#ማክሰኞ ኢየሱስ ለመጨረሻ ጊዜ በቤተ መቅድስ ያስተማረበት ቀን ነው።
ጌታ ከቃሉ ስንት ጊዜ አስተማረን? ምን ያህልስ ወደ ተግባር ለወጥነው? ወይስ እንደ ፈሪሳውያን በራሱ መጽሐፍ ላይ ጌታችንን እየተከራከርነውና አልፎ ተርፎም ከሕይወታችን ልናስወጣው እየከጀልን ይሆን? የማንስ ጽሕፈት በላያችን ይታያል?
ለመሆኑ ጌታችንና መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ምን አስተማረ? ወይም ምን ተማሩ አለ?
👉“እንግዲህ ከነዚህ ከሁሉ ካነሱት ትእዛዛት አንዲቱን የሚሽር ለሰውም እንዲሁ የሚያስተምር ማንም ሰው በመንግሥተ ሰማያት ከሁሉ ታናሽ ይባላል፤ የሚያደርግ ግን የሚያስተምርም ማንም ቢሆን እርሱ በመንግሥተ ሰማያት ታላቅ ይባላል።”
ማቴዎስ 5፥19
👉“የሰው ልጅ ብዙ መከራ ሊቀበል፥ ከሽማግሌዎችም ከካህናት አለቆችም ከጻፎችም ሊጣል፥ ሊገደልም ከሦስት ቀንም በኋላ ሊነሣ እንዲገባው ያስተምራቸው ጀመር፤ ቃሉንም ገልጦ ይናገር ነበር።”
ማርቆስ 8፥31
👉“ቀንበሬን በላያችሁ ተሸከሙ ከእኔም ተማሩ፥ እኔ የዋህ በልቤም ትሑት ነኝና፥ ለነፍሳችሁም ዕረፍት ታገኛላችሁ፤”
ማቴዎስ 11፥29
👉“ሲያስተምርም እንዲህ አለ፦ ረጃጅም ልብስ ለብሰው መዞርን፥ በገበያም ሰላምታን፥ በምኵራብም የከበሬታን ወንበር፥ በግብርም የከበሬታን ስፍራ ከሚወዱ ከጻፎች ተጠበቁ፤”
ማርቆስ 12፥38-39
👉 “እንግዲህ ሂዱና አሕዛብን ሁሉ በአብ በወልድና በመንፈስ ቅዱስ ስም እያጠመቃችኋቸው፥ ያዘዝኋችሁንም ሁሉ እንዲጠብቁ እያስተማራችኋቸው ደቀ መዛሙርት አድርጓቸው፤ እነሆም እኔ እስከ ዓለም ፍጻሜ ድረስ ሁልጊዜ ከእናንተ ጋር ነኝ።”
ማቴዎስ 28፥19-20
ወደ ቻናሉ ለመ🀄️ላ🀄️ል፦ @Holy_scriptures

❤15👍3
' ==❀❀❀===❀❀❀==
የዕለቱ ጥቅስ
==❀❀❀===❀❀❀==
“ኢየሱስ ግን እንዲህ አለ፦ ተዉአት፤ ስለ ምን ታደክሙአታላችሁ? መልካም ሥራ ሠርታልኛለች።”
ማርቆስ 14፥6

❤10👍1
#ረቡዕ የአስቆሮቱ ይሁዳ ኢየሱስን የካደበት ቀንና ማርያም (በማርቆስ ስሟ አልተጠቀሰም) በኢየሱስ እግር ስር ሽቶ ያፈሰሰችበትና በጸጉሯ ያበሰችበት ቀን ነው። (ማር. 14 ) እዚህ ጋር አንድ ነገር ማስቀመጥ ወደድኩ። ይህ ቀን ብዙ ጊዜ ከኢየሱስ ጋር የተጓዙ ሰዎች ትጥቃቸው መፈታት የጀመረበትና እውነተኛ ማንነታቸው የተገለጠበት ቀን ነበር። ከዚህ በፊት በርትተው ይጓዙ የነበሩ ሁሉ የሥጋ ድካም በብርቱ መገዳደር እና መጣል የጀመራቸው ጊዜ ነበር። አንዳዶች ወድቀው ሲነሱ አንዱ እስከወዲያኛው ወደቀ። በነገራችን ላይ የዚህን የሥጋን ከመንፈስ ጋር ለማበር መቸገር መፍትሄ በጌቴሴማኒ ነገራቸው ። እንዲህ በማለት፦ “ወደ ፈተና እንዳትገቡ ትጉና ጸልዩ፤ መንፈስስ ተዘጋጅታለች ሥጋ ግን ደካማ ነው አለው።” (ማቴዎስ 26፥41)
ወደ ረቡዕ ቀን ስንመለስ ይሁዳ እንዲህ አይነት ሰው ነበር፦
"ይህንም የተናገረ ሌባ ስለ ነበረ ነው እንጂ ለድሆች ተገድዶላቸው አይደለም፤ ከረጢትም ይዞ በውስጡ ከሚገባው ይወስድ ስለ ነበረ ነው።" (ዮሐ. 12፡6) በሌላ በኩል ደግሞ በምን ሰዓት ምን ማድረግ እንዳለባት የምታውቅን ሴት እንመለከታለን። ኢየሱስ ከሞተ በኋላ ለአካሉ ሽቶ ለመቀባት አስበው የሄዱ ቢኖሩም መቅደላዊት ማርያም ግን መችና የት ኢየሱስን ማግኘት እንደሚቻል የምታውቅ ሴት ነበረች። እናም የዛሬው ቀን ከኢየሱስ ጋር ለዘለአለሙ ለመጓዝ ኃይል እንድናገኝ፣ ከእርሱ አሳብና አጀንዳ ጋር ደግሞ ተባብረን እንድንጓዝ ጌታ ይርዳን!

❤10👍5
' ==❀❀❀===❀❀❀==
የዕለቱ ጥቅስ
==❀❀❀===❀❀❀==
“እርሱም፦ ይህ ስለ ብዙዎች የሚፈስ የአዲስ ኪዳን ደሜ ነው።”
ማርቆስ 14፥24
ወደ ቻናሉ ለመ🀄️ላ🀄️ል፦ @Holy_scriptures
የዕለቱ ጥቅስ
==❀❀❀===❀❀❀==
“እርሱም፦ ይህ ስለ ብዙዎች የሚፈስ የአዲስ ኪዳን ደሜ ነው።”
ማርቆስ 14፥24
ወደ ቻናሉ ለመ🀄️ላ🀄️ል፦ @Holy_scriptures
❤7👍2
#ሀሙስ ጌታችንና መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ከመሞቱ በፊት ከደቀ መዛሙርቱ ጋር የመጨረሻውን እራት የበላበትንና በእውነት ለእርሱ ተከታይ ለሆኑት ብርቱና መሰረታዊ ትምህርት፣ ምክር፣ ተግጻጽ ሲያስፈልግም በተግባር የተደገፈ ትምህርት ያስተላለፈበት እንዲሁም አሁን በመንግስቱ ላሉ በኋላም ለሚመጡ የጸለየው አስደናቂ ጸሎት፣ የደቀ መዛሙርቱ ድካም. . . ወዘተ የሀሙስ ቀን ሁነቶች ናቸው።
በገነት አዳም ከእግዚአብሔር አሳብ ይልቅ የራሱን መርጦ ለሰው ፍዳን አመጣ ከገነትም ተባረረ። ኢየሱስ ግን ከራሱ መከራ ይልቅ የአባቱን ፈቃድ አስቀደመ። አምላክ እና ጌታ ሆኖ ሳለ ሰውን አገለገለ።
"እናንተ መምህርና ጌታ ትሉኛላችሁ፤ እንዲሁ ነኝና መልካም ትላላችሁ። እንግዲህ እኔ ጌታና መምህር ስሆን እግራችሁን ካጠብሁ፥ እናንተ ደግሞ እርስ በርሳችሁ እግራችሁን ትተጣጠቡ ዘንድ ይገባችኋል። እኔ ለእናንተ እንዳደረግሁ እናንተ ደግሞ ታደርጉ ዘንድ ምሳሌ ሰጥቻችኋለሁና።" (ዮሐንስ 13፥13-15 )
የሚገርመኝ ነገር ቢኖር ኢየሱስን ከመከራሁ እንዲቀርና እርሱን ለመርዳት ተማሪዎቹ በስጋ ቢጣጣሩም ፍቅራቸውን በመሃላ ለማጽናት ቢሞክሩም በኋላ እየሸሹና እየካዱ መገኘታቸው ነው። ለካ እውነተኛ ማንነት በወቅታዊ ስሜት ሳይሆን በፈተና ወቅት የሚገለጥ ነው! የዮሐንስ ወንጌልን ከምዕራፍ 13-18 አጋማሽ በመመልከት፣ በማጥናትና በማሰላሰል ተባረኩበት።
“እውነተኛ አምላክ ብቻ የሆንህ አንተን የላክኸውንም ኢየሱስ ክርስቶስን ያውቁ ዘንድ ይህች የዘላለም ሕይወት ናት።”
(ዮሐንስ 17፥3)

👍6
#ትንሣኤ
#ፋሲካ
"የአይሁድ የፋሲካ በዓል ዋዜማ ምሽት ነበር። ያች ሌሊት፥ ኢየሱስ ወደ አባቱ ከመሄዱ በፊት በዚች ምድር ላይ የሚያሳልፋት፥ የመጨረሻይቱ፥ መሆኗን አወቀ። በዚህ ዓለም ያሉትን ወገኖቹን፥ ቀድሞውንም ይወዳቸው ነበር። አሁን ደግሞ፥ እስከ መጨረሻው የቱን ያህል የሚወዳቸው መሆኑን ፥ ሊገልጥላቸው ፈለገ።"
ዮሐ. 13፥1(ሕያው ቃል)

👍9❤1🥰1
' ==❀❀❀===❀❀❀==
የዕለቱ ጥቅስ
==❀❀❀===❀❀❀==
“ለኃጢአት ሞተን ለጽድቅ እንድንኖር፥ እርሱ ራሱ በሥጋው ኃጢአታችንን በእንጨት ላይ ተሸከመ፤ በመገረፉ ቁስል ተፈወሳችሁ።”
1ኛ ጴጥሮስ 2፥24

👍4❤2
#ትንሣኤ
#ፋሲካ
#የእግዚአብሔር_ቃል_ምን_ይላል?
ኢሳይያስ 53
¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯
¹ የሰማነውን ነገር ማን አምኖአል? የእግዚአብሔርስ ክንድ ለማን ተገልጦአል?
² በፊቱ እንደ ቡቃያ ከደረቅም መሬት እንደ ሥር አድጎአል፤ መልክና ውበት የለውም፥ ባየነውም ጊዜ እንወድደው ዘንድ ደም ግባት የለውም።
³ የተናቀ ከሰውም የተጠላ፥ የሕማም ሰው ደዌንም የሚያውቅ ነው፤ ሰውም ፊቱን እንደሚሰውርበት የተናቀ ነው፥ እኛም አላከበርነውም።
⁴ በእውነት ደዌያችንን ተቀበለ ሕመማችንንም ተሸክሞአል፤ እኛ ግን እንደ ተመታ በእግዚአብሔርም እንደ ተቀሠፈ እንደ ተቸገረም ቈጠርነው።
⁵ እርሱ ግን ስለ መተላለፋችን ቈሰለ፥ ስለ በደላችንም ደቀቀ፤ የደኅንነታችንም ተግሣጽ በእርሱ ላይ ነበረ፥ በእርሱም ቍስል እኛ ተፈወስን።
⁶ እኛ ሁላችን እንደ በጎች ተቅበዝብዘን ጠፋን፤ ከእኛ እያንዳንዱ ወደ ገዛ መንገዱ አዘነበለ፤ እግዚአብሔርም የሁላችንን በደል በእርሱ ላይ አኖረ።
⁷ ተጨነቀ ተሣቀየም አፉንም አልከፈተም፤ ለመታረድ እንደሚነዳ ጠቦት፥ በሸላቶቹም ፊት ዝም እንደሚል በግ፥ እንዲሁ አፉን አልከፈተም።
⁸ በማስጨነቅና በፍርድ ተወሰደ፤ ስለ ሕዝቤ ኃጢአት ተመትቶ ከሕያዋን ምድር እንደ ተወገደ ከትውልዱ ማን አስተዋለ?
⁹ ከክፉዎችም ጋር መቃብሩን አደረጉ፥ ከባለጠጎችም ጋር በሞቱ፤ ሆኖም ግፍን አላደረገም ነበር፥ በአፉም ተንኮል አልተገኘበትም ነበር።
¹⁰ እግዚአብሔርም በደዌ ያደቅቀው ዘንድ ፈቀደ፤ ነፍሱን ስለ ኃጢአት መሥዋዕት ካደረገ በኋላ ዘሩን ያያል፥ ዕድሜውም ይረዝማል፥ የእግዚአብሔርም ፈቃድ በእጁ ይከናወናል።
¹¹ ከነፍሱ ድካም ብርሃን ያያል ደስም ይለዋል፤ ጻድቅ ባሪያዬም በእውቀቱ ብዙ ሰዎችን ያጸድቃል፥ ኃጢአታቸውን ይሸከማል።
¹² ስለዚህም እርሱ ብዙዎችን ይወርሳል፥ ከኃያላንም ጋር ምርኮን ይከፋፈላል፤ ነፍሱን ለሞት አሳልፎ ሰጥቶአልና፥ ከዓመፀኞችም ጋር ተቈጥሮአልና እርሱ ግን የብዙ ሰዎችን ኃጢአት ተሸከመ፥ ስለ ዓመፀኞችም ማለደ።

❤9👍6🔥2
' ==❀❀❀===❀❀❀==
የዕለቱ ጥቅስ
==❀❀❀===❀❀❀==
“ዮናስ በዓሣ አንባሪ ሆድ ሦስት ቀንና ሦስት ሌሊት እንደ ነበረ፥ እንዲሁ የሰው ልጅ በምድር ልብ ሦስት ቀንና ሦስት ሌሊት ይኖራል።”
ማቴዎስ 12፥40

👍7❤1
#ትንሣኤ
#ፋሲካ
ኢየሱስ የተሰቀለው ዓርብ ነውን? ከሆነስ፣ በመቃብር ውስጥ ሦስት ቀናትን እንዴት ያሳልፋል፣ እሑድ እስከ ተነሣ ድረስ?
መጽሐፍ ቅዱስ ኢየሱስ በየትኛው የሳምንቱ ቀናት እንደተሰቀለ በዝርዝር (ቁልጭ ባለ መልኩ) አያስቀምጥም። ሁለቱ በስፋት የሚታወቁት አስተያየቶች ዓርብና ረቡዕ ናቸው። አንዳንዶች፣ ሆኖም፣ ሁለቱንም ዓርብና ረቡዕን አዳብሎ (አቀናጅቶ) በመውሰድ ዕለቱ ኀሙስ ነው ብለው ይከራከራሉ።
ኢየሱስ በማቴዎስ 12፡40 እንዳለው፣ “ዮናስ በዓሣ አንባሪ ሆድ ሦስት ቀንና ሦስት ሌሊት እንደ ነበረ፥ እንዲሁ የሰው ልጅ በምድር ልብ ሦስት ቀንና ሦስት ሌሊት ይኖራል።” ስቅለቱ ዓርብ እንደሆነ የሚከራከሩ፣ እንደሚሉት ተቀባይነት ያለው መንገድ አሁንም ቢሆን ይኖራል፣ ሦስት ቀን በመቃብር ይሆን ዘንድ። በአንደኛው ክፍለ ዘመን የአይሁድ አስተሳሰብ የቀን እኩሌታ እንደ ሙሉ ቀን ይወሰዳል። ኢየሱስ የዓርብ እኩሌታን በመቃብር ከሆነ፣ ቅዳሜ ሙሉ ቀን፣ እንዲሁም የእሑድ እኩሌታ — እናም እሱ በመቃብር ውስጥ ለሦስት ቀናት መኖሩን ግምት ውስጥ መውሰድ ይቻላል። አንደኛው ዋነኛ የዓርብ መከራከርያ የሚገኘው ማርቆስ 15፡42 ሲሆን፣ እሱም የሚያመለክተው ኢየሱስ የተሰቀለው “ከሰንበት በፊት መሆኑን ነው።” ያ የሳምንቱ ሰንበት ከሆነ፣ ማለትም ቅዳሜ፣ እናም ያ ሐቅ ወደ ዓርብ ስቅለት ያመራል። ሌለኛው የዓርብ ክርክር የሚለው እንደ ማቴዎስ 16፡21 እና ሉቃስ 9፡22 የመሳሰሉት ቁጥሮች የሚያስተምሩት ኢየሱስ በሦስተኛው ቀን እንደሚነሣ ነው፤ ስለሆነም፣ ሙሉውን ሦስት ሌሊትና ቀናት የግድ በመቃብር ውስጥ መቆየት አያስፈልገውም። ነገር ግን አንዳንድ ትርጉሞች “በሦስተኛው ቀንን” ይጠቀማሉ፣ ለእነዚህ ቁጥሮች፣ ሁሉም ግን አያደርጉም፣ እናም ሁሉም “በሦስተኛው ቀን” በሚለው አይስማማም፣ እነዚህን ቁጥሮች በተሻለ ለመተርጎም። ከዚህም በላይ፣ ማርቆስ 8፡31 ኢየሱስ ከሦስት ቀናት “በኋላ” ይነሣል ይላል።
የኀሙስ ክርክር የሚያያዘው ከዓርብ እይታ ጋር ሆኖ፣ የሚከራከረውም በአብዛኛው በወቅቱ በርካታ ሁነቶች ነበሩ (አንዳንዶቹ እስከ ሃያ ያደርሱታል) ሁነቶቹም ከክርስቶስ መቀበር እና እሑድ ጠዋት ሆነው የተፈጠሩትም ከዓርብ ምሽት እስከ እሑድ ጠዋት ይደርሳሉ። የኀሙስ ተከራካሪዎች አስተሳሰባቸው የሚያመለክተው ዋነኛው ችግር በዓርብና በእሑድ መሐል የሚገኘው ብቸኛ ሙሉ ቀን ቅዳሜ መሆኑን ነው፣ የአይሁድ ሰንበት። አንድ ተጨማሪ ቀን ወይም ሁለት ነው፣ ይህን ችግር ሊያቃልል የሚችለው። የኀሙስ ተከራካሪዎች ይሄን ምክንያት ሊያቀርቡ ይችላሉ፡ ጓደኛህን እስከ ሰኞ ምሽት አላየኸውም እንበል። በቀጣዩ ጊዜ የተመለከትከው ኀሙስ ጠዋት ነው፣ እናም አንተ የምትለው፣ “እነዚህን ሦስት ቀናት አላየውህም” ብለህ ነው፣ ምንም እንኳ ባቆጣጠር 60 ሰዓታት (2.5 ቀናት) ብቻ ቢሆንም። ኢየሱስ ኀሙስ ከተሰቀለ፣ ይህ ምሳሌ እንዴት ሦስት ቀናት እንደሆነው ያሳያል።
የረቡዕ አስተያየት መሠረት የሚያደርገው በዛ ሳምንት ሁለት ሰንበታት መኖራቸውን ነው። ከመጀመሪያው በኋላ (በስቅለቱ ምሽት ከሆነው [ማርቆስ 15፡42፤ ሉቃስ 23፡52-54])፣ ሴቶቹ ሽቶውን ገዙ— እነሱ ግብይት የሚያደርጉት ከሰንበት በኋላ መሆኑን ተገንዘብ (ማርቆስ 16፡1)። የረቡዕ አስተሳሰብ የሚነሣው ይህ “ሰንበት” ፋሲካ እንደሆነ ነው (ሌዋውያን 16፡29-31፣ 23፡24-32፣ 39፣ ታላቅ የክብረ በዓል ቀናት የግድ የሳምንቱ ሰባተኛ ቀን ያልሆኑ ሰንበት ተብለው ተጠቅሰውልናል)። ሁለተኛው የዛ ሳምንት ሰንበት መደበኛው ሳምንታዊ ሰንበት ነው። በሉቃስ 23፡56 ያለውን ተመልከት፣ ሽቶውን የገዙት ሴቶች፣ ከመጀመሪያው ሰንበት በኋላ ተመልሰው ሽቶውን አሰናዱት፣ ከዚያም “በሰንበት ዐረፉ” (ሉቃስ 23፡56)። ክርክሩ መሠረት የሚያደርገው እነሱ ከሰንበት በኋላ ሽቶውን መግዛት እንደማይችሉ ነው፣ እናም ሽቶውን ከሰንበት በፊት ያዘጋጃሉ— አለበለዚያ ሁለት ሰንበታት እስካልሆኑ ድረስ። በሁለት ሰንበት እይታ፣ ክርስቶስ ኀሙስ ከተሰቀለ፣ እናም ታላቁ ቅዱስ ሰንበት (ፋሲካ) ኀሙስ ይጀምራል ማለት ነው ፀሐይ ስትጠልቅ አንሥቶ ዓርብ ፀሐይ ስትጠልቅ ያበቃል— በሳምንታዊው ሰንበት ወይም ቅዳሜ መጀመሪያ ላይ። ከመጀመሪያው ሰንበት የሽቶ ግዥው ቢፈጸም (ፋሲካ) በቅዳሜ ገዝተውታል ማለት ይሆናል፣ በዚህም ሰንበትን ይሽራሉ።
ስለሆነም፣ እንደ ረቡዕ አተያይ ከሆነ፣ ብቸኛው መጽሐፍ ቅዱስን የማይጣረሰው፣ የሴቶቹንና የሽቶውን በተመለከተ በጥሬው በማቴዎስ 12፡40 ላይ የሰፈረው፣ ክርስቶስ ረቡዕ ተሰቅሏል ማለት ነው። ታላቁ ቅዱስ ሰንበት ቀን (ፋሲካ) ኀሙስ ሆኗል ማለት ነው፣ ሴቶቹ ሽቶውን ገዝተው (ከዚያ በኋላ) በዓርብ እንዲሁም ተመልሰው ሽቶውን ያሰናዳሉ በዚያው ቀን፣ እነሱም ቅዳሜ ያርፋሉ በሳምንቱ ሰንበት፣ ከዚያም ሽቶውን ይዘው እሑድ በማለዳ ወደ መቃብር መጥተዋል። ኢየሱስ የተቀበረው ረቡዕ ፀሐይ ስትጠልቅ አካባቢ ነው፣ እሱም እንደ አይሁድ የቀን አቆጣጠር ኀሙስ የሚጀምርበት ነው። የአይሁድን የቀን አቆጣጠር በመያዝ፣ ኀሙስ ምሽት ይኖራችኋል (አንደኛ ምሽት)፣ ኀሙስ ቀን (አንደኛ ቀን)፣ ዓርብ ምሽት (ሁለተኛ ምሽት)፣ ዓርብ ቀን (ሁለተኛ ቀን)፣ ቅዳሜ ምሽት (ሦስተኛ ምሽት)፣ ቅዳሜ ቀን (ሦስተኛ ቀን)። መቼ እንደ ተነሣ በትክክል አናውቀውም፣ ነገር ግን እሑድ ፀሐይ ከመውጣቷ በፊት እንደሆነ እናውቃለን (ዮሐንስ 20፡1፣ መግደላዊት ማርያም “ገና ጨለማ ሳለ” መጣች)፣ ስለዚህ ሊነሣ የሚችለው ፀሐይ ከጠለቀች በኋላ ቅዳሜ ሌሊት ነው፣ እሱም ለአይሁድ የሳምንቱ የመጀመሪያ ቀን።
በረቡዕ እይታ ላይ ሊኖር የሚችለው ችግር ከኢየሱስ ጋር በኢማኦስ መንገድ ከኢየሱስ ጋር የተጓዙት ደቀ መዛሙርት በተመሳሳይ መልኩ “በዛኑ ቀን” በእሱ ትንሣኤ መሆኑ ነው (ሉቃስ 24፡13)። ደቀ መዛሙርት፣ ኢየሱስን ስላላወቁት፣ ስለ ኢየሱስ ስቅለት ነገሩት (24፡21) እንዲህ በማለት “ይህም ነገር ከሆነ እነዚህ ሦስተኛ ቀናት ናቸው” (24፡22)። ከረቡዕ እስከ እሑድ አራት ቀናት ነው። ሊሆን የሚችለው ቆጠራውን የጀመሩት ከረቡዕ ምሽት ከኢየሱስ ቀብር፣ ከአይሁድ ኀሙስ ጀምሮ ነው፣ ለኀሙስ እስከ እሑድ ሲቆጠር ሦስት ቀን ይሆናል።
ከነገሮች የክብደት ደረጃ አኳያ፣ ኢየሱስ ከሳምንቱ በየትኛው ቀን እንደተሰቀለ ማወቁ አስፈላጊ ላይሆን ይችላል። በጣም አስፈላጊ ቢሆን ኖሮ፣ የእግዚአብሔር ቃል የቀንና የጊዜውን ሂደት በግልጽ ባስቀመጠው ነበር። ጠቃሚ የሚሆነው የእሱ በሥጋ መሞት ነው ፣ እንዲሁም በአካል ከሙታን መነሣቱ። በተመሳሳይ መልኩ ጠቃሚ የሚሆነው የሞተበት ምክንያት ነው— ሁሉም ኃጢአተኞች ይገባቸው የነበረውን ቅጣት መውሰድ ነው። ዮሐንስ 3፡16 እና 3፡36 ሁለቱም የሚገልጹት በእሱ ላይ እምነትን ማኖር ውጤቱ የዘላለም ሕይወት ነው! ይህ እንግዲህ እሱ ረቡዕም፣ ኀሙስም፣ ወይም ዓርብ ቢሰቀል ያው ነው።
ምንጭ፦ www.gotquestions.org

👍5❤3
ውድ የቻናላችን ቤተሰቦች "ማን ያንከባልልናል?" በምንላቸው ጉዳዮች ሁሉ ላይ ድንጋዩ ተንከባሎ የምንመለከትበት በዓል ይሁንልን! መልካም በዓል!!! መልካም ምኞታችሁን በኮሜንት መግለጽ ትችላላችሁ
"እርስ በርሳቸውም፦ ድንጋዩን ከመቃብር ደጃፍ ማን ያንከባልልልናል? ይባባሉ ነበር፤ ድንጋዩ እጅግ ትልቅ ነበርና፤ አሻቅበውም አይተው ድንጋዩ ተንከባሎ እንደ ነበር ተመለከቱ።"
ማርቆስ 16፥3-4
ወደ ቻናሉ ለመ🀄️ላ🀄️ል፦ @Holy_scriptures
"እርስ በርሳቸውም፦ ድንጋዩን ከመቃብር ደጃፍ ማን ያንከባልልልናል? ይባባሉ ነበር፤ ድንጋዩ እጅግ ትልቅ ነበርና፤ አሻቅበውም አይተው ድንጋዩ ተንከባሎ እንደ ነበር ተመለከቱ።"
ማርቆስ 16፥3-4
ወደ ቻናሉ ለመ🀄️ላ🀄️ል፦ @Holy_scriptures
❤5👍5
' ==❀❀❀===❀❀❀==
የዕለቱ ጥቅስ
==❀❀❀===❀❀❀==
“ሞት በሰው በኩል ስለ መጣ ትንሣኤ ሙታን በሰው በኩል ሆኖአልና።”
1ኛ ቆሮንቶስ 15፥21

👍7❤3
' ==❀❀❀===❀❀❀==
የዕለቱ ጥቅስ
==❀❀❀===❀❀❀==
“ያም ቀን እርሱም ከሳምንቱ ፊተኛው በመሸ ጊዜ፥ ደቀ መዛሙርቱ ተሰብስበው በነበሩበት፥ አይሁድን ስለ ፈሩ ደጆቹ ተዘግተው ሳሉ፥ ኢየሱስ መጣ፤ በመካከላቸውም ቆሞ፦ ሰላም ለእናንተ ይሁን አላቸው።”
ዮሐንስ 20፥19

❤3👍2
ትንሣኤ ሙታን
ወ/ዊ ያሬድ ጥላሁን
ክፍል-1
የክርስትና እምነት ምንድነው? ይህ ጥያቄ በአንደኛው ክፍለ ዘመን ለሚኖር ሰው ቢቀርብለት፣ ያለምንም ማመንታት “የትንሣኤ እንቅስቃሴ ነው!” ሊል እንደሚችል መገመት አያስቸግርም። ለዚህም በርካታ ማረጋገጫዎች አሉ። ከብዙዎቹ ጥቂቶቹን ላንሳ፡ -
የትንሣኤው ምሥክሮች፡ - ጌታ ኢየሱስ አገልግሎቱን የጀመረው ምሥክሮቹ የሚሆኑትን የዛሬ ደቀመዛሙርት የነገዎቹንም ሐዋርያት በመጥራት ነበር። የኃይማኖት መናኽሪያ ከሆነችው ኢየሩሳሌም ርቆ መልካም ነገር ሊወጣባት ይችላል ተብላ በማትገመተው የገሊላዋ ናዝሬት ሰዎችን መጥራት ጀመረ። ያልተማሩ ማንበብና መጻፍ የማያውቁ አሣ አጥማጆችና ቀራጮችን ሰብሰበ። በርግጥ እንኯን ሌላው ሰው፣ ራሳቸውም ቢሆኑ የተጠሩበትን ዓላማ በጊዜው አልተረዱም። የወንጌላውያኑን ትረካ በትዕግሥትና በጥሞና ስንከታተል ግን የተጠሩበት ዓላማ ፍንትው ብሎ ይታየናል። ይኽውም የትንሣኤው ምሥክሮች እንዲሆኑ ነው። መወለዱ ምሥክር አላስፈለገውም፣ ምክንያቱም ሰው ሁሉ ይወለዳል፣ በሰዎች መሃል መኖሩ የመወለዱ ማርጋገጫ ነው። መጠመቁ ምሥክር አላስፈለገውም፣ ማንም ሰው ይጠመቃላ! ሞቱም ቢሆን ምሥክር አላስፈለገውም፣ የተሰቀለውና የሞተው በሰው ሁሉ ፊት ነዋ! ካህናት ነበሩ፣ ፈሪሳውያን ነበሩ፣ ጻህፍት ነበሩ፣ ወዳጆቹ ነበሩ፣ የሮማ ወታደሮች ነበሩ፣ ምኑ ቅጡ በኢየሩሳሌም የሚኖሩ ሁሉ የሞቱን ዜና ሰምቷል፣ ደግሞም ሰው ሁሉ ይሞታል! ስለዚህ ምሥክር አላስፈለገውም። ነገር ግን በአካል ከሙታን መነሳቱ ምስክሮች አስፍልገውታል። ምክንያቱም የሞተ ሰው ተነስቶ አያውቅም፣ የኢየሱስ ትንሳኤ ከሞት መንቃትና ነፍስ መዝራት ሳይሆን ሙሉ በሙሉ በተለወጠና ልዕለ ተፈጥሮአዊ በሆነ የሕይወት ኃይል ነው የተነሳው። ተነስቶም አርባ ቀናት በብዙ ማስረጃ የታየው ለእነዚሁ ለመረጣቸው ምሥክሮቹ ነው። ምንም እንኩዋ ምሥክሮቹ አብና መንፈስ ቅዱስ፣ የነብያት ድምፆች የሆኑት ቅዱሳት መጻህፍት ጭምር ቢሆኑም የሐዋርያቱ ምሥክርነት ግን ድርሻው የማይናቅ ነው፣ ለሰው ልጅ ቅርብ ናቸዋ!
እምነት፡- ሐዋርያቱ ከሥፍራ ሥፍራ እየተዘዋወሩ ወንጌልን ሰበኩ። ለመሆኑ የሰበኩት የምሥራች ወንጌል ምንድን ነበር? ስለ ሰው ልጆች ኃጢአት የተሰዋው መሢሁ ኢየሱስ ከሙታን መነሳቱ ነው። ስለዚህ ያወጁት ትንሳኤውን ነው። ሉቃስ በሐዋ. 4፡33 “ሐዋርያትም የጌታን የኢየሱስ ክርስቶስ ትንሳኤ በታላቅ ኃይል ይመሠክሩ ነበር፣ በሁሉም ላይ ታላቅ ፀጋ ነበረባቸው” ይለናል። የኢየሩሳሌም ሐዋርያት ሆኑ የአሕዛብ ሐዋርያ ሊሆን የተሾመው ጳውሎስ ከትንሣኤው ውጪ የሰበኩት ወንጌል የለም። የተሰበከላቸውም ሰዎች እንዲያምኑ የተጠየቁት ሌላ ሳይሆን ስለ በደላችው የሞተው ኢየሱስ ከሙታን መነሣቱን ነው። እንደ ሮሜ መልዕክት ከሆነ መጽደቅም ሆነ መዳን የሚገኝው ሰው የኢየሱስ ክርስቶስን ትንሣኤ ሲያምን ብቻ ነው። ለዚህም ይህን ክፍል እንደ ዋቢ መመልከት ይበቃል። “ኢየሱስ ጌታ እንደሆነ በአፍህ ብትመሠክር፣ እግዚአብሔርም ከሙታን እንዳነሣው በልብህ ብታምን ትድናለህ” ሮሜ 10፡9። ስለዚህ በአዲስ ኪዳን የሚሠበከውም ትንሣኤ፣ የሚታመነውም ትንሳኤ ነው። አብርሃም የእምነት አባት ነው። “የእምነት አባት” ምን ማለት ነው? እግዚአብሔር የአብርሃምን እምነት ደረጃና ልክ አድርጎ መድቦታል። የሚቀበለው፣ የሚያከብረውና በምላሹም ጽድቅን የሚያጎናፅፈው እምነት የአብርሃም ዓይነት እምነት ነው። የአብርሃም እምነት ምን ነበር? ትንሳኤ ነበር። እግዚአብሔር ለሙታን ሕይወትን ይሰጣል፣ የሞቱትን ያስነሣል ብሎ አመነና እምነቱ ጽድቅ ሆኖ ተቆጠረለት። አብርሃም ትንሳኤን በጥቂቱም ቢሆን የተለማመደው በራሱ ሰውነትና በሚስቱ በሣራ ሰውነት ላይ ነው። “የመቶ ዓመትም ሽማግሌ ስለሆነ እንደ ሙት የሆነውን የራሱን ሥጋና የሣራን ማህፀን ሙት መሆኑን በእምነቱ ሳይደክም ተመለከተ . . . ስለዚህም ደግሞ ጽድቅ ሆኖ ተቆጠረለት” ሮሜ 4፡19፣22። ስለዚህ ማንም ‘እግዚአብሔር ሙታንን ያሥነሣል፣ ኢየሱስንም ከሙታን አስነሥቶታል’ ብሎ ቢያምን በእርግጥ የአብርሃም ልጅ ሆኗል፣ እግዚአብሔርም እምነቱን ጽድቅ አድርጎ ቆጥሮለታል። ለዚህ ነው ‘የአዲስ ኪዳን እምነት የትንሣኤ እምነት ነው’ የምንለው።
የእግዚአብሔር ማንነት፡- እግዚአብሔር ሁሉን ቻይ ነው። ነገር ግን መታወቅም ሆነ መታመን የሚፈልገው በአንድ ነገር ነው። “ለሙታን ሕይወትን የሚሰጥ፣ የሌለውንም እንዳለ አድርጎ የሚጠራ አምላክ” ሆኖ። [ሮሜ 4፡17] ለምን? እግዚአብሔር የሕይወት መንፈስ ነዋ! እርሱ ራሱ የዘላለም ሕይወት ነው። የማይሞት፣ የማይጠፋ፣ የማያልፍ የሕይወት ኃይል! ይህ ሕይወት የሕብረት ሕይወት ነው፤ ከአንድ በላይ የሆኑ አካላት በአንድ ጊዜ ሊካፈሉ የሚችሉት አስገራሚ ሕይወት። እግዚአብሔር በፀጋው ባለጠግነት ይህን ሕይወት ከሰው ልጅ ጋር ሊካፈለው ወደደ። ትንሣኤን ከሥላሴ አንፃር ብናየው፣ ኢየሱስን ከሙታን ያስነሳው ማነው? ለሚለው ጥያቄ የተለያዩ መልሶች እናገኛለን። መጽሐፍ ቅዱስ እግዚአብሔር አብ እንዳስነሣው ይነግረናል፣ ነገር ግን አንድ ሥፍራ ጌታ ራሱ “ነፍሴን ደግሞ አነሣት ዘንድ አኖራለሁና፣ ስለዚህ አብ ይወደኛል። እኔ በፈቃዴ አኖራታለሁ እንጂ ከእኔ ማንም አይወስዳትም። ላኖራት ሥልጣን አለኝ ደግሞም ላነሣት ሥልጣን አለኝ፣ ይህችን ትዕዛዝ ከአባቴ ተቀበልሁ” ዮሐ. 10፡18 ሲል እናነባለን። በሌሎች ክፍሎች ደግሞ መንፈስ ቅዱስ እንዳስነሳው እናነባለን። እነዚህን ክፍሎች ስንገጣጥማቸው የምናገኝው ሥዕል አብ፣ ወልድ፣ መንፈስ ቅዱስ አንድ አምላክ ሙታንን የሚያነሣ የትንሣኤ አምላክ መሆኑን ነው።
ይቀጥላል...
ምንጭ:- semayawithought.com

👍16
' ==❀❀❀===❀❀❀==
የዕለቱ ጥቅስ
==❀❀❀===❀❀❀==
“አሁንም፥ ልጆች ሆይ፥ በሚገለጥበት ጊዜ እምነት እንዲሆንልን በመምጣቱም በእርሱ ፊት እንዳናፍር በእርሱ ኑሩ።”
1ኛ ዮሐንስ 2፥28

❤6👍4
ትንሣኤ ሙታን
ወ/ዊ ያሬድ ጥላሁን
ክፍል-2
(የመጨረሻ ክፍል)
ሞት፡- የሰውን ልጅ ሁሉ ያንበረከከ፣ ጀግኖችን ያልፈራ፣ ነገሥታትን ያላፈረ፣ አዛውንትን ያላከበረ የሰው ጠላት ከሞት በላይ ማን ይኖር ይሆን!? በኃጢአት በኩል ወደ ዓለም ገብቶ በሥጋ ሁሉ ላይ የነገሠ፣ ከአዳም አንስቶ እስከ ሙሴ ከሕግ በፊትም ሆነ ከሕግ በኃላ የተንሰራፋ፣ የሰውን ልጅ ሁሉ አይሁድ ግሪክ ሳይል አንገት ያስደፋ ከሞት በላይ ማን ይኖር ይሆን? ሰው የፈለገውን ያህል ሃብት ቢያከማች፣ ዲግሪ ቢደረድር፣ ማዕረግ ቢጭን፣ ዝናው ቢናኝ ቀና ብሎ ነገን ሲያስብ አንድ ነገር ተስፋውን ያጨልምበታል። ሞት! ለዚህ ይሆን ያገሬ ሰው ልጁን “ሞት ባይኖር” ብሎ ስም የሚያውጣው? ሞት የሚያስፈራራን ሲገድለን ብቻ ቢሆን ምንኛ መልካም ነበር? ሞት አንዴ ነዋ! ነገር ግን እንደ ዕብራዊያን መልዕክት ጸሐፊ በሕይወታችን ዘመን ሁሉ ያስፈራራናል፡-
“እንግዲህ ልጆቹ በሥጋና በደም ስለሚካፈሉ፣ እርሱ ደግሞ በሞት ላይ ሥልጣን ያለውን በሞት እንዲሽር፣ ይኽውም ዲያቢሎስን ነው፣ በሕይወታቸውም ሁሉ ስለ ሞት ፍርሃት በባርነት ይታሰሩ የነበሩትን ሁሉ ነፃ እንዲያወጣ፣ በሥጋና በደም እንዲሁ ተካፈለ” ዕብ. 2፡14-15።
በዓለም ታሪክ ከሞት ወዲህ በሥጋ ሕይወት ላሉ የሰው ልጅ ችግሮች ሁሉ ሰው መፍትሄ ከማበጀት አልቦዘነም። እስቲ ትራንስፖርት፣ መገናኛ ብዙሃን፣ የህክምና ሳይንስ ወ.ዘ.ተ የደረሰበትን እንመልከት። ችግራችን ገንዘብ ቢሆን፣ ጤና፣ እውቀት ቢሆን ዝና ሰዎች ሊፈቱት ይችላሉ። ችግራችን ሲገለጥ ወዳጅ ዘመድ ይረባረባል፣ የቅርብ የሩቁ የራሱን ድርሻ ይጫወታል። ነገር ግን አንዴ ሞት ጥላውን ካጠላ ሰብዓዊ መፍትሄ ይሟጠጣል፣ ተስፋ ይቆረጣል፣ ከዋይታና ከሰቀቀን በስተቀር ሊዋጣ የሚችል መላ የለም። ሞት ግን ለእግዚአብሔር ብ ቻ የሚተው ጉዳይ ነው። ለዚህ ነው እግዚአብሔር ለሙታን ሕይወትን የሚሠጥ አምላክ ሆኖ የተገለጠው። እግዚአብሔር የሚፈልገው አንድ ነገር ብቻ ነው። መታመን! የሞቱትን ሰውነታቸው የበሰበሰውንና የፈረሰውን እንደገና የክብር ሕይወት ሰጥቶ እንደሚያነሣ፣ ይህንንም መሢህ ኢየሱስን ከሙታን በማስነሣቱ እንዳረጋገጠ፣ ቀን እንደቀጠረ በዚያም ቀን ሙታንን በእርግጥ እንደሚያነሣ፣ አስቀድሞ የእርሱ የሆኑትን በኃላም ሁሉን አስነስቶ ክብር ለሚገባው ክብርን፣ ውርደት ለሚገባውም እንደ ሥራው ለሁሉ እንደሚከፍል መታመን ይፈልጋል። እምነት ማለት ይህ ነው፣ ለሙታን ሕይውትን በሚሰጥ አምላክ ተደግፎ በሞት ላይ የሚስቅ ሕያው እምነት።
ተስፋ፡- ጌታ ኢየሱስ ከሙታን እንደተነሣ ምንም ያህል አስቀድሞ፣ ደጋግሞ የነገራቸው ቢሆንም ትንሣኤን ለማመን ልባቸው የዘገየውን ደቀመዛሙርቱን ለማስረዳት ያደረገው ነገር ቢኖር መጽሐፍትን ያስተውሉ ዘንድ አዕምሯቸውን መክፈት ነው። ይህም ትንሣኤው አስቀድሞ የተሰጠ መለኮታዊ ተስፋ መሆኑኑ ያረጋግጥልናል። እግዚአብሔር የተስፋ አምላክ ነው። ታዲያ ተስፋ መስጠት የጀመረው የተስፋው ወራሽ የሆነው ሰው ከተፈጠረ በኃላ ብቻ አልነበረም። ሐዋርያው ጳውሎስ በመንፈስ ቅዱስ መረዳት ወደ ዘላለም መጥቆ ዐለም ሳይፈጠር ስለተከናወነ አንድ ተግባር ይተርክልናል፡-
“ስለዚህም ሕይወት የማይዋሽ እግዚአብሔር ከዘላለም ዘመናት በፊት ተስፋን ሰጠ” ቲቶ 1፡2
“በክርስቶስ ኢየሱስ እንደሚሆን የሕይወት ተስፋ በእግዚአብሔር ፈቃድ የኢየሱስ ክርስቶስ ሐዋርያ የሆነ ጳውሎስ” 2ጢሞ. 1፡1
“… ይህም ፀጋ ከዘላለም ዘመናት በፊት በክርስቶስ ኢየሱስ ተሰጠን፣ አሁን ግን በመድኃኒታችን በኢየሱስ ክርስቶስ መገለጥ ታይቷል። እርሱ ሞትን ሽሯልና … በወንጌል ሕይወትንና አለመጥፋትን ወደ ብርሃን አውጥቷል” 2ጢሞ. 1፡9-11
ይህ የዘላለም ተስፋ ነው በዘመናት ውስጥ ከእግዚአብሔር ዘንድ ለአባቶች የተሰጠው። ተስፋው በሙሉ ከትንሳኤ ጋር የተያያዘ ነው። እግዚአብሔር በዘመናት ውስጥ ከተለያዩ ሰዎች ጋር ኪዳን የገባ ቢሆንም “ቅዱስ” ተብሎ የተጠራ ኪዳን እግዚአብሔር ከአብርሃምና ከዳዊት ጋር የገባው “የተስፋ ኪዳን” ነው። ተስፋችን ስንሞት ሥጋችን ወደ አፈር፣ ነፍሳችን ወደ እግዚአብሔር ሄዳ በዚያ ለዘላለም መኖራችን አይደለም። በፍፁም አይደለ! ምንም እንክዋ ነፍሳችን ከሥጋችን ከምትለይበት አንስቶ ጌታ ዳግመኛ እስኪመጣና የአካል ትንሣኤ እስኪሆን ድረስ ሕያው የሆነች ነፍሳችን በጌታ ዘንድ የምትቆይ ቢሆንም ያ ተስፋችን አይደለም። እዚያም ሆነን በናፍቆት የምንጠብቀው ተስፋ የሥጋ ትንሣኤን ይመሥለኛል። ለዚህ አይደል የጌታን ዳግም መምጣት ሲያወሳ ጳውሎስ “የተባረከው ተስፋችን የታላቁ የአምላካችንና የመድኃኒታችን የኢየሱስ ክርስቶስ መገለጥ” [ቲቶ 2፡11-13 በማለት የሚጠራው? ስለዚህ እኛም መገለጡን ከሚጠባበቁ አዕላፋት ቅዱሳን ጋር ተጨምረን “ማራናታ፡- አሜን ጌታ ኢየሱስ ሆይ ቶሎ ና!” እንበል። በቅድስና በመኖር ወንጌልንም በማሰራጨት መምጣቱን እናፋጥን።

👍10😁5❤1
' ==❀❀❀===❀❀❀==
የዕለቱ ጥቅስ
==❀❀❀===❀❀❀==
“ሰሎሞንም ይህን ነገር ስለ ለመነ፥ ነገሩ እግዚአብሔርን ደስ አሰኘው።”
1ኛ ነገሥት 3፥10

❤12
' ==❀❀❀===❀❀❀==
የዕለቱ ጥቅስ
==❀❀❀===❀❀❀==
“ኢዮአታምም በአምላኩ በእግዚአብሔር ፊት መንገዱን አቅንቶአልና በረታ።”
2 ዜና 27፥6
ወደ ቻናሉ ለመ🀄️ላ🀄️ል፦ @Holy_scriptures
የዕለቱ ጥቅስ
==❀❀❀===❀❀❀==
“ኢዮአታምም በአምላኩ በእግዚአብሔር ፊት መንገዱን አቅንቶአልና በረታ።”
2 ዜና 27፥6
ወደ ቻናሉ ለመ🀄️ላ🀄️ል፦ @Holy_scriptures
👍7❤2
የፀሎት ሃይል .pdf
6.2 MB
📔ርዕስ፦የፀሎት ኃይል
👤ደራሲ፦ሮናልድ ደን
🗣ተርጓሚ፦ ጳውሎስ ፈቃዱ (የብርሃን አንጓዎች ፣ የእግዚአብሔር ልጅ እና ያልተንኳኩ በሮች ደራሲ)
💾መጠን፦6.2MB

❤8👍3