ቅዱሳት መጻሕፍት
7.45K subscribers
1.37K photos
61 videos
332 files
808 links
በዚህ ቻናል

👉ቅዱሳት መጻሕፍት ይጠናሉ::
👉መጽሐፍ ቅዱሳዊ ትምህርቶች ይቀርባሉ::
👉 ለቅዱሳት መጽሐፍት ጥናት የሚያግዙ መጻሕፍት ይለቀቃሉ።

⭐️⭐️⭐️⭐️⭐️

@Holy_scriptures
Download Telegram
#የእግዚአብሔር_ቃል_ምን_ይላል?

እ.ኤ.አ 48-50 ዓ.ም ነው ተብሎ በሚገመተው በቤተክርስቲያን ታሪክ የመጀመሪያው የሆነ ጉባኤ በሐዋርያት ሥራ ምዕራፍ 15 ላይ ይገኛል። ጉባኤው የተካሄደበትን ገፊ ምክንያት ከክፍሉ ማየት ይቻላል። ለዛሬ፣ ጉባኤው ከተካሄደ በኋላ የጉባኤውን ውሳኔ ለመግለጽ ከአሕዛብ ወገን ለሆኑት የተላከውን ደብዳቤ ከታች ለጥፈነዋል። ውሳኔው በጣም አስደናቂ እና ለትምህርታችን የሚሆን ብዙ ቁምነገር ስላለበት እዩት እና አስተያየት ስጡበት።

ሐዋርያት 15
¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯
²³ እንዲህም ጽፈው በእነርሱ እጅ ላኩ። ሐዋርያትና ሽማግሌዎች ወንድሞችም በአንጾኪያና በሶርያ በኪልቅያም ለሚኖሩ ከአሕዛብ ወገን ለሆኑ ወንድሞች ሰላምታ ያቀርባሉ።
²⁴ ያላዘዝናቸው ሰዎች ከእኛ ወጥተው፦ ትገረዙ ዘንድና ሕግን ትጠብቁ ዘንድ ይገባችኋል ብለው ልባችሁን እያወኩ በቃል እንዳናወጡአችሁ ስለ ሰማን፥
²⁵-²⁶ ስለ ጌታችን ስለ ኢየሱስ ክርስቶስ ስም ነፍሳቸውን ከሰጡት ከምንወዳቸው ከበርናባስና ከጳውሎስ ጋር የተመረጡትን ሰዎች ወደ እናንተ እንልክ ዘንድ በአንድ ልብ ሆነን ፈቀድን።
²⁷ ራሳቸውም ደግሞ በቃላቸው ያንኑ ይነግሩአችሁ ዘንድ ይሁዳንና ሲላስን ልከናል።
²⁸-²⁹ ለጣዖት ከተሠዋ፥ ከደምም፥ ከታነቀም፥ ከዝሙትም ትርቁ ዘንድ ከዚህ ከሚያስፈልገው በቀር ሌላ ሸክም እንዳንጭንባችሁ እኛና መንፈስ ቅዱስ ፈቅደናልና፤ ከዚህም ሁሉ ራሳችሁን ብትጠብቁ በመልካም ትኖራላችሁ። ጤና ይስጣችሁ።




ወደ ቻናሉ ለመ🀄️🀄️ል፦ @Holy_scriptures
👍8
'    ==❀❀❀===❀❀❀==      
              የዕለቱ ጥቅስ
     ==❀❀❀===❀❀❀==
“እግዚአብሔር ይቀድማችኋልና፥ የእስራኤልም አምላክ ይከተላችኋልና በችኰላ አትወጡም በመኰብለልም አትሄዱም።”
               ኢሳይያስ 52፥12



ወደ ቻናሉ ለመ🀄️🀄️ል፦ @Holy_scriptures
9
ወደ ቻናሉ ለመ🀄️🀄️ል፦ @Holy_scriptures
👍3
feetoch-1.pdf
1.1 MB
👉ርዕስ፦ ከክብር ወደ ክብር
ጸሐፊ፦ ዎችማን ኒ
🗣ትርጉም፦ ዘካርያስ ጥላሁን


ወደ ቻናሉ ለመ🀄️🀄️ል፦ @Holy_scriptures
👍4
'    ==❀❀❀===❀❀❀==      
              የዕለቱ ጥቅስ
     ==❀❀❀===❀❀❀==
“ይህም ብቻ አይደለም፥ ነገር ግን መከራ ትዕግሥትን እንዲያደርግ፥ ትዕግሥትም ፈተናን ፈተናም ተስፋን እንዲያደርግ እያወቅን፥ በመከራችን ደግሞ እንመካለን፤”
                  ሮሜ 5፥3-4


ወደ ቻናሉ ለመ🀄️🀄️ል፦ @Holy_scriptures
6👍2
“ከሥጋ ተለይተን መኖር፣ በጌታም ዘንድ ማደር ደስ ይለናል”


ዳግም የተወለደው፣ የጌታ ፍቅር በልቡ በእውነት የፈሰሰለት፣ የመንፈስ ቅዱስን መገኘት እና የአምላክን ኅብረት የቀመሰ፣ እርሱ ሰው ዘላቂ ደስታ በሥጋዊነት ውስጥ የለውም። ለጊዜው ከጌታ ትምህርት ቢለይ፣ ከቃሉ ትእዛዝ ቢያፈነግጥ፣ ስቶም በክፉዎች ምክር ቢሄድ ወይም በኀጢአተኞች መንገድ ቢቈም፣ በፌዘኞችም ወንበር ቢቀመጥ፣ ወዘተ. ለጊዜው ነው እንጂ፣ በዚያ ለመቆየት ምቾት የለውም። በሥጋ ክፉ ምኞት እና መሻት መኖር፣ በዚያም ተረጋግቶ መቀመጥ አይችልም፤ በዚያ ምድር መከተም አይሆንለትም። ሥፍራው ከዚያ አይደለምና ቤተኝነት አይሰማውም፤ ይከብደዋል፤ ያቃስታል፤ ይቃትታልም።

በእውነት “የሕይወት ውሃ ወንዝ” የሆነውን ኢየሱስ ጠጥቶ የሚያውቅ ሰው፣ ከጌታ ተለይቶ በሥጋ ምድረበዳ ማደር ዘግይቶ አይመቸውም፣ ቆይቶ ይጎረብጠዋል። ከጌታ ተለይቶ በሄደበት መንገድ፣ በዚያ ሲጀምር ደስታን ወይም ተድላን ያገኘ የመሰለው ቢሆን እንኳን ከእንግዲህ ደስ አይለውም፤ ከአሁን በኋላ አይደላውም። ቀድሞ የጣፈጠው ነገር አሁን ይጎመዝዘዋል፤ አሁን ያሳፍረዋል። በዚያ የሚበላው ሽንኩርት በከንፈሩ ሬት ይሆንበታል፤ የሚያላምጠው ከጕሮሮው አልወርድ ይለዋል፤ የዋጠው ውስጡን ይረብሸዋል፤ አይረጋለትም። ምን ያህል ይዘገይ ይሆናል እንጂ፣ የተስፋይቱን አገር ዐስቦ ሳያለቅስ አይቀርም። እንደ ቆሬ ልጆችም፣ “ነፍሴ ወደ ሕያው አምላክ ተጠማች፤ መቼ እደርሳለሁ? የአምላክንስ ፊት መቼ አያለሁ?” ብሎ ይጠይቃል (መዝ. 42፥2)።
ከጌታ ኅብረት ለጊዜው የተለዩትን እያሰብን፣ “ታድያ የጠፉት የመመለሻቸው ጊዜ መች ነው?” ብለን ለምንጠይቅ መልሱ፣ አንዱ እንደ ጴጥሮስ የዶሮውን ጩኸት ሦስት ጊዜ እንደ ሰማ ወዲያው ያለቅሳል፤ ሌላኛው እንደ ዮናስ፣ “በሲዖልም ሆድ ውስጥ” ሆኖ ለመጮኽ፣ የዋጠውም ዓሣ እንዲተፋው ሦስት ቀን ይፈጅበታል፤ ደግሞም ሌላው እንደ እስራኤል የምሬቱ ልቅሶ ከሰማይ ሊሰማ፣ ከፈርዖንም ግዞት ለማምለጥ “የጌታ ኀይል” ይሆንለት ዘንድ አራት መቶ ሠላሳ ዓመት ያልፍበታል። ዋናው ነገር፣ “የጠፋው ልጅ” ምን ያህል ይዘገይ እንደ ሆነ አናውቅም እንጂ፣ ማልቀሱና መጮኹ ግን አይቀርም። ርዳታን ከማግኘቱ በፊት ግን፣ መጮኽ እና ማልቀስ ግድ ይለዋል። ጊዜውን እና ሰዓቱን አናውቅምና፣ እኛ በቤት የቀረን ቤተኞች ስለጠፋው ልጅ ማሰብ ከሆነልን “አቤቱ፤ እባክህ አሁን አድን” የሚለውን ጸሎት እናቅርብ (መዝ. 118፥25)።

የጠፋው ልጅ፣ አስቀድሞ የቀመሰው የጌታ ፍቅር ትዝታው ሲያገረሽበት፣ የተስፋው ናፍቆት ሲበረታበት፣ ያኔ ራሱን ካገኘበት ከባዕድ (ከሥጋዊነት) ምድር ሆኖ፣ “ከሥጋ ተለይተን በስደት መኖር፣ በጌታም ዘንድ ማደር ደስ ይለናል” የሚለውን ተመሳሳይ የናፍቆት ድምፅ ያሰማል (2ኛ ቆሮ. 5፥8)። ከሙታን ሠፈር የተከለውን ድንኳኑን አፈራርሶ፣ ካስማውን ነቅሎ፣ ወደ ብርሃን መንገድ፣ ወደ ተስፋይቱ አገር፣ ወደ ሕያዋን ማኅበር፣ ወደ ጌታም ገበታ ለመድረስ የሚቸኩልበት ቀን ይመጣል። ከድቅድቅ ጨለማ ወደ ብርሃን፣ ከባርነት ወደ ነጻነት ይፈልሳል። ከሞት ወደ ሕይወት ይሮጣል። እንደ ወፍ በርሮ ያመልጣል።



ምንጭ፦ hintset.org



ወደ ቻናሉ ለመ🀄️🀄️ል፦ @Holy_scriptures
👍4
'    ==❀❀❀===❀❀❀==      
              የዕለቱ ጥቅስ
     ==❀❀❀===❀❀❀==
“ቀድሞም የሚያውቁት ሁሉ ከነቢያት ጋር ትንቢት ሲናገር ባዩት ጊዜ ሕዝቡ እርስ በርሳቸው፦ የቂስን ልጅ ያገኘው ምንድር ነው? በውኑ ሳኦል ከነቢያት ወገን ነውን? ተባባሉ።”
             1ኛ ሳሙኤል 10፥11



ወደ ቻናሉ ለመ🀄️🀄️ል፦ @Holy_scriptures
3👍2
#እራሳችንን_እንመርምር

በምን ወይም በማን እንታመን? እንዴታ በእግዚአብሔር እንጂ! ይህን እውነት አምኖ ለመተግበር ቀላል ይመስላል ግን ከባድ እንደሆነ ሁላችንም እናውቀዋለን። ግን በዚህ እውነት ጸንቶ ከመኖር ወጪ ምን ምርጫ አለ? የትኛዎቹስ ልንመካባቸው የከጀልናቸው አዘለቁን?


“ወደ አንቺ የሰበሰብሻቸው በጮኽሽ ጊዜ ይታደጉሽ፤ ንፋስ ግን ይወስዳቸዋል ሽውሽውታም ሁሉን ያስወግዳቸዋል። በእኔ የታመነ ግን ምድሪቱን ይገዛል፥ የተቀደሰውንም ተራራዬን ይወርሳል።”
ኢሳይያስ 57፥13



ወደ ቻናሉ ለመ🀄️🀄️ል፦ @Holy_scriptures
👍61
'    ==❀❀❀===❀❀❀==      
              የዕለቱ ጥቅስ
     ==❀❀❀===❀❀❀==
“አቤቱ፥ አንተ መብራቴ ነህና፤ እግዚአብሔርም ጨለማዬን ያበራል።”
           2ኛ ሳሙኤል 22፥29



ወደ ቻናሉ ለመ🀄️🀄️ል፦ @Holy_scriptures
👍52
ከብሉይ ኪዳን ነቢያት መካከል በነቢዩ ኢሳይያስ ዘመን እንደነበረ የሚነገርለት፣ የትንቢቶቹ ወይም የመልዕክቱ ዋና ትኩረት ደግሞ ከላይ ያሉ መሪዎችን እና አስተዳዳሪዎችን የሆነው የቱ ነው?
Anonymous Quiz
21%
ሀ. ሚልክያስ
28%
ለ. ሆሴዕ
23%
ሐ. ኢዩኤል
23%
መ. ሚክያስ
6%
ሠ. ናሆም
6👍2
'    ==❀❀❀===❀❀❀==      
              የዕለቱ ጥቅስ
     ==❀❀❀===❀❀❀==
“ዓይናቸውም ተከፈተ፥ አወቁትም፤ እርሱም ከእነርሱ ተሰወረ።”
              ሉቃስ 24፥31



ወደ ቻናሉ ለመ🀄️🀄️ል፦ @Holy_scriptures
9
#ከተማ_ወይም_ቦታ_በቅዱሳት_መጻሕፍት


#ራማ፤ ከፍታ ማለት ነው። አንዳንድ ከተማዎች ራማ ተብለዋል፤ ከእነርሱም የታወቀው በገባዖንና በጊብዓ አጠገብ የነበረ ከተማ ነው፤ ኢያሱ 18፥25፤ መሳ. 19፥13። ይህ የዲቦራ አገር ነበር፤ መሳ. 4፥5። ኤርምያስ ታስሮ ከኢየሩሳሌም ከተወሰደ በኋላ ከራማ ተለቀቀ። ግን ይህ ራማ የትኛው እንደሆነ አልታወቀም፤ ኤር. 40፥1። ራሔል በራማ አጠገብ ተቀበረች፤ ስለዚህም የሐዘን ቦታ ሆነ፤ ኤር. 31፥15፤ ማቴ. 2፥18።

ምንጭ፦ የመጽሐፍ ቅዱስ መዝገበ ቃላት፤ ገጽ 67


ወደ ቻናሉ ለመ🀄️🀄️ል፦ @Holy_scriptures
👍1
'    ==❀❀❀===❀❀❀==      
              የዕለቱ ጥቅስ
     ==❀❀❀===❀❀❀==
“አሁን ግን ወንድሞች ከሚባሉት አንዱ ሴሰኛ ወይም ገንዘብን የሚመኝ ወይም ጣዖትን የሚያመልክ ወይም ተሳዳቢ ወይም ሰካር ወይም ነጣቂ ቢሆን ከእርሱ ጋር እንዳትተባበሩ እጽፍላችኋለሁ፤ እንደነዚህ ካለው ጋር መብል እንኳን አትብሉ።”
                1ኛ ቆሮንቶስ 5፥11



ወደ ቻናሉ ለመ🀄️🀄️ል፦ @Holy_scriptures
👍73
'    ==❀❀❀===❀❀❀==      
              የዕለቱ ጥቅስ
     ==❀❀❀===❀❀❀==
“ለኵነኔ አልልም፤ በአንድነት ለመሞትና በአንድነት ለመኖር በልባችን እንዳላችሁ አስቀድሜ ብዬአለሁና።”
               2ኛ ቆሮ 7፥3



ወደ ቻናሉ ለመ🀄️🀄️ል፦ @Holy_scriptures
👍31😁1
ወደ ቻናሉ ለመ🀄️🀄️ል፦ @Holy_scriptures
👍41
concord-ha-no-cr.pdf
2.7 MB
👉ርዕስ፦ የመጽሐፍ ቅዱስ ቃል ማውጫ
ጸሐፊ፦ ሚ/ር ሮበርት ሪቪ



ወደ ቻናሉ ለመ🀄️🀄️ል፦ @Holy_scriptures
👍4
'    ==❀❀❀===❀❀❀==      
              የዕለቱ ጥቅስ
     ==❀❀❀===❀❀❀==
“በውኑ እኔን አትፈሩምን? ከፊቴስ አትደነግጡምን? ይላል እግዚአብሔር፤ እንዳያልፍ አሸዋን በዘላለም ትእዛዝ ለባሕር ዳርቻ አድርጌአለሁ፤ ሞገዱም ቢናወጥ አያሸንፍም፥ ቢጮኽም አያልፍበትም።”
                   ኤርምያስ 5፥22



ወደ ቻናሉ ለመ🀄️🀄️ል፦ @Holy_scriptures
👍61
ከትንሳኤ ማግስት፡ መጽሐፍ ቅዱሳዊ መንፈሳዊነት

ቤተክርስቲያን ስላለችበት ሁኔታ እንዲሁም በውስጧ እየሆኑ ስለሉት ስብራቶችና ግራ የሚያጋቡ ነገሮች ስታስቡ “ኧረ መንፈሳዊነት ምን ማለት ነው?” የሚል ጥያቄ አይፈጠርባችሁም? ክርስቶስ የሞተውና የተነሳው “ለዚህ ነው?” አያስብላችሁም? ወይም ይህንን ጥያቄ እንደገና አንስተን እንደገና መመለስ እንዳለብን የዘነጋነው የቤት ሥራ አይመስላችሁም? ስለ ችግሩ እየተወያየንና አስተያየቶቻችንም እየቸርን የቤት-ሥራችን ግን ተቆለለ አይደል? እኔ ተቆልሎብኛል። ልክ የትዳር ሕይወት ከሠርግ ማግስት እንዲጀምር መጽሐፍ ቅዱሳዊውም “እውነተኛ ሕይወት” [ያ ጳውሎስ ለጢሞቴዎስ እየደጋገመ እንደ አዝማች ያሳሰበው ጉዳይ] እንዲሁ ከትንሳኤ ማግስት ይመስለኛል። መቼም ሞቱንና ትንሳኤውን አክብረን ስናበቃ ራሳችንን ማሳሰብ ያለብን ብዙ ነገሮች እንዳሉን ይሰማኛል። ከእነዚህ አንዱና ዋነኛ ግን “መንፈሳዊነት ምን ማለት ነው?” የሚለው መሆን አለበት። ይህ ወቅት ሞቱንና ትንሳኤውን ይዘን ሳናሰልስ ወደ ሥራ የምንሔድበት እንጂ፤ ወደ ሌላ ርእሰ-ጉዳይ የምንሸጋገርበት እንዳልሆነ ሁላችንም እናውቃለን። ይህ የሰሞኑ የመስቀልና የትንሳኤ ጉዳይ፣ ሌሎች አንገባጋቢ ጉዳዮቻችንን ወደ ጎን የሚያደርግ ሳይሆን፤ በእያንዳንዱ ጉዳዮቻችን ውስጥ ግን እንደ ጅማት ሊዘረጋ፤ እንደ ደም ስር ሊቀጣጠል፤ እንደ ደም በመላ የክርስትና ሕይወታችንና የቤተክርስቲያን ጉዳዮቻችንን ሊሰራጭ ይገባል። ጭንቅላት የሰውነት ብልቶች ተግባሮቻቸውን እንዲያከናውኑ ሁሉን እንደሚቆጣጠር፣ ይህ የሰሞኑ እውነታ የተግዳሮታችን ሁሉ ዓውድ ይሆን ዘንድ ልባዊ ጸሎቴ ነው። ስለዚህ መንፈሳዊ ሕይወት የመስቀልና የትንሳኤውን እውነታ የሚያንጸባርቅ መሆን አለበት። እንዲህ ከሆነ መንፈሳዊ ህይወት መስቀሉንና ክርስቶስን እንዲሁም በመስቀሉ ሥራ ላይ የተሳተፉት ስሉስ መለኮታዊ አካላትን የሚገልጥ መሆን አለበት። ትዝ አይላችሁም በቆሮንቶስ የነበረው የጸጋ-ሥጦታን አጠቃቀም ያለማወቅ ችግር? ምክኒያቱ? ስሉሱን አምላክ ያለማወቅ ችግር እንደሆነ ጽፎልናል “ስለ መንፈሳዊ ነገርም፥ ወንድሞች ሆይ፥ ታውቁ ዘንድ እወዳለሁ…መንፈስ አንድ ነው…ጌታም አንድ ነው…እግዚኢብሔር [አብ] አንድ ነው” (1 ቆሮ 12፥1-6). ” መንፈሳዊ ስጦታ የእግዚአብሔርን ክብርና ማንነት የሚገልጥ ነው እንጂ፣ ይለናል ጳውሎስ፤ የራሳችን እውነታ የምገልጥበት መንፈሳዊ-ልዕልና አይደለም። ይህም ከመንፈሳዊ ህይወት ጀርባ ጥልቅ ነገረ መለኮታዊ እውነታ አለ ማለት ነው፡፡ እናም አሁን የሰነበትንበት መንፈስ (የሰሞኑ መስቀል ተኮር ስብከት፤ መዝሙር፤ ጸሎት ምሥጋና፤ ይህ በትንሳኤው ሀይል ላይ የተደገፈ የሰሞኑ መታመናችን፤ ይህ ክርስቶስ ራሱን ለብዙዎች እስኪሰጥ ድረስ የወደደበት መውደድ ላይ የተመሰረተው ፍቅራችን) እንዴት ሳያቋርጥ ይቀጥል የሚለው ጥያቄ መታሰብ ያለበት ነው። መቼም ብዙ የሚያሳስበኝና የምጸልይበት ጉዳይ የዚህ የመንፈሳዊነት ጉዳይ ነው። “መንፈሳዊነት ምን ማለት ነው?” በየግል ሕይወታችን ውስጥ ለሚንጸባረቀው እንዲሁም በህብረት በየአብያተ-ክርስቲያናት በየእሑዱ ለምናካሒደው ስብሰባ ምን ፋይዳ አለው? ይህ ጥያቄ በአንድ ወገን በጣም ቀላል የሆነ፣ በክርስቶስ አምኖ የዳነ ሁሉ የቀመሰው እውነታ ነው። ነገር ግን በዚያው ልክ ጥልቅም ጥያቄ ነው። መንፈሳዊነት ትናንት ወደ መንግሥቱ የተጨመረ ሕጻን ሊዋኝበት የሚችል ገንዳ ነገር ግን ደግሞ ታላላቅ መርከቦችንም የሚያስተናግድ ባሕር ነው። በሕይወታችን የተለማመድነውን በቃላት ማስቀመጥ አንዳንዴ ትልቅ ጥበብን ይጠይቃል። ለምሳሌ ያህል የገላትያ ቤተክርስቲያን “ይህን ብቻ ከእናንተ እንድማር እወዳለሁ፤ [እንዴት] መንፈስን ተቀበላችሁን? (ገላ 3:2)” ሲል እነዚህ ሰዎች ጥልቅ የወንጌልን እውነት ሳይረዱ እንኳ ሕያው የሆነው መንፈስ ትልቅ መንፈሳዊ ሐይልን እንዲለማመዱ አብቅቷቸዋል። እዚህ ጋር ማብቃት ግን ትልቅ አደጋ ነው። ብስለት ባለው በጥበብ ቃል ይህንን ልምምድ መጽሐፍ ቅዱሳዊና ነገረ-መለኮታዊ በሆነ መንገድ መግለጥ እስካልቻልን ሲወሰድብንም፤ ከዚያም ስተን ስንወጣም (በሌላ መንፈስ) አናውቅም። ስለዚህ “መንፈሳዊነት ምንድር ነው?” የሚለውን አስፍተንና አጥልቀን እንደገና ማሰብ ያለብን ጉዳይ ይመስለኛል።

ይቀጥላል. . .


ምንጭ፦ semayawithought.org


ወደ ቻናሉ ለመ🀄️🀄️ል፦ @Holy_scriptures
👍84
'    ==❀❀❀===❀❀❀==      
              የዕለቱ ጥቅስ
     ==❀❀❀===❀❀❀==
“ስለዚህ እስራኤል ብቻውን በሰላም ይኖራል፤ የሰማያት ጠል በሚወርድበት፣ እህልና የወይን ጠጅ ባለበት ምድር፣ የያዕቆብ ምንጭ የሚነካው የለም።”
       ዘዳግም 33፥28 (አዲሱ መ.ት)



ወደ ቻናሉ ለመ🀄️🀄️ል፦ @Holy_scriptures
👍52