ጥምቀት በአብ፥ በወልድና በመንፈስ ቅዱስ ስም፤ በውኃ መርጨት፥ ማፍሰስና ማጥለቅ የሚደረግ ነው። በሐ.ሥ. «በኢየሱስ ክርስቶስ ስም ተጠመቁ» የሚለው፥ ሉቃስ የጴጥሮስን ትእዛዝ በሙሉ ሳይሆን በአጭሩ የጻፈው መሆኑን ያመለክታል። ሐዋርያት፥ አማኙ ከሥላሴ አካላት ጋር ግንኙነት እንዳለው ስለሚያውቁ የክርስቶስን ትእዛዝ አሟልተው የፈጸሙ መሆናቸውንም መረዳት አያስቸግርም፤ ሐ.ሥ. 2፥38። ሰው በኢየሱስ ከርስቶስ ስም ሲያምንም ኢየሱስ ክርስቶስ ፍጹም አምላክና ፍጹም ሰው ሆኖ የአብ አንድያ ልጅ፥ እንደዚሁም መንፈስ ቅዱስን ሰጭ መሆኑን ያምናል። ይህም በጴጥሮስ ስብከት ግልጥ ሆኗል፤ ሐ.ሥ. 2፥33:36። ይህን እውነት የማይቀበል መንፈስ ቅዱስን መሳደብ እንዳይሆንበት መጠንቀቅ አለበት፤ ማቴ. 12፥31:32። እንግዲህ «በክርስቶስ ስም መጠመቅ» ሥላሴን (ሦስቱን አካላት) እና ግብራቸውን ያጠቃልላል።

የመንፈስ ቅዱስ ጥምቀት

የመንፈስ ቅዱስ ጥምቀት በበዓለ ኀምሳ ዕለት በቤተክርስቲያን ተደረገ (ሐ.ሥ. 1፥5፤ 2፥1-4)፥ ከዚያ ጊዜ ጀምሮ ምእመናን ሁሉ በክርስቶስ ሥራ ከክርስቶስ አካል (ቤተክርስቲያን) ጋር አንድ በመሆን በቤተክርስቲያን ላይ የወረደውን መንፈስ ቅዱስ አብረው ይካፈላሉ፤ 1ቆሮ. 12፥13፤ ቲቶ 3፥3-5። ክርስቶስ ሲጠመቅ የውሃና የመንፈስ ጥምቀት የተያያዘ ነበር፥ ይህም ለእኛ ምሳሌ ነው፤ ሉቃ. 3፥21:22፤ ሐ.ሥ. 2፥38፤ ቲቶ 3፥5። የመንፈስ ቅዱስ ጥምቀት የውሃን ጥምቀት ሊከተል ወይም ሊቀድም ይችላል፤ ሐ.ሥ.8፥4-17፤ 10፥44-48።
ጥምቀት ከክርስቶስ ጋር አንድ ያደርገናልና በዚህ መሠረት ከኃጢአት እንደተለየን ቁጥረን በአዲስ ሕይወት እንኖራለን፤ ሮም 6፥1-11።

ጥምቀት በሊቃውንቶች ዘንድ

በቤተክርስቲያን ሊቃውንት የማይስማሙባቸው ነገሮች አሉ። ከእነዚህም ጥቂቶችን በአጭሩ እንገልጣለን።

1. አንዳንዶች ጥምቀት የሚለው ቃል በውሃ ውስጥ ማጥለቅን ያሳያል ሲሉ፥ ሌሎች ደግሞ «ማፍሰስ» የሚለው ቃል የጥምቀትን ምሥጢር ያመለክታል ይላሉ፤ ሐሥ.2፥33።

2. አንዳንዶች ማር. 16፥16 ና ሌላም ክፍልን ጠቅሰው ሰው ሳያምን ሊጠመቅ አይገባም ይላሉ። እንደዚሁም ሌሎች በብሉይ ኪዳን ዘመን ሕፃናት ተገረዙ፤ ስለዚህ ልጆች እንደ እግዚአብሔር ሕዝብ ተቈጥረው እግዚአብሔር የቃል ኪዳን አባሎች አድርጓቸዋልና (ዘፍ. 17፥7፤ ሮሜ 4፥11፤ ገላ. 3፥29፤ ቆላ. 2፥11-12፤ 1ቆሮ. 7፥14) ሊጠመቁ ይገባቸዋል ይላሉ፤ ሐ.ሥ.2÷39፤ 16፥15:33።

3. በዚያም ሆነ በዚህ ጥምቀት አስፈላጊ ነው፤ በረከቱ በክርስቶስ ከመንፈስ ቅዱስ ነውና። ተጠማቂው በረከትን የሚያገኘው ፦
(ሀ) በተለይ በሥርዓቱ፥
(ለ) በተለይ በእምነቱ፥
(ሐ) ጥምቀት
በተለይ የቃል ኪዳን ተስፋ ስለታተመበት ነው በማለት ሊቃውንት በአሳብ ይለያያሉ።


ይቀጥላል...


ምንጭ፦  የመጽሐፍ ቅዱስ መዝገበ ቃላት፤ ገጽ 256፣ የአዲስ ኪዳን ማብራሪያ፤ ገጽ 3




ወደ ቻናሉ ለመ🀄️🀄️ል፦ @Holy_scriptures
3👍2
የመጥምቁ ዮሐንስን አንገት ያስቀላው ገዢ ማን ነበር?
Anonymous Quiz
52%
ሀ. ታላቁ ሄሮድስ
32%
ለ. ሄሮድስ አንቲጳስ
10%
ሐ. ሄሮድስ ፊልጶስ
5%
መ. ጲላጦስ
3
.    ==❀❀❀===❀❀❀==      
              የዕለቱ ጥቅስ 
     ==❀❀❀===❀❀❀==
“አሁን ግን ከኃጢአት አርነት ወጥታችሁ ለእግዚአብሔርም ተገዝታችሁ፥ ልትቀደሱ ፍሬ አላችሁ፤ መጨረሻውም የዘላለም ሕይወት ነው።”
ሮሜ 6፥22



ወደ ቻናሉ ለመ🀄️🀄️ል፦ @Holy_scriptures
👍7
እፎይ-ታ ቀዳማይ | ክፍል 15 | ግደል እና ስቀለው
Evangelist Yared Tilahun
#መጻሕፍትን_በድምጽ

👉ርዕስ፦ እፎይታ
✍️ጸሐፊ፦ ወ/ዊ ያሬድ ጥላሁን
🔊ክፍል፦ 15


ይቀጥላል...


ወደ ቻናሉ ለመ🀄️🀄️ል፦ @Holy_scriptures
👍1
ወደ ቻናሉ ለመ🀄️🀄️ል፦ @Holy_scriptures
እፎይ-ታ.pdf
1.4 MB
👉ርዕስ:- እፎይታ
✍️ጸሐፊ:- ወ/ዊ ያሬድ ጥላሁን


ወደ ቻናሉ ለመ🀄️🀄️ል፦ @Holy_scriptures
👏3👍2
.    ==❀❀❀===❀❀❀==      
              የዕለቱ ጥቅስ 
     ==❀❀❀===❀❀❀==
“በክርስቶስም ከእናንተ ጋር የሚያጸናንና የቀባን እግዚአብሔር ነው፥”
2ኛ ቆሮ 1፥21



ወደ ቻናሉ ለመ🀄️🀄️ል፦ @Holy_scriptures
5👍1
Audio
#መጻሕፍትን_በድምጽ

👉ርዕስ፦ እፎይታ
✍️ጸሐፊ፦ ወ/ዊ ያሬድ ጥላሁን
🔊ክፍል፦ 16


ይቀጥላል...


ወደ ቻናሉ ለመ🀄️🀄️ል፦ @Holy_scriptures
👍1
የእግዚአብሔር ጸጋ ሲጣል ወይም ሲጎድል ምን ይከሰታል?

1. መራራ ስር መብቀል
2. ሌሎችን መበከል እና ማስጨነቅ
3. ጊዜያዊ ነገር ላይ ከልክ በላይ ትኩረት ማድረግ እና ዘላለማዊውን ማየት አለመቻል
4. ለዚህ ዓለም የሚመች ሰው መሆን
5. በኑሮ እግዚአብሔርን ማክበር አለመቻልን ያስከትላል። እግዚአብሔር ከዚህ ውድቀት እና ጉድለት ይጠብቀን!


"የእግዚአብሔር ጸጋ ለማንም እንዳይጎድለው፥ ብዙዎቹም የሚረክሱበት አንድ መራራ ሥር ወደ ላይ በቅሎ እንዳያስጨንቅ፥ ሴሰኛም የሚሆን እንዳይገኝ፥ ወይም ስለ አንድ መብል በኵርነቱን እንደ ሸጠ እንደ ዔሳው ለዚህ ዓለም የሚመች ሰው እንዳይሆን ተጠንቀቁ።"
ዕብራውያን 12፥15-16


"ከእናንተ ማንም የእግዚአብሔር ጸጋ እንዳይጐድልበት ደግሞም መራራ ሥር በቅሎ ችግር እንዳያስከትልና ብዙዎችን እንዳይበክል ተጠንቀቁ። ለአንድ ጊዜ መብል ሲል ብኵርናውን እንደ ሸጠው እንደ ዔሳው ማንም ሴሰኛ ወይም እግዚአብሔርን የማያከብር ሆኖ እንዳይገኝ ተጠንቀቁ።"
ዕብራውያን 12፥15-16 (አዲሱ መ.ት)




ወደ ቻናሉ ለመ🀄️🀄️ል፦ @Holy_scriptures
20👍1
.    ==❀❀❀===❀❀❀==      
              የዕለቱ ጥቅስ 
     ==❀❀❀===❀❀❀==
“ዳሩ ግን ሁሉን አንድ ጊዜ ፈጽሞ ምንም የተማራችሁ ብትሆኑ ጌታ ከግብፅ አገር ሕዝቡን አድኖ የማያምኑትን በኋላ እንዳጠፋቸው ላሳስባችሁ እወዳለሁ።”
ይሁዳ 1፥5



ወደ ቻናሉ ለመ🀄️🀄️ል፦ @Holy_scriptures
5
እፎይ-ታ ቀዳማይ | ክፍል 17 | አገላብጠው
Evangelist Yared Tilahun
#መጻሕፍትን_በድምጽ

👉ርዕስ፦ እፎይታ
✍️ጸሐፊ፦ ወ/ዊ ያሬድ ጥላሁን
🔊ክፍል፦ 17


ይቀጥላል...


ወደ ቻናሉ ለመ🀄️🀄️ል፦ @Holy_scriptures
1
#ጥምቀት


ክፍል-፬


በቅዱሳት መጻሕፍት መሠረት ማን ይጠመቅ?



1. ንስሐ ገብተው ኢየሱስ ክርስቶስን እንደ ጌታቸው አድርገው የተቀበሉ አማኞች

መጽሐፍ ቅዱስ ጥምቀት ኢየሱስ ክርስቶስን አውቀው አምነው ከኃጢአታቸው ንስሐ ለሚገቡ ሰዎች እንደሆነ አበክሮ ይናገራል።

“ጴጥሮስም፦ ንስሐ ግቡ፥ ኃጢአታችሁም ይሰረይ ዘንድ እያንዳንዳችሁ በኢየሱስ ክርስቶስ ስም ተጠመቁ፤ የመንፈስ ቅዱስንም ስጦታ ትቀበላላችሁ።”
ሐዋርያት 2፥38

“ያመነ የተጠመቀም ይድናል፥ ያላመነ ግን ይፈረድበታል።”
ማርቆስ 16፥16

2. ኢየሱስ ክርስቶስን በማመን የሚናዘዙ አዋቂዎች

በእምነት በግል የሚናዘዙ አዋቂዎች ለጥምቀት ብቁ ናቸው።

“ነገር ግን ስለ እግዚአብሔር መንግሥትና ስለ ኢየሱስ ክርስቶስ ስም እየሰበከላቸው ፊልጶስን ባመኑት ጊዜ፥ ወንዶችም ሴቶችም ተጠመቁ።”
ሐዋርያት 8፥12

3. መላው ቤተሰብ

በአዲስ ኪዳን ውስጥ፣ መላው ቤተሰብ የተጠመቁበት ምሳሌዎች አሉ፣ ይህም አንዳንዶች ልጆችን ይጨምራል ብለው ይተረጉማሉ።

“እርስዋም ከቤተ ሰዎችዋ ጋር ከተጠመቀች በኋላ፦ በጌታ የማምን እንድሆን ከፈረዳችሁልኝ፥ ወደ ቤቴ ገብታችሁ ኑሩ ብላ ለመነችን፤ በግድም አለችን።”
ሐዋርያት 16፥15

“የእስጢፋኖስንም ቤተ ሰዎች ደግሞ አጥምቄአለሁ፤ ጨምሬ ሌላ አጥምቄ እንደ ሆነ አላውቅም።”
1ኛ ቆሮንቶስ 1፥16

4. ልጆች በኪዳን ማህበረሰቦች (ግርዛትን እንደጥምቀት በመውሰድ በአንዳንድ ቤተ እምነቶች እንዲህ ይተረጎማል)

እንደ ካቶሊካዊነት፣ ፕሪስባይቴሪያኒዝም እና ሉተራን ያሉ አንዳንድ ቤተእምነቶች፣ ግርዛት በብሉይ ኪዳን ውስጥ ልጆችን ወደ ኪዳን እንደሚያጠቃልል በጸጋ ቃል ኪዳን ውስጥ እንደሚካተቱ በማመን ሕፃናትን ያጠምቃሉ።

“የስምንት ቀን ልጅ ይገረዝ፤ በቤት የተወለደ ወይም ከዘራችሁ ያይደለ በብርም ከእንግዳ ሰው የተገዛ፥ ወንድ ሁሉ በትውልዳችሁ ይገረዝ።”
ዘፍጥረት 17፥12


"የሥጋንም ሰውነት በመገፈፍ፥ በክርስቶስ መገረዝ፥ በእጅ ባልተደረገ መገረዝ በእርሱ ሆናችሁ ደግሞ ተገረዛችሁ፤ በጥምቀትም ከእርሱ ጋር ተቀብራችሁ፥ በጥምቀት ደግሞ፥ ከሙታን ባስነሣው በእግዚአብሔር አሠራር በማመናችሁ፥ ከእርሱ ጋር ተነሣችሁ። እናንተም በበደላችሁና ሥጋችሁን ባለመገረዝ ሙታን በሆናችሁ ጊዜ፥ ከእርሱ ጋር ሕይወትን ሰጣችሁ፤ በደላችሁን ሁሉ ይቅር አላችሁ፤"
ቆላስይስ 2፥11-13


ይቀጥላል...




ወደ ቻናሉ ለመ🀄️🀄️ል፦ @Holy_scriptures
10👍3😁1
በቅዱሳት መጻሕፍት ውስጥ ለመጀመሪያ ጊዜ ከተማን የሠራው ሰው ማን ነው?
Anonymous Quiz
9%
ሀ. አዳም
27%
ለ. ቃየን
47%
ሐ. ናምሩድ
16%
መ. ኖኅ
👍7