#አዲስ_ዓመት
ውድ የቻናላችን ቤተሰቦች እንኳን አደረሳችሁ! መጪው ዘመን መጻሕፍትን እናስተውል ዘንድ አእምሮአችን የሚከፈትበት ዘመን ይሁንልን!
“በዚያን ጊዜም መጻሕፍትን ያስተውሉ ዘንድ አእምሮአቸውን ከፈተላቸው፤”
ሉቃስ 24፥45
🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼
🌼🌼መልካም አዲስ አመት🌼🌼
🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼
ወደ ቻናሉ ለመ🀄️ላ🀄️ል፦ @Holy_scriptures

❤8👍2🔥2
. ==❀❀❀===❀❀❀==
🌼 የዕለቱ ጥቅስ 🌼
==❀❀❀===❀❀❀==
“ከማናቸውም ዓይነት ክፉ ነገር ራቁ።”
1ኛ ተሰሎንቄ 5፥22
ወደ ቻናሉ ለመ🀄️ላ🀄️ል፦ @Holy_scriptures
🌼 የዕለቱ ጥቅስ 🌼
==❀❀❀===❀❀❀==
“ከማናቸውም ዓይነት ክፉ ነገር ራቁ።”
1ኛ ተሰሎንቄ 5፥22
ወደ ቻናሉ ለመ🀄️ላ🀄️ል፦ @Holy_scriptures
❤9
. ==❀❀❀===❀❀❀==
🌼 የዕለቱ ጥቅስ 🌼
==❀❀❀===❀❀❀==
“የትእዛዝ ፍጻሜ ግን ከንጹሕ ልብና ከበጎ ሕሊና ግብዝነትም ከሌለበት እምነት የሚወጣ ፍቅር ነው፤”
1ኛ ጢሞቴዎስ 1፥5

❤5
#አዲስ_ዓመት
የሕሊና ዓይነቶች
በቅዱሳት መጻሕፍት በተለይም በአዲስ ኪዳን ይባስ ብሎም ደግሞ በሐዋርያው ቅዱስ ጳውሎስ ትምህርት "#ሕሊና" የሚለው አሳብ ተደጋግሞ ይነሳል። በአዲስ ዓመት እንዲህ አይነት አሳብ አንስተን መወያየት ግድ ይለናልና እነሆ ብለን። ከታች ከተዘረዘሩት ለአንድ ክርስቲያን የሚያስፈልገውና የግሉ ሊያደርገው ሊጋደልበት የሚገባው የቱ ነው? ለምን?
1. ክፉ ሕሊና
ክፉ ሕሊና ተበላሽቶ ወደ ሥነ ምግባር ዝቅጠት የሚመራ ነው። ይህ ሕሊና የእግዚአብሔርን ፈቃድ የሚጻረር እና የኃጢያት ባህሪን የሚያበረታታ ነው። (ዕብ. 10፥22)
2. የረከሰ ሕሊና
የረከሰ ሕሊና በኃጢአት የረከሰና ግልጽ የሆነ የሞራል ልዩነት ማድረግ የማይችል ነው። ትክክል እና
ስህተት መካከል ወደ ግራ መጋባት ይመራል። (ቲቶ. 1፥15)
3. የደነዘዘ ሕሊና
የደነዘዘ ሕሊና ማለት በድግግሞሽ ኃጢአት የተዳከመ ወይም የደነደነ ነው። ከጊዜ በኋላ
ሰውየው ለጥፋተኝነት ወይም ለጥፋተኝነት ግድየለሽ ይሆናል። ኃጢአትን እንደ ስህተት አይገነዘብም። (1ኛ ጢሞ.
4፥2)
4. ደካማ ሕሊና
ደካማ ሕሊና የሚያመለክተው ኃጢአት በሌለበት አካባቢም እንኳ በቀላሉ ሊኮነን የሚችል ያልበሰለ
ወይም ከልክ ያለፈ ስስ ሕሊና ነው። ይህ ሊሆን የሚችለው አንድ ሰው በተፈጥሮ ኃጢአተኛ ያልሆኑ የሥነ ምግባር ጉዳዮች ላይ እርግጠኛ ካልሆነ ነው። (1ኛ ቆሮ. 8፥7)
5. ንጹሕ ሕሊና
ንፁህ ህሊና ማለት ከጥፋተኝነት እና ከነቀፋ በጸዳ መልኩ በእግዚአብሔርና በሰው ፊት መኖር ፣ በታማኝነት እና በመታዘዝ መመላለስ ማለት ነው። (ሐዋ. 24፥16)
6. በጎ ሕሊና
በጎ ሕሊና ከእግዚአብሔር እውነት ጋር የሚስማማ እና ወደ ጽድቅ ሕይወት የሚመራ ነው። ግለሰቡ
ይቅርታን እንዲጠይቅ እና የሞራል ህይወት እንዲጠብቅ የሚገፋፋው ለኃጢያት እና የጥፋተኝነትን ድንበር በማወቅ ለእነዚህ ነገሮች ንቁ የሆነ ነው። (1 ጢሞ. 1፥19)

👍14🔥1
. ==❀❀❀===❀❀❀==
🌼 የዕለቱ ጥቅስ 🌼
==❀❀❀===❀❀❀==
“ስለዚህ እኔ ደግሞ በእግዚአብሔርና በሰው ፊት ሁልጊዜ ነውር የሌለባት ሕሊና ትኖረኝ ዘንድ እተጋለሁ።”
ሐዋርያት 24፥16

❤8
. ==❀❀❀===❀❀❀==
🌼 የዕለቱ ጥቅስ 🌼
==❀❀❀===❀❀❀==
“ለሥራ ከመትጋት አትለግሙ፤ በመንፈስ የምትቃጠሉ ሁኑ፤ ለጌታ ተገዙ፤”
ሮሜ 12፥11

👍8❤2
#እራሳችንን_እንመርምር
እስቲ እራሳችንን እንጠይቅ፣ ብዙ ዘመን ጸልየናል፣ ቃሉን አንብበናል ከማንበብም አልፈን አጥንተናል። ይህ ብቻ ሳይሆን የቅዱሳንን ጉባዔ በብዛት ተካፍለናል። ነገር ግን መንፈሳዊ ሰው ሆነናል ወይስ "ጸላይ"፣ "የእግዚአብሔር ቃል እውቀት ያለው/ላት"፣ "የቤተክርስቲያን ሰው" ብቻ እየተባልን እንገኛለን? ለመሆኑ እነዚህን ነገሮች ማዘውተር ጥቅሙ ምንድነው? የእግዚአብሔርስ ቃል ስለእነዚህ ነገሮች ምን ይላል? ታዲያ ከእነዚህ ነገሮች ልናገኘው የሚገባንን ጥቅም እያገኘን ነው? ካላገኘን ለምን?
“ነገር ግን ከዚያ አምላካችሁን እግዚአብሔርን ትሻላችሁ፤ በልብህም ሁሉ በነፍስህም ሁሉ የፈለግኸው እንደ ሆነ ታገኘዋለህ።”
ዘዳግም 4፥29

❤6👍2
. ==❀❀❀===❀❀❀==
🌼 የዕለቱ ጥቅስ 🌼
==❀❀❀===❀❀❀==
“ሥርዓቴንም አድርጉ፥ ፍርዶቼንም ጠብቁ አድርጉትም በምድሪቱም ውስጥ በጸጥታ ትኖራላችሁ።”
ዘሌዋውያን 25፥18

❤7
ቅዱሳት መጻሕፍት
ነቢዩ ኤርምያስ ክፍል-፪ ኤርምያስ መቼ እንደ ሞተ፣ የት እንደ ሞተ፣ ወይም እንዴት እንደ ሞተ በርግጥ የሚታወቅ ነገር የለም፡፡ በ44፥29- 30 መሠረት ኤርምያስ በ570 ዓመተ ቅድመ ክርስቶስ አካባቢም በሕይወት ነበር (ፈርዖን ሆፍራ (ኤፕሬስ) ከ588-569 ድረስ ገብቶአል፡፡ በልዩ የእግዚአብሔር መግቦት ሙሉ ሕይወቱን ግብፅን በመቃወም ያሳለፈው ነቢዩ…
ነቢዩ ኤርምያስ
ክፍል-፫
በጊዜው የነበሩ ሁነቶች የኤርምያስን ትንቢት ለመገንዘብ የነበረበትን ዘመን በትኵረት ማየትን ይጠይቃል፤ ምክንያቱም
(1) በዘመኑ የነበሩትን በፖለቲካው ዓለም የተከሠቱትን ወሳኝ ሁኔታዎች ማጤን ይጠይቃል፤ እነዚህም ሁኔታዎች ይሁዳ በቀጥታ የተነካችባቸው ሁኔታዎች ናቸው፡፡ እንዲሁም
(2) ከኤርምያስ ጋር ግንኙነት የነበራቸውን በእርሱ የአገልግሎት ዘመንም የነበሩትን የይሁዳ ነገሥታት ማንነት ማጤን ይጠይቃል፡፡ ኤርምያስ አገር ዐቀፋዊና ዓለም ዐቀፋዊ ሰው ነበር፡፡ የጊዜንና የሁኔታን ቅደም ተከተል ጠብቆ የሚጓዝ ሰንጠረዥ የኤርምያስን አገልግሎት ከትንቢተ መጽሐፍ አንጻር በዐይነ ኅሊና ለማየት ይረዳል፡፡
🗒639-609 የኢዮስያስ ዘመነ መንግሥት
🗒609 (3 ወር) የአካዝያስ ዘመነ መንግሥት
🗒609 - 597 የኢዮአቄም ዘመን መንግሥት
🗒597 (3 ወር) የዮአኪን ዘመነ መንግሥት
🗒597-586 የሴዴቅያስ ዘመነ መንግሥት
🗒586 የኢየሩሳሌም መውደቅ
🗒586 (?) የጎዶልያስ መገደል
የኤርምያስ ዘመናት በብሉይ ኪዳን ታሪክ ውስጥ ዐበይት ከሆኑት ጒዳዮች መካከል የሚመደቡ ናቸው፡፡ ፋይዳ ያላቸው በመሆናቸውም ከእስራኤል ሙሉ ታሪክ ሁሉ እጅግ በላቀ ሁኔታ ሰነድ ላይ የሰፈሩ ናቸው:: ትንቢተ ኤርምያስ በታሪካዊ፣ በሕይወት ታሪካዊና በግል ታሪካዊ ይዘት የተሞላ በመሆኑ፣ ከሌሎች ነቢያት ጋር በማይወዳደር ሁኔታ፣ ሕይወቱ ከወቅቶችና ከታወቁ ሁኔታዎች ጋር ተያይዞ ሊሆን ይችላል:: በዚህ ወቅት ዐበይት የሆኑትና ፋይዳ ያላቸው ሁኔታዎችም
የሚከተሉት ናቸው፡፡
🗒669-ገደማ 630 ከአሹርበኒፓል ሞት በኋላ የአሦር መንግሥት መፍረስ
🗒626 የኤርምያስ መጠራት
🗒612 የነነዌና የአሦራውያን መንግሥት መውደቅ
🗒609 በመጊዶ ኢዮስያስ መሞቱ
🗒605 በከርከሚሽ ባቢሎናውያን ድል አድራጊ ሆነው የታዩበት በግብፅና በባቢሎናውያን መካከል የተካሄደ ጦርነት
🗒605 ናቡከደነፆር ለመጀመሪያ ጊዜ ኢየሩሳሌምን መውረሩ (ዳንኤል ወደ ባቢሎን ተጋዘ
🗒597 ኢየሩሳሌም ለሁለተኛ ጊዜ መወረሯ (ሕዝቅኤል ወደ ባቢሎን ተጋዘ)
🗒588-586 ባቢሎናውያን ያካሄዱት ምርኮ
መጀመሩና ኢየሩሳሌም ለመጨረሻ ጊዜ መወረሯ
የናቡከደነፆር አባትና አሦርን ድል ያደረገው ናቡፓላስር በደቡባዊ ባቢሎን ከምትገኘው ከከለዳውያን ምድር፣ ከ625-605 ገዛ::
ከባቢሎን ነገሥታት በእጅጉ ዝነኛ የነበረው ናቡከደነፆር ከ605-562 ገዛ::
በመልክአ ምድርና በፖለቲካ ረገድ ይሁዳ፣ በግብፅና በአሦር የኀይል ፖለቲካ መካከል ለሥጋት በሚያጋልጥ ሁኔታ ትገኝ ነበር:: በስምንተኛው ምእት ዓመት ቅድመ ክርስቶስ ኢሳይያስ በግብፅ ላይ መተማመንን በመቃወም ማስጠንቀቂያ ሰጥቶ ነበር (ኢሳ 30፥ 1-7)፡፡ አሦር የይሁዳ ሥጋት መሆኗንም በሚገባ መዝኖ ነበር (ኢሳ 37)፡፡ በእግዚአብሔር ጥበቃ የይሁዳ መንግሥት ከሰናክሬም ኀይል አመለጠ፡፡ ነገር ግን ፈሪሀ እግዚአብሔር ከነበረበት ከሕዝቅያስ ዘመነ መንግሥት በማሸቈልቈል፣ ፈረሀ እግዚአብሔር አልባ ወደ ነበረው ወደ ምናሴ መንግሥት መንፈሳዊ ዝቅጠት ወረደ (2ነገ 21 ፥ 9-15፤ 24፥3-4)፡፡ ኤርምያስ ሃያ ዓመት እንደ ሞላው አካባቢ ተጠርቶ ከሆነ፣ በምናሴና በአሞን የአገዛዝ ዘመናት ኖሮአል ማለት ነው። በምናሴ ረጅም የኀምሳ ዓመት የክሕደት ዘመን ውስጥ ፈሪሀ እግዚአብሔር ያደረበት የአባቱ የሕዝቅያስ ተሐድሶዎች ተረስተው ነበር፡፡ በዚያ ዘመን ይሁዳ በአሦር ሥልጣን ሥር ነበረች፤ ስለዚህ አለቆቹን ለማስደሰት ሲል ምናሴ ኢየሩሳሌም በነበረው የቤተ መቅደስ አምልኮ ውስጥ ቅይጥ ነገሮችን አስገባ፡፡ የሰሜኑ መንግሥት (እስራኤል) ቀደም ሲል ተግዞአል (722)፤ በዚያ የነበሩት ትሩፋንም በእምነታቸው ውስጥ ቅይጥ ነገርን ዐቅፈው ይዘው ነበር (2ነገ 17፥28)፡፡ በአስራዶንና በአሹርባኒ ፖል የአገዛዝ ዘመናት የአሦር ኀይል ግብፅን ድል አደረገ፤ ሆኖም በኋላ የመጣው መንግሥት በቀደማዊ ስሜቲክ ዘመን (664-609) በኀይል አንሰራራ፤ ስለዚህ ይሁዳ የሁለቱን የኀይል ሚዛን በመጠበቅ ረገድ ተወጥራ ነበር፡፡
ይቀጥላል...
🚨ማሳሰቢያ የጊዜ አቆጣጠር ካልተጠቀሰ በቀር ዓመተ ቅድመ ክርስቶስ ነው።
ምንጭ፦ የብሉይ ኪዳን ማብራሪያ፤ ገጽ 824-825

👍9❤3
. ==❀❀❀===❀❀❀==
🌼 የዕለቱ ጥቅስ 🌼
==❀❀❀===❀❀❀==
“አምላክህን መፍራትህ መጽናናትህ፥ የቅንነትህም መንገድ ተስፋህ አይደለምን?”
ኢዮብ 4፥6

❤6
ከሚከተሉት መካከል ከታናናሽ ነቢያት የሚመደበው የቱ ነው?
Anonymous Quiz
1%
ሀ. ኢሳይያስ
4%
ለ. ኤርምያስ
5%
ሐ. ሕዝቅኤል
8%
መ. ዳንኤል
82%
ሠ. ሚልክያስ
የብልጽግና ወንጌል.pdf
6.7 MB
👉ርዕስ፦ የብልጽግና ወንጌል
"የዘመኑ የእምነት እንቅስቃሴ መሠረቶችና መዘዞች"
✍ጸሐፊ፦ ግርማዊ
📄የገጽ ብዛት፦ 169
ወደ ቻናሉ ለመ🀄️ላ🀄️ል፦ @Holy_scriptures
"የዘመኑ የእምነት እንቅስቃሴ መሠረቶችና መዘዞች"
✍ጸሐፊ፦ ግርማዊ
📄የገጽ ብዛት፦ 169
ወደ ቻናሉ ለመ🀄️ላ🀄️ል፦ @Holy_scriptures
👎2👍1
. ==❀❀❀===❀❀❀==
🌼 የዕለቱ ጥቅስ 🌼
==❀❀❀===❀❀❀==
“በምሕረትና በእውነት ኃጢአት ትሰረያለች፥ እግዚአብሔርንም በመፍራት ሰው ከክፋት ይመለሳል።”
ምሳሌ 16፥6

👍6❤1
ከቅዱሳት መጻሕፍት ውስጥ ከአንድ በላይ ምእራፍ ያለው መጽሐፍ የቱ ነው?
Anonymous Quiz
10%
ሀ. አብድዩ
11%
ለ. ይሁዳ
61%
ሐ. አሞጽ
18%
መ. 3ኛ ዮሐንስ
👍5❤1
. ==❀❀❀===❀❀❀==
🌼 የዕለቱ ጥቅስ 🌼
==❀❀❀===❀❀❀==
“በተወደደ ሰዓት ሰማሁህ በመዳንም ቀን ረዳሁህ ይላልና፤ እነሆ፥ የተወደደው ሰዓት አሁን ነው፤እነሆ፥ የመዳን ቀን አሁን ነው።”
2ኛ ቆሮ 6፥2
ወደ ቻናሉ ለመ🀄️ላ🀄️ል፦ @Holy_scriptures
🌼 የዕለቱ ጥቅስ 🌼
==❀❀❀===❀❀❀==
“በተወደደ ሰዓት ሰማሁህ በመዳንም ቀን ረዳሁህ ይላልና፤ እነሆ፥ የተወደደው ሰዓት አሁን ነው፤እነሆ፥ የመዳን ቀን አሁን ነው።”
2ኛ ቆሮ 6፥2
ወደ ቻናሉ ለመ🀄️ላ🀄️ል፦ @Holy_scriptures
❤10👍2
Audio
👉ርዕስ፦ የመናኝ ጉዞ
✍ጸሐፊ፦ ዮሐንስ ቡንያን
የቻናላችን ቤተሰቦች በተደጋጋሚ በጠየቃችሁን መሠረት ይኸው በትረካ ተከስተናል። የመናኝ ጉዞ መጽሐፍ የመጀመሪያው ክፍል እነሆ። ክፍል ሁለት ይቀጥላል...
ወደ ቻናሉ ለመ🀄️ላ🀄️ል፦ @Holy_scriptures
✍ጸሐፊ፦ ዮሐንስ ቡንያን
የቻናላችን ቤተሰቦች በተደጋጋሚ በጠየቃችሁን መሠረት ይኸው በትረካ ተከስተናል። የመናኝ ጉዞ መጽሐፍ የመጀመሪያው ክፍል እነሆ። ክፍል ሁለት ይቀጥላል...
ወደ ቻናሉ ለመ🀄️ላ🀄️ል፦ @Holy_scriptures
🔥1
. ==❀❀❀===❀❀❀==
🌼 የዕለቱ ጥቅስ 🌼
==❀❀❀===❀❀❀==
“ለዋኖቻችሁ ታዘዙና ተገዙ፤ እነርሱ ስሌትን እንደሚሰጡ አድርገው፥ ይህንኑ በደስታ እንጂ በኃዘን እንዳያደርጉት፥ ይህ የማይጠቅማችሁ ነበርና፥ ስለ ነፍሳችሁ ይተጋሉ።”
ዕብራውያን 13፥17

❤1👍1