ቅዱሳት መጻሕፍት
7.45K subscribers
1.36K photos
61 videos
332 files
807 links
በዚህ ቻናል

👉ቅዱሳት መጻሕፍት ይጠናሉ::
👉መጽሐፍ ቅዱሳዊ ትምህርቶች ይቀርባሉ::
👉 ለቅዱሳት መጽሐፍት ጥናት የሚያግዙ መጻሕፍት ይለቀቃሉ።

⭐️⭐️⭐️⭐️⭐️

@Holy_scriptures
Download Telegram
#እራሳችንን_እንመርምር

እስቲ እራሳችንን እንጠይቅ። እግዚአብሔር ስለ እኛ ክፉ አስቦ ያውቃል? በእውነት እርሱ እኛን በማሰቃየት የሚረካ አምላክ ነው? እርሱን የምንፈራ ከሆንን ከወዳጅነቱ ይልቅ ለእኛ ክፉ አሳቢ አድርገን ብንቆጥረው ያዋጣናል?

“ለእነርሱም መልካምን በማድረግ ደስ ይለኛል በእውነትም በፍጹም ልቤና በፍጹም ነፍሴ በዚህች ምድር እተክላቸዋለሁ።”
ኤርምያስ 32፥41


ወደ ቻናሉ ለመ🀄️🀄️ል፦ @Holy_scriptures
6
'    ==❀❀❀===❀❀❀==      
              የዕለቱ ጥቅስ
     ==❀❀❀===❀❀❀==
“በአንድ አካልም የተጠራችሁለት ደግሞ የክርስቶስ ሰላም በልባችሁ ይግዛ፤ የምታመሰግኑም ሁኑ።”
                 ቆላስይስ 3፥15




ወደ ቻናሉ ለመ🀄️🀄️ል፦ @Holy_scriptures
👍31
ቅዱሳት መጻሕፍት
የቀጠለ... አራቱ ደስታችንን ሊጠብቁ የሚችሉ አመለካከቶች 3. መንፈሳዊ አሳብ - ፊልጵስዩስ 3 በዚህ ምዕራፍ ውስጥ ጳውሎስ ወደ አሥራ አንድ ጊዜ ያህል «ነገር» የሚለውን ቃል ሲጠቀም ታገኛላችሁ። የአብዛኛዎቹ ሰዎች «አሳባቸው ምድራዊ» (3፡19) ለሆኑ ነገሮች ሲሆን፥ መንፈሳዊ ልብ ያላቸው ክርስቲያኖች ግን የሚጨነቁት ስለ ሰማያዊ ነገሮች መሆኑን ያሳየናል። «እኛ አገራችን በሰማይ ነውና፥ ከዚያም…
የቀጠለ...


አራቱ ደስታችንን ሊጠብቁ የሚችሉ አመለካከቶች


4. የተጠበቀ ልብ - ፊልጵስዩስ 4


በእውነቱ ጭንቀት ስለአጋጣሚዎች፥ ስለሰዎች እንዲሁም ስለነገሮች የተሳሳተ አመለካከት (በአእምሮአችን) ሲጸነስ እና ትክክለኛ ያልሆነ ስሜት (በልባችን) ሲሰርፅ የሚፈጠር ነው። ስለዚህ፥ አንድ አሳብ፥ ማለትም በትሕትና ላይ የተመሠረተ አሳብ፥ እና መንፈሳዊ አሳብ ካለን፥ ለጭንቀት ያን ያህል ክብደት ልንሰጠው አይገባም። የሚያስፈልገን ነገር ቢኖር ጭንቀት ወደውስጣችን እንዳይገባ አእምሮአችንንና ልባችንን የሚጠብቅ መከላከያ ማግኘት ነው። ጳውሎስ ስለተጠበቀ አሳብ ሲያስረዳ

«አእምሮን ሁሉ የሚያልፍ የእግዚአብሔር ሰላም ልባችሁንና አሳባችሁን በክርስቶስ ኢየሱስ ይጠብቃል» (4፡7) ብሏል።

ጠበቀ የሚለው ወታደራዊ ቃል ነው፤ ይኸውም «ምሽግን ከአደጋ ለመከላከል ዘብ መቆምን» የሚያመለክት ነው። (እንደምናስታውሰው ጳውሎስ በታሠረበት ጊዜ ከአንድ ወታደር ጋር በሰንሰለት ተቆራኝቶ ነበር)።

ምዕራፍ 4 አማኝ በክርስቶስ ስላለው መንፈሳዊ ሀብቶች የሚያስረዳ ነው፤ እነርሱም የእግዚአብሔር ሰላም (4፡1-9)፥ የእግዚአብሔር ኃይል (4፡10-13)፥ እና የእግዚአብሔር እርዳታ (4፡14-23) ናቸው። እነዚህ ሁሉ ሀብቶች ካሉን ታዲያ ለምን እንጨነቃለን? የሚጠብቀን የእግዚአብሔር ሰላም (4፡7) እንዲሁም የሚመራን የሰላም አምላክ (4፡9) አለን። የእግዚአብሔር ሰላም ወደ እኛ የሚመጣው ትክክለኛ የሆነ ጸሎት ስንለማመድ (4፡6-7)፥ ትክክለኛ የሆነ አስተሳሰብ ስናራምድ (4፡8)፥ እና ትክክለኛ የሆነ ኑሮን ስንኖር (4፡9) ነው። ይህም በጭንቀት ሁሉ ላይ ድል የሚሰጠን የእግዚአብሔር ምሥጢር ነው።




ምንጭ፦ ዋረን ደብልዩ ዌርዝ ቢ፤ ደስተኛ ሁን፤ የፊልጵስዩስ መልእክት ፤ ገጽ 8-9




ወደ ቻናሉ ለመ🀄️🀄️ል፦ @Holy_scriptures
👍21
'    ==❀❀❀===❀❀❀==      
              የዕለቱ ጥቅስ
     ==❀❀❀===❀❀❀==
“ጌታ እግዚአብሔር ኃይሌ ነው፤ እግሮቼን እንደ ዋላ እግሮች ያደርጋል፤ በከፍታዎችም ላይ ያስሄደኛል።”
              ዕንባቆም 3፥19




ወደ ቻናሉ ለመ🀄️🀄️ል፦ @Holy_scriptures
4👍1
ወደ ቻናሉ ለመ🀄️🀄️ል፦ @Holy_scriptures
👍1
finote-1.pdf
1.5 MB
👉ርዕስ፦ ፍኖተ መንግሥት
ከመጀመሪያ እስከ መጨረሻ አንድ መስመር አለ!
✍️ጸሐፊ፦ መርዓዊሥላሴ ንጉሤ (መጋቢ)
📑የገጽ ብዛት፦ 466
📆የታተመበት ዓመት፦ 2004 ዓ.ም



ወደ ቻናሉ ለመ🀄️🀄️ል፦ @Holy_scriptures
👍3
'    ==❀❀❀===❀❀❀==      
              የዕለቱ ጥቅስ
     ==❀❀❀===❀❀❀==
“እስራኤል ደግነትን ጥሎአል፤ ጠላትም ያሳድዱታል።”
                 ሆሴዕ 8፥3



ወደ ቻናሉ ለመ🀄️🀄️ል፦ @Holy_scriptures
2
#የእግዚአብሔር_ቃል_ምን_ይላል?


መዝሙር 119
¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯
⁶⁵ አቤቱ፥ እንደ ቃልህ ለባሪያህ መልካም አደረግህ።
⁶⁶ በትእዛዛትህ ታምኛለሁና መልካም ምክርና እውቀትን አስተምረኝ።
⁶⁷ እኔ ሳልጨነቅ ሳትሁ፤ አሁን ግን ቃልህን ጠበቅሁ።
⁶⁸ አቤቱ፥ አንተ ቸር ነህ፥ በቸርነትህም ሥርዓትህን አስተምረኝ።
⁶⁹ የትዕቢተኞች ዓመፅ በላዬ በዛ፤ እኔ ግን በፍጹም ልቤ ትእዛዛትህን እፈልጋለሁ።
⁷⁰ ልባቸው እንደ ወተት ረጋ፤ እኔ ግን በሕግህ ደስ ይለኛል።
⁷¹ ሥርዓትህን እማር ዘንድ ያስጨነቅኸኝ መልካም ሆነልኝ።
⁷² ከአእላፋት ወርቅና ብር ይልቅ የአፍህ ሕግ ይሻለኛል።
⁷³ እጆችህ ሠሩኝ አበጃጁኝም፤ እንዳስተውል አድርገኝ፥ ትእዛዛትህንም እማራለሁ።
⁷⁴ በቃልህ ታምኛለሁና የሚፈሩህ እኔን አይተው ደስ ይላቸዋል።
⁷⁵ አቤቱ፥ ፍርድህ ጽድቅ እንደ ሆነች፥ በእውነትህም እንዳስቸገርኸኝ አወቅሁ።
⁷⁶ ምሕረትህ ለመጽናናቴ ትሁነኝ፥ እንደ ቃልህም ለባሪያህ ይሁነው።
⁷⁷ ሕግህ ተድላዬ ናትና ቸርነትህ ትምጣልኝ፥ በሕይወትም ልኑር።
⁷⁸ ትዕቢተኞች በዓመፅ ጠምመውብኛልና ይፈሩ፤ እኔ ግን በትእዛዝህ እጫወታለሁ።
⁷⁹ የሚፈሩህና ምስክሮችህን የሚያውቁ ወደ እኔ ይመለሱ።
⁸⁰ እንዳላፍር ልቤ በሥርዓትህ የቀና ይሁን።



ወደ ቻናሉ ለመ🀄️🀄️ል፦ @Holy_scriptures
4👍1
'    ==❀❀❀===❀❀❀==      
              የዕለቱ ጥቅስ
     ==❀❀❀===❀❀❀==
“ነገር ግን ጥበብ የምትገኘው ወዴት ነው? የማስተዋልስ ስፍራ ወዴት ነው?”
               ኢዮብ 28፥12



ወደ ቻናሉ ለመ🀄️🀄️ል፦ @Holy_scriptures
👍41
የአማኝ ሕይወት በእድገት መቀጠል ሲገባው ለምን ወደ ኋላ ይላል?

በመንፈሳዊ ሕይወት ውስጥ ከማደግ ይልቅ ወደ ኋላ ማፈግፈግ ብዙ ጊዜ ይስተዋላል። ከእነዚህ ምክንያቶች ውስጥ ዛሬ አንዱን እንመለከታለን።

1. "ተንኰልን የሙጥኝ " ብሎ ሲይዝ

2. "ሊመለስም እንቢ" ሲል

“እንግዲህ ይህ የኢየሩሳሌም ሕዝብ ዘወትር ስለ ምን ወደ ኋላው ይመለሳል? ተንኰልን ይዞአል ሊመለስም እንቢ ብሎአል።”
(ኤርምያስ 8፥5)

“ታዲያ፣ ይህ ሕዝብ ለምን ፊቱን አዙሮ ወደ ኋላ ይሄዳል? ለምንስ ኢየሩሳሌም ዘወትር ወደ ኋላ ትመለሳለች? ተንኰልን የሙጥኝ ብለው ይዘዋል፤ ሊመለሱም ፈቃደኛ አይደሉም።”
ኤርምያስ 8፥5 (አዲሱ መ.ት)


"እንግዲህ ክፋትን ሁሉ ተንኰልንም ሁሉ ግብዝነትንም ቅንዓትንም ሐሜትንም ሁሉ አስወግዳችሁ፥ ጌታ ቸር መሆኑን ቀምሳችሁ እንደ ሆነ፥ ለመዳን በእርሱ እንድታድጉ አሁን እንደ ተወለዱ ሕፃናት ተንኰል የሌለበትን የቃልን ወተት ተመኙ።"
(1ኛ ጴጥሮስ 2፥1-3)

ለመሆኑ "ተንኮል" ማለት ምን ማለት ነው? እስቲ በዚህ ነገር በአሳብ መስጫው ላይ አሳብ ስጡበት፤ ተወያዩበትም።



ወደ ቻናሉ ለመ🀄️🀄️ል፦ @Holy_scriptures
👍112
'    ==❀❀❀===❀❀❀==      
              የዕለቱ ጥቅስ
     ==❀❀❀===❀❀❀==
“ለራስህ ታላቅን ነገር ትፈልጋለህን? በሥጋ ለባሽ ሁሉ ላይ፥ እነሆ፥ ክፉ ነገርን አመጣለሁና አትፈልገው፥ ይላል እግዚአብሔር፤ ነገር ግን በሄድህበት ስፍራ ሁሉ ነፍስህን እንደ ምርኮ አድርጌ እሰጥሃለሁ።”
              ኤርምያስ 45፥5




ወደ ቻናሉ ለመ🀄️🀄️ል፦ @Holy_scriptures
👍41
#ከተማ_ወይም_ቦታ_በቅዱሳት_መጻሕፍት


#ናዝሬት

ናዝሬት፤ ከገሊላ ባሕር በስተምዕራብ 25 ኪ.ሜ. ርቆ በዛብሎን ነገድ ድርሻ ውስጥ በተራራማ አገር ላይ የተመሠረተ ከተማ ናት። ናዝሬት በብሉይ ኪዳን አልተጠቀሰም፤ በአዲስ ኪዳን ዘመንም ቦታው ወደ አገሩ ጠረፍ ስለሆነ ዝቅተኛ ግምት ይሰጠው ነበር፤ ዮሐ. 1፥47። ናዝሬት የዮሴፍና የማርያም መኖሪያ ከተማ ነበረ። ኢየሱስ በዚህ ተፀነሰ፤ በኋላም አደገበት፤ ሉቃ. 1፥26:27፤ 2፥39:40:51። ኢየሱስ የማስተማር ሥራውን ከጀመረ በኋላ አንድ ጊዜ ወደ ናዝሬት መጣ፤ ሕዝቡ ግን አልተቀበሉትም፤ ሉቃ. 4፥16-30። ዛሬ 30 ሺህ ያህል ሰዎች በናዝሬት ይኖራሉ።



ምንጭ፦የመጽሐፍ ቅዱስ መዝገበ ቃላት፣ ገጽ 140-141




ወደ ቻናሉ ለመ🀄️🀄️ል፦ @Holy_scriptures
5👍4👎1
'    ==❀❀❀===❀❀❀==      
              የዕለቱ ጥቅስ
     ==❀❀❀===❀❀❀==
“ጥበብም ለልጆችዋ ሁሉ ጸደቀች።”
               ሉቃስ 7፥35



ወደ ቻናሉ ለመ🀄️🀄️ል፦ @Holy_scriptures
1👍1
ውድ የቻናላችን ቤተሰቦች ከ #4_ሺህ በላይ "subscribers" ስላገኘን ከልብ እናመሰግናለን! በዚህ ቻናል የሚመቻችሁን ነገር እና ይስተካከል፣ ይታረም፣ ይጨመር፣ ይቀነስ የምትሉትን ነገር በአሳብ መስጫው ላይ እንድታካፍሉን ስንል በትህትና እንጠይቃለን።



ወደ ቻናሉ ለመ🀄️🀄️ል፦ @Holy_scriptures
👍1
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
👍6
'    ==❀❀❀===❀❀❀==      
              የዕለቱ ጥቅስ
     ==❀❀❀===❀❀❀==
“ኃጢአተኛ መቶ ጊዜ ክፉን ቢሠራ ዘመኑም ረጅም ቢሆን፥ እግዚአብሔርን ለሚፈሩት በፊቱም ለሚፈሩት ደኅንነት እንዲሆን አውቃለሁ፤”
              መክብብ 8፥12



ወደ ቻናሉ ለመ🀄️🀄️ል፦ @Holy_scriptures
5
#እራሳችንን_እንመርምር


ለምንድነው የምንጸልየው? ጸሎታችን በእርግጥ እንደሚመለስ እናምናለን? የምንቀበለው የጸለይነውን ወይስ ከዚያ በላይ?


“እንግዲህ በእኛ እንደሚሠራው ኃይል መጠን ከምንለምነው ወይም ከምናስበው ሁሉ ይልቅ እጅግ አብልጦ ሊያደርግ ለሚቻለው፥”
ኤፌሶን 3፥20



ወደ ቻናሉ ለመ🀄️🀄️ል፦ @Holy_scriptures
👍52