ቅዱሳት መጻሕፍት
7.46K subscribers
1.37K photos
61 videos
332 files
808 links
በዚህ ቻናል

👉ቅዱሳት መጻሕፍት ይጠናሉ::
👉መጽሐፍ ቅዱሳዊ ትምህርቶች ይቀርባሉ::
👉 ለቅዱሳት መጽሐፍት ጥናት የሚያግዙ መጻሕፍት ይለቀቃሉ።

⭐️⭐️⭐️⭐️⭐️

@Holy_scriptures
Download Telegram
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
🔜 Coming soon...

👉ተሐድሶ (Reformation) ምንድነው? መሠረቶቹስ
👉ተሐድሶ ያስፈልጋል ወይስ አያስፈልግም?
👉ተሐድሶ መጽሐፍ ቅዱሳዊ ነው ወይስ በተለምዶ የመጣ?
👉የሉተር ተሐድሶ የክርስቶስን ቤተክርስቲያን ጎዳ ወይስ ጠቀመ?
👉"ፕሮቴስታንት" ማለት ምን ማለት ነው?



ወደ ቻናሉ ለመ🀄️🀄️ል፦ @Holy_scriptures
👍8
#ተሐድሶ


መጽሐፍ ቅዱስ የተሐድሶ (Reformation) መጽሐፍ ነው። ብሉይ ኪዳን በእግዚአብሔር የተፈጠረው ፍጹም ሰው፣ ከመውደቁ የተነሳ፣ ፍጥረተ ዓለሙ በኃጢአትና በሰይጣን ግዞት ውስጥ ያሳለፉትን መራራ፣ ጨላማና ያረጀ የቀድሞ ሕይወት ይወክላል። አዲስ ኪዳን ደግሞ በሰይጣን መታለል ወድቆ  የኃጢአት ግዞተኛ የሆነውን የሰው ልጅና ፍጥረተ ዓለሙን ሊያድስ ትልቅ የሕይወት ዋጋ ስለከፈለው ስለ ኢየሱስ ይተርካል።

ተሐድሶ

👉የሕያውነት ምልክት ነው።
👉የልጅነት ኪዳን ነው።
👉በሰው ድካም የእግዚአብሔር ኃይል
     የሚገለጥበት መንገድ ነው።
👉የእግዚአብሔር ቃል መለወጥ
     ሳይሆን ሰዋዊና እንደ ቃሉ ያልሆኑ
     አደናቃፊ ሰዋዊ ሥርዓት መለወጥ
     ነው።
👉ሰው ያለመቻሉን ለፈጣሪው
     በማሳወቅ ትዕቢቱን የሚሽርበት
     መንገድ ነው።
👉አሮጌ ነገራችን በአዲስ የሚተካበት
     ድንቅ ሂደት ነው።
👉የመክበር እንጂ የመዋረድ ምልክት
     አይደለም።
👉የእግዚአብሔርን ትክክለኛነት የሰውን
     ስህተተኝነት የሚያመለክት ሚዛን
     ነው።

በዓለማችን ላይ ተሐድሶ የማያስፈልጋት የክርስቶስ ቤተክርስቲያን የለችም። ተሐድሶ የብሉይ ኪዳን ቁልፍ ትምህርት ነው። እንደገና ካልተሰራን እንደገና መስራት አንችልም።

ተሐድሶ የሚለው ቃል የግዕዝ ቃል ሲሆን፣ የአለቃ ኪዳነ ወልድ ክፍሌ መዝገበ ቃላት ተሐድሶን በገቢር ግስ (ሐደሰ) ሲፈታው፦ ማደስ፣ መለወጥ፣ ሐዲስ ማድረግ፣ ማጥናት ፣ ማበረታታት፣ መስራት፣ መጠገን፣ በተጨማሪም አዲስ ነገር ማውጣት፣ መፍጠር ነው።

ተሐድሶ የሚለውን የአማርኛ ቃል፣ ኢንግሊዘኛው በሶስት ቃል (Reformation, Renewal, Restoration) በማለት ያብራራል። አንድ በአንድ ስንመለከታቸው፦

፩. Re-formation፦ እንደገና መስራት፣ እንደገና መለወጥ፣ የሚል አንድምታ ሲኖረው፣ በግሪክ ደግሞ “ዳዮርቶሲስ” (Diorthosis) የሚል ቃል ነው። ትርጉሙም የተበላሸውንና የተመሰቃቀለውን ነገር በትክክለኛ ቦታ ሥርዓት አስይዞ ማስቀመጥን፣ ወደ ቀድሞ ይዞቱ መመለስን፣ የቀድሞውን ፈር የለቀቀውን አዲስ ሥርዓት ማስያዝን ያመለክታል።

፪. Re-newal፦ ማደስ፣ የቀድሞውን መልክና ውበት መመለስ፣ የዚህ ቃል መሠረት "አናካይኖ" (Anakaino) የሚል የግሪክ ቃል ሲሆን፣ ትርጉሙም አዲስ ማድረግ ማለት ነው።

፫. Re-storation፦ ወደ ቀድሞ ሥፍራ ወይም ባለቤት መመለስ። ይህ ቃል "አካታስታቶስ" (Akatastatos) ከሚለው የግሪክ ቃል የመጣ ሲሆን፣ ስፍራውን የለቀቀውን፣ የተሰረቀውን፣ የተወሰደውን ወደ ሥፍራው መመለስን ያመለክታል።



🗞ምንጭ፦ ተሐድሶ ቅጽ-1 በጸጋአብ
                    በቀለ ከገጽ 22-27




ወደ ቻናሉ ለመ🀄️🀄️ል፦ @Holy_scriptures
👍7
#ተሐድሶ




የተሐድሶ እና የመነቃቃት ልዩነት (Reformation vs Revival)


መነቃቃት ተሐድሶ አይደለም፤ ተሐድሶም መነቃቃት አይደለም። በተለምዶ ብዙውን ጊዜ እነዚህ ሁለት የተለያዩ ጽንሰ አሳቦች እንደ አንድ አሳብ ሲቀርቡ ይታያሉ። ሁለቱ አሳቦች ተደጋጋፊና ለቤተክርስቲያን እጅግ በጣም አስፈላጊ ሲሆኑ ልዩነታቸውን ማወቅ ግን ግድ ይላል።

👉የመነቃቃትና የተሐድሶ ልዩነት በንጽጽር ቦቢ ግልያም እንዲህ አስቀምጠዋል፦

ቤተክርስቲያን አካል እንደሆነች አስቡ፤ በዚህም መሠረት መነቃቃት ለልብና ለአእምሮ ሕይወትና መታደስን እንደሚያመጣ ነው። ተሐድሶ ደግሞ የአካል አጥንቶችን እንደሚገጣጥም ነው። መነቃቃት የእምነትን፣ እሴቶችንና ውሳኔዎችን ለውጥ ያስገኛል። ተሐድሶ ደግሞ የባህሪ፣ የአወቃቀርና የትጥቅ ለወጥ ያመጣል። መነቃቃት ንጹህ ውሃ ወደ ውሃ ጉድጓድ መጨመር ነው። ተሐድሶ ደግሞ በውሃ ጉድጓድ ላይ ያሉትን ቀዳዳዎች መድፈን ነው። በመነቃቃትና በተሐድሶ መካከል ያለው የመጀመሪያ ልዩነት መነቃቃት በግለሰብ ደረጃ ሊጀምር የሚችል ሲሆን ውጤታማ ተሐድሶ ግን ከላይኛው የሥልጣን መዋቅር፣ ከቤተ ክርስቲያን አመራር ወይም ከአንድ ቤተ እምነት ይጀምራል።


Revival is an ongoing experience in the life of every believer. Since our natures are fallen, the Holy Spirit leads us to spiritual renewal every day. God’s mercies are new every morning (Lam. 3:23). God daily pours out fresh supplies of His grace and power on those who kneel before His throne. Spending time in His presence we are changed. The psalmist cried out, “I am afflicted very much; revive me, O Lord, according to Your word” (Ps. 119:107, NKJV).

Reformation is the outgrowth of revival. New Testament writers used different words to describe reformation. The apostle Paul called it “sanctification by the Spirit” (2 Thess. 2:13). In Romans he described it as being “transformed by the renewing of your mind” (Rom. 12:2). In Hebrews the apostle urged us to be “partakers of His holiness”(Heb. 12:10). Peter encouraged believers to “grow” in grace (2 Peter 3:18). John defined it as practicing “righteousness” (1 John 2:29).

Reformation is simply choosing to allow the Holy Spirit to realign our lives with biblical values; to submit to God’s will in every area of our lives. It is the commitment to please God in everything we do; the willingness to make any change necessary to live in harmony with God’s commands. Ellen White defined revival and reformation this way: “Revival and reformation are two different things. Revival signifies a renewal of spiritual life, a quickening of the powers of mind and heart, a resurrection from spiritual death. Reformation signifies a reorganization, a change in ideas and theories, habits and practices. Reformation will not bring forth the good fruit of righteousness unless it is connected with the revival of the Spirit. Revival and reformation are to do their appointed work, and in doing this work they must blend” (Selected Messages, book 1, p. 128).



ምንጭ፦ ተሐድሶ ቅጽ-1 በጸጋአብ በቀለ ከገጽ 29-33፣ revivalandreformation.org፣ Selected Messages, book 1, p. 128



ወደ ቻናሉ ለመ🀄️🀄️ል፦ @Holy_scriptures
4
.    ==❀❀❀===❀❀❀==      
              የዕለቱ ጥቅስ 
     ==❀❀❀===❀❀❀==
“እንግዲህ ኀጢአታችሁ እንዲደመሰስ ንስሓ ግቡ፤ ከመንገዳችሁም ተመለሱ፤ ከጌታም ዘንድ የመታደስ ዘመን ይመጣላችኋል፤”
ሐዋርያት 3፥19 (አዲሱ መ.ት)




ወደ ቻናሉ ለመ🀄️🀄️ል፦ @Holy_scriptures
🔥6👍2🤯1
፺፭ቱ_የማርቲን_ሉተር_የመከራከሪያ_ነጥቦች.pdf
109.6 KB
ርዕስ፦ "፺፭ቱ የማርቲን ሉተር መከራከሪያ ነጥቦች"




ወደ ቻናሉ ለመ🀄️🀄️ል፦ @Holy_scriptures
👍62
የፕሮቴስታንት ተሐድሶ አምስቱ ምሶሶያት



የፕሮቴስታንት ተሐድሶ መሪዎች ማርቲን ሉተር፣ ጆን ካልቪን፣ ኡልሪች ዝዊንግሊ፣ ጆን ኖክስ በዘመኑ ከነበረችው ከሮም ካቶሊክ ቤተ ክርስቲያን ልዩ የሚያደርጋቸውን አምስት ነገረ መለኮታዊ ቁልፍ የአስተምህሮ ምሶሶያት አስቀምጠዋል። እነዚህ የተሐድሶ ምሶሶያት “አምስቱ ሶላዎች” (Five solas) ተብለው ይታወቃሉ። ሶላ (sola) ማለት የላቲን ቃል ሲሆን ትርጉሙም “ብቻ” ማለት ነው። አምስቱ ብቻዎች የተባሉት፦

፩. ለድነት መጽሐፍ ቅዱስ ብቻ “Sola Scriptura,” or “Scripture Alone”.

መጽሐፍ ቅዱስ የእግዚአብሔር ቃል ነው። “እግዚአብሔር እንዲህ ይላል” የሚልና ተመሳሳይ ዓረፍተ ነገር በብሉይ ኪዳን 3,808 ጊዜ ተጠቅሷል። በፔንታቱክ 700 ጊዜ፣ በታሪክ መጽሐፍት 400 በኢሳይያስ ብቻ 150 ጊዜ፣ በሕዝቅኤል 350 የተጻፈ ሲሆን ይህም የቃሉ ምንጭና ባለቤት እግዚአብሔር እንደሆነ ያመለክታል።

በቤተ ክርስቲያን ያለው ልምምድ፣ አስተምህሮና ማንኛውም ሥርዓት በመጽሐፍ ቅዱስ ብቻ ይዳኛል፣ ይመራል፣ ይገመገማል፣ ይታረማል፣ የሚል ሲሆን ማርቲን ሉተር በአንድ ወቅት ፍርድ ቤት ቀርቦ አቋሙን እንዲለውጥ ሲጠየቅ፦ “መጽሐፍ ቅዱስና ሕሊናዬ መሳሳቴን ካልገለጡልኝ በስተቀር የሮም ጳጳስና አማካሪዎቹን ትምህርት አልቀበልም፤ እርስ በእርሳቸው ይጣረሳሉና። አእምሮዬና ልቤ ለእግዚአብሔር ቃል እሥረኞች ናቸው። የሕሊናዬ ተቃዋሚ ሆኜ መሰለፍ አይሆንልኝም። ከዚህች አቋሜ ፍንክች አልልም። እግዚአብሔር ይርዳኝ። አሜን" ብሏል::

፪. ድነት በጸጋ ብቻ “Sola Gratia,” or “Salivation by Grace Alone”.

“ጸጋው በእምነት አድኖአችኋልና ይህም የእግዚአብሔር ሥጦታ ነው እንጂ ከእናንተ አይደለም፤ ማንም እንዳይመካ ከሥራ አይደለም” (ኤፌ. 2፡8)።

“ሰዎችን ሁሉ የሚያድን የእግዚአብሔር ጸጋ ተገልጦአልና“ (ቲቶ 2፡11)።

“ጸጋ” የሚለው ቃል በፕሮቴስታንት አብያተ ክርስቲያናት ዘንድ ወሳኝ ጥቅልና ሰፊ ጽንሰ አሳብ ያዘለ ቃል ነው። ብዙ ሰዎችም በተሳሳተ መንገድ የሚረዱት ቃል ነው። ጸጋን ከአንደበት ይልቅ ተቀብለን ስንኖርበት እናውቀዋለን። ጸጋን ከኢየሱስ ክርስቶስ ነጥለን ማየት አንችልም። የሚያድን ጸጋ የተገለጠው በኢየሱስ ክርስቶስ እንደሆነ ሐዋሪያው ዮሐንስ በአራተኛው ወንጌል መግቢያ ላይ ጠቅሶታል “ሕግ በሙሴ ተሰጥቶን ነበርና ጸጋና እውነት ግን በኢየሱስ ክርስቶስ ሆነ” (ዮሐ. 1፡17)። ሐዋሪያው ጳውሎስ ከዮሐንስ በላይ በጸጋ አስተምህሮ ላይ ልዩ ትኩረት መስጠቱን ስንመለከት የፕሮቴስታንት አብያተ ክርስቲያናትም በጸጋ ላይ የተለየ ትኩረት ቢሰጡ አያስደንቅም።

“በክርስቶስ ኢየሱስ ስላመናችሁ በተሰጣችሁ በእግዚአብሔር ጸጋ ምክንያት ሁልጊዜ ስለ እናንተ አምላክን አመሰግናለሁ፤” (1ቆሮ. 1፡4)

“ነገር ግን በእግዚአብሔር ጸጋ የሆንሁ እኔ ነኝ፤ ለእኔም የተሰጠኝ ጸጋው ከንቱ አልነበረም ከሁላቸው ይልቅ ግን ደከምሁ፥ ዳሩ ግን ከእኔ ጋር ያለው የእግዚአብሔር ጸጋ ነው እንጂ እኔ አይደለሁም።” (1ቆሮ.15፡10)

“የጌታ የኢየሱስ ክርስቶስ ጸጋ የእግዚአብሔርም ፍቅር የመንፈስ ቅዱስም ኅብረት ከሁላችሁ ጋር ይሁን። አሜን።” (2ቆሮ. 13፡14)


ይቀጥላል...


ምንጭ፦ "ተሐድሶ" ቅጽ-1፤ በጸጋአብ በቀለ፤ ከገጽ 230-243





ወደ ቻናሉ ለመ🀄️🀄️ል፦ @Holy_scriptures
👍121
"ጻድቅ በእምነት ይኖራል" የሚለው ጥቅስ የት ይገኛል?
Anonymous Quiz
52%
ሀ. ሮሜ
14%
ለ. ገላትያ
18%
ሐ. ዕብራውያን
16%
መ. ሁሉም
👍9
.    ==❀❀❀===❀❀❀==      
              የዕለቱ ጥቅስ 
     ==❀❀❀===❀❀❀==
“የእግዚአብሔርን ጸጋ አልጥልም፤ ጽድቅስ በሕግ በኩል ከሆነ እንኪያስ ክርስቶስ በከንቱ ሞተ።”
ገላትያ 2፥21




ወደ ቻናሉ ለመ🀄️🀄️ል፦ @Holy_scriptures
👍5
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
ቅዱሳት መጻሕፍት
የፕሮቴስታንት ተሐድሶ አምስቱ ምሶሶያት የፕሮቴስታንት ተሐድሶ መሪዎች ማርቲን ሉተር፣ ጆን ካልቪን፣ ኡልሪች ዝዊንግሊ፣ ጆን ኖክስ በዘመኑ ከነበረችው ከሮም ካቶሊክ ቤተ ክርስቲያን ልዩ የሚያደርጋቸውን አምስት ነገረ መለኮታዊ ቁልፍ የአስተምህሮ ምሶሶያት አስቀምጠዋል። እነዚህ የተሐድሶ ምሶሶያት “አምስቱ ሶላዎች” (Five solas) ተብለው ይታወቃሉ። ሶላ (sola) ማለት የላቲን ቃል ሲሆን ትርጉሙም…
የቀጠለ...



፫. ድነት በእምነት ብቻ “Sola Fide,”
“Salivation by Faith Alone”


ለጸጋ ያለን ምላሽ እምነት ነው። እምነት እጅግ ቀላል የሚመስል ከባድ ነገር ነው። እምነት ከባድ ያደረገው ለማመን አስቸጋሪ የሆነውን ነገር እንድናምን እኛን መጠየቁ ነው። በአዲስ ኪዳን ውስጥ 150 ጊዜ ኃጢአተኛ ድነት የሚያገኘው በእምነት ብቻ እንደሆነ ተገልጿል። የሰውን ነፍስ ማዳን የሚችለው እግዚአብሔር ብቻ ሲሆን ይህን እውን የሚያደርገው ሰዎች በልጁ የመስቀል ሥራ ሲያምኑ ብቻ ነው። እምነት ሥራ ሳይሆን በጌታ በኢየሱስ ክርስቶስ ሥራ ሙሉ በሙሉ መደገፍ ማለት ነው።

በሮማን ካቶሊክ ቤተ ክርስቲያን ድነት ሂደት ነው። ድነት በኢየሱስ ክርስቶስ ባለን እምነት፣ በሥራና ቅዱስ ሚስጢራትን በመፈጸም እንደሚገኝ ያምናሉ። እምነትና ሥራም ለድነት አስፈላጊነታቸው ላይ ያሰምራሉ። ማርቲን ሉተር ሲናገር፦ “እምነትና ሥራ እንደ እሳትና ሙቀት የማይለያዩ ቢሆኑም ለነፍስ ድነት በክርስቶስ እናምናለን እንጂ ለመዳን መልካም ሥራ አንሰራም። እምነትና ሥራ አንድ ባይሆኑም በፍጹም ማለያየት አይቻልም፤ መልካም ሥራ እምነታችንን የማይከተል ከሆነ የሚያድን እምነት እንደሌለን ያመለክታል። የዳነው በእምነት ብቻ ነው፤ ነገር ግን ብቻውን በሆነ እምነት ግን አይደለም። ያለ ሥራ እምነት ሙት ነውና (ያዕ. 2፡17-20)። እንደዚሁም ሥራ የእምነት ውጤት እንጂ እምነት የሥራ ውጤት አይደለም። መልካም ሥራ የመዳናችን መሠረት ሳይሆን ማስረጃ ነው (ኤፌ. 2፡10)። መልካም ሥራ የመዳናችን ምልክት እንጂ ምክንያት አይደለም። ስለዚህ ለመዳን እናምናለን እንጂ አንሠራም፤” ብሏል።

ድነት ነጻ ስጦታ ነው። ድነት በጾምና ጸሎት፣ ለደሃ በመወጽወት፣ በባሕታዊነት፣ ራስን በማጎሳቆል፣ በመገርጣትና በመራብ፣ በተዝካር ድግስ፣ አማላጆችና ቅዱሳን በተባሉ ልዩ ሰዎች መካከለኛነት፣ በቤተ ክርስቲያን አባልነት ሳይሆን በኢየሱስ ክርስቶስ በመስቀል ሥራ በማመን ብቻ ነው።

#እምነት_ምንድነው? ለሚለው ቃሉ መልስ አለው፦ “እምነት ተስፋ ስለምናደርገው ነገር የሚያስረግጠን የማናየውንም ነገር የሚያስረዳን ነው” (ዕብ. 11፡1)። በዚህ ክፍል ስለ መጽሐፍ ቅዱሳዊ እምነት የሚያስረዱን ሁለት ቁልፍ ቃሎች “ማስረገጥ” እና “ማስረዳት” የሚሉት ናቸው። ማስረገጥ ማለት፦ “ምርኩዝ መሆን” “መደገፍ” ማለት ነው። እምነት ለድነታችን እንደ ጠንካራ ምርኩዝ በክርስቶስ እንድንደገፍ ይረዳናል። ሁለተኛው ቃል “ማስረዳት” የሚል ሲሆን ይህም እምነት አንድ ግልጽ ያልሆነውን ነገር የመረዳት አቅም እንደሚሰጠን ያመለክታል።

“በእርሱ የሚያምን ሁሉ የዘላለም ሕይወት እንዲኖረው እንጂ እንዳይጠፋ እግዚአብሔር አንድያ ልጁን እስኪሰጥ ድረስ ዓለሙን እንዲሁ ወዶአልና።” (ዮሐ. 3፡16)

፬. ድነት በኢየሱስ ክርስቶስ ብቻ “Solus Christus,” “In Christ Alone”

“እንግዲህ በክርስቶስ ኢየሱስ ላሉት አሁን ኵነኔ የለባቸውም።” (ሮሜ. 8፡1) ኃጢአት የሌለበት ፍጹም ጽድቅና ቅዱስ የእግዚአብሔር ልጅ ኢየሱስ ክርስቶስ በሰው ልጆች ሁሉ ምትክ መሞቱና መነሳቱ ከአብ ጋር መታረቅ ሆኖልናል። ኢየሱስ ክርስቶስ በሞቱ ለብዙዎች ቤዛ እንደ ሆነ ተናግሯል። ስለዚህ ድነት በእርሱ ብቻ ነው።

“ኢየሱስም፦ እኔ መንገድና እውነት ሕይወትም ነኝ፤ በእኔ በቀር ወደ አብ የሚመጣ የለም።” (ዮሐ. 14፡6)

“የዘላለም ሕይወት እንዳላችሁ ታውቁ ዘንድ በእግዚአብሔር ልጅ ስም ለምታምኑ ይህን ጽፌላችኋለሁ።” (1ዮሐ. 5፡13)

“መጽሐፉን ትወስድ ዘንድ ማኅተሞቹንም ትፈታ ዘንድ ይገባሃል፥ ታርደሃልና፥ በደምህም ለእግዚአብሔር ከነገድ ሁሉ ከቋንቋም ሁሉ ከወገንም ሁሉ ከሕዝብም ሁሉ ሰዎችን ዋጅተህ ለአምላካችን መንግሥትና ካህናት ይሆኑ ዘንድ አደረግሃቸው፥ በምድርም ላይ ይነግሣሉ እያሉ አዲስን ቅኔ ይዘምራሉ።” (ራዕ. 5፡9-10)

፭. ለእግዚአብሔር ክብር ብቻ “Soli Deo Gloria,” “For the Glory of God Alone”

የዳንነው በእግዚአብሔር ኃይል ለእግዚአብሔር ክብር ብቻ እንደሆነ በማወቅ በእርሱ ፊት በእውነተኛ ቅድስናና አምልኮ መኖር ይገባናል። በእግዚአብሔር ፊት፣ በእግዚአብሔር ሥልጣን ሥር ለእግዚአብሔር ክብር ብቻ መኖር አለብን።

“የእግዚአብሔርንም መሠዊያ ደግሞ አደሰ፥ የደኅንነትና የምስጋናም መሥዋዕት ሠዋበት ይሁዳም የእስራኤልን አምላክ እግዚአብሔርን እንዲያመልኩ አዘዘ። ሕዝቡ ግን ገና በኮረብታው መስገጃዎች ይሠዋ ነበር ቢሆንም ለአምላኩ ለእግዚአብሔር ብቻ ነበር።” (2ዜና 33፡16-17)



ምንጭ፦ "ተሐድሶ" ቅጽ-1 በጸጋአብ በቀለ ከገጽ 243-248
       



ወደ ቻናሉ ለመ🀄️🀄️ል፦ @Holy_scriptures
👍105🔥1
መግቢያ በቃሉ ብቻ.pdf
3.3 MB
ርዕስ፦ ቅዱሳት መጻሕፍት ብቻ (ቃሉ ብቻ)
ብራና ሴሚናር 2016፣ ወደ ተነሳንበት መመለስ፣ የተሐድሷውያን አምስቱ "ብቻዎች"


ወደ ቻናሉ ለመ🀄️🀄️ል፦ @Holy_scriptures
7🔥2👍1👏1
በእምነት ብቻ.pdf
2.1 MB
ርዕስ፦ በእምነት ብቻ
ብራና ሴሚናር 2016፣ ወደ ተነሳንበት መመለስ፣ የተሐድሷውያን አምስቱ "ብቻዎች"


ወደ ቻናሉ ለመ🀄️🀄️ል፦ @Holy_scriptures
6🔥1👏1
በክርስቶስ ብቻ.pdf
2.3 MB
ርዕስ፦ ክርስቶስ ብቻ
ብራና ሴሚናር 2016፣ ወደ ተነሳንበት መመለስ፣ የተሐድሷውያን አምስቱ "ብቻዎች"


ወደ ቻናሉ ለመ🀄️🀄️ል፦ @Holy_scriptures
9🔥1👏1
በጸጋ ብቻ.pdf
2.2 MB
ርዕስ፦ በጸጋ ብቻ
ብራና ሴሚናር 2016፣ ወደ ተነሳንበት መመለስ፣ የተሐድሷውያን አምስቱ "ብቻዎች"


ወደ ቻናሉ ለመ🀄️🀄️ል፦ @Holy_scriptures
8🔥1👏1
ክብር ለእግዚአብሔር ብቻ.pdf
1.6 MB
ርዕስ፦ ክብር ለእግዚአብሔር ብቻ
ብራና ሴሚናር 2016፣ ወደ ተነሳንበት መመለስ፣ የተሐድሷውያን አምስቱ "ብቻዎች"


ወደ ቻናሉ ለመ🀄️🀄️ል፦ @Holy_scriptures
9🔥2👍1👏1
.    ==❀❀❀===❀❀❀==      
              የዕለቱ ጥቅስ 
     ==❀❀❀===❀❀❀==
“ስለዚህ፥ የተወደዳችሁ ወንድሞቼ ሆይ፥ ሰው ሁሉ ለመስማት የፈጠነ ለመናገርም የዘገየ ለቍጣም የዘገየ ይሁን፤”
ያዕቆብ 1፥19



ወደ ቻናሉ ለመ🀄️🀄️ል፦ @Holy_scriptures
👍83
ሃይማኖትስ ይታደሳል?
      


ክርስትና በአስተርእዮተ እግዚአብሔር ላይ የተመሰረተ እምነት ነው (ለምሳሌ ዮሐ. 1፥18፤ ገላ. 2፥2)። ጌታ እግዚአብሔር በዘመናት ሁሉ የገለጠው እውነትና የሰጣቸው ተስፋዎች ሁሉ ፍጻሜም ነው። በክርስቶስ መገለጥ ያልተፈጸመ ምንም የለም፤ "በእግዚአብሔር የተሰጡ ተስፋዎች ሁሉ 'አዎን' የሚኾኑት በእርሱ ነውና" (2ቆሮ. 1፥20 ዐ.መ.ት)። በእግዚአብሔር ልጅ በጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ አማካይነት የመጣው አስተርእዮ የቀዳሚዎቹ ፍጻሜ ብቻ ሳይኾን፣ የመጨረሻውና ከሁሉ በላይ የላቀ መገለጥ ነው (ዕብ. 1)። እንግዲህ ይህ መገለጥና እምነት እውነተኛ ፍጹም ቢኾንም፣ እኛ ሰዎች በምንሰጠው ምላሽና ተግባር ላይ ግን ጉድለት ሊከሠት መቻሉ እውነት ነው፤ የሰው ልጅ መሳሳቱ አይቀርም። የመታረሙና መታደሱ አስፈላጊነትም የሚመነጨው ከዚሁ የሰው ድካም ውስጥ ነው።

የሰው ልጅ እውነተኛን እምነት በመበረዝ በኑፋቄ ጮረቃ ሲያልኮሰኩሰው እግዚአብሔር በተሐድሶ ውሃ ያጠራዋል። በዚያን ጊዜ ምርቱን ከግርዱ መለየት ይኖራል። ፍሬውን ከገለባው ማበጠር ይከተላል። ለዚህም ዐላማ ሲል እግዚአብሔር በምሕረቱ የተሐድሶ ነፋስ ያነፍስበታል። በዚህ ማጥራትና ማንፈስ ሂደት ደግሞ የሚሠራ ብቻ ሳይኾን የሚፈርስ የቁሻሻ ክምር ይኖራል። ይህን መሳይ ታላቅ ተግባር ለማከናወን ብሩህ አእምሮ የታደሉ ዐዳሾች ያስፈልጋሉ ማለት ነው። ፕሮፌሰር ጌታቸው ኃይሌ እንዳሉት፣ "አሕይዎና ተሐድሶ (Revival and Renewal or Reformation) ተደላድሎና ተመቻችቶ በተቀመጠ ሥርዐት (Establishement) ውስጥ የዛገና የሚራገፍ ነገር የሚያይ የአእምሮ ችሎታና የተፈጥሮ ተሰጥዎ ካላቸው ታላላቅ ሰዎች ዘንድ የሚመጡ ሐሳቦች ናቸው።"

ስለዚህ ሃይማኖትም ቢኾን "በዛገና በሚራገፍ ነገር" ብልሽት ከገጠመው ይታደሳል። እግዚአብሔር ራሱ አሮጌውን በዐዲሱ ዐድሷል። አሮጌውን በዐዲሱ ሰው ተክቶታል (ኤፌ. 4፥24፤ ቆላ. 3፥10)። ነቀፋ የተገኘበትን ፊተኛውን ኪዳን  (ኤር. 31፥ 31-34) ለዐዲሱ ስፍራ አስለቅቆታል (ዕብ. 8፥6-7)። ስለዚህም፣ "ዐዲስ በማለቱ ፊተኛውን አስረጅቶአል፤ አሮጌውና ውራጅ የሆነውስ ሊጠፋ ቀርቦአል" (ዕብ.8፥13) የተባለው ቃል ተጻፈ። አዎን! ሃይማኖትም ቢኾን ቅይጥነት ሲገዳደረው፣ አደፋ ሲጠናወተው መለኮተ መድኀኒት ያዝዝለታል።

"ማፍረስም መስራት ነው" ከሚለው ጽሁፍ የተቀነጨቡ ሃሳቦች

ከእግዚአብሔር የተቀበልናቸውን ጠቃሚ ሀብታት አንድም በማበላሸት ካቆሸሽናቸው፣ ደግሞም ለእርሱ ክብር ከማድረግ ይልቅ ለሥጋዊ ትምክሕትና ሌላውን ወገን ለማክፋፋት ካዋልናቸው ዐላማቸውን ስተዋልና የተሐድሶ ነፋስ ያሻቸዋል። 

መጽሐፍ ቅዱሳችን ራሱ የተሐድሶ መጽሐፍ ነው።  እግዚአብሔር በታሪከ ድነት ውስጥ ያቆመው ዋነኛ መርሕም የተሐድሶ ምልሰት ነው።      

ቅዱሱን መጽሐፍ የልብ ዐይኖቻችን ተከፍተውልን ካነበብነው ተሐድሶን እንናፍቀው እንደኾነ እንጂ እናክፋፋው ዘንድ ዐቅም አይኖረንም። ይህም[በክርስቶስ የሆነው ድነት] በእግዚአብሔር ምሕረትና ጸጋ አማካይነት ወደ ቀደመው ክብር፣ ጸጋና ቦታ የመመለስና የመታደስ ወንጌል ነው። ከውድቀት በኃላ ለአዳም የተሰጠው ያ ተስፋ ቤዝዎታዊ ተሐድሶ ነበር።     

ተሐድሶን ለማምጣትና ወደ እውነቱ ለመመለስ ሲባል የሐሰት ትምህርት ላይ መጨከን ግዴታ ነው እንጂ፣ አማራጭ አልነበረም፤ ዛሬም ሊሆን አይችልም።

"ልዩ ወንጌል" ወደ ቤተ እግዚአብሔር ሲያቀና እንቢ ማለትና አዋኪዎች ያስገቡትን ኑፋቄና የአጋንንት ትምህርት ማፍረስ ተሐድሶ ነው። ይህ ሊኮነን ሳይኾን ሊወደስ የሚገባው ዘመቻ ነው። ጥያቄው ለምን፣ መቼ፣ የት፣ ምንና እንዴት ይታደስ የሚለው እንጂ "ዝንቡ እሽ የሚባል የለም" ብሎ ማፍጠጥ መፍትሔ አይኾንም። በደፈናው "ሃይማኖት አይታደስም" እያልን ከማገንገን፣ ለምን እንደማይታደስ ብናስረዳ ጥሩ ነበር። ጌታ ኢየሱስ አዳሽ አልነበረምን? ሐዋርያቱስ? የአሮጌው መነካት ባይመቸንም እንኳ፣ ለተሻለው ስፍራ እንዲለቅ ውራጅ የኾነው ትምህርትና ልምምድ ይፈርሳል።

ማንኛውንም ነገር በደባልነት ደርበን ለማምለክ ብንሞክር፣ ይህ ብክለት ነውና ሃይማኖት ይታደሳል። ማንኛውም ነገር ከመለኮታዊው አስተምህሮ በተፃሮ ሲቆም፣ ወይም ቅይጥነት ሲዳበለው ተሐድሶ ያስፈልጋል። የእግዚአብሔር ሰው ነኝ የሚል ሁሉ አምልኮተ ባዕድን፣ ርኩሰትን፣ ጥንቆላን፣ ኑፋቄን። በወንጌል ስም መነገድን፣ ወዘተ. ማፍረስ ግድ ይለዋል። በእግዚአብሔር ከተሰጠው መመሪያ ውጭ በሰው የተገነቡ መሠዊያዎች እስከሚሰነጠቁና ዐመዳቸው እስከሚፈስ ድረስ ቢሰነጣጠቁ እንደነቃለንን(1ነገ. 13)?     



ምንጭ፦ ሰሎሞን  አበበ ገብረ መድሕን፤ የትሩፋን ናፍቆት፣ ማፍረስም መስራት ነው፣ ጌታቸው ኃይሌ ፤ ደቂቀ እስጢፋኖስ:- በሕግ አምላክ




ወደ ቻናሉ ለመ🀄️🀄️ል፦ @Holy_scriptures
6👍5🥰1
.    ==❀❀❀===❀❀❀==      
              የዕለቱ ጥቅስ 
     ==❀❀❀===❀❀❀==
“ንቁ፥ በሃይማኖት ቁሙ፥ ጎልምሱ ጠንክሩ።”
1ኛ ቆሮንቶስ 16፥13



ወደ ቻናሉ ለመ🀄️🀄️ል፦ @Holy_scriptures
👍52🔥2
ወደ ቻናሉ ለመ🀄️🀄️ል፦ @Holy_scriptures
2
የኢትዮጵያ ቤተክርስቲያን ተሐድሶ.pdf
11.1 MB
👉ርዕስ፦ የኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያን ተሐድሶ፣ ቅጽ 1፣ ሳታድግ ያረጀች የኢትዮጵያ ቤተክርስቲያን
ጸሐፊ፦ ወ/ዊ ጸጋአብ በቀለ
🗓 የታተመበት ዓመት፦ 2006 ዓ.ም


ወደ ቻናሉ ለመ🀄️🀄️ል፦ @Holy_scriptures
6👍6👎1