' ==❀❀❀===❀❀❀==
የዕለቱ ጥቅስ
==❀❀❀===❀❀❀==
“እግዚአብሔር ፊቱን ወደ አንተ ያንሣ፥ ሰላምንም ይስጥህ።”
ዘኍልቁ 6፥26
ወደ ቻናሉ ለመ🀄️ላ🀄️ል፦ @Holy_scriptures
የዕለቱ ጥቅስ
==❀❀❀===❀❀❀==
“እግዚአብሔር ፊቱን ወደ አንተ ያንሣ፥ ሰላምንም ይስጥህ።”
ዘኍልቁ 6፥26
ወደ ቻናሉ ለመ🀄️ላ🀄️ል፦ @Holy_scriptures
❤9👍1
ከወንጌላት መካከል “የእግዚአብሔር ልጅ የኢየሱስ ክርስቶስ ወንጌል መጀመሪያ።” ብሎ የሚጀምረው ወንጌል የቱ ነው?
Anonymous Quiz
34%
ሀ. ማቴዎስ
32%
ለ. ማርቆስ
10%
ሐ. ሉቃስ
24%
መ. ዮሐንስ
❤13👍2
ከወንጌላት መካከል “ዘወትርም እግዚአብሔርን እያመሰገኑና እየባረኩ በመቅደስ ኖሩ።” ብሎ የሚጨርሰው ወንጌል የቱ ነው?
Anonymous Quiz
10%
ሀ. ማቴዎስ
15%
ለ. ማርቆስ
47%
ሐ. ሉቃስ
28%
መ. ዮሐንስ
🥰6👍3
' ==❀❀❀===❀❀❀==
የዕለቱ ጥቅስ
==❀❀❀===❀❀❀==
“በወንድማማች መዋደድ እርስ በርሳችሁ ተዋደዱ፤ እርስ በርሳችሁ ተከባበሩ፤”
ሮሜ 12፥10
ወደ ቻናሉ ለመ🀄️ላ🀄️ል፦ @Holy_scriptures
የዕለቱ ጥቅስ
==❀❀❀===❀❀❀==
“በወንድማማች መዋደድ እርስ በርሳችሁ ተዋደዱ፤ እርስ በርሳችሁ ተከባበሩ፤”
ሮሜ 12፥10
ወደ ቻናሉ ለመ🀄️ላ🀄️ል፦ @Holy_scriptures
👍4❤2
#እራሳችንን_እንመርምር
በዚህ ምድር ላይ ስንኖር ምን እያደረግን ነው ያለነው? ጉዞአችንን ስንጨርስ የት ለመሄድ ተልመናል? ጉዞኣችንን ስንጨርስ የሚለውን ሌላ ጊዜ እንመለስበታለን። እሺ አሁን በምንኖረው ኑሮ ማንን እየጠቀምን እንገኛለን?
"ነገር ግን በሥጋ መኖሬ ለእናንተ ይበልጥ አስፈላጊ ነው። ይህን በማስተዋል፣ በእምነት እንድታድጉና ደስ እንዲላችሁ፣ በሁላችሁ ዘንድ እንደምቈይና እንደምኖር ተረድቻለሁ።"
ፊልጵስዩስ 1፥24-25 (አዲሱ መ.ት)

👍6❤1
' ==❀❀❀===❀❀❀==
የዕለቱ ጥቅስ
==❀❀❀===❀❀❀==
“ከእናንተ የሆነ የክርስቶስ ባሪያ ኤጳፍራ ሰላምታ ያቀርብላችኋል፤ በእግዚአብሔር ፈቃድ ሁሉ ተረድታችሁና ፍጹማን ሆናችሁ እንድትቆሙ፥ ሁልጊዜ ስለ እናንተ በጸሎቱ ይጋደላል።”
ቆላስይስ 4፥12

👍6❤2
' ==❀❀❀===❀❀❀==
የዕለቱ ጥቅስ
==❀❀❀===❀❀❀==
“ሰውን ትዕቢቱ ያዋርደዋል፤ መንፈሱን የሚያዋርድ ግን ክብርን ይቀበላል።”
ምሳሌ 29፥23

👍3❤2
ቅዱሳት መጻሕፍት
አራቱ ደስታችንን ሊጠብቁ የሚችሉ አመለካከቶች 1. አንድ አሳብ - ፊልጵስዩስ 1 «ሁለት አሳብ ላለው በመንገዱ ሁሉ ለሚወላውል ... አንዳች እንዲያገኝ አይምሰለው» (ያዕ. 1፡8)። ወይንም በጥንት ላቲን ቋንቋ፥ «የመርከቡ ነጂ የሚያርፍበትን ወደብ ካላወቀ የትኛውም ነፋስ አይረዳውም» የሚል ምሳሌ አለ። ለብዙ ክርስቲያኖች በሁኔታዎች አለመሳካት የብስጭት ምክንያት የሚሆነው በ«አንድ አሳብ» ስለማይረጉ…
የቀጠለ...
አራቱ ደስታችንን ሊጠብቁ የሚችሉ አመለካከቶች
2. የሚገዛ አሳብ - ፊልጵስዩስ 2
ይህ ምዕራፍ የሚያተኩረው በሰዎች ላይ ነው፥ መሪ ጥቅሱም «ለወገኔ ይጠቅማል በማለት ወይም በከንቱ ውዳሴ ምክንያት አንድ እንኳ አታድርጉ፥ ነገር ግን እያንዳንዱ ባልንጀራው ከራሱ ይልቅ እንዲሻል በትሕትና ይቁጠር» (2፡3)። በምዕራፍ 1 ላይ ጳውሎስ ክርስቶስን የመጀመሪያው መሻቱ ሲያደርግ፥ በዚህ ምዕራፍ፥ ደግሞ ሌሎችን በሁለተኛ ደረጃ አስቀምጧቸዋል። ይህም የሚያሳየን ራሱን መጨረሻ ማድረጉ ነው! ብዙ ጊዜ በሰዎች ላይ የምንቆጣበት ምክንያት በእኛ አሳብ ስለማይመሩልን ነው። በሕይወት በምንጓዝበት ወቅት እራሳችንን መጀመሪያ ካደረግን፥ እንዲሁም ሌሎችም ራሳቸውን መጀመሪያ ካደረጉ፥ ያንጊዜ በብዙ ነጥቦች ላይ ኃይለኛ ግጭት ይፈጠራል።
አንዲት እናት እና ወንድ ልጇ ወደ ሐኪም ቢሮ ለመሄድ ወደ አሳንሰሩ (ሊፍት) ውስጥ ገቡ። ከሁለተኛው ፎቅ ላይ እንደደረሱም ሌሎች ሰዎች ተጨመሩ። ከእነርሱም መሀል አንዲት ወፍራም ሴት ነበረች። አሳንሰሩም ወደ ላይ መውጣቱን እንደቀጠለ ጸጥታው በወፍራሟ ሴት ጩኸት ደፈረሰ። ወደ ልጁም እናት ዘወር ብላ «ልጅሽ ነከሰኝ እኮ!» አለቻት።
እናትየው በጣም ተሳቀቀች፥ ልጁ ግን ማብራሪያ ነበረው «ፊቴን በቂጧ ስላጣበቀችኝ ነው የነከስኳት» ብሎ አስረዳት።
በአሳንሰሩ ውስጥ የተከሰተው ድርጊት በዓለም ዙሪያ ሁሉ ሲፈፀም የምንመለከተው ነው። ሕዝብ ከሕዝብ፥ መንግሥታት ከመንግሥታት ይነካከሳሉ፥ ምክንያቱም ተፋፍገው ስለሚኖሩ ነው።
ነገር ግን የሚገዛ ትሑት ልብ ያለው ክርስቲያን ሌሎችን ያገለግላል እንጂ ሌላ ሰው እርሱን መጥቶ እንዲያገለግለው አይጠብቅም። ከራሱ ፍላጎትና እቅድ ይልቅ ለሌሎች ምኞት መሟላት ቅድሚያ ይሰጣል። በምዕራፍ 2 ውስጥ በትሑት ልቦናቸው ምሳሌ ሊሆኑን የሚችሉ 4 አስገራሚ ሰዎች እናገኛለን። እነርሱም ኢየሱስ ክርስቶስ (2፡1-11)፥ ጳውሎስ (2፡12-18)፥ ጢሞቴዎስ (2፡19-24) እና አፍሮዲጡን (2፡25-30) ናቸው። እነዚህ ምሳሌዎች «ራሱን ከፍ የሚያደርግ ሁሉ ይዋረዳልና፤ ራሱንም የሚያዋርድ ከፍ ይላል» (ሉቃ. 14፡11) የሚለውን መርሆ ያረጋግጡልናል።
ይቀጥላል...
ምንጭ፦ ዋረን ደብልዩ ዌርዝ ቢ፤ ደስተኛ ሁን፤ የፊልጵስዩስ መልእክት ፤ ገጽ 7-8

👍5❤3
' ==❀❀❀===❀❀❀==
የዕለቱ ጥቅስ
==❀❀❀===❀❀❀==
“እርሱ ለሰዎች ሁሉ ሕይወትንና እስትንፋስን እንዲሁም ሌላውንም ነገር ሁሉ የሚሰጥ ስለ ሆነ፣ የሚጐድለው ነገር ባለመኖሩ በሰው እጅ አይገለገልም።”
ሐዋርያት 17፥25 (አዲሱ መ.ት)

#ከተማ_ወይም_ቦታ_በቅዱሳት_መጻሕፍት
#ጌሤም
ጌሤም፤ በግብጽ ውስጥ በስተሰሜን ምሥራቅ በኩል፥ ወደ ከነዓን የሚቀርብና በራምሴ አቅራቢያ የእስራኤል ልጆች የተቀመጡበት ለም ምድር፤ ዘፍ. 45፥10፤ 46፥28፤ 47፥11:27፤ ዘጸ. 8፥22፤ 9፥26። የጥንቷ ግብፅ ክልል ከአባይ ዴልታ በስተ ምሥራቅ ያለ፡ ለያዕቆብና ለዘሮቹ በግብፅ ንጉሥ እጅ ተሰጥቶ እስከ ዘጸአት ድረስ ይኖሩባቸው ነበር (ዘፍ 45፡10)። የምቾት እና የተትረፈረፈ ቦታ ነው።
ምንጭ፦የመጽሐፍ ቅዱስ መዝገበ ቃላት፣ ገጽ 244፤ www.collinsdictionary.com

👍2
' ==❀❀❀===❀❀❀==
የዕለቱ ጥቅስ
==❀❀❀===❀❀❀==
“ሥጋዬና ልቤ ሊደክሙ ይችላሉ፤ እግዚአብሔር ግን የልቤ ብርታት፣ የዘላለም ዕድል ፈንታዬ ነው።”
መዝሙር 73፥26 (አዲሱ መ.ት)

❤9👍2
ውድ የቻናላችን ቤተሰቦች ዛሬ አንድ "website" ወይም ድኅረ ገጽ (የማታውቁት ከሆነ) ልናስተዋውቃችሁ ወደናል። ሊንኩን ከታች አስቀምጠናል። በዓለም ላይ መጽሐፍ ቅዱስን በተለያዩ ቋንቋዎች በቀላሉ ለመረዳት እንዲቻል የሚሰራ ድርጅት ነው። የዩትዩብ ቻናልም አላቸው። ለመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት እንዲያግዝዎ ገብተው አጫጭር ቪድዮችን መመልከት ይችላሉ። በተጨማሪም በድኅረ ገጹ በመግባት ቪድዮችን ማውረድ በቪድዮ ውስጥ የተሰጡትን ትምህርቶች አንድ ላይ በአንድ ፎቶ አድርጎ ማውረድ ይችላሉ። ለዛሬ የብሉይ ኪዳን (ታናክ) ዳሰሳ ከታች ለጥፈነዋል። ተባረኩ!
ወደ ቻናሉ ለመ🀄️ላ🀄️ል፦ @Holy_scriptures
ወደ ቻናሉ ለመ🀄️ላ🀄️ል፦ @Holy_scriptures
❤2👍2
' ==❀❀❀===❀❀❀==
የዕለቱ ጥቅስ
==❀❀❀===❀❀❀==
“የእግዚአብሔርን ሥራ በቸልታ የሚያደግ ርጉም ይሁን፥ ሰይፉንም ከደም የሚከለክል ርጉም ይሁን።”
ኤርምያስ 48፥10

👍9❤1
#የሮሜ_መልእክት_ጥናት
የእግዚአብሔር ፍትሕ (9:19-29)
የእግዚአብሔር ሉዓላዊነት ሌላ ችግር የሚፈጥር ይመስላል፡፡ «እግዚአብሔር ሉዓላዊ ከሆነ፣ ማን ሊቋቋመው ይችላል? የሚቋቋመው ካለ ደግሞ እንዴት ሊዳኝ ይችላል?» ይህ እግዚአብሔር በሰው ዘር ታሪክ ውስጥ ስለ ፍትሐዊ አሠራሩ የሚጠየቅ የቆየ ጥያቄ ነው፡፡
በቺካጐ ጎዳና በራሪ መንፈሳዊ ወረቀቶችን ስበትን የሆነውን አስታውሳለሁ። አብዛኛዎቹ ሰዎች ትራክቶችን በምሥጋና የተቀበሉኝ ሲሆን፣ አንዱ ግን ጭምድድ አድርጎ የውኃ አሸንዳ ውስጥ ወረወረው። የትራክቱ ስም «እግዚአብሔር እንድታውቃቸው የሚፈልገው አራት ነገሮች» የሚል ነበር።
ሰውየው፣ «እግዚአብሔር እንዲያውቃቸው የምፈልገው ጥቂት ነገሮች አሉ» አለ፡፡ «በዚህ ዓለም ለምን ብዙ ኀዘንና ሰቆቃ ኖረ? ሀብታሞች በነጻነት ሲመላለሱ ምስኪኖች ለምን ይሠቃያሉ?» ብሎ በንቀት ገላመጠኝና፣ «እግዚአብሔር አለ ብለህ አትንገረኝ! እግዚአብሔር ካለ በዓለም ላይ ከኖሩ ኃጢአተኞች ትልቁ እርሱ ነው!» አለና በንቀት ጀርባውን ሰጥቶኝ ከሕዝቡ ጋር ተቀላቀለ፡፡
እግዚአብሔር በባሕርይው ፍጹም እንደሆነ እናውቃለን፡፡ «የምድር ሁሉ ፈራጅ በቅን ፍርድ አይፈርድምን?» (ዘፍጥ. 18:25) እግዚአብሔር ዓመፅን ሲያደርግ ወይም ዐመፀኛ ዓላማና ፈቃድ እንዳለው ፈጽሞ የማይታሰብ ነው፡፡ አንዳንድ ጊዜ ግን እንዲህ የሚያደርግ ይመስላል፡፡ ለሙሴ ምሕረትን አደረገ፣ በፈርዖን ላይ ግን ፈረደበት፡፡ ይህ ትክክል ነውን? እስራኤልን መረጠ፣ ሌሎቹን አሕዛብ ተዋቸው። ይህ ልክ ነውን? ጳውሎስ ለዚህ ክስ ሦስት መልሶችን ሰጥቷል::
ሀ) ለእግዚአብሔር የምንመልስ እኛ ማን ነን? (9:19-21)
ይህ ሥነ - አመክንዮአዊ ነው፡፡ እግዚአብሔር ሠሪያችን ከሆነ፣ እኛ ደግሞ ሸክላዎች ነን፡፡ እግዚአብሔር ከእኛ ይልቅ ጥበበኛ ስለሆነ፣ የእግዚአብሔርን ፈቃድ ልናርም ወይም ልንቋቋም መሞከራችን ሞኝነት ነው:: (የዚህ ምንባብ ማጣቃሻ ኢሳ. 45:9 ነው::) ሸክላ ሕይወት የለውም፣ በሠሪው እጅም ላይ ተጽዕኖ ማሳደር አይችልም:: ስሜት፣ እውቀትና ፈቃድ ስላለን ከፈለግን እግዚአብሔርን ልንቃወመው እንችላለን:: (ኤርምያስ 18ን አንብቡ)፡፡ ነገር ግን አንድ ሰው ሙሴን ወይም ፈርዖንን እንዲሆን የሚወስነው እግዚአብሔር ነው፡፡ ሙሴም ሆነ ፈርዖን እንዲሁም ማንኛውም ሰው ወላጆችን መምረጥ፣ የሚወለድበትን ቦታና ጊዜ መምረጥ ወይም ምን ዓይነት ቁመና እንደሚኖረው መምረጥ፣ አይችልም:: እነዚህ ነገሮች በእግዚአብሔር እጅ መሆናቸውን ማመን አለብን::
ነገር ግን፣ ይህ መሆኑ ከተጠያቂነት አያድነንም፡፡ ፈርዖን ስለ እውነተኛው አምላክ የመማር ትልቅ ዕድል ነበረው፡፡ ነገር ግን ማመፅ ፈለገ፡፡ ጳውሎስ ይህንን እውነት የጠቀሰው የሚያስተምረው ጭብጥ መለኮታዊ ሉዓላዊነት እንጂ የሰው ተጠያቂነት ስለሆነ አይደለም፡፡ ውስኑ አእምሮአችን ሁለቱንም በሙላት ባይረዳም፣ አንዱ ሌላኛውን አይክድም፡፡
ለ) እግዚአብሔር የራሱ ዓላማ አለው (9:22-24)
እግዚአብሔር እንደ ፈርዖን ያለውን ጨካኝ እያየ ይደሰታል ማለት አይደለም፡፡ እግዚአብሔር ለሙሴ «የሕዝቤን መከራ በእውነት አየሁ ጨኸታቸውን ሰማሁ ሥቃያቸውን አውቃለሁ» (ዘጸ. 3:7) አለው፡፡ ይህ የሚያመለክተው እግዚአብሔር ለፈርዖን ዕድል መስጠቱን ነው (2ኛ ጴጥ. 3፡9)። በቁጥር 22 ላይ እግዚአብሔር ፈርዖንን የቁጣ ዕቃ አድርጎ አልመረጠውም፡፡ እግዚአብሔር ሰዎችን የሚያዘጋጃቸው ለክብር ነው (ቁ. 23):: ነገር ግን ኃጢአተኞች ራሳቸውን ለፍርድ ያዘጋጃሉ፡፡ በሙሴና በእስራኤል እግዚአብሔር የምሕረቱን ባለጠግነት ገለጠ፡፡ በፈርዖንና በግብፅ ላይ ደግሞ ኃይሉንና ቁጣውን ገለጠ፡፡ ማናቸውም ምሕረት የተገባቸው ስላልሆኑ፣ እግዚአብሔር በዐመፅ ሊከሰስ አይችልም፡፡
በፍጻሜውም የእግዚአብሔር ዓላማው በቤተ ክርስቲያኑ አይሁድንና አሕዛብን (ቁ. 24) ለመፍጠር ነው:: ዛሬ አማኞች በእግዚአብሔር ጸጋ «የምሕረት ዕቃዎች» ሆነው ለክብር እየተዘጋጁ ሲሆን፣ ይህም እውነት ሮሜ 8:29-30 ያለውን ክፍል ያስታውሰናል፡፡
ይቀጥላል. . .
ምንጭ፦ ዋረን ደብልዩ ዌርዝ ቢ፤ ተስማማ፤ ገጽ 98-100

👍8
' ==❀❀❀===❀❀❀==
የዕለቱ ጥቅስ
==❀❀❀===❀❀❀==
“ቈዳዬ ቢጠፋም፣ ከሥጋዬ ብለይም፣ እግዚአብሔርን አየዋለሁ፤”
ኢዮብ 19፥26 (አዲሱ መ.ት)
ወደ ቻናሉ ለመ🀄️ላ🀄️ል፦ @Holy_scriptures
የዕለቱ ጥቅስ
==❀❀❀===❀❀❀==
“ቈዳዬ ቢጠፋም፣ ከሥጋዬ ብለይም፣ እግዚአብሔርን አየዋለሁ፤”
ኢዮብ 19፥26 (አዲሱ መ.ት)
ወደ ቻናሉ ለመ🀄️ላ🀄️ል፦ @Holy_scriptures
❤5