ቅዱሳት መጻሕፍት
7.46K subscribers
1.36K photos
61 videos
332 files
806 links
በዚህ ቻናል

👉ቅዱሳት መጻሕፍት ይጠናሉ::
👉መጽሐፍ ቅዱሳዊ ትምህርቶች ይቀርባሉ::
👉 ለቅዱሳት መጽሐፍት ጥናት የሚያግዙ መጻሕፍት ይለቀቃሉ።

⭐️⭐️⭐️⭐️⭐️

@Holy_scriptures
Download Telegram
#እራሳችንን_እንመርምር


እኔምለው ከእግዚአብሔር ቃል ጋር እየተዋለ፣ ቃሉ እንዴት ይሆን እየተባለ ቃሉ ሳያውቁ መኖር ይቻላል እንዴ? ምንስ ቢሆን ነው እንደዚህ ባለማወቅ ጨለማ ውስጥ የሚኖረው?


“ካህናቱም። እግዚአብሔር ወዴት አለ? አላሉም፥ ባለ ኦሪቶችም አላወቁኝም ገዢዎችም ዐመፁብኝ፥ ነቢያትም በበኣል ትንቢት ተናገሩ፥ የማይረባንም ነገር ተከተሉ።”
ኤርምያስ 2፥8




ወደ ቻናሉ ለመ🀄️🀄️ል፦ @Holy_scriptures
👍6
.    ==❀❀❀===❀❀❀==      
              የዕለቱ ጥቅስ 
     ==❀❀❀===❀❀❀==
“ነገር ግን በጌታችንና በመድኃኒታችን በኢየሱስ ክርስቶስ ጸጋና እውቀት እደጉ። ለእርሱ አሁንም እስከ ዘላለምም ቀን ድረስ ክብር ይሁን፤ አሜን።”
2ኛ ጴጥሮስ 3፥18




ወደ ቻናሉ ለመ🀄️🀄️ል፦ @Holy_scriptures
👍42
በእግዚአብሄር ቃል የመኖር አምስቱ ደረጃዎች



በእውነት ፍሬያማ ለመሆን በክርስቶስ መኖር ግድ ነው፡፡ የፍሬያማነታችን ልክ በክርስቶስ የመኖራችን ልክ ብቻ ነው፡፡ በኢየሱስ መኖር ደግሞ በቃሉ መኖር ነው፡፡ በእግዚአብሄር ቃል የመኖር አምስቱን ደረጃዎች ከመፅሃፍ ቅዱስ እንመልከት፡፡

1. የእግዚአብሄርን ቃል መስማት

በቃል የመኖር የመጀመሪያው ደረጃ የእግዚአብሄርን ቃል መስማት ነው፡፡ ካለ እግዚአብሄር ቃል መስማት ፍሬያማነት የማይታሰብ ነው፡፡ የፍሬማነታችን ቁልፍ በቃሉ መኖር ነው፡፡ ስለዚህ ቃሉም ለመስማት ራሳችንን ልንሰጥ ይገባል፡፡ ቃሉን መስማት ሁኔታዎችን ማመቻቸት አለብን፡፡ በአሁኑ ጊዜ በተለይ በአሁኑ ጊዜ መፅሃፍ ቅዱስ በኰምፒተር በታብሌት በስልካችን በፅሁፍና በድምፅ እናገኘዋለን፡፡ በቤታችን ቴፕ ውስጥ ከፍተነው ማዳመጥ እንችላለን፡፡ መኪና ስንነዳና ወረፋ ስንጠብቅ ቃሉን መስማት እንችላለን፡፡

"እንግዲያስ እምነት ከመስማት ነው መስማትም በእግዚአብሔር ቃል ነው።" (ሮሜ 10፡17)

2. ለእግዚአብሄርን ቃል የመጀመሪያውን ስፍራ መስጠት

ፍሬያማ የሚያደርገን ቃሉ እንደመሆናችን መጠን ጠላትም የሚመጣው ቃሉን ሊነጥቅ ነው፡፡ ቃሉን ከሰረቀ ህይወታቸንን ይሰርቃል ቃሉን ከጠበቅን ህይወታቸነ በደህንነት የጠበቃል፡፡ ሰይጣን ቃሉን መስረቅ ካልቻለ ምንም ነገራችንን መስረቅ አይችልም፡፡

"የመንግሥትን ቃል ሰምቶ በማያስተውል ሁሉ፥ ክፉው ይመጣል፥ በልቡ የተዘራውንም ይነጥቃል፤ በመንገድ ዳር የተዘራው ይህ ነው።" (ማቴዎስ 13፡19)

ሰው ውድ የሆነ ነገሩን እጅግ ውስጠኛው ቦታ ያስቀምጠዋል እንጂ ውጭ አይተወውም፡፡ እንዲሁ የእግዚአብሄርን ቃል የመጀመሪያውንም ስፍራ ልባችንን ልንሰጠው ይገባል፡፡ የእግዚአብሄርን ቃል ለመሰረቅ በማይመች በውስጠኛው የህይወታችን ክፍል ውስጥ ልናደርገውና በልባችን ልንሰውረው እና ልንሸሽገው ይገባል፡፡

"ከእርሱም ይልቅ እጅግ የጸና የትንቢት ቃል አለን፤ ምድርም እስኪጠባ ድረስ የንጋትም ኮከብ በልባችሁ እስኪወጣ ድረስ፥ ሰው በጨለማ ስፍራ የሚበራን መብራት እንደሚጠነቀቅ ይህን ቃል እየጠነቀቃችሁ መልካም ታደርጋላችሁ።"
(2ኛ ጴጥሮስ 1፡19)

"በፍጹም ልቤ ፈለግሁህ፥ ከትእዛዝህ አታርቀኝ። አንተን እንዳልበድል፥ ቃልህን በልቤ ሰወርሁ።" (መዝሙር 119፡10-11)

3. የእግዚአብሄርን ቃል ማሰላሰል

የእግዚአብሄርን ቃል ለመታተዘዝ ያስችለን ዘንድ በቃሉ ከባቢ ውስጥ ለመገኘት የእግዚአብሄርን ቃል ማሰብና ማሰላሰል ወሳኝ ነው፡፡ ቃሉን ስናሰላስል ቃሉን እናስታውሳለን፡፡ ቃሉን ስናሰላስል ቃሉን ለማድረግ ሃይል እናገኛለን፡፡

"የዚህ ሕግ መጽሐፍ ከአፍህ አይለይ፥ ነገር ግን የተጻፈበትን ሁሉ ትጠብቅና ታደርግ ዘንድ በቀንም በሌሊትም አስበው፤ የዚያን ጊዜም መንገድህ ይቀናልሃል ይከናወንልሃልም።" (ኢያሱ 1፡8)

"በቀረውስ፥ ወንድሞች ሆይ፥ እውነተኛ የሆነውን ነገር ሁሉ፥ ጭምትነት ያለበትን ነገር ሁሉ፥ ጽድቅ የሆነውን ነገር ሁሉ፥ ንጹሕ የሆነውን ነገር ሁሉ፥ ፍቅር ያለበትን ነገር ሁሉ፥ መልካም ወሬ ያለበትን ነገር ሁሉ፥ በጎነት ቢሆን ምስጋናም ቢሆን፥ እነዚህን አስቡ፤"  (ፊልጵስዩስ 4፡8)

4. የእግዚአብሄርን ቃል መናገር

ሌላው የእግዚአብሄርን ቃል የምናደርግበት መንገድ የእግዚአብሄርን ቃል መናገር ነው፡፡ ንግግራችን እንደ እግዚአብሄር ቃል መሆን አለበት፡፡

"እውነት እላችኋለሁ፥ ማንም ያለው ነገር እንዲደረግለት ቢያምን በልቡ ሳይጠራጠር፥ ይህን ተራራ፦ ተነቅለህ ወደ ባሕር ተወርወር ቢል ይሆንለታል።" (ማርቆስ 11፡23)

5. የእግዚአብሄርን ቃል ማድረግ

"ነገር ግን ነጻ የሚያወጣውን ፍጹሙን ሕግ ተመልክቶ የሚጸናበት፥ ሥራንም የሚሠራ እንጂ ሰምቶ የሚረሳ ያልሆነው፥ በሥራው የተባረከ ይሆናል።" (ያዕቆብ 1፡25)



ምንጭ :- አብይ ዋቁማ




ወደ ቻናሉ ለመ🀄️🀄️ል፦ @Holy_scriptures
9👍6🔥5🥰2👎1
.    ==❀❀❀===❀❀❀==      
              የዕለቱ ጥቅስ 
     ==❀❀❀===❀❀❀==
“በጽድቅ የሚጸና በሕይወት ይኖራል፤ ክፋትን የሚከተል ግን ለሞቱ ነው።”
ምሳሌ 11፥19




ወደ ቻናሉ ለመ🀄️🀄️ል፦ @Holy_scriptures
3👍2👏1
#ከተማ_ወይም_ቦታ_በቅዱሳት_መጻሕፍት



#ቤትአዌን

ቤት-አዌን(በዕብራይስጥ ቤይት አቨን፣ בֵּית אָוֶן፣ የከንቱነት ቤት፣ ማለትም የክፋት፣ ጣዖት አምልኮ ቤት። በብንያም ተራሮች በቤቴል በስተምስራቅ የሚገኝ ቦታ ነው። 1ሳሙ 13፡5፣ በኢያሱ 18፡12 ላይ የቤተ-አዌን “ምድረ በዳ” (ሚድባር = የግጦሽ መሬት) በሚል ተጠቅሷል። በሆሴዕ 4:15፣ ሆሴዕ 5:8፣ ሆሴዕ 10፡5፣ ስሙ በዚህ ነቢይ በተገለጸው ቃል መሠረት ወደ አጎራባች ቤቴል - አንድ ጊዜ “የእግዚአብሔር ቤት” ወደ ነበረው፣ ከዚያ በኋላ ግን “ከንቱ” ወደሚለው የጣዖት ቤት ተላልፏል። ታልሙዲስቶች በየቦታው ቤቴል-አቨንን ከቤቴል ጋር አንድ እንደሆኑ ያወራሉ (ኮምፕ ሽዋርዝ፣ ፓለስት ገጽ 89) ይህ ቅርበት ቃሉ በቅጽል ስምነት ተቆጥሮ ሊሆን ይችላል፤ ማለትም ቤቴል የወርቅ ጥጆች አምልኮ መቀመጫ ከሆነች በኋላ ማለት ነው። ይሁን እንጂ ቤተ-አዌን የሚለው ስም በትክክል ከቤቴል (ኢያሱ 7፡2፣ ወዘተ.) የተለየ አካባቢ ነበር፣ እና ከደቡብ-ምስራቅ ሀያ ደቂቃዎች በስተደቡብ-ምስራቅ በምትገኘው ቋጥኝ ቡርጅ ቤቲን ላይ በምትገኝ መንደር ላይ ያለ ይመስላል። ቤቲን (ቤቴል)፣ እና ከቴል ኤል-ሃጃር (አይ) በስተ ምዕራብ ሀያ ደቂቃ (Van de Velde፣ Memoir፣ p. 294) የሚገኝ ስፍራ ነው።


ምንጭ፦ www.biblicalcyclopedia.com




ወደ ቻናሉ ለመ🀄️🀄️ል፦ @Holy_scriptures
👍51
.    ==❀❀❀===❀❀❀==      
              የዕለቱ ጥቅስ 
     ==❀❀❀===❀❀❀==
“ልቤን ወደ ክፉ ነገር አትመልሰው፥ ዓመፅን ከሚያደርጉ ሰዎች ጋር ለኃጢአት ምክንያት እንዳልሰጥ፤ ከምርጦቻቸውም ጋር አልተባበር።”
መዝሙር 141፥4




ወደ ቻናሉ ለመ🀄️🀄️ል፦ @Holy_scriptures
7👍4
በቅዱሳት መጻሕፍት ውስጥ ይሁዳ በባቢሎን ስትማረክ የመጨረሻው ንጉሥ ማን ነበር?
Anonymous Quiz
43%
ሀ. ሰዴቅያስ
28%
ለ. ኢዮአቄም
18%
ሐ. ዮአኪን
12%
መ. ኢዮአክስ
.    ==❀❀❀===❀❀❀==      
              የዕለቱ ጥቅስ 
     ==❀❀❀===❀❀❀==
“ለእያንዳንዱ እንዴት እንድትመልሱ እንደሚገባችሁ ታውቁ ዘንድ ንግግራችሁ ሁልጊዜ፥ በጨው እንደ ተቀመመ፥ በጸጋ ይሁን።”
ቆላስይስ 4፥6




ወደ ቻናሉ ለመ🀄️🀄️ል፦ @Holy_scriptures
10👍2
#የእግዚአብሔር_ቃል_ምን_ይላል?



1ኛ ጢሞቴዎስ 3
¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯
¹ ማንም ኤጲስ ቆጶስነትን ቢፈልግ መልካምን ሥራ ይመኛል የሚለው ቃል የታመነ ነው።
² እንግዲህ ኤጲስ ቆጶስ እንዲህ ሊሆን ይገባዋል፤ የማይነቀፍ፥ የአንዲት ሚስት ባል፥ ልከኛ፥ ራሱን የሚገዛ፥ እንደሚገባው የሚሰራ፥ እንግዳ ተቀባይ፥ ለማስተማር የሚበቃ፥
³ የማይሰክር፥ የማይጨቃጨቅ ነገር ግን ገር የሆነ፥ የማይከራከር፥ ገንዘብን የማይወድ፥
⁴ ልጆቹን በጭምትነት ሁሉ እየገዛ የራሱን ቤት በመልካም የሚያስተዳድር፤
⁵ ሰው ግን የራሱን ቤት እንዲያስተዳድር ባያውቅ፥ የእግዚአብሔርን ቤተ ክርስቲያን እንዴት ይጠብቃታል?
⁶ በትዕቢት ተነፍቶ በዲያብሎስ ፍርድ እንዳይወድቅ፥ አዲስ ክርስቲያን አይሁን።
⁷ በዲያብሎስ ነቀፋና ወጥመድም እንዳይወድቅ፥ በውጭ ካሉት ሰዎች ደግሞ መልካም ምስክር ሊኖረው ይገባዋል።
⁸ እንዲሁም ዲያቆናት ጭምቶች፥ በሁለት ቃል የማይናገሩ፥ ለብዙ ወይን ጠጅ የማይጎመጁ፥
⁹ ነውረኛ ረብ የማይወዱ፥ በንጹሕ ሕሊና የሃይማኖትን ምሥጢር የሚይዙ ሊሆኑ ይገባቸዋል።
¹⁰ እነዚህም ደግሞ አስቀድሞ ይፈተኑ፥ ከዚያም በኋላ ያለ ነቀፋ ቢሆኑ በዲቁና ሥራ ያገልግሉ።
¹¹ እንዲሁም ሴቶች ጭምቶች፥ የማያሙ፥ ልከኞች፥ በነገር ሁሉ የታመኑ ሊሆኑ ይገባቸዋል።
¹² ዲያቆናት ልጆቻቸውንና የራሳቸውን ቤቶች በመልካም እየገዙ እያንዳንዳቸው የአንዲት ሴት ባሎች ይሁኑ።
¹³ በዲቁና ሥራ በመልካም ያገለገሉ ለራሳቸው ትልቅ ማዕርግና በክርስቶስ ኢየሱስ ባለው እምነት ብዙ ድፍረት ያገኛሉ።
¹⁴ ፈጥኜ ወደ አንተ እንድመጣ ተስፋ አድርጌ ይህን እጽፍልሃለሁ።
¹⁵ ብዘገይ ግን፥ በእግዚአብሔር ማደሪያ ቤት መኖር እንዴት እንደሚገባ ታውቅ ዘንድ እጽፍልሃለሁ፤ ቤቱም የእውነት ዓምድና መሠረት፥ የሕያው እግዚአብሔር ቤተ ክርስቲያን ነው።
¹⁶ እግዚአብሔርንም የመምሰል ምሥጢር ያለ ጥርጥር ታላቅ ነው፤ በሥጋ የተገለጠ፥ በመንፈስ የጸደቀ፥ ለመላእክት የታየ፥ በአሕዛብ የተሰበከ፥ በዓለም የታመነ፥ በክብር ያረገ።




ወደ ቻናሉ ለመ🀄️🀄️ል፦ @Holy_scriptures
4👏3👍2
.    ==❀❀❀===❀❀❀==      
              የዕለቱ ጥቅስ 
     ==❀❀❀===❀❀❀==
“ለእናንተም የምነግራችሁ ለሁሉ እላለሁ፤ ትጉ።”
ማርቆስ 13፥37



ወደ ቻናሉ ለመ🀄️🀄️ል፦ @Holy_scriptures
👍64
የሚከተለው ጥቅስ የየትኛው የቅዱሳት መጻሕፍት መግቢያ ነው? “...በእግዚአብሔር ለተመረጡት እምነት እንዲሆንላቸው በዘላለምም ሕይወት ተስፋ እንደ አምልኮት ያለውን እውነት እንዲያውቁ የተላከ፤ ”
Anonymous Quiz
33%
ሀ. 2ኛ ዮሐንስ
8%
ለ. ፊልሞና
11%
ሐ. ፊልጵስዩስ
25%
መ. ቲቶ
24%
ሠ. 2ኛ ተሰሎንቄ
👏8
ቅዱሳት መጻሕፍት
ነቢዩ ኤርምያስ                         ክፍል-፬ ኤርምያስ በነበረበት ዘመን ገዦች እነማን ነበሩ? ኢዮስያስ ወደ ዙፋን የመጣው ገና የስምንት ዓመት ልጅ እያለ ነው፡፡ በፖለቲካ ረገድ ህልውናዋን ለመጠበቅ እየተከለከለች ሳለ፣ አሦር በባቢሎን ብርቱ ፍጥጫ ሥር ወድቃ ነበር፡፡ ይህም ሁኔታ ለይሁዳ ከአምልኮዋ ውስጥ የአሦርን ቅይጥ ነገሮች ለማስወገድ የላቀ ነጻነት አመጣለት፡፡ በ633…
ነቢዩ ኤርምያስ




                        ክፍል-


በኢዮአቄም የዐሥራ አንድ ዓመት ዘመነ መንግሥት ውስጥ የከርከሚሽ ጦርነት ተካሄደ (ከ46 ፥ 2 ጋር ያነጻ)፡፡ በመካከለኛው ምሥራቅ የኀይል ሚዛን ከግብፅ ወደ ባቢሎን መተላለፉን ያመላከተ ስለ ሆነ፣ ዘላቂ ፋይዳ ያለው ሁኔታ (ክሥተት) ነበር፡፡ ይህ ሽንፈት በግብፅ የመስፋፋት ምኞት ላይ የመጨረሻ በትር ሲሆን፤ ከለዳውያን በምዕራቡ ዓለም ላይ የበላይነት እንዲኖራቸው ዋስትናን ሰጠ፡፡ ይህ ሁኔታ ለዘመኑ ወደ ዐዲስ ምዕራፍ መሸጋገሪያ ነበር፤ ለእስራኤልም የወደፊት ዕጣ ፈንታ ዐቢይ ሚና ነበረው፡፡ ባቢሎናውያን ኢዮአቄምን በሥልጣናቸው ሥር ገዥ (መስፍን) አልባ አደረጉት፤ ጥቂት የማይባሉትን የአይሁድ መሳፍንት ያጋዙ ሲሆን (2ነገ 24 ፥ 1)፣ ከእነዚህ ከተጋዙት መካከል ዳንኤል አንዱ ነበር (ዳን 1፥1)፡፡

አንዳንድ ሊቃውንት በናቡደነፆር ይህ የኢየሩሳሌም ለመጀመሪያ ጊዜ መወሰድ የአይሁድ የሰባ ዓመት፣ የባቢሎን ግዞት መጀመሪያ ነው ይላሉ (25፥11)፤ ከዚህም ጋር የዳዊት ሥርወ መንግሥት መፍረስ ጀምሮ ነበር፡፡

ኢዮአቄም የጣዖት አምልኮን ደገፈ፤ በመንግሥቱ በሰፊው ይካሄድ ለነበረው ማኅበራዊ ኢፍትሓዊነትም ደንታ አልነበረውም (22 ፥ 13-19 2ነገ23፥37)፡፡ ኤርምያስ በዘመነ ንግሣቸው ትንቢቱን መናገር ከቀጠለባቸው ነገሥታት መካከል ኢዮአቄም የእግዚአብሔር መልእክትና የእግዚአብሔር መልእክተኛ ደመኛ ጠላት ነበር (ከ26 ፥ 20-23 ፤ ከ36 ፥ 20-26)፡፡ በ598-597 በባቢሎን ላይ ዐመፀ፤ ነገር ግን አልተሳካለትም፤ ከዚህም የተነሣ የይሁዳን መከራ አባባሰው (2ነገ 24 ፥ 1-5)፡፡ በኢዮአቄም ዘመነ መንግሥት ኤርምያስ ሥቃይ ደረሰበት፤ አሤሩበት፤ በከንቱ ስሙ ጠፋበት፤ ታሰረም፡፡ ንጉሡ የተጻፈውን ትንቢት አወደመበት፤ ነቢዩ ግን ከመለኮታዊ ተልእኮው አልተነቃነቀም (ከ11፥ 18-23 ፤ ከ12 ፥ 6፤ ከ15፥15-18፤ ከ18፥18፤ ከ20 ፥ 2 ፤ ከ26፥ 10-11:24፤ ከ36፥ 23)፡፡ ኤርምያስ እንደ ተነበየው (22 ፥ 18-19) ኢዮአቄም በዐሥራ አንደኛው ዓመት የሥልጣን ዘመኑ 598-597 በኢየሩሳሌም በዐመፅ ሞተ፡፡ ኢዮአቄም በናቡከደነፆር ሥልጣን ዘመን ወደ ባቢሎን መጋዙን የዜና መዋዕል ጸሓፊ አስፍሮአል (2ዜና 36፥6-7፤ እንዲሁም ዳን 1፥1)፡፡

(መ) ኢዮአኪን፤

የኢዮአቄምን ዙፋን የወረሰው ልጅ ኢዮአኪን ነው እንዲሁም ኢኮንያንና ኮንያ ይባላል [አዲሱ መደበኛ ትርጉም በ22 ፥ 24፤ በ24፥1 ላይ ያለውን ይመልከቱ]፤ በዙፋን ላይ የቈየውም ሦስት ወር ብቻ ነው (ከ2ነገ 24፥8)፡፡ ነገር ግን ይህ በዐሥራዎቹ የዕድሜ ዘመኑ መግዛት የጀመረው ንጉሥ ጨካኝ ንጉሥነቱን ጒልሕ አስኪያደርግ ድረስ በሥልጣን ላይ ቈየ፤ ይህንኑ ጨካኝ ንጉሥም ኤርምያስ በብርቱ አወገዘው (22፥24-30)፡፡ በባቢሎን ላይ የኢዮአኪን አባት ያካሄደው ዐመፅም በ597 ናቡከደነፆር ኢየሩሳሌምን እንዲወርር አስገደደው፤ ይህም ኢዮአኪን መሸነፉን አምኖ በተቀበለ ጊዜ ነበር (2ነገ 24፥17)፡፡ እርሱም ከብዙ የይሁዳ ገዥ መደቦች ጋር (ከእነርሱ መካከል ነቢዩ ሕዝቅኤል ይገኝ ነበር [ሕዝ 1፥2] ወደ ባቢሎን ተጋዘ፤ ቤተ መቅደሱም ተመዘበረ (2ነገ 24 ፥ 10-16)፡፡ ኢዮአኪን ሠላሳ ሰባት ዓመት ሙሉ በባቢሎን እስረኛ ነበር፡፡ በክፉው በአልጋ ወራሹ፤ በናቡከደነፆር ልጅ በዮርማሮዴቅ ከእስራት ነጻ ሆነ (2ነገ 25 ፥ 27-30)፡፡ አይሁድ እርሱ በዳዊት ዙፋን ላይ ተመልሶ ይነግሣል ብለው ለረዥም ዘመናት ባልተለመደ ሁኔታ ተስፋ ያደርጉ ነበር፡፡ ሕዝቅያስም ንጉሥ ሆኖ በእግሬ ይተካል ያለው ሴዴቅያስን ሳይሆን ኢዮአኪንን ነበር፡፡

(ሠ) ሴዴቅያስ፤

ታላቁ ናቡከደነፆር ካከናወናቸው አያሌ ተግባሮች መካከል ንጉሥ አድርጎ መሾምና ስም መለወጥ ይገኛ ሉ፡፡ ናቡከደነፆር ኢዮአኪንን ካጋዘ በኋላ የኢዮስያስን ልጅ ፤ የኢዮአኪንም አጎት የሆነውን ማታንያንን በይሁዳ ዙፋን ላይ አስቀመጠው፤ ስሙንም ሴዴቅያስ ብሎ ለወጠው (2ነገ 23 ፥ 34 ፤ 24 17: 2ዜና 36 10 ኤር 13) ይህም ሐቅ በባቢሎናውያን ዜና መዋዕል የተረጋገጠ ነው፡፡ የሴዴቅያስ ዘመነ መንግሥት ገና እንደ ተጀመረ፣ ይሁዳ ተከታታይ ወረራና ግዞት የደረሰበት ሲሆን፣ ገዦች በተለዋወጡ ቊጥር ተሸራርፎ የቀረው መንግሥት የሊቃውንት መኻን ሆኖአል፡፡ ሲዴቅያስ ደካማ፣ ወላዋይ፣ መልካም ሰብእናም የጐደለው ሰው ነበርና ውጤታማ አስተዳደርን እውን ለማድረግ ከዐቅሙ በላይ ሆኖ አገኘው፡፡ የባቢሎን አሻንጉሊት ሆኖ ለንጉሡ ታጥቆ ለመኖር በእስራኤል አምላክ ስም የማለ ሲሆን፣ በማንኛውም ውሳኔው ላይ አፍቃሬ ግብፅ በሆኑት ሹሞቹ ተጽዕኖ ሥር የሚገኝ ሰው ነበር፡፡

የእግዚአብሔር ሰው የነበረውን ኢዮስያስን አቈይተን፣ ሴዴቅያስ ከኤርምያስ ጋር የነበረው ግንኙነት ቀደም ካሉት የይሁዳ ነገሥታት ይልቅ በጣም የጠበቀ ነበር፡፡ ሆኖም ኤርምያስን ከመሳፍንቱ ተንኰለኛ ዕቅድ ለመጠበቅና ለናቡከደነፆር ይገዙ ዘንድ ኤርምያስ በተደጋጋሚ ይፋ ያደረገውን ከእግዚአብሔር የተቀበለውን ምክር ለመከተል ዐቅም የነበረው ሰው አልነበረም፡፡ ሴዴቅያስ በነገሠ በአራተኛው ዓመት ከኤዶም፣ ከሞዓብ፣ ከአሞን፣ ከጢሮስና ከሲዶን ነገሥታት ጋር ግምባር በመግጠም (27-3-11): በባቢሎን ላይ ዐመፀ:: ተወካዮችን ወደ ኢየሩሳሌም ሲልኩም ዐላማቸው ይህ ነበር፡፡ ይህን ሤራ ኤርምያስ አወገዘው፤ በመጨረሻም ይኸው ሤራ ከንቱ ሆኖ ቀረ:: በዚያው ዓመት ሴዴቅያስ ባቢሎንን የጐበኘበት ምክንያት፣ ታማኝነቱን ለናቡከደነፆር ለመግለጽ ታልሞ ሳይሆን አይቀርም (51፥ 59)፡፡


ይቀጥላል...


🚨ማሳሰቢያ የጊዜ አቆጣጠር ካልተጠቀሰ በቀር ዓመተ ቅድመ ክርስቶስ ነው።



ምንጭ፦ የብሉይ ኪዳን ማብራሪያ፤ ገጽ 825-826




ወደ ቻናሉ ለመ🀄️🀄️ል፦ @Holy_scriptures
👍5
.    ==❀❀❀===❀❀❀==      
              የዕለቱ ጥቅስ 
     ==❀❀❀===❀❀❀==
“በክርስቶስ ኢየሱስ ወደ ዘላለም ክብሩ የጠራችሁ የጸጋ ሁሉ አምላክ ለጥቂት ጊዜ መከራን ከተቀበላችሁ በኋላ ራሱ ፍጹማን ያደርጋችኋል ያጸናችሁማል ያበረታችሁማል።”
1ኛ ጴጥሮስ 5፥10



ወደ ቻናሉ ለመ🀄️🀄️ል፦ @Holy_scriptures
7
በሚከተለው በሮሜ መልእክት ውስጥ በተጠቀሰው መሠረት በባዶ ቦታ የሚገባው ስም የማን ነው? "ይህንን መልእክት የጻፍሁ እኔ __ በጌታ ሰላምታ አቀርብላችኋለሁ።"
Anonymous Quiz
69%
ሀ. ሐዋርያው ጳውሎስ
5%
ለ. ጢሞቴዎስ
23%
ሐ. ጤርጥዮስ
2%
መ. በርናባስ
0%
ሠ. ሲላስ
👍41
ወደ ቻናሉ ለመ🀄️🀄️ል፦ @Holy_scriptures
👍61
የትንቢተ_ኢሳይያስ_የጥናት_መምሪያና_ማብራሪያ.pdf
36.3 MB
👉ርዕስ፦ የትንቢተ ኢሳይያስ የጥናት መምሪያ እና ማብራሪያ በትምህርተ መለኮት ማስፋፊያ (ት.መ.ማ) መልክ የተዘጋጀ
ጸሐፊ፦ ቲም ፌሎውስ
🗣ትርጉም፦ ግርማዊ ቡሾ
🖨አሳታሚ፦ ኤስ አይ ኤም (SIM Publishing)



ይህ በጣም ሰፊ የሆነ በትንቢተ ኢሳይያስ ላይ የሚያተኩረው የጥናት መምሪያ በቤተ ክርስቲያን አገልግሎት ላይ በተሰማሩ ሰዎች ላይ ሲሆን የጥናት መምሪያውን በብዙ የተለያዩ መንገዶች መጠቀም ይቻላል።

👉በግል የእግዚአብሔርን ቃል ለማጥናት
👉በአዋቂዎች የሰንበት ትምህርት ቤት ወይም
👉በመጽሐፍ ቅዱስ ትምህርት ቤት መጠቀም ይቻላል።



ወደ ቻናሉ ለመ🀄️🀄️ል፦ @Holy_scriptures
🔥31
.    ==❀❀❀===❀❀❀==      
              የዕለቱ ጥቅስ 
     ==❀❀❀===❀❀❀==
“ከአፉም ሕጉን ተቀበል፥ በልብህም ቃሉን አኑር፤”
ኢዮብ 22፥22




ወደ ቻናሉ ለመ🀄️🀄️ል፦ @Holy_scriptures
7🔥6👍3
“በኢየሱስ ክርስቶስ ከሙታንም ባነሣው በእግዚአብሔር አብ ሐዋርያ የሆነ እንጂ ከሰዎች ወይም በሰው ያልሆነ ጳውሎስ...” ይህ ከቅዱሳት መጻሕፍት ውስጥ የየትኛው መጽሐፍ መግቢያ ነው?
Anonymous Quiz
31%
ሀ. ሮሜ
46%
ለ. ገላትያ
8%
ሐ. ፊልጵስዩስ
6%
መ. ቆላስይስ
2%
ሠ. ፊልሞና
6%
ረ. 1ኛ ጢሞቴዎስ
👍4
#እራሳችንን_እንመርምር

በሕይወታችን የሚያደናቅፍ ነገር በሞላበት አልፎም ተርፎ ስንፍገመገም የሚያቆም እና የሚያጸና በሚፈለግበት ጊዜ ረድኤት እና መድኃኒት ከየት ይገኛል?

"ሕግህን የሚወዱ ፍጹም ሰላም ያገኛሉ፤ ሊያደናቅፋቸውም የሚችል አንዳች ነገር የለም።"
መዝሙር 119፥165 (ሕያው ቃል)




ወደ ቻናሉ ለመ🀄️🀄️ል፦ @Holy_scriptures
👍32
.    ==❀❀❀===❀❀❀==      
              የዕለቱ ጥቅስ 
     ==❀❀❀===❀❀❀==
“ክፉ ከሆነ ከአሁኑ ዓለም ያድነን ዘንድ እንደ አምላካችንና እንደ አባታችን ፈቃድ ስለ ኃጢአታችን ራሱን ሰጠ።”
ገላትያ 1፥4



ወደ ቻናሉ ለመ🀄️🀄️ል፦ @Holy_scriptures
👍54
የእግዚአብሔር ቃል እውቀት




ዛሬ በዓለማችን በሃይማኖት ሽፋን ሕሊናን በመሸንገል ለሚመጣው መራራ ቅጣት ራስን የማዘጋጀት ዝንባሌ የሚታየው በእውቀትና በመረዳት ሳይሆን ከእግዚአብሔር ቃል ውጭ በሆነ ከንቱ ሐሳብ በመመራት እንደሆነ ይታያል፡፡ አንዳንድ ጊዜም የተሳሳተ የሃይማኖት ትምህርትን በእግዚአብሔር ቃል ለመደገፍ የሚደረገው ጥረትም ቃሉን ካለመረዳት የመነጨ መሆኑን እናስተውላለን፡፡

ብዙ ዓመታት ያስቆጠረ ውሸት እውነት ሊመስል ቢችል እንኳ ውሸትነቱ መገለጡ አይቀሬ ነው፤ ለዚህም ደግሞ እውነት የሚመስለውን ነገር ሁሉ መርምሮ ለማረጋገጥ ብቸኛው መሣሪያ ጊዜ የማይለውጠው ሕያው የእግዚአብሔር ቃል ብቻ ነው፤ እርሱ ለእኛ እንደ ወንፊት ነው፤ እንክርዳድ የሞላበትን የፈጠራ ትምህርት እንለይበታለን፤ እግዚአብሔር ይመስገን፡፡

መጽሐፍ ቅዱስ የእግዚአብሔርን ቃል የያዘ ብቸኛና ታላቅ መጽሐፍ ነው፤ ይኸም መጽሐፍ የአባቶቻቸውን የቆየና የተሳሳተ መንገድ እንደ ጽድቅ ቆጥረው በመመካት ይጓዙ ለነበሩት የእስራኤል አዲስ ትውልድ ሲናገር «በአባቶቻችሁ ሥርዓት አትሂዱ፣ ወጋቸውንም አትጠብቁ፣ በጣዖቶቻቸውም አትርከሱ» በማለት ያስጠነቅቃል (ሕዝ.20፡18)፡፡

ጌታችን ኢየሱስ የእግዚአብሔርን ቃል ዕውቀት ወደ ጐን በመተው የሰውን ሥርዓት በመጠበቅ ለእርሱ የሚቀኑ የሚመስላቸውን ሰዎች ደጋግሞ ገሥጿል፤ ባሕልና ወግን የሚሰብኩትን የሕግ መምህራንንም «የሰውም ሥርዓት የሆነ ትምህርት እያስተማሩ በከንቱ ያመልኩኛል» (ማቴ.15፡9፣ ማር.7፡1-3) በማለት ተናግሯል፡፡ ይህም ንግግሩ እግዚአብሔርን እንደሚገባ ሳያውቁ የሚቀርብ አምልኮ ከንቱ መሆኑን ያስረዳል፡፡

እርግጥ ነው ለሰዎች ዓይን «መልካም የምትመስል መንገድ አለች፤ ፍጻሜዋ ግን ሞት ነው» እንደተባለው ከጥንት የኖረም ቢሆን እንደ እግዚአብሔር ቃል ያልሆነ መንገድ ሁሉ ፍጻሜው «ሞት» ብቻ ነው (ምሳ.16፡25)፡፡ ነገር ግን ሰው በጌታ በኢየሱስ ብቸኛ አዳኝነት ካመነ ከቀድሞ አባቶቹ ከወረሰው ከንቱ ኑሮ ይድናል፤ ጴጥሮስ ስለዚህ ነገር ሲጽፍ «ከአባቶቻችሁ ከወረሳችሁት ከከንቱ ኑሮአችሁ በሚያልፍ ነገር በብር ወይም በወርቅ ሳይሆን ነውርና እድፍ እንደሌለው እንደ በግ ደም በክቡር የክርስቶስ ደም እንደተዋጃችሁ ታውቃላችሁ» (1ጴጥ.1፡19) ብሏል፡፡

የእግዚአብሔር ቃል እውቀት ጥቅሞች

የእግዚአብሔር ቃል በሰው አንደበት ተነግረው የማያልቁ ብዙ ጥቅሞች እንዳሉት ቃሉን የሚጠቀሙበት ሁሉ ያውቁታል፡፡
የእግዚአብሔር ቃል፦

👉አስተዋይ ለመሆን (መዝ.118፡98፣104)፣
👉ጌታን ላለመበደል (መዝ.118፡11)፣
👉በሥራችን መከናወንን ለማግኘት (ኢያ.1፡7-9)፣

👉የልብ ደስታን ለማግኘት (ኤር.15፡16)፣
👉ለበጎ ሥራ ለመዘጋጀት (2ጢሞ.3፡15)፣
👉ለትምህርታችን (ሮሜ.15፡3-4)፣
👉የክፋት መንፈሳዊ ሠራዊትን ለመዋጋት (ኤፌ.6፡10)፣ ይጠቅማል፡፡ እንደዚሁም የእግዚአብሔር ቃል እውቀት በዚህ ጽሑፍ ውስጥ ቀጥሎ በዝርዝር የምንመለከታቸው ሌሎች ጥቅሞችም አሉት፡፡

1. ላለመሳሳት ይጠቅማል

ሁላችንም የሔዋን መሳሳት እንዴት እንደነበረ እናውቃለን፤ የሔዋንም የመጀመርያ ጥፋቷ ፍሬ ቆርጣ መብላቷ አልነበረም፤ ቀዳሚው ጥፋቷ ከፈጣሪ ቃል ይልቅ የፍጥረትን ድምፅ ማዳመጧ ነበር፡፡ ይህም ድምፅ ፍጹም ወዳጅና ተቆርቋሪ ከሚመስል ጠላት የመጣ ነበር፡፡ ማስጠንቀቂያ ከታከለበት የጌታ ቃል ይልቅ ማባበያ የተሞላው የፍጥረት ድምፅ አሳታት፡፡ ዛሬም ጠላት በምንም ዓይነት ጽድቅን ፊት ለፊት ተቃውሞ አይሰብክም፡፡ ግማሽ እውነት ግማሽ ውሸት በዘመኑ የሚሠራበት የሰይጣን ብልሃት መሆኑ ከታወቀ ውሎ አድሮአል፤ አንድ የቲያትር ተዋናይ(አርቲስት) ገጸ ባሕርይውን መስሎ ለመታየት ብዙ ነገሮችን ሊያደርግ ይችላል፤ ለምሣሌ ሰው ሰራሽ ፂም ሊያደርግ ረዥም ቀሚስ ሊለብስ ይችላል፤ አስመስሎም ይናገራል፤ ነገር ግን ያንን የወከለውን ነገር መሆን አይችልም፤ ከለበሳቸው አልባሳት ውስጥ ያለው ራሱ ነውና፡፡ በመሆኑም እንዲህ ካለው የሰይጣን ማታለል ለመዳን የሚቻልበት ብቸኛው መሣሪያ የእግዚአብሔር ቃል እውቀት ነው፡፡ ሰዎችም ቢሆኑ በተመሣሣይ መንገድ የክርስትናን መልክ ተላብሰው ሊያታልሉ ሲሞክሩ አሁንም መፍትሔው ያው የእግዚአብሔር ቃል እውቀት ነው፡፡


ይቀጥላል...



ምንጭ:- ewnetone.com




ወደ ቻናሉ ለመ🀄️🀄️ል፦ @Holy_scriptures
8👍4