ቅዱሳት መጻሕፍት
7.45K subscribers
1.36K photos
61 videos
332 files
807 links
በዚህ ቻናል

👉ቅዱሳት መጻሕፍት ይጠናሉ::
👉መጽሐፍ ቅዱሳዊ ትምህርቶች ይቀርባሉ::
👉 ለቅዱሳት መጽሐፍት ጥናት የሚያግዙ መጻሕፍት ይለቀቃሉ።

⭐️⭐️⭐️⭐️⭐️

@Holy_scriptures
Download Telegram
ወደ ቻናሉ ለመ🀄️🀄️ል፦ @Holy_scriptures
3👍1
ኤርምያስና መልእክቱ.pdf
3.2 MB
👉ርዕስ፦ ኤርምያስና መልእክቱ
📑የገጽ ብዛት፦ 95


ወደ ቻናሉ ለመ🀄️🀄️ል፦ @Holy_scriptures
👍31
'    ==❀❀❀===❀❀❀==      
              የዕለቱ ጥቅስ
     ==❀❀❀===❀❀❀==
“ከኤልያስም የወደቀውን መጎናጸፊያ ወስዶ ውኃውን መታና፦ የኤልያስ አምላክ እግዚአብሔር ወዴት ነው? አለ፤ ውኃውንም በመታ ጊዜ ወዲህና ወዲያ ተከፈለ፤ ኤልሳዕም ተሻገረ።”
                   2ኛ ነገሥት 2፥14



ወደ ቻናሉ ለመ🀄️🀄️ል፦ @Holy_scriptures
👍81
#ከተማ_ወይም_ቦታ_በቅዱሳት_መጻሕፍት



#ቤተ_ሳይዳ

ቤተ ሳይዳ የዓሣ አጥማጅ ቤት ማለት

1. ከገሊላ ባሕር በስተሰሜን የዮርዳኖስ ወንዝ ወደሚገባበት አቅራቢያ ያለ ከተማ፤ የጴጥሮስና የእንድርያስ የፊልጶስም አገር፤ ዮሐ. 1፥44-50፤ 12፥21። ክርስቶስ በቤተ ሳይዳ ዐይነ ስውሩን ፈወሰ፤ ማር. 8፥22-26። ነገር ግን ከተማው ትምህርቱን አልተቀበለም፤ ሉቃ. 1፥13።

2. ሄሮድስ ፊልጶስ ምናልባት ይህን ከተማ፥ ወይም ቤተ ሳይዳ የተባለ ሌላውን ከተማ እንደገና በስተምሥራቅ ሠራ፤ ክርስቶስ በዚህ ከተማ አቅራቢያ ባለው በምድረ በዳ አምስት ሺህ ሰው መገብ፤ ሉቃ. 9፥10-17።

3. በኢየሩሳሌም ውስጥ ደግሞ ቤተ ሳይዳ የምትባል የበሽተኞች መጠመቂያ ቦታ ነበረች፤ ዮሐ. 5፥2። ግን ስምዋ ቤተ ሳይዳ ሳይሆን፥ ቤተ ሔሰዳ፥ ወይም ቤተ ዛታ የነበረ ይመስላል፤ ትርጕሙም «የምሕረት ቤት» ማለት ነው።


ምንጭ፦የመጽሐፍ ቅዱስ መዝገበ ቃላት፣ ገጽ 113-114




ወደ ቻናሉ ለመ🀄️🀄️ል፦ @Holy_scriptures
👍31👏1
'    ==❀❀❀===❀❀❀==      
              የዕለቱ ጥቅስ
     ==❀❀❀===❀❀❀==
“ጠላቴም ታያለች፥ እኔንም፦ አምላክህ እግዚአብሔር ወዴት ነው? ያለች በእፍረት ትከደናለች።”
                        ሚክያስ 7፥10




ወደ ቻናሉ ለመ🀄️🀄️ል፦ @Holy_scriptures
👍62
#እራሳችንን_እንመርምር

በሕይወት ውጣ ውረድ እና ስንክሳር ውስጥ ስንገባ እግዚአብሔር እንደሚያየን እና እኛ ለመርዳት መፍጠኑን መጠራጠር እንጀምራለን። ግን እውነታው እንደዛ ነው? እግዚአብሔር የማይገደው ሰው አለ? እሺ እሱ እንዳለ ሆኖ እኛስ በሕይወት ጉዞአችን ዓይኖቻችን ወደ እግዚአብሔር ወይስ ወደ ሁኔታ ናቸው?


“እርስዋም ይናገራት የነበረውን የእግዚአብሔርን ስም ኤልሮኢ ብላ ጠራች የሚያየኝን በውኑ እዚህ ደግሞ አየሁትን? ብላለችና።”
ዘፍጥረት 16፥13


“እርሱ እግሮቼን ከወጥመድ ያወጣቸዋልና ዓይኖቼ ሁልጊዜ ወደ እግዚአብሔር ናቸው።”
መዝሙር 25፥15




ወደ ቻናሉ ለመ🀄️🀄️ል፦ @Holy_scriptures
👍61
'    ==❀❀❀===❀❀❀==      
              የዕለቱ ጥቅስ
     ==❀❀❀===❀❀❀==
“እነሆም እኔ ከአንተ ጋር ነኝ፥ በምትሄድባትም መንገድ ሁሉ እጠብቅሃለሁ፥ ወደዚችም ምድር እመልስሃለሁ፤ የነገርሁህን ሁሉ እስካደርግልህ ድረስ አልተውህምና።”
                  ዘፍጥረት 28፥15




ወደ ቻናሉ ለመ🀄️🀄️ል፦ @Holy_scriptures
👍91
በብሉይ ኪዳን ካሉት መጻሕፍት ውስጥ እንደ ዮሐንስ ራእይ አቡቀለምሲሳዊ የሥነ ጹሑፍ መንገድ የሚከተለው የቱ ነው?
Anonymous Quiz
21%
ሀ. ትንቢተ ሕዝቅኤል
14%
ለ. ትንቢተ ኢሳይያስ
57%
ሐ. ትንቢተ ዳንኤል
2%
መ. ትንቢተ ኤርምያስ
3%
ሠ. መዝሙረ ዳዊት
2%
ረ. መጽሐፈ ኢዮብ
2
👍61
'    ==❀❀❀===❀❀❀==      
              የዕለቱ ጥቅስ
     ==❀❀❀===❀❀❀==
“ደመናም መጥቶ ጋረዳቸው፥ ከደመናውም፦ የምወደው ልጄ ይህ ነው፥ እርሱን ስሙት የሚል ድምፅ መጣ።”
                         ማርቆስ 9፥7



ወደ ቻናሉ ለመ🀄️🀄️ል፦ @Holy_scriptures
👍82🔥1
በክፉ ቀን..!



'' ስለዚህ በክፉው ቀን ለመቃወም ሁሉንም ፈጽማችሁ ለመቆም እንድትችሉ የእግዚአብሔርን እቃ ጦር ሁሉ አንሱ፡፡'' ኤፌ.6፤10-19

   "የክፉው ቀን" የቱ ነው?  የክፉው ቀን መቼስ ነው?

ልክ እንደ አሁኑ ጊዜ ማለት ነው ፡፡ ብዙ ፈተና የበዛበት፣ የጸለዩት የማይሰማበት የሚመስልበት ቀን፤ ለጠላት የተፈቀደለት ቀን ይመስላል፡፡ ምናልባትም የዓለም ፍጻሜ ቀን የመጨረሻዎቹ ደቂቃ ላይ እንገኛለን፡፡ ስለዚህም ምጡ በዛ፣ እጅግ ዘግናኝና አሰቃቂ ነገሮች እየተከናወኑ ነው፡፡ ማስቆም አልተቻለም፣ ደግሞስ የቱን ከየትኛው ማስጣል ይቻላል? ብዙዎች በየቤታቸው እንቆቅልሽ ውስጥ ናቸው ያሉት፣ የፈተናውና የመከራው ዓይነት ብዙ ነው፡፡ በፍጹም ያልጠበቅነው ነገር ገጥሞናል፡፡ በዚህ ክፉ ቀን የብዙዎች አቅም የሚፈተሽበት ፣ ጉልበታቸው የሚላላበት፣ እምነታቸውን የሚፈትን ነገር የሚገጥምበት ...ጊዜ ነው፡፡

 በሕይወት ያልታሰበ  ነገር ሲገጥም ያስደነግጣል፤ ቢሆንም የመጨረሻው ዘመን ባህሪ በመሆኑ ልንታገስ ደግሞ ይገባል፡፡ ሐዋርያው ጳውሎስ ለልጁ ለጢሞቴዎስ እንደጻፈለት ''ነገር ግን በመጨረሻ ቀን የሚያስጨንቅ ዘመን እንዲመጣ ይህን እወቅ ሰዎች ራሳቸውን የሚወዱ ይሆናሉና ፣ገንዘብን የሚወዱ፣ ትምክህተኞች፣ ትዕቢተኞች፣ ተሳዳቢዎች፣ ለወላጆቻቸው የማይታዘዙ፣ የማያመሰግኑ፣ ቅድስና የሌላቸው ፣ፍቅር የሌላቸው፣ ዕርቅን የማይሰሙ ፣ሐሜተኞች ፣ራሳቸውን የማይገዙ ፣ጨካኞች፣ መልካም የሆነውን የማይወዱ ፣ከዳተኞች ፤ችኩሎች፣ በትዕቢት የተነፉ፣ ከእግዚአብሔር ይልቅ ተድላን የሚወዱ፣ ይሆናሉ፤ የአምልኮት መልክ አላቸው ኀይሉን ግን ክደዋል ከእነዚህ ደግሞ ራቅ፡፡" 2ኛ ጢሞ.3፤1-5 

ማናችሁም ሰዎች የሆነባችሁ ነገር ከዚ ውጪ አይሆንም ብዬ እገምታለሁ፤ የሚያስጨንቀውን ዘመን ሁላችንም እየቀመስነው ነው፡፡ በዚህ ወቅት የሚያስፈልገው መጽናት ብቻ ነው፡፡

 አንዳንዱ ነገር ለምን እንደሆነብን እና እንደሚሆን ላይገባን ይችላል፡፡ አንገታቸውን በሰይፍ የሚቀሉ ሰዎች ብዛት፣ በህክምና ስህተት ያሳደጉዋቸውን ወላጆች የሚያጡ ሰዎች ብዛት፣ ጽኑ ወዳጅነት ወደ ጠላትነት መቀየር፣ ልጆችን በተለያየ አደጋ ማጣት፣ ክፉ ዘዴኛነት ፣ ብልጠት፣ ራስ ወዳድነት፣ ማታለል አስገራሚ ጭካኔዎች ሲሆኑ፤ ለምን ? እንዴት ማለታችን አልቀረም፡፡ ጌታ  የት ሄዶ ነው ይህ  ሁሉ የሚሆንብን ትሉ ይሆናል፡፡
 
የብሉይ ኪዳን የመጨረሻው ነብይ መጥምቁ ዮሐንስ እንዲህ ዓይነት ጥያቄ ተፈጥሮበት ነበረ '' የምትመጣው መሲህ አንተ ነህ  ወይስ ሌላ እንጠብቅ ?'' ብሎ ወደ ኢየሱስ መልዕክተኞችን ላከ፡፡ ወንጀል ሳይሰራ እስር ቤት መግባቱ ፣ በዚህም ላይ ብዙ የመሰከረለት ብርቱው ኢየሱስ በርሱ ጉዳይ ጣልቃ ገብቶ ፣ አልያም አንዳች ተአምራት ሰርቶ እርሱን ከእስር አለማስፈታቱ አደናግሮት ይሆናል፤ ነገር ግን ከዚህም የከፋ ሆነ፡፡ በእስራቱ ጊዜ ዝም ማለቱ ሲገርመን ጭራሽ በሔሮደስ ልደት ላይ ለዘፈነች አንዲት ወጣት ብላቴና ጥያቄ መሰረት አንገቱ ተቆርጦ በወጪት ቀረበ፡፡ ጌታስ? ዝም! በቃ ዝም!

አንዳንዱ ጉዳይ ከእኛ አእምሮ በላይ ነው፡፡ ምናልባት ከጌታ ጋር መግባባት ስለማንችል ይሆን ዝም የሚለን? እስጢፋኖስን በድንጋይ ወግረው ሲገድሉት ሁሉን የሚችለው ጌታ በዙፋኑ ላይ ቆሞ እያየው ነበር፤ ለምን እንዳላስጣለው አይታወቅም፣ የታመነው ምስክሩ አንቲጳስ ሲገደል ጌታ ጣልቃ አልገባም ፣ ሐዋርያቱ በዘይት ተጠብሰው ሲሞቱ፣ ህዝብ በተሰበሰበበት አናብስት ቦጫጭቀው ሲገድሉዋቸው የጠራቸው ጌታ በዙፋኑ ላይ ነበር፡፡ ለአንዳንዱ ጥያቄ መልስ በእጃችን የለም፡፡ አንድ የእግዚአብሔር ሰው እንዳሉት በፊሊፒንስ የጭቃ ጎርፍ 250 ህጻናትን ለምን ከድኖ እንደገደለ አናውቅም፡፡ በቅርብ ጊዜ አንድ የምታሳሳ ወጣት ከሲያትል ለሚሽን ጉዞ ወደ ህንድ ሄዳ በተመሳሳይ ለአገልግሎት ወደ ኢትዮጵያ የሄደው መጋቢ አባት ከጥቂት ቀናት በሁዋላ ተጠርቶ የመጣው ልጅህ ድንገት ሞታለች ተብሎ ተረድቶ ነበር፡፡ በጣም አሳዛኝ ነበረ፡፡

ወገኖች ለእኛ የሚበጀን ወደ እግዚአብሔር መቅረብ ነው ፤ ጥያቄያችን ባይመለስም እናመልከዋለን ፣እንወደዋለን፡፡ እንደዚህ የመሰሉ ቀናትን ልናሸንፍ  (ልንቋቋም) እንችላለን ፤የምንችለው ግን የእግዚአብሔርን ዕቃ ጦር በመልበስ  (በማንሳት) ነው፡፡ መሳሪያው ሰው ሰራሽ  ወይም አሜሪካ ፣ጃፓን ሰራሽ መሳሪያ ሳይሆን የእግዚአብሔር ዕቃ ጦር ይለዋል፡፡ እግዚአብሔር ለዚህ ክፉ ጊዜ እንዲሆነን ያዘጋጀልን መከላከያ እና ማሸነፊያ ዕቃ ጦር ነው፡፡ ቢያንስ ስድስት ነገሮች ናቸው ፤ቀጥለን እናያቸዋለን፡-
 

👉የእምነት መታጠቂያ- ወገባችን ላይ

👉የጽድቅ ጥሩር- ደረታችን አካባቢ

👉የሰላም ወንጌል- እግሮቻችን ላይ

👉የእምነት ጋሻ- በአንደኛው እጃችና ላይ

👉የመዳን ራስ ቁር- በጭንቅላታችን ላይ የሚደረግ

👉የመንፈስ ሰይፍ (የእግዚአብሔር ቃል ነው)- በቀኝ እጃችን ይዘን የምናጠቃበት ነው፡፡

 
ከራስ እስከ እግራችን ድረስ መሸፈን ያስፈለገን ምክንያት ጠላት እኛን ለመጉዳት ወይም ለመግደል ከጭንቅላታችን ጀምሮ ወርውሮ ስለሚሞክረን ነው፡፡ መዳኑ አስተማማኝ የሆነን ክርስቲያን ጭንቅላቱን መትቶ ሊጎዳው አይችልም፡፡ ነገር ግን ደረቱን በጥሩር ካልታጠቀ ማለትም ጽድቅ ላይ ገና የሚያመቻምች ሆኖ ካገኘው ይጎዳዋል፡፡ ነገር ግን እርሱም ከተሸፈነበት ቢያንስ እግሩን ስበሩት ብሎ መልዕክተኛ ይልካል:: ይህን ጊዜ ጠንካራ የወንጌል ከስክስ ያላደረገ  ሆኖ ከተገኘ ባይሞትም እንኩዋ ዘመኑን ሁሉ በመንፈስ እያነከሰ ይኖራል ስለዚህ ሙሉውን ትጥቅ መታጠቅና መመላለስ አለብን፡፡ እንደሚታወቀው ሰይጣን ትንሽ ቀዳዳ ፈልጎ  ነው የሚያጠቃን ፤ያልተሸፈነ አካላችንን ፈትሸን እንልበስ (እንታጠቅ)፡፡

የእስራኤል ንጉስ አክአብ የሞተው በጥሩርና በጥሩር መጋጠሚያ በኩል ከጠላት ወገን በተወረወረ ቀስት ተወግቶ ነው፡፡ ምናልባት ሁሉን ታጥቆ ነበር፤ ይሁንና  መቀነት ግን አላደረገም እንደማለት ነው፡፡ ምንም እንኩዋ በእርሱ ሞት ላይ ፍርድ ከእግዚአብሔር ዘንድ የወጣም ቢሆን፡፡ጥቃት የደረሰበትና ለሞት የበቃው ግን በተገኘው ክፍተት በኩል ነበር፡፡

 ወገኖች ሙሉ የእግዚአብሔርን ትጥቅ ታጥቀን በዚህ ዘመን እንድንኖር አሳስባችሁዋለሁ! እስቲ የላሉትን ጠበቅ እናድርጋቸው፤ ከትናንሽ ጥያቄዎቻችን እንውጣና ኩርፊያውን ትተን በእግዚአብሔር ፊት በጽድቅ ፣ በእውነት እንመላለስ!! የሚመጣልን መድኃኒት እርሱም ክርስቶስ ወደ ልዩ እረፍት ቦታ ይወስደናል፡፡ ብንጸና እንወርሳለን፡፡ በነገር ሁሉ ጌታ ከሁላችን ጋር ይሁን ፡፡ አሜን!!!


ምንጭ:- lemekeru.com



ወደ ቻናሉ ለመ🀄️🀄️ል፦ @Holy_scriptures
👍7🔥31
'    ==❀❀❀===❀❀❀==      
              የዕለቱ ጥቅስ
     ==❀❀❀===❀❀❀==
“ቀርበውም፦ አቤቱ፥ አቤቱ ጠፋን እያሉ አስነሡት። እርሱም ነቅቶ ነፋሱንና የውኃውን ማዕበል ገሠጻቸው፤ ተዉም፥ ጸጥታም ሆነ።”
                 ሉቃስ 8፥24




ወደ ቻናሉ ለመ🀄️🀄️ል፦ @Holy_scriptures
👍31
ቅዱሳት መጻሕፍት
የያዕቆብ ልጆች እና በረከቶቻቸው                    ክፍል - ፬ ስምዖን (ዘፍ. 49፥5-7) ስምዖን ከልያ ለያዕቆብ የተወለደለት ሁለተኛው ልጁ ነው። ልያም እኔ እንደ ተጠላሁ እግዚአብሔር ስለ ሰማ ይህንን ደገመኝ ስትል የሁለተኛ ልጇን ስም ስምዖን ብላ ጠራችው (ዘፍ. 29፥33)፡፡ ያዕቆብም ልጆቹን ሊመርቅ በተነሳ ጊዜ ስምዖንና ሌዊ በሰኬም ሰዎች ላይ ያደረጉትን በማስታወስ በልቡ የቆየና…
የያዕቆብ ልጆች እና በረከቶቻቸው



                   ክፍል - ፭



ሌዊ (ዘፍ. 49፥5-7፤ ዘዳ. 33፥8)


ሌዊ ያዕቆብ ከልያ የወለደው ሦስተኛው ልጅ ነው፡፡ እናቱ ልያም አስቀድሞ ባሌ ይጠላኝ ነበር ትል ስለ ነበር ይህን ሦስተኛ ልጅ በመውለዷ ምክንያት ባሌ ወደ አኔ ይጠጋል ስትል ስሙን ሌዊ ብላ ሰየመችው (ዘፍ. 29፥34)፡፡ ሌዊ ከታላቅ ወንድሙ ከስምዖን ጋር አብሮ ሰለ እኅቱ ዲና በሴኬም ሰው መደፈር ለበቀል ዘምቶ ስለ ነበር ይህ የበቀል ተግባሩ በያዕቆብ ምንኛ የተጠላ እንደ ነበር ያዕቆብ ስለ ስምዖንና ሌዊ በተናገረው የመጨረሻው ኑዛዜ ተመልክተናል (ዘፍ. 49፥5-7)፡፡ ይህ የስምዖንና የሌዊ ተግባር ከያዕቆብ ልብ ውስጥ ሳይጠፋ ለረዥም ዓመታት በመቆየቱ ሁኔታውን ያዕቆብ በእድሜው መጨረሻ እንኳ እንደ ትኩስ ድርጊት ሲያነሳው ይታያል፡፡ በዚህም ምክንያት ያዕቆብ ልክ እንደ ስምዖን ሌዊንም በምንም ነገር ሳይባርከው ተወው፡፡ አንዲያውም የተበተነ ሕዝብ እንዲሆን ተናግሮ የቆየ የልቡን መራራ ትዝታ ዘርግፎ አወጣው፡፡

በአንድ ሰው አለመታዘዝ እርግማን ለብዙ እንደሚተርፍ እንዲሁ በአንዱ መታዘዝ በረከት ለብዙዎች ይሆናል፡፡ በአንዱ አዳም ምክንያት ሞት ወደ ሰው ሁሉ እንደ መጣ በሁለተኛው አዳም በጌታ በኢየሱስ ክርስቶስ በኩል ደግሞ ሕይወት ለሰው ልጅ ሁሉ ሆነ (ሮሜ 5፥12-21)፡፡ ምንም እንኳ ሌዊ ከእርሱ ለወጣ ነገድ በሠራው በደል እርግማን ቢሆንም ከሌዊ ወገን በሆነ በሙሴ መታዘዝ እግዚአብሔር የሌዊን ወገን በምሕረት ተመለከተ፡፡ እርግማንን የሚሽር የበረከት ጉልበት
እግዚአብሔር በሙሴ ውስጥ አኖረ፡፡ በኋላም የሌዊ ነገድ ባጋጠማቸው መልካም አጋጣሚ ራሳቸውን ለእግዚአብሔር የለዩና የተቀደሱ ሆኑ፡፡

ሙሴ በእግዚአብሔር ትዕዛዝ ሕግንና ሥርዓትን ለመቀበል ወደ ኮሬብ ተራራ ወጥቶ በዘገየ ጊዜ የእስራኤል ልጆች ሁሉ ወደ አሮን ተሰብስበው ሙሴ በሄደበት ስለ ዘገየና ምን እንደ ሆነም ስለማናውቅ ከግብጽ ያወጣንን አምላክ ምሳሌ ሥራልን በማለት የወርቅ ጥጃን ሠርተው ለሠሩት ምስል መስገድና መሠዋት ጀመሩ፡፡ በዚህም ጊዜ ሙሴ በእግዚአብሔር ጣት የተጻፉትን የኪዳን ጽላቶች ይዞ ከተራራው ሲወርድ በእስራኤል ሰፈር ውስጥ እየተከናወነ ያለውን ሁኔታ በማየቱ ቁጣው ነደደ፡፡ ከእግዚአብሔርም የተቀበሳቸውን ጽላቶች ጥሎ ከተራራው በታች ሰበራቸው፡፡ በዚህም ቁጣው ውስጥ ሙሴ በሰፈሩ ደጅ ቆሞ የእግዚአብሔር ወገን የሆነ ወደ እኔ ይምጣ በማለት ድምጹን ለሕዝቡ አሰማ፡፡ ይህንንም እስቸኳይ ጥሪ ተቀብለው የሌዊ ልጆች ሁሉ ወደ እርሱ ተሰበሰቡ፡፡ ራሳቸውንም በሙሴ ፊት ለእግዚአብሔር ለዩ፡፡ የሰይፍ ሰዎችም ስለ ነበሩ የእግዚአብሔር ባሪያ ሙሴ እንዳዘዛቸው ሰይፋቸውን መዝዘው ለእግዚአብሔር ያልተገዛውን ሁሉ አጠፉ፡፡ የሌዊም ልጆች ሙሴ አንዳለ አደረጉ፡፡ የተነጠቁትን በረከት መልሰው ለማግኘት እጃቸውን ለእግዚአብሔር ቀደሱ። በዚያም ቀን ከሕዝቡ ሦስት ሺህ ሰዎች ሞቱ (ዘጸ. 32፥25-29)፡፡

በዚህም መታዘዛቸው ምክንያት የሌዊ ወገን ለእግዚአብሔር የተለዩ ሆኑ፡፡ ምንም እንኳ ያዕቆብ ያለ በረከት ምርቃት ቢተዋቸውም ወደ እግዚአብሔር አሳብ በመምጣታቸው ከጌታ ምሕረት ተካፋዮች፣ የእርሱንም በጎነት አዋጅ ነጋሪዎች፥ የጌታም መቅደስ አገልጋዮች ሊሆኑ ተመረጡ፡፡ ሙሴም ሊመርቃቸው እንዲህ በማለት ጀመረ (ዘዳ. 33፥8-11)::

1ኛ. ቱሚምህና ኡሪምህ ለቅዱሰህ ሰው ነው

ቱሚምና ኡሪም ሊቀ ካህኑ የክህነቱን ልብስ በለበስ ጊዜ በልብሱ ላይ ባለ የደረት ኪስ ውስጥ የሚቀመጡ፥ በእግዚእብሔርም ፊት ሊቀ ካህኑ የእስራኤልን ልጆች ፍርድ የመሸከሙ መግለጫ ምልኮቶች ናቸው (ዘጸ. 28፥29-30)፡፡ እነዚህ ቱሚምና ኡሪም በኤፉዱ የደረት ኪስ ውስጥ ዘወትር ይቀመጣሉ፡፡ በእነዚህም ቱሚምና ኡሪም የእግዚአብሔር ፈቃድ ይጠየቅ ነበር (ዘኁ. 27፥21፤ ዕዝ. 2፥63፤ 1ኛ ሳሙ. 23፥6-12)፡፡ ነገሥታት ወይም የእግዚአብሔርን ፈቃድ ለማወቅ የሚወዱ ሁሉ ቱሚምና ኡሪም ባሉበት ሊያደርጉ ያስቡትን ነገር እግዚአብሔር ያከናውንላቸው እንደሆን ይጠይቃሉ፡፡ በዚያም የእግዚእብሔርን ፈቃድ ይለያሉ፡፡



ይቀጥላል...



ምንጭ፦ አበራ ጌታሁን (ዶ/ር)፤ የያዕቆብ ልጆች እና በረከቶቻቸው፤ ገጽ 17-19



ወደ ቻናሉ ለመ🀄️🀄️ል፦ @Holy_scriptures
5👍5
'    ==❀❀❀===❀❀❀==      
              የዕለቱ ጥቅስ
     ==❀❀❀===❀❀❀==
“ከአፉም ሕጉን ተቀበል፥ በልብህም ቃሉን አኑር፤”
                      ኢዮብ 22፥22



ወደ ቻናሉ ለመ🀄️🀄️ል፦ @Holy_scriptures
5👍2
ነቢዩ ኤርምያስ



ክፍል-፩


ኤርምያስ ካህንና የኬልቅያስ ቤተ ሰው ወገን ነበር፤ የትውልድ አገሩ አናቶት ሲሆን (1፥1)፣ በንጉሥ ሰሎሞን ጊዜ ካህን የነበረው የአብያታር ወገን ሳይሆን አይቀርም (1ነገ 2፥26)፡፡ በይሁዳ ያለው ቀጣይ ትውልድ በእግዚአብሔር መለኮታዊ ፍርድ ተጠራርጎ የሚጠፋበት ጊዜ ሩቅ ስላልነበረ፣ እግዚ አብሔር ኤርምያስን ሚስት እንዳያገባና ልጆችን ወልዶ እንዳያሳድግ አዘዘው (16፥14)። ኤርምያስ ገና ከመጀመሪያው የሚናገረው የትንቢት ቃል ፍርድንና ጥፋትን ያዘለ ነበር፤ ያፈራቸውም ወዳጆች እጅግ ጥቂት ሲሆኑ፣ ከእነርሱም መካከል አኪቃም (26፥24)፣ የአኪቃም ልጅ ጎዶልያስና (39፥14) ኢትዮጵ ያዊው አቤሜሌክ (38፥7-13፤ ከ39፥15-18) ይገኙበታል፡፡

የኤርምያስ የቅርብ ጓደኛና ታማኝ ጸሓፊው የነበረው ባሮክ ሲሆን፣ እርሱም ነቢዩ ኤርምያስ በቃሉ የተናገረውን የእግዚአብሔር ቃል በቀጥታ ይጽፍ ነበር(36፥4-32)፡፡ ባሮክ ምድራዊን ነገር ለማግኘት ያለውን ምኞት ገትቶ፣ እግዚአብሔር ዕድል ፈንታ አድርጎ በሰጠው ነገር ብቻ እንዲረካ ነቢዩ ኤርምያስ መክሮታል (ምዕራፍ 45)፡፡ ባሮክ የግዢ ውል የተፈጸመበትን ሠነድ ከኤርምያስ ተቀብሎ በሸክላ ዕቃ ውስጥ በጥንቃቄ እንዲቀመጥ አደረገ (32፥11- 16)፤ በኋላም ነቢዩ ተሰዶ ወደ ሄደበት ወደ ግብፅ አብሮት በመሰደድ ረጅም መንገድ ከእርሱ ጋር ተጓዘ (43፥6-7)፡፡ ከምዕራፍ 1-51 ከተጠቀሱት ድርጊቶች ውስጥ በ580 ዓመተ ቅድመ ክርሰቶስ በኋላ የተፈጸመ ነገር ስለ ሌለ፣ የነቢዩ ኤርምያስን መጽሐፍ አጠቃሎ የጻፈውና ያዘጋጀው ያለ ጥርጥር ራሱ ባሮክ ነው (ምዕራፍ 52 በሌላ ሰው እጅ ተጽፎ የገባ ተጨማሪ ታሪክ ነው)፡፡

ኤርምያስ ለምርመራና ለግል ሂስ ራሱን ግልጥ በማድረጉ ባሕርዩና ማንነቱ ምን እንደ ሚመስል በሚገባ አሳይቶአል (10፥24)፡፡ በተፈጥሮው ፈሪ ቢሆንም (1፥6)፣ እግዚአብሔር ብርቱና ደፋር እንደ ሚያደርገው አረጋግጦለታል (1፥18፤ 6፥27፤ 15፥20)፡፡ በተናገራቸው የንስሐ ቃሎች ውስጥ (11፥18-23፤ 12፥1-4፣ 15፥10-21፤ 17፥12-18፣ 18፥18-23፣ 20፥7-18)ግልጽ በሆነ ሁኔታ ስሜቱን ለእግዚአብሔር በመንገር፣ ጥልቅ የሆነውን ውስጣዊ ትግል ገልጦአል (12፥1:15፥18)፡፡ ለወገኖቹም እጅግ የማለደ ቢሆንም አንዳንድ ጊዜ ደግሞ በግል ጠላቶቹ ላይ በቀልን የሚጋብዝ የርግማንና የውግዘት ቃልን ተጠ ቅሞአል (12፥1-3፤ 15፥15፤ 17፥18፤ 18፥19-23)። ኤርምያስ አብዛኛውን ጊዜ መንፈሱ በሐዘን የተሰበረ ስለ ነበር (4፥19፤ 9፥1፤ 10፥19-20፤ 23፥9)፣ “#አልቃሻው_ነቢይ” በመባል ይታወቃል፡፡ ይሁን እንጂ ከእግዚአብሔር የተቀበለውን መለኮታዊ ጥሪ በማሰቡና (1፥17) እግዚአብሔርም በተደጋጋሚ ነቢይ አድርጎ እንደ ላከው ስላረጋገጠለት (3፥12፤ 7፥2: 27-28፤ 11፥26፤ 13፥12-13፤ 17፥19-20) በእግዚአ ብሔር አገልግሎት ውስጥ ፈሪ እንዳይሆን አድርጎታል (ከ15፥20)፡፡

ኤርምያስ ከማንኛውም የብሉይ ኪዳን ነቢይ ይልቅ ከብዙ ጠላቶች አያሌ ተቃውሞ ገጥሞታል:: ብዙው ተቃውሞ የመጣው አዘውትሮ አንድ ዐይነተኛ ነገርን በመስበኩ የተነሣ ነው፤ ይኸውም ድርድር የሌለበት ዐልፎ መሰጠት ነው፡፡ እግዚአብሔር ባይጠብቀው ኖሮ ኤርምያስ ሰማዕት ይሆን ነበር፡፡



ይቀጥላል...


ምንጭ፦ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ከማጥኛ ጽሑፍ ጋር፤ ገጽ 1107፣ የብሉይ ኪዳን ማብራሪያ፤ ገጽ 823




ወደ ቻናሉ ለመ🀄️🀄️ል፦ @Holy_scriptures
👍7🔥21
'    ==❀❀❀===❀❀❀==      
              የዕለቱ ጥቅስ
     ==❀❀❀===❀❀❀==
“አባታችሁንም አብርሃምን ከወንዝ ማዶ ወስጄ በከነዓን ምድር ሁሉ መራሁት፤ ዘሩንም አበዛሁ፥ ይስሐቅንም ሰጠሁት።”
                      ኢያሱ 24፥3




ወደ ቻናሉ ለመ🀄️🀄️ል፦ @Holy_scriptures
👍81
ወደ ቻናሉ ለመ🀄️🀄️ል፦ @Holy_scriptures
3👍1
እምነት እና አመክንዮ.pdf
2.5 MB
👉ርዕስ፦ እምነትና አመክንዮ-የተጣመሩ ወይስ የተፋቱ? (Faith and Reason)

እያመንን እናስብ፣ እያሰብን እንመን

ጸሐፊ፦ ምሕረቱ ጴ. ጉታ

📑የገጽ ብዛት፦ 128



ወደ ቻናሉ ለመ🀄️🀄️ል፦ @Holy_scriptures
👍3
'    ==❀❀❀===❀❀❀==      
              የዕለቱ ጥቅስ
     ==❀❀❀===❀❀❀==
“የራሱንም ሁሉ ካወጣቸው በኋላ በፊታቸው ይሄዳል፥ በጎቹም ድምፁን ያውቃሉና ይከተሉታል፤”
                 ዮሐንስ 10፥4



ወደ ቻናሉ ለመ🀄️🀄️ል፦ @Holy_scriptures
👍86
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
5