ቅዱሳት መጻሕፍት
7.46K subscribers
1.37K photos
61 videos
332 files
808 links
በዚህ ቻናል

👉ቅዱሳት መጻሕፍት ይጠናሉ::
👉መጽሐፍ ቅዱሳዊ ትምህርቶች ይቀርባሉ::
👉 ለቅዱሳት መጽሐፍት ጥናት የሚያግዙ መጻሕፍት ይለቀቃሉ።

⭐️⭐️⭐️⭐️⭐️

@Holy_scriptures
Download Telegram
ዳግማዊ ትንሣኤ ምንድነው?


ከትንሣኤ ዕለት ቀጥሎ ያለው ሰንበት #ዳግማዊ_ትንሳኤ በመባል ይታወቃል። ይህ እለት በዚህ ስም ሊጠራ የቻለበት ምክንያት ጌታችን አምላካችንና መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በዋናው የትንሣኤ ቀን በእለተ ፋሲካ ለቅዱሳን ሐዋርያት በዝግ በር ገብቶ በመካከላቸው ተገኝቶ «ሰላም ለሁላችሁ ይሁን» ብሎ ትንሣኤውን ሲገልጽላቸው ሐዋርያው ቶማስ አልተገኘም ነበር፡፡እናም በኋላ ከሔደበት ሲመጣ ወንድሞቹ ጌታችን መነሣቱን እንደተገለጸላቸው በደስታ ሲነግሩት ቅር ተሰኝቶ «በኋላ እናንተ ዐየን ብላችሁ ልትመሰክሩ፣ ልታስተምሩ፣ እኔ ግን 'ሰምቼአለሁ' ብዬ ልመሰክር፣ ላስተምር? አይሆንም እኔም ካላየሁ አላምንም» በማለቱ የሰውን ሁሉ፤ ይልቁንም የመረጣቸው ወዳጆቹን የልብ ሐሳብ ምክንያቱን ለይቶ የሚያውቀው፣ ቸርነቱ ወሰን የሌለው የባሕርይ አምላክ መድኃኒዓለም ክርስቶስ ልክ እንደመጀመሪያው ትንሣኤ ዕለት ሐዋርያት በአንድነት በተዘጋ ቤት እንዳሉ በሩን ሳይከፍት ገብቶ «ሰላም ለሁላችን ይሁን» በማለት በመካከላቸው ቆመ፤ ቶማስንም «ያመንክ እንጂ ተጠራጣሪ አትሁን እነሆ የተቸነከሩ እጆቼንና እግሮቼን፣ የተወጋ ጐኔንም ናና እይ» ብሎ አሳየው፡፡ እርሱም ምልክቱን በማየቱ በመዳሰሱ ትንሣኤውንና አምላክነቱን እንደፍላጎቱ በመረዳቱ «ጌታዬ አምላኬ ብሎ መስክሮ» አመነ፡፡

👉እንግዲህ ይህ የትንሣኤው ምስጢር ለሁለተኛ ጊዜ ለሐዋርያት የተገለጠበት ዕለት ስለሆነ «ዳግም ትንሣኤ» ተብሎ ሰንበቱ ይጠራበታል፤ ይከበርበታል፡፡ ዮሐ. 20፥24-30



ምንጭ፦ ከፌስቡክ መንደር



ወደ ቻናሉ ለመ🀄️🀄️ል፦ @Holy_scriptures
👍101👏1
'    ==❀❀❀===❀❀❀==      
              የዕለቱ ጥቅስ
     ==❀❀❀===❀❀❀==
“የእግዚአብሔር ቃል ቅን ነውና ሥራውም ሁሉ በእምነት ነውና።”
               መዝሙር 33፥4



ወደ ቻናሉ ለመ🀄️🀄️ል፦ @Holy_scriptures
6🔥1
"ጸሎት የሰውን ፈቃድ በሰማይ ለመፈፀም ሳይሆን ዳሩ ግን የእግዚአብሔርን ፈቃድ በምድር ላይ ለመፈፀም የሚረዳ ኃያል መሣሪያ ነው::"

ሮበርት ሎው



ወደ ቻናሉ ለመ🀄️🀄️ል፦ @Holy_scriptures
5👍2🥰2
'    ==❀❀❀===❀❀❀==      
              የዕለቱ ጥቅስ
     ==❀❀❀===❀❀❀==
“እግዚአብሔር በተስፋ ለሚጠብቁት ለምትሻውም ነፍስ መልካም ነው።”
                 ሰቆ. 3፥25



ወደ ቻናሉ ለመ🀄️🀄️ል፦ @Holy_scriptures
9🥰1
#የሮሜ_መልእክት_ጥናት


ሮሜ 9
¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯
¹⁹ እንግዲህ ስለ ምን እስከ አሁን ድረስ ይነቅፋል? ፈቃዱንስ የሚቃወም ማን ነው? ትለኝ ይሆናል።
²⁰ ነገር ግን፥ አንተ ሰው ሆይ፥ ለእግዚአብሔር የምትመልስ ማን ነህ? ሥራ ሠሪውን፦ ስለ ምን እንዲህ አድርገህ ሠራኸኝ ይለዋልን?
²¹ ወይም ሸክላ ሠሪ ከአንዱ ጭቃ ክፍል አንዱን ዕቃ ለክብር አንዱንም ለውርደት ሊሠራ በጭቃ ላይ ሥልጣን የለውምን?
²²-²³ ነገር ግን እግዚአብሔር ቍጣውን ሊያሳይ ኃይሉንም ሊገልጥ ወዶ፥ አስቀድሞ ለክብር ባዘጋጃቸው በምሕረት ዕቃዎች ላይ የክብሩን ባለ ጠግነት ይገልጥ ዘንድ፥ ለጥፋት የተዘጋጁትን የቁጣ ዕቃዎች በብዙ ትዕግሥት ከቻለ፥ እንዴት ነው?
²⁴ የምሕረቱ ዕቃዎችም ከአይሁድ ብቻ አይደሉም፥ ነገር ግን ከአሕዛብ ደግሞ የጠራን እኛ ነን።
²⁵ እንዲሁ ደግሞ በሆሴዕ፦ ሕዝቤ ያልሆነውን ሕዝቤ ብዬ፥ ያልተወደደችውንም የተወደደችው ብዬ እጠራለሁ፤
²⁶ እናንተ ሕዝቤ አይደላችሁም በተባለላቸውም ስፍራ በዚያ የሕያው እግዚአብሔር ልጆች ተብለው ይጠራሉ ይላል።
²⁷-²⁸ ኢሳይያስም፦ የእስራኤል ልጆች ቁጥር ምንም እንደ ባሕር አሸዋ ቢሆን ቅሬታው ይድናል፤ ጌታ ነገሩን ፈጽሞና ቆርጦ በምድር ላይ ያደርገዋልና ብሎ ስለ እስራኤል ይጮኻል።
²⁹ ኢሳይያስም እንደዚሁ፦ ጌታ ፀባዖት ዘር ባላስቀረልን እንደ ሰዶም በሆንን ገሞራንም በመሰልን ነበር ብሎ አስቀድሞ ተናገረ።


ሮሜ 9 (አዲሱ መ.ት)
¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯
¹⁹ ከእናንተ አንዱ፣ “ታዲያ እንደዚህ ከሆነ እግዚአብሔር እስከ አሁን ለምን ይወቅሰናል? ምክንያቱም ፈቃዱን ሊቋቋም የሚችል ማን አለ?” ይለኝ ይሆናል።
²⁰ ነገር ግን ለእግዚአብሔር መልስ የምትሰጥ አንተ ማን ነህ? “ሥራ ሠሪውን፣ ‘ለምን እንዲህ ሠራኸኝ?’ ይለዋልን?”
²¹ ሸክላ ሠሪ፣ ከሚሠራው ጭቃ፣ አንዳንዱን ሸክላ ለክብር፣ ሌላውን ደግሞ ለተራ አገልግሎት የማድረግ መብት የለውምን?
²² እግዚአብሔር ቊጣውን ለማሳየት፣ ኀይሉንም ለማሳወቅ ፈልጎ የቍጣው መግለጫ የሆኑትን፣ ለጥፋትም የተዘጋጁትን እጅግ ታግሦ ቢሆንሳ!
²³ አስቀድሞ ለክብር ላዘጋጃቸው፣ የምሕረቱም መግለጫዎች ለሆኑት፣ የክብሩ ባለጠግነት እንዲታወቅ ይህን አድርጎ እንደሆነስ?
²⁴ የጠራው ከአይሁድ ወገን ብቻ ሳይሆን ከአሕዛብ ወገን የሆነውን እኛን እንኳ ሳይቀር አይደለምን?
²⁵ በሆሴዕ እንዲህ እንደሚል፤ “ሕዝቤ ያልሆኑትን፣ ‘ሕዝቤ’ ብዬ እጠራቸዋለሁ”፤ ያልተወደደችውንም ‘የተወደደችው’ ብዬ እጠራለሁ።
²⁶ ደግሞም፣ “ ‘ሕዝቤ አይደላችሁም’፤ ተብሎ በተነገራቸው በዚያ ቦታ፣ ‘የሕያው እግዚአብሔር ልጆች’ ተብለው ይጠራሉ።”
²⁷ ኢሳይያስም ስለ እስራኤል እንዲህ ሲል ይጮኻል፤ “የእስራኤል ልጆች ቊጥር በባሕር ዳር እንዳለ አሸዋ ቢሆንም፣ ትሩፉ ብቻ ይድናል።
²⁸ ጌታ ፍርዱን በምድር ላይ፣ በፍጥነትና ለመጨረሻ ጊዜ ይፈጽማልና።”
²⁹ ይኸውም ቀደም ሲል ኢሳይያስ እንደ ተናገረው ነው፤ “የሰራዊት ጌታ፣ ዘር ባያስቀርልን ኖሮ፣ እንደ ሰዶም በሆን ነበር፤ ገሞራንም በመሰልን ነበር።”


ሮሜ 9 (ሕያው ቃል)
¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯
¹⁹ ምናልባት ከእናንተ አንዳንዶቻችሁ ፥ «የእግዚአብሔርን ፈቃድ መቃወም ካልተቻለ ፥ ታዲያ እግዚአብሔር ሰዎችን ለምን በክፉ ሥራቸው ተጠያቂ ያደርጋቸዋል?» ትሉ ይሆናል።
²⁰ ለዚህ ጥያቄ እኔ ያለኝ መልስ፥ «እንዲህ ያለውን ቃል ለእግዚአብሔር መመለስ የምትችል ለመሆኑ አንተ ማን ነህ? የሸክላ ዕቃ፥ ሠሪውን ባለሙያ 'ለምን በዚህ ዓይነት ቅርጽ ሠራኸኝ' ሊለው ይችላልን?
²¹ ወይስ የሸክላ ሥራ ባለሙያው ከአንዱ የሸክላ አፈር ላይ አንሥቶ፥ አንዱን ሸልሞ ሸላልሞ በክብር የሚቀመጥ ዕቃ፥ ሌላውን ግን በክብር ሊይዙት ለማይገባ አገልግሎት የሚውል ተራ ዕቃ አድርጎ ለመሥራት መብት የለውምን?
²² ጌታ እግዚአብሔርስ እስከ አሁን ድረስ የታገሣቸውን ፥ ለጥፋት የተመደቡትን ሰዎች ቁጣውንና ኃይሉን ሊገልጽባቸው ሙሉ ሥልጣን የለውምን?
²³¯²⁴ እነርሱን የታገሣቸው ፥ ከአይሁድም ሆነ ከአሕዛብ ወገን መርጦ ለክብሩ ላዘጋጀን ለእኛ፥ ምሕረቱንና የክብሩን ባለጠግነት ሊያሳይ ስለፈለገ ነው።»
²⁵ ነቢዩ ሆሴዕ ፥ «ሕዝቤ ያልነበረውን 'ሕዝቤ' ብዬ እጠራዋለሁ። ያልተወደደውንም ሕዝብ ፥ 'የተወደደ' እለዋለሁ።
²⁶ 'ሕዝቤ አይደላችሁም' በተባሉበት ሥፍራ ፥ 'የሕያው እግዚአብሔር ልጆች' ተብለው ይጠራሉ» ብሏል።
²⁷ ነቢዩ ኢሳይያስም ፥ «የእሥራኤል ሕዝብ ብዛት እንደ ባሕር አሸዋ ቢሆን እንኳ የሚድኑት ጥቂቶች ብቻ ናቸው።
²⁸ ጌታ በፍጥነት በዓለም ላይ ፍርዱን ይሰጣል» ሲል ተናግሯል።
²⁹ በሌላም ቦታ ይኸው ነቢይ ፥ «ጌታ እግዚአብሔር ለትውልዳችን ዘር አስቀርቶ ምሕረቱን ባያሳይ ኖሮ ፥ እኛም አይሁዶች እንደ ሰዶምና ገሞራ ሰዎች በጠፋን ነበር»




ወደ ቻናሉ ለመ🀄️🀄️ል፦ @Holy_scriptures
2👍2
'    ==❀❀❀===❀❀❀==      
              የዕለቱ ጥቅስ
     ==❀❀❀===❀❀❀==
“የእግዚአብሔርንም መንግሥት እንዲሰብኩና ድውዮችን እንዲፈውሱ ላካቸው፥”
               ሉቃስ 9፥2


ወደ ቻናሉ ለመ🀄️🀄️ል፦ @Holy_scriptures
6
#የእግዚአብሔር_ቃል_ምን_ይላል?

እ.ኤ.አ 48-50 ዓ.ም ነው ተብሎ በሚገመተው በቤተክርስቲያን ታሪክ የመጀመሪያው የሆነ ጉባኤ በሐዋርያት ሥራ ምዕራፍ 15 ላይ ይገኛል። ጉባኤው የተካሄደበትን ገፊ ምክንያት ከክፍሉ ማየት ይቻላል። ለዛሬ፣ ጉባኤው ከተካሄደ በኋላ የጉባኤውን ውሳኔ ለመግለጽ ከአሕዛብ ወገን ለሆኑት የተላከውን ደብዳቤ ከታች ለጥፈነዋል። ውሳኔው በጣም አስደናቂ እና ለትምህርታችን የሚሆን ብዙ ቁምነገር ስላለበት እዩት እና አስተያየት ስጡበት።

ሐዋርያት 15
¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯
²³ እንዲህም ጽፈው በእነርሱ እጅ ላኩ። ሐዋርያትና ሽማግሌዎች ወንድሞችም በአንጾኪያና በሶርያ በኪልቅያም ለሚኖሩ ከአሕዛብ ወገን ለሆኑ ወንድሞች ሰላምታ ያቀርባሉ።
²⁴ ያላዘዝናቸው ሰዎች ከእኛ ወጥተው፦ ትገረዙ ዘንድና ሕግን ትጠብቁ ዘንድ ይገባችኋል ብለው ልባችሁን እያወኩ በቃል እንዳናወጡአችሁ ስለ ሰማን፥
²⁵-²⁶ ስለ ጌታችን ስለ ኢየሱስ ክርስቶስ ስም ነፍሳቸውን ከሰጡት ከምንወዳቸው ከበርናባስና ከጳውሎስ ጋር የተመረጡትን ሰዎች ወደ እናንተ እንልክ ዘንድ በአንድ ልብ ሆነን ፈቀድን።
²⁷ ራሳቸውም ደግሞ በቃላቸው ያንኑ ይነግሩአችሁ ዘንድ ይሁዳንና ሲላስን ልከናል።
²⁸-²⁹ ለጣዖት ከተሠዋ፥ ከደምም፥ ከታነቀም፥ ከዝሙትም ትርቁ ዘንድ ከዚህ ከሚያስፈልገው በቀር ሌላ ሸክም እንዳንጭንባችሁ እኛና መንፈስ ቅዱስ ፈቅደናልና፤ ከዚህም ሁሉ ራሳችሁን ብትጠብቁ በመልካም ትኖራላችሁ። ጤና ይስጣችሁ።




ወደ ቻናሉ ለመ🀄️🀄️ል፦ @Holy_scriptures
👍8
'    ==❀❀❀===❀❀❀==      
              የዕለቱ ጥቅስ
     ==❀❀❀===❀❀❀==
“እግዚአብሔር ይቀድማችኋልና፥ የእስራኤልም አምላክ ይከተላችኋልና በችኰላ አትወጡም በመኰብለልም አትሄዱም።”
               ኢሳይያስ 52፥12



ወደ ቻናሉ ለመ🀄️🀄️ል፦ @Holy_scriptures
9
ወደ ቻናሉ ለመ🀄️🀄️ል፦ @Holy_scriptures
👍3
feetoch-1.pdf
1.1 MB
👉ርዕስ፦ ከክብር ወደ ክብር
ጸሐፊ፦ ዎችማን ኒ
🗣ትርጉም፦ ዘካርያስ ጥላሁን


ወደ ቻናሉ ለመ🀄️🀄️ል፦ @Holy_scriptures
👍4
'    ==❀❀❀===❀❀❀==      
              የዕለቱ ጥቅስ
     ==❀❀❀===❀❀❀==
“ይህም ብቻ አይደለም፥ ነገር ግን መከራ ትዕግሥትን እንዲያደርግ፥ ትዕግሥትም ፈተናን ፈተናም ተስፋን እንዲያደርግ እያወቅን፥ በመከራችን ደግሞ እንመካለን፤”
                  ሮሜ 5፥3-4


ወደ ቻናሉ ለመ🀄️🀄️ል፦ @Holy_scriptures
6👍2
“ከሥጋ ተለይተን መኖር፣ በጌታም ዘንድ ማደር ደስ ይለናል”


ዳግም የተወለደው፣ የጌታ ፍቅር በልቡ በእውነት የፈሰሰለት፣ የመንፈስ ቅዱስን መገኘት እና የአምላክን ኅብረት የቀመሰ፣ እርሱ ሰው ዘላቂ ደስታ በሥጋዊነት ውስጥ የለውም። ለጊዜው ከጌታ ትምህርት ቢለይ፣ ከቃሉ ትእዛዝ ቢያፈነግጥ፣ ስቶም በክፉዎች ምክር ቢሄድ ወይም በኀጢአተኞች መንገድ ቢቈም፣ በፌዘኞችም ወንበር ቢቀመጥ፣ ወዘተ. ለጊዜው ነው እንጂ፣ በዚያ ለመቆየት ምቾት የለውም። በሥጋ ክፉ ምኞት እና መሻት መኖር፣ በዚያም ተረጋግቶ መቀመጥ አይችልም፤ በዚያ ምድር መከተም አይሆንለትም። ሥፍራው ከዚያ አይደለምና ቤተኝነት አይሰማውም፤ ይከብደዋል፤ ያቃስታል፤ ይቃትታልም።

በእውነት “የሕይወት ውሃ ወንዝ” የሆነውን ኢየሱስ ጠጥቶ የሚያውቅ ሰው፣ ከጌታ ተለይቶ በሥጋ ምድረበዳ ማደር ዘግይቶ አይመቸውም፣ ቆይቶ ይጎረብጠዋል። ከጌታ ተለይቶ በሄደበት መንገድ፣ በዚያ ሲጀምር ደስታን ወይም ተድላን ያገኘ የመሰለው ቢሆን እንኳን ከእንግዲህ ደስ አይለውም፤ ከአሁን በኋላ አይደላውም። ቀድሞ የጣፈጠው ነገር አሁን ይጎመዝዘዋል፤ አሁን ያሳፍረዋል። በዚያ የሚበላው ሽንኩርት በከንፈሩ ሬት ይሆንበታል፤ የሚያላምጠው ከጕሮሮው አልወርድ ይለዋል፤ የዋጠው ውስጡን ይረብሸዋል፤ አይረጋለትም። ምን ያህል ይዘገይ ይሆናል እንጂ፣ የተስፋይቱን አገር ዐስቦ ሳያለቅስ አይቀርም። እንደ ቆሬ ልጆችም፣ “ነፍሴ ወደ ሕያው አምላክ ተጠማች፤ መቼ እደርሳለሁ? የአምላክንስ ፊት መቼ አያለሁ?” ብሎ ይጠይቃል (መዝ. 42፥2)።
ከጌታ ኅብረት ለጊዜው የተለዩትን እያሰብን፣ “ታድያ የጠፉት የመመለሻቸው ጊዜ መች ነው?” ብለን ለምንጠይቅ መልሱ፣ አንዱ እንደ ጴጥሮስ የዶሮውን ጩኸት ሦስት ጊዜ እንደ ሰማ ወዲያው ያለቅሳል፤ ሌላኛው እንደ ዮናስ፣ “በሲዖልም ሆድ ውስጥ” ሆኖ ለመጮኽ፣ የዋጠውም ዓሣ እንዲተፋው ሦስት ቀን ይፈጅበታል፤ ደግሞም ሌላው እንደ እስራኤል የምሬቱ ልቅሶ ከሰማይ ሊሰማ፣ ከፈርዖንም ግዞት ለማምለጥ “የጌታ ኀይል” ይሆንለት ዘንድ አራት መቶ ሠላሳ ዓመት ያልፍበታል። ዋናው ነገር፣ “የጠፋው ልጅ” ምን ያህል ይዘገይ እንደ ሆነ አናውቅም እንጂ፣ ማልቀሱና መጮኹ ግን አይቀርም። ርዳታን ከማግኘቱ በፊት ግን፣ መጮኽ እና ማልቀስ ግድ ይለዋል። ጊዜውን እና ሰዓቱን አናውቅምና፣ እኛ በቤት የቀረን ቤተኞች ስለጠፋው ልጅ ማሰብ ከሆነልን “አቤቱ፤ እባክህ አሁን አድን” የሚለውን ጸሎት እናቅርብ (መዝ. 118፥25)።

የጠፋው ልጅ፣ አስቀድሞ የቀመሰው የጌታ ፍቅር ትዝታው ሲያገረሽበት፣ የተስፋው ናፍቆት ሲበረታበት፣ ያኔ ራሱን ካገኘበት ከባዕድ (ከሥጋዊነት) ምድር ሆኖ፣ “ከሥጋ ተለይተን በስደት መኖር፣ በጌታም ዘንድ ማደር ደስ ይለናል” የሚለውን ተመሳሳይ የናፍቆት ድምፅ ያሰማል (2ኛ ቆሮ. 5፥8)። ከሙታን ሠፈር የተከለውን ድንኳኑን አፈራርሶ፣ ካስማውን ነቅሎ፣ ወደ ብርሃን መንገድ፣ ወደ ተስፋይቱ አገር፣ ወደ ሕያዋን ማኅበር፣ ወደ ጌታም ገበታ ለመድረስ የሚቸኩልበት ቀን ይመጣል። ከድቅድቅ ጨለማ ወደ ብርሃን፣ ከባርነት ወደ ነጻነት ይፈልሳል። ከሞት ወደ ሕይወት ይሮጣል። እንደ ወፍ በርሮ ያመልጣል።



ምንጭ፦ hintset.org



ወደ ቻናሉ ለመ🀄️🀄️ል፦ @Holy_scriptures
👍4
'    ==❀❀❀===❀❀❀==      
              የዕለቱ ጥቅስ
     ==❀❀❀===❀❀❀==
“ቀድሞም የሚያውቁት ሁሉ ከነቢያት ጋር ትንቢት ሲናገር ባዩት ጊዜ ሕዝቡ እርስ በርሳቸው፦ የቂስን ልጅ ያገኘው ምንድር ነው? በውኑ ሳኦል ከነቢያት ወገን ነውን? ተባባሉ።”
             1ኛ ሳሙኤል 10፥11



ወደ ቻናሉ ለመ🀄️🀄️ል፦ @Holy_scriptures
3👍2
#እራሳችንን_እንመርምር

በምን ወይም በማን እንታመን? እንዴታ በእግዚአብሔር እንጂ! ይህን እውነት አምኖ ለመተግበር ቀላል ይመስላል ግን ከባድ እንደሆነ ሁላችንም እናውቀዋለን። ግን በዚህ እውነት ጸንቶ ከመኖር ወጪ ምን ምርጫ አለ? የትኛዎቹስ ልንመካባቸው የከጀልናቸው አዘለቁን?


“ወደ አንቺ የሰበሰብሻቸው በጮኽሽ ጊዜ ይታደጉሽ፤ ንፋስ ግን ይወስዳቸዋል ሽውሽውታም ሁሉን ያስወግዳቸዋል። በእኔ የታመነ ግን ምድሪቱን ይገዛል፥ የተቀደሰውንም ተራራዬን ይወርሳል።”
ኢሳይያስ 57፥13



ወደ ቻናሉ ለመ🀄️🀄️ል፦ @Holy_scriptures
👍61
'    ==❀❀❀===❀❀❀==      
              የዕለቱ ጥቅስ
     ==❀❀❀===❀❀❀==
“አቤቱ፥ አንተ መብራቴ ነህና፤ እግዚአብሔርም ጨለማዬን ያበራል።”
           2ኛ ሳሙኤል 22፥29



ወደ ቻናሉ ለመ🀄️🀄️ል፦ @Holy_scriptures
👍52
ከብሉይ ኪዳን ነቢያት መካከል በነቢዩ ኢሳይያስ ዘመን እንደነበረ የሚነገርለት፣ የትንቢቶቹ ወይም የመልዕክቱ ዋና ትኩረት ደግሞ ከላይ ያሉ መሪዎችን እና አስተዳዳሪዎችን የሆነው የቱ ነው?
Anonymous Quiz
21%
ሀ. ሚልክያስ
28%
ለ. ሆሴዕ
23%
ሐ. ኢዩኤል
23%
መ. ሚክያስ
6%
ሠ. ናሆም
6👍2
'    ==❀❀❀===❀❀❀==      
              የዕለቱ ጥቅስ
     ==❀❀❀===❀❀❀==
“ዓይናቸውም ተከፈተ፥ አወቁትም፤ እርሱም ከእነርሱ ተሰወረ።”
              ሉቃስ 24፥31



ወደ ቻናሉ ለመ🀄️🀄️ል፦ @Holy_scriptures
9
#ከተማ_ወይም_ቦታ_በቅዱሳት_መጻሕፍት


#ራማ፤ ከፍታ ማለት ነው። አንዳንድ ከተማዎች ራማ ተብለዋል፤ ከእነርሱም የታወቀው በገባዖንና በጊብዓ አጠገብ የነበረ ከተማ ነው፤ ኢያሱ 18፥25፤ መሳ. 19፥13። ይህ የዲቦራ አገር ነበር፤ መሳ. 4፥5። ኤርምያስ ታስሮ ከኢየሩሳሌም ከተወሰደ በኋላ ከራማ ተለቀቀ። ግን ይህ ራማ የትኛው እንደሆነ አልታወቀም፤ ኤር. 40፥1። ራሔል በራማ አጠገብ ተቀበረች፤ ስለዚህም የሐዘን ቦታ ሆነ፤ ኤር. 31፥15፤ ማቴ. 2፥18።

ምንጭ፦ የመጽሐፍ ቅዱስ መዝገበ ቃላት፤ ገጽ 67


ወደ ቻናሉ ለመ🀄️🀄️ል፦ @Holy_scriptures
👍1
'    ==❀❀❀===❀❀❀==      
              የዕለቱ ጥቅስ
     ==❀❀❀===❀❀❀==
“አሁን ግን ወንድሞች ከሚባሉት አንዱ ሴሰኛ ወይም ገንዘብን የሚመኝ ወይም ጣዖትን የሚያመልክ ወይም ተሳዳቢ ወይም ሰካር ወይም ነጣቂ ቢሆን ከእርሱ ጋር እንዳትተባበሩ እጽፍላችኋለሁ፤ እንደነዚህ ካለው ጋር መብል እንኳን አትብሉ።”
                1ኛ ቆሮንቶስ 5፥11



ወደ ቻናሉ ለመ🀄️🀄️ል፦ @Holy_scriptures
👍73
'    ==❀❀❀===❀❀❀==      
              የዕለቱ ጥቅስ
     ==❀❀❀===❀❀❀==
“ለኵነኔ አልልም፤ በአንድነት ለመሞትና በአንድነት ለመኖር በልባችን እንዳላችሁ አስቀድሜ ብዬአለሁና።”
               2ኛ ቆሮ 7፥3



ወደ ቻናሉ ለመ🀄️🀄️ል፦ @Holy_scriptures
👍31😁1