"
ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ
ወደ ቻናሉ ለመ🀄️ላ🀄️ል፦ @Holy_scriptures
ቅዱሳት መጻሕፍት በልባችን እንድናተም እንጂ በመጻሕፍት መልክ እንድንይዛቸው አልተሰጡንም።"ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ
ወደ ቻናሉ ለመ🀄️ላ🀄️ል፦ @Holy_scriptures
👍7👏1
. ==❀❀❀===❀❀❀==
የዕለቱ ጥቅስ
==❀❀❀===❀❀❀==
“ወደ እርሱም ጸለየ፤ እርሱም ተለመነው፥ ጸሎቱንም ሰማው፥ ወደ መንግሥቱም ወደ ኢየሩሳሌም መለሰው ምናሴም እግዚአብሔር እርሱ አምላክ እንደ ሆነ አወቀ።”
2 ዜና 33፥13

👍6
#እራሳችንን_እንመርምር
የእስራኤል ሕዝብ ከግብፅ ምድር ወጥቶ ወደ ከነዓን ለመድረስ የጀመረው ጉዞ እጅግ ፈታኝ ነበር። ጉዞውን በጣም ፈታኝ ያደረገው በምድረበዳ መጓዛቸው ሳይሆን እነርሱ ምድረበዳውን ሲያዩ የሚያሰሙት እሮሮና በሕይወታቸው የሚወስኑት ውሳኔ ነበር። እና ምን ማድረግ ይገባቸው ነበር? እኛስ በዘመናችን እንዲህ የሁኔታ ማዕበል እና ወጀብ ሲመታን ምን እናድርግ?
“ባሪያዬ ካሌብ ግን ሌላ መንፈስ ከእርሱ ጋር ስለ ሆነ ፈጽሞም ስለተከተለኝ እርሱ ወደ ገባባት ምድር አገባዋለሁ፤ ዘሩም ይወርሳታል።”
ዘኍልቁ 14፥24
“ከእኔ ጋር የወጡ ወንድሞቼ ግን የሕዝቡን ልብ አቀለጡ፤ እኔ ግን አምላኬን እግዚአብሔርን ፈጽሜ ተከተልሁ።”
ኢያሱ 14፥8

👍5❤1
. ==❀❀❀===❀❀❀==
የዕለቱ ጥቅስ
==❀❀❀===❀❀❀==
“ነገር ግን ቀስቱ እንደ ጸና ቀረ፤ የእጆቹም ክንድ በያዕቆብ አምላክ እጅ በረታ፥ በዚያው በጠባቂው በእስራኤል ዓምድ፥”
ዘፍጥረት 49፥24

“በዚያን ጊዜም መጻሕፍትን ያስተውሉ ዘንድ አእምሮአቸውን ከፈተላቸው፤”
ሉቃስ 24፥45

❤4
#አዲስ_ዓመት
#New_year
ውድ የቻናላችን ቤተሰቦች ጌታ ቢፈቅድ እና በሕይወት ብንኖር ከአንድ ሳምንት በኋላ በኢትዮጵያ የጊዜ ሰሌዳ አቆጣጠር አዲስ ዓመት እንቀበላለን። በዚህ መሠረት ለቻናላችን ቤተሰቦች በአዲሱ ዓመት ቅዱሳት መጻሕፍትን በተገቢው ሁኔታ ለማጥናት እና ለመረዳት እንዲያመቻቸው ለአንድ ዓመት የሚሆን የተለያየ የጥናት ስልት፣ አጋዥ መጻሕፍትን በዚህ ቻናል እንለጥፋለን። እናንተም ቤተሰቦቻችን ለአዲስ ዓመት እንዲመች ሊነሱ ይገባሉ የምትሉትን አሳቦች በነጻነት ማንጸባረቅ ትችላላችሁ።

👍20
. ==❀❀❀===❀❀❀==
የዕለቱ ጥቅስ
==❀❀❀===❀❀❀==
“ይህም ዳንኤል በዳርዮስ መንግሥትና በፋርሳዊው በቂሮስ መንግሥት ኑሮው ተቃናለት።”
ዳንኤል 6፥28

❤5👍2
በኢትዮጵያ ዘመን አቆጣጠር መሠረት 2017 ዓ.ም ዘመነ ማን ይባላል?
Anonymous Quiz
38%
ሀ. ዮሐንስ
16%
ለ. ሉቃስ
17%
ሐ. ማርቆስ
29%
መ. ማቴዎስ
👍9👎5
. ==❀❀❀===❀❀❀==
የዕለቱ ጥቅስ
==❀❀❀===❀❀❀==
“ቃሉን ልኮ ፈወሳቸው፤ ከመቃብርም አፋፍ መለሳቸው።”
መዝሙር 107፥20 (አዲሱ መ.ት)
ወደ ቻናሉ ለመ🀄️ላ🀄️ል፦ @Holy_scriptures
የዕለቱ ጥቅስ
==❀❀❀===❀❀❀==
“ቃሉን ልኮ ፈወሳቸው፤ ከመቃብርም አፋፍ መለሳቸው።”
መዝሙር 107፥20 (አዲሱ መ.ት)
ወደ ቻናሉ ለመ🀄️ላ🀄️ል፦ @Holy_scriptures
👍5
መጽሐፍ ቅዱስን በሚገባ ለመረዳት.pdf
4 MB
#አዲስ_ዓመት
#New_Year
👉ርዕስ፦ መጽሐፍ ቅዱስን በሚገባ ለመረዳት
✍ጸሐፊ፦ ቲ. ኖርተን ስቴሬት
🗣ትርጉም፦ ተክሉ መንገሻ
ይህ መጽሐፍ፣ መጽሐፍ ቅዱስን በሚገባ ለመረዳት በጣም ጠቃሚ መጽሐፍ ስለሆነ በአዲስ ዓመት ቅዱሳት መጻሕፍትን በአዲስ መልኩ ለማጥናት ሁነኛ መጽሐፍ እንደሆነ አምነን እነሆ ብለናችኋል። በውስጡም የሚከተሉትን ጉዳዮች አካቷል፦
መሠረታዊ አሳቦች
👉መጽሐፍ ቅዱስን ማን ሊረዳው ይችላል?
👉ለማጥናት ትክክለኛውን መሣሪያ እንዴት መጠቀም እችላለሁ?
👉ለማጥናት እንዴት መጀመር እችላለሁ?
አጠቃላይ መመሪያዎች
👉አገባቡን፣ ቃላትን፣ ሰዋሰውን እና የደራሲውን ዓላማ እንዴት ልረዳው እችላለሁ?
👉ቅድመ ሁኔታውን ማጥናት
👉ቅዱስ ቃሉን በራሱ መተርጎም
ልዩ መመሪያዎች
👉ዘይቤያዊ አነጋገር፣ ተምሳሌቶች(Symbols), አምሳያዎች (Types), ምሳሌዎችና ምሳሌያዊ ገለጣዎች
👉የዕብራይስጥ ቋንቋ ፈሊጦች፣ ሥነ-ግጥም መረዳት
👉ትንቢት እና ትምህርተ-ሃይማኖት መረዳት
👉የብሉይና የአዲስ ኪዳናት ግንኙነትን መረዳት
በስተመጨረሻም ያጠናነውን ለግል ጥቅም ሥራ ላይ ማዋል እንዴት እንደሚቻል የሚያብራራ ድንቅ መጽሐፍ ነው።

👍12
. ==❀❀❀===❀❀❀==
የዕለቱ ጥቅስ
==❀❀❀===❀❀❀==
“አባታችሁ ርኅሩኅ እንደ ሆነ ርኅሩኆች ሁኑ።”
ሉቃስ 6፥36
ወደ ቻናሉ ለመ🀄️ላ🀄️ል፦ @Holy_scriptures
የዕለቱ ጥቅስ
==❀❀❀===❀❀❀==
“አባታችሁ ርኅሩኅ እንደ ሆነ ርኅሩኆች ሁኑ።”
ሉቃስ 6፥36
ወደ ቻናሉ ለመ🀄️ላ🀄️ል፦ @Holy_scriptures
👍5❤3
#የእግዚአብሔር_ቃል_ምን_ይላል?
ኢሳይያስ 6
¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯
¹ ንጉሡ ዖዝያን በሞተበት ዓመት እግዚአብሔርን በረጅምና ከፍ ባለ ዙፋን ላይ ተቀምጦ አየሁት፥ የልብሱም ዘርፍ መቅደሱን ሞልቶት ነበር።
² ሱራፌልም ከእርሱ በላይ ቆመው ነበር፥ ለእያንዳንዱም ስድስት ክንፍ ነበረው፤ በሁለት ክንፍ ፊቱን ይሸፍን ነበር፥ በሁለቱም ክንፍ እግሮቹን ይሸፍን ነበር፥ በሁለቱም ክንፍ ይበር ነበር።
³ አንዱም ለአንዱ፦ ቅዱስ፥ ቅዱስ፥ ቅዱስ፥ የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር፤ ምድር ሁሉ ከክብሩ ተሞልታለች እያለ ይጮኽ ነበር።
⁴ የመድረኩም መሠረት ከጭዋኺው ድምፅ የተነሣ ተናወጠ፥ ቤቱንም ጢስ ሞላበት።
⁵ እኔም፦ ከንፈሮቼ የረከሱብኝ ሰው በመሆኔ፥ ከንፈሮቻቸውም በረከሱባቸው ሕዝብ መካከል በመቀመጤ ዓይኖቼ የሠራዊትን ጌታ ንጉሡን እግዚአብሔርን ስለ አዩ ጠፍቻለሁና ወዮልኝ! አልሁ።
⁶ ከሱራፌልም አንዱ እየበረረ ወደ እኔ መጣ፥ በእጁም ከመሠዊያው በጕጠት የወሰደው ፍም ነበረ።
⁷ አፌንም ዳሰሰበትና፦ እነሆ፥ ይህ ከንፈሮችህን ነክቶአል፤ በደልህም ከአንተ ተወገደ፥ ኃጢአትህም ተሰረየልህ አለኝ።
⁸ የጌታንም ድምፅ፦ ማንን እልካለሁ? ማንስ ይሄድልናል? ሲል ሰማሁ። እኔም፦ እነሆኝ፥ እኔን ላከኝ አልሁ።
⁹ እርሱም፦ ሂድ፥ ይህን ሕዝብ፦ መስማትን ትሰማላችሁ አታስተውሉምም ማየትንም ታያላችሁ አትመለከቱምም በላቸው።
¹⁰ በዓይናቸው እንዳያዩ፥ በጆሮአቸውም እንዳይሰሙ፥ በልባቸውም እንዳያስተውሉ፥ ተመልሰውም እንዳይፈወሱ፥ የዚህን ሕዝብ ልብ አደንድን፥ ጆሮአቸውንም አደንቍር፥ ዓይናቸውንም ጨፍን አለኝ።
¹¹ እኔም፦ ጌታ ሆይ፥ እስከ መቼ ድረስ ነው? አልሁ። እርሱም መልሶ እንዲህ አለ፦ ከተሞች የሚኖርባቸውን አጥተው እስኪፈርሱ ድረስ፥ ቤቶችም ሰው አልቦ እስኪሆኑ ምድርም ፈጽሞ ባድማ ሆና እስክትቀር ድረስ፥
¹² እግዚአብሔርም ሰዎችን እስኪያርቅ፥ በምድርም መካከል ውድማው መሬት እስኪበዛ ድረስ ነው።
¹³ በእርስዋም ዘንድ አሥረኛ እጅ ቀርቶ እንደ ሆነ እርሱ ደግሞ ይቃጠላል፤ በተቈረጡ ጊዜ ጉቶቻቸው እንደ ቀሩ እንደ ግራርና እንደ ኮምበል ዛፍ ሆኖ፥ ጉቶው የተቀደሰ ዘር ይሆናል።

👍4
. ==❀❀❀===❀❀❀==
የዕለቱ ጥቅስ
==❀❀❀===❀❀❀==
“ከእርሱም የሰማናት ለእናንተም የምናወራላችሁ መልእክት፦ እግዚአብሔር ብርሃን ነው ጨለማም በእርሱ ዘንድ ከቶ የለም የምትል ይህች ናት።”
1ኛ ዮሐንስ 1፥5

❤6
#አዲስ_ዓመት
#New_Year
መጽሐፍ ቅዱስን እንዴት እናንብብ? ጠቃሚ መርሆች
ክፍል-1
መጽሐፍ ቅዱስ ማዕከላዊ መልዕክቱ ለማንኛውም ሰው ግልፅ ሊሆን በሚችልበት ሁኔታ የተቀመጠ ስለሆነ በሁሉም የዕድሜ ክልሎችና በየትኛውም የትምህርት ደረጃ ላይ ላሉ ሰዎች መናገር የሚችል መጽሐፍ ነው፡፡ 2ኛ ጢሞቴዎስ 3፡14-15 ላይ ህጻናት እንኳ የመጽሐፍ ቅዱስን ዋና መልዕክት መረዳት እንደሚችሉ ይናገራል፡፡ ይህ ማለት ግን ሁሉም የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍሎች እኩል በሆነ ሁኔታ ግልፅ ናቸው ወይንም ደግሞ በቀላሉ ለመረዳት የሚያዳግቱ ክፍሎች የሉም ማለት አይደለም፡፡ ነገር ግን ማንኛውም ሰው የዘላለምን ሕይወት ማግኘት እንዲችል ማዕከላዊ መልእክቱ ብዙ ጊዜ በመደጋገምና እጅግ ግልጽ በሆነ ሁኔታ ተቀምጧል፡፡
መጽሐፍ ቅዱስ የተጻፈው እንድናነበው እንጂ እንደ ምትሃታዊ መጽሐፍ በመቁጠር ተንተርሰነው እንድንተኛ ወይንም ደግሞ ሊነካካ በማይችልበት ስፍራ በጥንቃቄ እንድናስቀምጠው አይደለም፡፡ የእግዚአብሔር ቃል በሕይወታችን ውስጥ ሊሠራ የሚችለው ሲነበብ ነው፡፡ የእግዚአብሔር ቃል እንደ አድካሚ ኃይማኖታዊ ሕግጋት ስብስብ ሊታሰብ አይገባም፡፡ የእግዚአብሔር ቃል የሕይወት ቃል ነው፤ ሕያውና የሚሠራም ነው፡፡ ስናነበው እምነትን በውስጣችን ይፈጥራል፣ ነፍሳችንን ያድሳል፤ ይለውጠናልም፡፡ በውስጡ የተቀመጡትን ሕግጋት በራሳችን ኃይልና ጥረት ልንፈፅማቸው እንደምንችል መቁጠር አይኖርብንም፡፡ በእግዚአብሔር ቃል ሐሳብ ለመኖር መጀመርያ ቃሉ በውስጣችን በሚፈጥረው እምነት በክርስቶስ ኢየሱስ አዳኝነት በማመን አዲስ ፍጥረት መሆን ያስፈልገናል፤ ከዚያም ኃይል የሚሰጠውን የክርስቶስን መንፈስ መቀበል ያስፈልገናል፡፡
የእግዚአብሔርን ቃል አንብበን የምንረዳው ሰዎች ባወጡት ቀመር መሠረት ባይሆንም ነገር ግን ሊታወቁ የሚገባቸው መርሆች አሉ፡፡ በማስከተል እነዚህን መርሆች እንዳስሳለን፡፡
የልብ ዝግጅት
አንዳድ ሰዎች በተደጋጋሚ የሚናገሩት የተለመደ ነገር ቢኖር መጽሐፍ ቅዱስን በማንበባቸው ሳብያ ትክክል አለመሆኑን እንደተገነዘቡና በቀደመው ሃይማኖታቸው እንዲፀኑ እንደረዳቸው ነው፡፡ እነዚህ ወገኖቻችን ያልተገነዘቡት አንድ እውነት ቢኖር የእግዚአብሔር ቃል ተልዕኮ ሁለት ገጽታ ያለው መሆኑን ነው፡፡ መጽሐፍ ቅዱስ እውነትን ለሚጠሙ ሰዎች የሕይወት ቃል ሲሆን በእውነት ላይ ለሚያምጹ ሰዎች ደግሞ የፍርድ ቃል ነው፡፡ የእግዚአብሔር ቃል ሰዎችን ወደ እምነት ያመጣል አለዚያም ደግሞ ልባቸውን በማደንደን ይገፈትራቸዋል፡፡ ሁለቱም ውጤቶች ግን ከሰዎቹ የልብ ዝግጅት አንጻር የሚከወኑ ናቸው፡፡ የእግዚአብሔር ቃል ሕይወት አልባ ንግግር ሳይሆን የሚሠራ ነው፡-
“የእግዚአብሔር ቃል ሕያው ነውና፥ የሚሠራም፥ ሁለትም አፍ ካለው ሰይፍ ሁሉ ይልቅ የተሳለ ነው፥ ነፍስንና መንፈስንም ጅማትንና ቅልጥምንም እስኪለይ ድረስ ይወጋል፥ የልብንም ስሜትና አሳብ ይመረምራል”
(ዕብ. 4፡12)
ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ እንደተናገረው በመጨረሻው ቀን በኛ ላይ የሚፈርደው ቃሉ ነው፡-
“ዓለምን ላድን እንጂ በዓለም ልፈርድ አልመጣሁምና ቃሌን ሰምቶ የማይጠብቀው ቢኖር የምፈርድበት እኔ አይደለሁም። የሚጥለኝ ቃሌንም የማይቀበለው እርሱ የሚፈርድበት አለው፤ እኔ የተናገርሁት ቃል እርሱ በመጨረሻው ቀን ይፈርድበታል።”
(ዮሐ. 12፡47-48)
ሐዋርያው ቅዱስ ጳውሎስ በ2ኛ ቆሮንቶስ መልዕክቱ ላይ የሚከተለውን ይናገራል፡-
“በሚድኑቱና በሚጠፉቱ ዘንድ ለእግዚአብሔር የክርስቶስ መዓዛ ነንና፤ ለእነዚህ ለሞት የሚሆን የሞት ሽታ ለእነዚያም ለሕይወት የሚሆን የሕይወት ሽታ ነን። ለዚህም ነገር የሚበቃ ማን ነው?” 2ኛ ቆሮንቶስ 2፡15-16
ሐዋርያው እያለ ያለው ነገር ቢኖር ወንጌል ዝም ብለን የምንቀበለው ወይንም ደግሞ የምንጥለው ነገር ሳይሆን ብንቀበለው ወይንም ደግሞ ባንቀበለው በሕይወታችን ላይ ተፅዕኖ ማምጣቱ ግድ መሆኑን ነው፡፡ ስለዚህ ሰዎች የእግዚአብሔርን ቃል ሲንቁ፣ መዘባበቻ ሲያደርጉና ሲያምጹበት የተሸነፉት እነርሱ እንጂ ቃሉ አይደለም፡፡ በዚህም ሆነ በዚያ የእግዚአብሔር ቃል አሸናፊ ነው፡፡ ለተቀበሉት የዘላለምን ሕይወት ሲሰጥ ባልተቀበሉት ላይ ግን ይፈርዳል፡፡ የወንጌል መልዕክት እውነትን ለማወቅ ለሚፈልጉ ሰዎች የሕይወት ዜና ነው፤ ለዘባቾች ግን የሞት ዜና ነው፡፡ ውድ አንባቢያን እናንተ የእግዚአብሔርን ቃል እውነትን በሚፈልግ ልብ ከሚያነቡት ወገን ናችሁ ወይንስ ከቃሉ ውስጥ “ስህተቶችን” ነቅሰው ለማውጣት ከሚያነቡት ሰዎች ወገን ናችሁ? ቀና በሆነ ልብ ቃሉን በማንበብ የዘላለምን ሕይወት ታገኙ ዘንድ ምኞታችንና ጸሎታችን ነው፡፡
ሥነ ፍታቴ (Hermeneutics)
የሥነ ፍታቴ ጥቅም መጽሐፍ ቅዱስ በተጻፈበት ዘመን ለመጀመርያዎቹ ተቀባዮች የነበረውን ትርጉምና ዛሬም ደግሞ ለኛ ምን ማለት እንደሆነ እንድንረዳ ማገዝ ነው፡፡ በዘመናት መካከል ሰዎች ይህንን ቃል ብዙ ክፉ ሥራዎቻቸውን ለማጽደቅ ጠቅሰውታል፡፡ በዚህ ዘመንም ብዙ ሰዎች በመልካምም ሆነ በእኩይ ፍላጎት በመነሳሳት መጽሐፍ ቅዱስ ያላለውን ነገር ሲያስብሉት እናያለን፡፡ በቤተ ክርስቲያን ውስጥ የሚገኙ ብዙ ሰባኪያን ትግላቸው በአንድ ጥቅስ ውስጥ ያለን ልዩ ትርጉም ማግኘት ይመስላል፡፡ የስህተት አስተማሪዎችና ከክርስትና ውጪ ያሉ የአንዳንድ ሃይማኖቶች ተከታዮችም ደግሞ የራሳቸውን አስተምህሮ ለመደገፍ ወይንም ደግሞ መጽሐፍ ቅዱስ ስህተት እንዳለበት ለማሳየት በማለም ጥቅሶችን ይጠመዝዛሉ፡፡
መጽሐፍ ቅዱስን በምናጠናበት ሰዓት ከመሠረታዊ የሥነ ፍታቴ መርሆች ጋራ የሚጣረስ አተረጓጎም የምንጠቀም ከሆነ ወደ ስህተት እንገባለን፡፡ ስለዚህ ማንኛውም መጽሐፍ ቅዱስን ለግል ሕይወቱም ሆነ ሌሎችን ለማስተማር ማጥናት የሚፈልግ ሰው እነዚህን ጠቃሚ መርሆች ማወቅ ይኖርበታል፡፡
ጎርደን ዲ. ፊ. እና ዳግላስ ስቱዋርት የተባሉ ክርስቲያን ጸሐፍት የሥነ ፍታቴን አስፈላጊነት በተመለከተ የሚከተለውን ብለዋል፡-
ሥነ ፍታቴ አስፈላጊ መሆኑን የሚያሳይ መርህ በመጽሐፍ ቅዱስ ባሕርይ ውስጥ ይገኛል፡፡ ቤተክርስቲያን የመጽሐፍ ቅዱስን ባሕርይ የክርስቶስን ባሕርይ በምትረዳበት ሁኔታ ስትረዳ እንደኖረች ታሪክ ያሳያል፡፡ መጽሐፍ ቅዱስ በአንድ ጊዜ ሰብዓዊም መለኮታዊም ነው፡፡ ፕሮፌሰር ጆርጅ ላድ አንድ ጊዜ እንደተናገሩት፦ “መጽሐፍ ቅዱስ በሰዎች ቃላት በታሪክ ውስጥ የተሰጠ የእግዚአብሔር ቃል ነው፡፡” እንግዲህ ይህ ሁለትዮሽያዊ የመጽሐፍ ቅዱስ ባሕርይ ነው እንድንተረጉመው የሚያስገድደን፡፡
ይቀጥላል...
ምንጭ:- www.ewnetlehulu.org

የመፅሐፍ_ቅዱስ_ማጥኛ_እቅድ_bible_reading.pdf
182.9 KB
#አዲስ_ዓመት
#New_Year
መጽሐፍ ቅዱስን በአንድ ዓመት ውስጥ አጥንቶ ለመጨረስ የሚረዳ የጥናት እቅድ
👉 እያንዳንዱ ወር 25 የማጥኛ ቀናቶች አሉት:: ቀሪዎቹ 5 ቀናት ምናልባትም
የተዘለለ ቀን ካለ ወይም ለክለሳ የሚሆን ነው::
👉 እያንዳንዱ ቀን ከ ብሉይ ኪዳን እና ከ አዲስ ኪዳን ሁለቱንም ያጠቃለለ ሲሆን
የመፅሐፍ ቅዱስ ውህደቱንም በሚገባ እንድንረዳ ይረዳናል::
👉ይሄ pdf የተዘጋጀው ከ JUNE - M A Y /ሰኔ-ግንቦት) ግን ከማንኛውም ወር መጀመር ይቻላል::
በአክሊሉ ተፈራ

👍12🔥2😁1
. ==❀❀❀===❀❀❀==
የዕለቱ ጥቅስ
==❀❀❀===❀❀❀==
“በመልካም መሬት ላይም የወደቀ እነርሱ በመልካምና በበጎ ልብ ቃሉን ሰምተው የሚጠብቁት በመጽናትም ፍሬ የሚያፈሩ ናቸው።”
ሉቃስ 8፥15
ወደ ቻናሉ ለመ🀄️ላ🀄️ል፦ @Holy_scriptures
የዕለቱ ጥቅስ
==❀❀❀===❀❀❀==
“በመልካም መሬት ላይም የወደቀ እነርሱ በመልካምና በበጎ ልብ ቃሉን ሰምተው የሚጠብቁት በመጽናትም ፍሬ የሚያፈሩ ናቸው።”
ሉቃስ 8፥15
ወደ ቻናሉ ለመ🀄️ላ🀄️ል፦ @Holy_scriptures
👍9
ቅዱሳት መጻሕፍት
#አዲስ_ዓመት #New_Year መጽሐፍ ቅዱስን እንዴት እናንብብ? ጠቃሚ መርሆች ክፍል-1 መጽሐፍ ቅዱስ ማዕከላዊ መልዕክቱ ለማንኛውም ሰው ግልፅ ሊሆን በሚችልበት ሁኔታ የተቀመጠ ስለሆነ በሁሉም የዕድሜ ክልሎችና በየትኛውም የትምህርት ደረጃ ላይ ላሉ ሰዎች መናገር የሚችል መጽሐፍ ነው፡፡ 2ኛ ጢሞቴዎስ 3፡14-15 ላይ ህጻናት እንኳ የመጽሐፍ ቅዱስን ዋና መልዕክት…
#አዲስ_ዓመት
#New_Year
መጽሐፍ ቅዱስን እንዴት እናንብብ? ጠቃሚ መርሆች
ክፍል-2
መጽሐፍ ቅዱስ የእግዚአብሔር ቃል በመሆኑ ዘላለማዊ አስፈላጊነት አለው፤ የእግዚአብሔር ቃል በመሆኑ ልንሰማውና ልንታዘዘው ይገባናል፡፡ ነገር ግን እግዚአብሔር ቃሉን በታሪክ ውስጥ በሰው ቋንቋ ለመናገር ስለመረጠ በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ያለ መጽሐፍ ሁሉ ታሪካዊ ውስንነት አለው፡፡ እያንዳንዱ ክፍል መጀመርያ በተጻፈበት ቋንቋ፣ ዘመንና ባሕል የተወሰነ ነው (በአንዳንድ ሁኔታዎች ውስጥ በተጨማሪም በጽሑፍ ከመስፈሩ በፊት በነበረው የአፈታሪክ ትውፊት [የተወሰነ ነው])፡፡ በዘላለማዊ አስፈላጊነቱና በታሪካዊ ውስንነቱ መካከል ያለው “ውጥረት” መተርጎምን አስፈላጊ ያደርገዋል፡፡ (Gordon D. Fee & Douglas Stuart: How to Read the Bible For All Its Worth, Second Edition, Zondervan, Grand Rapids, 1993, Introduction)
ይህ ርዕስ በጣም ሰፊና ጥልቅ ቢሆንም ነገር ግን መጽሐፍ ቅዱስን በግላቸው ለማጥናትና በትክክል ለመረዳት ለሚሹ ወገኖች ጠቃሚ የሆኑ ምክረ ሐሳቦችን ብቻ አጠር አድርገን እናስቀምጣለን፡፡
በሥነ ፍታቴ ውስጥ ሦስቱ መሠረታውያን ነጥቦች፡- ሐቲት፣ መተርጎምና ማዛመድ ናቸው፡፡
ሐቲት (Exegesis)
“ኤክሰጂሰስ” የሚለው የእንግሊዘኛ ቃል ከግሪክ የተገኘ ነው፤ ትርጉሙም “ማውጣት” እንደማለት ሲሆን አንድ ቃል ለመጀመርዎቹ ተቀባዮች በራሳቸው ቋንቋና ባሕል ምን ማለት እንደነበር ለማግኘት የሚደረግ ሥርዓትን የጠበቀ ጥናት ነው፡፡ በሐቲት ውስጥ ሁለት መሠረታውያን ነጥቦች አሉ፡፡ የመጀመርያው አውድ ሲሆን ሁለተኛው ደግሞ ይዘት ነው፡፡
1. አውድ
ሁለት ዓይነት አውዶች አሉ፡-
ሀ. ታሪካዊ አውድ
ይህ መጽሐፉ የተጻፈበትን ጊዜና ባሕል የሚመለከት ሲሆን የጸሐፊውንና የተደራሲያኑን መንፈሳዊ፣ ማህበራዊ፣ ፖለቲካዊ፣ ምጣኔ ሃብታዊ፣ መልክአ ምድራዊ አቀማመጥና ሌሎች ከጽሑፉ ይዘትና ትርጉም ጋር ሊገናኙ የሚችሉ ነጥቦችን ሁሉ ከግምት ውስጥ የማስገባት ሥራ ነው፡፡ የሚከተሉትን ጥያቄዎች በመጠየቅ የአንድን የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍል ታሪካዊ አውድ ማወቅ እንችላለን፡-
👉ጸሐፊው ማነው? (የጸሐፊውን ስም እርግጠኛ በመሆን ማወቅ ቢሳነን እንኳ ከአጻጻፉ በመነሳት ስለ እርሱ መገመት እንችላለን)
👉ተደራሲያኑ እነ ማን ናቸው?
👉መቼ ተጻፈ?
👉የት ተጻፈ?
👉የተጻፈበት ምክንያት ምን ነበር?
ከላይ የተጠቀሱትንና ሌሎች ጥያቄዎችን ብንጠይቅ የመጽሐፉን ታሪካዊ አውድ በቀላሉ ማወቅ እንችላለን፡፡ እነዚህን ለመሳሰሉ ጥያቄዎች ምላሽ ማግኘት ያን ያህል የሚቸግር ባይሆንም ነገር ግን ስለ ጉዳዩ የበለጠ እውቀት ባላቸው ሰዎች የተጻፉ ጥሩ ሐተታዎችንና መዝገበ ቃላትን ብንጠቀም ግንዛቤያችን ይበልጥ ሊሰፋ ይችላል፡፡
ለ.የምንባብ አውድ
ይህ ቀላል የሆነ፣ ነገር ግን ብዙ ሰዎች ትኩረት ስለማይሰጡት በመጽሐፍ ቅዱስ አተረጓጎም ላይ ትልልቅ ስህተቶችን እንዲሰሩ ምክንያት የሚሆናቸው ነጥብ ነው፡፡ የሥነ ፍታቴ ምሑራን የዚህን መርህ አስፈላጊነት አፅንዖት ሰጥተው ሲናገሩ “#ምንባቡ_ንጉሥ_ነው” ይላሉ፡፡ አንድን ቃል፣ ሐረግ ወይንም ደግሞ ዓረፍተ ነገር በምንባብ አውድ ውስጥ መረዳት ማለት ዙሪያ ገባውን በማንበብ በተጻፈበት በዚያ ክፍል መሠረት የሚሰጠውን ትርጉም መረዳት ማለት ነው፡፡ ዛሬ ብዙ ሰዎች፣ በተለይም ደግሞ ሙስሊም ጸሐፍት ይህንን ቀላል መርህ ባይዘነጉ ኖሮ ስለ መጽሐፍ ቅዱስ “ስህተቶችና” “ግጭቶች” ብዙ በመጻፍ ባልደከሙ ነበር፡፡ በተደጋጋሚ የሚነሳውን አንድ ምሳሌ ለመጥቀስ ያህል፤ የምንባብ አውዱን ባንጠብቅ መጽሐፍ ቅዱስን “አምላክ የለም” ልናስብለው እንኳ እንችላለን፡፡ መዝሙር 14፥1 “አምላክ የለም” ይላል፡፡ ነገር ግን ሙሉ ጥቅሱ፡- “ሰነፍ በልቡ አምላክ የለም ይላል። በሥራቸው ረከሱ፥ ጐሰቈሉ በጎ ነገርን የሚሠራ የለም” የሚል ነው፡፡ ብዙ ጊዜ በተለያዩ መጻሕፍት ታትመው የሚወጡ ስለ መጽሐፍ ቅዱስ “ግጭቶችና” “ስህተቶች” የሚነገሩ አብዘኞቹ ውንጀላዎች ከዚህ የዘለለ ጥልቀት የሌላቸው ናቸው፡፡
የአንድን የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍል የምንባብ አውድ ለመረዳት የሚከተሉትን ጥያቄዎች ልናነሳ እንችላለን፡-
👉ተናጋሪው ማነው?
👉ለማነው የተናገረው?
👉ጸሐፊው ለምን ይህንን በዚህ ስፍራ አስገባው?
👉ከፊት ምን ተባለ?
👉ከኋላ ምን ተባለ?
👉ይህ ቃል፣ ሐረግ ወይም አረፍተ ነገር በዚህ ስፍራ ላይ የሚሰጠው ትርጉም ምንድነው?
👉ዋናው ጭብጥ ምንድነው?
ማንኛውንም የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍል በተጻፈበት አውድ ውስጥ ለመረዳት እነዚህንና መሰል ቀላል ጥያቄዎች ማንሳት ጠቃሚ ነው፡፡
2. ይዘቱን ማተት
ይዘት ከቃላትና ሐረጎች ትርጉም፣ የሰዋሰው አወቃቀርና በጥንታውያን የእጅ ጽሑፎች ውስጥ የተለያዩ አነባበቦች የሚገኙ ከሆነ ትክክለኛውን ከመምረጥ ጋር ይያያዛል፡፡ እነዚህን ነጥቦች ለማወቅ በዘርፉ ላይ ዕውቀት ባላቸው ሰዎች የተጻፉ የተለያዩ ሐተታዎችንና መዝገበ ቃላትን መጠቀም በጣም አስፈላጊ ነው፡፡
በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ እኛ ከለመድናቸው ትርጉሞች የተለየ ትርጉም ያላቸው ቃላትና ሐረጎች ሊኖሩ ይችላሉ፡፡ እንደምሳሌ ለማንሳት ያህል የጥንት አይሁዳውያን ማንኛውንም የቀን ክፍል እንደ ሙሉ ቀንና ሌሊት ነው የሚቆጥሩት፡፡ ለምሳሌ ሦስት ቀንና ሦስት ሌሊት ማለት የግድ 72 ሰዓታት ማለት ላይሆን ይችላል፡፡ አንዳንድ ጊዜ ደግሞ የአማርኛ ቃላት እንኳ ሆነው በትክክል የማንረዳቸው ቃላትና ሐረጎች ያጋጥማሉ፡፡
መጽሐፍ ቅዱስ በተጻፈበት ዘመን የነበሩ የተለያዩ መለኪያዎች፣ የቀን አቆጣጠሮችና የመሳሰሉት እኛ ከምናውቃቸው የተለዩ ስለሆኑ ምን ማለት እንደሆኑ ለማወቅ መዝገበ ቃላትን ወይንም ደግሞ ሐተታዎችን መጠቀም ያስፈልገናል፡፡ ሌላው ስለ ይዘት ሲታሰብ ሊታወቅ የሚገባው ነገር ቢኖር አንዳንድ ጊዜ የዓረፍተ ነገሮች ሰዋሰዋዊ አወቃቀር ዓረፍተ ነገሩ የተለያዩ ሁለት ትርጉሞች እንዲኖሩት ሊያደርግ መቻሉ ነው፡፡ በዚህ ጊዜ ሌሎች ትርጉሞችን ማየት ወይንም ደግሞ ሐተታዎችን በመጠቀም በመጀመርያዎቹ ቋንቋዎች ውስጥ ያለውን ትርጉም መፈለግ ጠቃሚ ነው፡፡

👍11