ቅዱሳት መጻሕፍት
7.46K subscribers
1.37K photos
61 videos
332 files
808 links
በዚህ ቻናል

👉ቅዱሳት መጻሕፍት ይጠናሉ::
👉መጽሐፍ ቅዱሳዊ ትምህርቶች ይቀርባሉ::
👉 ለቅዱሳት መጽሐፍት ጥናት የሚያግዙ መጻሕፍት ይለቀቃሉ።

⭐️⭐️⭐️⭐️⭐️

@Holy_scriptures
Download Telegram
ትንሣኤ ሙታን



                 ወ/ዊ ያሬድ ጥላሁን


          ክፍል-2
   (የመጨረሻ ክፍል)


ሞት፡- የሰውን ልጅ ሁሉ ያንበረከከ፣ ጀግኖችን ያልፈራ፣ ነገሥታትን ያላፈረ፣ አዛውንትን ያላከበረ የሰው ጠላት ከሞት በላይ ማን ይኖር ይሆን!? በኃጢአት በኩል ወደ ዓለም ገብቶ በሥጋ ሁሉ ላይ የነገሠ፣ ከአዳም አንስቶ እስከ ሙሴ ከሕግ በፊትም ሆነ ከሕግ በኃላ የተንሰራፋ፣ የሰውን ልጅ ሁሉ አይሁድ ግሪክ ሳይል አንገት ያስደፋ ከሞት በላይ ማን ይኖር ይሆን? ሰው የፈለገውን ያህል ሃብት ቢያከማች፣ ዲግሪ ቢደረድር፣ ማዕረግ ቢጭን፣ ዝናው ቢናኝ ቀና ብሎ ነገን ሲያስብ አንድ ነገር ተስፋውን ያጨልምበታል። ሞት! ለዚህ ይሆን ያገሬ ሰው ልጁን “ሞት ባይኖር” ብሎ ስም የሚያውጣው? ሞት የሚያስፈራራን ሲገድለን ብቻ ቢሆን ምንኛ መልካም ነበር? ሞት አንዴ ነዋ! ነገር ግን እንደ ዕብራዊያን መልዕክት ጸሐፊ በሕይወታችን ዘመን ሁሉ ያስፈራራናል፡-

“እንግዲህ ልጆቹ በሥጋና በደም ስለሚካፈሉ፣ እርሱ ደግሞ በሞት ላይ ሥልጣን ያለውን በሞት እንዲሽር፣ ይኽውም ዲያቢሎስን ነው፣ በሕይወታቸውም ሁሉ ስለ ሞት ፍርሃት በባርነት ይታሰሩ የነበሩትን ሁሉ ነፃ እንዲያወጣ፣ በሥጋና በደም እንዲሁ ተካፈለ” ዕብ. 2፡14-15።

በዓለም ታሪክ ከሞት ወዲህ በሥጋ ሕይወት ላሉ የሰው ልጅ ችግሮች ሁሉ ሰው መፍትሄ ከማበጀት አልቦዘነም። እስቲ ትራንስፖርት፣ መገናኛ ብዙሃን፣ የህክምና ሳይንስ ወ.ዘ.ተ የደረሰበትን እንመልከት። ችግራችን ገንዘብ ቢሆን፣ ጤና፣ እውቀት ቢሆን ዝና ሰዎች ሊፈቱት ይችላሉ። ችግራችን ሲገለጥ ወዳጅ ዘመድ ይረባረባል፣ የቅርብ የሩቁ የራሱን ድርሻ ይጫወታል። ነገር ግን አንዴ ሞት ጥላውን ካጠላ ሰብዓዊ መፍትሄ ይሟጠጣል፣ ተስፋ ይቆረጣል፣ ከዋይታና ከሰቀቀን በስተቀር ሊዋጣ የሚችል መላ የለም። ሞት ግን ለእግዚአብሔር ብ ቻ የሚተው ጉዳይ ነው። ለዚህ ነው እግዚአብሔር ለሙታን ሕይወትን የሚሠጥ አምላክ ሆኖ የተገለጠው። እግዚአብሔር የሚፈልገው አንድ ነገር ብቻ ነው። መታመን! የሞቱትን ሰውነታቸው የበሰበሰውንና የፈረሰውን እንደገና የክብር ሕይወት ሰጥቶ እንደሚያነሣ፣ ይህንንም መሢህ ኢየሱስን ከሙታን በማስነሣቱ እንዳረጋገጠ፣ ቀን እንደቀጠረ በዚያም ቀን ሙታንን በእርግጥ እንደሚያነሣ፣ አስቀድሞ የእርሱ የሆኑትን በኃላም ሁሉን አስነስቶ ክብር ለሚገባው ክብርን፣ ውርደት ለሚገባውም እንደ ሥራው ለሁሉ እንደሚከፍል መታመን ይፈልጋል። እምነት ማለት ይህ ነው፣ ለሙታን ሕይውትን በሚሰጥ አምላክ ተደግፎ በሞት ላይ የሚስቅ ሕያው እምነት።

ተስፋ፡- ጌታ ኢየሱስ ከሙታን እንደተነሣ ምንም ያህል አስቀድሞ፣ ደጋግሞ የነገራቸው ቢሆንም ትንሣኤን ለማመን  ልባቸው የዘገየውን ደቀመዛሙርቱን ለማስረዳት ያደረገው ነገር ቢኖር መጽሐፍትን ያስተውሉ ዘንድ አዕምሯቸውን መክፈት ነው። ይህም ትንሣኤው አስቀድሞ የተሰጠ መለኮታዊ ተስፋ መሆኑኑ ያረጋግጥልናል። እግዚአብሔር የተስፋ አምላክ ነው። ታዲያ ተስፋ መስጠት የጀመረው የተስፋው ወራሽ የሆነው ሰው ከተፈጠረ በኃላ ብቻ አልነበረም። ሐዋርያው ጳውሎስ በመንፈስ ቅዱስ መረዳት ወደ ዘላለም መጥቆ ዐለም ሳይፈጠር ስለተከናወነ አንድ ተግባር ይተርክልናል፡-

“ስለዚህም ሕይወት የማይዋሽ እግዚአብሔር ከዘላለም ዘመናት በፊት ተስፋን ሰጠ” ቲቶ 1፡2

“በክርስቶስ ኢየሱስ እንደሚሆን የሕይወት ተስፋ በእግዚአብሔር ፈቃድ የኢየሱስ ክርስቶስ  ሐዋርያ የሆነ ጳውሎስ” 2ጢሞ. 1፡1

“… ይህም ፀጋ ከዘላለም ዘመናት በፊት በክርስቶስ ኢየሱስ ተሰጠን፣ አሁን ግን በመድኃኒታችን በኢየሱስ ክርስቶስ መገለጥ ታይቷል። እርሱ ሞትን ሽሯልና … በወንጌል ሕይወትንና አለመጥፋትን ወደ ብርሃን አውጥቷል” 2ጢሞ. 1፡9-11

 
ይህ የዘላለም ተስፋ ነው በዘመናት ውስጥ ከእግዚአብሔር ዘንድ ለአባቶች የተሰጠው። ተስፋው በሙሉ ከትንሳኤ ጋር የተያያዘ ነው። እግዚአብሔር በዘመናት ውስጥ ከተለያዩ ሰዎች ጋር ኪዳን የገባ ቢሆንም “ቅዱስ” ተብሎ የተጠራ ኪዳን እግዚአብሔር ከአብርሃምና ከዳዊት ጋር የገባው “የተስፋ ኪዳን” ነው። ተስፋችን ስንሞት ሥጋችን ወደ አፈር፣ ነፍሳችን ወደ እግዚአብሔር ሄዳ በዚያ ለዘላለም መኖራችን አይደለም። በፍፁም አይደለ! ምንም እንክዋ ነፍሳችን ከሥጋችን ከምትለይበት አንስቶ ጌታ ዳግመኛ እስኪመጣና የአካል ትንሣኤ እስኪሆን ድረስ ሕያው የሆነች ነፍሳችን በጌታ ዘንድ የምትቆይ ቢሆንም ያ ተስፋችን አይደለም። እዚያም ሆነን በናፍቆት የምንጠብቀው ተስፋ የሥጋ ትንሣኤን ይመሥለኛል። ለዚህ አይደል የጌታን ዳግም መምጣት ሲያወሳ ጳውሎስ “የተባረከው ተስፋችን የታላቁ የአምላካችንና የመድኃኒታችን የኢየሱስ ክርስቶስ መገለጥ” [ቲቶ 2፡11-13 በማለት የሚጠራው? ስለዚህ እኛም መገለጡን ከሚጠባበቁ አዕላፋት ቅዱሳን ጋር ተጨምረን “ማራናታ፡- አሜን ጌታ ኢየሱስ ሆይ ቶሎ ና!” እንበል። በቅድስና በመኖር ወንጌልንም በማሰራጨት መምጣቱን እናፋጥን። 



ምንጭ:- semayawithought.com




                  
ወደ ቻናሉ ለመ🀄️🀄️ል፦ @Holy_scriptures
👍10😁51
'    ==❀❀❀===❀❀❀==      
              የዕለቱ ጥቅስ
     ==❀❀❀===❀❀❀==
“ሰሎሞንም ይህን ነገር ስለ ለመነ፥ ነገሩ እግዚአብሔርን ደስ አሰኘው።”
                 1ኛ ነገሥት 3፥10


                  
ወደ ቻናሉ ለመ🀄️🀄️ል፦ @Holy_scriptures
12
'    ==❀❀❀===❀❀❀==      
              የዕለቱ ጥቅስ
     ==❀❀❀===❀❀❀==
“ኢዮአታምም በአምላኩ በእግዚአብሔር ፊት መንገዱን አቅንቶአልና በረታ።”
                 2 ዜና 27፥6


                  
ወደ ቻናሉ ለመ🀄️🀄️ል፦ @Holy_scriptures
👍72
                  
ወደ ቻናሉ ለመ🀄️🀄️ል፦ @Holy_scriptures
👍2
የፀሎት ሃይል .pdf
6.2 MB
📔ርዕስ፦የፀሎት ኃይል
👤ደራሲ፦ሮናልድ ደን
🗣ተርጓሚ፦ ጳውሎስ ፈቃዱ (የብርሃን አንጓዎች ፣ የእግዚአብሔር ልጅ እና ያልተንኳኩ በሮች ደራሲ)
💾መጠን፦6.2MB


                  
ወደ ቻናሉ ለመ🀄️🀄️ል፦ @Holy_scriptures
8👍3
'    ==❀❀❀===❀❀❀==      
              የዕለቱ ጥቅስ
     ==❀❀❀===❀❀❀==
“የፍጹም ሰው ጽድቁ መንገዱን ያቀናለታል፤ ኀጥእ ግን በኃጢአቱ ይወድቃል።”
             ምሳሌ 11፥5



ወደ ቻናሉ ለመ🀄️🀄️ል፦ @Holy_scriptures
👍63
ቅዱሳት መጻሕፍት
መዳን በሥራ ካልሆነ ለመልካም ሥራ ከጌታ የምናገኘው ምንድነው?                  ክፍል-2 እግዚአብሔር ይህ እምነት እውነተኛ መሆን አለመሆኑን በራሱ አምላካዊ እውቀት ያውቃል፤ ሰው ግን ይህን የሚያውቀው ሥራውን አይቶ ነው፤ እዚህ ላይ የተጠቀሰው «እምነት አለኝ» ባዩ ሰው ደግሞ ሥራ እንደሌለው ታውቋል፤ ስለዚህ በቊ.17 ላይ «ሥራ የሌለው እምነት ቢኖር በራሱ የሞተ ነው» ተብሏል፡፡ በእግዚአብሔር…
መዳን በሥራ ካልሆነ ለመልካም ሥራ ከጌታ የምናገኘው ምንድነው?


                 ክፍል-3
         (የመጨረሻ ክፍል)


በእምነት የጸደቀ ሰው ግን በሥራም ይጸድቃል፤ ይህ ማለት ግን ሥራ በእግዚአብሔር ዘንድ ያጸድቃል ከማለት በፍጹም የተለየ ነው፤ በሥራ መጽደቅ በእምነት የተገኘው ጽድቅ በሰው ዘንድ በሚታይ ሥራ መረጋጡን የሚያመለክት ነው፡፡ እንዲሁም እውነተኛ እምነትን ተከትሎ ለሚሠራው መልካም ሥራ በክርስቶስ የፍርድ ወንበር ፊት የጽድቅ አክሊልን በብድራት መቀበልን የሚያሳይ ነው፡፡ ይህም በእምነት የጸደቁ ሰዎች የሥራቸውን ዋጋ ይቀበላሉ ማለት ነው እንጂ ሰዎች የሚጸድቁት ገና ያን ጊዜ ነው ማለት አይደለም፡፡ ነገር ግን በእግዚአብሔር ፊት ሰውን የሚያጸድቀው እምነት ቀድሞውኑ ከሥራው ጋር አብሮ ያደርግ እንደነበር እንመለከታለን፤ ይህም ማለት በኋላ ይገለጥ ዘንድ ያለው ሥራ በእምነት ውስጥ ተሰውሮ እንደነበር እናያለን ማለት ነው፤

«ሰው በእምነት ብቻ ሳይሆን በሥራም እንዲጸድቅ ታያላችሁ» ማለትም በሥራ ሊገለጥ በሚችል እውነተኛ እምነት የጸደቀ ሰው በኋላ በሥራውም ይጸድቃል ወይም መጽደቁ በድጋሚ ይረጋገጣል፣ ብድራትን ይቀበላል፣ ይሸለማል ማለት ነው እንጂ በእግዚአብሔር ዘንድ ለመጽደቅ ሰው በክርስቶስ ማመኑ ብቻውን በቂ ስለማይሆን ሥራም መሥራት ያስፈልገዋል ማለት አይደለም፡፡

የእውነተኛ እምነት ትክክለኛ ገጽታ በጊዜውም ይሁን ቈይቶ በሥራ ሊገለጥ የሚችል መሆኑ ነው፡፡ የእስራኤል አባት በሆነው በአብርሃም እምነት የተመለከትነውም ይህንን ነው፡፡ ከአሕዛብ በሆነችው በረዓብ እምነትም የምንማረው ይህንኑ እውነታ ነው፤ ስለዚህ በመቀጠል የረዓብ ማስረጃነት ቀርቧል፤

«እንደዚሁም ጋለሞታይቱ ረዓብ ደግሞ መልእክተኛቹን ተቀብላ በሌላ መንገድ በሰደደቻቸው ጊዜ በሥራ አልጸደቀችምን?» ይላል(ቊ.25)፡፡ ከኢያሱ 2፡9‐11 ባለው ክፍል ረዓብ ለመልእክተኞቹ የተናገረችውን ስናነብ እርስዋ በእስራኤል አምላክ ያመነችው እግዚአብሔር የኤርትራን ባሕር በእስራኤል ልጆች ፊት እንዳደረቀና ጠላቶቻቸውን ሁሉ እንዳጠፋላቸው እርስዋና ወገኖችዋ በሰሙ ጊዜ መሆኑን እንረዳለን፤ ይህንንም ስትገልጥ:-

«እግዚአብሔር ምድሪቱን እንደሰጣችሁ እናንተንም መፍራት በላይችን እንደወደቀ፣ በምድሪቱ የሚኖሩት ሁሉ ከፊታችሁ እንደቀለጡ አወቅሁ፤ ከግብፅ ምድር በወጣችሁ ጊዜ እግዚአብሔር የኤርትራን ባሕር ባደረቀ ጊዜ በዮርዳኖስ ማዶ በነበሩት እናንተም ፈጽማችሁ ባጠፋችኋቸው በሁለቱ በአሞራውያን ነገሥታት በሴዎንና በዐግ ያደረጋችሁትን ሰምተናል፤ ይህንንም ሰምተን ልባችን ቀለጠ» ብላለች (ቊ.9)፡፡ እንዲሁም በመቀጠል «አምላካችሁ በላይ በሰማይ በታችም በምድር እርሱ አምላክ ነውና ከእናንተ የተነሣ ከዚያ ወዲያ ማንም ነፍስ አልቀረለትም» ብላለች፤ በዚህ ቃል ረዓብ በእግዚአብሔር ያመነችው መልእክተኞቹን ተቀብላ በሌላ መንገድ ከመስደድዋ በፊት መሆኑን እናውቃለን፤ ስለሆነም በእግዚአብሔር ዘንድ እርስዋ እንደ አብርሃም ሁሉ ባመነች ጊዜ የጸደቀች ወይም ተቀባይነት ያገኘች እንደሆነች እንገነዘባለን፤ እንዲሁም ደግሞ መልእክተኞቹን ተቀብላ በሌላ መንገድ በሰደደቻቸው ጊዜ በሥራም ጸድቃለች ወይም ተረጋግጦላታል፤ በእርስዋም ሕይወት እምነት ከሥራ ጋር ያደርግ እንደነበር እናስተውላለን፤ ይህ አባባል ሥራ ከእምነት ጋር ያደርግ ነበር ከሚለው አባባል የተለየ ነው፤ በዋናነት እየተነገረለት ያለው እምነት ነው፤ እምነት ከሥራ ጋር ያደርግ ነበር ሲባል ያ እምነት በውስጡ ሰውሮ የያዘው ያልተገለጠ ሥራ እንዳለው የሚያሳይ ነው፤ ይህ እምነት ግን በውስጡ ይህን ሥራ ካልያዘ ማለትም ሥራ የተዋሐደው ካልሆነ የሞተ እምነት ነው፤ በቊ 26 ላይ ይህን በተመለከተ ሲናገር «ከነፍስ የተለየ ሥጋ የሞተ እንደሆነ እንዲሁ ደግሞ ከሥራ የተለየ እምነት የሞተ ነው» ይላል፤ በእግዚአብሔር ዘንድ መዳን በእምነት ነው ሲባልም በእንዲህ ያለ የሞተ እምነት ነው ማለት አይደለም፤ በውስጡ ሥራ በተዋሐደው እውነተኛ እምነት ነው ማለት ነው እንጂ፤ ይህ በእምነት ውስጥ በሐሳብ ደረጃ ተሰውሮ የነበረ ሥራ የሚገለጥበትን መስክ ሲያገኝ ከዚያ እምነት ውስጥ ወጥቶ በሰው ዘንድ በሚታይ መልኩ ይገለጣል፤ ነገር ግን ያን ጊዜ ያ ሰው እንደ አዲስ በእግዚአብሔር ፊት ገና መጽደቁ አይደለም፤ ቀደም ብሎ የጸደቀው ሰው አሁንም የጸደቀ መሆኑ በሥራው በሰው ፊት ይረጋገጥለታል ማለት ነው እንጂ፤ በሰማይም የሥራው ዋጋ የሆነውን የጽድቅ ብድራቱንም በቅዱሳን ሁሉ ፊት ያገኛል፡፡



ምንጭ፦ 1bible.page



ወደ ቻናሉ ለመ🀄️🀄️ል፦ @Holy_scriptures
👍9
'    ==❀❀❀===❀❀❀==      
              የዕለቱ ጥቅስ
     ==❀❀❀===❀❀❀==
“እግዚአብሔርም እንዲህ ይላል፦ ነፋስ አታዩም፥ ዝናብም አታዩም፥ ይህ ሸለቆ ግን ውኃ ይሞላል፤ እናንተም ከብቶቻችሁም እንስሶቻችሁም ትጠጣላችሁ።”
              2ኛ ነገሥት 3፥17




ወደ ቻናሉ ለመ🀄️🀄️ል፦ @Holy_scriptures
10👍1
'    ==❀❀❀===❀❀❀==      
              የዕለቱ ጥቅስ
     ==❀❀❀===❀❀❀==
“ከስምንት ቀን በኋላም ደቀ መዛሙርቱ ደግመው በውስጥ ነበሩ፥ ቶማስም ከእነርሱ ጋር ነበረ። ደጆች ተዘግተው ሳሉ ኢየሱስ መጣ፤ በመካከላቸውም ቆሞ፦ ሰላም ለእናንተ ይሁን አላቸው።”
             ዮሐንስ 20፥26




ወደ ቻናሉ ለመ🀄️🀄️ል፦ @Holy_scriptures
4👍2
ዳግማዊ ትንሣኤ ምንድነው?


ከትንሣኤ ዕለት ቀጥሎ ያለው ሰንበት #ዳግማዊ_ትንሳኤ በመባል ይታወቃል። ይህ እለት በዚህ ስም ሊጠራ የቻለበት ምክንያት ጌታችን አምላካችንና መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በዋናው የትንሣኤ ቀን በእለተ ፋሲካ ለቅዱሳን ሐዋርያት በዝግ በር ገብቶ በመካከላቸው ተገኝቶ «ሰላም ለሁላችሁ ይሁን» ብሎ ትንሣኤውን ሲገልጽላቸው ሐዋርያው ቶማስ አልተገኘም ነበር፡፡እናም በኋላ ከሔደበት ሲመጣ ወንድሞቹ ጌታችን መነሣቱን እንደተገለጸላቸው በደስታ ሲነግሩት ቅር ተሰኝቶ «በኋላ እናንተ ዐየን ብላችሁ ልትመሰክሩ፣ ልታስተምሩ፣ እኔ ግን 'ሰምቼአለሁ' ብዬ ልመሰክር፣ ላስተምር? አይሆንም እኔም ካላየሁ አላምንም» በማለቱ የሰውን ሁሉ፤ ይልቁንም የመረጣቸው ወዳጆቹን የልብ ሐሳብ ምክንያቱን ለይቶ የሚያውቀው፣ ቸርነቱ ወሰን የሌለው የባሕርይ አምላክ መድኃኒዓለም ክርስቶስ ልክ እንደመጀመሪያው ትንሣኤ ዕለት ሐዋርያት በአንድነት በተዘጋ ቤት እንዳሉ በሩን ሳይከፍት ገብቶ «ሰላም ለሁላችን ይሁን» በማለት በመካከላቸው ቆመ፤ ቶማስንም «ያመንክ እንጂ ተጠራጣሪ አትሁን እነሆ የተቸነከሩ እጆቼንና እግሮቼን፣ የተወጋ ጐኔንም ናና እይ» ብሎ አሳየው፡፡ እርሱም ምልክቱን በማየቱ በመዳሰሱ ትንሣኤውንና አምላክነቱን እንደፍላጎቱ በመረዳቱ «ጌታዬ አምላኬ ብሎ መስክሮ» አመነ፡፡

👉እንግዲህ ይህ የትንሣኤው ምስጢር ለሁለተኛ ጊዜ ለሐዋርያት የተገለጠበት ዕለት ስለሆነ «ዳግም ትንሣኤ» ተብሎ ሰንበቱ ይጠራበታል፤ ይከበርበታል፡፡ ዮሐ. 20፥24-30



ምንጭ፦ ከፌስቡክ መንደር



ወደ ቻናሉ ለመ🀄️🀄️ል፦ @Holy_scriptures
👍101👏1
'    ==❀❀❀===❀❀❀==      
              የዕለቱ ጥቅስ
     ==❀❀❀===❀❀❀==
“የእግዚአብሔር ቃል ቅን ነውና ሥራውም ሁሉ በእምነት ነውና።”
               መዝሙር 33፥4



ወደ ቻናሉ ለመ🀄️🀄️ል፦ @Holy_scriptures
6🔥1
"ጸሎት የሰውን ፈቃድ በሰማይ ለመፈፀም ሳይሆን ዳሩ ግን የእግዚአብሔርን ፈቃድ በምድር ላይ ለመፈፀም የሚረዳ ኃያል መሣሪያ ነው::"

ሮበርት ሎው



ወደ ቻናሉ ለመ🀄️🀄️ል፦ @Holy_scriptures
5👍2🥰2
'    ==❀❀❀===❀❀❀==      
              የዕለቱ ጥቅስ
     ==❀❀❀===❀❀❀==
“እግዚአብሔር በተስፋ ለሚጠብቁት ለምትሻውም ነፍስ መልካም ነው።”
                 ሰቆ. 3፥25



ወደ ቻናሉ ለመ🀄️🀄️ል፦ @Holy_scriptures
9🥰1
#የሮሜ_መልእክት_ጥናት


ሮሜ 9
¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯
¹⁹ እንግዲህ ስለ ምን እስከ አሁን ድረስ ይነቅፋል? ፈቃዱንስ የሚቃወም ማን ነው? ትለኝ ይሆናል።
²⁰ ነገር ግን፥ አንተ ሰው ሆይ፥ ለእግዚአብሔር የምትመልስ ማን ነህ? ሥራ ሠሪውን፦ ስለ ምን እንዲህ አድርገህ ሠራኸኝ ይለዋልን?
²¹ ወይም ሸክላ ሠሪ ከአንዱ ጭቃ ክፍል አንዱን ዕቃ ለክብር አንዱንም ለውርደት ሊሠራ በጭቃ ላይ ሥልጣን የለውምን?
²²-²³ ነገር ግን እግዚአብሔር ቍጣውን ሊያሳይ ኃይሉንም ሊገልጥ ወዶ፥ አስቀድሞ ለክብር ባዘጋጃቸው በምሕረት ዕቃዎች ላይ የክብሩን ባለ ጠግነት ይገልጥ ዘንድ፥ ለጥፋት የተዘጋጁትን የቁጣ ዕቃዎች በብዙ ትዕግሥት ከቻለ፥ እንዴት ነው?
²⁴ የምሕረቱ ዕቃዎችም ከአይሁድ ብቻ አይደሉም፥ ነገር ግን ከአሕዛብ ደግሞ የጠራን እኛ ነን።
²⁵ እንዲሁ ደግሞ በሆሴዕ፦ ሕዝቤ ያልሆነውን ሕዝቤ ብዬ፥ ያልተወደደችውንም የተወደደችው ብዬ እጠራለሁ፤
²⁶ እናንተ ሕዝቤ አይደላችሁም በተባለላቸውም ስፍራ በዚያ የሕያው እግዚአብሔር ልጆች ተብለው ይጠራሉ ይላል።
²⁷-²⁸ ኢሳይያስም፦ የእስራኤል ልጆች ቁጥር ምንም እንደ ባሕር አሸዋ ቢሆን ቅሬታው ይድናል፤ ጌታ ነገሩን ፈጽሞና ቆርጦ በምድር ላይ ያደርገዋልና ብሎ ስለ እስራኤል ይጮኻል።
²⁹ ኢሳይያስም እንደዚሁ፦ ጌታ ፀባዖት ዘር ባላስቀረልን እንደ ሰዶም በሆንን ገሞራንም በመሰልን ነበር ብሎ አስቀድሞ ተናገረ።


ሮሜ 9 (አዲሱ መ.ት)
¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯
¹⁹ ከእናንተ አንዱ፣ “ታዲያ እንደዚህ ከሆነ እግዚአብሔር እስከ አሁን ለምን ይወቅሰናል? ምክንያቱም ፈቃዱን ሊቋቋም የሚችል ማን አለ?” ይለኝ ይሆናል።
²⁰ ነገር ግን ለእግዚአብሔር መልስ የምትሰጥ አንተ ማን ነህ? “ሥራ ሠሪውን፣ ‘ለምን እንዲህ ሠራኸኝ?’ ይለዋልን?”
²¹ ሸክላ ሠሪ፣ ከሚሠራው ጭቃ፣ አንዳንዱን ሸክላ ለክብር፣ ሌላውን ደግሞ ለተራ አገልግሎት የማድረግ መብት የለውምን?
²² እግዚአብሔር ቊጣውን ለማሳየት፣ ኀይሉንም ለማሳወቅ ፈልጎ የቍጣው መግለጫ የሆኑትን፣ ለጥፋትም የተዘጋጁትን እጅግ ታግሦ ቢሆንሳ!
²³ አስቀድሞ ለክብር ላዘጋጃቸው፣ የምሕረቱም መግለጫዎች ለሆኑት፣ የክብሩ ባለጠግነት እንዲታወቅ ይህን አድርጎ እንደሆነስ?
²⁴ የጠራው ከአይሁድ ወገን ብቻ ሳይሆን ከአሕዛብ ወገን የሆነውን እኛን እንኳ ሳይቀር አይደለምን?
²⁵ በሆሴዕ እንዲህ እንደሚል፤ “ሕዝቤ ያልሆኑትን፣ ‘ሕዝቤ’ ብዬ እጠራቸዋለሁ”፤ ያልተወደደችውንም ‘የተወደደችው’ ብዬ እጠራለሁ።
²⁶ ደግሞም፣ “ ‘ሕዝቤ አይደላችሁም’፤ ተብሎ በተነገራቸው በዚያ ቦታ፣ ‘የሕያው እግዚአብሔር ልጆች’ ተብለው ይጠራሉ።”
²⁷ ኢሳይያስም ስለ እስራኤል እንዲህ ሲል ይጮኻል፤ “የእስራኤል ልጆች ቊጥር በባሕር ዳር እንዳለ አሸዋ ቢሆንም፣ ትሩፉ ብቻ ይድናል።
²⁸ ጌታ ፍርዱን በምድር ላይ፣ በፍጥነትና ለመጨረሻ ጊዜ ይፈጽማልና።”
²⁹ ይኸውም ቀደም ሲል ኢሳይያስ እንደ ተናገረው ነው፤ “የሰራዊት ጌታ፣ ዘር ባያስቀርልን ኖሮ፣ እንደ ሰዶም በሆን ነበር፤ ገሞራንም በመሰልን ነበር።”


ሮሜ 9 (ሕያው ቃል)
¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯
¹⁹ ምናልባት ከእናንተ አንዳንዶቻችሁ ፥ «የእግዚአብሔርን ፈቃድ መቃወም ካልተቻለ ፥ ታዲያ እግዚአብሔር ሰዎችን ለምን በክፉ ሥራቸው ተጠያቂ ያደርጋቸዋል?» ትሉ ይሆናል።
²⁰ ለዚህ ጥያቄ እኔ ያለኝ መልስ፥ «እንዲህ ያለውን ቃል ለእግዚአብሔር መመለስ የምትችል ለመሆኑ አንተ ማን ነህ? የሸክላ ዕቃ፥ ሠሪውን ባለሙያ 'ለምን በዚህ ዓይነት ቅርጽ ሠራኸኝ' ሊለው ይችላልን?
²¹ ወይስ የሸክላ ሥራ ባለሙያው ከአንዱ የሸክላ አፈር ላይ አንሥቶ፥ አንዱን ሸልሞ ሸላልሞ በክብር የሚቀመጥ ዕቃ፥ ሌላውን ግን በክብር ሊይዙት ለማይገባ አገልግሎት የሚውል ተራ ዕቃ አድርጎ ለመሥራት መብት የለውምን?
²² ጌታ እግዚአብሔርስ እስከ አሁን ድረስ የታገሣቸውን ፥ ለጥፋት የተመደቡትን ሰዎች ቁጣውንና ኃይሉን ሊገልጽባቸው ሙሉ ሥልጣን የለውምን?
²³¯²⁴ እነርሱን የታገሣቸው ፥ ከአይሁድም ሆነ ከአሕዛብ ወገን መርጦ ለክብሩ ላዘጋጀን ለእኛ፥ ምሕረቱንና የክብሩን ባለጠግነት ሊያሳይ ስለፈለገ ነው።»
²⁵ ነቢዩ ሆሴዕ ፥ «ሕዝቤ ያልነበረውን 'ሕዝቤ' ብዬ እጠራዋለሁ። ያልተወደደውንም ሕዝብ ፥ 'የተወደደ' እለዋለሁ።
²⁶ 'ሕዝቤ አይደላችሁም' በተባሉበት ሥፍራ ፥ 'የሕያው እግዚአብሔር ልጆች' ተብለው ይጠራሉ» ብሏል።
²⁷ ነቢዩ ኢሳይያስም ፥ «የእሥራኤል ሕዝብ ብዛት እንደ ባሕር አሸዋ ቢሆን እንኳ የሚድኑት ጥቂቶች ብቻ ናቸው።
²⁸ ጌታ በፍጥነት በዓለም ላይ ፍርዱን ይሰጣል» ሲል ተናግሯል።
²⁹ በሌላም ቦታ ይኸው ነቢይ ፥ «ጌታ እግዚአብሔር ለትውልዳችን ዘር አስቀርቶ ምሕረቱን ባያሳይ ኖሮ ፥ እኛም አይሁዶች እንደ ሰዶምና ገሞራ ሰዎች በጠፋን ነበር»




ወደ ቻናሉ ለመ🀄️🀄️ል፦ @Holy_scriptures
2👍2
'    ==❀❀❀===❀❀❀==      
              የዕለቱ ጥቅስ
     ==❀❀❀===❀❀❀==
“የእግዚአብሔርንም መንግሥት እንዲሰብኩና ድውዮችን እንዲፈውሱ ላካቸው፥”
               ሉቃስ 9፥2


ወደ ቻናሉ ለመ🀄️🀄️ል፦ @Holy_scriptures
6
#የእግዚአብሔር_ቃል_ምን_ይላል?

እ.ኤ.አ 48-50 ዓ.ም ነው ተብሎ በሚገመተው በቤተክርስቲያን ታሪክ የመጀመሪያው የሆነ ጉባኤ በሐዋርያት ሥራ ምዕራፍ 15 ላይ ይገኛል። ጉባኤው የተካሄደበትን ገፊ ምክንያት ከክፍሉ ማየት ይቻላል። ለዛሬ፣ ጉባኤው ከተካሄደ በኋላ የጉባኤውን ውሳኔ ለመግለጽ ከአሕዛብ ወገን ለሆኑት የተላከውን ደብዳቤ ከታች ለጥፈነዋል። ውሳኔው በጣም አስደናቂ እና ለትምህርታችን የሚሆን ብዙ ቁምነገር ስላለበት እዩት እና አስተያየት ስጡበት።

ሐዋርያት 15
¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯
²³ እንዲህም ጽፈው በእነርሱ እጅ ላኩ። ሐዋርያትና ሽማግሌዎች ወንድሞችም በአንጾኪያና በሶርያ በኪልቅያም ለሚኖሩ ከአሕዛብ ወገን ለሆኑ ወንድሞች ሰላምታ ያቀርባሉ።
²⁴ ያላዘዝናቸው ሰዎች ከእኛ ወጥተው፦ ትገረዙ ዘንድና ሕግን ትጠብቁ ዘንድ ይገባችኋል ብለው ልባችሁን እያወኩ በቃል እንዳናወጡአችሁ ስለ ሰማን፥
²⁵-²⁶ ስለ ጌታችን ስለ ኢየሱስ ክርስቶስ ስም ነፍሳቸውን ከሰጡት ከምንወዳቸው ከበርናባስና ከጳውሎስ ጋር የተመረጡትን ሰዎች ወደ እናንተ እንልክ ዘንድ በአንድ ልብ ሆነን ፈቀድን።
²⁷ ራሳቸውም ደግሞ በቃላቸው ያንኑ ይነግሩአችሁ ዘንድ ይሁዳንና ሲላስን ልከናል።
²⁸-²⁹ ለጣዖት ከተሠዋ፥ ከደምም፥ ከታነቀም፥ ከዝሙትም ትርቁ ዘንድ ከዚህ ከሚያስፈልገው በቀር ሌላ ሸክም እንዳንጭንባችሁ እኛና መንፈስ ቅዱስ ፈቅደናልና፤ ከዚህም ሁሉ ራሳችሁን ብትጠብቁ በመልካም ትኖራላችሁ። ጤና ይስጣችሁ።




ወደ ቻናሉ ለመ🀄️🀄️ል፦ @Holy_scriptures
👍8
'    ==❀❀❀===❀❀❀==      
              የዕለቱ ጥቅስ
     ==❀❀❀===❀❀❀==
“እግዚአብሔር ይቀድማችኋልና፥ የእስራኤልም አምላክ ይከተላችኋልና በችኰላ አትወጡም በመኰብለልም አትሄዱም።”
               ኢሳይያስ 52፥12



ወደ ቻናሉ ለመ🀄️🀄️ል፦ @Holy_scriptures
9
ወደ ቻናሉ ለመ🀄️🀄️ል፦ @Holy_scriptures
👍3
feetoch-1.pdf
1.1 MB
👉ርዕስ፦ ከክብር ወደ ክብር
ጸሐፊ፦ ዎችማን ኒ
🗣ትርጉም፦ ዘካርያስ ጥላሁን


ወደ ቻናሉ ለመ🀄️🀄️ል፦ @Holy_scriptures
👍4
'    ==❀❀❀===❀❀❀==      
              የዕለቱ ጥቅስ
     ==❀❀❀===❀❀❀==
“ይህም ብቻ አይደለም፥ ነገር ግን መከራ ትዕግሥትን እንዲያደርግ፥ ትዕግሥትም ፈተናን ፈተናም ተስፋን እንዲያደርግ እያወቅን፥ በመከራችን ደግሞ እንመካለን፤”
                  ሮሜ 5፥3-4


ወደ ቻናሉ ለመ🀄️🀄️ል፦ @Holy_scriptures
6👍2