ቅዱሳት መጻሕፍት
7.45K subscribers
1.37K photos
61 videos
332 files
808 links
በዚህ ቻናል

👉ቅዱሳት መጻሕፍት ይጠናሉ::
👉መጽሐፍ ቅዱሳዊ ትምህርቶች ይቀርባሉ::
👉 ለቅዱሳት መጽሐፍት ጥናት የሚያግዙ መጻሕፍት ይለቀቃሉ።

⭐️⭐️⭐️⭐️⭐️

@Holy_scriptures
Download Telegram
'    ==❀❀❀===❀❀❀==      
              የዕለቱ ጥቅስ
     ==❀❀❀===❀❀❀==
“አቤቱ ጌታ እግዚአብሔር ሆይ፥ እነሆ፥ አንተ ሰማይንና ምድርን በታላቅ ኃይልህና በተዘረጋች ክንድህ ፈጥረሃል፥ ከአንተም የሚያቅት ነገር የለም።”
                ኤርምያስ 32፥17



ወደ ቻናሉ ለመ🀄️🀄️ል፦ @Holy_scriptures
5
አትፍራ



"አትፍራ" የሚለው ቃል በቅዱሳት መጻሕፍት ውስጥ ተደጋግሞ ይገኛል። እናላቹ አንድ ሰው ብድግ ብሎ ለምንድነው የማልፈራው ቢል ትፈርዱበታላችሁ? የሚፈራበትን ምክንያት ዘርዝር ካላችሁትም ስፍር ቁጥር የሌለውን ተራ በተራ ይሰድርላችኋል። ግን የእግዚአብሔር ቃል ለምን መፍራት እንደ ሌለብን ሲገልጽ አንድ አጭር መልስ አለው እርሱም፦ "#እኔ_ከአንተ_ጋር_ነኝ" የሚለው ነው። እንዴ? እንዴት ለእነዚህ ፍጻሜ ለማይገኝላቸው ለሚያስፈሩን ነገሮች አንድ ዓረፍተ ነገር ብቻውን መልስ ይሆናል? እንዴታ መልስማ ይሆናል! ምክንያት ጥቀስልኝ ካላችሁ፦

፩. እኔ ከአንተ ጋር ነኝ ያለው ሁሉን ቻዩና ሁሉን የሚገዛው እግዚአብሔር ነው።

፪. ከአንተ ጋር እሆናለሁ ሳይሆን ያለው እኔ ከአንተ ጋር ነኝ ነው። ወደፊት እሆናለሁ ካለማ እስከዛ እንዴት ይዘለቃል ይባል ይሆናል "ነኝ" ካለ ግን ፍርሃት ዘሎ እንዳይገባ መፈናፈኛ ያጣልና ዋስትናችን ሙሉ ነው።

ከእኔ ጋር ያለው እርሱ እግዚአብሔር ከሆነ፣ ዛሬዬም በእርሱ ቁጥጥር ስር ካለ ምን ይመጣል? ብቻ እግዚአብሔር ከእኔ ጋር እንዳለ እኔም ከእርሱ ጋር እንዳለው እርግጠኛ ልሁን እንጂ


“ከዚያም ወደ ቤርሳቤህ ወጣ። በዚያችም ሌሊት እግዚአብሔር ተገለጠለት፥ እንዲህም አለው፦ እኔ የአባትህ የአብርሃም አምላክ ነኝ አትፍራ፥ እኔ ከአንተ ጋር ነኝና እባርክሃለሁ ስለ ባሪያዬ ስለ አብርሃም ዘርህን አበዛለሁ።”
ዘፍጥረት 26፥23-24

“ጽኑ፥ አይዞአችሁ፥ አትፍሩ፥ ከፊታቸውም አትደንግጡ፤ አምላክህ እግዚአብሔር እርሱ ከአንተ ጋር ይሄዳል፤ አይጥልህም፥ አይተውህም።”
ዘዳግም 31፥6

“በምትሄድበት ሁሉ አምላክህ እግዚአብሔር ከአንተ ጋር ነውና ጽና፥ አይዞህ አትፍራ፥ አትደንግጥ ብዬ አላዘዝሁህምን?”
ኢያሱ 1፥9

“እኔ ከአንተ ጋር ነኝና አትፍራ፤ እኔ አምላክህ ነኝና አትደንግጥ፤ አበረታሃለሁ፥ እረዳህማለሁ፥ በጽድቄም ቀኝ ደግፌ እይዝሃለሁ።”
ኢሳይያስ 41፥10

“እኔ ከአንተ ጋር ነኝና አትፍራ፤ ዘርህንም ከምሥራቅ አመጣዋለሁ፥ ከምዕራብም እሰበስብሃለሁ።”
ኢሳይያስ 43፥5


ወደ ቻናሉ ለመ🀄️🀄️ል፦ @Holy_scriptures
6👍6
'    ==❀❀❀===❀❀❀==      
              የዕለቱ ጥቅስ
     ==❀❀❀===❀❀❀==
“በጠራሁህ ቀን ቀርበህ፦ አትፍራ አልህ።”
               ሰቆ. 3፥57



ወደ ቻናሉ ለመ🀄️🀄️ል፦ @Holy_scriptures
5👍4
ከሐዋርያት መካከል ኢየሱስ ክርስቶስ ያልመረጠው ሐዋርያ የቱ ነው?
Anonymous Quiz
1%
ሀ. ጴጥሮስ
3%
ለ. ይሁዳ
53%
ሐ. ማትያስ
12%
መ. በርተሎሜዎስ
31%
ሠ. ኢየሱስ ያልመረጠው ሐዋርያ የለም
👍75
'    ==❀❀❀===❀❀❀==      
              የዕለቱ ጥቅስ
     ==❀❀❀===❀❀❀==
“የአምላኬም እጅ በእኔ ላይ መልካም እንደሆነች፥ ንጉሡም የነገረኝን ቃል ነገርኋቸው። እነርሱም፦ እንነሣና እንሥራ አሉ። እጃቸውንም ለበጎ ሥራ አበረቱ።”
              ነህምያ 2፥18




ወደ ቻናሉ ለመ🀄️🀄️ል፦ @Holy_scriptures
👍62
አራቱ ደስታችንን ሊጠብቁ የሚችሉ አመለካከቶች


1. አንድ አሳብ - ፊልጵስዩስ 1

«ሁለት አሳብ ላለው በመንገዱ ሁሉ ለሚወላውል ... አንዳች እንዲያገኝ አይምሰለው» (ያዕ. 1፡8)። ወይንም በጥንት ላቲን ቋንቋ፥ «የመርከቡ ነጂ የሚያርፍበትን ወደብ ካላወቀ የትኛውም ነፋስ አይረዳውም» የሚል ምሳሌ አለ። ለብዙ ክርስቲያኖች በሁኔታዎች አለመሳካት የብስጭት ምክንያት የሚሆነው በ«አንድ አሳብ» ስለማይረጉ ነው። ጳውሎስ ለክርስቶስ፥ በአንድ ልብ የመሰጠትን አመለካከት ሲገልጽ፤ «ለእኔ ሕይወት ክርስቶስ ሞትም ጥቅም ነውና» (1፡21) ብሏል።

በምዕራፍ አንድ ጳውሎስ የገጠሙትን አስቸጋሪ ሁኔታዎች በታማኝነት እንደተጋፈጠ አስረድቷል። ግን የገጠሙት ሁኔታዎች ያለውን ደስታ ሊያሳጡት አልቻሉም። ምክንያቱም እርሱ የሚኖረው በሁኔታዎች ውጤት ለመደሰት ሳይሆን ኢየሱስ ክርስቶስን ለማገልገል በመሆኑ ነው። እርሱ ዓላማ ያለው ሰው ነው። «አንድ ነገር አደርጋለሁ» (3፡13)። የሚገጥሙትን ነገሮች ሁሉ ከክርስቶስ ጋር በማያያዝ እንጂ ነገሮችን ብቻቸውን አይመለከትም። ጳውሎስ የሮም እስረኛ አይደለም፥ ነገር ግን እራሱም «የክርስቶስ እስረኛ የሆንሁ» (ኤፌ. 3፡1) በማለት ገልጾታል። እስራቱንም «እስራቴ ለክርስቶስ» (ፊልጵ. 1፡13) ነው ይላል። የተራ ሰው ክስ አልተጋፈጠም፤ እርሱ ግን «ወንጌልን መመከቻ ለማድረግ እንደተሾምሁ» (1፡17) አውቃለሁ ይላል። በችግሮቹ ውስጥ ሆኖ ክርስቶስን አያይም፤ ነገር ግን በክርስቶስ ውስጥ ሆኖ ችግሮቹን ይመለከታል። ይህ ደግሞ ሁሉን ለውጧል።

ክርስቲያን በአንድ አሳብ ሲሆን፥ ስለወንጌል አንድነት (1፥1 - 11) ፣ ስለ ወንጌል መስፋፋት (1፡12-26)፥ እና ስለ ወንጌል እምነት (1፡27-30) ያስባል፤ ጳውሎስ በአስቸጋሪ ሁኔታዎች ውስጥ ሁሉ ሆኖ ይደሰታል። ችግሩ ከሌሎች ክርስቲያኖች ጋር ያለውን ኅብረት ለማጠናከር ረድቶታል፥ ሌሎችንም ደግሞ ወደ ክርስቶስ ለማምጣት ዕድል አግኝቷል፥ እንዲሁም ስለወንጌል በሮማ ፍርድ ቤት ፊት ቆሞ ማስረዳት ችሏል። አንድ ልብ ካላችሁ የሚገጥሟችሁ ችግሮች ሁሉ በማብቂያው መልካም ውጤት ያስገኙላችኋል እንጂ ለጥፋት አይዳርጓችሁም።


ይቀጥላል...



ምንጭ፦ ዋረን ደብልዩ ዌርዝ ቢ፤ ደስተኛ ሁን፤ የፊልጵስዩስ መልእክት ፤ ገጽ 6-7




ወደ ቻናሉ ለመ🀄️🀄️ል፦ @Holy_scriptures
👍43
'    ==❀❀❀===❀❀❀==      
              የዕለቱ ጥቅስ
     ==❀❀❀===❀❀❀==
“ለእነርሱም መልካምን በማድረግ ደስ ይለኛል በእውነትም በፍጹም ልቤና በፍጹም ነፍሴ በዚህች ምድር እተክላቸዋለሁ።”
             ኤርምያስ 32፥41




ወደ ቻናሉ ለመ🀄️🀄️ል፦ @Holy_scriptures
👍43
'    ==❀❀❀===❀❀❀==      
              የዕለቱ ጥቅስ
     ==❀❀❀===❀❀❀==
“እንግዲህ እግዚአብሔር በላይ በሰማይ በታችም በምድር አምላክ እንደ ሆነ፥ ሌላም እንደሌለ ዛሬ እወቅ፥ በልብህም ያዝ።”
              ዘዳግም 4፥39



ወደ ቻናሉ ለመ🀄️🀄️ል፦ @Holy_scriptures
7👍3
#የእግዚአብሔር_ቃል_ምን_ይላል?


ኢሳይያስ 41
¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯
⁸ ባሪያዬ እስራኤል፥ የመረጥሁህ ያዕቆብ፥ የወዳጄ የአብርሃም ዘር ሆይ፥
⁹ አንተ ከምድር ዳርቻ የያዝሁህ ከማዕዘንዋም የጠራሁህና፦ አንተ ባሪያዬ ነህ፥ መርጬሃለሁ አልጥልህም ያልሁህ ሆይ፥
¹⁰ እኔ ከአንተ ጋር ነኝና አትፍራ፤ እኔ አምላክህ ነኝና አትደንግጥ፤ አበረታሃለሁ፥ እረዳህማለሁ፥ በጽድቄም ቀኝ ደግፌ እይዝሃለሁ።
¹¹ እነሆ የሚቆጡህ ሁሉ ያፍራሉ፥ ይዋረዱማል፤ የሚከራከሩህም እንዳልነበሩ ይሆናሉ፥ ይጠፉማል።
¹² የሚያጣሉህንም ትሻቸዋለህ አታገኛቸውምም፥ የሚዋጉህም እንዳልነበሩና እንደ ምናምን ይሆናሉ።
¹³ እኔ አምላክህ እግዚአብሔር፦ አትፍራ፥ እረዳሃለሁ ብዬ ቀኝህን እይዛለሁና።
¹⁴ አንተ ትል ያዕቆብ የእስራኤልም ሰዎች ሆይ፥ አትፍሩ፤ እረዳሃለሁ፥ ይላል እግዚአብሔር፥ የሚቤዥህም የእስራኤል ቅዱስ ነው።
¹⁵ እነሆ፥ እንደ ተሳለች እንደ አዲስ ባለ ጥርስ ማሄጃ አድርጌሃለሁ፤ ተራሮችንም ታሄዳለህ ታደቅቃቸውማለህ፥ ኮረብቶችንም እንደ ገለባ ታደርጋቸዋለህ።
¹⁶ ታበጥራቸዋለህ፥ ነፋስም ይጠርጋቸዋል፥ ዐውሎ ነፋስም ይበትናቸዋል፤ አንተም በእግዚአብሔር ደስ ይልሃል፥ በእስራኤልም ቅዱስ ትመካለህ።
¹⁷ ድሆችና ምስኪኖችም ውኃ ይሻሉ አያገኙምም፥ ምላሳቸውም በጥማት ደርቋል፤ እኔ እግዚአብሔር እሰማቸዋለሁ፥ የእስራኤል አምላክ እኔ አልተዋቸውም።
¹⁸ በወናዎቹ ኮረብቶች ላይ ወንዞችን፥ በሸለቆችም መካከል ምንጮችን እከፍታለሁ፤ ምድረ በዳውን ለውኃ መቆሚያ፥ የጥማትንም ምድር ለውኃ መፍለቂያ አደርጋለሁ።
¹⁹-²⁰ የእግዚአብሔር እጅ ይህን እንደ ሠራች፥ የእስራኤልም ቅዱስ እንደ ፈጠረው ያዩ ዘንድ ያውቁም ዘንድ ያስቡም ዘንድ በአንድነትም ያስተውሉ ዘንድ፥ በምድረ በዳ ዝግባውንና ግራሩን ባርሰነቱንና የዘይቱን ዛፍ አበቅላለሁ፥ በበረሀውም ጥዱንና አስታውን ወይራውንም በአንድነት አኖራለሁ።



ወደ ቻናሉ ለመ🀄️🀄️ል፦ @Holy_scriptures
5👍2
'    ==❀❀❀===❀❀❀==      
              የዕለቱ ጥቅስ
     ==❀❀❀===❀❀❀==
“እግዚአብሔር ፊቱን ወደ አንተ ያንሣ፥ ሰላምንም ይስጥህ።”
               ዘኍልቁ 6፥26



ወደ ቻናሉ ለመ🀄️🀄️ል፦ @Holy_scriptures
9👍1
ከወንጌላት መካከል “የእግዚአብሔር ልጅ የኢየሱስ ክርስቶስ ወንጌል መጀመሪያ።” ብሎ የሚጀምረው ወንጌል የቱ ነው?
Anonymous Quiz
34%
ሀ. ማቴዎስ
32%
ለ. ማርቆስ
10%
ሐ. ሉቃስ
24%
መ. ዮሐንስ
13👍2
ከወንጌላት መካከል “ዘወትርም እግዚአብሔርን እያመሰገኑና እየባረኩ በመቅደስ ኖሩ።” ብሎ የሚጨርሰው ወንጌል የቱ ነው?
Anonymous Quiz
10%
ሀ. ማቴዎስ
15%
ለ. ማርቆስ
47%
ሐ. ሉቃስ
28%
መ. ዮሐንስ
🥰6👍3
'    ==❀❀❀===❀❀❀==      
              የዕለቱ ጥቅስ
     ==❀❀❀===❀❀❀==
“በወንድማማች መዋደድ እርስ በርሳችሁ ተዋደዱ፤ እርስ በርሳችሁ ተከባበሩ፤”
             ሮሜ 12፥10



ወደ ቻናሉ ለመ🀄️🀄️ል፦ @Holy_scriptures
👍42
#እራሳችንን_እንመርምር

በዚህ ምድር ላይ ስንኖር ምን እያደረግን ነው ያለነው? ጉዞአችንን ስንጨርስ የት ለመሄድ ተልመናል? ጉዞኣችንን ስንጨርስ የሚለውን ሌላ ጊዜ እንመለስበታለን። እሺ አሁን በምንኖረው ኑሮ ማንን እየጠቀምን እንገኛለን?


"ነገር ግን በሥጋ መኖሬ ለእናንተ ይበልጥ አስፈላጊ ነው። ይህን በማስተዋል፣ በእምነት እንድታድጉና ደስ እንዲላችሁ፣ በሁላችሁ ዘንድ እንደምቈይና እንደምኖር ተረድቻለሁ።"
ፊልጵስዩስ 1፥24-25 (አዲሱ መ.ት)




ወደ ቻናሉ ለመ🀄️🀄️ል፦ @Holy_scriptures
👍61
'    ==❀❀❀===❀❀❀==      
              የዕለቱ ጥቅስ
     ==❀❀❀===❀❀❀==
“ከእናንተ የሆነ የክርስቶስ ባሪያ ኤጳፍራ ሰላምታ ያቀርብላችኋል፤ በእግዚአብሔር ፈቃድ ሁሉ ተረድታችሁና ፍጹማን ሆናችሁ እንድትቆሙ፥ ሁልጊዜ ስለ እናንተ በጸሎቱ ይጋደላል።”
             ቆላስይስ 4፥12



ወደ ቻናሉ ለመ🀄️🀄️ል፦ @Holy_scriptures
👍62
ወደ ቻናሉ ለመ🀄️🀄️ል፦ @Holy_scriptures
1👍1
እግዚአብሔር ለምን ዝም ይላል.pdf
1017.4 KB
👉ርዕስ፦ እግዚአብሔር ለምን ዝም ይላል?
✍️ጸሐፊ፦ ዶ/ር መለሰ ወጉ
📑የገጽ ብዛት፦ 100


ወደ ቻናሉ ለመ🀄️🀄️ል፦ @Holy_scriptures
👍42
'    ==❀❀❀===❀❀❀==      
              የዕለቱ ጥቅስ
     ==❀❀❀===❀❀❀==
“ሰውን ትዕቢቱ ያዋርደዋል፤ መንፈሱን የሚያዋርድ ግን ክብርን ይቀበላል።”
                 ምሳሌ 29፥23



ወደ ቻናሉ ለመ🀄️🀄️ል፦ @Holy_scriptures
👍32
ቅዱሳት መጻሕፍት
አራቱ ደስታችንን ሊጠብቁ የሚችሉ አመለካከቶች 1. አንድ አሳብ - ፊልጵስዩስ 1 «ሁለት አሳብ ላለው በመንገዱ ሁሉ ለሚወላውል ... አንዳች እንዲያገኝ አይምሰለው» (ያዕ. 1፡8)። ወይንም በጥንት ላቲን ቋንቋ፥ «የመርከቡ ነጂ የሚያርፍበትን ወደብ ካላወቀ የትኛውም ነፋስ አይረዳውም» የሚል ምሳሌ አለ። ለብዙ ክርስቲያኖች በሁኔታዎች አለመሳካት የብስጭት ምክንያት የሚሆነው በ«አንድ አሳብ» ስለማይረጉ…
የቀጠለ...


አራቱ ደስታችንን ሊጠብቁ የሚችሉ አመለካከቶች


2. የሚገዛ አሳብ - ፊልጵስዩስ 2

ይህ ምዕራፍ የሚያተኩረው በሰዎች ላይ ነው፥ መሪ ጥቅሱም «ለወገኔ ይጠቅማል በማለት ወይም በከንቱ ውዳሴ ምክንያት አንድ እንኳ አታድርጉ፥ ነገር ግን እያንዳንዱ ባልንጀራው ከራሱ ይልቅ እንዲሻል በትሕትና ይቁጠር» (2፡3)። በምዕራፍ 1 ላይ ጳውሎስ ክርስቶስን የመጀመሪያው መሻቱ ሲያደርግ፥ በዚህ ምዕራፍ፥ ደግሞ ሌሎችን በሁለተኛ ደረጃ አስቀምጧቸዋል። ይህም የሚያሳየን ራሱን መጨረሻ ማድረጉ ነው! ብዙ ጊዜ በሰዎች ላይ የምንቆጣበት ምክንያት በእኛ አሳብ ስለማይመሩልን ነው። በሕይወት በምንጓዝበት ወቅት እራሳችንን መጀመሪያ ካደረግን፥ እንዲሁም ሌሎችም ራሳቸውን መጀመሪያ ካደረጉ፥ ያንጊዜ በብዙ ነጥቦች ላይ ኃይለኛ ግጭት ይፈጠራል።

አንዲት እናት እና ወንድ ልጇ ወደ ሐኪም ቢሮ ለመሄድ ወደ አሳንሰሩ (ሊፍት) ውስጥ ገቡ። ከሁለተኛው ፎቅ ላይ እንደደረሱም ሌሎች ሰዎች ተጨመሩ። ከእነርሱም መሀል አንዲት ወፍራም ሴት ነበረች። አሳንሰሩም ወደ ላይ መውጣቱን እንደቀጠለ ጸጥታው በወፍራሟ ሴት ጩኸት ደፈረሰ። ወደ ልጁም እናት ዘወር ብላ «ልጅሽ ነከሰኝ እኮ!» አለቻት።

እናትየው በጣም ተሳቀቀች፥ ልጁ ግን ማብራሪያ ነበረው «ፊቴን በቂጧ ስላጣበቀችኝ ነው የነከስኳት» ብሎ አስረዳት።

በአሳንሰሩ ውስጥ የተከሰተው ድርጊት በዓለም ዙሪያ ሁሉ ሲፈፀም የምንመለከተው ነው። ሕዝብ ከሕዝብ፥ መንግሥታት ከመንግሥታት ይነካከሳሉ፥ ምክንያቱም ተፋፍገው ስለሚኖሩ ነው።

ነገር ግን የሚገዛ ትሑት ልብ ያለው ክርስቲያን ሌሎችን ያገለግላል እንጂ ሌላ ሰው እርሱን መጥቶ እንዲያገለግለው አይጠብቅም። ከራሱ ፍላጎትና እቅድ ይልቅ ለሌሎች ምኞት መሟላት ቅድሚያ ይሰጣል። በምዕራፍ 2 ውስጥ በትሑት ልቦናቸው ምሳሌ ሊሆኑን የሚችሉ 4 አስገራሚ ሰዎች እናገኛለን። እነርሱም ኢየሱስ ክርስቶስ (2፡1-11)፥ ጳውሎስ (2፡12-18)፥ ጢሞቴዎስ (2፡19-24) እና አፍሮዲጡን (2፡25-30) ናቸው። እነዚህ ምሳሌዎች «ራሱን ከፍ የሚያደርግ ሁሉ ይዋረዳልና፤ ራሱንም የሚያዋርድ ከፍ ይላል» (ሉቃ. 14፡11) የሚለውን መርሆ ያረጋግጡልናል።


ይቀጥላል...



ምንጭ፦ ዋረን ደብልዩ ዌርዝ ቢ፤ ደስተኛ ሁን፤ የፊልጵስዩስ መልእክት ፤ ገጽ 7-8




ወደ ቻናሉ ለመ🀄️🀄️ል፦ @Holy_scriptures
👍53