በቅዱሳት መጻሕፍት ውስጥ በእስራኤል ታሪክ የመጀመሪያው እና የመጨረሻው መስፍን ማን ነው?
Anonymous Quiz
11%
ሀ. ናዖድ እና ኤሊ
27%
ለ. ጎቶንያል እና ሳሙኤል
12%
ሐ. ጎቶንያል እና ኤሊ
32%
መ. ጌዴዎን እና ሳምሶን
17%
ሠ. መልስ የለም
👍2🔥1
. ==❀❀❀===❀❀❀==
የዕለቱ ጥቅስ
==❀❀❀===❀❀❀==
“እግዚአብሔር እንደ ሰጠን ሁሉ፥ የእግዚአብሔርን ቸርነትና የእግዚአብሔርን ምስጋና፥ እንደ ምሕረቱና እንደ ቸርነቱም ብዛት ለእስራኤል ቤት የሰጠውን ትልቅ በጎነት አሳስባለሁ።”
ኢሳይያስ 63፥7
ወደ ቻናሉ ለመ🀄️ላ🀄️ል፦ @Holy_scriptures

👍6
ቅዱሳት መጻሕፍት
#የሮሜ_መልእክት_ጥናት ሮሜ 10፥1-4 የዚህ ምዕራፍ ጭብጥ እስራኤል አሁን እግዚአብሔርን የመግፋቷ ጉዳይ ነው፡፡ ጳውሎስ ከመለኮታዊ ሉዓላዊነት (ምዕራፍ 9) ወደ ሰው ተጠያቂነት ያመራል፡፡ ባለፈው ምዕራፍ (ሮሜ 9:30-33) የጽድቅን ጭብጥ ካስተዋወቀ በኋላ የእስራኤልን የእምቢታ ሦስት ገጽታዎች ያብራራል፡፡ እስራኤል እንደ ሕዝብ የመሢሑን መምጣት በጉጉት እየጠበቁ ሊቀበሉት የተዘጋጁ እንደነበሩ…
#የሮሜ_መልእክት_ጥናት
ሮሜ 10፥2-3
ለ) ለእግዚአብሔር ይቀኑ ነበር (10:2)
እስራኤላውያን ከባቢሎን ምርኮ መልስ ከጣዖት አምልኮ ተፈውሰው ነበር፡፡ በምኩራብና በቤተ መቅደስ እውነተኛው አምላክ ይመለክና ያገለግሉ ነበር፡፡ እውነተኛውም ሕግ በትምህርት ይሰጥ ነበር፡፡ አይሁድ ከቅናታቸው የተነሣ ‹‹የእግዚአብሔርን ሕግ አሻሽለው» የራሳቸውን ትውፊት በማከል ከሕጉ ጋር እኩል አደረጓቸው፡፡ ጳውሎስ ለሕግና ለትውፊት ቀናተኛ ነበር (የሐዋ. 26፡1-11፤ ገላ. 1:13-14)
ቅናታቸው ግን በእውቀት ላይ የተመሠረተ አልነበረም፤ ብርሃን የሌለበት ሙቀት ነበረ፡፡ ዛሬም ብዙ የሃይማኖት ሰዎች ተመሳሳይ ስሕተት ይፈጽማሉ፡፡ መልካም ሥራቸውና መንፈሳዊ ድርጊታቸው ከመዳን እንደሚያርቋቸው ሳይገነዘቡ፣ ደኅንነት የሚሰጧቸው ይመስላቸዋል፡፡ በእርግጥ አብዛኛዎቹ ቅንና የተሰጡ ናቸው፣ ነገር ግን ቅንነትና መሰጠት ነፍስን አያድንም፡፡ «ይህም የሕግን ሥራ በመሥራት ሥጋ የለበሰ ሁሉ በእርሱ ፊት ስለማይጸድቅ ነው» (ሮሜ 3፡20)፡፡
ብዙ ሰዎች የእግዚአብሔርን ነገር በትጋት ይፈልጋሉ፤ ነገር ግን ትጋታቸው እውነትን በማወቅ ላይ የተመሠረተ ካልሆነ ከንቱ ነው። በሐሰት ላይ የተመሠረተ ትጋት በጣም አደገኛ ነው፤ ብዙውን ጊዜ የሚመራው ወደ ታላቅ ጥፋት
ነው።
ሐ) ኩሩና ራሳቸውን ያጸደቁ ነበሩ (10:3)
ስላልሰሙ ሳይሆን፣ ለመማር ባለመፍቀዳቸው፣ እስራኤላውያን ስለ እግዚአብሔር ጽድቅ የማያውቁ ነበሩ፡፡ ዕድል ከማጣት የሚመጣ አለማወቅ ቢኖርም፣ እስራኤላውያን ግን ለመዳን በጣም ብዙ ዕድል ነበራቸው፡፡ በራሳቸው እልከኝነት የመጣ እውነትን የመቃወም ባሕርይ ኖሮባቸው ለእግዚአብሔር አይገዙም፡፡ በመልካም ሥራቸውና በጽድቃቸው ስለታመኑ፣ ኃጢአተኝነታቸውን አምነው አዳኙን አልታመኑበትም፡፡ ጌታን ከመገናኘቱ በፊት ጳውሎስም ተመሳሳይ ስሕተት ፈጽሟል (ፊልጵ. 3፡1-11)።
አይሁዳውያን ከእግዚአብሔር የሚመጣውን ጽድቅ በክርስቶስ በማመን የሚመጣውን ስለማያውቁ፥ ማለትም ጽድቅ ስለማያውቁ ለእርሱ ሊታዘዙ
አልቻሉም። የእግዚአብሔር ጽድቅ አካል ክርስቶስ ራሱ መሆኑን አልተረዱም።
"አሁን ግን በሕግና በነቢያት የተመሰከረለት የእግዚአብሔር ጽድቅ ያለ ሕግ ተገልጦአል፥ እርሱም፥ ለሚያምኑ ሁሉ የሆነ፥ በኢየሱስ ክርስቶስ በማመን የሚገኘው የእግዚአብሔር ጽድቅ ነው፤ ልዩነት የለምና፤"
ሮሜ. 3፥21-22
ሮበርት ሙሬይ ማክቼኒ የተባለ አንድ ሰው፣ መንፈሳዊ ጽሑፎችን ሲያድል በጥሩ ሁኔታ ልብስ ለለበሰች ሴት ሰጣት፡፡ ሴትየዋም በንቀት አየችውና፣ «ጌታው፣ ማን እንደሆንኩ አታውቅም!›› አለችው፡፡ እርሱም በእርጋታ፣ «የእኔ እመቤት፣ የፍርድ ቀን መጥቷል፣ በዚያ ቀን ማንነትዎ ዋጋ የለውም!›› አላት፡፡
ይቀጥላል...
ምንጭ፦ ዋረን ደብልዩ ዌርዝ ቢ፤ ተስማማ፤ ገጽ 105-106፣ የአዲስ ኪዳን ማብራሪያ፤ ገጽ 374

👍9❤4
. ==❀❀❀===❀❀❀==
የዕለቱ ጥቅስ
==❀❀❀===❀❀❀==
“እኔ የአባቴን ሥራ ባላደርግ አትመኑኝ፤”
ዮሐንስ 10፥37
ወደ ቻናሉ ለመ🀄️ላ🀄️ል፦ @Holy_scriptures
የዕለቱ ጥቅስ
==❀❀❀===❀❀❀==
“እኔ የአባቴን ሥራ ባላደርግ አትመኑኝ፤”
ዮሐንስ 10፥37
ወደ ቻናሉ ለመ🀄️ላ🀄️ል፦ @Holy_scriptures
❤4👍4👏2
የብሉይ_ኪዳን_የጥናት_መምሪያ_እና_ማብራሪያ_2ኛ_መጽሐፍ.pdf
21.2 MB
👉ርዕስ፦ የብሉይ ኪዳን የጥናት መምሪያና ማብራሪያ 2ኛ መጽሐፍ
✍️ጸሐፊ፦ ቲም ፌሎስ
🖨አሳታሚ፦ ኤስ አይ ኤም
ወደ ቻናሉ ለመ🀄️ላ🀄️ል፦ @Holy_scriptures
✍️ጸሐፊ፦ ቲም ፌሎስ
🖨አሳታሚ፦ ኤስ አይ ኤም
ወደ ቻናሉ ለመ🀄️ላ🀄️ል፦ @Holy_scriptures
❤8👍2
. ==❀❀❀===❀❀❀==
የዕለቱ ጥቅስ
==❀❀❀===❀❀❀==
“አምላክህ እግዚአብሔር፥ ታላቅና የሚያስፈራ አምላክ፥ በመካከልህ ነውና ከእነርሱ የተነሣ አትደንግጥ።”
ዘዳግም 7፥21

❤8👍2🔥1
ቅዱሳት መጻሕፍት
ነቢዩ ኤርምያስ ክፍል-፰ መሲሓዊ ትንቢትን በተመለከተም ኤርምያስ መሲሓዊውን ጊዜ በዝርዝር አይገልጽም፡፡ የመሲሑ ማንነት በመጽሐፉ ላይ በጒልሕ አልተመለከተም፡፡ ይሁን እንጂ ኤርምያስ አንዳንድ ፋይዳ ያላቸውን መሲሓውያን ምንባቦች ይሰጣል ፡- 1. ከኪዳኑ ታቦት የላቀ የእግዚአብሔር መገለጥ እውን እንድሚሆን መታወጁ (3፥14-17) 2. የዐዲሱ ኪዳን መገለጥ…
ነቢዩ ኤርምያስ
ክፍል-፱
መላው ሕዝብ ቢቃወመውም እንኳ፣ ኤርምያስ የተለየ የድፍረት ሰው እንደ ነበርና ሳያወለውል የእግዚአብሔርን እውነት ለማወጅ የቈረጠ ጀግና እንደ ነበር ብዙ ጊዜ እንዘነጋለን፡፡ ይህን አቋሙን ጠብቆ የኖረው ከፍተኛ የሆነ አእምሮኣዊና አካላዊ ዋጋ በመክፈል ነው፡፡ ሕዝቡ ሳያውላውሉ ወደ አደጋ ሲጣደፉ፣ እርሱ ሁኔታውን ለመለወጥ ዐቅመ ቢስ መሆኑ ሲሰማው ለጥቅማቸው ሲል ትንቢት ከሚናገርላቸው ወገኖች ዘንድ በሚመጣውና በማያቋርጠው ተቃውሞአቸው ውስጥ ሲያልፍ፣ የልቡና የአእምሮው ሥቃይ የቱን ያህል ከባድ እንደሚሆን እንግዲህ ዐስቡት፡፡ እነዚህ ተግዳሮቶችና ፈተናዎች ምንጊዜም ከታላላቅ መንፈሳውያን ጀግኖች ውስጥ እንዲታይ አድርገው ቀረጹት፡፡ ፈሪ ሰው ስለ ነበር ተስፋ ለመቊረጥና አበቃልኝ ለማለት ተጋልጦ ነበር፡፡ ጌታ ትንቢቱ የቱን ያህል ፋይዳ እንዳለው ለማሳየት አንዳች ምልክት ወይም ታምር አልሰጠውም፡፡ በሕይወቱ ዘመን በአንድ ወቅት ኤርምያስ ዐደራውን ለመተው ወስኖ ነበር (20፥8-9)። ነገር ግን በውስጡ የሚሰማው መለኮታዊ አስገዳጅነት ይህን እንዲፈጽም አልፈቀደለትም፡፡ እግዚአብሔር የብረት ዐምድና (ምሰሶና) የነሐስ ቅጥር እንደሚያደርገው ቃል ገብቶለታል፤ እርሱ ደግሞ ቃሉን አያጥፍም፡፡
ከእግዚአብሔር ጋር ረዘም ያለ ውይይት ማካሄድ ለኤርምያስ የተለመደ ባሕርይ ነበር፡፡ እነዚህ ውይይቶች በመርሕ ደረጃ ዋጋ ያላቸው ናቸው፤ ምክንያቱም ውይይቶቹ ኤርምያስ (በተመሳሳይ ሁኔታ የነበሩት ሌሎች ነቢያትም) የግል ግንዛቤውንና የእግዚአብሔርን መልእክት እንዴት ለይቶ እንዳስቀመጠ ያሳያሉና (ከ12፥1-6፤ ከ1፥47 ፤ ከ15፥21 ጋር ያነጻ)፡፡
ኤርምያስ በጠላቶቹ ላይ የበቀል ርምጃ እንዲወስድ ወደ እግዚአብሔር ልመና በማቅረቡ አንዳንድ ተንታኞች ድንጋጤያቸውን ገልጸዋል፤ በእነርሱ ዐይን ይህ በሕይወቱ ላይ ጒልሕ ጒድለት ነው፡፡ እነዚህ ልመናዎች ግን በመዝሙረ ዳዊት ላይ እንደሚገኙት ያሉ ናቸውና የሚብራሩት በዚሁ መልክ ነው፤ ስለዚህ የግል በቀልን እንደሚመለከቱ ሆነው መታየት የለባቸውም፡፡ የእግዚአብሔር መልእክተኛ እንደ ነበር ኤርምያስ ያውቃል፤ ስለዚህ እርሱን የሚያጠቁ ሁሉ የእግዚአብሔር ጠላቶች በመሆን ራሳቸውን ያደራጁ ነበር፡፡ ኤርምያስ ለአምላኩ የነበረው ጥብቅ ታማኝነትና የመለኮት ጽድቅ አሸናፊ ሆኖ እንዲታይ የነበረው ናፍቆት፣ የጌታ ክብር ይገለጥ ዘንድ እነዚህ ርግማኖች ከአፉ በወጡ ጊዜ፣ ነቢዩ ግላዊ ፍላጎት እንዳልነበረው ያሳያሉ፤ ከዚህም በላይ የብሉይ ኪዳን ቅዱሳን ስለሚመጣው ተገቢ ቅጣት ግልጽ የሆነ ራእይ አልነበራቸውም፡፡
የእግዚአብሔርን ሰው እንደ ጸሎት ሕይወቱ ማንነቱን ገልጦ የሚያሳይ ሌላ ነገር የለም፡፡ በጸሎትና በጌታ ፊት ግልጽ በመሆን ዐውድ ውስጥ ኤርምያስ ኖረ፤ ሥራውን አከናወነ፤ አለቀሰም፡፡ መንገዳቸውን ለሳቱት ወገኖቹ አጥብቆ ይማልድ ነበርና እግዚአብሔር እንዲህ ያለውን ድርጊቱን ነቀፈበት (7 ፥ 16፤ 11፥14፤ 14፥11)፡፡ በጸሎቱም ውስጥ ራሱን ጨምሮአል፦ 11 ፥ 18-20 12 ፥ 1-4 ፤ 15፥ 10:15-18፤ 17፥14- 18: 18-19-23 20:7-11: 14-18 ላይ ያሉት ምንባቦች የኤርምያስ ኑዛዜዎች በመባል ይታወቃሉ፡፡ በእነዚህ ውስጥ የማንኛውም የእስራኤል ነቢይ ግልጥልጥ ያሉ ሐሳቦች ይገኛሉ፡፡ ሌሎች ነቢያት ተመክሮአቸውን ይተርካሉ፤ ይሁን እንጂ ብሉይ ኪዳን እንደዚህ ራስን የሚያጋልጡ ጸሎቶች ያሉት በቊጥር ነው:: በእነዚህ ኑዛዜዎች ውስጥ ተሰባሪ ሰውነቱ ይታያል፤ ለሕዝቡ ያለው ፍቅር፣ ለእግዚአብሔር ፈቃድና ጥሪ ያለው ታማኝነትም በእነዚህ ኑዛዜዎች ውስጥ ይታያሉ፡፡
ይቀጥላል...
ምንጭ፦ የብሉይ ኪዳን ማብራሪያ፤ ገጽ 828

👍9❤2👏1
በቅዱሳት መጻሕፍት ውስጥ በብሉይ ኪዳን ካሉት ነቢያቶች መካከል "የእግዚአብሔር ቀን" የሚለውን ሐረግ በተደጋጋሚ በመጠቀም የሚታወቀው ነቢይ የቱ ነው?
Anonymous Quiz
6%
ሀ. ዮናስ
30%
ለ. ኤርምያስ
14%
ሐ. ሐጌ
41%
መ. ኢዩኤል
9%
ሠ. ናሆም
👍7
. ==❀❀❀===❀❀❀==
የዕለቱ ጥቅስ
==❀❀❀===❀❀❀==
“ስለዚህ የምወደውንና የታመነውን በጌታ ልጄ የሆነውን ጢሞቴዎስን ልኬላችኋለሁ፥ እኔም በየስፍራው በአብያተ ክርስቲያናት ሁሉ እንደማስተምር በክርስቶስ ኢየሱስ የሚሆነውን መንገዴን እርሱ ያሳስባችኋል።”
1ኛ ቆሮንቶስ 4፥17
ወደ ቻናሉ ለመ🀄️ላ🀄️ል፦ @Holy_scriptures
የዕለቱ ጥቅስ
==❀❀❀===❀❀❀==
“ስለዚህ የምወደውንና የታመነውን በጌታ ልጄ የሆነውን ጢሞቴዎስን ልኬላችኋለሁ፥ እኔም በየስፍራው በአብያተ ክርስቲያናት ሁሉ እንደማስተምር በክርስቶስ ኢየሱስ የሚሆነውን መንገዴን እርሱ ያሳስባችኋል።”
1ኛ ቆሮንቶስ 4፥17
ወደ ቻናሉ ለመ🀄️ላ🀄️ል፦ @Holy_scriptures
👍6❤3
#እራሳችንን_እንመርምር
በሕይወት ውጣውረድ ነፍሳችን ስትናወጥ፣ የሕይወት ውሉ ሲጠፋ በአእምሯችን ውልብ ከማለት አልፎ ሰቅዘው የሚይዙን ጥያቄዎች ይበዛሉ። ከእነዚህ አንዱ "በዚህ ሁኔታ ውስጥ እግዚአብሔር አለ ወይ"፣ "እግዚአብሔር ለምን ዝም ይላል"፣ "ለምን እንደዚህ አይነት ነገር በሕይወቴ መጣ?"፣ "የእግዚአብሔር አሳብ ምንድነው"... እያልን በጥያቄዎች እንኳትናለን። ታዲህ ለዚህ ምስቅልቅል መፍትሄው ምን ይሆን? ቅዱሳት መጻሕፍትስ ምን ይላሉ?
“ሁሉን ታደርግ ዘንድ ቻይ እንደ ሆንህ፥ አሳብህም ይከለከል ዘንድ ከቶ እንደማይቻል አወቅሁ።”
ኢዮብ 42፥2

❤10👍5
. ==❀❀❀===❀❀❀==
የዕለቱ ጥቅስ
==❀❀❀===❀❀❀==
“እንደ ፈቃዱ ምክር ሁሉን የሚሠራ እንደ እርሱ አሳብ፥ አስቀድመን የተወሰንን በክርስቶስ ደግሞ ርስትን ተቀበልን።”
ኤፌሶን 1፥11

👍8❤1🔥1
#ቃልም_ሥጋ_ሆነ
በቅዱሳት መጻሕፍት ውስጥ፣ ኢየሱስ ክርስቶስ የእግዚአብሔር ልጅ፣ መሲሁ (የተቀባው) እና የዓለም አዳኝ እንደሆነ ማመን የክርስትና ዋና መሠረት እና ምሰሶ ነው። ከዚህ በታች የኢየሱስ ክርስቶስ ቁልፍ መግለጫዎች ከቅዱሳት መጻሕፍት በጥቂቱ እንመለከታለን፦
1. የእግዚአብሔር ልጅ
ኢየሱስ መለኮታዊ ማንነቱን በማሳየት የእግዚአብሔር ልጅ እንደሆነ መጻሕፍት ይናገራሉ።
“... በእርሱ ደስ የሚለኝ የምወደው ልጄ ይህ ነው አለ።”
ማቴዎስ 3፥17
2. መሲሕ (ክርስቶስ)
መጻሕፍት ኢየሱስ የብሉይ ኪዳንን ትንቢቶች የሚፈጽም ተስፋ የተደረገለት መሲሕ እንደሆነ ይገልጻሉ።
"ሴቲቱ፦ ክርስቶስ የሚባል መሲሕ እንዲመጣ አውቃለሁ፤ እርሱ ሲመጣ ሁሉን ይነግረናል አለችው። ኢየሱስ፦ የምናገርሽ እኔ እርሱ ነኝ አላት።"
ዮሐንስ 4፥25-26
3. የአለም አዳኝ
ኢየሱስ የሰውን ልጅ ከኃጢአት ለማዳን እና ከእግዚአብሔር ጋር ለማስታረቅ የመጣ አዳኝ እንደሆነ ቅዱሳት መጻሕፍት ይመሰክራሉ።
“በእርሱ የሚያምን ሁሉ የዘላለም ሕይወት እንዲኖረው እንጂ እንዳይጠፋ እግዚአብሔር አንድያ ልጁን እስኪሰጥ ድረስ ዓለሙን እንዲሁ ወዶአልና።”
ዮሐንስ 3፥16

❤19👍12😱1
. ==❀❀❀===❀❀❀==
የዕለቱ ጥቅስ
==❀❀❀===❀❀❀==
“ስለዚህ ወደ አምላክህ ተመለስ፤ ምሕረትንና ፍርድን ጠብቅ፥ ዘወትርም በአምላክህ ታመን።”
ሆሴዕ 12፥7

👍11
የአዲስ_ኪዳን_የጥናት_መምሪያና_ማብራሪያ_1ኛ_መጽሐፍ.pdf
28.1 MB
👉ርዕስ፦ የአዲስ ኪዳን የጥናት መምሪያና ማብራሪያ 1ኛ መጽሐፍ፣
በትምህርተ መለኮት ማስፋፊያ (ት.መ.ማ) መልክ የተዘጋጀ
✍ጸሐፊ፦ ቲም ፌሎስ
🗣ትርጉም፦ ግርማዊ
🖨አሳታሚ፦ ኤስ.አይ.ኤም
ወደ ቻናሉ ለመ🀄️ላ🀄️ል፦ @Holy_scriptures
በትምህርተ መለኮት ማስፋፊያ (ት.መ.ማ) መልክ የተዘጋጀ
✍ጸሐፊ፦ ቲም ፌሎስ
🗣ትርጉም፦ ግርማዊ
🖨አሳታሚ፦ ኤስ.አይ.ኤም
ወደ ቻናሉ ለመ🀄️ላ🀄️ል፦ @Holy_scriptures
👍11❤7
በቅዱሳት መጻሕፍት ውስጥ ጌታችን እና መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ሲወለድ በየእርከኑ መሪዎች እነማን ነበሩ?
Anonymous Quiz
39%
ሀ. የሮም ንጉሥ፦ ጲላጦስ ፣ የይሁዳ ገዢ፦ ታላቁ ሄሮድስ፣ ሊቀ ካህን፦ ቀያፋ
26%
ለ. የሮም ንጉሥ፦ አውግስጦስ ፣ የይሁዳ ገዢ፦ ታላቁ ሄሮድስ፣ ሊቀ ካህን፦ ሐና
16%
ሐ. የሮም ንጉሥ፦ ቀላውዴዎስ፣ የይሁዳ ገዢ፦ ታላቁ ሄሮድስ፣ ሊቀ ካህን፦ ዘካርያስ
19%
መ. የሮም ንጉሥ፦ ጢባርዮስ ፣ የይሁዳ ገዢ፦ ጲላጦስ ፣ ሊቀ ካህን፦ ሐናና ቀያፋ
👍8
. ==❀❀❀===❀❀❀==
የዕለቱ ጥቅስ
==❀❀❀===❀❀❀==
“በእምነት በኩል ሁላችሁ በክርስቶስ ኢየሱስ የእግዚአብሔር ልጆች ናችሁና፤”
ገላትያ 3፥26
ወደ ቻናሉ ለመ🀄️ላ🀄️ል፦ @Holy_scriptures
የዕለቱ ጥቅስ
==❀❀❀===❀❀❀==
“በእምነት በኩል ሁላችሁ በክርስቶስ ኢየሱስ የእግዚአብሔር ልጆች ናችሁና፤”
ገላትያ 3፥26
ወደ ቻናሉ ለመ🀄️ላ🀄️ል፦ @Holy_scriptures
👍7❤5
#ቃልም_ሥጋ_ሆነ
የኢየሱስ ክርስቶስ የማስተማር ዘይቤ እና ዘዴዎች
መቼስ ስለጌታችን ልደት ከማንሳታችን በፊት ስለማስተማሩ እና ምክሩ ቀድመን ማንሳት ግድ ይለናል።
በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ያሉት የጌታችን እና የመድኃኒታችን የኢየሱስ ክርስቶስ ትምህርቶች ቀለል በማለት፣ በሥልጣን እና በተዛምዶነታቸው ተለይተው የሚታወቁበትን ልዩ አቀራረብ ያሳያሉ። ጌታችን የተጠቀመባቸው ዘይቤዎችና ዘዴዎች እነሆ፡-
1. ምሳሌዎች
ኢየሱስ ብዙ ጊዜ ምሳሌዎችን ይጠቀም ነበር፤ እነዚህም ጥልቅ መንፈሳዊ እውነቶች ያሏቸው ቀላልና ተዛማጅ ታሪኮች ናቸው። ምሳሌዎች ውስብስብ ትምህርቶችን ተደራሽ እና የማይረሱ ያደረጓቸው ሲሆን እውነቶችን ለመቀበል ለማይፈልጉትንም ይጋርዱባቸው ነበር።
ምሳሌ፡-
👉የዘሪው ምሳሌ (ማቴዎስ 13፥3-9)
👉የደጉ ሳምራዊ ምሳሌ (ሉቃስ 10፥25–37)
2. ማብራሪያዎች እና ከዕለት ተዕለት ነገሮች ጋር የተያያዙ ትምህርቶች
ኢየሱስ ነጥቦቹን በምሳሌ ለማስረዳት የዕለት ተዕለት ነገሮችን ወይም ሁኔታዎችን ተጠቅሟል። ይህ ዘዴ በእይታ ቶሎ የሚገባቸውን ተማሪዎችን ይስባል ይህም ትምህርቶቹን ተግባራዊ የመሆን አቅማቸውንም ጨምሯል።
ምሳሌ፡-
👉የበለስ ዛፍ፣ እንደ እምነት እና የፍሬያማነት ትምህርት (ማር. 11፥12–14፥20–25)
👉"እኔ የወይኑ ግንድ ነኝ እናንተም ቅርንጫፎች ናችሁ" (ዮሐ. 15፥1-8)
3. ውይይት እና ጥያቄዎች
ኢየሱስ በጥልቅ እንዲያስቡ እና ራሳቸውን እንዲመረምሩ በማነሳሳት ጥያቄዎችን በመጠየቅ አድማጮቹን አሳትፏል።
ምሳሌ፡-
👉“እናንተስ እኔን ማን እንደ ሆንሁ ትላላችሁ?” (ማቴ. 16፥15)
👉"ሰው ዓለሙን ሁሉ ቢያተርፍ ነፍሱን ግን ቢያጐድል ምን ይጠቅመዋል?" (ማር. 8፥36 )

👍7❤6🔥1