ቅዱሳት መጻሕፍት
7.45K subscribers
1.37K photos
61 videos
332 files
808 links
በዚህ ቻናል

👉ቅዱሳት መጻሕፍት ይጠናሉ::
👉መጽሐፍ ቅዱሳዊ ትምህርቶች ይቀርባሉ::
👉 ለቅዱሳት መጽሐፍት ጥናት የሚያግዙ መጻሕፍት ይለቀቃሉ።

⭐️⭐️⭐️⭐️⭐️

@Holy_scriptures
Download Telegram
ሃይማኖትስ ይታደሳል?
      


ክርስትና በአስተርእዮተ እግዚአብሔር ላይ የተመሰረተ እምነት ነው (ለምሳሌ ዮሐ. 1፥18፤ ገላ. 2፥2)። ጌታ እግዚአብሔር በዘመናት ሁሉ የገለጠው እውነትና የሰጣቸው ተስፋዎች ሁሉ ፍጻሜም ነው። በክርስቶስ መገለጥ ያልተፈጸመ ምንም የለም፤ "በእግዚአብሔር የተሰጡ ተስፋዎች ሁሉ 'አዎን' የሚኾኑት በእርሱ ነውና" (2ቆሮ. 1፥20 ዐ.መ.ት)። በእግዚአብሔር ልጅ በጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ አማካይነት የመጣው አስተርእዮ የቀዳሚዎቹ ፍጻሜ ብቻ ሳይኾን፣ የመጨረሻውና ከሁሉ በላይ የላቀ መገለጥ ነው (ዕብ. 1)። እንግዲህ ይህ መገለጥና እምነት እውነተኛ ፍጹም ቢኾንም፣ እኛ ሰዎች በምንሰጠው ምላሽና ተግባር ላይ ግን ጉድለት ሊከሠት መቻሉ እውነት ነው፤ የሰው ልጅ መሳሳቱ አይቀርም። የመታረሙና መታደሱ አስፈላጊነትም የሚመነጨው ከዚሁ የሰው ድካም ውስጥ ነው።

የሰው ልጅ እውነተኛን እምነት በመበረዝ በኑፋቄ ጮረቃ ሲያልኮሰኩሰው እግዚአብሔር በተሐድሶ ውሃ ያጠራዋል። በዚያን ጊዜ ምርቱን ከግርዱ መለየት ይኖራል። ፍሬውን ከገለባው ማበጠር ይከተላል። ለዚህም ዐላማ ሲል እግዚአብሔር በምሕረቱ የተሐድሶ ነፋስ ያነፍስበታል። በዚህ ማጥራትና ማንፈስ ሂደት ደግሞ የሚሠራ ብቻ ሳይኾን የሚፈርስ የቁሻሻ ክምር ይኖራል። ይህን መሳይ ታላቅ ተግባር ለማከናወን ብሩህ አእምሮ የታደሉ ዐዳሾች ያስፈልጋሉ ማለት ነው። ፕሮፌሰር ጌታቸው ኃይሌ እንዳሉት፣ "አሕይዎና ተሐድሶ (Revival and Renewal or Reformation) ተደላድሎና ተመቻችቶ በተቀመጠ ሥርዐት (Establishement) ውስጥ የዛገና የሚራገፍ ነገር የሚያይ የአእምሮ ችሎታና የተፈጥሮ ተሰጥዎ ካላቸው ታላላቅ ሰዎች ዘንድ የሚመጡ ሐሳቦች ናቸው።"

ስለዚህ ሃይማኖትም ቢኾን "በዛገና በሚራገፍ ነገር" ብልሽት ከገጠመው ይታደሳል። እግዚአብሔር ራሱ አሮጌውን በዐዲሱ ዐድሷል። አሮጌውን በዐዲሱ ሰው ተክቶታል (ኤፌ. 4፥24፤ ቆላ. 3፥10)። ነቀፋ የተገኘበትን ፊተኛውን ኪዳን  (ኤር. 31፥ 31-34) ለዐዲሱ ስፍራ አስለቅቆታል (ዕብ. 8፥6-7)። ስለዚህም፣ "ዐዲስ በማለቱ ፊተኛውን አስረጅቶአል፤ አሮጌውና ውራጅ የሆነውስ ሊጠፋ ቀርቦአል" (ዕብ.8፥13) የተባለው ቃል ተጻፈ። አዎን! ሃይማኖትም ቢኾን ቅይጥነት ሲገዳደረው፣ አደፋ ሲጠናወተው መለኮተ መድኀኒት ያዝዝለታል።

"ማፍረስም መስራት ነው" ከሚለው ጽሁፍ የተቀነጨቡ ሃሳቦች

ከእግዚአብሔር የተቀበልናቸውን ጠቃሚ ሀብታት አንድም በማበላሸት ካቆሸሽናቸው፣ ደግሞም ለእርሱ ክብር ከማድረግ ይልቅ ለሥጋዊ ትምክሕትና ሌላውን ወገን ለማክፋፋት ካዋልናቸው ዐላማቸውን ስተዋልና የተሐድሶ ነፋስ ያሻቸዋል። 

መጽሐፍ ቅዱሳችን ራሱ የተሐድሶ መጽሐፍ ነው።  እግዚአብሔር በታሪከ ድነት ውስጥ ያቆመው ዋነኛ መርሕም የተሐድሶ ምልሰት ነው።      

ቅዱሱን መጽሐፍ የልብ ዐይኖቻችን ተከፍተውልን ካነበብነው ተሐድሶን እንናፍቀው እንደኾነ እንጂ እናክፋፋው ዘንድ ዐቅም አይኖረንም። ይህም[በክርስቶስ የሆነው ድነት] በእግዚአብሔር ምሕረትና ጸጋ አማካይነት ወደ ቀደመው ክብር፣ ጸጋና ቦታ የመመለስና የመታደስ ወንጌል ነው። ከውድቀት በኃላ ለአዳም የተሰጠው ያ ተስፋ ቤዝዎታዊ ተሐድሶ ነበር።     

ተሐድሶን ለማምጣትና ወደ እውነቱ ለመመለስ ሲባል የሐሰት ትምህርት ላይ መጨከን ግዴታ ነው እንጂ፣ አማራጭ አልነበረም፤ ዛሬም ሊሆን አይችልም።

"ልዩ ወንጌል" ወደ ቤተ እግዚአብሔር ሲያቀና እንቢ ማለትና አዋኪዎች ያስገቡትን ኑፋቄና የአጋንንት ትምህርት ማፍረስ ተሐድሶ ነው። ይህ ሊኮነን ሳይኾን ሊወደስ የሚገባው ዘመቻ ነው። ጥያቄው ለምን፣ መቼ፣ የት፣ ምንና እንዴት ይታደስ የሚለው እንጂ "ዝንቡ እሽ የሚባል የለም" ብሎ ማፍጠጥ መፍትሔ አይኾንም። በደፈናው "ሃይማኖት አይታደስም" እያልን ከማገንገን፣ ለምን እንደማይታደስ ብናስረዳ ጥሩ ነበር። ጌታ ኢየሱስ አዳሽ አልነበረምን? ሐዋርያቱስ? የአሮጌው መነካት ባይመቸንም እንኳ፣ ለተሻለው ስፍራ እንዲለቅ ውራጅ የኾነው ትምህርትና ልምምድ ይፈርሳል።

ማንኛውንም ነገር በደባልነት ደርበን ለማምለክ ብንሞክር፣ ይህ ብክለት ነውና ሃይማኖት ይታደሳል። ማንኛውም ነገር ከመለኮታዊው አስተምህሮ በተፃሮ ሲቆም፣ ወይም ቅይጥነት ሲዳበለው ተሐድሶ ያስፈልጋል። የእግዚአብሔር ሰው ነኝ የሚል ሁሉ አምልኮተ ባዕድን፣ ርኩሰትን፣ ጥንቆላን፣ ኑፋቄን። በወንጌል ስም መነገድን፣ ወዘተ. ማፍረስ ግድ ይለዋል። በእግዚአብሔር ከተሰጠው መመሪያ ውጭ በሰው የተገነቡ መሠዊያዎች እስከሚሰነጠቁና ዐመዳቸው እስከሚፈስ ድረስ ቢሰነጣጠቁ እንደነቃለንን(1ነገ. 13)?     



ምንጭ፦ ሰሎሞን  አበበ ገብረ መድሕን፤ የትሩፋን ናፍቆት፣ ማፍረስም መስራት ነው፣ ጌታቸው ኃይሌ ፤ ደቂቀ እስጢፋኖስ:- በሕግ አምላክ




ወደ ቻናሉ ለመ🀄️🀄️ል፦ @Holy_scriptures
6👍5🥰1
.    ==❀❀❀===❀❀❀==      
              የዕለቱ ጥቅስ 
     ==❀❀❀===❀❀❀==
“ንቁ፥ በሃይማኖት ቁሙ፥ ጎልምሱ ጠንክሩ።”
1ኛ ቆሮንቶስ 16፥13



ወደ ቻናሉ ለመ🀄️🀄️ል፦ @Holy_scriptures
👍52🔥2
ወደ ቻናሉ ለመ🀄️🀄️ል፦ @Holy_scriptures
2
የኢትዮጵያ ቤተክርስቲያን ተሐድሶ.pdf
11.1 MB
👉ርዕስ፦ የኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያን ተሐድሶ፣ ቅጽ 1፣ ሳታድግ ያረጀች የኢትዮጵያ ቤተክርስቲያን
ጸሐፊ፦ ወ/ዊ ጸጋአብ በቀለ
🗓 የታተመበት ዓመት፦ 2006 ዓ.ም


ወደ ቻናሉ ለመ🀄️🀄️ል፦ @Holy_scriptures
6👍6👎1
በአባቱ በዳዊት መንገድ እንደሄደ የተነገረለት፣ እስራኤላዊያን ያጥኑለት የነበረውን ሙሴ የሰራውን የናሱ እባብ የሰባበረ፣ በኮረብታ ያሉትን መስገጃዎች ያስወገደው ንጉሥ ማን ነው?
Anonymous Quiz
27%
ሀ. ሰሎሞን
11%
ለ. ምናሴ
22%
ሐ. አሳ
39%
መ. ሕዝቅያስ
👏64
.    ==❀❀❀===❀❀❀==      
              የዕለቱ ጥቅስ 
     ==❀❀❀===❀❀❀==
“ነገር ግን ሩጫዬንና ከጌታ ከኢየሱስ የተቀበልሁትን አገልግሎት እርሱም የእግዚአብሔርን ጸጋ ወንጌልን መመስከር እፈጽም ዘንድ ነፍሴን በእኔ ዘንድ እንደማትከብር እንደ ከንቱ ነገር እቆጥራለሁ።”
ሐዋርያት 20፥24



ወደ ቻናሉ ለመ🀄️🀄️ል፦ @Holy_scriptures
👍62
ፕሮቴስታንት ማለት ምን ማለት ነው?




ፕሮቴስታንት የሚለው ቃል በላቲን ፕሮቴስታሪ ከሚል የተገኘ ሲሆን ትርጉሙም "በአደባባይ ማወጅ" ወይም "ተቃውሞ ማድረግ" ማለት ነው። ቃሉ በመጀመሪያ እ.ኤ.አ በ1529 በስፔየር አመጋገብ ላይ በፖለቲካዊ አውድ ውስጥ ጥቅም ላይ ዋለ። ከዚህ በመቀጠል በስብሰባ ላይ የጀርመን መሳፍንት እና የንጉሠ ነገሥት ከተሞች ቡድን የለውጥ አራማጁን ማርቲን ሉተርን ያወገዘውን የዎርምስን አዋጅ ለመደገፍ የተላለፈውን ውሳኔ ተቃወሙ። እነዚህ ተቃዋሚዎች የሀይማኖት ነፃነት መብት እና የእምነታቸው ተግባር ላይ የሚጣሉ ገደቦችን በመቃወም የካቶሊክ አብላጫውን ድንጋጌ በመቃወም መደበኛ የሆነ “ተቃውሞ” አቅርበዋል።

እንቅስቃሴው በሃይማኖታዊ ገጽታው ብቻ ሳይሆን በተሃድሶ ላይ በማተኮር እና በተቋቋሙት የሃይማኖት ባለስልጣናት ላይ በማተኮር "ፕሮቴስታንቲዝም" በመባል ይታወቃል። በጊዜ ሂደት፣ “ፕሮቴስታንቶች” ከተሃድሶ የተነሱትን እና ከሮማ ካቶሊክ ቤተ ክርስቲያን የተለየ ማንነት ያለው የትኛውንም የክርስቲያን ቤተ እምነት በሰፊው ለማመልከት የሚውል ቃል ሆነ።


ምንጭ፦
👉MacCulloch, Diarmaid. The Reformation: A History. Viking, 2003.
👉Bainton, Roland H. Here I Stand: A Life of Martin Luther. Abingdon-Cokesbury, 1950.
👉The Oxford Dictionary of the Christian Church, edited by F.L. Cross and E.A. Livingstone, 2005.



ወደ ቻናሉ ለመ🀄️🀄️ል፦ @Holy_scriptures
👍71🙏1
ተሐድሶ መቼ ይጠበቃል?


፩. በክርስቲያን ነን ባዮች መሃል ወንድማዊ ፍቅርና ክርስቲያናዊ መተማመን ሊኖር ግድ ሲል።

፪. የአሳብ መለያየት፣ ቅናት እና ክፉ ንግግር በክርስቲያን ነን ባዮች ቦታ ሲይዝ።

፫. በቤተ ክርስቲያን ውስጥ ዓለማዊ መንፈስ ሲኖር። ክርስቲያኖች በአለባበስ፣ ሀብት በመሰብሰብና በጭፈራ በዓለም መደነቅን በመፈለግ የዓለምን ነገር ሲመርጡ ሲታይ።

፬. ቤተ ክርስቲያን ምዕመኖቿ በኃጢአት ሲዘፈቁና ወደ ኃጢአት ሲገቡ።

፭. አገልጋይ በየትኛውም ደረጃ የሚያገለግለውን ሕዝብ አመኔታ ባጣ ጊዜ።

፮. ሰው በተሰበከው መጠን ልቡ ንስሃ ከመግባት ይልቅ የሚደነድን ከሆነ።

፯. አማኞች የጌታ መልክ የማይታይባቸው ከሆነ።

፰. ጸጋ የማያድግበት ከሆነ እና አማኙ ከሳምንት ሳምንት ለክርስትና ግዴታው የማይነሳሳ ከሆነ

፱. መጸለይ ከባድና አስቸጋሪ ሲሆን።

፲. ክርስቲያኖች ኃጢአታቸውን እርስ በእርሳቸው መናዘዝ ሲያቅታቸው

፲፩. ክርስቲያኖች መስዋዕትነት መክፈል በሚያስፈልግበት መስዋዕትነትን ለመክፈል ፈቃደኛ መሆን ሲያቅታቸው




ምንጭ፦ ቻርለስ ፊኒ፤ ተሐድሶ እንዲሆን፤ ከገጽ 6-10




ወደ ቻናሉ ለመ🀄️🀄️ል፦ @Holy_scriptures
👍6🔥21👏1
.    ==❀❀❀===❀❀❀==      
              የዕለቱ ጥቅስ 
     ==❀❀❀===❀❀❀==
“ያን መንፈስም፥ በጸጋው ጸድቀን በዘላለም ሕይወት ተስፋ ወራሾች እንድንሆን፥ በመድኃኒታችን በኢየሱስ ክርስቶስ በእኛ ላይ አትርፎ አፈሰሰው።”
ቲቶ 3፥6-7




ወደ ቻናሉ ለመ🀄️🀄️ል፦ @Holy_scriptures
3👍3🔥1
Audio
👉ርዕስ፦ የመናኝ ጉዞ
ጸሐፊ፦ ዮሐንስ ቡንያን
🔈ክፍል ስድስት


ይቀጥላል...


ወደ ቻናሉ ለመ🀄️🀄️ል፦ @Holy_scriptures
1👍1🥰1
#ከተማ_ወይም_ቦታ_በቅዱሳት_መጻሕፍት


#ቀርጤስ

ቀርጤስ ከግሪክ ደሴቶች ትልቁ እና ከዋናው ግሪክ በደቡብ ምስራቅ የምትገኝ ከተማ ናት። በጥንት ጊዜ፣ በአውሮፓ ውስጥ ከመጀመሪያዎቹ የላቁ ባህሎች አንዱ ተደርጎ በሚቆጠር ኃይለኛ በሚኖአን ሥልጣኔ (2700-1420 ከክርስቶስ ልደት በፊት) ትታወቅ ነበር። በአዲስ ኪዳን ዘመን፣ ቀርጤስ የአይሁድ ማህበረሰቦችን ጨምሮ በባህሏ እና በተለያዩ ህዝቦቿ የምትታወቅ የሮማ ግዛት አካል ነበረች።

ከሊታውያን የቀርጤስ ሰዎች ነበሩ፤ 1ሳሙ. 30፥14። በጰንጠቆስጤ ቀን ከቀርጤስ የመጡ አንዳንድ ሰዎች በኢየሩሳሌም ነበሩ፤ ሐሥ. 2፥11። ጳውሎስና ቲቶ በቀርጤስ ቤተ ክርስቲያንን መሠረቱ ቲቶ 1፥5-14።

በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ስለ ቀርጤስ ቁልፍ ነጥቦች፡-

ስትራቴጂካዊ ቦታ፦ የቀርጤስ መገኛ በሜዲትራኒያን ባህር ውስጥ ለንግድ እና ለጉዞ አስፈላጊ መስቀለኛ መንገድ አድርጎታል።

የባህል ጠቀሜታ፦ ደሴቲቱ ተረት እና ፍልስፍናን ጨምሮ የበለጸገ ባህላዊ ቅርስ ነበራት።

የሥነ ምግባር ዝና፡- የቀርጤስ ሰዎች የሚታወቁት በመዋሸትና በሥነ ምግባር ብልሹነት ነበር (ቲቶ 1፥12)

ክርስቲያናዊ ተልእኮ፡- የጳውሎስ የቀርጤስ ጉብኝት እና ቲቶ መሪ አድርጎ መሾሙ ክርስትና ወደ ደሴቲቱ መስፋፋቱን ያመለክታል።



ምንጭ፦ የመጽሐፍ ቅዱስ መዝገበ ቃላት፤ ገጽ 89፣ The Book of Titus: A Counter-Cultural Gospel for Cretans: https://bibleproject.com/articles/titus/
Crete Meaning - Bible Definition and References:

https://www.biblestudytools.com/dictionary/crete/




ወደ ቻናሉ ለመ🀄️🀄️ል፦ @Holy_scriptures
👍111
.    ==❀❀❀===❀❀❀==      
              የዕለቱ ጥቅስ 
     ==❀❀❀===❀❀❀==
“ያም እድል ፈንታው ነውና ሰው በሥራው ደስ ከሚለው በቀር ሌላ መልካም ነገር እንደሌለው አየሁ፤ ከእርሱ በኋላስ የሚሆነውን ያይ ዘንድ የሚያመጣው ማን ነው?”
መክብብ 3፥22



ወደ ቻናሉ ለመ🀄️🀄️ል፦ @Holy_scriptures
👍61
ከቅዱሳት መጻሕፍት ውስጥ በሚከተለው ዑደት የተሞላው መጽሐፍ የቱ ነው? እስራኤላውያን ኃጢአት ይሰራሉ ----❯ እግዚአብሔር አስጨናቂ የአሕዛብ ገዢዎች ይሰድባቸዋል ---❯ ሕዝቡ ወደ እግዚአብሔር ይጮኻል ----❯ተለምኖም ነጻ ያወጣቸዋል። ---❯ ተመልሰው ወደ ኃጢአት ይገባሉ...
Anonymous Quiz
12%
ሀ. 2ኛ ነገሥት
5%
ለ. 2ኛ ዜና
68%
ሐ. መጽሐፈ መሳፍንት
14%
መ. ትንቢተ ኤርምያስ
1%
ሠ. መጽሐፈ ሩት
👍4
ለቃሉ መታዘዝ




መጽሐፍ ቅዱስ የተጻፈው፡ ለታሪክ፡ለምርምር፡ ለጠቅላላ ዕውቀት፡ ለግንዛቤ፡ ወይም ለመረጃ አይደለም። የተጻፈበት ቀዳሚ ዓላማ ለሕይወት ነው።

"የእግዚአብሔር ቃል ሕያው ነውና፥ የሚሠራም፥ ሁለትም አፍ ካለው ሰይፍ ሁሉ ይልቅ የተሳለ ነው፥ ነፍስንና መንፈስንም  ጅማትንና ቅልጥምንም እስኪለይ ድረስ ይወጋል፥ የልብንም ስሜትና አሳብ ይመረምራል፤" ዕብ ፬፡፲፪

መጽሐፍ ቅዱስን መታዘዝ አለብን ስንል መጽሐፉ ከዳር እስከ ዳር ይህን አድርግ ይህን አታድርግ በሚሉ ትእዛዛት የተሞላ መጽሐፍ ነው ማለታችን አይደለም። እግዚአብሔር እንድንታዘዘው የሚፈልገውን ሃሳብ በቃሉ ውስጥ በተለያየ መንገድ አስቀምጧል። ይህንንም ማስተዋል የኛ ድርሻ ይሆናል።

« እግዚአብሔር በአንድ መንገድ በሌላም ይናገራል ሰው ግን አያስተውለውም።» ኢዮ ፴፫፥፲፬፤

እግዚአብሔር ከሚያስተምርባቸው መንገዶች የሚከተሉት ዋናዎቹ ናቸው።

፩. በቀጥተኛ ትዕዛዝ

መጽሐፍ ቅዱስ አድርግ፣ አታድርግ የሚሉ ቀጥተኛ ትእዛዛት አሉት፤ ለምሳሌ እንደ አሥርቱ ቃላት እና ትእዛዛተ-ወንጌል፤ እነዚህንም በቀጥታ መፈጸም ይጠበቅብናል።

«አትግደል፤ አትስረቅ፤ አታመንዝር…. በሰማይ መዝገብ ሰብስቡ፤ አትጨነቁ፤ ጽድቁን ፈልጉ።…» ዘጸ ፳፤ ማቴ ፮።

፪. በምክር መልክ

በቅኔ እና በጥበብ መጻሕፍት ውስጥ በምሳሌ፣ በምስጋና፣ በግጥም፣ በጸሎት መልክ በተጻፉት በምክር ያስተምራል። እነዚህም በመከራ ጊዜ ድጋፍ፣ መጽናኛ የሚሆኑ ኃይል ያላቸው ቃላት ናቸው።

            «እግዚአብሔር ብርሃኔና መድኃኒቴ ነው የሚያስፈራኝ ማን ነው? እግዚአብሔር የሕይወቴ መታመኛዋ ነው የሚያስደነግጠኝ ማን ነው?» መዝ ፳፯፥፩

፫. በሰዎች ታሪክ

ደካማም ይሁኑ ብርቱ፣ ከድካማቸው እንድንማር፣ ብርታታቸውን እንድንከተል በመላው መጽሐፍ ቅዱስ ታሪካቸው የተጻፈላቸው ሰዎች ሁሉ ምንጊዜም ለኛ የሚያስተምሩት ነገር  አለ። ለምሳሌ አብርሃም የእግዚአብሔር ወዳጅ ለመባል የበቃው በእምነት ባሳየው መታዘዝ በመሆኑ እኛም እንደ አብርሃም በእምነት እግዚአብሔርን ብንታዘዝ የበረከቱ ተካፋዮች እንደምንሆን እግዚአብሔር ተናግሯል።

«መጽሐፍም እግዚአብሔር አሕዛብን በእምነት እንዲያጸድቅ አስቀድሞ አይቶ። በአንተ አሕዛብ ሁሉ ይባረካሉ ብሎ ወንጌልን ለአብርሃም አስቀድሞ ሰበከ። እንደዚህ ከእምነት የሆኑት ካመነው ከአብርሃም ጋር ይባረካሉ። » ገላ ፫፣፰

፬. በኢየሱስ ክርስቶስ ሕይወት

ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ወደ ዚች ምድር የመጣው አንደኛ ለቤዛነት (ዓለምን ሁሉ ለማዳን) ሲሆን በሁለተኛ ደረጃ ለአርአያነት ወይም በኑሮአችን እንድንመስለው በተግባር ለማስተማር ነው። ከልደቱ እስከ ሞቱ መላው የክርስቶስ ሕይወቱ ለእኛ አስተማሪ ነው።

« የተጠራችሁለት ለዚህ ነውና፤ ክርስቶስ ደግሞ ፍለጋውን እንድትከተሉ ምሳሌ ትቶላችሁ ስለ እናንተ መከራን ተቀብሎአልና።» ፩ ጴጥ ፪፣፳፩።

ልጆች ለወላጆቻቸው እንዲታዘዙ መጀመሪያ በቃል በ፲ቱ ትዕዛዛት በኋላም ሰው ሆኖ በተግባር እየታዘዘ  አስተማረን - የሕይወት መምህር ኢየሱስ ክርሰቶስ። ይህን በማስታወስ ቅዱስ ጳውሎስ ልጆች ለወላጆች እንዲታዘዙ ይመክራል።

« ልጆች ሆይ፥ ለወላጆቻችሁ በጌታ ታዘዙ፥ ይህ የሚገባ ነውና። መልካም እንዲሆንልህ ዕድሜህም በምድር ላይ እንዲረዝም አባትህንና እናትህን አክብር፤ እርስዋም የተስፋ ቃል ያላት ፊተኛይቱ ትእዛዝ ናት።» ኤፌ ፮፣፩

የአዳም አለመታዘዝ ለሰዎች ሁሉ ሞትን እንዳመጣ የክርስቶስ መታዘዝ ደግሞ ሕይወትን አስገኝቷል። ሮሜ ፭፣ ፲፱ ይመልከቱ።

መታዘዝ የበረከት ብቻ ሳይሆን የሕይወትም ጉዳይ ነው። ክርስቶስ እንደታዘዘ የሕይወትንም መንገድ እንዳመጣ እኛም በእርሱ በማመን፣ እምነታችንንም በመልካም ሥራ በመግለጽ ስንታዘዝ የዘላላም ሕይወትን እናገኛለን።

ሐዋርያት ኢየሱስ ክርስቶስን መጀመሪያ በእግር ቀጥሎም በግብር ተከተሉት ሲባል ሕይወታቸው በሙሉ እርሱን የሚመስል ሆኖ ለእግዚአብሔር በመታዘዝ ኖሩ ማለት ነው። እኛም በክርስቶስ በስሙ ተጠርተን ክርስቲያኖች (የክርስቶስ) ስንባል ሕይወታችንም እርሱን የሚመስል ሊሆን ይገባዋል ማለት ነው።

ለእግዚአብሔር ከምናቀርብለት ከየትኛውም መሥዋዕታችን ይልቅ ለእግዚአብሔር እንደመታዘዝ ያለ ነገር የለም።  

"በውኑ የእግዚአብሔርን ቃል በመስማት ደስ እንደሚለው እግዚአብሔር በሚቃጠልና በሚታረድ መሥዋዕት ደስ ይለዋልን? እነሆ፥ መታዘዝ ከመሥዋዕት፥ ማዳመጥም የአውራ በግ ስብ ከማቅረብ ይበልጣል።"  ፩ሳሙ ፲፭፣፳፪።

በብሉይ ኪዳን ለእግዚአብሔር ይቀርብ የነበረው መሥዋዕት የአውራ በግ፣ ዋኖስ፣…. ነበር። በሐዲስ ኪዳን እነዚህን አናቀርብም፤ የቀረበ አንድ መሥዋዕት አለ። እርሱም የእግዚአብሔር በግ ኢየሱስ ክርስቶስ ነው። እንግዲህ እኛ የምናቀርበው መሥዋዕት ምስጋና ነው። ጸሎትም ወደ እግዚአብሔር እናደርሳለን። ምጽዋት በእግዚአብሔር ስም ለተቸገሩት እንሰጣለን። ወደ እግዚአብሔር ከሚደርሱት ምስጋና፣ ጸሎት፣ ጾም፣ ምጽዋት….ከእነዚህ ሁሉ በላይ/በፊት ለእግዚአብሔር መታዘዝ እንደሚቀድም ቃሉ ያስተምረናል።

እንግዲህ በመጽሐፍ ቅዱስ የሚገኘው የእግዚአብሔር ቃል እያንዳንዳችን አድራሻ ያደረገ የሰማያዊ አባታችን መልእክት ስለሆነ በእምነት ስንቀበለው፣ በተግባርም ስንታዘዘው ያን ጊዜ የበረከቱ ተካፋዮች እንሆናለን። የእግዚአብሔር ቃል ከወተት እስከ አጥንት በተለያየ ደረጃ የሚገኝ በመሆኑ እኛም በመጀመሪያ በመንፈስ ሕጻናት ሆነን የቃሉን ወተት እየተመገብን በእርሱ ስናድግ እየተገለጠልን፣ እየተረዳነው እንመጣለን።

« ከጊዜው የተነሳ አስተማሪዎች ልትሆኑ ሲገባችሁ፥ አንድ ሰው ስለ እግዚአብሔር ቃላት መጀመሪያ ያለውን የሕፃንነትን ትምህርት እንዲያስተምራችሁ እንደ ገና ያስፈልጋችኋልና፤ የሚያስፈልጋችሁም ወተት ነው እንጂ ጠንካራ ምግብ አይደለም። » ዕብ ፭፣፲፪

ቃሉ እንዲሠራብን ከኛ ግንዛቤን ሳይሆን ተግባራዊ ምላሽን  ይፈልጋል። ስለዚህ ለቃሉ እንታዘዝ።

«ቃሉን የምታደርጉ ሁኑ እንጂ ራሳችሁን እያሳታችሁ የምትሰሙ ብቻ አትሁኑ።» ያዕ ፩፣፳፪

ቃሉን ሰምተን እንድንታዘዝ ጸጋውን ያብዛልን!!!


ምንጭ:- abrhamha.blogspot.com




ወደ ቻናሉ ለመ🀄️🀄️ል፦ @Holy_scriptures
5👍4👏1
.    ==❀❀❀===❀❀❀==      
              የዕለቱ ጥቅስ 
     ==❀❀❀===❀❀❀==
“እናንተ ደግሞ እንደ ሕያዋን ድንጋዮች ሆናችሁ፥ በኢየሱስ ክርስቶስ ለእግዚአብሔር ደስ የሚያሰኝ መንፈሳዊ መሥዋዕትን ታቀርቡ ዘንድ ቅዱሳን ካህናት እንድትሆኑ መንፈሳዊ ቤት ለመሆን ተሠሩ።”
1ኛ ጴጥሮስ 2፥5



ወደ ቻናሉ ለመ🀄️🀄️ል፦ @Holy_scriptures
4🔥4👍3
ወደ ቻናሉ ለመ🀄️🀄️ል፦ @Holy_scriptures
ትምህርተ እግዚአብሔር.pdf
18.9 MB
👉ርዕስ፦ ትምህርተ እግዚአብሔር
ጸሐፊ፦ በቄስ ኮሊንስ ማንሰል

ስለ መጽሐፉ፦
አጠቃላይ የነገረ መለኮት ትምህርት
ትምህርተ እግዚአብሔር 1ኛ መጽሐፍ

በውስጡ ያሉ ጥናቶች፦
👉ጥናት 1. ትምህርተ አስተርእዮ
👉ጥናት 2. ትምህርተ ባሕርየ እግዚአብሔር
👉ጥናት 3. ትምህርተ ፍጥረት



ወደ ቻናሉ ለመ🀄️🀄️ል፦ @Holy_scriptures
👍41
በእስራኤል ነገሥታት ታሪክ ብቸኛዋ ሴት ገዢ ንግሥት ማን ናት?
Anonymous Quiz
59%
ሀ. ዲቦራ
5%
ለ. ኢያዔል
19%
ሐ. ጎቶልያ
9%
መ. ቤርሳቤህ
8%
ሠ. አቢግያ
👍4
.    ==❀❀❀===❀❀❀==      
              የዕለቱ ጥቅስ 
     ==❀❀❀===❀❀❀==
“ስለዚህ የተወደዳችሁ ወንድሞቼ ሆይ፤ ጸንታችሁ ቁሙ፤ በምንም ነገር አትናወጡ። ለጌታ ሥራ ዘወትር የምትተጉ ሁኑ፤ ምክንያቱም ለጌታ የምትደክሙት በከንቱ እንዳልሆነ ታውቃላችሁ።”
1ኛ ቆሮንቶስ 15፥58 (አዲሱ መ.ት)




ወደ ቻናሉ ለመ🀄️🀄️ል፦ @Holy_scriptures
👍41
ቅዱሳት መጻሕፍት
ነቢዩ ኤርምያስ                         ክፍል-፭ በኢዮአቄም የዐሥራ አንድ ዓመት ዘመነ መንግሥት ውስጥ የከርከሚሽ ጦርነት ተካሄደ (ከ46 ፥ 2 ጋር ያነጻ)፡፡ በመካከለኛው ምሥራቅ የኀይል ሚዛን ከግብፅ ወደ ባቢሎን መተላለፉን ያመላከተ ስለ ሆነ፣ ዘላቂ ፋይዳ ያለው ሁኔታ (ክሥተት) ነበር፡፡ ይህ ሽንፈት በግብፅ የመስፋፋት ምኞት ላይ የመጨረሻ በትር ሲሆን፤ ከለዳውያን በምዕራቡ…
ነቢዩ ኤርምያስ




                        ክፍል-


ነገር ግን መጨረሻው ሩቅ አልነበረም:: በዘጠነኛው የአገዛዝ ዘመኑ (588)፣ ሴዴቅያስ ከፈርዖን ኡፍራ ጋር ግምባር በመግጠም በናቡከደነፆር ላይ ዐመፀ:: ባቢሎን ይሁዳን በመውረር ምላሽ ሰጥታ በ586 ከተማዋ በእጇ ስትወድቅ ወረራው ፍጻሜ ላይ ደረሰ (2ነገ 36፥17፤ ኤር 38 ፥ 28-39፥ 10)፡፡ በወረራው ዘመን ሁሉ ሴዴቅያስ እጁን ይሰጥ ዘንድ ኤርምያስ አደፋፈረው (21 ፥ 1-10 ፤ 34፥ 1-5፤ 17-22 37 ፥ 3-10፤ 16-17 ፤ 38፥ 14-23)፡፡ በአንድ ወቅት የግብፅ ሰራዊት እየገፋ መምጣት፣ የባቢሎንን ተዋጊ ሰራዊት ያፈገፍግ ዘንድ አስገደደው፤ ይሁን እንጂ ወረራው ተመልሶ ቀጠለ (37 ፥ 1-10)፡፡ በዚህም ጊዜ ሴዴቅያስ ፍርሀት ያደረበት ሰው ስለ ነበር፣ ኤርምያስ በይሁዳ በሚገኙት ጠላቶቹ ግፍ ደረሰበት (37 ፥ 11-21፤ ምዕ 38)፡፡ በዚህ ወቅት ኢየሩሳሌም የወደቀችበት ዕለት፣ በዓለም ዙሪያ በሚገኙ አይሁድ ዘንድ፣ በአቢብ ወር በዘጠነኛው ቀን በሐዘን የሚታሰብ ሲሆን፣ በብሉይ ኪዳን ውስጥ በእስራኤል ላይ ከፍተኛው የእግዚአብሔር ፍርድ ነበር፡፡ ሴዴቅያስ ለማምለጥ ሲሞክር ተያዘ፤ ወንዶች ልጆቹም ዐይኑ እያየ በፊቱ ታረዱ፤ ዐይኑም ወጣ፤ ከዚያም ከተከታዮቹ ጋር ወደ ባቢሎን ተጋዘ፡፡

ከከተማዪቱና ከቤተ መቅደሱ ውድመት በኋላ የባቢሎን ንጉሥ፣ ጎዶልያስን የይሁዳ ገዥ አድርጎ ሾመው፡፡ ከጥቂት ጊዜ በኋላ (በቂ ማስረጃ በሌለበት ሦስት ወር ወይም ጥቂት ዓመታት ሊሆን ይችላል)፣ ጎዶልያስ ከዳዊት ቤት በሆነው ወገን ተገደለ፤ ይህም አፍቃሬ ግብፅ በሆኑት ሰዎች ቀስቃሽነት ሳይፈጸም አልቀረም፡፡ የብርቱው መከራ ሰለባዎች የሆኑት የባቢሎንን የዐመፅ ምላሽ በመፍራት ኤርምያስንና ባሮክን ዐብረዋቸው እንዲሸሹ በማስገደድ ወደ ግብፅ ወረዱ፡፡ ስለዚህ ከምእት ዓመታት በፊት በሙሴ አማካይነት ከፈርዖን ትድግና የተገኘበት ዑደት በዚህ ጊዜ ፍጻሜ ላይ ደረሰ፡፡ ሌላው የሚያስገርመው ጒዳይ ደግሞ በአገልግሎቱ ዘመን ሁሉ በግብፅ ላይ እንዳይታመኑ ሲመክር የነበረው ኤርምያስ ያለፈቃዱ የምድር ሕይወቱን በዚያ እንዲጨርስ መደረጉ ነው፡፡ ስለዚህ በእስራኤል ውስጥ ዐይነተኛ ዘመን የነበረው መለኮታዊ አገዛዝ አከተመ፡፡ በሴሎ የማደሪያው ድንኳን መውደሙም የመሳፍንትን ዘመን ደመደመው፡፡ የሰሎሞን ቤተ መቅደስ መውደም በእስራኤል ዘንድ የንጉሣዊ አገዛዝ ዘመን ማክተሙን አመለከተ፡፡ በቲቶ (ጥጦስ) ዘመን (70 ዓ.ም.) ሁለተኛው ቤተ መቅደስ መውደሙ እስከ ዐዲሱ ዘመን ድረስ እስራኤል በምድሯ ላይ የምትኖርበት ዘመን በአደገኛ ሁኔታ ማክተሙን አመላካች ነበር፡፡

ነገረ መለኮታዊ አጽንዖት

የኤርምያስ መልእክት ጒሉሓን ባሕርያት፣ ለእርሱ ዘመንና ለእኛ ዘመን ዐቢይ ፋይዳ አላቸው፡፡ ኤርምያስ በዕድሜ ዘመኑ ሁሉ የደረሰበትን ሐዘንና ተቃውሞ ለመዝለቅ የበቃው በእግዚአብሔርና እግዚአብሔር በሰጠው ተስፋ ጽኑ እምነት ስለ ነበረው ነው (18+7! 29:14: 32:1-5):: የሕይወቱም የአገልግሎቱም ሁለት ትኲረቶች እግዚአብሔር (ማለት ቸርነቱ፣ በሰው ዘር ላይ ያለው ባለቤትነቱ፣ ንስሓና እምነት እውን ይሆኑ ዘንድ ግድ መሰኘቱ) እና ተንከራታች ሕዝቡ ሲሆኑ፣ ይህም የሥጋዊና የመንፈሳዊ ሕይወታቸውን ደኅንነት ያካትታል፡፡

ኤርምያስ እግዚአብሔር የፍጥረት ሁሉ አምላክ መሆኑን በማመን (27፥5)፣ ስለ እግዚአብሔር ከፍ ያለ ሐሳብ አለው፡፡ የአሕዛብ አማልክት ህልውና የላቸውም (10፥11 (በአራማይስጥ ቋንቋ መጽሐፍ ውስጥ ብቸኛ ጥቅስ ነው)፤ 14 14፥ 22)፡፡ እግዚአብሔር የሰውን ልብ ክፋት ያውቃል (17፥9-10)፤ ይሁን እንጂ በእርሱ ላይ የሚታመኑትን ለመባረክ በመናፈቅ (17 ፥ 7) ሕዝቡን በጥልቅ ይወዳል (31፥1-3)፡፡ የጣዖት አምልኮና ልበ ደንዳናነት እንዲሁም ንስሓ አልባ አገልግሎት በእርሱ ፊት አስጸያፊዎች ናቸው (19:4-6 14፥12)፡፡ እግዚአብሔርን ሕይወት በሌላቸው ጣዖታት ከመወከል የበለጠ በእርሱ ላይ የሚሰነዘር ስድብ የለም፡፡ ኤርምያስ ያለመታከት በመቃወም ስብከት ያቀረበበት ልዩ ኀጢአት የጣዖት አምልኮ ነበር፡፡ ሦስት ዐይነት ሐሰት አስቈጣው፡-

(1) ንስሓ ይገባ ዘንድ የተደረገውን ጥሪ ሁሉ አልቀበልም እያለ ምንም አልሆንም የሚል ዐመፀኛ የሆነ ከንቱ ዋስትና፣

(2) ሕዝቡን በአደገኛ አስተማማኝነት እንዲሸፈኑ ያደረጉ የሐሰት ነቢያት፣

(3) ጣዖታትን በከንቱ ማምለክ፡፡  አምልኮ ለበኣል፣ ለሞሎክና ለሰማይ ንግሥት (ለኢሽታር) ይደረግ ነበር፡፡ የእነዚህ አማልክት ምስል በቤተ መቅደስ ውስጥ ሳይቀር ተቀምጦ ነበር (32፥34፤ ከ7፥31 ፤ ከ19፥5፤ ከ32 ፥ 35፤ ከ44፥18-19)፡፡


ይቀጥላል...


🚨ማሳሰቢያ የጊዜ አቆጣጠር ካልተጠቀሰ በቀር ዓመተ ቅድመ ክርስቶስ ነው።



ምንጭ፦ የብሉይ ኪዳን ማብራሪያ፤ ገጽ 826




ወደ ቻናሉ ለመ🀄️🀄️ል፦ @Holy_scriptures
3👍3👏1