ቅዱሳት መጻሕፍት
7.45K subscribers
1.36K photos
61 videos
332 files
806 links
በዚህ ቻናል

👉ቅዱሳት መጻሕፍት ይጠናሉ::
👉መጽሐፍ ቅዱሳዊ ትምህርቶች ይቀርባሉ::
👉 ለቅዱሳት መጽሐፍት ጥናት የሚያግዙ መጻሕፍት ይለቀቃሉ።

⭐️⭐️⭐️⭐️⭐️

@Holy_scriptures
Download Telegram
.    ==❀❀❀===❀❀❀==      
              የዕለቱ ጥቅስ 
     ==❀❀❀===❀❀❀==
“የእስራኤል ጌታ አምላክ ይባረክ፥ ጐብኝቶ ለሕዝቡ ቤዛ አድርጎአልና፤”
ሉቃስ 1፥68



ወደ ቻናሉ ለመ🀄️🀄️ል፦ @Holy_scriptures
👍21
በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ እስራኤላውያን የኢያርኮ ቅጥሩ ሳይፈርስ በአጠቃላይ ስንት ጊዜ ኢያሪኮን ዞሩ?
Anonymous Quiz
11%
ሀ. 13
3%
ለ. 3
69%
ሐ. 7
17%
መ. 6
👍5
.    ==❀❀❀===❀❀❀==      
              የዕለቱ ጥቅስ 
     ==❀❀❀===❀❀❀==
“ከወገናችንም ያሉት ደግሞ ፍሬ ቢሶች ሆነው እንዳይቀሩ፥ የግድ ስለሚያስፈልገው ነገር በመልካም ሥራ እንዲጸኑ ይማሩ።”
ቲቶ 3፥14



ወደ ቻናሉ ለመ🀄️🀄️ል፦ @Holy_scriptures
👍42
ወደ ቻናሉ ለመ🀄️🀄️ል፦ @Holy_scriptures
1
መጨረሻቸው_ካላማረ_አገልጋዮች_ስህተት_እንማር.pdf
1 MB
👉ርዕስ፦ መጨረሻቸው ካላማረ አገልጋዮች ስህተት እንማር
አዘጋጅ፦ ዶክተር መለሰ ወጉ
🗒የገጽ ግዛት፦ 91


በዚህ መጽሐፍ ውስጥ ለትምህርታችን የሚከተሉት ነገሮች ተዳሰዋል፦

👉"የሎጥ ሚስት"— በሁለት አሳብ ለሚያነክሱ
👉"ርብቃ" — በትዳራቸው "አንድነት" ለሌላቸው
👉"ዲቦራ" — እግዚአብሔርን "እሺ!" ማለት ላቃታቸው
👉"ደሊላ" — ኃጢአት የሚያስከትለው ውድቀት ላልታያቸው
👉"ሱነማዊት"— አገልግሎት "በአደባባይ" ብቻ ለሚመስላቸው
👉"አስቴር"— በሕይወታቸው የእግዚአብሔር ዕቅድ አልታይ ላላቸው



ወደ ቻናሉ ለመ🀄️🀄️ል፦ @Holy_scriptures
👍111
.    ==❀❀❀===❀❀❀==      
              የዕለቱ ጥቅስ 
     ==❀❀❀===❀❀❀==
“‘እግዚአብሔር ወዴት ነው?’ ብለው፣ ካህናቱ አልጠየቁም፤ ከሕጉ ጋር የሚውሉት አላወቁኝም፤ መሪዎቹ ዐመፁብኝ፤ ነቢያቱም በበኣል ስም ተነበዩ፤ ከንቱ ነገሮችን ተከተሉ።”
ኤርምያስ 2፥8 (አዲሱ መ.ት)



ወደ ቻናሉ ለመ🀄️🀄️ል፦ @Holy_scriptures
👍6
Audio
👉ርዕስ፦ የመናኝ ጉዞ
ጸሐፊ፦ ዮሐንስ ቡንያን
🔈ክፍል አምስት


ይቀጥላል...


ወደ ቻናሉ ለመ🀄️🀄️ል፦ @Holy_scriptures
2
በቅዱሳት መጻሕፍት፣ በመጽሐፈ ምሳሌ ውስጥ ጠቢብ በመሆኑ የተመሰገነው እንስሳ የቱ ነው?
Anonymous Quiz
22%
ሀ. እባብ
2%
ለ. አንበሳ
14%
ሐ. ንስር
62%
መ. ጉንዳን
👍1
.    ==❀❀❀===❀❀❀==      
              የዕለቱ ጥቅስ 
     ==❀❀❀===❀❀❀==
“በመሠዊያዬ ላይ እሳትን በከንቱ እንዳታቃጥሉ ከእናንተ ዘንድ ደጅ የሚዘጋ ሰው ምነው በተገኘ! በእናንተ ደስ አይለኝም፥ ቍርባንንም ከእጃችሁ አልቀበልም፥ ይላል የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር።”
ሚልክያስ 1፥10




ወደ ቻናሉ ለመ🀄️🀄️ል፦ @Holy_scriptures
👍5
ከኢየሩሳሌም መፍረስ በኋላ የይሁዳ ሰዎች ነቢዩ ኤርምያስን ወዴት እንዲሄድ አስገደዱት?
Anonymous Quiz
39%
ሀ. ባቢሎን
12%
ለ. ሶርያ
27%
ሐ. ግብፅ
22%
መ. አሦር
👍2
#እራሳችንን_እንመርምር


እኔምለው ከእግዚአብሔር ቃል ጋር እየተዋለ፣ ቃሉ እንዴት ይሆን እየተባለ ቃሉ ሳያውቁ መኖር ይቻላል እንዴ? ምንስ ቢሆን ነው እንደዚህ ባለማወቅ ጨለማ ውስጥ የሚኖረው?


“ካህናቱም። እግዚአብሔር ወዴት አለ? አላሉም፥ ባለ ኦሪቶችም አላወቁኝም ገዢዎችም ዐመፁብኝ፥ ነቢያትም በበኣል ትንቢት ተናገሩ፥ የማይረባንም ነገር ተከተሉ።”
ኤርምያስ 2፥8




ወደ ቻናሉ ለመ🀄️🀄️ል፦ @Holy_scriptures
👍6
.    ==❀❀❀===❀❀❀==      
              የዕለቱ ጥቅስ 
     ==❀❀❀===❀❀❀==
“ነገር ግን በጌታችንና በመድኃኒታችን በኢየሱስ ክርስቶስ ጸጋና እውቀት እደጉ። ለእርሱ አሁንም እስከ ዘላለምም ቀን ድረስ ክብር ይሁን፤ አሜን።”
2ኛ ጴጥሮስ 3፥18




ወደ ቻናሉ ለመ🀄️🀄️ል፦ @Holy_scriptures
👍42
በእግዚአብሄር ቃል የመኖር አምስቱ ደረጃዎች



በእውነት ፍሬያማ ለመሆን በክርስቶስ መኖር ግድ ነው፡፡ የፍሬያማነታችን ልክ በክርስቶስ የመኖራችን ልክ ብቻ ነው፡፡ በኢየሱስ መኖር ደግሞ በቃሉ መኖር ነው፡፡ በእግዚአብሄር ቃል የመኖር አምስቱን ደረጃዎች ከመፅሃፍ ቅዱስ እንመልከት፡፡

1. የእግዚአብሄርን ቃል መስማት

በቃል የመኖር የመጀመሪያው ደረጃ የእግዚአብሄርን ቃል መስማት ነው፡፡ ካለ እግዚአብሄር ቃል መስማት ፍሬያማነት የማይታሰብ ነው፡፡ የፍሬማነታችን ቁልፍ በቃሉ መኖር ነው፡፡ ስለዚህ ቃሉም ለመስማት ራሳችንን ልንሰጥ ይገባል፡፡ ቃሉን መስማት ሁኔታዎችን ማመቻቸት አለብን፡፡ በአሁኑ ጊዜ በተለይ በአሁኑ ጊዜ መፅሃፍ ቅዱስ በኰምፒተር በታብሌት በስልካችን በፅሁፍና በድምፅ እናገኘዋለን፡፡ በቤታችን ቴፕ ውስጥ ከፍተነው ማዳመጥ እንችላለን፡፡ መኪና ስንነዳና ወረፋ ስንጠብቅ ቃሉን መስማት እንችላለን፡፡

"እንግዲያስ እምነት ከመስማት ነው መስማትም በእግዚአብሔር ቃል ነው።" (ሮሜ 10፡17)

2. ለእግዚአብሄርን ቃል የመጀመሪያውን ስፍራ መስጠት

ፍሬያማ የሚያደርገን ቃሉ እንደመሆናችን መጠን ጠላትም የሚመጣው ቃሉን ሊነጥቅ ነው፡፡ ቃሉን ከሰረቀ ህይወታቸንን ይሰርቃል ቃሉን ከጠበቅን ህይወታቸነ በደህንነት የጠበቃል፡፡ ሰይጣን ቃሉን መስረቅ ካልቻለ ምንም ነገራችንን መስረቅ አይችልም፡፡

"የመንግሥትን ቃል ሰምቶ በማያስተውል ሁሉ፥ ክፉው ይመጣል፥ በልቡ የተዘራውንም ይነጥቃል፤ በመንገድ ዳር የተዘራው ይህ ነው።" (ማቴዎስ 13፡19)

ሰው ውድ የሆነ ነገሩን እጅግ ውስጠኛው ቦታ ያስቀምጠዋል እንጂ ውጭ አይተወውም፡፡ እንዲሁ የእግዚአብሄርን ቃል የመጀመሪያውንም ስፍራ ልባችንን ልንሰጠው ይገባል፡፡ የእግዚአብሄርን ቃል ለመሰረቅ በማይመች በውስጠኛው የህይወታችን ክፍል ውስጥ ልናደርገውና በልባችን ልንሰውረው እና ልንሸሽገው ይገባል፡፡

"ከእርሱም ይልቅ እጅግ የጸና የትንቢት ቃል አለን፤ ምድርም እስኪጠባ ድረስ የንጋትም ኮከብ በልባችሁ እስኪወጣ ድረስ፥ ሰው በጨለማ ስፍራ የሚበራን መብራት እንደሚጠነቀቅ ይህን ቃል እየጠነቀቃችሁ መልካም ታደርጋላችሁ።"
(2ኛ ጴጥሮስ 1፡19)

"በፍጹም ልቤ ፈለግሁህ፥ ከትእዛዝህ አታርቀኝ። አንተን እንዳልበድል፥ ቃልህን በልቤ ሰወርሁ።" (መዝሙር 119፡10-11)

3. የእግዚአብሄርን ቃል ማሰላሰል

የእግዚአብሄርን ቃል ለመታተዘዝ ያስችለን ዘንድ በቃሉ ከባቢ ውስጥ ለመገኘት የእግዚአብሄርን ቃል ማሰብና ማሰላሰል ወሳኝ ነው፡፡ ቃሉን ስናሰላስል ቃሉን እናስታውሳለን፡፡ ቃሉን ስናሰላስል ቃሉን ለማድረግ ሃይል እናገኛለን፡፡

"የዚህ ሕግ መጽሐፍ ከአፍህ አይለይ፥ ነገር ግን የተጻፈበትን ሁሉ ትጠብቅና ታደርግ ዘንድ በቀንም በሌሊትም አስበው፤ የዚያን ጊዜም መንገድህ ይቀናልሃል ይከናወንልሃልም።" (ኢያሱ 1፡8)

"በቀረውስ፥ ወንድሞች ሆይ፥ እውነተኛ የሆነውን ነገር ሁሉ፥ ጭምትነት ያለበትን ነገር ሁሉ፥ ጽድቅ የሆነውን ነገር ሁሉ፥ ንጹሕ የሆነውን ነገር ሁሉ፥ ፍቅር ያለበትን ነገር ሁሉ፥ መልካም ወሬ ያለበትን ነገር ሁሉ፥ በጎነት ቢሆን ምስጋናም ቢሆን፥ እነዚህን አስቡ፤"  (ፊልጵስዩስ 4፡8)

4. የእግዚአብሄርን ቃል መናገር

ሌላው የእግዚአብሄርን ቃል የምናደርግበት መንገድ የእግዚአብሄርን ቃል መናገር ነው፡፡ ንግግራችን እንደ እግዚአብሄር ቃል መሆን አለበት፡፡

"እውነት እላችኋለሁ፥ ማንም ያለው ነገር እንዲደረግለት ቢያምን በልቡ ሳይጠራጠር፥ ይህን ተራራ፦ ተነቅለህ ወደ ባሕር ተወርወር ቢል ይሆንለታል።" (ማርቆስ 11፡23)

5. የእግዚአብሄርን ቃል ማድረግ

"ነገር ግን ነጻ የሚያወጣውን ፍጹሙን ሕግ ተመልክቶ የሚጸናበት፥ ሥራንም የሚሠራ እንጂ ሰምቶ የሚረሳ ያልሆነው፥ በሥራው የተባረከ ይሆናል።" (ያዕቆብ 1፡25)



ምንጭ :- አብይ ዋቁማ




ወደ ቻናሉ ለመ🀄️🀄️ል፦ @Holy_scriptures
9👍6🔥5🥰2👎1
.    ==❀❀❀===❀❀❀==      
              የዕለቱ ጥቅስ 
     ==❀❀❀===❀❀❀==
“በጽድቅ የሚጸና በሕይወት ይኖራል፤ ክፋትን የሚከተል ግን ለሞቱ ነው።”
ምሳሌ 11፥19




ወደ ቻናሉ ለመ🀄️🀄️ል፦ @Holy_scriptures
3👍2👏1
#ከተማ_ወይም_ቦታ_በቅዱሳት_መጻሕፍት



#ቤትአዌን

ቤት-አዌን(በዕብራይስጥ ቤይት አቨን፣ בֵּית אָוֶן፣ የከንቱነት ቤት፣ ማለትም የክፋት፣ ጣዖት አምልኮ ቤት። በብንያም ተራሮች በቤቴል በስተምስራቅ የሚገኝ ቦታ ነው። 1ሳሙ 13፡5፣ በኢያሱ 18፡12 ላይ የቤተ-አዌን “ምድረ በዳ” (ሚድባር = የግጦሽ መሬት) በሚል ተጠቅሷል። በሆሴዕ 4:15፣ ሆሴዕ 5:8፣ ሆሴዕ 10፡5፣ ስሙ በዚህ ነቢይ በተገለጸው ቃል መሠረት ወደ አጎራባች ቤቴል - አንድ ጊዜ “የእግዚአብሔር ቤት” ወደ ነበረው፣ ከዚያ በኋላ ግን “ከንቱ” ወደሚለው የጣዖት ቤት ተላልፏል። ታልሙዲስቶች በየቦታው ቤቴል-አቨንን ከቤቴል ጋር አንድ እንደሆኑ ያወራሉ (ኮምፕ ሽዋርዝ፣ ፓለስት ገጽ 89) ይህ ቅርበት ቃሉ በቅጽል ስምነት ተቆጥሮ ሊሆን ይችላል፤ ማለትም ቤቴል የወርቅ ጥጆች አምልኮ መቀመጫ ከሆነች በኋላ ማለት ነው። ይሁን እንጂ ቤተ-አዌን የሚለው ስም በትክክል ከቤቴል (ኢያሱ 7፡2፣ ወዘተ.) የተለየ አካባቢ ነበር፣ እና ከደቡብ-ምስራቅ ሀያ ደቂቃዎች በስተደቡብ-ምስራቅ በምትገኘው ቋጥኝ ቡርጅ ቤቲን ላይ በምትገኝ መንደር ላይ ያለ ይመስላል። ቤቲን (ቤቴል)፣ እና ከቴል ኤል-ሃጃር (አይ) በስተ ምዕራብ ሀያ ደቂቃ (Van de Velde፣ Memoir፣ p. 294) የሚገኝ ስፍራ ነው።


ምንጭ፦ www.biblicalcyclopedia.com




ወደ ቻናሉ ለመ🀄️🀄️ል፦ @Holy_scriptures
👍51
.    ==❀❀❀===❀❀❀==      
              የዕለቱ ጥቅስ 
     ==❀❀❀===❀❀❀==
“ልቤን ወደ ክፉ ነገር አትመልሰው፥ ዓመፅን ከሚያደርጉ ሰዎች ጋር ለኃጢአት ምክንያት እንዳልሰጥ፤ ከምርጦቻቸውም ጋር አልተባበር።”
መዝሙር 141፥4




ወደ ቻናሉ ለመ🀄️🀄️ል፦ @Holy_scriptures
7👍4
በቅዱሳት መጻሕፍት ውስጥ ይሁዳ በባቢሎን ስትማረክ የመጨረሻው ንጉሥ ማን ነበር?
Anonymous Quiz
43%
ሀ. ሰዴቅያስ
28%
ለ. ኢዮአቄም
18%
ሐ. ዮአኪን
12%
መ. ኢዮአክስ
.    ==❀❀❀===❀❀❀==      
              የዕለቱ ጥቅስ 
     ==❀❀❀===❀❀❀==
“ለእያንዳንዱ እንዴት እንድትመልሱ እንደሚገባችሁ ታውቁ ዘንድ ንግግራችሁ ሁልጊዜ፥ በጨው እንደ ተቀመመ፥ በጸጋ ይሁን።”
ቆላስይስ 4፥6




ወደ ቻናሉ ለመ🀄️🀄️ል፦ @Holy_scriptures
10👍2
#የእግዚአብሔር_ቃል_ምን_ይላል?



1ኛ ጢሞቴዎስ 3
¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯
¹ ማንም ኤጲስ ቆጶስነትን ቢፈልግ መልካምን ሥራ ይመኛል የሚለው ቃል የታመነ ነው።
² እንግዲህ ኤጲስ ቆጶስ እንዲህ ሊሆን ይገባዋል፤ የማይነቀፍ፥ የአንዲት ሚስት ባል፥ ልከኛ፥ ራሱን የሚገዛ፥ እንደሚገባው የሚሰራ፥ እንግዳ ተቀባይ፥ ለማስተማር የሚበቃ፥
³ የማይሰክር፥ የማይጨቃጨቅ ነገር ግን ገር የሆነ፥ የማይከራከር፥ ገንዘብን የማይወድ፥
⁴ ልጆቹን በጭምትነት ሁሉ እየገዛ የራሱን ቤት በመልካም የሚያስተዳድር፤
⁵ ሰው ግን የራሱን ቤት እንዲያስተዳድር ባያውቅ፥ የእግዚአብሔርን ቤተ ክርስቲያን እንዴት ይጠብቃታል?
⁶ በትዕቢት ተነፍቶ በዲያብሎስ ፍርድ እንዳይወድቅ፥ አዲስ ክርስቲያን አይሁን።
⁷ በዲያብሎስ ነቀፋና ወጥመድም እንዳይወድቅ፥ በውጭ ካሉት ሰዎች ደግሞ መልካም ምስክር ሊኖረው ይገባዋል።
⁸ እንዲሁም ዲያቆናት ጭምቶች፥ በሁለት ቃል የማይናገሩ፥ ለብዙ ወይን ጠጅ የማይጎመጁ፥
⁹ ነውረኛ ረብ የማይወዱ፥ በንጹሕ ሕሊና የሃይማኖትን ምሥጢር የሚይዙ ሊሆኑ ይገባቸዋል።
¹⁰ እነዚህም ደግሞ አስቀድሞ ይፈተኑ፥ ከዚያም በኋላ ያለ ነቀፋ ቢሆኑ በዲቁና ሥራ ያገልግሉ።
¹¹ እንዲሁም ሴቶች ጭምቶች፥ የማያሙ፥ ልከኞች፥ በነገር ሁሉ የታመኑ ሊሆኑ ይገባቸዋል።
¹² ዲያቆናት ልጆቻቸውንና የራሳቸውን ቤቶች በመልካም እየገዙ እያንዳንዳቸው የአንዲት ሴት ባሎች ይሁኑ።
¹³ በዲቁና ሥራ በመልካም ያገለገሉ ለራሳቸው ትልቅ ማዕርግና በክርስቶስ ኢየሱስ ባለው እምነት ብዙ ድፍረት ያገኛሉ።
¹⁴ ፈጥኜ ወደ አንተ እንድመጣ ተስፋ አድርጌ ይህን እጽፍልሃለሁ።
¹⁵ ብዘገይ ግን፥ በእግዚአብሔር ማደሪያ ቤት መኖር እንዴት እንደሚገባ ታውቅ ዘንድ እጽፍልሃለሁ፤ ቤቱም የእውነት ዓምድና መሠረት፥ የሕያው እግዚአብሔር ቤተ ክርስቲያን ነው።
¹⁶ እግዚአብሔርንም የመምሰል ምሥጢር ያለ ጥርጥር ታላቅ ነው፤ በሥጋ የተገለጠ፥ በመንፈስ የጸደቀ፥ ለመላእክት የታየ፥ በአሕዛብ የተሰበከ፥ በዓለም የታመነ፥ በክብር ያረገ።




ወደ ቻናሉ ለመ🀄️🀄️ል፦ @Holy_scriptures
4👏3👍2
.    ==❀❀❀===❀❀❀==      
              የዕለቱ ጥቅስ 
     ==❀❀❀===❀❀❀==
“ለእናንተም የምነግራችሁ ለሁሉ እላለሁ፤ ትጉ።”
ማርቆስ 13፥37



ወደ ቻናሉ ለመ🀄️🀄️ል፦ @Holy_scriptures
👍64