የመፅሐፍ_ቅዱስ_ማጥኛ_እቅድ_bible_reading.pdf
182.9 KB
#አዲስ_ዓመት
#New_Year
መጽሐፍ ቅዱስን በአንድ ዓመት ውስጥ አጥንቶ ለመጨረስ የሚረዳ የጥናት እቅድ
👉 እያንዳንዱ ወር 25 የማጥኛ ቀናቶች አሉት:: ቀሪዎቹ 5 ቀናት ምናልባትም
የተዘለለ ቀን ካለ ወይም ለክለሳ የሚሆን ነው::
👉 እያንዳንዱ ቀን ከ ብሉይ ኪዳን እና ከ አዲስ ኪዳን ሁለቱንም ያጠቃለለ ሲሆን
የመፅሐፍ ቅዱስ ውህደቱንም በሚገባ እንድንረዳ ይረዳናል::
👉ይሄ pdf የተዘጋጀው ከ JUNE - M A Y /ሰኔ-ግንቦት) ግን ከማንኛውም ወር መጀመር ይቻላል::
በአክሊሉ ተፈራ
ወደ ቻናሉ ለመ🀄️ላ🀄️ል፦ @Holy_scriptures

👍12🔥2😁1
. ==❀❀❀===❀❀❀==
የዕለቱ ጥቅስ
==❀❀❀===❀❀❀==
“በመልካም መሬት ላይም የወደቀ እነርሱ በመልካምና በበጎ ልብ ቃሉን ሰምተው የሚጠብቁት በመጽናትም ፍሬ የሚያፈሩ ናቸው።”
ሉቃስ 8፥15

👍9
ቅዱሳት መጻሕፍት
#አዲስ_ዓመት #New_Year መጽሐፍ ቅዱስን እንዴት እናንብብ? ጠቃሚ መርሆች ክፍል-1 መጽሐፍ ቅዱስ ማዕከላዊ መልዕክቱ ለማንኛውም ሰው ግልፅ ሊሆን በሚችልበት ሁኔታ የተቀመጠ ስለሆነ በሁሉም የዕድሜ ክልሎችና በየትኛውም የትምህርት ደረጃ ላይ ላሉ ሰዎች መናገር የሚችል መጽሐፍ ነው፡፡ 2ኛ ጢሞቴዎስ 3፡14-15 ላይ ህጻናት እንኳ የመጽሐፍ ቅዱስን ዋና መልዕክት…
#አዲስ_ዓመት
#New_Year
መጽሐፍ ቅዱስን እንዴት እናንብብ? ጠቃሚ መርሆች
ክፍል-2
መጽሐፍ ቅዱስ የእግዚአብሔር ቃል በመሆኑ ዘላለማዊ አስፈላጊነት አለው፤ የእግዚአብሔር ቃል በመሆኑ ልንሰማውና ልንታዘዘው ይገባናል፡፡ ነገር ግን እግዚአብሔር ቃሉን በታሪክ ውስጥ በሰው ቋንቋ ለመናገር ስለመረጠ በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ያለ መጽሐፍ ሁሉ ታሪካዊ ውስንነት አለው፡፡ እያንዳንዱ ክፍል መጀመርያ በተጻፈበት ቋንቋ፣ ዘመንና ባሕል የተወሰነ ነው (በአንዳንድ ሁኔታዎች ውስጥ በተጨማሪም በጽሑፍ ከመስፈሩ በፊት በነበረው የአፈታሪክ ትውፊት [የተወሰነ ነው])፡፡ በዘላለማዊ አስፈላጊነቱና በታሪካዊ ውስንነቱ መካከል ያለው “ውጥረት” መተርጎምን አስፈላጊ ያደርገዋል፡፡ (Gordon D. Fee & Douglas Stuart: How to Read the Bible For All Its Worth, Second Edition, Zondervan, Grand Rapids, 1993, Introduction)
ይህ ርዕስ በጣም ሰፊና ጥልቅ ቢሆንም ነገር ግን መጽሐፍ ቅዱስን በግላቸው ለማጥናትና በትክክል ለመረዳት ለሚሹ ወገኖች ጠቃሚ የሆኑ ምክረ ሐሳቦችን ብቻ አጠር አድርገን እናስቀምጣለን፡፡
በሥነ ፍታቴ ውስጥ ሦስቱ መሠረታውያን ነጥቦች፡- ሐቲት፣ መተርጎምና ማዛመድ ናቸው፡፡
ሐቲት (Exegesis)
“ኤክሰጂሰስ” የሚለው የእንግሊዘኛ ቃል ከግሪክ የተገኘ ነው፤ ትርጉሙም “ማውጣት” እንደማለት ሲሆን አንድ ቃል ለመጀመርዎቹ ተቀባዮች በራሳቸው ቋንቋና ባሕል ምን ማለት እንደነበር ለማግኘት የሚደረግ ሥርዓትን የጠበቀ ጥናት ነው፡፡ በሐቲት ውስጥ ሁለት መሠረታውያን ነጥቦች አሉ፡፡ የመጀመርያው አውድ ሲሆን ሁለተኛው ደግሞ ይዘት ነው፡፡
1. አውድ
ሁለት ዓይነት አውዶች አሉ፡-
ሀ. ታሪካዊ አውድ
ይህ መጽሐፉ የተጻፈበትን ጊዜና ባሕል የሚመለከት ሲሆን የጸሐፊውንና የተደራሲያኑን መንፈሳዊ፣ ማህበራዊ፣ ፖለቲካዊ፣ ምጣኔ ሃብታዊ፣ መልክአ ምድራዊ አቀማመጥና ሌሎች ከጽሑፉ ይዘትና ትርጉም ጋር ሊገናኙ የሚችሉ ነጥቦችን ሁሉ ከግምት ውስጥ የማስገባት ሥራ ነው፡፡ የሚከተሉትን ጥያቄዎች በመጠየቅ የአንድን የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍል ታሪካዊ አውድ ማወቅ እንችላለን፡-
👉ጸሐፊው ማነው? (የጸሐፊውን ስም እርግጠኛ በመሆን ማወቅ ቢሳነን እንኳ ከአጻጻፉ በመነሳት ስለ እርሱ መገመት እንችላለን)
👉ተደራሲያኑ እነ ማን ናቸው?
👉መቼ ተጻፈ?
👉የት ተጻፈ?
👉የተጻፈበት ምክንያት ምን ነበር?
ከላይ የተጠቀሱትንና ሌሎች ጥያቄዎችን ብንጠይቅ የመጽሐፉን ታሪካዊ አውድ በቀላሉ ማወቅ እንችላለን፡፡ እነዚህን ለመሳሰሉ ጥያቄዎች ምላሽ ማግኘት ያን ያህል የሚቸግር ባይሆንም ነገር ግን ስለ ጉዳዩ የበለጠ እውቀት ባላቸው ሰዎች የተጻፉ ጥሩ ሐተታዎችንና መዝገበ ቃላትን ብንጠቀም ግንዛቤያችን ይበልጥ ሊሰፋ ይችላል፡፡
ለ.የምንባብ አውድ
ይህ ቀላል የሆነ፣ ነገር ግን ብዙ ሰዎች ትኩረት ስለማይሰጡት በመጽሐፍ ቅዱስ አተረጓጎም ላይ ትልልቅ ስህተቶችን እንዲሰሩ ምክንያት የሚሆናቸው ነጥብ ነው፡፡ የሥነ ፍታቴ ምሑራን የዚህን መርህ አስፈላጊነት አፅንዖት ሰጥተው ሲናገሩ “#ምንባቡ_ንጉሥ_ነው” ይላሉ፡፡ አንድን ቃል፣ ሐረግ ወይንም ደግሞ ዓረፍተ ነገር በምንባብ አውድ ውስጥ መረዳት ማለት ዙሪያ ገባውን በማንበብ በተጻፈበት በዚያ ክፍል መሠረት የሚሰጠውን ትርጉም መረዳት ማለት ነው፡፡ ዛሬ ብዙ ሰዎች፣ በተለይም ደግሞ ሙስሊም ጸሐፍት ይህንን ቀላል መርህ ባይዘነጉ ኖሮ ስለ መጽሐፍ ቅዱስ “ስህተቶችና” “ግጭቶች” ብዙ በመጻፍ ባልደከሙ ነበር፡፡ በተደጋጋሚ የሚነሳውን አንድ ምሳሌ ለመጥቀስ ያህል፤ የምንባብ አውዱን ባንጠብቅ መጽሐፍ ቅዱስን “አምላክ የለም” ልናስብለው እንኳ እንችላለን፡፡ መዝሙር 14፥1 “አምላክ የለም” ይላል፡፡ ነገር ግን ሙሉ ጥቅሱ፡- “ሰነፍ በልቡ አምላክ የለም ይላል። በሥራቸው ረከሱ፥ ጐሰቈሉ በጎ ነገርን የሚሠራ የለም” የሚል ነው፡፡ ብዙ ጊዜ በተለያዩ መጻሕፍት ታትመው የሚወጡ ስለ መጽሐፍ ቅዱስ “ግጭቶችና” “ስህተቶች” የሚነገሩ አብዘኞቹ ውንጀላዎች ከዚህ የዘለለ ጥልቀት የሌላቸው ናቸው፡፡
የአንድን የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍል የምንባብ አውድ ለመረዳት የሚከተሉትን ጥያቄዎች ልናነሳ እንችላለን፡-
👉ተናጋሪው ማነው?
👉ለማነው የተናገረው?
👉ጸሐፊው ለምን ይህንን በዚህ ስፍራ አስገባው?
👉ከፊት ምን ተባለ?
👉ከኋላ ምን ተባለ?
👉ይህ ቃል፣ ሐረግ ወይም አረፍተ ነገር በዚህ ስፍራ ላይ የሚሰጠው ትርጉም ምንድነው?
👉ዋናው ጭብጥ ምንድነው?
ማንኛውንም የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍል በተጻፈበት አውድ ውስጥ ለመረዳት እነዚህንና መሰል ቀላል ጥያቄዎች ማንሳት ጠቃሚ ነው፡፡
2. ይዘቱን ማተት
ይዘት ከቃላትና ሐረጎች ትርጉም፣ የሰዋሰው አወቃቀርና በጥንታውያን የእጅ ጽሑፎች ውስጥ የተለያዩ አነባበቦች የሚገኙ ከሆነ ትክክለኛውን ከመምረጥ ጋር ይያያዛል፡፡ እነዚህን ነጥቦች ለማወቅ በዘርፉ ላይ ዕውቀት ባላቸው ሰዎች የተጻፉ የተለያዩ ሐተታዎችንና መዝገበ ቃላትን መጠቀም በጣም አስፈላጊ ነው፡፡
በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ እኛ ከለመድናቸው ትርጉሞች የተለየ ትርጉም ያላቸው ቃላትና ሐረጎች ሊኖሩ ይችላሉ፡፡ እንደምሳሌ ለማንሳት ያህል የጥንት አይሁዳውያን ማንኛውንም የቀን ክፍል እንደ ሙሉ ቀንና ሌሊት ነው የሚቆጥሩት፡፡ ለምሳሌ ሦስት ቀንና ሦስት ሌሊት ማለት የግድ 72 ሰዓታት ማለት ላይሆን ይችላል፡፡ አንዳንድ ጊዜ ደግሞ የአማርኛ ቃላት እንኳ ሆነው በትክክል የማንረዳቸው ቃላትና ሐረጎች ያጋጥማሉ፡፡
መጽሐፍ ቅዱስ በተጻፈበት ዘመን የነበሩ የተለያዩ መለኪያዎች፣ የቀን አቆጣጠሮችና የመሳሰሉት እኛ ከምናውቃቸው የተለዩ ስለሆኑ ምን ማለት እንደሆኑ ለማወቅ መዝገበ ቃላትን ወይንም ደግሞ ሐተታዎችን መጠቀም ያስፈልገናል፡፡ ሌላው ስለ ይዘት ሲታሰብ ሊታወቅ የሚገባው ነገር ቢኖር አንዳንድ ጊዜ የዓረፍተ ነገሮች ሰዋሰዋዊ አወቃቀር ዓረፍተ ነገሩ የተለያዩ ሁለት ትርጉሞች እንዲኖሩት ሊያደርግ መቻሉ ነው፡፡ በዚህ ጊዜ ሌሎች ትርጉሞችን ማየት ወይንም ደግሞ ሐተታዎችን በመጠቀም በመጀመርያዎቹ ቋንቋዎች ውስጥ ያለውን ትርጉም መፈለግ ጠቃሚ ነው፡፡
ይቀጥላል...
ምንጭ:- www.ewnetlehulu.org

👍11
. ==❀❀❀===❀❀❀==
የዕለቱ ጥቅስ
==❀❀❀===❀❀❀==
“እግዚአብሔር ፊቱን ያብራልህ፥ ይራራልህም፤”
ዘኍልቁ 6፥25
ወደ ቻናሉ ለመ🀄️ላ🀄️ል፦ @Holy_scriptures
የዕለቱ ጥቅስ
==❀❀❀===❀❀❀==
“እግዚአብሔር ፊቱን ያብራልህ፥ ይራራልህም፤”
ዘኍልቁ 6፥25
ወደ ቻናሉ ለመ🀄️ላ🀄️ል፦ @Holy_scriptures
👍7❤5🔥2
የመጽሐፍ ቅዱስ መዝገበ ቃላት.pdf
11.4 MB
#አዲስ_ዓመት
#New_Year
👉ርዕስ፦ የመጽሐፍ ቅዱስ መዝገበ ቃላት
የኢትዮጵያ መጽሐፍ ቅዱስ ማኅበር
ሌላ ለመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት የሚጠቅም መጽሐፍ እነሆ። ከተቻ በመጽሐፉ መግቢያው ላይ ያለውን ለጥፈንላችኋል።
ስለ መጽሐፍ ቅዱስ በየጊዜው ብዙ መጻሕፍት ተጽፈዋል። አጻጻፋቸውም በስብከት፥ በንግግርና በትርጓሜ መልክ ነው። ነገር ግን በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ የሚገኙትን ዋና ዋና አርእስት ተራ በተራ በማስቀመጥ ትርጓሜአቸውንም በመግለጥ የተጻፉ መጻሕፍት ጥቂቶች ናቸው። ስለዚህም ለወንጌል አስተማሪዎችና ለመጽሐፍ ቅዱስ ወዳጆች ጠቃሚ እንደሚሆን በልዩ ልዩ ቤተ ክርስቲያን መሪዎች ከ1962 ዓ.ም. ጀምሮ ታስቦ እነሆ፥ ይህ «የመጽሐፍ ቅዱስ መዝገበ ቃላት» ተዘጋጀ።
ይህ መጽሐፍ ትርጓሜ አይደለም፤ ሆኖም ብዙ ጥቅሶችን ያብራራል። ማውጫ አይደለም፤ ግን ብዙ አሳቦችን ከመጽሐፍ ቅዱስ ለማግኘት ያስችላል። መጽሐፉ ከመጠን በላይ እንዳይሆን በማለት ሁለት ሺህ የሚያህሉ አርእስት ብቻ እንዲይዝ ተደርጓል። ሙሉ ማውጫ ቢሆን ከዐሥር ሺህ በላይ አርእስት ስለሚኖሩት መጽሐፉ ይከብድ ነበር። እርግጥ የመጽሐፍ ቅዱስን መሠረታዊ አሳብ ከሚገልጹት አርእስት መካከል የቀረ እንደሌለ ተስፋ እናደርጋለን። ብዙ ሰዎችንና ቦታዎችን በስም ዝርዝር ማቅረብ አስፈላጊ ሆኖ አልተገኘም፤ ታሪካውያን አይደሉምና ነው። ብዙ የታወቁ ቃላትንም ማብራራት አላስፈለገም። ነገር ግን ታሪካውያን ሰዎች፥ ቦታዎችና ድርጊቶች፥ የሃይማኖትና ዘመናዊ ያልሆኑ አማርኛ ቃላት፥ የመጽሐፍ ቅዱስ ዘመን ባህል፥ ልማድ፥ ሁኔታ፥ ድርጅት፥ ሥርዓትና የኅብረተሰብ አቋም፥ መጻሕፍት በየርእስ ይገኛሉ። አስተዋይ አንባቢ ብዙ ትምህርት እንደሚያገኝባቸው እንተማመናለን።

👍7❤2👏1
ሁለንተናዬ ለእርሱ ክብር.pdf
13.1 MB
#አዲስ_ዓመት
#New_Year
👉ርዕስ፦ ሁለንተናዬ ለእርሱ ክብር
✍ጸሐፊ፦ ኦዝዋልድ ቻምበርስ
🗣ትርጉም፦ ተስፋዬ መስፍን
ለአዲስ ዓመት ካሰብንላችሁ መጽሐፍ ውስጥ አንዱ "ሁለንተናዬ ለእርሱ ክብር" የሚለው መጽሐፍ ነው። ለጥሞና በጣም ጠቃሚ መጽሐፍ እንደሆነ በስፋት የሚነገርለት ይህ መጽሐፍ በቀን አንድ ገጽ ብቻ የሚነበብ ሲሆን በየቀኑ የመጽሐፍ ቅዱስን መልእክት በጸሎት ተዋዝቶ የቀረበበት ድንቅ መጽሐፍ ነው። ከታች በመጽሐፉ መግቢያው ላይ ያለውን እንዲህ አቅርበንላችኋል፦
አንድ ዓለም አቀፍ ተነባቢነት ያለው መጽሔት "My Utmost for His Highest" የተሰኘውን ዕለታዊ መንፈሳዊ ንባብ በክፍለ ዘመኑ ውስጥ በጣም ተወዳጅነት ከነበራቸው አሥር መጻሕፍት ተራ አግብቶታል፡፡
ሁለንተናዬ ለእርሱ ክብር በሚል ርዕስ ተተርጕሞ የቀረበላችሁ ይህ መጽሐፍ ለመጀመሪያ ጊዜ በእንግሊዝኛ ቋንቋ የተጻፈው በ1927 ቢሆንም ዘመናት ጥልቅ̧ መንፈሳዊ መልእክቱን አላደበዘዙትም፣ ታዋቂነትና ተወዳጅነቱን አልቀነሱበትም፣ ይልቁንም እስከ አሁን ድረስ በየዕለቱ በሚሊዮኖች የሚነበብ ሆኖአል፡፡ በየዓመቱ 300,000 የእንግሊዝኛ ኮፒዎች ይሸጣሉ፡፡ ይህም ሌሎች ቋንቋዎችን ሳይጨምር ነው፡፡ በሰላሣ ቋንቋዎች ተተርጕሞአል፤ በሰባት ቋንቋዎች ተርጕሞ ለማቅረብ ዝግጅት ላይ ነው፡፡
በዕለታዊ የጽሞና ጊዜያቸው የሚጠቀሙበት ክርስቲያኖችና የዓለማችን ታላላቅ መንፈሳዊ መሪዎች እውነትም ሁለንተናዬ ለእርሱ ክብር ብለዋል፡፡ እርስዎም ይህን መጽሐፍ ካነበቡ በኋላ "ሁለንተናዬ ለእርሱ ክብር" ይላሉ፡፡

👍7
. ==❀❀❀===❀❀❀==
የዕለቱ ጥቅስ
==❀❀❀===❀❀❀==
“እንደ ክርስቶስ ትምህርት ሳይሆን፥ እንደ ሰው ወግና እንደ ዓለማዊ እንደ መጀመሪያ ትምህርት ባለ በፍልስፍና በከንቱም መታለል ማንም እንዳይማርካችሁ ተጠበቁ።”
ቆላስይስ 2፥8

❤5
ቅዱሳት መጻሕፍት
#አዲስ_ዓመት #New_Year መጽሐፍ ቅዱስን እንዴት እናንብብ? ጠቃሚ መርሆች ክፍል-2 መጽሐፍ ቅዱስ የእግዚአብሔር ቃል በመሆኑ ዘላለማዊ አስፈላጊነት አለው፤ የእግዚአብሔር ቃል በመሆኑ ልንሰማውና ልንታዘዘው ይገባናል፡፡ ነገር ግን እግዚአብሔር ቃሉን በታሪክ ውስጥ በሰው ቋንቋ ለመናገር ስለመረጠ በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ያለ መጽሐፍ ሁሉ ታሪካዊ ውስንነት አለው፡፡…
#አዲስ_ዓመት
#New_Year
መጽሐፍ ቅዱስን እንዴት እናንብብ? ጠቃሚ መርሆች
ክፍል-3
መተርጎም
ይህ ርዕስ እጅግ ሰፊ ከመሆኑ የተነሳ ወደ ውስጥ ጠልቀን በመግባት እያንዳንዱን ነጥብ መተንተን ስለማንችል ጠቅለል ባለ ሁኔታ መሠረታዊውን ሐሳብ ብቻ እናስቀምጣለን፡፡ በመጀመርያው ምዕራፍ ላይ መጽሐፍ ቅዱስ አንድ ዓይነት የሥነ ጽሑፍ ዘይቤን ያልተከተለ መሆኑን ገልፀናል፡፡ ለተለያዩ የሥነ ጽሑፍ ዓይነቶች የተለያዩ አተረጓገሞችን እንጠቀማለን፡፡
#የሕግ_መጻሕፍት- የብሉይ ኪዳን ሕግጋት በ 3 ይከፈላሉ፡፡ እነርሱም:-
ሀ. የግብረገብ ሕግጋት
ለ. የሥርዓት ሕግጋትና
ሐ. የማሕበረሰብ ሕግጋት ናቸው፡፡
የግብረገብ ሕግጋት የማይለወጠውን የእግዚአብሔርን ባሕርይ የሚገልጹ ስለሆኑ ሊለወጡ ወይንም ደግሞ ሊሻሻሉ የሚችሉ አይደሉም፡፡ ስለዚህ እነዚህ ሕግጋት በየትኛውም ዘመን ሊጠበቁ ይገባል፡፡ ለምሳሌ አትግደል፣ አትስረቅ፣ አታመንዝር ወዘተ. የሚሉት እነዚህ ሕግጋት የግብረገብ ሕግጋት ስለሆኑ ዓለም አቀፋዊ ናቸው፡፡ የሥርዓት ሕግጋትና የማሕበረሰብ ሕግጋት ግን ለእስራኤላውያን ብቻ የተሰጡ ናቸው፡፡ የሥርዓት ሕግጋት ስለ መቅደሱ የአምልኮ ሥርዓቶች፣ ስለሚበሉና የማይበሉ እንስሳት፣ ስለ መንጻት ሥርአቶች፣ ወዘተ... የሚናገሩ ናቸው፡፡ አይሁዳውያን ያልሆኑ ሕዝቦች እነዚህን ሕግጋት የመጠበቅ ግዴታ የለባቸውም፡፡ የማሕበረሰብ ሕግጋት ደግሞ የጋብቻ ሥርዓቶች፣ የወንጀለኛ መቅጫ ሕግጋት፣ የካሳ አከፋፈል፣ የንብረት ክፍፍል፣ ወዘተ... ናቸው፡፡ እነዚህ ሕግጋት ሊሠሩ የሚችሉት መለኮታዊ አስተዳደር (Theocracy) ባለበት ቦታ ብቻ ነው፡፡ ስለዚህ የሕግ መጻሕፍትን ስናጠና እነዚህን ሦስቱን በመለየትና የትኞቹ ለእስራኤላውያን ብቻ እንደተሰጡና የትኞቹ ደግሞ ዓለም አቀፋዊ ይዘት እንዳላቸው በመረዳት መሆን አለበት፡፡
ሌላው እዚህ ጋር ሊታወስ የሚገባው ነጥብ ቢኖር አብዛኞቹ የመቅደሱ የአምልኮ ሥርዓቶች ክርስቶስ ኢየሱስን የሚያሳዩ መሆናቸው ነው፡፡ ስለዚህ የትኞቹ በክርስቶስ ሕይወት እንደተፈጸሙ መመልከት ያስፈልገናል፡፡ ይህንን በሚገባ ለመረዳት የዕብራውያንን መጽሐፍ ማንበብ በጣም ጠቃሚ ነው፡፡
#ትረካዎች – መጽሐፍ ቅዱስ በብዙ ታሪኮች የተሞላ መጽሐፍ ነው፡፡ አንድ ታሪክ በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ስለተጻፈ ብቻ እንደ እግዚአብሔር ሐሳብ የተፈጸመ ትክክለኛ ድርጊት ነው ማለት አይደለም፡፡ ነገር ግን የተጻፈው እያንዳንዱ ታሪክ ለትምህርታችን ተጽፏል፡፡ የብሉይ ኪዳን ታሪኮች እግዚአብሔር በፍጥረቱ ውስጥ እንዴት እንደሠራና ሰዎች ደግሞ ለእርሱ የሰጡትን ምላሽ የሚያሳዩ ናቸው፡፡ እነዚህን ታሪኮች ባሉበት ሁኔታ ከመረዳት ይልቅ ስውር ትርጉሞችን በመፈለግ ልንተነትናቸው አይገባም፡፡ በአጠቃላይ በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ የሚገኙ ትረካዎችን ስናጠና የሚከተሉትን ነጥቦች ማስታወስ ያሻናል፡-
👉ትረካዎች እውነተኛ ታሪኮችን የሚናገሩ ናቸው ነገር ግን የእያንዳንዱን ክንውን ዝርዝር ሁኔታ የመናገር ዓላማ ላይኖራቸው ይችላል፡፡
👉ትረካዎች መጽሐፍ ቅዱስ በሌሎች ስፍራዎች ላይ የሚያስተምራቸውን እውነታዎች የሚያብራሩ ናቸው፡፡
👉ትረካዎች ብዙ ጊዜ የሚዘግቡት የተፈፀመውን እንጂ ሊፈፀም የሚገባውን ላይሆን ይችላል፡፡
👉ትረካዎች ልንከተላቸው የሚገቡ በጎ ምሳሌዎችን ወይንም ደግሞ ልንርቃቸው የሚገቡት መጥፎ ምሳሌዎችን ሊይዙ ይችላሉ፡፡
👉የሁሉም ትረካዎች ዋና ባለታሪክ እግዚአብሔር መሆኑ ሊታወቅ የሚገባው መርህ ነው፡፡
#መዝሙራት– በቅኔ ውስጥ የሚመደቡ ሲሆኑ በተለያዩ ዘመናት የእግዚአብሔር ሰዎች የዘመሯቸውን መዝሙራትና የጸለዩዋቸውን ጸሎቶች ያጠቃልላሉ፡፡ እነዚህም በመዝሙር መጽሐፍ ውስጥ የተሰበሰቡ ሲሆኑ አብዛኞቹ በዳዊት የተጻፉ ናቸው፡፡ ብዙ ጊዜ መዝሙራት ትዕምርታዊ ንግግሮችን ስለሚጠቀሙ እያንዳንዱን ነገር በቀጥታ መተርጎም ትክክል አይደለም፡፡ ለምሳሌ ለእግዚአብሔር የተሰጡ ሰዋዊ ባሕርያትን በቀጥታ በመውሰድ እግዚአብሔርን በዚያ ሁኔታ መሳል ስህተት ነው፡፡ እነዚህ መዝሙራት ከሰው ወደ እግዚአብሔር የቀረቡ ምስጋናዎችና ጸሎቶች እንደመሆናቸው መጠን ዘማርያኑ የግል ስሜቶቻቸውን፣ ቁጣቸውን ወይንም ደግሞ ኀዘናቸውን የሚገልጹባቸውን ክፍሎች በመውሰድ ተግባራዊ ልናደርጋቸው እንደሚገቡ ነገሮች መቁጠርም እንደዚሁ ስህተት ነው፡፡ ሌላው ዘማርያኑ ስለ ተፈጥሮ፣ ስለ ዓለም፣ ባጠቃላይ ስለ አፅናፈ ዓለም ባላቸው መረዳት መጠን መናገራቸውን የመጽሐፍ ቅዱስ ሳይንሳዊ ስህተቶች እንደሆኑ ማሰብ ተገቢ አይደለም፡፡

👍6❤3
. ==❀❀❀===❀❀❀==
የዕለቱ ጥቅስ
==❀❀❀===❀❀❀==
“ሰው በከንቱ ወራቱ ቍጥርና እንደ ጥላ በሚያሳልፈው ዘመኑ በሕይወቱ ሳለ ለሰው የሚሻለውን የሚያውቅ ማነው? ወይስ ለሰው ከፀሐይ በታች ከእርሱ በኋላ የሚሆነውን ማን ይነግረዋል?”
መክብብ 6፥12

👍1
ቅዱሳት መጻሕፍት
#አዲስ_ዓመት #New_Year መጽሐፍ ቅዱስን እንዴት እናንብብ? ጠቃሚ መርሆች ክፍል-3 መተርጎም ይህ ርዕስ እጅግ ሰፊ ከመሆኑ የተነሳ ወደ ውስጥ ጠልቀን በመግባት እያንዳንዱን ነጥብ መተንተን ስለማንችል ጠቅለል ባለ ሁኔታ መሠረታዊውን ሐሳብ ብቻ እናስቀምጣለን፡፡ በመጀመርያው ምዕራፍ ላይ መጽሐፍ ቅዱስ አንድ ዓይነት የሥነ ጽሑፍ ዘይቤን ያልተከተለ መሆኑን ገልፀናል፡፡ ለተለያዩ…
መጽሐፍ ቅዱስን እንዴት እናንብብ? ጠቃሚ መርሆች
ክፍል-4
(የመጨረሻ ክፍል)
#የጥበብ_መጻሕፍት- መጽሐፈ ኢዮብ፣ መጽሐፈ ምሳሌ፣ መጽሐፈ መክብብና መኃልየ መኃልይ ሲሆኑ በቅኔ መጻሕፍት ውስጥ ይመደባሉ፡፡ እነዚህን መጻሕፍት ሙሉ በሙሉ ካላነበብን ብዙ ጊዜ በተሳሳተ መንገድ ልንተረጉማቸው እንችላለን፡፡ ለምሳሌ መጽሐፈ መክብብን ከምዕራፍ 11፡9 በፊት የሚገኘውን ብቻ በማንበብ ብንተው ትክክለኛ ነጥቡን ሳናገኝ እንቀራለን፡፡ እነዚህ መጻሕፍት በአብዛኛው ምሳሌያዊ ንግግሮችን፣ ምፀቶችን፣ ቅኔያዊ አገላለፆችን ወዘተ... ይጠቀማሉ፡፡ እነዚህን የንግግር ዓይነቶች መረዳትና መተርጎም ያለብን እንደየባሕርያቸው ነው፡፡ ሌላው የቅኔ መጻሕፍትን ስንተረጉም ልንረዳው የሚገባን ነገር ቢኖር የየዕለት ተግባራዊ የሕይወት መመርያን ከማስተላለፍ በዘለለ ጠንካራ የሥነ መለኮት አስተምህሮዎችን በቀጥታ የማስተላለፍ ሁኔታቸው አነስተኛ መሆኑን ነው፡፡ እንደ ተጨማሪ ድጋፍ ከመጠቀም ያለፈ መሠረታዊ አስተምህሮዎችን በቅኔ መጻሕፍት ውስጥ በሚገኙ ጥቅሶች ላይ ብቻ ሙሉ በሙሉ መመሥረት አይገባንም የሚል አጠቃላይ ግንዛቤ በመጽሐፍ ቅዱስ ምሑራን ዘንድ አለ፡፡
#ትንቢቶች- የትንቢት መጻሕፍት ስለወደፊቱ ሁኔታዎች የሚናገሩ ናቸው፡፡ ቅዱሳት መጻሕፍትን በምንተረጉበት ሰዓት ከፍተኛ የሆነ ጥንቃቄ ልናደርግባቸው ከሚገቡ ክፍሎች መካከል ትንቢቶች የመጀመርያዎቹ ናቸው፡፡ የሚከተሉት ጥያቄዎች የትንቢት መጽሐፍትን ለመረዳት ያግዛሉ፡-
👉የቋንቋ አጠቃቀሙ ምን ዓይነት ነው? (ትዕምርታዊ፣ ቅኔያዊ፣ ራዕያዊ፣ አቡቀለምሲሳዊ፥ ወዘተ.)
👉የምንባብ አውዱ ምንድነው?
👉የትንቢቱና የተናጋሪው ታሪካዊ ዳራ ምንድነው?
👉የተሰጠው ተስፋ አኳኋናዊ (conditional) ነው ወይንስ ኢ-አኳኋናዊ (unconditional)?
👉የተነገረው ትንቢት የተፈፀመ፣ እየተፈፀመ ያለ ወይንስ ወደፊት የሚፈፀም?
#ምሳሌዎች- ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ትምህርቶቹን ብዙ ጊዜ በምሳሌዎች ያስተምር ነበር፡፡ እነዚህ ምሳሌዎች ትምህርቶቹን ይበልጥ ያብራራሉ ወይንም ደግሞ ከሰዎች አዕምሮ እንዳይጠፉ ያደርጋሉ፡፡ እነዚህን ምሳሌዎች በምናነብበት ሰዓት ከእነርሱ በፊት ወይንም በኋላ የተነገሩትን ነገሮች ልብ ብሎ ማንበብ አስፈላጊ ነው፡፡ የምሳሌ እያንዳንዱ ነጥብ ትርጉም ባለው መልኩ ከፍቺው ጋር ላይገናኝ ስለሚችል ጥንቃቄ ማድረግም ያስፈልጋል፡፡ ለምሳሌ ያህል ስለ ወይን እርሻ ገበሬዎች በተሰጠው ምሳሌ ውስጥ ከተዘረዘሩ የወይኑ ጌታ ባህርያት መካከል ከእግዚአብሔር ባሕርት ጋር የማይገጥሙ አሉ (ማቴዎስ 21፡33-43)፡፡ ምሳሌዎች ደግሞ በክፍሉ ላይ ከተጠቀሰው ፍቺ ውጪ ሌላ የተደበቀ ትርጉም ይኖራቸዋል ብሎ ማሰብ ስህተት ነው፤ ስለዚህ በወቅቱ ምሳሌው የተነገረበትን ትክክለኛ ነጥብ ካገኘን ዘንዳ ሌላ አላስፈላጊ ሐተታ ውስጥ መግባት አያሻንም፡፡
#መልዕክቶች- መልዕክቶች እንደስማቸው ከሰዎች ወደ ሌሎች የተላኩ ደብዳቤዎች ናቸው፡፡ ነገር ግን እነዚህ ደብዳቤዎች ተራ ደብዳቤዎች ሳይሆኑ ቅዱሳን ሐዋርያት በመንፈስ ቅዱስ ተመርተው የጻፏቸው ናቸው፡፡ የእነዚህን መልዕክቶች አጻጻፍ በምናይበት ጊዜ በአብዛኛው ተመሳሳይ የሆነ ቅርፅ እንዳላቸው እናስተውላለን፡፡ እነዚህም፡-
👉ጸሐፊው
👉የተቀባዩ ስም
👉ሰላምታ
👉ጸሎት፣ መልካም ምኞት ወይንም ምስጋና
👉የመልዕክቱ ዋና አካል
👉የመጨረሻ የስንብት ሰላምታ ናቸው፡፡
መልዕክቶችን በምንተረጉምበት ሰዓት ታሪካዊና ምንባባዊ አውዳቸውን ተከትለን የማጥናት መርህ እንደተጠበቀ ሆኖ በተጨማሪም መልዕክቶች እንደመሆናቸው ሳናቆራርጥ የንባብ ሂደቱን መጨረስ ይገባናል፡፡
3. ማዛመድ
ዕብራውያን 4፡2 ላይ የእግዚአብሔር ቃል ሲናገር “ዳሩ ግን የሰሙት ቃል ከሰሚዎቹ ጋር በእምነት ስላልተዋሐደ አልጠቀማቸውም” ይላል፡፡ ያጠናነው ቃል ከሕይወታችን ጋር ካልተዛመደ ከላይ የተጠቀሱትን ሁለቱን መንገዶች ተጠቅመን መጽሐፍ ቅዱስን ብንመረምር ለአዕምሯችን ዕውቀትን ከማግኘት ያለፈ ለመንፈሳችን የሚሆን በረከት ልናገኝ አንችልም፡፡ መጽሐፍ ቅዱስ ከብዙ ዘመናት በፊት ለነበሩ ሰዎች የተሰጠ ቃል ነው፤ ነገርግን በሐቲትና በመተርጎም በእኛና በእነርሱ መካከል የሚገኙትን የማንነት፣ የቋንቋ፣ የባሕል፣ የታሪክ፣ የቦታ፣ የአጻጻፍ፣ የዘመን፣ ወዘተ... ልዩነቶችን አስወግደን በየትኛውም ዘመንና በሁሉም ቦታ ሊሠራ የሚችል ለሁሉም ሕዝቦች ጠቃሚ የሆነን መልዕክት እናገኛለን፡፡ ማዛመድ ማለት በአጭር ቋንቋ ያጠናነው ቃል አሁን ስላለንበት ሁኔታ ወይንም ደግሞ ስለ ሕይወታችን ምን እንደሚልና ቃሉን ተግባራዊ ማድርግ የምንችለው እንዴት እንደሆነ በማወቅ በቃሉ መሠረት መኖር ማለት ነው፡፡ ዕለት ዕለት ይህንን ማድረግ ከቻልን የእግዚአብሔርን ኃይልና አብሮነት በሕይወታችን ውስጥ እንለማመዳለን፡፡
ይህንን ጽሑፍ ስንደመድም አፅንዖት ሰጥተን ልንናገረው የምንፈልገው የመጨረሻው ነጥብ ቢኖር መጽሐፍ ቅዱስን ስናጠና የመንፈስ ቅዱስን ድርሻ ልንዘነጋ እንደማይገባን ነው፡፡ እርሱ ከማንኛውም መዝገበ ቃላት፣ ሐተታ ወይንም ደግሞ አስተማሪ ይልቅ ሊያስተምረን የሚችል ሕልውናው እውን የሆነ መምህር ነው፡፡ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ እርሱ በመጣ ጊዜ ወደ እውነት ሁሉ እንደሚመራን ነግሮናል (ዮሐንስ 16፡13)፡፡ ጴጥሮስና ሌሎቹ ሐዋርያት ቅዱሳት መጻሕፍትን ያልተማሩ ሰዎች ቢሆኑም እንኳ መንፈስ ቅዱስ እራሱ ስላስተማራቸው ስለ ቅዱሳት መጻሕፍት የነበራቸው ጥልቅ ዕውቀት በወቅቱ የነበሩትን የአይሁድ መምህራን ሳይቀር አስገርሞ ነበር (የሐዋርያት ሥራ 3፡13)፡፡ መጽሐፍ ቅዱሳችንን ስናነብ እኔና እናንተንም መንፈስ ቅዱስ እንዲያስተምረን በጸሎት ልንጠይቀው ይገባል፡፡
“አብ በስሜ የሚልከው ግን መንፈስ ቅዱስ የሆነው አጽናኝ እርሱ ሁሉን ያስተምራችኋል እኔም የነገርኋችሁን ሁሉ ያሳስባችኋል።” (ዮሐንስ 14፡26)

👍8❤3
🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼
ውድ የቻናላችን ቤተሰቦች እንኳን ለአዲሱ ዓመት በሰላም አደረሳችሁ። ለመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት የሚመቻችሁን ማብራሪያ (commentary) መጠየቅ ትችላላችሁ። እንዲሁም ያላችሁን መጽሐፍ እዚህ በመለጠፍ ተባበሩን።

🔥5👍2
#አዲስ_ዓመት
ውድ የቻናላችን ቤተሰቦች እንኳን አደረሳችሁ! መጪው ዘመን መጻሕፍትን እናስተውል ዘንድ አእምሮአችን የሚከፈትበት ዘመን ይሁንልን!
“በዚያን ጊዜም መጻሕፍትን ያስተውሉ ዘንድ አእምሮአቸውን ከፈተላቸው፤”
ሉቃስ 24፥45
🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼
🌼🌼መልካም አዲስ አመት🌼🌼

❤8👍2🔥2
. ==❀❀❀===❀❀❀==
🌼 የዕለቱ ጥቅስ 🌼
==❀❀❀===❀❀❀==
“ከማናቸውም ዓይነት ክፉ ነገር ራቁ።”
1ኛ ተሰሎንቄ 5፥22
ወደ ቻናሉ ለመ🀄️ላ🀄️ል፦ @Holy_scriptures
🌼 የዕለቱ ጥቅስ 🌼
==❀❀❀===❀❀❀==
“ከማናቸውም ዓይነት ክፉ ነገር ራቁ።”
1ኛ ተሰሎንቄ 5፥22
ወደ ቻናሉ ለመ🀄️ላ🀄️ል፦ @Holy_scriptures
❤9
. ==❀❀❀===❀❀❀==
🌼 የዕለቱ ጥቅስ 🌼
==❀❀❀===❀❀❀==
“የትእዛዝ ፍጻሜ ግን ከንጹሕ ልብና ከበጎ ሕሊና ግብዝነትም ከሌለበት እምነት የሚወጣ ፍቅር ነው፤”
1ኛ ጢሞቴዎስ 1፥5

የሕሊና ዓይነቶች
በቅዱሳት መጻሕፍት በተለይም በአዲስ ኪዳን ይባስ ብሎም ደግሞ በሐዋርያው ቅዱስ ጳውሎስ ትምህርት "#ሕሊና" የሚለው አሳብ ተደጋግሞ ይነሳል። በአዲስ ዓመት እንዲህ አይነት አሳብ አንስተን መወያየት ግድ ይለናልና እነሆ ብለን። ከታች ከተዘረዘሩት ለአንድ ክርስቲያን የሚያስፈልገውና የግሉ ሊያደርገው ሊጋደልበት የሚገባው የቱ ነው? ለምን?
1. ክፉ ሕሊና
ክፉ ሕሊና ተበላሽቶ ወደ ሥነ ምግባር ዝቅጠት የሚመራ ነው። ይህ ሕሊና የእግዚአብሔርን ፈቃድ የሚጻረር እና የኃጢያት ባህሪን የሚያበረታታ ነው። (ዕብ. 10፥22)
2. የረከሰ ሕሊና
የረከሰ ሕሊና በኃጢአት የረከሰና ግልጽ የሆነ የሞራል ልዩነት ማድረግ የማይችል ነው። ትክክል እና
ስህተት መካከል ወደ ግራ መጋባት ይመራል። (ቲቶ. 1፥15)
3. የደነዘዘ ሕሊና
የደነዘዘ ሕሊና ማለት በድግግሞሽ ኃጢአት የተዳከመ ወይም የደነደነ ነው። ከጊዜ በኋላ
ሰውየው ለጥፋተኝነት ወይም ለጥፋተኝነት ግድየለሽ ይሆናል። ኃጢአትን እንደ ስህተት አይገነዘብም። (1ኛ ጢሞ.
4፥2)
4. ደካማ ሕሊና
ደካማ ሕሊና የሚያመለክተው ኃጢአት በሌለበት አካባቢም እንኳ በቀላሉ ሊኮነን የሚችል ያልበሰለ
ወይም ከልክ ያለፈ ስስ ሕሊና ነው። ይህ ሊሆን የሚችለው አንድ ሰው በተፈጥሮ ኃጢአተኛ ያልሆኑ የሥነ ምግባር ጉዳዮች ላይ እርግጠኛ ካልሆነ ነው። (1ኛ ቆሮ. 8፥7)
5. ንጹሕ ሕሊና
ንፁህ ህሊና ማለት ከጥፋተኝነት እና ከነቀፋ በጸዳ መልኩ በእግዚአብሔርና በሰው ፊት መኖር ፣ በታማኝነት እና በመታዘዝ መመላለስ ማለት ነው። (ሐዋ. 24፥16)
6. በጎ ሕሊና
በጎ ሕሊና ከእግዚአብሔር እውነት ጋር የሚስማማ እና ወደ ጽድቅ ሕይወት የሚመራ ነው። ግለሰቡ
ይቅርታን እንዲጠይቅ እና የሞራል ህይወት እንዲጠብቅ የሚገፋፋው ለኃጢያት እና የጥፋተኝነትን ድንበር በማወቅ ለእነዚህ ነገሮች ንቁ የሆነ ነው። (1 ጢሞ. 1፥19)

👍14🔥1
. ==❀❀❀===❀❀❀==
🌼 የዕለቱ ጥቅስ 🌼
==❀❀❀===❀❀❀==
“ስለዚህ እኔ ደግሞ በእግዚአብሔርና በሰው ፊት ሁልጊዜ ነውር የሌለባት ሕሊና ትኖረኝ ዘንድ እተጋለሁ።”
ሐዋርያት 24፥16

❤8