ቅዱሳት መጻሕፍት
7.45K subscribers
1.36K photos
61 videos
332 files
807 links
በዚህ ቻናል

👉ቅዱሳት መጻሕፍት ይጠናሉ::
👉መጽሐፍ ቅዱሳዊ ትምህርቶች ይቀርባሉ::
👉 ለቅዱሳት መጽሐፍት ጥናት የሚያግዙ መጻሕፍት ይለቀቃሉ።

⭐️⭐️⭐️⭐️⭐️

@Holy_scriptures
Download Telegram
.    ==❀❀❀===❀❀❀==      
         🌼  የዕለቱ ጥቅስ  🌼
     ==❀❀❀===❀❀❀==
“ሥርዓቴንም አድርጉ፥ ፍርዶቼንም ጠብቁ አድርጉትም በምድሪቱም ውስጥ በጸጥታ ትኖራላችሁ።”
ዘሌዋውያን 25፥18



ወደ ቻናሉ ለመ🀄️🀄️ል፦ @Holy_scriptures
7
ቅዱሳት መጻሕፍት
ነቢዩ ኤርምያስ                            ክፍል-፪ ኤርምያስ መቼ እንደ ሞተ፣ የት እንደ ሞተ፣ ወይም እንዴት እንደ ሞተ በርግጥ የሚታወቅ ነገር የለም፡፡ በ44፥29- 30 መሠረት ኤርምያስ በ570 ዓመተ ቅድመ ክርስቶስ አካባቢም በሕይወት ነበር (ፈርዖን ሆፍራ (ኤፕሬስ) ከ588-569 ድረስ ገብቶአል፡፡ በልዩ የእግዚአብሔር መግቦት ሙሉ ሕይወቱን ግብፅን በመቃወም ያሳለፈው ነቢዩ…
ነቢዩ ኤርምያስ



                        ክፍል-



በጊዜው የነበሩ ሁነቶች የኤርምያስን ትንቢት ለመገንዘብ የነበረበትን ዘመን በትኵረት ማየትን ይጠይቃል፤ ምክንያቱም

(1) በዘመኑ የነበሩትን በፖለቲካው ዓለም የተከሠቱትን ወሳኝ ሁኔታዎች ማጤን ይጠይቃል፤ እነዚህም ሁኔታዎች ይሁዳ በቀጥታ የተነካችባቸው ሁኔታዎች ናቸው፡፡ እንዲሁም

(2) ከኤርምያስ ጋር ግንኙነት የነበራቸውን በእርሱ የአገልግሎት ዘመንም የነበሩትን የይሁዳ ነገሥታት ማንነት ማጤን ይጠይቃል፡፡ ኤርምያስ አገር ዐቀፋዊና ዓለም ዐቀፋዊ ሰው ነበር፡፡ የጊዜንና የሁኔታን ቅደም ተከተል ጠብቆ የሚጓዝ ሰንጠረዥ የኤርምያስን አገልግሎት ከትንቢተ መጽሐፍ አንጻር በዐይነ ኅሊና ለማየት ይረዳል፡፡

🗒639-609 የኢዮስያስ ዘመነ መንግሥት
🗒609 (3 ወር) የአካዝያስ ዘመነ መንግሥት
🗒609 - 597 የኢዮአቄም ዘመን መንግሥት
🗒597 (3 ወር) የዮአኪን ዘመነ መንግሥት
🗒597-586 የሴዴቅያስ ዘመነ መንግሥት
🗒586 የኢየሩሳሌም መውደቅ
🗒586 (?) የጎዶልያስ መገደል

የኤርምያስ ዘመናት በብሉይ ኪዳን ታሪክ ውስጥ ዐበይት ከሆኑት ጒዳዮች መካከል የሚመደቡ ናቸው፡፡ ፋይዳ ያላቸው በመሆናቸውም ከእስራኤል ሙሉ ታሪክ ሁሉ እጅግ በላቀ ሁኔታ ሰነድ ላይ የሰፈሩ ናቸው:: ትንቢተ ኤርምያስ በታሪካዊ፣ በሕይወት ታሪካዊና በግል ታሪካዊ ይዘት የተሞላ በመሆኑ፣ ከሌሎች ነቢያት ጋር በማይወዳደር ሁኔታ፣ ሕይወቱ ከወቅቶችና ከታወቁ ሁኔታዎች ጋር ተያይዞ ሊሆን ይችላል:: በዚህ ወቅት ዐበይት የሆኑትና ፋይዳ ያላቸው ሁኔታዎችም
የሚከተሉት ናቸው፡፡

🗒669-ገደማ 630 ከአሹርበኒፓል ሞት በኋላ የአሦር መንግሥት መፍረስ
🗒626 የኤርምያስ መጠራት
🗒612 የነነዌና የአሦራውያን መንግሥት መውደቅ
🗒609 በመጊዶ ኢዮስያስ መሞቱ
🗒605 በከርከሚሽ ባቢሎናውያን ድል አድራጊ ሆነው የታዩበት በግብፅና በባቢሎናውያን መካከል የተካሄደ ጦርነት
🗒605 ናቡከደነፆር ለመጀመሪያ ጊዜ ኢየሩሳሌምን መውረሩ (ዳንኤል ወደ ባቢሎን ተጋዘ
🗒597 ኢየሩሳሌም ለሁለተኛ ጊዜ መወረሯ (ሕዝቅኤል ወደ ባቢሎን ተጋዘ)
🗒588-586 ባቢሎናውያን ያካሄዱት ምርኮ
መጀመሩና ኢየሩሳሌም ለመጨረሻ ጊዜ መወረሯ
የናቡከደነፆር አባትና አሦርን ድል ያደረገው ናቡፓላስር በደቡባዊ ባቢሎን ከምትገኘው ከከለዳውያን ምድር፣ ከ625-605 ገዛ::

ከባቢሎን ነገሥታት በእጅጉ ዝነኛ የነበረው ናቡከደነፆር ከ605-562 ገዛ::
በመልክአ ምድርና በፖለቲካ ረገድ ይሁዳ፣ በግብፅና በአሦር የኀይል ፖለቲካ መካከል ለሥጋት በሚያጋልጥ ሁኔታ ትገኝ ነበር:: በስምንተኛው ምእት ዓመት ቅድመ ክርስቶስ ኢሳይያስ በግብፅ ላይ መተማመንን በመቃወም ማስጠንቀቂያ ሰጥቶ ነበር (ኢሳ 30፥ 1-7)፡፡ አሦር የይሁዳ ሥጋት መሆኗንም በሚገባ መዝኖ ነበር (ኢሳ 37)፡፡ በእግዚአብሔር ጥበቃ የይሁዳ መንግሥት ከሰናክሬም ኀይል አመለጠ፡፡ ነገር ግን ፈሪሀ እግዚአብሔር ከነበረበት ከሕዝቅያስ ዘመነ መንግሥት በማሸቈልቈል፣ ፈረሀ እግዚአብሔር አልባ ወደ ነበረው ወደ ምናሴ መንግሥት መንፈሳዊ ዝቅጠት ወረደ (2ነገ 21 ፥ 9-15፤ 24፥3-4)፡፡ ኤርምያስ ሃያ ዓመት እንደ ሞላው አካባቢ ተጠርቶ ከሆነ፣ በምናሴና በአሞን የአገዛዝ ዘመናት ኖሮአል ማለት ነው። በምናሴ ረጅም የኀምሳ ዓመት የክሕደት ዘመን ውስጥ ፈሪሀ እግዚአብሔር ያደረበት የአባቱ የሕዝቅያስ ተሐድሶዎች ተረስተው ነበር፡፡ በዚያ ዘመን ይሁዳ በአሦር ሥልጣን ሥር ነበረች፤ ስለዚህ አለቆቹን ለማስደሰት ሲል ምናሴ ኢየሩሳሌም በነበረው የቤተ መቅደስ አምልኮ ውስጥ ቅይጥ ነገሮችን አስገባ፡፡ የሰሜኑ መንግሥት (እስራኤል) ቀደም ሲል ተግዞአል (722)፤ በዚያ የነበሩት ትሩፋንም በእምነታቸው ውስጥ ቅይጥ ነገርን ዐቅፈው ይዘው ነበር (2ነገ 17፥28)፡፡ በአስራዶንና በአሹርባኒ ፖል የአገዛዝ ዘመናት የአሦር ኀይል ግብፅን ድል አደረገ፤ ሆኖም በኋላ የመጣው መንግሥት በቀደማዊ ስሜቲክ ዘመን (664-609) በኀይል አንሰራራ፤ ስለዚህ ይሁዳ የሁለቱን የኀይል ሚዛን በመጠበቅ ረገድ ተወጥራ ነበር፡፡


ይቀጥላል...



🚨ማሳሰቢያ የጊዜ አቆጣጠር ካልተጠቀሰ በቀር ዓመተ ቅድመ ክርስቶስ ነው።



ምንጭ፦ የብሉይ ኪዳን ማብራሪያ፤ ገጽ 824-825




ወደ ቻናሉ ለመ🀄️🀄️ል፦ @Holy_scriptures
👍93
.    ==❀❀❀===❀❀❀==      
         🌼  የዕለቱ ጥቅስ  🌼
     ==❀❀❀===❀❀❀==
“አምላክህን መፍራትህ መጽናናትህ፥ የቅንነትህም መንገድ ተስፋህ አይደለምን?”
ኢዮብ 4፥6



ወደ ቻናሉ ለመ🀄️🀄️ል፦ @Holy_scriptures
6
ከሚከተሉት መካከል ከታናናሽ ነቢያት የሚመደበው የቱ ነው?
Anonymous Quiz
1%
ሀ. ኢሳይያስ
4%
ለ. ኤርምያስ
5%
ሐ. ሕዝቅኤል
8%
መ. ዳንኤል
82%
ሠ. ሚልክያስ
ወደ ቻናሉ ለመ🀄️🀄️ል፦ @Holy_scriptures
የብልጽግና ወንጌል.pdf
6.7 MB
👉ርዕስ፦ የብልጽግና ወንጌል
"የዘመኑ የእምነት እንቅስቃሴ መሠረቶችና መዘዞች"
ጸሐፊ፦ ግርማዊ
📄የገጽ ብዛት፦ 169


ወደ ቻናሉ ለመ🀄️🀄️ል፦ @Holy_scriptures
👎2👍1
.    ==❀❀❀===❀❀❀==      
         🌼  የዕለቱ ጥቅስ  🌼
     ==❀❀❀===❀❀❀==
“በምሕረትና በእውነት ኃጢአት ትሰረያለች፥ እግዚአብሔርንም በመፍራት ሰው ከክፋት ይመለሳል።”
ምሳሌ 16፥6




ወደ ቻናሉ ለመ🀄️🀄️ል፦ @Holy_scriptures
👍61
ከቅዱሳት መጻሕፍት ውስጥ ከአንድ በላይ ምእራፍ ያለው መጽሐፍ የቱ ነው?
Anonymous Quiz
10%
ሀ. አብድዩ
11%
ለ. ይሁዳ
61%
ሐ. አሞጽ
18%
መ. 3ኛ ዮሐንስ
👍51
.    ==❀❀❀===❀❀❀==      
         🌼  የዕለቱ ጥቅስ  🌼
     ==❀❀❀===❀❀❀==
“በተወደደ ሰዓት ሰማሁህ በመዳንም ቀን ረዳሁህ ይላልና፤ እነሆ፥ የተወደደው ሰዓት አሁን ነው፤እነሆ፥ የመዳን ቀን አሁን ነው።”
2ኛ ቆሮ 6፥2




ወደ ቻናሉ ለመ🀄️🀄️ል፦ @Holy_scriptures
10👍2
Audio
👉ርዕስ፦ የመናኝ ጉዞ
ጸሐፊ፦ ዮሐንስ ቡንያን

የቻናላችን ቤተሰቦች በተደጋጋሚ በጠየቃችሁን መሠረት ይኸው በትረካ ተከስተናል። የመናኝ ጉዞ መጽሐፍ የመጀመሪያው ክፍል እነሆ። ክፍል ሁለት ይቀጥላል...


ወደ ቻናሉ ለመ🀄️🀄️ል፦ @Holy_scriptures
🔥1
.    ==❀❀❀===❀❀❀==      
         🌼  የዕለቱ ጥቅስ  🌼
     ==❀❀❀===❀❀❀==
“ለዋኖቻችሁ ታዘዙና ተገዙ፤ እነርሱ ስሌትን እንደሚሰጡ አድርገው፥ ይህንኑ በደስታ እንጂ በኃዘን እንዳያደርጉት፥ ይህ የማይጠቅማችሁ ነበርና፥ ስለ ነፍሳችሁ ይተጋሉ።”
ዕብራውያን 13፥17




ወደ ቻናሉ ለመ🀄️🀄️ል፦ @Holy_scriptures
1👍1
ከትንቢት መጻሕፍት መካከል "ኢይዝራኤል" የሚለው ስም በብዛት የተጠቀሰው የት ነው?
Anonymous Quiz
19%
ሀ. ኢሳይያስ
49%
ለ. ሆሴዕ
11%
ሐ. ኤርምያስ
21%
መ. ሕዝቅኤል
7👍4👏1
#ከተማ_ወይም_ቦታ_በቅዱሳት_መጻሕፍት



#ኢይዝራኤል

የቃሉ ትርጒም እግዚአብሔር ይበትናል ወይም «እግዚአብሔር ይዘራል» ማለት ነው። የሆሴዕ ታላቅ ልጅ ስያሜም ነው። ከቦታው ስንጀምር የይሁዳ ከተማ፤ ኢያሱ 15፥56፤ 1ሳሙ. 25፥43። በይሳኮር ርስት ድርሻ ውስጥ ነበረ። በከተማውም አቅራቢያ ያለው ሰፊ ሸለቆ በዚህ ስም ተጠራ፤ ኢያሱ 19፥18፤ ሆሴዕ 1፥5። የናቡቴ ወይን ቦታ በዚያ ነበረ፤ 1ነገ. 20። በዚያም ኢዩ የአክዓብን ቤተ ሰዎችና አለቆች አስፈጀ፤ 2ነገ. 9፥ 17-10፥11። በዚህ ስፍራ በገዦች ላይ ይፈጸም ዘንድ የተነገረውን ፍርድ የሚያጸና ነው፡፡ ዳግማዊ ኢዮርብዓም፣ የአክአብን ልጅ የኢዮራምን መንግሥት በመገልበጥ (2ነገ 9፥14-37፤ ከ1ነገ19፥16-17) በኢይዝራኤል ከተመሠረተው ከኢዩ ሥርወ መንግሥት የመጣ ነው (በ841-814 ዓመተ ቅድመ ክርስቶስ)፤ የኢዩ ሥርወ መንግሥት ያከተመው ዘካርያስ በተገደለበት በ753 ዓመተ ቅድመ ክርስቶስ ነው (2ነገ 15፥8-10)፡፡

ለሆሴዕና ለጎሜር ሦስት ልጆች ተወለዱ፤ ለእያንዳንዳቸውም ትእምርታዊ ስም ተሰጥቶአቸዋል፡፡ “ኢይዝራኤል” የሚለው ስም የሚያመለክተው፣ ኢዩ ያፈሰሰውን “ደም” ለመበቀል እግዚአብሔር በቅጣት የሚነሣበትን የወደፊቱን ቀን ነው፡፡ ኢዩ የእግዚአብሔርን ትእዛዝ በመፈጸሙ መልካም ቢያደርግም (2ነገ 9፥1-10)፣ እግዚአብሔር ካዘዘው በላይ ብዙ ሰዎችን ገድሎ ነበር፡፡ የኢዩ ኀጢአት የተቀጣው እስራኤል መንግሥት መሆኗ እንዲቆም በመደረጉ ነበር (ይህ በ722 ዓመተ ቅድመ ክርስቶስ ሆኖአል)፡፡



ምንጭ፦ የመጽሐፍ ቅዱስ መዝገበ ቃላት፤ ገጽ 170፣ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ከማጥኛ ጹሑፍ ጋር፤ ገጽ 1318፣ የብሉይ ኪዳን ማብራሪያ፤ ገጽ 1005



ወደ ቻናሉ ለመ🀄️🀄️ል፦ @Holy_scriptures
👍121
.    ==❀❀❀===❀❀❀==      
         🌼  የዕለቱ ጥቅስ  🌼
     ==❀❀❀===❀❀❀==
“ጻድቅ ግን መንገዱን ያጠነክራል፥ እጁም ንጹሕ የሆነ ሰው ኃይልን እየጨመረ ይሄዳል።”
ኢዮብ 17፥9




ወደ ቻናሉ ለመ🀄️🀄️ል፦ @Holy_scriptures
👍7
ከሚከተሉት መካከል የያዕቆብ ልጅ ያልሆነው የቱ ነው?
Anonymous Quiz
14%
ሀ. ዛብሎን
41%
ለ. ኤፍሬም
3%
ሐ. ንፍታሌም
4%
መ. ዳን
10%
ሠ. ሁሉም
28%
ረ. መልስ የለም
8👍1
.    ==❀❀❀===❀❀❀==      
         🌼  የዕለቱ ጥቅስ  🌼
     ==❀❀❀===❀❀❀==
“ለሁላችን አንድ አባት ያለን አይደለምን? አንድ አምላክስ የፈጠረን አይደለምን? የአባቶቻችንን ቃል ኪዳን ለማስነቀፍ እኛ እያንዳንዳችን ወንድማችንን ስለ ምን አታለልን?”
ሚልክያስ 2፥10



ወደ ቻናሉ ለመ🀄️🀄️ል፦ @Holy_scriptures
6👍1
ከአራቱ ወንጌላት መካከል በይበልጥ ስለኢየሱስ ክርስቶስ የእግዚአብሔር ልጅነት የሚያስረዳው የቱ ነው?
Anonymous Quiz
11%
ሀ. ማቴዎስ
6%
ለ. ማርቆስ
11%
ሐ. ሉቃስ
72%
መ. ዮሐንስ
4😁3👏2
#የእግዚአብሔር_ቃል_ምን_ይላል?


1ኛ ጢሞቴዎስ 1
¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯
³-⁴ ወደ መቄዶንያ በሄድሁ ጊዜ፥ አንዳንዶች ልዩ ትምህርትን እንዳያስተምሩና ወደ ተረት መጨረሻም ወደሌለው ወደ ትውልዶች ታሪክ እንዳያደምጡ ልታዛቸው በኤፌሶን ትቀመጥ ዘንድ ለመንሁህ፤ እንደ እነዚህ ያሉ ነገሮች ክርክርን ያመጣሉና በእምነት ግን ላለ ለእግዚአብሔር መጋቢነት አይጠቅሙም።
⁵ የትእዛዝ ፍጻሜ ግን ከንጹሕ ልብና ከበጎ ሕሊና ግብዝነትም ከሌለበት እምነት የሚወጣ ፍቅር ነው፤
⁶-⁷ ከእነዚህም አንዳንዶች ስተው፥ የሚሉትን ወይም ስለ እነርሱ አስረግጠው የሚናገሩትን ሳያስተውሉ፥ የሕግ አስተማሪዎች ሊሆኑ እየወደዱ፥ ወደ ከንቱ ንግግር ፈቀቅ ብለዋል።
⁸ ነገር ግን ሰው እንደሚገባ ቢሰራበት ሕግ መልካም እንደ ሆነ እናውቃለን፤
⁹-¹¹ ይኸውም፥ ለበደለኞችና ለማይታዘዙ፥ ለዓመጸኞችና ለኃጢአተኞች፥ ቅድስና ለሌላቸውና ለርኵሳን፥ አባትና እናትን ለሚገድሉ፥ ለነፍሰ ገዳዮችና ለሴሰኞች፥ ከወንድ ጋርም ለሚተኙ፥ በሰዎችም ለሚነግዱ፥ ለውሸተኞችም በውሸትም ለሚምሉ፥ የብሩክ እግዚአብሔርንም ክብር እንደሚገልጥ ለእኔ አደራ እንደ ተሰጠኝ ወንጌል የሆነውን ደኅና ትምህርት ለሚቃወም ለሌላ ነገር ሁሉ ሕግ እንደ ተሰራ እንጂ ለጻድቅ እንዳልተሰራ ሲያውቅ ነው።
¹² ለአገልግሎቱ ሾሞኝ ታማኝ አድርጎ ስለ ቈጠረኝ፥ ኃይል የሰጠኝን ክርስቶስ ኢየሱስን ጌታችንን አመሰግናለሁ፤
¹³ አስቀድሞ ተሳዳቢና አሳዳጅ አንገላችም ምንም ብሆን፥ ይህን አደረገልኝ፤ ነገር ግን ሳላውቅ ባለማመን ስላደረግሁት ምህረትን አገኘሁ፥
¹⁴ የጌታችንም ጸጋ በክርስቶስ ኢየሱስ ካሉ ከእምነትና ከፍቅር ጋር አብልጦ በዛ።
¹⁵ ኃጢአተኞችን ሊያድን ክርስቶስ ኢየሱስ ወደ ዓለም መጣ የሚለው ቃል የታመነና ሁሉ እንዲቀበሉት የተገባ ነው፤ ከኃጢአተኞችም ዋና እኔ ነኝ፤
¹⁶ ስለዚህ ግን፥ የዘላለምን ሕይወት ለማግኘት በእርሱ ያምኑ ዘንድ ላላቸው ሰዎች ምሳሌ እንድሆን፥ ኢየሱስ ክርስቶስ ዋና በምሆን በእኔ ላይ ትዕግስቱን ሁሉ ያሳይ ዘንድ፥ ምህረትን አገኘሁ።
¹⁷ ብቻውን አምላክ ለሚሆን ለማይጠፋው ለማይታየውም ለዘመናት ንጉሥ ምስጋናና ክብር እስከ ዘላለም ድረስ ይሁን፤ አሜን።
¹⁸ ጢሞቴዎስ ልጄ ሆይ፥ አስቀድሞ ስለ አንተ እንደ ተነገረው ትንቢት፥ በእርሱ መልካም ጦርነት ትዋጋ ዘንድ ይህችን ትእዛዝ አደራ እሰጥሃለሁ፤
¹⁹ እምነትና በጎ ሕሊና ይኑርህ፥ አንዳንዶች ሕሊናን ጥለው፥ መርከብ አለ መሪ እንደሚጠፋ፥ በእምነት ነገር ጠፍተዋልና፤
²⁰ ከእነዚያም፥ እንዳይሳደቡ ይማሩ ዘንድ ለሰይጣን አሳልፌ የሰጠኋቸው፥ ሄሜኔዎስና እስክንድሮስ ናቸው።




ወደ ቻናሉ ለመ🀄️🀄️ል፦ @Holy_scriptures
5👍4
.    ==❀❀❀===❀❀❀==      
         🌼  የዕለቱ ጥቅስ  🌼
     ==❀❀❀===❀❀❀==
“በጸሎትና በልመናም ሁሉ ዘወትር በመንፈስ ጸልዩ፤ በዚህም አሳብ ስለ ቅዱሳን ሁሉ እየለመናችሁ በመጽናት ሁሉ ትጉ፤”
ኤፌሶን 6፥18




ወደ ቻናሉ ለመ🀄️🀄️ል፦ @Holy_scriptures
👍61
#እራሳችንን_እንመርምር

በዚህ ዘመን ብዙ ነገር ያስከትለናል። ተከታይም ብዙ ነው። ነገር ግን ምን ብንከተል ያዋጣናል? ለምን?


“ከክፉ ሽሽ መልካምንም አድርግ፤ ሰላምን እሻ ተከተላትም።”
መዝሙር 34፥14


“ከክፉ የጎልማሳነት ምኞት ግን ሽሽ፥ በንጹሕም ልብ ጌታን ከሚጠሩ ጋር ጽድቅን እምነትን ፍቅርን ሰላምን አጥብቀህ ተከተል።”
2ኛ ጢሞቴዎስ 2፥22


“አንተ ግን ትምህርቴንና አካሄዴን አሳቤንም እምነቴንም ትዕግሥቴንም ፍቅሬንም መጽናቴንም ስደቴንም መከራዬንም ተከተልህ፤”
2ኛ ጢሞቴዎስ 3፥10





ወደ ቻናሉ ለመ🀄️🀄️ል፦ @Holy_scriptures
9👍1