' ==❀❀❀===❀❀❀==
የዕለቱ ጥቅስ
==❀❀❀===❀❀❀==
“የሰነፍ መንገድ በዓይኑ የቀናች ናት፤ ጠቢብ ግን ምክርን ይሰማል።”
ምሳሌ 12፥15
ወደ ቻናሉ ለመ🀄️ላ🀄️ል፦ @Holy_scriptures

👍3
መጽሐፍ ቅዱስ ምን ዓይነት መጽሐፍ ነው?
ምዕራፍ ፩
ክፍል-4
ወንጌላውያን አብያተ ክርስቲያናት እና የግሪክ ኦርቶዶክስን የመሳሰሉት አብያተ ክርስቲያናት እነዚህን መጽሐፍት እንደ ቃለ እግዚአብሔር የማይቀበሉበት ሌላው ምክንያት ደግሞ እነዚህ መጻሕፍት በአይሁድ ቀኖና ውስጥ የማይገኙ መሆናቸው ነው፡፡ በ90 ዓ.ም. ዮሐናን ቤን ዛካይ በተባለ ረቢ መሪነት በጃምኒያ በተደረገ የአይሁድ ሊቃውንት ጉባኤ ላይ በአይሁድ ታሪክ ውስጥ በቀኖናነት ተቀባይነት እንደነበራቸው ተረጋግጠው እስትንፋሰ መለኮት መሆናቸው ዕውቅና የተሰጣቸው የብሉይ ኪዳን መጻሕፍት ሰላሳ ዘጠኙ ብቻ ነበሩ፡፡ የጉባኤው አላማ ቀኖናን ማጽደቅ ሳይሆን የትኞቹ መጻሕፍት በቀኖናነት ከትውልድ ወደ ትውልድ ሲተላለፉ እንደነበሩ ለይቶ ዕውቅና መስጠት እንደ ነበር ልብ ሊባል ይገባል፡፡ የአይሁድ መምህር የነበረው የእስክንድርያው ፋይሎ (20 ዓ.ዓ. – 40 ዓ.ም.) ሙሉ በሙሉ ሊባል በሚቻልበት ሁኔታ ከሁሉም የብሉይ ኪዳን መጻሕፍት የጠቀሰ ሲሆን ከአፖክሪፋ ግን አንድም ጊዜ አልጠቀሰም፡፡
የአይሁድ ጸሐፌ ታሪክ የነበረው ጆሲፈስ ፍላቪየስ (ዮሴፍ ወልደ ኮርዮን) (30 ዓ.ም. – 100 ዓ.ም.) የብሉይ ኪዳን መጻሕፍት 22 ብቻ መሆናቸውን በመጥቀስ የአፖክሪፋን መጻሕፍ ውድቅ አድርጓቸዋል፡፡ አይሁድ አንዳንድ መጻሕፍትን እንደ አንድ መጽሐፍ ስለሚቆጥሯቸው እንጂ እነዚህ በወንጌላውያን አብያተ ክርስቲያናት ቆጠራ መሠረት 39 ከሆኑት የብሉይ ኪዳን መጻሕፍት የተለዩ አይደሉም፡፡ ሐዋርያው ቅዱስ ጳውሎስ ሮሜ 3፡1-2 ላይ እንደጻፈው እግዚአብሔር ብሉይ ኪዳንን በአደራ የሰጠው ለአይሁድ ሕዝብ ነው፡-
“እንግዲህ የአይሁዳዊ ብልጫው ምንድር ነው? ወይስ የመገረዝ ጥቅሙ ምንድር ነው? በሁሉ ነገር ብዙ ነው።አስቀድሞ የእግዚአብሔር ቃላት አደራ ተሰጡአቸው፡፡”
ስለዚህ አይሁድ የትኞቹ የብሉይ ኪዳን መጻሕፍት ከእግዚአብሔር እንደሆኑና እንዳልሆኑ ለይተው ያውቃሉ፡፡ የአይሁድ ሕዝብ ቅዱሳት መጻሕፍትን በታላቅ አክብሮትና በጥንቃቄ ይዘው እንደቆዩ ታሪክ ምስክር ነው፡፡ የጥንቃቄያቸውን ብዛት ለመረዳት እስኪ ተከታዮቹን እውነታዎች ተመልከቱ፡-
የጽሑፍ ሥራው ከመጀመሩ በፊት በእድሜ የሁሉ ታላቅ የሆነ ረቢ ተነስቶ በመቆም አንድ ፊደል እንኳ መቀነስ ወይንም ደግሞ መጨመር ለጥፋት እንደሚዳርጋቸው ጸሐፍቱን ያስጠነቅቃል፡፡ ጸሐፍቱ ሥራቸውን እየሠሩ ሳሉ ንጉሥ እንኳ ቢገባ ስህተት ላለመስራት የጀመሩትን ገፅ እስኪጨርሱ ድረስ ቀና ብለው ማናገር እንደ ሌለባቸው ማስጠንቀቂያ ይሰጣቸዋል፡፡
ብሉይ ኪዳን የሚጻፍበት ብራና ከንፁህ እንስሳት ቆዳ በአይሁዳዊ እጅ ብቻ መዘጋጀት አለበት፡፡ እያንዳንዱ ወርድ ከ 48 በታች እና ከ 60 በላይ መስመሮች ሊኖሩት አይገባም፡፡ ቀለሙ ጥቁር ብቻ መሆን አለበት፣ በተለየ ሁኔታም ይዘጋጃል፡፡ ከትውስታ የሚጻፍ ምንም ዓይነት ቃል ወይንም ፊደል መኖር የለበትም፡፡ ጸሐፊው ተኣማኒ የሆነ ኮፒ ከፊት ለፊቱ ማስቀመጥ አለበት፣ ከመጻፉ በፊትም ከፍ ባለ ድምፅ በትክክል ሊያነበው ይገባል፡፡ ጸሐፊው ከመጻፉ በፊት አክብሮት በተሞላበት ሁኔታ መጻፍያውን መወልወል አለበት፡፡
ጸሐፊው ያሕዌ የሚለውን የእግዚአብሔርን ስም ከመጻፉ በፊት መላ ሰውነቱን መታጠብ አለበት፡፡ ጸሐፊው ያሕዌ የሚለውን የእግዚአብሔርን ስም ለመጻፍ አዲስ ብዕር ይጠቀማል፡፡ ያሕዌ የሚለውን ስም የጻፈበትን ብዕር ሌላ ቃል ለመጻፍ አይጠቀምበትም፡፡ በአንድ ገፅ ላይ የሚፈጠር አንድ ስህተት ገፁን በሙሉ ያበላሸዋል፡፡ በአንድ ገፅ ላይ ሦስት ስህተቶች ከተገኙ ብራናው በሙሉ ከጥቅም ውጪ ይሆናል፡፡ እያንዳንዱ ቃል እና እያንዳንዱ ፊደል ተቆጥሮ ተመዝግቧል፡፡
ስለዚህ ወንጌላውያን አብያተ ክርስቲያናት የብሉይ ኪዳንን ቀኖና በተመለከተ እግዚአብሔር ታማኝ አድርጎ ቆጥሮ ቃሉን በአደራ ከሰጣቸውና እንዲህ ባለ ጥንቃቄና አክብሮት የእግዚአብሔርን ቃል ከትውልድ ወደ ትውልድ ሲያስተላልፉ ከኖሩት ሕዝቦች ጋር ይስማማሉ፡፡
ጌታችን ኢየሱስ ዕውቅናን የሰጠው ለአይሁድ ቀኖና ብቻ ነበር፡፡ በጌታ ዘመን ብሉይ ኪዳን ሕግ፣ ነቢያት እና መዝሙራት በመባል ለሦስት ተከፍሎ ነበር (ሉቃስ 24፥44)፡፡ በነዚህ ሦስቱ ክፍሎች ውስጥ የአፖክሪፋ መጻሕፍት አልነበሩም፡፡ በተጨማሪም ጌታችን ኢየሱስ “ከአቤል ደም እስከ ዘካርያስ ደም” በማለት ብሉይ ኪዳን ከአቤል ጀምሮ እስከ ዘካርያስ ዘመን ድረስ የሚገኘውን የታሪክ ዘመን እንደሚሸፍን አመላክቷል (ማቴ 23፡35፣ ሉቃ 11፡51)፡፡ ይህም ከዘፍጥረት ጀምሮ እስከ መጨረሻዎቹ ነቢያት ድረስ የሚገኘው ዘመን ነው፡፡ ነቢዩ ዘካርያስ እና ነቢዩ ሚልኪያስ በአንድ ዘመን የኖሩ ሲሆኑ ከእነርሱ በኋላ እስከ ክርስቶስ ዘመን ድረስ የነበረው ዘመን የዝምታ ዘመን በመባል ይታወቃል፡፡ በይሁዳ መልዕክት ቁጥር 14-15 ላይ ከአፖክሪፋ መጻሕፍት መካከል አንዱ የሆነው መጽሐፈ ሄኖክ መጠቀሱ መጽሐፉ ትምህርት ሰጪ የሆነን መልዕክት በውስጡ የያዘ መሆኑን የሚያመለክት እንጂ መጽሐፉ ሙሉ በሙሉ እውነት መሆኑን የሚያመለክት አይደለም፡፡ የጌታ ሐዋርያት ለተደራሲያኖቻቸው ትምህርት ሊሰጡ የሚችሉ የግሪክ ጽሑፎችንና ሌሎች የአይሁድ መጻሕፍትን እንኳ ሲጠቅሱ እንመለከታለን፡፡ ይህ ጽሑፎቹን እስትንፋሰ መለኮት አያደርጋቸውም፡፡
ማጠቃለያ
የአፖክሪፋ መጻሕፍት ቀኖና መሆን አለመሆናቸው የክርስትናን ዋና ዋና አስተምህሮዎች በምንም መልኩ የሚነካ አይደለም፡፡ የተቀሩት የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍሎች መቀየራቸውንም አያሳይም፡፡ የአፖክሪፋ መጻሕፍት ከቀኖና መቆጠራቸው በመጽሐፍ ቅዱስ አጠቃላይ መልዕክት ላይ የሚጨምረውም ሆነ የሚቀንሰው ምንም ነገር የለም፡፡ በየትኛውም ቤተ እምነት ቀኖና የታተመውን መጽሐፍ ቅዱስ ያነበበ ሰው መሠረታዊ የሆኑ የክርስትና አስተምህሮዎችን በተሟላ ሁኔታ ያገኛል፡፡ የአፖክሪፋን መጻሕፍት እንደ ቃለ እግዚአብሔር የማይቆጥሩ አብያተ ክርስቲያናትም ቢሆኑ እነዚህን መጻሕፍት ሙሉ በሙሉ ውድቅ የማያደርጉ ሲሆን መንፈሳዊ ትምህርቶችን እንደያዙ አስተማሪ መጻሕፍት ይቀበሏቸዋል፤ ከሌሎች የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍሎች ጎን ለጎን ለተጨማሪ ዕውቀት ያጠኗቸዋል፡፡ ሙስሊም ወገኖች ራሳቸው “ሐዲስ ቁድሲ” በማለት የሚጠሯቸው የሐዲስ ክፍሎች እንደ ቁርአን ሁሉ የአላህ ቃል ናቸው ወይስ አይደሉም? በሚለው ላይ ስምምነት የላቸውም፡፡ ክርስቲያኖች በአፖክሪፋ መጻሕፍት ዙርያ ያላቸውን ልዩነት በዚሁ መንገድ መረዳት ያስፈልጋል፡፡
ምንጭ:- www.ewnetlehulu.org

👍6❤1
ቅዱሳት መጻሕፍት
መጽሐፍ ቅዱስ ምን ዓይነት መጽሐፍ ነው? ምዕራፍ ፩ ክፍል-4 ወንጌላውያን አብያተ ክርስቲያናት እና የግሪክ ኦርቶዶክስን የመሳሰሉት አብያተ ክርስቲያናት እነዚህን መጽሐፍት እንደ ቃለ እግዚአብሔር የማይቀበሉበት ሌላው ምክንያት ደግሞ እነዚህ መጻሕፍት በአይሁድ ቀኖና ውስጥ የማይገኙ መሆናቸው ነው፡፡ በ90 ዓ.ም. ዮሐናን ቤን ዛካይ በተባለ ረቢ…
ቅዱሳት መጻሕፍት 66፣ 72፣ 75 . . . ወይስ 81? እዚህ ላይ "ነው" ብላችሁ የምታምኑትን ነገር ከነማስረጃው በማቅረብ መሟገት ትችላላችሁ። ግን ሁሉ በቅንነትና በጨዋነት ይሁን።
' ==❀❀❀===❀❀❀==
የዕለቱ ጥቅስ
==❀❀❀===❀❀❀==
“አምላካችን ሆይ፥ አንተ አትፈርድባቸውምን? ይህን የመጣብንን ታላቅ ወገን እንቃወም ዘንድ አንችልም፤ የምናደርገውንም አናውቅም፤ ነገር ግን ዓይኖቻችን ወደ አንተ ናቸው።”
2 ዜና 20፥12
ወደ ቻናሉ ለመ🀄️ላ🀄️ል፦ @Holy_scriptures
የዕለቱ ጥቅስ
==❀❀❀===❀❀❀==
“አምላካችን ሆይ፥ አንተ አትፈርድባቸውምን? ይህን የመጣብንን ታላቅ ወገን እንቃወም ዘንድ አንችልም፤ የምናደርገውንም አናውቅም፤ ነገር ግን ዓይኖቻችን ወደ አንተ ናቸው።”
2 ዜና 20፥12
ወደ ቻናሉ ለመ🀄️ላ🀄️ል፦ @Holy_scriptures
👍4❤1
#የእግዚአብሔር_ቃል_ምን_ይላል?
መዝሙር 105
¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯
¹ እግዚአብሔርን አመስግኑ ስሙንም ጥሩ፥ ለአሕዛብም ሥራውን አውሩ።
² ተቀኙለት፥ ዘምሩለት፥ ተአምራቱንም ሁሉ ተናገሩ።
³ በቅዱስ ስሙ ተጓደዱ፤ እግዚአብሔርን የሚፈልግ ልብ ደስ ይበለው።
⁴ እግዚአብሔርን ፈልጉት ትጸናላችሁም፤ ሁልጊዜ ፊቱን ፈልጉ።
⁵-⁶ ባሪያዎቹ የአብርሃም ዘር፥ ለእርሱም የተመረጣችሁ የያዕቆብ ልጆች ሆይ፥ የሠራትን ድንቅ አስቡ፥ ተአምራቱን የአፉንም ፍርድ።
⁷ እርሱ እግዚአብሔር አምላካችን ነው፤ ፍርዱ በምድር ሁሉ ነው።
⁸ ቃል ኪዳኑን ለዘላለም፥ እስከ ሺህ ትውልድ ያዘዘውን ቃሉን አሰበ፥
⁹ ለአብርሃም ያደረገውን፥ ለይስሐቅም የማለውን፤
¹⁰ ለያዕቆብ ሥርዓት እንዲሆን ለእስራኤልም የዘላለም ኪዳን እንዲሆን አጸና፤
¹¹ እንዲህም አለ፦ ለአንተ የከነዓንን ምድር የርስታችሁን ገመድ እሰጣለሁ፤
¹² ይህም የሆነው እነርሱ በቍጥር ጥቂቶች ሰዎች፥ እጅግ ጥቂቶችና ስደተኞች ሲሆኑ ነው።
¹³ ከሕዝብ ወደ ሕዝብ፥ ከመንግሥታትም ወደ ሌላ ሕዝብ አለፉ።
¹⁴-¹⁵ የቀባኋቸውን አትዳስሱ፥ በነቢያቴም ክፉ አታድርጉ ብሎ፥ ሰው ግፍ ያደርግባቸው ዘንድ አልፈቀደም፥ ስለ እነርሱም ነገሥታትን ገሠጸ።
¹⁶ በምድር ላይ ራብን ጠራ፥ የእህልን ኃይል ሁሉ ሰበረ።
¹⁷ በፊታቸው ሰውን ላከ ዮሴፍ ለባርነት ተሸጠ።
¹⁸ እግሮቹም በእግር ብረት ደከሙ፥ እርሱም በብረት ውስጥ ገባ።
¹⁹ ቃሉ እስኪመጣለት ድረስ፥ የእግዚአብሔር ቃል ፈተነው።
²⁰ ንጉሥ ላከ ፈታውም፥ የአሕዛብም አለቃ አስፈታው።
²¹ የቤቱ ጌታ፥ የጥሪቱ ሁሉ ገዢ አደረገው፥
²² አለቆቹን እንደ ፈቃዱ ይገሥጽ ዘንድ፥ ሽማግሌዎቹንም ጥበበኞች ያደርጋቸው ዘንድ።
²³ እስራኤልም ወደ ግብጽ ገባ፥ ያዕቆብም በካም አገር ተቀመጠ።
²⁴ ሕዝቡንም እጅግ አበዛ፥ ከጠላቶቻቸውም ይልቅ አበረታቸው።
²⁵ ሕዝቡን ይጠሉ ዘንድ በባሪያዎቹም ላይ ይተነኰሉ ዘንድ ልባቸውን ለወጠ።
²⁶ ባሪያውን ሙሴን የመረጠውንም አሮንን ላከ።
²⁷ የተኣምራቱን ነገር በላያቸው ድንቁንም በካም አገር አደረገ።
²⁸ ጨለማን ላከ ጨለመባቸውም፤ በቃሉም ዐመፁ።
²⁹ ውኃቸውን ወደ ደም ለወጠ፥ ዓሦቻቸውንም ገደለ።
³⁰ ምድራቸው የንጉሦቻቸውም ቤቶች በጓጕንቸር ሞሉ።
³¹ ተናገረ፥ የውሻ ዝንብ ትንኝም በዳርቻቸው መጡ።
³² ዝናባቸውን በረዶ አደረገው፥ እሳትም በምድራቸው ተቃጠለች።
³³ ወይናቸውንና በለሳቸውን መታ፥ የአገራቸውንም ዛፍ ሁሉ ሰበረ።
³⁴ ተናገረ፥ አንበጣም ስፍር ቍጥር የሌለውም ኩብኩባ መጣ፥
³⁵ የአገራቸውንም ለምለም ሁሉ በላ፥ የምድራቸውንም ፍሬ በላ።
³⁶ የአገራቸውንም በኵር ሁሉ፥ የጕልበታቸውን መጀመሪያ ሁሉ መታ።
³⁷ ከወርቅና ከብርም ጋር አወጣቸው፥ በወገናቸውም ውስጥ ደዌ አልነበረም።
³⁸ ፈርተዋቸው ነበርና ግብጽ በመውጣታቸው ደስ አላት።
³⁹ ደመናን ለመሸፈኛ ዘረጋባቸው፥ እሳትንም በሌሊት ያበራላቸው ዘንድ ዘረጋ።
⁴⁰ ለመኑ፥ ድርጭትንም አመጣላቸው፥ የሰማይንም እንጀራ አጠገባቸው።
⁴¹ ዓለቱን ሰነጠቀ፥ ውኃውም ፈሰሰ፤ ወንዞች በበረሃ ሄዱ፤
⁴² ለባሪያው ለአብርሃም የነገረውን ቅዱስ ቃሉን አስቦአልና።
⁴³ ሕዝቡንም በደስታ የተመረጡትንም በእልልታ አወጣ።
⁴⁴ የአሕዛብንም አገሮች ሰጣቸው፥ የወገኖችንም ድካም ወረሱ፥
⁴⁵ ሕጉን ይጠብቁ ዘንድ፥ ሥርዓቱንም ይፈልጉ ዘንድ። ሃሌ ሉያ

👍10
' ==❀❀❀===❀❀❀==
የዕለቱ ጥቅስ
==❀❀❀===❀❀❀==
“እንግዲህ ምድሪቱን ስለምሰጥህ ተነሣ፤ በርዝመቷም፣ በስፋቷም ተመላለስባት።””
ዘፍጥረት 13፥17 (አዲሱ መ.ት)

👍4
' ==❀❀❀===❀❀❀==
የዕለቱ ጥቅስ
==❀❀❀===❀❀❀==
“በዙፋኑ መካከል ያለው በጉ እረኛቸው ይሆናልና፥ ወደ ሕይወትም ውኃ ምንጭ ይመራቸዋልና፤ እግዚአብሔርም እንባዎችን ሁሉ ከዓይናቸው ያብሳል።”
ራእይ 7፥17

❤9👍2
በመጽሐፍ ቅዱሳችን ውስጥ ረጅሙ መጽሐፍ የቱ ነው?
Anonymous Quiz
83%
ሀ. መዝሙረ ዳዊት
10%
ለ. ትንቢተ ኢሳይያስ
6%
ሐ. ትንቢተ ኤርምያስ
1%
መ. ትንቢተ ሕዝቅኤል
😢8👍6
' ==❀❀❀===❀❀❀==
የዕለቱ ጥቅስ
==❀❀❀===❀❀❀==
“አቤቱ፥ ነፍሴን ከሲኦል አወጣሃት፥ ወደ ጕድጓድም እንዳልወርድ አዳንኸኝ።”
መዝሙር 30፥3
ወደ ቻናሉ ለመ🀄️ላ🀄️ል፦ @Holy_scriptures
የዕለቱ ጥቅስ
==❀❀❀===❀❀❀==
“አቤቱ፥ ነፍሴን ከሲኦል አወጣሃት፥ ወደ ጕድጓድም እንዳልወርድ አዳንኸኝ።”
መዝሙር 30፥3
ወደ ቻናሉ ለመ🀄️ላ🀄️ል፦ @Holy_scriptures
❤10
#እራሳችንን_እንመርምር
ሰዎች እንደ እኛ እንዲሆኑ እንፈልጋለን? ከምናችን በስተቀር? ወይስ ሙሉ በሙሉ ከነአካቴው እኛኑ እንዲሆኑ እንፈልጋለን? "ኧረ ወዲያ እኔ እራሴ ምን አለ ሌላ ሰው በሆንኩ" እያልን እንገኛለን? ለምን?
“ጳውሎስም፦ በጥቂት ቢሆን ወይም በብዙ አንተ ብቻ አይደለህም ነገር ግን ዛሬ የሚሰሙኝ ሁሉ ደግሞ ከዚህ እስራቴ በቀር እንደ እኔ ይሆኑ ዘንድ ወደ እግዚአብሔር እለምናለሁ አለው።”
ሐዋርያት 26፥29

👍6👏1
' ==❀❀❀===❀❀❀==
የዕለቱ ጥቅስ
==❀❀❀===❀❀❀==
“ከያዕቆብም ቤት ፊቱን የመለሰውን እግዚአብሔርን እጠብቃለሁ፥ እተማመንበትማለሁ።”
ኢሳይያስ 8፥17

❤8
ከቅዱሳት መጻሕፍት መካከል መጀመሪያ እና መጨረሻ እንደተጻፈ የሚገመተው የቱ ነው?
Anonymous Quiz
57%
ሀ. ዘፍጥረት እና የዮሐንስ ራእይ
36%
ለ. ኢዮብ እና ራእይ
4%
ሐ. መሳፍንት እና ራእይ
4%
መ. መዝሙረ ዳዊት እና ራእይ
❤2
ሰሞኑ በቻናላችን በለጠፍነው ጥያቄ ላይ ብዙዎቻችሁ ግራ ተጋብታችኋል። ጥያቄም ጠይቃችኋል። በነገራችን ላይ ብዙ ሰው ተሳትፎ ግር መሰኙቱን በስፋት ስለገለጸልን ምን ያህል ለጥያቄዎቻችን ትኩረት እንደሰጣችሁ አይተናል። ደስ ብሎናል እናመሰግናለን!🙏 ከዚህ በታች በመጽሐፍ ቅዱሳችን ውስጥ ረጃጅም መጻሕፍትን ከነቃላት ብዛታቸው (ማለትም በተጻፉበት ቋንቋ) እነሆ፦
1. ኤርምያስ (33,002 ቃላት)
2. ኦሪት ዘፍጥረት (32,046 ቃላት)
3. መዝሙረ ዳዊት (30,147 ቃላት)
4. ሕዝቅኤል (29,918 ቃላት)
5. ዘጸአት (25, 957 ቃላት)
6. ኢሳይያስ (25,608 ቃላት)
7. ኦሪት ዘኁልቁ (25,048 ቃላት)
8. ኦሪት ዘዳግም (23,008 ቃላት)
9. ሁለተኛ ዜና መዋዕል (21,349 ቃላት)
10. አንደኛ ሳሙኤል (20,361 ቃላት)
ከዚህ ጋር በተያያዘ ጥሩ ቅዱሳት መጻሕፍትን መሠረት ያደረገ ፕሮግራም ያለው ሰው ሊያናግረን ይችላል። በተረፈ ያቋረጥነውን የሮሜ መልእክት ጥናታችንን በቅርቡ እንቀጥላለን።

👍11❤2
' ==❀❀❀===❀❀❀==
የዕለቱ ጥቅስ
==❀❀❀===❀❀❀==
“በውኑ በአሕዛብ ጣዖታት መካከል ያዘንብ ዘንድ የሚችል ይገኛልን? ወይስ ሰማይ ዝናብ ማፍሰስ ይችላልን? አቤቱ አምላካችን ሆይ፥ አንተ አይደለህምን? አንተ ይህን ነገር ሁሉ አድርገሃልና ስለዚህ አንተን በተስፋ እንጠባበቃለን።”
ኤርምያስ 14፥22

👍2
ነቢዩ ኤርምያስ
#ኤርምያስ በመጽሐፍ ቅዱሳችን ውስጥ ረጅሙን መጽሐፍ የጻፈ ነቢይ ነው። ለመሆኑ ነቢዩ ኤርምያስ ማን ነው? በአብዛኛው አማኝ ዘንድ የብሉይ ኪዳን ነቢይ ማለትም ትንቢታቸው ወጥ በሆነ መጽሐፍ ከተሰደሩ ሲባል አእምሮው ላይ የሚመጣው እና የሚወደደው ነቢይ፣ ነቢዩ ኢሳይያስ ነው። ነገር ግን በእስራኤላዊያን ዘንድ ነቢዩ ኤርምያስ ነው። "አልቃሻው ነቢይ" በመባልም ይታወቃል። በእስራኤላውያን ዘንድ ተወዳጅ እንደሆነ ማሳያው ጌታችን እና መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ "ሰዎች የሰውን ልጅ ማን እንደ ሆነ ይሉታል?” (ማቴ. 16፥13) ብሎ ሲጠይቅ ከደቀ መዛሙርቱ ካገኘው አንዱ ምላሽ ኤርምያስ የሚል ነበር። ታዲያ ነቢዩ ኤርምያስ ማን ነው?
ኤርምያስ፤ ትርጕሙ «እግዚአብሔር ከፍ ያደርጋል» ማለት ነው። ከእስራኤል ታላላቅ ነቢያት አንዱ። በኢየሩሳሌም አቅራቢያ ካለው ከተማ ከዓናቶት፥ ከካህናትም ወገን ነበረ። አባቱ በኢዮስያስ ዘመን የሕጉን መጽሐፍ ያገኘው ኬልቅያስ መሆኑን ብዙ ሊቃውንት ያምናሉ። ለእስራኤል ብቻ ሳይሆን ለአሕዛብም ጭምር ነቢይ እንዲሆን በተጠራ ጊዜ ደነገጠ፤ «ብላቴና ነኝ» በማለት አመነታ። በኋላ ግን በተሰጠው ተስፋ መሠረት በረታ። የተጠራውም 626 ከክርስቶስ ልደት በፊት፥ የይሁዳ ንጉሥ ኢዮስያስ በነገሠ በ13ኛው ዓመት ነበር። በኢዮስያስም ልጆች ዘመን ትንቢት እየተናገረ ቆይቶ፥ ከተጠራ ከ40 ዓመት በኋላ የኢየሩሳሌምን መማረክ አየ፤ ኤር. 1፡1-10። በዚህም ዘመን አምስት ነገሥታት ነገሡ።
መጽሐፉ የተጻፈው ከሚከተሉት ዐላማ የተነሣ ነው፣
(1) የኤርምያስን ነቢያዊ አገልግሎትና መልእክት በዘላቂነት በሰነድነት ለመያዝ፤
(2) ሕዝቡ ኪዳን ሲተላለፉና በእግዚአብሔርና በቃሉ ላይ በዐመፀኝነት ሲቀጥሉ የእግዚአብሔርን የማይቀርንና የማያመልጡት ፍርድ ለማሳየት፣
(3) ነቢያዊ ቃሉ የቱን ያህል ሐቅና የቱን ያህልስ ሥልጣን እንዳለው ለማሳየት፡፡ ብዙዎቹ የኤርምያስ ተንቢቶች በሕይወት ዘመኑ ተፈጽመዋል (ለምሳሌ 16፥9፤ 20፥4፤ 25፥1-14፣ 27፥19-22፤ 28፥15-17፤ 32፥10-13፡ 34፥1-5)፤ በረጅም ዘመን ውስጥ የሚፈጸሙት ሌሎቹ ትንቢቶቹ ከጊዜ በኋላ ተፈጽመዋል፤ ወይም ገና ወደ ፊት ይፈጸማሉ (ለምሳሌ 23፥5-6፣ 30፥8-9፣ 31፥31-34፤ 33፥14-16)፡፡
ይቀጥል የሚል አስተያየት ከበዛ በስፋት ስለነቢዩ እና አገልግሎቱ እንመለስበታለን። በተለይም ልዩ ባህሪያቶቹ፣ ስለምርኮው፣ ስለደረሰበት መከራ፣ ተቃውሞ፣ አሟሟቱ. . . ወ.ዘ.ተ
ምንጭ፦ የመጽሐፍ ቅዱስ መዝገበ ቃላት፤ ገጽ 174፣ ምሉእ ሕይወት፤ ገጽ 1099-1100

👍18👏2😁2❤1
' ==❀❀❀===❀❀❀==
የዕለቱ ጥቅስ
==❀❀❀===❀❀❀==
“እግዚአብሔርም ራሔልን አሰበ፥ እግዚአብሔርም ተለመናት፥ ማኅፀንዋንም ከፈተላት፤”
ዘፍጥረት 30፥22

❤9👍1