ቅዱሳት መጻሕፍት
7.46K subscribers
1.36K photos
61 videos
332 files
806 links
በዚህ ቻናል

👉ቅዱሳት መጻሕፍት ይጠናሉ::
👉መጽሐፍ ቅዱሳዊ ትምህርቶች ይቀርባሉ::
👉 ለቅዱሳት መጽሐፍት ጥናት የሚያግዙ መጻሕፍት ይለቀቃሉ።

⭐️⭐️⭐️⭐️⭐️

@Holy_scriptures
Download Telegram
'    ==❀❀❀===❀❀❀==      
              የዕለቱ ጥቅስ
     ==❀❀❀===❀❀❀==
“አምላካችን ሆይ፥ አንተ አትፈርድባቸውምን? ይህን የመጣብንን ታላቅ ወገን እንቃወም ዘንድ አንችልም፤ የምናደርገውንም አናውቅም፤ ነገር ግን ዓይኖቻችን ወደ አንተ ናቸው።”
                       2 ዜና 20፥12




ወደ ቻናሉ ለመ🀄️🀄️ል፦ @Holy_scriptures
👍41
#የእግዚአብሔር_ቃል_ምን_ይላል?


መዝሙር 105
¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯
¹ እግዚአብሔርን አመስግኑ ስሙንም ጥሩ፥ ለአሕዛብም ሥራውን አውሩ።
² ተቀኙለት፥ ዘምሩለት፥ ተአምራቱንም ሁሉ ተናገሩ።
³ በቅዱስ ስሙ ተጓደዱ፤ እግዚአብሔርን የሚፈልግ ልብ ደስ ይበለው።
⁴ እግዚአብሔርን ፈልጉት ትጸናላችሁም፤ ሁልጊዜ ፊቱን ፈልጉ።
⁵-⁶ ባሪያዎቹ የአብርሃም ዘር፥ ለእርሱም የተመረጣችሁ የያዕቆብ ልጆች ሆይ፥ የሠራትን ድንቅ አስቡ፥ ተአምራቱን የአፉንም ፍርድ።
⁷ እርሱ እግዚአብሔር አምላካችን ነው፤ ፍርዱ በምድር ሁሉ ነው።
⁸ ቃል ኪዳኑን ለዘላለም፥ እስከ ሺህ ትውልድ ያዘዘውን ቃሉን አሰበ፥
⁹ ለአብርሃም ያደረገውን፥ ለይስሐቅም የማለውን፤
¹⁰ ለያዕቆብ ሥርዓት እንዲሆን ለእስራኤልም የዘላለም ኪዳን እንዲሆን አጸና፤
¹¹ እንዲህም አለ፦ ለአንተ የከነዓንን ምድር የርስታችሁን ገመድ እሰጣለሁ፤
¹² ይህም የሆነው እነርሱ በቍጥር ጥቂቶች ሰዎች፥ እጅግ ጥቂቶችና ስደተኞች ሲሆኑ ነው።
¹³ ከሕዝብ ወደ ሕዝብ፥ ከመንግሥታትም ወደ ሌላ ሕዝብ አለፉ።
¹⁴-¹⁵ የቀባኋቸውን አትዳስሱ፥ በነቢያቴም ክፉ አታድርጉ ብሎ፥ ሰው ግፍ ያደርግባቸው ዘንድ አልፈቀደም፥ ስለ እነርሱም ነገሥታትን ገሠጸ።
¹⁶ በምድር ላይ ራብን ጠራ፥ የእህልን ኃይል ሁሉ ሰበረ።
¹⁷ በፊታቸው ሰውን ላከ ዮሴፍ ለባርነት ተሸጠ።
¹⁸ እግሮቹም በእግር ብረት ደከሙ፥ እርሱም በብረት ውስጥ ገባ።
¹⁹ ቃሉ እስኪመጣለት ድረስ፥ የእግዚአብሔር ቃል ፈተነው።
²⁰ ንጉሥ ላከ ፈታውም፥ የአሕዛብም አለቃ አስፈታው።
²¹ የቤቱ ጌታ፥ የጥሪቱ ሁሉ ገዢ አደረገው፥
²² አለቆቹን እንደ ፈቃዱ ይገሥጽ ዘንድ፥ ሽማግሌዎቹንም ጥበበኞች ያደርጋቸው ዘንድ።
²³ እስራኤልም ወደ ግብጽ ገባ፥ ያዕቆብም በካም አገር ተቀመጠ።
²⁴ ሕዝቡንም እጅግ አበዛ፥ ከጠላቶቻቸውም ይልቅ አበረታቸው።
²⁵ ሕዝቡን ይጠሉ ዘንድ በባሪያዎቹም ላይ ይተነኰሉ ዘንድ ልባቸውን ለወጠ።
²⁶ ባሪያውን ሙሴን የመረጠውንም አሮንን ላከ።
²⁷ የተኣምራቱን ነገር በላያቸው ድንቁንም በካም አገር አደረገ።
²⁸ ጨለማን ላከ ጨለመባቸውም፤ በቃሉም ዐመፁ።
²⁹ ውኃቸውን ወደ ደም ለወጠ፥ ዓሦቻቸውንም ገደለ።
³⁰ ምድራቸው የንጉሦቻቸውም ቤቶች በጓጕንቸር ሞሉ።
³¹ ተናገረ፥ የውሻ ዝንብ ትንኝም በዳርቻቸው መጡ።
³² ዝናባቸውን በረዶ አደረገው፥ እሳትም በምድራቸው ተቃጠለች።
³³ ወይናቸውንና በለሳቸውን መታ፥ የአገራቸውንም ዛፍ ሁሉ ሰበረ።
³⁴ ተናገረ፥ አንበጣም ስፍር ቍጥር የሌለውም ኩብኩባ መጣ፥
³⁵ የአገራቸውንም ለምለም ሁሉ በላ፥ የምድራቸውንም ፍሬ በላ።
³⁶ የአገራቸውንም በኵር ሁሉ፥ የጕልበታቸውን መጀመሪያ ሁሉ መታ።
³⁷ ከወርቅና ከብርም ጋር አወጣቸው፥ በወገናቸውም ውስጥ ደዌ አልነበረም።
³⁸ ፈርተዋቸው ነበርና ግብጽ በመውጣታቸው ደስ አላት።
³⁹ ደመናን ለመሸፈኛ ዘረጋባቸው፥ እሳትንም በሌሊት ያበራላቸው ዘንድ ዘረጋ።
⁴⁰ ለመኑ፥ ድርጭትንም አመጣላቸው፥ የሰማይንም እንጀራ አጠገባቸው።
⁴¹ ዓለቱን ሰነጠቀ፥ ውኃውም ፈሰሰ፤ ወንዞች በበረሃ ሄዱ፤
⁴² ለባሪያው ለአብርሃም የነገረውን ቅዱስ ቃሉን አስቦአልና።
⁴³ ሕዝቡንም በደስታ የተመረጡትንም በእልልታ አወጣ።
⁴⁴ የአሕዛብንም አገሮች ሰጣቸው፥ የወገኖችንም ድካም ወረሱ፥
⁴⁵ ሕጉን ይጠብቁ ዘንድ፥ ሥርዓቱንም ይፈልጉ ዘንድ። ሃሌ ሉያ





ወደ ቻናሉ ለመ🀄️🀄️ል፦ @Holy_scriptures
👍10
'    ==❀❀❀===❀❀❀==      
              የዕለቱ ጥቅስ
     ==❀❀❀===❀❀❀==
“እንግዲህ ምድሪቱን ስለምሰጥህ ተነሣ፤ በርዝመቷም፣ በስፋቷም ተመላለስባት።””
       ዘፍጥረት 13፥17 (አዲሱ መ.ት)



ወደ ቻናሉ ለመ🀄️🀄️ል፦ @Holy_scriptures
👍4
ወደ ቻናሉ ለመ🀄️🀄️ል፦ @Holy_scriptures
👍7
የዘላለም ኪዳን.pdf
3.7 MB
👉 ርዕስ፦ የዘላለም ኪዳን
ጸሐፊ፦ ዎችማን ኒ
🗣 ተርጓሚ፦ ጳውሎስ ፈቃዱ
📑 የገጽ ብዛት፦ 140



ወደ ቻናሉ ለመ🀄️🀄️ል፦ @Holy_scriptures
👍9
'    ==❀❀❀===❀❀❀==      
              የዕለቱ ጥቅስ
     ==❀❀❀===❀❀❀==
“በዙፋኑ መካከል ያለው በጉ እረኛቸው ይሆናልና፥ ወደ ሕይወትም ውኃ ምንጭ ይመራቸዋልና፤ እግዚአብሔርም እንባዎችን ሁሉ ከዓይናቸው ያብሳል።”
               ራእይ 7፥17



ወደ ቻናሉ ለመ🀄️🀄️ል፦ @Holy_scriptures
9👍2
😢8👍6
'    ==❀❀❀===❀❀❀==      
              የዕለቱ ጥቅስ
     ==❀❀❀===❀❀❀==
“አቤቱ፥ ነፍሴን ከሲኦል አወጣሃት፥ ወደ ጕድጓድም እንዳልወርድ አዳንኸኝ።”
                    መዝሙር 30፥3



ወደ ቻናሉ ለመ🀄️🀄️ል፦ @Holy_scriptures
10
#እራሳችንን_እንመርምር

ሰዎች እንደ እኛ እንዲሆኑ እንፈልጋለን? ከምናችን በስተቀር? ወይስ ሙሉ በሙሉ ከነአካቴው እኛኑ እንዲሆኑ እንፈልጋለን? "ኧረ ወዲያ እኔ እራሴ ምን አለ ሌላ ሰው በሆንኩ" እያልን እንገኛለን? ለምን?

“ጳውሎስም፦ በጥቂት ቢሆን ወይም በብዙ አንተ ብቻ አይደለህም ነገር ግን ዛሬ የሚሰሙኝ ሁሉ ደግሞ ከዚህ እስራቴ በቀር እንደ እኔ ይሆኑ ዘንድ ወደ እግዚአብሔር እለምናለሁ አለው።”
ሐዋርያት 26፥29


ወደ ቻናሉ ለመ🀄️🀄️ል፦ @Holy_scriptures
👍6👏1
'    ==❀❀❀===❀❀❀==      
              የዕለቱ ጥቅስ
     ==❀❀❀===❀❀❀==
“ከያዕቆብም ቤት ፊቱን የመለሰውን እግዚአብሔርን እጠብቃለሁ፥ እተማመንበትማለሁ።”
               ኢሳይያስ 8፥17



ወደ ቻናሉ ለመ🀄️🀄️ል፦ @Holy_scriptures
8
ከቅዱሳት መጻሕፍት መካከል መጀመሪያ እና መጨረሻ እንደተጻፈ የሚገመተው የቱ ነው?
Anonymous Quiz
57%
ሀ. ዘፍጥረት እና የዮሐንስ ራእይ
36%
ለ. ኢዮብ እና ራእይ
4%
ሐ. መሳፍንት እና ራእይ
4%
መ. መዝሙረ ዳዊት እና ራእይ
2
ሰሞኑ በቻናላችን በለጠፍነው ጥያቄ ላይ ብዙዎቻችሁ ግራ ተጋብታችኋል። ጥያቄም ጠይቃችኋል። በነገራችን ላይ ብዙ ሰው ተሳትፎ ግር መሰኙቱን በስፋት ስለገለጸልን ምን ያህል ለጥያቄዎቻችን ትኩረት እንደሰጣችሁ አይተናል። ደስ ብሎናል እናመሰግናለን!🙏 ከዚህ በታች በመጽሐፍ ቅዱሳችን ውስጥ ረጃጅም መጻሕፍትን ከነቃላት ብዛታቸው (ማለትም በተጻፉበት ቋንቋ) እነሆ፦

1. ኤርምያስ (33,002 ቃላት)
2. ኦሪት ዘፍጥረት (32,046 ቃላት)
3. መዝሙረ ዳዊት (30,147 ቃላት)
4. ሕዝቅኤል (29,918 ቃላት)
5. ዘጸአት (25, 957 ቃላት)
6. ኢሳይያስ (25,608 ቃላት)
7. ኦሪት ዘኁልቁ (25,048 ቃላት)
8. ኦሪት ዘዳግም (23,008 ቃላት)
9. ሁለተኛ ዜና መዋዕል (21,349 ቃላት)
10. አንደኛ ሳሙኤል (20,361 ቃላት)


ከዚህ ጋር በተያያዘ ጥሩ ቅዱሳት መጻሕፍትን መሠረት ያደረገ ፕሮግራም ያለው ሰው ሊያናግረን ይችላል። በተረፈ ያቋረጥነውን የሮሜ መልእክት ጥናታችንን በቅርቡ እንቀጥላለን።


ወደ ቻናሉ ለመ🀄️🀄️ል፦ @Holy_scriptures
👍112
'    ==❀❀❀===❀❀❀==      
              የዕለቱ ጥቅስ
     ==❀❀❀===❀❀❀==
“በውኑ በአሕዛብ ጣዖታት መካከል ያዘንብ ዘንድ የሚችል ይገኛልን? ወይስ ሰማይ ዝናብ ማፍሰስ ይችላልን? አቤቱ አምላካችን ሆይ፥ አንተ አይደለህምን? አንተ ይህን ነገር ሁሉ አድርገሃልና ስለዚህ አንተን በተስፋ እንጠባበቃለን።”
                  ኤርምያስ 14፥22




ወደ ቻናሉ ለመ🀄️🀄️ል፦ @Holy_scriptures
👍2
ነቢዩ ኤርምያስ



#ኤርምያስ በመጽሐፍ ቅዱሳችን ውስጥ ረጅሙን መጽሐፍ የጻፈ ነቢይ ነው። ለመሆኑ ነቢዩ ኤርምያስ ማን ነው? በአብዛኛው አማኝ ዘንድ የብሉይ ኪዳን ነቢይ ማለትም ትንቢታቸው ወጥ በሆነ መጽሐፍ ከተሰደሩ ሲባል አእምሮው ላይ የሚመጣው እና የሚወደደው ነቢይ፣ ነቢዩ ኢሳይያስ ነው። ነገር ግን በእስራኤላዊያን ዘንድ ነቢዩ ኤርምያስ ነው። "አልቃሻው ነቢይ" በመባልም ይታወቃል። በእስራኤላውያን ዘንድ ተወዳጅ እንደሆነ ማሳያው ጌታችን እና መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ "ሰዎች የሰውን ልጅ ማን እንደ ሆነ ይሉታል?” (ማቴ. 16፥13) ብሎ ሲጠይቅ ከደቀ መዛሙርቱ ካገኘው አንዱ ምላሽ ኤርምያስ የሚል ነበር። ታዲያ ነቢዩ ኤርምያስ ማን ነው?

ኤርምያስ፤ ትርጕሙ «እግዚአብሔር ከፍ ያደርጋል» ማለት ነው። ከእስራኤል ታላላቅ ነቢያት አንዱ። በኢየሩሳሌም አቅራቢያ ካለው ከተማ ከዓናቶት፥ ከካህናትም ወገን ነበረ። አባቱ በኢዮስያስ ዘመን የሕጉን መጽሐፍ ያገኘው ኬልቅያስ መሆኑን ብዙ ሊቃውንት ያምናሉ። ለእስራኤል ብቻ ሳይሆን ለአሕዛብም ጭምር ነቢይ እንዲሆን በተጠራ ጊዜ ደነገጠ፤ «ብላቴና ነኝ» በማለት አመነታ። በኋላ ግን በተሰጠው ተስፋ መሠረት በረታ። የተጠራውም 626 ከክርስቶስ ልደት በፊት፥ የይሁዳ ንጉሥ ኢዮስያስ በነገሠ በ13ኛው ዓመት ነበር። በኢዮስያስም ልጆች ዘመን ትንቢት እየተናገረ ቆይቶ፥ ከተጠራ ከ40 ዓመት በኋላ የኢየሩሳሌምን መማረክ አየ፤ ኤር. 1፡1-10። በዚህም ዘመን አምስት ነገሥታት ነገሡ።

መጽሐፉ የተጻፈው ከሚከተሉት ዐላማ የተነሣ ነው፣

(1) የኤርምያስን ነቢያዊ አገልግሎትና መልእክት በዘላቂነት በሰነድነት ለመያዝ፤

(2) ሕዝቡ ኪዳን ሲተላለፉና በእግዚአብሔርና በቃሉ ላይ በዐመፀኝነት ሲቀጥሉ የእግዚአብሔርን የማይቀርንና የማያመልጡት ፍርድ ለማሳየት፣

(3) ነቢያዊ ቃሉ የቱን ያህል ሐቅና የቱን ያህልስ ሥልጣን እንዳለው ለማሳየት፡፡ ብዙዎቹ የኤርምያስ ተንቢቶች በሕይወት ዘመኑ ተፈጽመዋል (ለምሳሌ 16፥9፤ 20፥4፤ 25፥1-14፣ 27፥19-22፤ 28፥15-17፤ 32፥10-13፡ 34፥1-5)፤ በረጅም ዘመን ውስጥ የሚፈጸሙት ሌሎቹ ትንቢቶቹ ከጊዜ በኋላ ተፈጽመዋል፤ ወይም ገና ወደ ፊት ይፈጸማሉ (ለምሳሌ 23፥5-6፣ 30፥8-9፣ 31፥31-34፤ 33፥14-16)፡፡


ይቀጥል የሚል አስተያየት ከበዛ በስፋት ስለነቢዩ እና አገልግሎቱ እንመለስበታለን። በተለይም ልዩ ባህሪያቶቹ፣ ስለምርኮው፣ ስለደረሰበት መከራ፣ ተቃውሞ፣ አሟሟቱ. . . ወ.ዘ.ተ


ምንጭ፦ የመጽሐፍ ቅዱስ መዝገበ ቃላት፤ ገጽ 174፣ ምሉእ ሕይወት፤ ገጽ 1099-1100


ወደ ቻናሉ ለመ🀄️🀄️ል፦ @Holy_scriptures
👍18👏2😁21
'    ==❀❀❀===❀❀❀==      
              የዕለቱ ጥቅስ
     ==❀❀❀===❀❀❀==
“እግዚአብሔርም ራሔልን አሰበ፥ እግዚአብሔርም ተለመናት፥ ማኅፀንዋንም ከፈተላት፤”
                ዘፍጥረት 30፥22




ወደ ቻናሉ ለመ🀄️🀄️ል፦ @Holy_scriptures
9👍1
#የእግዚአብሔር_ቃል_ምን_ይላል?



ኤርምያስ 20
¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯
¹ በእግዚአብሔርም ቤት የተሾመው አለቃ የካህኑ የኢሜር ልጅ ጳስኮር ኤርምያስ በዚህ ነገር ትንቢት ሲናገር ሰማ።
² ጳስኮርም ነቢዩን ኤርምያስን መታው፥ በእግዚአብሔርም ቤት በነበረው በላይኛው በብንያም በር ባለው በእግር ግንድ ውስጥ አኖረው።
³ በነጋውም ጳስኮር ኤርምያስን ከግንድ ውስጥ አወጣው። ኤርምያስም እንዲህ አለው፦ እግዚአብሔር ስምህን፦ ማጎርሚሳቢብ እንጂ ጳስኮር ብሎ አይጠራህም።
⁴ እግዚአብሔር እንዲህ ይላልና፦ እነሆ፥ ለራስህና ለወዳጆችህ ሁሉ ፍርሃት አደርግሃለሁ፤ እነርሱም በጠላቶቻቸው ሰይፍ ይወድቃሉ ዓይኖችህም ያያሉ፤ ይሁዳንም ሁሉ በባቢሎን ንጉሥ እጅ አሳልፌ እሰጣለሁ፥ እርሱም ወደ ባቢሎን ያፈልሳቸዋል በሰይፍም ይገድላቸዋል።
⁵ የዚህችንም ከተማ ባለጠግነት ሁሉ ጥሪትዋንም ሁሉ ክብርዋንም ሁሉ የይሁዳንም ነገሥታት መዝገብ ሁሉ በጠላቶቻቸው እጅ አሳልፌ እሰጣለሁ፥ እነርሱም ይበዘብዙአቸዋል ይዘውም ወደ ባቢሎን ያፈልሱአቸዋል።
⁶ አንተም፥ ጳስኮር ሆይ፥ በቤትህም የሚኖሩት ሁሉ ተማርካችሁ ትሄዳላችሁ፤ አንተም በሐሰትም ትንቢት የተናገርህላቸው ወዳጆችህ ሁሉ ወደ ባቢሎን ትገባላችሁ፥ በዚያም ትሞታላችሁ፥ በዚያም ትቀበራላችሁ።
⁷ አቤቱ፥ አታለልኸኝ እኔም ተታለልሁ፥ ከእኔም በረታህ አሸነፍህም፤ ቀኑን ሁሉ መሳቂያ ሆኛለሁ፥ ሁሉም ያላግጡብኛል።
⁸ በተናገርሁ ቍጥር እጮኻለሁ፤ ግፍና ጥፋት ብዬ እጮኻለሁ፤ የእግዚአብሔር ቃል ቀኑን ሁሉ ስድብና ዋዛ ሆኖብኛልና።
⁹ እኔም፦ የእግዚአብሔርን ስም አላነሣም፥ ከእንግዲህ ወዲህም በስሙ አልናገርም ብል፥ በአጥንቶቼ ውስጥ እንደ ገባ እንደሚነድድ እሳት ያለ በልቤ ሆነብኝ፤ ደከምሁ፥ መሸከምም አልቻልሁም።
¹⁰ የብዙ ሰዎችን ስድብ ሰምቻለሁ፥ ማስፈራራትም ከብቦኛል። መውደቄን የሚጠብቁ የሰላሜ ሰዎች ሁሉ፦ ምናልባት ይታለል እንደ ሆነ፥ እናሸንፈውም እንደ ሆነ፥ እርሱንም እንበቀል እንደ ሆነ፥ ክሰሱት እኛም እንከስሰዋለን ይላሉ።
¹¹ እግዚአብሔር ግን እንደ ኃያልና እንደ ጨካኝ ከእኔ ጋር ነው፤ ስለዚህ አሳዳጆቼ ይሰናከላሉ አያሸንፉም፤ አይከናወንላቸውምና በጽኑ እፍረት ያፍራሉ፥ ለዘላለምም በማይረሳ ጕስቍልና ይጐሰቍላሉ።
¹² አቤቱ፥ ጻድቅን የምትመረምር ኵላሊትንና ልብን የምትመለከት የሠራዊት ጌታ ሆይ፥ ክርክሬን ገልጬልሃለሁና በቀልህን በላያቸው ለይ።
¹³ ለእግዚአብሔር ዘምሩ እግዚአብሔርንም አመስግኑ፤ የችግረኛውን ነፍስ ከክፉ አድራጊዎች እጅ አድኖአልና።
¹⁴ የተወለድሁባት ቀን የተረገመች ትሁን፤ እናቴ እኔን የወለደችባት ቀን የተባረከች አትሁን።
¹⁵ ወንድ ልጅ ተወልዶልሃል ብሎ ለአባቴ የምሥራች ነግሮ ደስ ያሰኘው ሰው የተረገመ ይሁን።
¹⁶ ያም ሰው እግዚአብሔር ሳይጸጸት እንደ ገለበጣቸው ከተሞች ይሁን፥ በማለዳም ልቅሶን በቀትርም ጩኸትን ይስማ፤
¹⁷ እናቴ መቃብር ትሆነኝ ዘንድ ማኅፀንዋም ዘወትር ይዞኝ ያቆይ ዘንድ በማኅፀን ውስጥ አልገደለኝምና።
¹⁸ ድካምንና ጣርን አይ ዘንድ ዘመኔም በእፍረት ታልቅ ዘንድ ስለ ምን ከማኅፀን ወጣሁ?





ወደ ቻናሉ ለመ🀄️🀄️ል፦ @Holy_scriptures
👍2
'    ==❀❀❀===❀❀❀==      
              የዕለቱ ጥቅስ
     ==❀❀❀===❀❀❀==
“እርሱ ግን እባቢቱን ወደ እሳት አራገፋት አንዳችም አልጐዳችውም፤”
                  ሐዋርያት 28፥5



ወደ ቻናሉ ለመ🀄️🀄️ል፦ @Holy_scriptures
👍4
ቅዱሳት መጻሕፍት
#የሮሜ_መልእክት_ጥናት የእግዚአብሔር ፍትሕ (9:19-29) የእግዚአብሔር ሉዓላዊነት ሌላ ችግር የሚፈጥር ይመስላል፡፡ «እግዚአብሔር ሉዓላዊ ከሆነ፣ ማን ሊቋቋመው ይችላል? የሚቋቋመው ካለ ደግሞ እንዴት ሊዳኝ ይችላል?» ይህ እግዚአብሔር በሰው ዘር ታሪክ ውስጥ ስለ ፍትሐዊ አሠራሩ የሚጠየቅ የቆየ ጥያቄ ነው፡፡ በቺካጐ ጎዳና በራሪ መንፈሳዊ ወረቀቶችን ስበትን የሆነውን አስታውሳለሁ። አብዛኛዎቹ…
#የሮሜ_መልእክት_ጥናት



የእግዚአብሔር ፍትሕ (9:19-29)



ሐ) ይህ ሁሉ በትንቢት ተነግሯል (9:25-29)

በመጀመሪያ ጳውሎስ ሆሴዕ 2:23ን ጠቅሶ፣ እግዚአብሔር አይሁድን ትቶ አሕዛብን እንደሚጠራ ያውጃል፡፡ ቀጥሎ ሆሴዕ 1፡10ን አጣቅሶ፣ እነዚህ አዲስ ሕዝቦች የእግዚአብሔር ሕዝብ እና «የሕያው እግዚአብሔር ልጆች›› ተብለው እንደሚጠሩ ያረጋግጣል:: ኢሳይያስ 10:22-23ን ጠቅሶ፣ አብዛኛው እስራኤላዊ ፍርድን እንደሚቀበል ቅሬታዎቹ ግን እንደሚድኑ ያሳያል፡፡ ቁጥር 28 ምናልባትም የሚናገረው እግዚአብሔር በእስራኤል ላይ ስደትንና ፍርድን ስለሚፈጸምበት ስለ መከራው ዘመን ይመስላል፡፡ ቅሬታዎች ብቻ ናቸው ኢየሱስ ክርስቶስ ወደ ምድር ሲመለስ ወደ መንግሥቱ የሚገቡት፡፡ ነገር ግን ዛሬ ከዚህ የምንማረው ነገር ግልጽ ነው፡፡ የሚያምኑት በጣም ጥቂት አይሁድ ብቻ ሲሆኑ፣ እነርሱም ከአሕዛብ ጋር «በእግዚአብሔር የተጠሩ» (ቁ. 24) ይባላሉ፡፡

የመጨረሻው ጥቅስ ከኢሳይያስ 1፡9 የሚያወሳ ሲሆን፣ አጽንኦት የሚሰጠው የሚያምኑትን ቅሬታዎች በሚያድነው እግዚአብሔር ጸጋ ላይ ነው፡፡
አሁን ታዲያ፣ ይህ ሁሉ የሚያስረግጠው ምንድን ነው? እግዚአብሔር አንዳንዶቹን አድኖ በሌሎቹ ላይ መፍረዱ ዐመፀኛ አያደርገውም፤ በብሉይ ኪዳን ከዘመናት በፊት የተነገሩትን ትንቢቶች ወደ ፍጻሜ እያመጣ ነውና፡፡ ቃሉን ባይጠብቅ ኖሮ ዐመፀኛ ይሆን ነበር፡፡ እነዚህ ትንቢቶች እንደሚያሳዩት የእግዚአብሔር ምርጫ አሕዛብ እንዲድኑ አስችሎአቸዋል፡፡ ይህ የእግዚአብሔር ጸጋ ነው፡፡ ከግብጽ ባርነት ነፃ በወጡበት ጊዜ እግዚአብሔር አሕዛብን ትቶ አይሁድን የመረጠው፣ በአይሁድ በኩል አሕዛብን ለማዳን ነው፡፡ የእስራኤል ሕዝብ ፈቃዱን ተቃወሙ፣ ይህ ግን ዓላማውን እንዲያጥፍ አላደረገም:: የአይሁድ ቅሬታዎች አመኑ፣ የእግዚአብሔም ቃል ተፈጸመ፡፡
እስካሁን፣ ጳውሎስ የእግዚአብሔርን ታማኝነት፣ ጽድቅና ፍትሐዊነት በማሳየት የእግዚአብሔርን ባሕርይ ትክክለኝነቱን እንደሚገልጽ እያስረዳ ነው፡፡ እስራኤላውያን ባይቀበሉም፣ የእግዚአብሔርን ምርጫ ሊገቱት አልቻሉም፡፡ ነገር ግን እርሱ ለባሕርይውና ለዓላማው እውነተኛ መሆኑን አረጋገጠ እንጂ፡፡


ይቀጥላል. . .


ምንጭ፦ ዋረን ደብልዩ ዌርዝ ቢ፤ ተስማማ፤ ገጽ 100-101




ወደ ቻናሉ ለመ🀄️🀄️ል፦ @Holy_scriptures
4👍1
'    ==❀❀❀===❀❀❀==      
              የዕለቱ ጥቅስ
     ==❀❀❀===❀❀❀==
“ዓለም እናንተን ሊጠላ አይቻለውም፤ እኔ ግን ሥራው ክፉ መሆኑን እመሰክርበታለሁና እኔን ይጠላኛል።”
                     ዮሐንስ 7፥7




ወደ ቻናሉ ለመ🀄️🀄️ል፦ @Holy_scriptures
👍51