ቅዱሳት መጻሕፍት
7.46K subscribers
1.37K photos
61 videos
332 files
808 links
በዚህ ቻናል

👉ቅዱሳት መጻሕፍት ይጠናሉ::
👉መጽሐፍ ቅዱሳዊ ትምህርቶች ይቀርባሉ::
👉 ለቅዱሳት መጽሐፍት ጥናት የሚያግዙ መጻሕፍት ይለቀቃሉ።

⭐️⭐️⭐️⭐️⭐️

@Holy_scriptures
Download Telegram
#ትንሣኤ
#ፋሲካ


#ሆሣዕና፣ ኢየሱስ ብዙ አጀብና ሙገሳ የገጠመው ቀን ነው። ነገር ግን "ስቀለው፣ ስቀለው" የሚል ተቃውሞም ከፊቱ ነበር። በዚህ ሁሉ ግን ዓላማውንና የምድር ጉዞውን በሚገባ ስለሚያውቅ በሰው ሁኔታ አልሞቀውም አልበረደውምም። እኛም ዓላማችንንና ፍጻሜያችንን በሚገባ በማወቅ በኑሮአችን ጸንተን ጌታችንን እንድናስከብር ጌታ ይርዳን!



ወደ ቻናሉ ለመ🀄️🀄️ል፦ @Holy_scriptures
👍4🔥21
ወደ ቻናሉ ለመ🀄️🀄️ል፦ @Holy_scriptures
6👍2🔥1
#ትንሣኤ
#ፋሲካ


#ሰኞ
ጌታ ሆይ፣ በቤትህ የምትናገረውን ሁሉ የምንሰማበት፣ የእኛም ጩኹት በአንተ ዘንድ የሚሰማበት የጸሎት ቤት ይሁን!


ወደ ቻናሉ ለመ🀄️🀄️ል፦ @Holy_scriptures
👍62
'    ==❀❀❀===❀❀❀==      
              የዕለቱ ጥቅስ
     ==❀❀❀===❀❀❀==
“ይህስ ስሜ የተጠራበት ቤት በዓይናችሁ የሌቦች ዋሻ ሆኖአልን? እነሆ፥ እኔ አይቻለሁ፥ ይላል እግዚአብሔር።”
             ኤርምያስ 7፥11



ወደ ቻናሉ ለመ🀄️🀄️ል፦ @Holy_scriptures
7👍1
#ሰኞ፣ ከሆሳዕና ማግሥት ጌታችን ከቢታንያ ወደ ኢየሩሳሌም ሲገባ ሁለት ነገሮችን አድርጓል፡፡ አንደኛ ከቅጠል በስተቀር ፍሬ ያልተገኘባትን ዕፀ በለስ ረግሟል፡፡ ሁለተኛ ወደ ቤተ መቅደስ ገብቶ የሚሸጡትንና የሚለውጡትን አስወጥቷል፡፡ (ማቴ.21÷12-17፤ ማር.11÷17፤ ሉቃ.19÷45-46፡፡)

መልእክት፦ ቤተ መቅደሱ እንዲሁም በለሷ የሚጠበቅባቸውን በተገቢው ሁኔታ አልያዙም።

👉 በለሷ ከፍሬ ጎድላ ተገኝታለች።
👉 ቤተመቅደሱ የማይጠበቅበትን ይዟል።

በቅዱስ ሉቃስ ወንጌል ላይ እንደተገለጸው ይህንም ምሳሌ አለ "ለአንድ ሰው በወይኑ አትክልት የተተከለች በለስ ነበረችው ፍሬም ሊፈልግባት ወጥቶ ምንም አላገኘም፡፡" ሉቃ 13፡6 በማለት በበለስ ስለተመሰለ የሰው ልጅ ሕይወት በማሰብ እንዲመለስ ንስሐ እንዲገባ በሕይወትም እንዲኖር እግዚአብሔር ኢየሱስ ክርስቶስ ማሳሰቡን ያጠይቃል፡፡ ንስሐ አልገባም አልመለስም ያለም በለሷ እንደጠወለገችና እንደተቆረጠች ሁሉ ፍሬ ባለማፍራታቸው እንደሚቆረጡ እንዲሁም ወደ እሳት እንደሚጣሉ መጽሐፍ ቅዱስ በግልጽ ያስረዳል፡፡ ፍሬ አልባ እንዳንሆን ጌታ ሲመጣም እንዳናፍር የመጽሐፉን ቃል ልንጠብቅና ልንፈጽም ይገባናል፡፡ በዚህ የሕማማት የመጀመሪያ ቀን ዕለተ ሰኞ የምናስበው የምንዘክረው የሰው ልጅ ሕይወት በከንቱ በቸልተኝነት እንዳይደክም እንዳይጠወለግ እንዳይደርቅ ወደ እሳትም እንዳይጣል ማድረግ ይገባናል፡፡

ጌታችን መድኃኒታችን ወደ ቤተ መቅደስ ግብቶ የሚሸጡትንና የሚለውጡትን እንዳስወጣ ሁሉ፤ ዛሬ የእግዚአብሔር ቤተሰቦች ጌታችን ወደ መቅደስ ሕይወታችን ቢመጣ ምን ያገኝ ይሆን? ፍፌስ እያፈራን ይሆን? የእግዚአብሔር ቃል ግን ለንስሐ የሚገባ ፍሬ አድርጉ ይለናል። ማቴ 3፡8

ምንጭ:- tesfalem7.blogspot.com




ወደ ቻናሉ ለመ🀄️🀄️ል፦ @Holy_scriptures
👍7
'    ==❀❀❀===❀❀❀==      
              የዕለቱ ጥቅስ
     ==❀❀❀===❀❀❀==
“አቤቱ፥ መንገድህን አመልክተኝ፥ ፍለጋህንም አስተምረኝ።”
            መዝሙር 25፥4



ወደ ቻናሉ ለመ🀄️🀄️ል፦ @Holy_scriptures
3👍3
#ማክሰኞ ኢየሱስ ለመጨረሻ ጊዜ በቤተ መቅድስ ያስተማረበት ቀን ነው።

ጌታ ከቃሉ ስንት ጊዜ አስተማረን? ምን ያህልስ ወደ ተግባር ለወጥነው? ወይስ እንደ ፈሪሳውያን በራሱ መጽሐፍ ላይ ጌታችንን እየተከራከርነውና አልፎ ተርፎም ከሕይወታችን ልናስወጣው እየከጀልን ይሆን? የማንስ ጽሕፈት በላያችን ይታያል?

ለመሆኑ ጌታችንና መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ምን አስተማረ? ወይም ምን ተማሩ አለ?

👉“እንግዲህ ከነዚህ ከሁሉ ካነሱት ትእዛዛት አንዲቱን የሚሽር ለሰውም እንዲሁ የሚያስተምር ማንም ሰው በመንግሥተ ሰማያት ከሁሉ ታናሽ ይባላል፤ የሚያደርግ ግን የሚያስተምርም ማንም ቢሆን እርሱ በመንግሥተ ሰማያት ታላቅ ይባላል።”
        ማቴዎስ 5፥19


👉“የሰው ልጅ ብዙ መከራ ሊቀበል፥ ከሽማግሌዎችም ከካህናት አለቆችም ከጻፎችም ሊጣል፥ ሊገደልም ከሦስት ቀንም በኋላ ሊነሣ እንዲገባው ያስተምራቸው ጀመር፤ ቃሉንም ገልጦ ይናገር ነበር።”
         ማርቆስ 8፥31

👉“ቀንበሬን በላያችሁ ተሸከሙ ከእኔም ተማሩ፥ እኔ የዋህ በልቤም ትሑት ነኝና፥ ለነፍሳችሁም ዕረፍት ታገኛላችሁ፤”
          ማቴዎስ 11፥29

👉“ሲያስተምርም እንዲህ አለ፦ ረጃጅም ልብስ ለብሰው መዞርን፥ በገበያም ሰላምታን፥ በምኵራብም የከበሬታን ወንበር፥ በግብርም የከበሬታን ስፍራ ከሚወዱ ከጻፎች ተጠበቁ፤”
         ማርቆስ 12፥38-39

👉 “እንግዲህ ሂዱና አሕዛብን ሁሉ በአብ በወልድና በመንፈስ ቅዱስ ስም እያጠመቃችኋቸው፥ ያዘዝኋችሁንም ሁሉ እንዲጠብቁ እያስተማራችኋቸው ደቀ መዛሙርት አድርጓቸው፤ እነሆም እኔ እስከ ዓለም ፍጻሜ ድረስ ሁልጊዜ ከእናንተ ጋር ነኝ።”
      ማቴዎስ 28፥19-20




ወደ ቻናሉ ለመ🀄️🀄️ል፦ @Holy_scriptures
15👍3
'    ==❀❀❀===❀❀❀==      
              የዕለቱ ጥቅስ
     ==❀❀❀===❀❀❀==
“ኢየሱስ ግን እንዲህ አለ፦ ተዉአት፤ ስለ ምን ታደክሙአታላችሁ? መልካም ሥራ ሠርታልኛለች።”
                ማርቆስ 14፥6



ወደ ቻናሉ ለመ🀄️🀄️ል፦ @Holy_scriptures
10👍1
#ረቡዕ የአስቆሮቱ ይሁዳ ኢየሱስን የካደበት ቀንና ማርያም (በማርቆስ ስሟ አልተጠቀሰም) በኢየሱስ እግር ስር ሽቶ ያፈሰሰችበትና በጸጉሯ ያበሰችበት ቀን ነው። (ማር. 14 ) እዚህ ጋር አንድ ነገር ማስቀመጥ ወደድኩ። ይህ ቀን ብዙ ጊዜ ከኢየሱስ ጋር የተጓዙ ሰዎች ትጥቃቸው መፈታት የጀመረበትና እውነተኛ ማንነታቸው የተገለጠበት ቀን ነበር። ከዚህ በፊት በርትተው ይጓዙ የነበሩ ሁሉ የሥጋ ድካም በብርቱ መገዳደር እና መጣል የጀመራቸው ጊዜ ነበር። አንዳዶች ወድቀው ሲነሱ አንዱ እስከወዲያኛው ወደቀ። በነገራችን ላይ የዚህን የሥጋን ከመንፈስ ጋር ለማበር መቸገር መፍትሄ በጌቴሴማኒ ነገራቸው ። እንዲህ በማለት፦ “ወደ ፈተና እንዳትገቡ ትጉና ጸልዩ፤ መንፈስስ ተዘጋጅታለች ሥጋ ግን ደካማ ነው አለው።” (ማቴዎስ 26፥41)

ወደ ረቡዕ ቀን ስንመለስ ይሁዳ እንዲህ አይነት ሰው ነበር፦
"ይህንም የተናገረ ሌባ ስለ ነበረ ነው እንጂ ለድሆች ተገድዶላቸው አይደለም፤ ከረጢትም ይዞ በውስጡ ከሚገባው ይወስድ ስለ ነበረ ነው።" (ዮሐ. 12፡6) በሌላ በኩል ደግሞ በምን ሰዓት ምን ማድረግ እንዳለባት የምታውቅን ሴት እንመለከታለን። ኢየሱስ ከሞተ በኋላ ለአካሉ ሽቶ ለመቀባት አስበው የሄዱ ቢኖሩም መቅደላዊት ማርያም ግን መችና የት ኢየሱስን ማግኘት እንደሚቻል የምታውቅ ሴት ነበረች። እናም የዛሬው ቀን ከኢየሱስ ጋር ለዘለአለሙ ለመጓዝ ኃይል እንድናገኝ፣ ከእርሱ አሳብና አጀንዳ ጋር ደግሞ ተባብረን እንድንጓዝ ጌታ ይርዳን!




ወደ ቻናሉ ለመ🀄️🀄️ል፦ @Holy_scriptures
10👍5
'    ==❀❀❀===❀❀❀==      
              የዕለቱ ጥቅስ
     ==❀❀❀===❀❀❀==
“እርሱም፦ ይህ ስለ ብዙዎች የሚፈስ የአዲስ ኪዳን ደሜ ነው።”
                ማርቆስ 14፥24



ወደ ቻናሉ ለመ🀄️🀄️ል፦ @Holy_scriptures
7👍2
#ሀሙስ ጌታችንና መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ከመሞቱ በፊት ከደቀ መዛሙርቱ ጋር የመጨረሻውን እራት የበላበትንና በእውነት ለእርሱ ተከታይ ለሆኑት ብርቱና መሰረታዊ ትምህርት፣ ምክር፣ ተግጻጽ ሲያስፈልግም በተግባር የተደገፈ ትምህርት ያስተላለፈበት እንዲሁም አሁን በመንግስቱ ላሉ በኋላም ለሚመጡ የጸለየው አስደናቂ ጸሎት፣ የደቀ መዛሙርቱ ድካም. . . ወዘተ የሀሙስ ቀን ሁነቶች ናቸው።

በገነት አዳም ከእግዚአብሔር አሳብ ይልቅ የራሱን መርጦ ለሰው ፍዳን አመጣ ከገነትም ተባረረ። ኢየሱስ ግን ከራሱ መከራ ይልቅ የአባቱን ፈቃድ አስቀደመ። አምላክ እና ጌታ ሆኖ ሳለ ሰውን አገለገለ።

"እናንተ መምህርና ጌታ ትሉኛላችሁ፤ እንዲሁ ነኝና መልካም ትላላችሁ። እንግዲህ እኔ ጌታና መምህር ስሆን እግራችሁን ካጠብሁ፥ እናንተ ደግሞ እርስ በርሳችሁ እግራችሁን ትተጣጠቡ ዘንድ ይገባችኋል። እኔ ለእናንተ እንዳደረግሁ እናንተ ደግሞ ታደርጉ ዘንድ ምሳሌ ሰጥቻችኋለሁና።" (ዮሐንስ 13፥13-15 )
                    
የሚገርመኝ ነገር ቢኖር ኢየሱስን ከመከራሁ እንዲቀርና እርሱን ለመርዳት ተማሪዎቹ በስጋ ቢጣጣሩም ፍቅራቸውን በመሃላ ለማጽናት ቢሞክሩም በኋላ እየሸሹና እየካዱ መገኘታቸው ነው። ለካ እውነተኛ ማንነት በወቅታዊ ስሜት ሳይሆን በፈተና ወቅት የሚገለጥ ነው! የዮሐንስ ወንጌልን ከምዕራፍ 13-18 አጋማሽ በመመልከት፣ በማጥናትና በማሰላሰል ተባረኩበት።

“እውነተኛ አምላክ ብቻ የሆንህ አንተን የላክኸውንም ኢየሱስ ክርስቶስን ያውቁ ዘንድ ይህች የዘላለም ሕይወት ናት።”
(ዮሐንስ 17፥3)



ወደ ቻናሉ ለመ🀄️🀄️ል፦ @Holy_scriptures
👍6
#ትንሣኤ
#ፋሲካ


"የአይሁድ የፋሲካ በዓል ዋዜማ ምሽት ነበር። ያች ሌሊት፥ ኢየሱስ ወደ አባቱ ከመሄዱ በፊት በዚች ምድር ላይ የሚያሳልፋት፥ የመጨረሻይቱ፥ መሆኗን አወቀ። በዚህ ዓለም ያሉትን ወገኖቹን፥ ቀድሞውንም ይወዳቸው ነበር። አሁን ደግሞ፥ እስከ መጨረሻው የቱን ያህል የሚወዳቸው መሆኑን ፥ ሊገልጥላቸው ፈለገ።"
ዮሐ. 13፥1(ሕያው ቃል)




ወደ ቻናሉ ለመ🀄️🀄️ል፦ @Holy_scriptures
👍91🥰1
'    ==❀❀❀===❀❀❀==      
              የዕለቱ ጥቅስ
     ==❀❀❀===❀❀❀==
“ለኃጢአት ሞተን ለጽድቅ እንድንኖር፥ እርሱ ራሱ በሥጋው ኃጢአታችንን በእንጨት ላይ ተሸከመ፤ በመገረፉ ቁስል ተፈወሳችሁ።”
               1ኛ ጴጥሮስ 2፥24




ወደ ቻናሉ ለመ🀄️🀄️ል፦ @Holy_scriptures
👍42
#ትንሣኤ
#ፋሲካ

#የእግዚአብሔር_ቃል_ምን_ይላል?


ኢሳይያስ 53
¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯
¹ የሰማነውን ነገር ማን አምኖአል? የእግዚአብሔርስ ክንድ ለማን ተገልጦአል?
² በፊቱ እንደ ቡቃያ ከደረቅም መሬት እንደ ሥር አድጎአል፤ መልክና ውበት የለውም፥ ባየነውም ጊዜ እንወድደው ዘንድ ደም ግባት የለውም።
³ የተናቀ ከሰውም የተጠላ፥ የሕማም ሰው ደዌንም የሚያውቅ ነው፤ ሰውም ፊቱን እንደሚሰውርበት የተናቀ ነው፥ እኛም አላከበርነውም።
⁴ በእውነት ደዌያችንን ተቀበለ ሕመማችንንም ተሸክሞአል፤ እኛ ግን እንደ ተመታ በእግዚአብሔርም እንደ ተቀሠፈ እንደ ተቸገረም ቈጠርነው።
⁵ እርሱ ግን ስለ መተላለፋችን ቈሰለ፥ ስለ በደላችንም ደቀቀ፤ የደኅንነታችንም ተግሣጽ በእርሱ ላይ ነበረ፥ በእርሱም ቍስል እኛ ተፈወስን።
⁶ እኛ ሁላችን እንደ በጎች ተቅበዝብዘን ጠፋን፤ ከእኛ እያንዳንዱ ወደ ገዛ መንገዱ አዘነበለ፤ እግዚአብሔርም የሁላችንን በደል በእርሱ ላይ አኖረ።
⁷ ተጨነቀ ተሣቀየም አፉንም አልከፈተም፤ ለመታረድ እንደሚነዳ ጠቦት፥ በሸላቶቹም ፊት ዝም እንደሚል በግ፥ እንዲሁ አፉን አልከፈተም።
⁸ በማስጨነቅና በፍርድ ተወሰደ፤ ስለ ሕዝቤ ኃጢአት ተመትቶ ከሕያዋን ምድር እንደ ተወገደ ከትውልዱ ማን አስተዋለ?
⁹ ከክፉዎችም ጋር መቃብሩን አደረጉ፥ ከባለጠጎችም ጋር በሞቱ፤ ሆኖም ግፍን አላደረገም ነበር፥ በአፉም ተንኮል አልተገኘበትም ነበር።
¹⁰ እግዚአብሔርም በደዌ ያደቅቀው ዘንድ ፈቀደ፤ ነፍሱን ስለ ኃጢአት መሥዋዕት ካደረገ በኋላ ዘሩን ያያል፥ ዕድሜውም ይረዝማል፥ የእግዚአብሔርም ፈቃድ በእጁ ይከናወናል።
¹¹ ከነፍሱ ድካም ብርሃን ያያል ደስም ይለዋል፤ ጻድቅ ባሪያዬም በእውቀቱ ብዙ ሰዎችን ያጸድቃል፥ ኃጢአታቸውን ይሸከማል።
¹² ስለዚህም እርሱ ብዙዎችን ይወርሳል፥ ከኃያላንም ጋር ምርኮን ይከፋፈላል፤ ነፍሱን ለሞት አሳልፎ ሰጥቶአልና፥ ከዓመፀኞችም ጋር ተቈጥሮአልና እርሱ ግን የብዙ ሰዎችን ኃጢአት ተሸከመ፥ ስለ ዓመፀኞችም ማለደ።



ወደ ቻናሉ ለመ🀄️🀄️ል፦ @Holy_scriptures
9👍6🔥2
'    ==❀❀❀===❀❀❀==      
              የዕለቱ ጥቅስ
     ==❀❀❀===❀❀❀==
“ዮናስ በዓሣ አንባሪ ሆድ ሦስት ቀንና ሦስት ሌሊት እንደ ነበረ፥ እንዲሁ የሰው ልጅ በምድር ልብ ሦስት ቀንና ሦስት ሌሊት ይኖራል።”
             ማቴዎስ 12፥40



ወደ ቻናሉ ለመ🀄️🀄️ል፦ @Holy_scriptures
👍71
#ትንሣኤ
#ፋሲካ


ኢየሱስ የተሰቀለው ዓርብ ነውን? ከሆነስ፣ በመቃብር ውስጥ ሦስት ቀናትን እንዴት ያሳልፋል፣ እሑድ እስከ ተነሣ ድረስ?


መጽሐፍ ቅዱስ ኢየሱስ በየትኛው የሳምንቱ ቀናት እንደተሰቀለ በዝርዝር (ቁልጭ ባለ መልኩ) አያስቀምጥም። ሁለቱ በስፋት የሚታወቁት አስተያየቶች ዓርብና ረቡዕ ናቸው። አንዳንዶች፣ ሆኖም፣ ሁለቱንም ዓርብና ረቡዕን አዳብሎ (አቀናጅቶ) በመውሰድ ዕለቱ ኀሙስ ነው ብለው ይከራከራሉ።

ኢየሱስ በማቴዎስ 12፡40 እንዳለው፣ “ዮናስ በዓሣ አንባሪ ሆድ ሦስት ቀንና ሦስት ሌሊት እንደ ነበረ፥ እንዲሁ የሰው ልጅ በምድር ልብ ሦስት ቀንና ሦስት ሌሊት ይኖራል።” ስቅለቱ ዓርብ እንደሆነ የሚከራከሩ፣ እንደሚሉት ተቀባይነት ያለው መንገድ አሁንም ቢሆን ይኖራል፣ ሦስት ቀን በመቃብር ይሆን ዘንድ። በአንደኛው ክፍለ ዘመን የአይሁድ አስተሳሰብ የቀን እኩሌታ እንደ ሙሉ ቀን ይወሰዳል። ኢየሱስ የዓርብ እኩሌታን በመቃብር ከሆነ፣ ቅዳሜ ሙሉ ቀን፣ እንዲሁም የእሑድ እኩሌታ — እናም እሱ በመቃብር ውስጥ ለሦስት ቀናት መኖሩን ግምት ውስጥ መውሰድ ይቻላል። አንደኛው ዋነኛ የዓርብ መከራከርያ የሚገኘው ማርቆስ 15፡42 ሲሆን፣ እሱም የሚያመለክተው ኢየሱስ የተሰቀለው “ከሰንበት በፊት መሆኑን ነው።” ያ የሳምንቱ ሰንበት ከሆነ፣ ማለትም ቅዳሜ፣ እናም ያ ሐቅ ወደ ዓርብ ስቅለት ያመራል። ሌለኛው የዓርብ ክርክር የሚለው እንደ ማቴዎስ 16፡21 እና ሉቃስ 9፡22 የመሳሰሉት ቁጥሮች የሚያስተምሩት ኢየሱስ በሦስተኛው ቀን እንደሚነሣ ነው፤ ስለሆነም፣ ሙሉውን ሦስት ሌሊትና ቀናት የግድ በመቃብር ውስጥ መቆየት አያስፈልገውም። ነገር ግን አንዳንድ ትርጉሞች “በሦስተኛው ቀንን” ይጠቀማሉ፣ ለእነዚህ ቁጥሮች፣ ሁሉም ግን አያደርጉም፣ እናም ሁሉም “በሦስተኛው ቀን” በሚለው አይስማማም፣ እነዚህን ቁጥሮች በተሻለ ለመተርጎም። ከዚህም በላይ፣ ማርቆስ 8፡31 ኢየሱስ ከሦስት ቀናት “በኋላ” ይነሣል ይላል።

የኀሙስ ክርክር የሚያያዘው ከዓርብ እይታ ጋር ሆኖ፣ የሚከራከረውም በአብዛኛው በወቅቱ በርካታ ሁነቶች ነበሩ (አንዳንዶቹ እስከ ሃያ ያደርሱታል) ሁነቶቹም ከክርስቶስ መቀበር እና እሑድ ጠዋት ሆነው የተፈጠሩትም ከዓርብ ምሽት እስከ እሑድ ጠዋት ይደርሳሉ። የኀሙስ ተከራካሪዎች አስተሳሰባቸው የሚያመለክተው ዋነኛው ችግር በዓርብና በእሑድ መሐል የሚገኘው ብቸኛ ሙሉ ቀን ቅዳሜ መሆኑን ነው፣ የአይሁድ ሰንበት። አንድ ተጨማሪ ቀን ወይም ሁለት ነው፣ ይህን ችግር ሊያቃልል የሚችለው። የኀሙስ ተከራካሪዎች ይሄን ምክንያት ሊያቀርቡ ይችላሉ፡ ጓደኛህን እስከ ሰኞ ምሽት አላየኸውም እንበል። በቀጣዩ ጊዜ የተመለከትከው ኀሙስ ጠዋት ነው፣ እናም አንተ የምትለው፣ “እነዚህን ሦስት ቀናት አላየውህም” ብለህ ነው፣ ምንም እንኳ ባቆጣጠር 60 ሰዓታት (2.5 ቀናት) ብቻ ቢሆንም። ኢየሱስ ኀሙስ ከተሰቀለ፣ ይህ ምሳሌ እንዴት ሦስት ቀናት እንደሆነው ያሳያል።

የረቡዕ አስተያየት መሠረት የሚያደርገው በዛ ሳምንት ሁለት ሰንበታት መኖራቸውን ነው። ከመጀመሪያው በኋላ (በስቅለቱ ምሽት ከሆነው [ማርቆስ 15፡42፤ ሉቃስ 23፡52-54])፣ ሴቶቹ ሽቶውን ገዙ— እነሱ ግብይት የሚያደርጉት ከሰንበት በኋላ መሆኑን ተገንዘብ (ማርቆስ 16፡1)። የረቡዕ አስተሳሰብ የሚነሣው ይህ “ሰንበት” ፋሲካ እንደሆነ ነው (ሌዋውያን 16፡29-31፣ 23፡24-32፣ 39፣ ታላቅ የክብረ በዓል ቀናት የግድ የሳምንቱ ሰባተኛ ቀን ያልሆኑ ሰንበት ተብለው ተጠቅሰውልናል)። ሁለተኛው የዛ ሳምንት ሰንበት መደበኛው ሳምንታዊ ሰንበት ነው። በሉቃስ 23፡56 ያለውን ተመልከት፣ ሽቶውን የገዙት ሴቶች፣ ከመጀመሪያው ሰንበት በኋላ ተመልሰው ሽቶውን አሰናዱት፣ ከዚያም “በሰንበት ዐረፉ” (ሉቃስ 23፡56)። ክርክሩ መሠረት የሚያደርገው እነሱ ከሰንበት በኋላ ሽቶውን መግዛት እንደማይችሉ ነው፣ እናም ሽቶውን ከሰንበት በፊት ያዘጋጃሉ— አለበለዚያ ሁለት ሰንበታት እስካልሆኑ ድረስ። በሁለት ሰንበት እይታ፣ ክርስቶስ ኀሙስ ከተሰቀለ፣ እናም ታላቁ ቅዱስ ሰንበት (ፋሲካ) ኀሙስ ይጀምራል ማለት ነው ፀሐይ ስትጠልቅ አንሥቶ ዓርብ ፀሐይ ስትጠልቅ ያበቃል— በሳምንታዊው ሰንበት ወይም ቅዳሜ መጀመሪያ ላይ። ከመጀመሪያው ሰንበት የሽቶ ግዥው ቢፈጸም (ፋሲካ) በቅዳሜ ገዝተውታል ማለት ይሆናል፣ በዚህም ሰንበትን ይሽራሉ።

ስለሆነም፣ እንደ ረቡዕ አተያይ ከሆነ፣ ብቸኛው መጽሐፍ ቅዱስን የማይጣረሰው፣ የሴቶቹንና የሽቶውን በተመለከተ በጥሬው በማቴዎስ 12፡40 ላይ የሰፈረው፣ ክርስቶስ ረቡዕ ተሰቅሏል ማለት ነው። ታላቁ ቅዱስ ሰንበት ቀን (ፋሲካ) ኀሙስ ሆኗል ማለት ነው፣ ሴቶቹ ሽቶውን ገዝተው (ከዚያ በኋላ) በዓርብ እንዲሁም ተመልሰው ሽቶውን ያሰናዳሉ በዚያው ቀን፣ እነሱም ቅዳሜ ያርፋሉ በሳምንቱ ሰንበት፣ ከዚያም ሽቶውን ይዘው እሑድ በማለዳ ወደ መቃብር መጥተዋል። ኢየሱስ የተቀበረው ረቡዕ ፀሐይ ስትጠልቅ አካባቢ ነው፣ እሱም እንደ አይሁድ የቀን አቆጣጠር ኀሙስ የሚጀምርበት ነው። የአይሁድን የቀን አቆጣጠር በመያዝ፣ ኀሙስ ምሽት ይኖራችኋል (አንደኛ ምሽት)፣ ኀሙስ ቀን (አንደኛ ቀን)፣ ዓርብ ምሽት (ሁለተኛ ምሽት)፣ ዓርብ ቀን (ሁለተኛ ቀን)፣ ቅዳሜ ምሽት (ሦስተኛ ምሽት)፣ ቅዳሜ ቀን (ሦስተኛ ቀን)። መቼ እንደ ተነሣ በትክክል አናውቀውም፣ ነገር ግን እሑድ ፀሐይ ከመውጣቷ በፊት እንደሆነ እናውቃለን (ዮሐንስ 20፡1፣ መግደላዊት ማርያም “ገና ጨለማ ሳለ” መጣች)፣ ስለዚህ ሊነሣ የሚችለው ፀሐይ ከጠለቀች በኋላ ቅዳሜ ሌሊት ነው፣ እሱም ለአይሁድ የሳምንቱ የመጀመሪያ ቀን።

በረቡዕ እይታ ላይ ሊኖር የሚችለው ችግር ከኢየሱስ ጋር በኢማኦስ መንገድ ከኢየሱስ ጋር የተጓዙት ደቀ መዛሙርት በተመሳሳይ መልኩ “በዛኑ ቀን” በእሱ ትንሣኤ መሆኑ ነው (ሉቃስ 24፡13)። ደቀ መዛሙርት፣ ኢየሱስን ስላላወቁት፣ ስለ ኢየሱስ ስቅለት ነገሩት (24፡21) እንዲህ በማለት “ይህም ነገር ከሆነ እነዚህ ሦስተኛ ቀናት ናቸው” (24፡22)። ከረቡዕ እስከ እሑድ አራት ቀናት ነው። ሊሆን የሚችለው ቆጠራውን የጀመሩት ከረቡዕ ምሽት ከኢየሱስ ቀብር፣ ከአይሁድ ኀሙስ ጀምሮ ነው፣ ለኀሙስ እስከ እሑድ ሲቆጠር ሦስት ቀን ይሆናል።

ከነገሮች የክብደት ደረጃ አኳያ፣ ኢየሱስ ከሳምንቱ በየትኛው ቀን እንደተሰቀለ ማወቁ አስፈላጊ ላይሆን ይችላል። በጣም አስፈላጊ ቢሆን ኖሮ፣ የእግዚአብሔር ቃል የቀንና የጊዜውን ሂደት በግልጽ ባስቀመጠው ነበር። ጠቃሚ የሚሆነው የእሱ በሥጋ መሞት ነው ፣ እንዲሁም በአካል ከሙታን መነሣቱ። በተመሳሳይ መልኩ ጠቃሚ የሚሆነው የሞተበት ምክንያት ነው— ሁሉም ኃጢአተኞች ይገባቸው የነበረውን ቅጣት መውሰድ ነው። ዮሐንስ 3፡16 እና 3፡36 ሁለቱም የሚገልጹት በእሱ ላይ እምነትን ማኖር ውጤቱ የዘላለም ሕይወት ነው! ይህ እንግዲህ እሱ ረቡዕም፣ ኀሙስም፣ ወይም ዓርብ ቢሰቀል ያው ነው።



ምንጭ፦ www.gotquestions.org



ወደ ቻናሉ ለመ🀄️🀄️ል፦ @Holy_scriptures
👍53
ውድ የቻናላችን ቤተሰቦች "ማን ያንከባልልናል?" በምንላቸው ጉዳዮች ሁሉ ላይ ድንጋዩ ተንከባሎ የምንመለከትበት በዓል ይሁንልን! መልካም በዓል!!! መልካም ምኞታችሁን በኮሜንት መግለጽ ትችላላችሁ

"እርስ በርሳቸውም፦ ድንጋዩን ከመቃብር ደጃፍ ማን ያንከባልልልናል? ይባባሉ ነበር፤ ድንጋዩ እጅግ ትልቅ ነበርና፤ አሻቅበውም አይተው ድንጋዩ ተንከባሎ እንደ ነበር ተመለከቱ።"
ማርቆስ 16፥3-4



ወደ ቻናሉ ለመ🀄️🀄️ል፦ @Holy_scriptures
5👍5
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
“እግዚአብሔር ግን ከሙታን አስነሣው፤”
ሐዋርያት 13፥30



ወደ ቻናሉ ለመ🀄️🀄️ል፦ @Holy_scriptures
9👍1
'    ==❀❀❀===❀❀❀==      
              የዕለቱ ጥቅስ
     ==❀❀❀===❀❀❀==
“ሞት በሰው በኩል ስለ መጣ ትንሣኤ ሙታን በሰው በኩል ሆኖአልና።”
            1ኛ ቆሮንቶስ 15፥21



ወደ ቻናሉ ለመ🀄️🀄️ል፦ @Holy_scriptures
👍73
'    ==❀❀❀===❀❀❀==      
              የዕለቱ ጥቅስ
     ==❀❀❀===❀❀❀==
“ያም ቀን እርሱም ከሳምንቱ ፊተኛው በመሸ ጊዜ፥ ደቀ መዛሙርቱ ተሰብስበው በነበሩበት፥ አይሁድን ስለ ፈሩ ደጆቹ ተዘግተው ሳሉ፥ ኢየሱስ መጣ፤ በመካከላቸውም ቆሞ፦ ሰላም ለእናንተ ይሁን አላቸው።”
                   ዮሐንስ 20፥19




ወደ ቻናሉ ለመ🀄️🀄️ል፦ @Holy_scriptures
3👍2