ቅዱሳት መጻሕፍት
7.46K subscribers
1.37K photos
61 videos
332 files
808 links
በዚህ ቻናል

👉ቅዱሳት መጻሕፍት ይጠናሉ::
👉መጽሐፍ ቅዱሳዊ ትምህርቶች ይቀርባሉ::
👉 ለቅዱሳት መጽሐፍት ጥናት የሚያግዙ መጻሕፍት ይለቀቃሉ።

⭐️⭐️⭐️⭐️⭐️

@Holy_scriptures
Download Telegram
.    ==❀❀❀===❀❀❀==      
              የዕለቱ ጥቅስ 
     ==❀❀❀===❀❀❀==
“እንደ ሥጋ ፈቃድ የሚኖሩ የሥጋን ነገር ያስባሉና፥ እንደ መንፈስ ፈቃድ የሚኖሩ ግን የመንፈስን ነገር ያስባሉ።”
ሮሜ 8፥5




ወደ ቻናሉ ለመ🀄️🀄️ል፦ @Holy_scriptures
👍82
ወደ ቻናሉ ለመ🀄️🀄️ል፦ @Holy_scriptures
👍42
የብሉይ ኪዳን ማብራሪያ.pdf
23.3 MB
👉ርዕስ፦ የብሉይ ኪዳን ማብራሪያ፣
ከ "ZONDERVAN NIV
BIBLE COMMENTARY VOLUME 1: Old Testamen" የተተረጎመ
🗣ተርጓሚዎች፦ ምንሊክ አስፋው፣ ንጉሤ ቡልቻ፣ ተጋፋው ትርፌ፣ ሰሎሞን ጥላሁን፣ ናሁሠናይ አፈወርቅ፣ ፍትሐ አምላክ እንየው፣ ደርበው አዱኛ፣ መስፍን ታዬ፣ ቁምላቸው ፋንታሁን፣ ዮናስ አስፋው፣ ፍሥሓ ፈይሣ፣ ተስፋዬ መስፍን፣ ወርቁ ኤጀሬ እና ቴዎፍሎስ ቀነዓ ናቸው፡፡
አርታዕያን፦ ንጉሤ ቡልቻ፣ ናሁሠናይ አፈወርቅ፣ ሰሎሞን ጥላሁን፣ ደርበው አዱኛ፣ ምንሊክ አስፋው እና ፍሥሓ ፈይሣ
📝ዋና አርታዒ ፦ ፍትሐ አምላክ እንየው ናቸው፡፡
🖨አሳታሚ፦ ራዕይ አሳታሚ


ወደ ቻናሉ ለመ🀄️🀄️ል፦ @Holy_scriptures
5👍5
ከቅዱሳት መጻሕፍት ውስጥ ብዙ ቁጥሮችን የያዘው መጽሐፍ የቱ ነው? (ጥያቄው ስለምዕራፍ ቁጥር አይደለም)
Anonymous Quiz
6%
ሀ. ኦሪት ዘፍጥረት
3%
ለ. ኦሪት ዘኁልቊ
72%
ሐ. መዝሙረ ዳዊት
2%
መ. የዮሐንስ ራእይ
15%
ሠ. ትንቢተ ኢሳይያስ
2%
ረ. ኦሪት ዘጸአት
👍41
.    ==❀❀❀===❀❀❀==      
              የዕለቱ ጥቅስ 
     ==❀❀❀===❀❀❀==
“አካሄድን እንደ ቃልህ አቅና፤ ኃጢአትም ሁሉ አይግዛኝ።”
መዝሙር 119፥133



ወደ ቻናሉ ለመ🀄️🀄️ል፦ @Holy_scriptures
👍3
ቅዱሳት መጻሕፍት
ነቢዩ ኤርምያስ                         ክፍል-፮ ነገር ግን መጨረሻው ሩቅ አልነበረም:: በዘጠነኛው የአገዛዝ ዘመኑ (588)፣ ሴዴቅያስ ከፈርዖን ኡፍራ ጋር ግምባር በመግጠም በናቡከደነፆር ላይ ዐመፀ:: ባቢሎን ይሁዳን በመውረር ምላሽ ሰጥታ በ586 ከተማዋ በእጇ ስትወድቅ ወረራው ፍጻሜ ላይ ደረሰ (2ነገ 36፥17፤ ኤር 38 ፥ 28-39፥ 10)፡፡ በወረራው ዘመን ሁሉ ሴዴቅያስ…
ነቢዩ ኤርምያስ




                        ክፍል-

በኤርምያስ ዘመን ግብረ ገባዊ ዝቅጠት በሰፊው የተሠራጨ ሲሆን፣ ኢፍትሓዊነትም በዚያው ልክ ተስፋፍቶ ነበር (5፥1-9፤ 7 ፥ 1-11 ፤ 23 ፥ 10-14)፡፡ ካህናትና ነቢያት እንደ ሌሎቹ አይሁድ ጥፋተኞች ነበሩ (6፥ 13-15)፡፡ ሆኖም ሕዝቡ ሃይማኖታዊ ሥርዐትን ፈጸሙ፡፡ እግዚአብሔር ግን በዚህ ውጫዊ ሥርዐት ከቊጣው የሚመለስ አልነበረም:: ኤርምያስ ከፍርድ ሊያመልጡ እንደማይችሉ ሰበከ፡፡ እግዚአብሔር ድርቅን፣ ረኃብንና የውጭ ወራሪዎችን ቀደም ሲል ተጠቅሞአል (14፥1-6፤ 4 ፥ 11-22) ፤ ከዚያም በናቡከደነፆር በኩል የመጨረሻ ጒብኝቱን ያካሂዳል (25፥9)፡፡ ይሁን እንጂ የእግዚአብሔር ፍቅርና ለኪዳኑ ያለው ታማኝነት ፍርዱ አጥፊ ወይም የመጨረሻ እንዲሆን አያደርጉም:: የወደፊት ተስፋ ነበር፡፡ ከባቢሎን ምርኮ መመለስ እውን እንደሚሆንና (25፥11፤ 29፥10) ባቢሎን ራሷ እንደምትጠፋ (ምዕራፍ 50-51) ኤርምያስ አስቀድሞ ተናገረ፡፡ የእስራኤልን ተስፋ ተጨባጭ መገለጥ ለመስጠት አለወላወለም (32፥1-5)::

ኤርምያስ ለአሕዛብም አገልግሎት ነበረው፡፡ በዚያ ዘመን ለነበሩት ሁናቴዎች ናቡከደነፆር የእግዚአብሔር መሣሪያ መሆኑን አየ (27፥ 6)፡ ፤ ሌሎች ሕዝቦች ናቡከደነፆርን እንዳይቃወሙትም አስጠነቀቀ (27፥1-11)፡፡ ሕዝቡ ሁሉ በጽድቅ እንዲጓዝ በእግዚአብሔር ስም ጥሪ አቀረበ (ምዕራፍ 46-51)፡፡ እግዚአብሔር ለሰዎች ሁሉ ደኅንነት ግድ ያለው መሆኑን በመግለጽም ድምፁን አሰማ (29፥ 1-14 በተለይ ቊጥር 7)፡፡

በኤርምያስ አገልግሎት ውስጥ የነበረው ዐቢይ አጽንዖት፣ ከማንኛውም ነገር ይልቅ መንፈሳዊ ጒዳዩ የላቀ መሆኑ ነው፡፡ የይሁዳ እምነት ጊዜያዊ ገጽታ የቱን ያህል ዝቅተኛ መሆኑን አስተዋለ፡፡ የእምነት ብጤዎቹ ቀጥሎ የተመለከቱትን ይበጅ ብለው መያዛቸውንም አየ፤

(1) የጌታን ኪዳን በአፍኣዊ መልኩ መቀበል (11፥1-5)፣

(2) ግዝረት (9 ፥ 25-26)

(3) ቤተ መቅደሱ (7፥1-15)፣

(4) የመሥዋዕት ሥርዐት (6፥20፤ 7፥21-23)፣

(5) የሙሴን ሕግ በውጫዊ መልኩ መቀበል (8፥8)፣

(6) የሐሰት ትንቢት (2 ፥ 39-40)፣

(7) ጸሎት (11 ፥ 14 ፤ 15፥ 1)፣

(8) ዙፋኑ (22 ፥ 1-9)፣ እናም

(9) ታቦቱ (3፥16)፡፡

ከማንኛውም ነቢይ ይልቅ ኤርምያስ ስለ ንስሓ አብዝቶ ሰበከ፡፡ በማንኛውም ጊዜ ያሳስበው የነበረ ዋና ጒዳይ የእያንዳንዱ ሰው (የግለሰቡ) የልብ ሁናቴ ነበር፡፡ የዐዲሱ ኪዳን ገለጻው (ትንታኔው) በቅዱሳት መጻሕፍት ውስጥ በእጅጉ ድንቅ ነው (31 ፥ 31-34)፡፡ ይህ እውነት በጌታችን ሥራ ላይ የቱን ያህል ዘልቆ እንደ ገባ ዐዲስ ኪዳን ያሳያል፡፡

ኤርምያስ በሩቅ ስላለው ስለ ወደፊቱ ወቅት የተነበየው እስራኤል በንስሓ ወደ ጌታ እንደምትመለስ ነው (32 ፥ 37-40)፡፡ መሲሕ በፍትሕና በጽድቅ በእርሷ ላይ ይነግሣል (23፥5-8)፡፡ በዚያን ጊዜ የሕዝቡ ትሩፋን በረከትን ያገኛሉ (3፥17፤ 16፥19)፡፡


ይቀጥላል...



ምንጭ፦ የብሉይ ኪዳን ማብራሪያ፤ ገጽ 827




ወደ ቻናሉ ለመ🀄️🀄️ል፦ @Holy_scriptures
👍81
.    ==❀❀❀===❀❀❀==      
              የዕለቱ ጥቅስ 
     ==❀❀❀===❀❀❀==
“ጌታ እግዚአብሔር ሆይ፥ ታላቅነትህን የጸናችውንም እጅህን ለእኔ ለባሪያህ ማሳየት ጀምረሃል፤ በሰማይና በምድርም እንደ ሥራህ እንደ ኃይልህም ይሠራ ዘንድ የሚችል አምላክ ማን ነው?”
ዘዳግም 3፥24




ወደ ቻናሉ ለመ🀄️🀄️ል፦ @Holy_scriptures
3👍2
#የእግዚአብሔር_ቃል_ምን_ይላል?


ሉቃስ 12
¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯
³⁵ ወገባችሁ የታጠቀ መብራታችሁም የበራ ይሁን፤
³⁶ እናንተም ጌታቸው መጥቶ ደጁን ሲያንኳኳ ወዲያው እንዲከፍቱለት ከሰርግ እስኪመለስ ድረስ የሚጠብቁ ሰዎችን ምሰሉ፤
³⁷ ጌታቸው በመጣ ጊዜ ሲተጉ የሚያገኛቸው እነዚያ ባሪያዎች ብፁዓን ናቸው፤ እውነት እላችኋለሁ፥ ታጥቆ በማዕድ ያስቀምጣቸዋል ቀርቦም ያገለግላቸዋል።
³⁸ ከሌሊቱም በሁለተኛው ወይም በሦስተኛው ክፍል መጥቶ እንዲሁ ቢያገኛቸው፥ እነዚያ ባሪያዎች ብፁዓን ናቸው።
³⁹ ይህን ግን እወቁ ባለቤት በምን ሰዓት ሌባ እንዲመጣ ቢያውቅ ኖሮ፥ በነቃ፥ ቤቱም እንዲቆፈር ባልፈቀደም ነበር።
⁴⁰ እናንተ ደግሞ ተዘጋጅታችሁ ኑሩ፥ የሰው ልጅ በማታስቡበት ሰዓት ይመጣልና።




ወደ ቻናሉ ለመ🀄️🀄️ል፦ @Holy_scriptures
👍61
በቅዱሳት መጻሕፍት ውስጥ ጳውሎስ እና ሲላስ በእስር ቤት ሆነው እግዚአብሔርን ሲያመሰግኑ የወኅኒው መሠረት የተናወጠበት ከተማ የት ነበር?
Anonymous Quiz
15%
ሀ. ኤፌሶን
30%
ለ. ፊልጵስዩስ
11%
ሐ. ቆሮንቶስ
7%
መ. ተሰሎንቄ
37%
ሠ. አቴና
👍9
.    ==❀❀❀===❀❀❀==      
              የዕለቱ ጥቅስ 
     ==❀❀❀===❀❀❀==
“ጽድቅን የሚያደርገውን በመንገዶችህም የሚያስቡህን ትገናኛቸዋለህ። እነሆ፥ አንተ ተቈጣህ እኛም ኃጢአት ሠራን ስለዚህም ተሳሳትን።”
ኢሳይያስ 64፥5



ወደ ቻናሉ ለመ🀄️🀄️ል፦ @Holy_scriptures
4🔥2👍1
#እራሳችንን_እንመርምር



በሕይወት ዘመናችን መመካታችን እና እምነታችን ምን ላይ እንዲሆን እንሻለን? ምንደሰተው እና ልባችን በሐሴት የሚሞላው ምን አይነት ሰው ስናይ ነው?

“ነፍሴ በእግዚአብሔር ትከብራለች፥ ገሮችም ሰምተው ደስ ይላቸዋል።”
መዝሙር 34፥2

“በቃልህ ታምኛለሁና የሚፈሩህ እኔን አይተው ደስ ይላቸዋል።”
መዝሙር 119፥74




ወደ ቻናሉ ለመ🀄️🀄️ል፦ @Holy_scriptures
👍2👏1😁1
.    ==❀❀❀===❀❀❀==      
              የዕለቱ ጥቅስ 
     ==❀❀❀===❀❀❀==
“የሥጋንም ሰውነት በመገፈፍ፥ በክርስቶስ መገረዝ፥ በእጅ ባልተደረገ መገረዝ በእርሱ ሆናችሁ ደግሞ ተገረዛችሁ፤”
ቆላስይስ 2፥11




ወደ ቻናሉ ለመ🀄️🀄️ል፦ @Holy_scriptures
👍6
የሐዋርያው ጳውሎስ መልእክቶች የአጻጻፍ ስልት እና ይዘት


ሐዋርያው ​​ጳውሎስ የተለያዩ የአጻጻፍ ስልቶችን እና ቴክኒኮችን በመልእክቶቹ ውስጥ ተጠቅሟል፣ ይህም ትምህርቱን፣ የራሱን ባህላዊ ነባራዊ ሁኔታ እና የጻፈላቸውን የተለያዩ የመልእክቱ ተቀባዮቹን ሁኔታ የሚያንጸባርቅ ነበር። የተጠቀመባቸው ቁልፍ መንገዶች እና ዘዴዎች እነሆ፦

1. ዶክትሪን እና ሥነ-መለኮታዊ ጹሑፍ

ጳውሎስ ውስብስብ ሥነ-መለኮታዊ ሃሳቦችን በተለይም ስለ ድነት፣ ጸጋ፣ መጽደቅ እና እምነት ለማብራራት ብዙ ጊዜ ጽፏል።
ምሳሌ፡- ሮሜ ስለ ኃጢአት፣ ድነት እና የእግዚአብሔር ጽድቅ ስልታዊ ሥነ-መለኮታዊ ሙግቶችን ይዟል።

2. የግል እና መጋቢያዊ ቃና ያለው ድምጽ

ለአንባቢዎቹ እውነተኛ እንክብካቤ እና ፍቅር አሳይቷል፣ ብዙ ጊዜ “ወንድሞች እና እህቶች” ብሎ ይጠራቸዋል።
ምሳሌ፡- በ1ኛ ተሰሎንቄ ውስጥ፣ ጳውሎስ አማኞችን አመስግኗል እናም እነርሱን ለመጎብኘት ያለውን ጉጉት ገልጿል።

3. ሪቶሪካል ጥያቄዎች

ሪቶሪካል ጥያቄዎች "rhetorical question" ማለት መልሱ ምን እንደሆነ እየታወቀ መልስ እንዲመለስ ሳይሆን በአንባቢው ወይንም በሰሚዎቹ አእምሮ ውስጥ ጥያቄ ከስቶ ለማሰላሰል የሚገፋፋ ነው። ሀሳብን ለመቀስቀስ እና አንባቢዎችን ለማሳተፍ የአጻጻፍ ጥያቄዎችን ተጠቅሟል።
ምሳሌ፦ ሮሜ 6፡1፡ "እንግዲህ ምን እንላለን? ጸጋ እንዲበዛ በኃጢአት እንኑርን?"

4. አመክንዮአዊ ሙግት

ጳውሎስ አድማጮቹን ለማሳመን አመክንዮ በመጠቀም ሙግቶቹን በጥንቃቄ አዘጋጀ።
ምሳሌ፦ ገላትያ በዘዴ ይሟገታል በህግ ላይ ለድነት መታመንን እና በክርስቶስ ያለውን እምነት አጽንዖት ይሰጣል።


ይቀጥላል...


ወደ ቻናሉ ለመ🀄️🀄️ል፦ @Holy_scriptures
👍91
.    ==❀❀❀===❀❀❀==      
              የዕለቱ ጥቅስ 
     ==❀❀❀===❀❀❀==
“እናንተ በጌታ ጸንታችሁ ብትቆሙ፥ አሁን በሕይወት እንኖራለንና።”
1ኛ ተሰሎንቄ 3፥8



ወደ ቻናሉ ለመ🀄️🀄️ል፦ @Holy_scriptures
9🔥1
ወደ ቻናሉ ለመ🀄️🀄️ል፦ @Holy_scriptures
2
የአዲስ ኪዳን ማብራሪያ.pdf
55.3 MB
👉ርዕስ፦ የአዲስ ኪዳን ማብራሪያ
The Applied New Testament Commentary by Thomas Hale ከሚለው የተወሰደ
🗣ተርጓሚ፦ መስፍን ተስፋዬ፣ ተስፋዬ መስፍን፣ ምንሊክ አስፋውና ቴዎድሮስ በየነ ናቸው።
✏️ዋና ኦርታኢ፦ ደረጀ በቀለ ሲሆኑ ሰሎሞን ጥላሁንም አግዘዋል።
🖨አሳታሚ፦ ራዕይ አሳታሚ



ወደ ቻናሉ ለመ🀄️🀄️ል፦ @Holy_scriptures
5👍5
በቅዱሳት መጻሕፍት ውስጥ በዮሐንስ ራእይ ከሰባቱ አብያተ ክርስቲያናት መካከል አንድም ነቀፋ ያልቀረበበት ቤተ ክርስቲያን የቱ ነው?
Anonymous Quiz
33%
ሀ. ፊላደልፊያ
8%
ለ. ጴርጋሞን
13%
ሐ. ሰምርኔስ
7%
መ. ሰርዴስ
12%
ሠ. ኤፌሶን
11%
ረ. ሀ እና መ
17%
ሰ. ሀ እና ሐ
👍2🔥2
.    ==❀❀❀===❀❀❀==      
              የዕለቱ ጥቅስ 
     ==❀❀❀===❀❀❀==
“ዘመኑ ቀርቦአልና የሚያነበው፥ የትንቢቱን ቃል የሚሰሙትና በውስጡ የተጻፈውን የሚጠብቁት ብፁዓን ናቸው።”
ራእይ 1፥3



ወደ ቻናሉ ለመ🀄️🀄️ል፦ @Holy_scriptures
4🔥3👍1
የሐዋርያው ጳውሎስ መልእክቶች የአጻጻፍ ስልት እና ይዘት


5. የግጥም እና የመዝሙር ይዘቶች

ጳውሎስ ሥነ-መለኮታዊ እውነቶችን ለማጉላት መዝሙሮችን ወይም ቅኔያዊ ምንባቦችን አካቷል።
ምሳሌ፡- ፊልጵስዩስ 2፡6-11 ስለ ኢየሱስ ትህትና እና ከፍ ያለ የክርስቶስ መዝሙር ይዟል።

6. የወላጅ እና የዲሲፕሊን ድምጸት ያላቸው መልእክቶች

በአብያተ ክርስቲያናት ውስጥ ያሉ ስህተቶችን ወይም ግጭቶችን ለመፍታት አንዳንድ ጊዜ የማስተካከያ ዘዴ ይጠቀማል።
ምሳሌ፡- 1ኛ ቆሮንቶስ በቤተክርስቲያን ውስጥ መለያየትንና ብልሹ ባህሪይን ይገስጻል።

7. መምሰል እና ምሳሌ

ጳውሎስ የክርስቶስን ምሳሌ በመከተል የእሱን እምነትና ሕይወት እንዲኮርጁ አንባቢዎቹ አበረታቷቸዋል።
ምሳሌ፦ 1ኛ ቆሮንቶስ 11፥1፦ “እኔ ክርስቶስን እንደምመስል እኔን ምሰሉ።”

8. የባህል ማጣቀሻዎች እና ምስለት

ሐዋሪያው ጳውሎስ ለአድማጮቹ የተለመዱ ዘይቤዎችን እና ምሳሌዎችን ተጠቅሟል። ለምሳሌ ከስፖርት ፣ ከግብርና እና ከወታደራዊ ሕይወት ጋር እያነጻጸረ ይጠቀማል።
ምሳሌ፡- 1ኛ ቆሮንቶስ 9፡24-27 የክርስትናን ሕይወት ከሩጫ ጋር ያነጻጽራል።

9. ልባዊ ምክር እና ማበረታቻ

ጳውሎስ አንባቢዎቹን በቅዱስና በጽድቅ ሕይወት እንዲመሩ ደጋግሞ ይመክራል።
ምሳሌ፡- ኤፌሶን 4-6 ግንኙነትን እና መንፈሳዊ ጦርነትን ጨምሮ ለክርስቲያናዊ ኑሮ መመሪያዎችን ይዟል።



ይቀጥላል...


ወደ ቻናሉ ለመ🀄️🀄️ል፦ @Holy_scriptures
8👍2
.    ==❀❀❀===❀❀❀==      
              የዕለቱ ጥቅስ 
     ==❀❀❀===❀❀❀==
“አንተ በምሕረትህ ብዛት በምድረ በዳ አልተውሃቸውም፤ በመንገድም ይመራቸው ዘንድ የደመና ዓምድ በቀን፥ የሚሄዱበትንም መንገድ ያበራላቸው ዘንድ የእሳት ዓምድ በሌሊት ከእነርሱ አልራቀም።”
ነህምያ 9፥19




ወደ ቻናሉ ለመ🀄️🀄️ል፦ @Holy_scriptures
👍7
#የሮሜ_መልእክት_ጥናት




ሮሜ 10፥1-4


የዚህ ምዕራፍ ጭብጥ እስራኤል አሁን እግዚአብሔርን የመግፋቷ ጉዳይ ነው፡፡ ጳውሎስ ከመለኮታዊ ሉዓላዊነት (ምዕራፍ 9) ወደ ሰው ተጠያቂነት ያመራል፡፡ ባለፈው ምዕራፍ (ሮሜ 9:30-33) የጽድቅን ጭብጥ ካስተዋወቀ በኋላ የእስራኤልን የእምቢታ ሦስት ገጽታዎች ያብራራል፡፡

እስራኤል እንደ ሕዝብ የመሢሑን መምጣት በጉጉት እየጠበቁ ሊቀበሉት የተዘጋጁ እንደነበሩ አድርጋችሁ ታስቡ ይሆናል፡፡ ለዘመናት የብሉይ ኪዳን ትንቢቶችን ያውቃሉ፤ ሕጉንም ሲሠሩበት ኖረዋል፣ እርሱም ወደ ክርስቶስ እንዲመራቸው የተሰጠ እንደ «ሥራ መሪ» ነበር (ገላ. 3፡24)፡፡ እግዚአብሔር ሕዝቡን ሊያዘጋጅ ፈልጓል፣ ነገር ግን ኢየሱስ ክርስቶስ በመጣ ጊዜ አልተቀበሉትም፡፡ ‹‹የእርሱ ወደ ሆነው መጣ፣ የገዛ ወገኖቹም አልተቀበሉትም» (ዮሐንስ 1፡11)፡፡ እርግጥ ነው፣ መምጣቱን ሲጠባበቁ የነበሩት ቅሬታዎች ነበሩ፣ ለምሳሌ ስምዖንና ሐና (ሉቃስ 2፡25-38)፤ ነገር ግን አብዛኛው ሕዝብ ክርስቶስ ሲመጣ ዝግጁ አልነበረም፡፡

ይህን አሳዛኝ ነገር እንዴት መግለጽ እንችላለን? እስራኤላውያን መሢሑን ያልተቀበሉበትን ብዙ ምክንያቶች ጳውሎስ አቅርቧል፡፡

ሀ) ደኅንነት እንደሚያስፈልጋቸው አልተሰማቸውም ( 10፥1)

ጳውሎስ ለእስራኤላውያን ወይም ለአይሁዳውያን ወደ እግዚአብሔር የሚጸልየው ለምንድን ነው?
በሮሜ 9÷18 እግዚአብሔር ምሕረት ለሚያደርግለት ምሕረቱን ያሳያል፥ ልቡን ሊያጠነክር የሚፈልገውንም ያጠነክረዋል ብሎ ከጻፈ፤ አሁን ታዲያ ለአይሁዳውያን ደኅንነት ሲጸልይ ምን ጥቅም ያገኝበታል? ጳውሎስ እግዚአብሔርን ለማግባባት ይሞክራልን? ወይስ በጸሎቱ የእግዚአብሔርን አስተሳሰብ ለመለወጥ ይጥራል?

መልሱ አዎን ነው። እጅግ በሚያስደንቅ መንገድ፤ እግዚአብሔር በፀሎታችን እንድናግባባው ይፈቅዳል። ይህን በማስረጃ ለማስደገፍ በመላው መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ በጣም ብዙ ምሳሌዎች አሉ። በተጨማሪም በጸሎታችን የሰይጣንን ሥራ ማሰናከል እንችላለን። ከእግዚአብሔር ቃል ቀጥሎ
ጸሎት በጣም ኀይለኛ የሆነ መንፈሳዊ የጦር መሣሪያ ነው (ኤፌ. 6፥17-18)። አንድ ነገር ለማግኘት በኢየሱስ ስም ብንጸልይ፥ እግዚአብሔር ይመልስልናል (ዮሐ. 15፥16)። ስለዚህም ጳውሎስ ለአይሁዳውያን ይጸልያል።

ጳውሎስ ከሕዝቡ ጋር ተስማምቶ ወንጌልን ተቃውሞ ኢየሱስን እንደ አታላይ የቆጠረበት ጊዜ ነበር፡፡ እስራኤላውያን ደኅንነት የሚያስፈልጋቸው አይሁድ ሳይሆኑ አሕዛብ ብቻ እንደሆኑ ቆጠሩ፡፡ በብዙ ምሳሌዎቹ እነዚህን የተሳሳቱ አሳቦች ኢየሱስ አንድ በአንድ አንሥቶአቸዋል፡- ታላቁ ወንድም (ሉቃስ 15፡11- 32) እና ፈሪሳዊው (ሉቃስ 18:9-14) ሁለት ምሳሌዎች ናቸው፡፡ እስራኤላውያን ከሮም ነፃ የሚወጡበት የፖለቲካ አርነት ቢፈልጉም፣ መንፈሳዊ ደኅንነት እንደሚያስፈልጋቸው ግን አልተረዱም ነበር፡፡


ይቀጥላል...



ምንጭ፦ ዋረን ደብልዩ ዌርዝ ቢ፤ ተስማማ፤ ገጽ 104-105፣ የአዲስ ኪዳን ማብራሪያ፤ ገጽ 374




ወደ ቻናሉ ለመ🀄️🀄️ል፦ @Holy_scriptures
👍84