. ==❀❀❀===❀❀❀==
🌼 የዕለቱ ጥቅስ 🌼
==❀❀❀===❀❀❀==
“ክፉ ለማድረግ የሚያስብ ተንኰለኛ ይባላል።”
ምሳሌ 24፥8
ወደ ቻናሉ ለመ🀄️ላ🀄️ል፦ @Holy_scriptures
🌼 የዕለቱ ጥቅስ 🌼
==❀❀❀===❀❀❀==
“ክፉ ለማድረግ የሚያስብ ተንኰለኛ ይባላል።”
ምሳሌ 24፥8
ወደ ቻናሉ ለመ🀄️ላ🀄️ል፦ @Holy_scriptures
👍6
ቅዱሳት መጻሕፍት
ነቢዩ ኤርምያስ ክፍል-፫ በጊዜው የነበሩ ሁነቶች የኤርምያስን ትንቢት ለመገንዘብ የነበረበትን ዘመን በትኵረት ማየትን ይጠይቃል፤ ምክንያቱም (1) በዘመኑ የነበሩትን በፖለቲካው ዓለም የተከሠቱትን ወሳኝ ሁኔታዎች ማጤን ይጠይቃል፤ እነዚህም ሁኔታዎች ይሁዳ በቀጥታ የተነካችባቸው ሁኔታዎች ናቸው፡፡ እንዲሁም (2) ከኤርምያስ ጋር ግንኙነት የነበራቸውን በእርሱ…
ነቢዩ ኤርምያስ
ክፍል-፬
ኤርምያስ በነበረበት ዘመን ገዦች እነማን ነበሩ?
ኢዮስያስ
ወደ ዙፋን የመጣው ገና የስምንት ዓመት ልጅ እያለ ነው፡፡ በፖለቲካ ረገድ ህልውናዋን ለመጠበቅ እየተከለከለች ሳለ፣ አሦር በባቢሎን ብርቱ ፍጥጫ ሥር ወድቃ ነበር፡፡ ይህም ሁኔታ ለይሁዳ ከአምልኮዋ ውስጥ የአሦርን ቅይጥ ነገሮች ለማስወገድ የላቀ ነጻነት አመጣለት፡፡ በ633
ኢዮስያስ እግዚአብሔርን ፈለገ (2ዜና 34፥3)፤ ተሐድሶው የጀመረው በ629 ነው (2ዜና 24 ፥ 36)፤ በ623-622 የሕጉ መጽሐፍ በቤተ መቅደሱ ውስጥ ተገኘ (2ነገ 22 ፥ 3-8 ፤ 2ዜና 34፥8-15)፤ ኢየሩሳሌምም በይፋ የታወቀች የአምልኮ ማእከል ሆነች፡፡ በዚያን ዘመን የተከናውኑት ተሐድሶዎች በ2ነገ 22-23 ላይ ቁልጭ ተደርገው ተዘርዝረዋል፤ በሰፊው የተሠራጩና በደንብ የተከበሩ ቢሆኑም እንኳ የሕዝቡን በደሎች አስመልክቶ ኤርምያስ ካሰማው ውግዘት በግልጽ እንደሚታየው ተሐድሶዎቹ ረጅም ዘመን አልቈዩም፡፡
በ609 ፈርዖን ኒካዑ አሦርን ለማጠናከር ከእነርሱ ጋር ተባባረ፡፡ ኢዮስያስ ከኒካዑ ማስጠንቀቂያ ቢደርሰውም እንኳ ጣልቃ ገባና በመጊዶ ጦርነት ላይ ሕይወቱን ዐጣ (2ነገ 23 ፥ 29 ፤ 2ዜና 35፥20-24)፡፡ ይሁን እንጂ ከግብፅ ይልቅ ኀያል የነበረችው ባቢሎን በ625 የባቢሎን ንጉሥ በነበረውና በ612ም ነነዌን ባወደማት በከለዳዊው በናቡፓላስር ዘመነ መንግሥት በዓለም ላይ ገናና ሆነች:: ልጁ ደግማዊ ናቡከደነፆር ዙፋኑን በመውረስ በ605 በኤፍራጥስ ወንዝ በከርከሚሽ ጦርነት ላይ ግብፅን አሽንፎ አርባ ሦስት ዓመት ገዛ (42 ፥ 2 ፤ 2ዜና 35 ፥ 20)፡፡ ከዚያ በኋላ ባቢሎን የዓለም ኀያል ሆነች:: ይሁዳ በዓለም ፖለቲካ ውስጥ እጇን እንዳታስገባ ኤርምያስ ለዓመታት ሲመክር ቈየ፡፡ ሕዝቡ ምክሩን ለመቀበል ፈቃደኞች ባልሆኑ ጊዜ፣ በዚያ ወቅት የእግዚአብሔርን ፈቃድ ለመፈጸም መሣሪያ ለነበረው፣ ለኃያሉ የባቢሎን ሰራዊት እጃቸውን እንዲሰጡ ኤርምያስ በተደጋጋሚ ተማጸናቸው፡፡
ኢዮአካዝ
በእግዚአብሔር ሰው በኢዮስያስ ያልታሰበ ሞት በመበሳጨት ሕዝቡ በራሳቸው ሥልጣን የኢዮስያስን ልጅ ኢዮአካዝን (ሻሎም [22፥11] ዙፋን ላይ አስቀመጡት፡፡ ኢዮአካዝ በሦስት ወር ንግሥና ወቅት ውስጥ ፀረ ግብፅ አቋምና አፍቃሬ ባቢሎን ፖሊሲ አሳየ፤ ከዚህም የተነሣ ፈርዖን ኒካዑ ወደ ግብፅ አጋዘውና በአገሪቱ ላይ ግብር ጣለባት፡፡ በእርሱም ምትክ ስሙን ወደ ኢዮአቄም በመለወጥ (2ነገ 23 ፥ 30-35 ፤ 2ዜና 36 ፥ 1-4) የኢዮስያስን በኲር ልጅና የኢዮአካዝም የአባት ልጅ የሆነውን ኤልያቄምን (2ነገ 23 ፥ 34-36) በዙፋን ላይ አስቀመጠው፡፡
ኢዮአቄም
በዚህ ንጉሥ ዘመነ መንግሥት ኤርምያስን ብርቱ ፈተናና ከፍተኛ ተቃውም ያጋጠመበት ዘመን ነበር፡፡ በፖለቲካ ረገድ ንጉሥና ነቢይ ሆድና ጀርባ ነበሩ፤ ንጉሡ ግብፅን ፈቀደ፤ ኤርምያስ ደግሞ ለባቢሎን ይገዙ ዘንድ ምክር ሰጠ፡፡ በመንፈሳዊ ረገድም ቢሆን ሁለቱ እጅግ የተራራቁ ነበሩ፡፡ ኢዮአቄም ከይሁዳ ነገሥታት ሁሉ በጣም ጨካኝና ፈሪሀ እግዚአብሔር ያላደረበት ንጉሥ ነበር፡፡ ደም የተጠማና የእውነት ደመኛ ጠላት ተደርጎ ይታይ ነበር፡፡ ለእስራኤል አምላክ አምልኮ ደንታ አልነበረውም፤ በሕዝቡ ላይ ከፍተኛ ግብር ጣለ፤ ያለክፍያ የግዳጅ ሥራን ተግባር ላይ አዋለ፤ ለእግዚአብሔር ቃልና ለእግዚአብሔርም ነቢይ ደንታ አልበረውም (22፥ 13-14፤ ምዕ 36)፡፡
ይቀጥላል...
🚨ማሳሰቢያ የጊዜ አቆጣጠር ካልተጠቀሰ በቀር ዓመተ ቅድመ ክርስቶስ ነው።
ምንጭ፦ የብሉይ ኪዳን ማብራሪያ፤ ገጽ 825

👍9👏1
. ==❀❀❀===❀❀❀==
የዕለቱ ጥቅስ
==❀❀❀===❀❀❀==
“ከእናንተ እግዚአብሔርን የሚፈራ፥ የባሪያውንም ቃል የሚሰማ፥ በጨለማም የሚሄድ፥ ብርሃንም የሌለው፥ ነገር ግን በእግዚአብሔር ስም የሚታመን፥ በአምላኩም የሚደገፍ ማን ነው?”
ኢሳይያስ 50፥10

👍4
https://play.google.com/store/apps/details?id=com.kf.amharic_bible_dictionary
ይህ የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ መዝገበ ቃላት የተዘጋጀው በዘላለም መንግስቱ ነው። በ23 አመት ውስጥ ተዘጋጅቶ በ2023 እ.ኤ.አ ተጠናቅቋል። ይህ መዝገበ ቃላት የዕብራይስጥ እና የግሪክ አቻዎች ጋር ከ4,800 በላይ ቃላትን ይሸፍናል።
ወደ ቻናሉ ለመ🀄️ላ🀄️ል፦ @Holy_scriptures
ይህ የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ መዝገበ ቃላት የተዘጋጀው በዘላለም መንግስቱ ነው። በ23 አመት ውስጥ ተዘጋጅቶ በ2023 እ.ኤ.አ ተጠናቅቋል። ይህ መዝገበ ቃላት የዕብራይስጥ እና የግሪክ አቻዎች ጋር ከ4,800 በላይ ቃላትን ይሸፍናል።
ወደ ቻናሉ ለመ🀄️ላ🀄️ል፦ @Holy_scriptures
👍3
ቅዱሳት መጻሕፍት ውስጥ ከሚገኙ መሪዎች መካከል ስልጣን ላይ ለመውጣት ብሎ ሰባ ወንድሞቹን ያስገደለው ሰው ማን ነው?
Anonymous Quiz
14%
ሀ. ናብከደነፆር
16%
ለ. አቤሴሎም
23%
ሐ. ኢዮርብዓም
27%
መ. አቤሜሌክ
20%
ሠ. አዶንያስ
👍3
. ==❀❀❀===❀❀❀==
የዕለቱ ጥቅስ
==❀❀❀===❀❀❀==
“ወይም ይህ ወይም ያ ማናቸው እንዲበቅል ወይም ሁለቱ መልካም እንዲሆኑ አታውቅምና በማለዳ ዘርህን ዝራ፥ በማታም እጅህን አትተው።”
መክብብ 11፥6
ወደ ቻናሉ ለመ🀄️ላ🀄️ል፦ @Holy_scriptures
የዕለቱ ጥቅስ
==❀❀❀===❀❀❀==
“ወይም ይህ ወይም ያ ማናቸው እንዲበቅል ወይም ሁለቱ መልካም እንዲሆኑ አታውቅምና በማለዳ ዘርህን ዝራ፥ በማታም እጅህን አትተው።”
መክብብ 11፥6
ወደ ቻናሉ ለመ🀄️ላ🀄️ል፦ @Holy_scriptures
👍5❤1
#የእግዚአብሔር_ቃል_ምን_ይላል?
ሮሜ 1
¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯
¹-² ሐዋርያ ሊሆን የተጠራ የኢየሱስ ክርስቶስ ባሪያ ጳውሎስ በነቢያቱ አፍ በቅዱሳን መጻሕፍት አስቀድሞ ተስፋ ለሰጠው ለእግዚአብሔር ወንጌል ተለየ።
³-⁴ ይህም ወንጌል በሥጋ ከዳዊት ዘር ስለ ተወለደ እንደ ቅድስና መንፈስ ግን ከሙታን መነሣት የተነሣ በኃይል የእግዚአብሔር ልጅ ሆኖ ስለ ተገለጠ ስለ ልጁ ነው፤ እርሱም ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ነው።
⁵ በእርሱም ስለ ስሙ በአሕዛብ ሁሉ መካከል ከእምነት የሚነሣ መታዘዝ እንዲገኝ ጸጋንና ሐዋርያነትን ተቀበልን፤
⁶ በእነርሱም መካከል የኢየሱስ ክርስቶስ ልትሆኑ የተጠራችሁ እናንተ ደግሞ ናችሁ።
⁷ በእግዚአብሔር ለተወደዳችሁና ቅዱሳን ልትሆኑ ለተጠራችሁ በሮሜ ላላችሁት ሁሉ፥ ከእግዚአብሔር ከአባታችን ከጌታም ከኢየሱስ ክርስቶስ ጸጋና ሰላም ለእናንተ ይሁን።
⁸ እምነታችሁ በዓለም ሁሉ ስለ ተሰማች አስቀድሜ ስለ ሁላችሁ አምላኬን በኢየሱስ ክርስቶስ አመሰግናለሁ።
⁹-¹⁰ በልጁ ወንጌል በመንፈሴ የማገለግለው እግዚአብሔር ምስክሬ ነውና፤ ምናልባት ብዙ ቆይቼ ወደ እናንተ አሁን እንድመጣ በእግዚአብሔር ፈቃድ መንገዴን እንዲያቀናልኝ እየለመንሁ ሁልጊዜ ስጸልይ ስለ እናንተ ሳላቋርጥ አሳስባለሁ።
¹¹ ትጸኑ ዘንድ መንፈሳዊ ስጦታ እንዳካፍላችሁ ላያችሁ እናፍቃለሁና፤
¹² ይህንም ማለቴ በመካከላችን ባለች በእናንተና በእኔ እምነት አብረን በእናንተ እንድንጽናና ነው።
¹³ ወንድሞች ሆይ፥ በሌሎቹ አሕዛብ ደግሞ እንደ ሆነ በእናንተም ፍሬ አገኝ ዘንድ ብዙ ጊዜ ወደ እናንተ ልመጣ እንዳሰብሁ እስከ አሁን ግን እንደ ተከለከልሁ ታውቁ ዘንድ እወዳለሁ።
¹⁴ ለግሪክ ሰዎችና ላልተማሩም፥ ለጥበበኞችና ለማያስተውሉም ዕዳ አለብኝ፤
¹⁵ ስለዚህም በሚቻለኝ መጠን በሮሜ ላላችሁ ለእናንተ ደግሞ ወንጌልን ልሰብክ ተዘጋጅቼአለሁ።

❤3👍1
. ==❀❀❀===❀❀❀==
የዕለቱ ጥቅስ
==❀❀❀===❀❀❀==
“እግዚአብሔርን ለማወቅ ባልወደዱት መጠን እግዚአብሔር የማይገባውን ያደርጉ ዘንድ ለማይረባ አእምሮ አሳልፎ ሰጣቸው፤”
ሮሜ 1፥28

#እራሳችንን_እንመርምር
እምነታችን አለ? ጌታችን በመጣ ጊዜ እምነት ያገኝ ይሆን? እምነታችን የት ደረጃ ይገኛል? የሌለን(ማር. 4፥40)፣ ጎዶሎ(ማቴ 14፥31)፣ ያነሰ(ማቴ 17፥20)፣ ብርቱ(ሮሜ 4፥20-21)፣ የደከመ(ሮሜ 4፥19)፣ በእድገት ደረጃ ላይ ያለ(2ቆሮ 10፥15-16)፣ የተፈተነ(1 ጴጥ. 1፥6-7) ወይስ ትልቅ(ሉቃስ 7፥9)?
“...ነገር ግን የሰው ልጅ በመጣ ጊዜ በምድር እምነትን ያገኝ ይሆንን?”
ሉቃስ 18፥8

❤10
. ==❀❀❀===❀❀❀==
የዕለቱ ጥቅስ
==❀❀❀===❀❀❀==
“ልጅንም አይቶ በእርሱ የሚያምን ሁሉ የዘላለም ሕይወትን እንዲያገኝ የአባቴ ፈቃድ ይህ ነው፥ እኔም በመጨረሻው ቀን አስነሣዋለሁ።”
ዮሐንስ 6፥40

👍6❤1
Audio
👍4
ከአዲስ ኪዳን ቅዱሳት መጻሕፍት ውስጥ "የአዲስ ኪዳን መጽሐፈ ምሳሌ" በመባል የሚታወቀው መጽሐፍ የቱ ነው?
Anonymous Quiz
23%
ሀ. ሮሜ
5%
ለ. 1ኛ ቆሮንቶስ
6%
ሐ. ኤፌሶን
29%
መ. ያዕቆብ
7%
ሠ. ገላትያ
11%
ረ. የዮሐንስ ራእይ
18%
ሰ. የዮሐንስ ወንጌል
👍2❤1
. ==❀❀❀===❀❀❀==
የዕለቱ ጥቅስ
==❀❀❀===❀❀❀==
“ፈርዖንም ጸጥታ እንደሆነ ባየ ጊዜ ልቡን አደነደነ፤ እግዚአብሔርም እንደተናገረ አልሰማቸውም።”
ዘጸአት 8፥15
ወደ ቻናሉ ለመ🀄️ላ🀄️ል፦ @Holy_scriptures
የዕለቱ ጥቅስ
==❀❀❀===❀❀❀==
“ፈርዖንም ጸጥታ እንደሆነ ባየ ጊዜ ልቡን አደነደነ፤ እግዚአብሔርም እንደተናገረ አልሰማቸውም።”
ዘጸአት 8፥15
ወደ ቻናሉ ለመ🀄️ላ🀄️ል፦ @Holy_scriptures
👍2
#ከተማ_ወይም_ቦታ_በቅዱሳት_መጻሕፍት
#የአኮር_ሸለቆ
የአኮርንም ሸለቆ፤ በኢያሪኮ አቅራቢያ የሚገኝ ነው (ኢሱ 7፥1-26፥ 15፥7፤ ኢሳ 65፡10)፡፡ አኮር የሚለው ቃል “ችግር” ማለት ሲሆን ኢያሱም የአካንን ስም ትንሽ ለወጥ በማድረግ “ለምን አስጨነቅኸን?” ሲል ጠየቀው። ( ኢያሱ 7:25 ) አካን ከተገደለ በኋላ የሞተበት ሸለቆ “የአኮር ሸለቆ” የሚል ስም ተሰጠው። ይህ ሸለቆ ከኢያሪኮ በስተ ምዕራብ የሚገኘው ዋዲ ቂልት ሊሆን ይችላል። ሸለቆው፣ በተስፋይቱ ምድር እግዚአብሔር በመጀመሪያ ፍርዱን በሕዝቡ ላይ የገለጠበት ቦታ ሲሆን፣ በሌላ ስፍራ ማለትም ሆሴዕ 2፥17 ላይ ደግሞ የአዲስ ተስፋ ምልክት ሆኖ ተጠቅሶአል።
ምንጭ፦ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ከማጥኛ ጹሑፍ ጋር፤ ገጽ 1319፣ www.waynestiles.com

“ነገር ግን፥ ወንድሞች ሆይ፥ እናንተ የተማራችሁትን ትምህርት የሚቃወሙትን መለያየትንና ማሰናከያን የሚያደርጉትን ሰዎች እንድትመለከቱ እለምናችኋለሁ፥ ከእነርሱ ዘንድ ፈቀቅ በሉ፤”
ሮሜ 16፥17

❤2👍2
ጌታችንና መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በመጀመሪያ የጠራው ደቀ መዝሙር ማን ነው?
Anonymous Quiz
51%
ሀ. ጴጥሮስ
31%
ለ. እንድርያስ
6%
ሐ. ያዕቆብ
11%
መ. ዮሐንስ
1%
ሠ. ይሁዳ
👍2
ቅዱሳት መጻሕፍት
#የሮሜ_መልእክት_ጥናት ሮሜ 9 ¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯ ³⁰ እንግዲህ ምን እንላለን? ጽድቅን ያልተከተሉት አሕዛብ ጽድቅን አገኙ፥ እርሱ ግን ከእምነት የሆነ ጽድቅ ነው፤ ³¹ እስራኤል ግን የጽድቅን ሕግ እየተከተሉ ወደ ሕግ አልደረሱም። ³²-³³ ይህስ ስለ ምንድር ነው? በሥራ እንጂ በእምነት ጽድቅን ስላልተከተሉ ነው፤ እነሆ፥ በጽዮን የእንቅፋት ድንጋይና የማሰናከያ ዓለት አኖራለሁ በእርሱም የሚያምን አያፍርም…
#የሮሜ_መልእክት_ጥናት
የእግዚአብሔር ጸጋ (9:30-33)
ጳውሎስ በመቀጠል ከመለኮታዊ ሉዓላዊነት ወደ ሰው ተጠያቂነት አመራ፡፡ ጳውሎስ «የተመረጡና» «ያልተመረጡ» ከማለት ይልቅ በእምነት ላይ አጽንኦት መስጠቱን አስተውሉ፡፡ እዚህ ላይ የተምታታ ነገር ያለ ይመስላል አይሁድ ጽድቅን ፈለጉ ነገር ግን አላገኙም፡፡ አሕዛብ ግን ሳይፈልጉት አገኙት! ምክንያቱም ምንድን ነው? እስራኤላውያን መዳን የፈለጉት በሥራ እንጂ በእምነት ስላልነበረ ነው፡፡
‹‹በጸጋ የሚገኝን ጽድቅ›› ተቃውመው «በሕግ ጽድቅ›› እግዚአብሔርን ሊያስደስቱ ፈለጉ፡፡ አሕዛብ ለመዳን እንደ እስራኤላውያን መሆን እንዳለባቸው አይሁዳውያን ቆጠሩ፡፡ ነገር ግን አይሁድ ለመዳን ዝቅ ብለው እንደ አሕዛብ መሆን አለባቸው፡፡ ‹‹ልዩነት የለምና፤ ሁሉ ኃጢአትን ሠርተዋል የእግዚአብሔርም ክብር ጐድሎአቸዋል» (ሮሜ 3:22-23):: የተሰጣቸውን ዕድል ወደ ክርስቶስ እንዲመራቸው በማድረግ ፈንታ (ሮሜ 9፡1-5)፣ ክርስቶስን ምትክ አድርገው ተጠቀሙበት፡፡
ነገር ግን የእግዚአብሔርን ጸጋ ካየን፣ የእስራኤል አለማመን የአሕዛብ መዳን ሆነ! የጳውሎስ የመጨረሻው ጥቅስ የተወሰደው ከኢሳይያስ 28:16 ነው:: ይህም ክርስቶስ የደኅንነት ዓለት መሆኑን ይናገራል መዝ. (118)፡22፡፡ እግዚአብሔር ክርስቶስ የመሠረት ድንጋይ እንዲሆን ሰጠን፡፡ ነገር ግን እስራኤል አልተቀበለውምና የማሰናከያ ዓለት ሆነ፡፡ በዚህ ዓለት ላይ «በመቆም» ፋንታ እስራኤል ወደቀች (ሮሜ 11፡11)፤ ነገር ግን እንደምናየው ውድቀታቸው አሕዛብ በእግዚአብሔር ጸጋ እንዲድኑ አስቻለ፡፡ ምን ዓይነት ጽድቅ እንደምንሻ መወሰን አለብን፡፡ ለመዳን በሥራችንና በባሕርያችን ነው የምንመካው ወይስ በክርስቶስ ብቻ ነው የምንታመነው? እግዚአብሔር ሰዎችን በአወላለዳቸው ወይም በባሕርያቸው ላይ ተመርኩዞ አያድናቸውም፡፡ «በእምነት አማካኝነት በጸጋው» (ኤፌ. 2:8-9) ያድናቸዋል:: ጥያቄው ከእግዚአብሔር ምርጦች መካከል መሆን ያለመሆናችን አይደለም፡፡ ይህ በእግዚአብሔር ብቻ የሚታወቅ ምሥጢር ነው፡፡ እርሱ ደኅንነትን በእምነት ሰጥቶናል፡፡ ይህም ዕድል የተሰጠው «ለሚፈልግ» ሁሉ ነው (ራእ. 22፡17)፡፡ በክርስቶስ ካመንን በኋላ ከተመረጡት መሃል ለመሆናችን ምስክርና ማስረጃ ይኖረናል (ኤፌ. 1:414፣ 1ኛ ተሰ. 1፡1-10)፡፡ በመጀመሪያ ግን በእርሱ ታምነን የመንግሥተ ሰማያትን ዋስትና የሚሰጠውን ጽድቁን በእምነት መቀበል ያሻናል፡፡
ከመለኮታዊ ሉዓላዊነት ከሰው ተጠያቂነት ጋር የተያያዙ ብዙ ምሥጢሮች መኖራቸውን ማንም አይክድም፡፡ ሁለቱም ከእግዚአብሔር ስለሚመጡና የዕቅዱም አካል ስለሆኑ፣ ከሁለቱ አንዱን እንድንመርጥ እግዚአብሔር ጠይቆን አያውቅም፡፡ እርስ በርሳቸው አይመካከሩም፣ ይተጋገዛሉ እንጂ፡፡ ሁለቱ ባንድ ላይ እንዴት እንደሚጓዙ አለመረዳታችን አብረው የመሄዳቸውን እውነት አይቃረንም፡፡ አንድ ሰው ቻርልስ ስፐርጀንን እንዴት አድርጎ መለኮታዊ ሉዓላዊነትንና የሰውን ተጠያቂነት እንደሚያስታርቅ ቢጠይቀው፣ ‹‹በጭራሽ ወዳጆችን ለማስታረቅ አልሞክርም!» ሲል መልሶለታል፡፡ ነገር ግን የዚህ ምዕራፍ ጣልቃ መግባት ግልጽ ነው፡፡ ይህም የእስራኤል ክርስቶስን አለመቀበል የእግዚአብሔርን ታማኝነት አያስቀርም:: ሮሜ 9 ሮሜ 8ን አይሽርም፡፡ እግዚአብሔር አሁንም ታማኝ፣ ጻድቅ፣ ትክክልና ቸር ሲሆን፣ ዓላማውንና ቃል ኪዳኑን እንደሚፈጽም ልንታመንበት እንችላለን፡፡
ምንጭ፦ ዋረን ደብልዩ ዌርዝ ቢ፤ ተስማማ፤ ገጽ 101-102

👍4❤2
. ==❀❀❀===❀❀❀==
የዕለቱ ጥቅስ
==❀❀❀===❀❀❀==
“የእስራኤል ጌታ አምላክ ይባረክ፥ ጐብኝቶ ለሕዝቡ ቤዛ አድርጎአልና፤”
ሉቃስ 1፥68

በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ እስራኤላውያን የኢያርኮ ቅጥሩ ሳይፈርስ በአጠቃላይ ስንት ጊዜ ኢያሪኮን ዞሩ?
Anonymous Quiz
11%
ሀ. 13
3%
ለ. 3
69%
ሐ. 7
17%
መ. 6
👍5
. ==❀❀❀===❀❀❀==
የዕለቱ ጥቅስ
==❀❀❀===❀❀❀==
“ከወገናችንም ያሉት ደግሞ ፍሬ ቢሶች ሆነው እንዳይቀሩ፥ የግድ ስለሚያስፈልገው ነገር በመልካም ሥራ እንዲጸኑ ይማሩ።”
ቲቶ 3፥14