' ==❀❀❀===❀❀❀==
የዕለቱ ጥቅስ
==❀❀❀===❀❀❀==
“ከባሕርም እስከ ባሕር ድረስ፥ ከሰሜንም እስከ ምሥራቅ ድረስ ይቅበዘበዛሉ፤ የእግዚአብሔርን ቃል ለመሻት ይርዋርዋጣሉ፥ አያገኙትምም።”
አሞጽ 8፥12
ወደ ቻናሉ ለመ🀄️ላ🀄️ል፦ @Holy_scriptures

❤5👍1🔥1
#ፋሲካ
#ትንሣኤ
ውድ የቻናላችን ቤተሰቦች ከዛሬ ጀምሮ የፋሲካን በዓል ምክንያት በማድረግ በእናንተ በቤተሰቦቻችን አእምሮ ውስጥ ጥያቄ የሚከስቱ ነገሮችን እና ከቅዱሳት መጻሕፍት አንጻር በዚህ በዓል ዙሪያ ሊዳሰሱ የሚገቡ ነገሮችን እናያለን። በዚህ መሠረት ጥያቄ የጫረባችሁን ነገር በነጻነት በአስተያየት መስጫ ወይም ኮሜንት ቦክስ ውስጥ ማስፈር ትችላላችሁ።

❤2
#ፋሲካ
#ትንሣኤ
የጌታችን እና የመድኃኒታችን የኢየሱስ ክርስቶስ ትንሣኤ በየትኛውም ሁኔታ ፍትህና ፍርድ ለተዛባባችሁ ትክክለኛ ፍርድ እና ፍትህ እንዳለ ማሳያ ነው። እስቲ አስቡት #ትንሣኤ ባይኖር የተዳፈነው፣ የተቀበረው እንዴት ይገለጣል? ክብር ለትንሣኤው ጀግና ይሁን እንጂ!
“ቀን ቀጥሮአልና፥ በዚያም ቀን ባዘጋጀው ሰው እጅ በዓለሙ ላይ በጽድቅ ሊፈርድ አለው፤ ስለዚህም እርሱን ከሙታን በማስነሣቱ ሁሉን አረጋግጦአል።”
ሐዋርያት 17፥31

👍7❤2
' ==❀❀❀===❀❀❀==
የዕለቱ ጥቅስ
==❀❀❀===❀❀❀==
“ስለ ሥጋ ማሰብ ሞት ነውና፥ ስለ መንፈስ ማሰብ ግን ሕይወትና ሰላም ነው።”
ሮሜ 8፥6

👍6❤3
"ሆሣዕና በአርያም እያሉ ይጮኹ ነበር" ማቴ ፳፩፣፱
🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿
ነገ "ሆሳዕና" ነው:: ለትንሣኤ በዓል አንድ ሳምንት ቀረው::
«#ሆሳዕና» ቃሉ ከሁለት አረማይክ ቃላት የተሰራ ሲሆን ትርጉም «እባክህ እርዳ፣ አሁን አድን» ማለት ነው። እብራይስጡም ይህንኑ ቃል ወርሶ «הושענא » ሆሻአና ሲል ይገኛል። አዎ «አሁን አድን፣ እባክህ እርዳን» ብሎ የአዳም ዘር ያጣውን ልጅነትና የደረሰበትን ሞት ለመላቀቅ የሚያሰማው የጩኸት ድምጽ ነው፣ «ሆሳዕና»!!!
ዳዊት ነቢይ በመንፈስ ቅዱስ ተመልክቶ ማዳኑን ሲጣራና አሁን ናልን ሲል ከዘመናት በፊት አድምጠነዋል። የውስጥ ዓይኖቹ ሩቅ አይተዋል። ማዳኑንም ሽተው እንዲህ ሲል ዘምሮለታል።
«አቤቱ፥ እባክህ፥ አሁን አድን አቤቱ፥ እባክህ፥ አሁን አቅና» መዝ ፻፲፰፣፳፭
ያ ማለት ደግሞ « אָנָּ֣א יְ֭הוָה הֹושִׁ֘יעָ֥ה נָּ֑א אָֽנָּ֥א יְ֝הוָ֗ה הַצְלִ֘יחָ֥ה נָּֽא » እና ያኽዌ ሆሳአና አና ያኽዌ ሆስሊኻ ና» የሚለው የእብራይስጡ ቃል ነው።
አዎ ንጉሥ ክርስቶስ ከዘጠና ዘጠኙ በጎች መካከል የጠፋውን አንዱን በግ ፍለጋ ንጉሥ ሆኖ ሳለ እንደንጉሥ ያይደለ በአህያ፣ ለዚያውም በውርንጫ ተቀምጦ «የአሁን አድን (ሆሳዕና)» ጩኸት ሊመልስ በጽዮን ከተማ ይመጣል፤ ይህንንም ዘካርያስ ከዘመረው ዘመናት ተቆጥረው ነበር።
«አንቺ የጽዮን ልጅ ሆይ፥ እጅግ ደስ ይበልሽ አንቺ የኢየሩሳሌም ልጅ ሆይ፥ እልል በዪ እነሆ፥ ንጉሥሽ ጻድቅና አዳኝ ነው ትሑትም ሆኖ በአህያም፥ በአህያይቱ ግልገል በውርጫይቱ ላይ ተቀምጦ ወደ አንቺ ይመጣል» ዘካ ፱፣፱
ምንኛ ይደንቅ? ምንኛስ ይረቅ? ንጉሥ ስለመምጣቱ አስቀድመው የተናገሩለትና ከዘመናት በፊት ማዳኑን አይተው በእልልታ የዘመሩለት!!
አዎ የደም ግባት ብቻ ሳይሆን የንጉሥ ወግ የሌለው፣ በአህያ ለዚያውም በውርንጫ የሚመጣ ንጉሥ እንዴት ለመቀበል ይቀላል?
አባቶቻቸው ለዘመናት «ሆሳዕና፣ ማዳንህ አሁን ይሁን» ያሉለትና የዘመሩለት በዕለተ ቀጠሮው ማዳኑን ሊያሳይ ከጽዮን ደጃፍ ቀርቦ ሳለ የማያውቁት፣ ያልሰሙት፣ ትንቢቱን ያላነበቡት «ሆሳዕና» ሲሉ ትልልቆቹ ዕብራውያን ግን ዝም አሉ፣ ዝም በሉም አሉ!
«ነገር ግን የካህናት አለቆችና ጻፎች ያደረገውን ድንቃ ድንቅ በመቅደስም፣ሆሣዕና ለዳዊት ልጅ እያሉ የሚጮኹትን ልጆች ባዩ ጊዜ፥ ተቈጥተው፣ እነዚህ የሚሉትን አትሰማምን? አሉት»
የማዳኑ ጌታም፣
«እሰማለሁ፤ ከሕፃናትና ከሚጠቡት አፍ ምስጋናን ለራስህ አዘጋጀህ የሚለውን ቃል ከቶ አላነበባችሁምን? አላቸው» ማቴ ፳፩፣ ፲፭-፲፮
ኢየሱስ ክርስቶስ የእነዚህን ሕፃናት ዝማሬና ምስጋናን የሰማው ከቤተ ፋጌ ወደ ኢየሩሳሌም ማዳኑን ሊፈጽም በመጣ ጊዜ ነበር። ቤተ ፋጌ ከኢየሩሳሌም ከተማ ምሥራቃዊ አቅጣጫ በቢታንያና በደብረ ዘይት ተራራ መካከል የምትገኝ መንደር ነበረች። ቤተ ፋጌ ማለት በአረማይክ «ያልበሰለ በለስ ቤት» ማለት ነው። ርቀቱም ከኢየሩሳሌም የሰንበት ያህል ምዕራፍ ነበር።
ጌታ ኢየሱስም ከኢያሪኰ ከተማ ወደ ኢየሩሳሌም ሲወጣ ካረፈባት ከቤተ ፋጌ መንደር ሁለቱን ደቀ መዛሙርት ልኰ ውርንጫይቱን ከታሰረችበት ፈትተው እንዲያመጡለት አዟል።
«ወደ ኢየሩሳሌምም ቀርበው ወደ ደብረ ዘይት ወደ ቤተ ፋጌ ሲደርሱ፥ ያንጊዜ ኢየሱስ ከደቀ መዛሙርቱ ሁለት ላከ፥እንዲህም አላቸው፦ በፊታችሁ ወዳለችው መንደር ሂዱ፥ በዚያን ጊዜም የታሰረችን አህያ ውርንጫም ከእርስዋ ጋር ታገኛላችሁ፤ ፈትታችሁ አምጡልኝ» ማቴ ፳፩፤፪
ያን ጊዜም በቀደምት አበው የተነገረው ትንቢትና ዝማሬ ፍጻሜ አገኘ ማለት ነው።
«የሚቀድሙትም ሕዝብ የሚከተሉትም። ሆሣዕና ለዳዊት ልጅ በጌታ ስም የሚመጣ የተባረከ ነው፤ ሆሣዕና በአርያም እያሉ ይጮኹ ነበር» ማቴ ፳፩፣፱
ይሁን እንጂ ኢየሩሳሌም ለሆሳዕና አልተዘጋጀችም ነበር። ይልቁንም ቤተ መቅደሱ አካባቢ ስለማዳኑ ዝማሬ በማቅረብ ፋንታ የጦፈ የንግድ ገበያ ደርቶበት ነበር። ቤተመቅደሱ የጸሎት ሥፍራ መሆኑ ቀርቶ የሻጮችና የለዋጮች መድረክ ሆኖ ነበር። ያኔ ማዳኑ የቀረበላት ኢየሩሳሌም በመቅደሱ በራፍ ስትሸጥ፣ ስትለውጥ መድኃኒቱን ሆሳዕና እያለች መቀበልን እንዳልቻለች ሁሉ የዛሬዋ ቤተክርስቲያንስ ንግድና ሸቀጥ የሌለበትን «ሆሳዕና» እያከበረች ነው ወይ? ብለን ብንጠይቅ ራስን ማታለል ካልተጨመረበት በስተቀር፣ መሸጥ መሸቀጡ የሌለበትን «ሆሳዕና» የሚያከብር የለም ነው መልሱ። ዐውደ ምሕረቱ ሱቅ በደረቴ ያልሆነበትን ሥፍራ ማግኘት ከባድ ነው።
ኢየሱስ ማዳኑን ከመፈጸሙ በፊት እነዚህን ነጋዴዎች አስወግዷል። ገበታቸውን ገልብጧል። እየገረፈ አስወጥቷል። የወንበዴዎች ዋሻ የሆነውን የጸሎት ቤት ጠራርጓል። ዛሬስ ቤቱ ስንት ወንበዴ መሽጎበት ይሆን? ወንበዴዎቹ ይዘምራሉ፣ ሆሳዕና ይላሉ፣ የዘንባባ ዝንጣፊ ይይዛሉ፣ በጣታቸው፣ በግንባራቸው ያስራሉ። ወንበዴዎች ናቸው ተብለው እንዳይርቋቸው የአምልኰ መልክ አላቸው። ቤተመቅደሱን የወንበዴዎች ዋሻ አደረጋችሁ ያለው በግብር ውንብድና በመልክ ግን አገልጋይ ይመስሉ የነበሩትን የመቅደሱን ሰዎች ነበር። ዛሬም እንደዚያው!!
በእድሜአችን ስንት «ሆሳዕና በአርያም» አሳለፍን? ማዳኑ በተደረገለት ማንነታችን ውስጥ ስንት ፍሬ አፈራን? የተራበው ኢየሱስ ከእኛ የሚፈልገውን ፍሬ ይዘናል? ወይስ ፍሬ አልባ ሆነን ለቁጣ የተዘጋጀን እንሆን? «ሆሳዕና በአርያም» ማለቱ ብቻውን አያድንም፣ ማዳኑንም አያመጣም። የወንበዴ ዋሻ ማንነታችንን እናጽዳ። ከዚህ ዓለም ሽቃጭና ልዋጭ ማስመሰያ ማንነት እንውጣ! በጎ ፍሬ እንዲያፈራ ለተላከው የወይኑ ባለቤት ወራሽ እንገዛ! ያኔ «ሆሳዕና በአርያም» ስንል ማዳኑ ፈጥኖ ይሆንልናል።
አዎ ሆሳዕና በአርያም! በዚህም በወዲያኛውም! ሆሳዕና በአርያም።ሃሌ ሉያ!!!!!!!
ምንጭ:- ደጀ ብርሃን

❤5👍4
' ==❀❀❀===❀❀❀==
የዕለቱ ጥቅስ
==❀❀❀===❀❀❀==
“የሚቀድሙትም ሕዝብ የሚከተሉትም፦ ሆሣዕና ለዳዊት ልጅ በጌታ ስም የሚመጣ የተባረከ ነው፤ ሆሣዕና በአርያም እያሉ ይጮኹ ነበር።”
ማቴዎስ 21፥9

❤7👍1
#ትንሣኤ
#ፋሲካ
#ሆሣዕና፣ ኢየሱስ ብዙ አጀብና ሙገሳ የገጠመው ቀን ነው። ነገር ግን "ስቀለው፣ ስቀለው" የሚል ተቃውሞም ከፊቱ ነበር። በዚህ ሁሉ ግን ዓላማውንና የምድር ጉዞውን በሚገባ ስለሚያውቅ በሰው ሁኔታ አልሞቀውም አልበረደውምም። እኛም ዓላማችንንና ፍጻሜያችንን በሚገባ በማወቅ በኑሮአችን ጸንተን ጌታችንን እንድናስከብር ጌታ ይርዳን!

👍4🔥2❤1
ሆሣዕና ማለት ምን ማለት ነው?
Anonymous Quiz
0%
ሀ. አሁን ንገሥ
61%
ለ. በእግዚአብሔር ስም የሚመጣ ንጉሥ የተባረከ ነው።
36%
ሐ. አሁን አድን
3%
መ. የነገሥታት ንጉሥ
👍5❤1
#ትንሣኤ
#ፋሲካ
#ሰኞ
ጌታ ሆይ፣ በቤትህ የምትናገረውን ሁሉ የምንሰማበት፣ የእኛም ጩኹት በአንተ ዘንድ የሚሰማበት የጸሎት ቤት ይሁን!
ወደ ቻናሉ ለመ🀄️ላ🀄️ል፦ @Holy_scriptures
#ፋሲካ
#ሰኞ
ጌታ ሆይ፣ በቤትህ የምትናገረውን ሁሉ የምንሰማበት፣ የእኛም ጩኹት በአንተ ዘንድ የሚሰማበት የጸሎት ቤት ይሁን!
ወደ ቻናሉ ለመ🀄️ላ🀄️ል፦ @Holy_scriptures
👍6❤2
' ==❀❀❀===❀❀❀==
የዕለቱ ጥቅስ
==❀❀❀===❀❀❀==
“ይህስ ስሜ የተጠራበት ቤት በዓይናችሁ የሌቦች ዋሻ ሆኖአልን? እነሆ፥ እኔ አይቻለሁ፥ ይላል እግዚአብሔር።”
ኤርምያስ 7፥11

#ሰኞ፣ ከሆሳዕና ማግሥት ጌታችን ከቢታንያ ወደ ኢየሩሳሌም ሲገባ ሁለት ነገሮችን አድርጓል፡፡ አንደኛ ከቅጠል በስተቀር ፍሬ ያልተገኘባትን ዕፀ በለስ ረግሟል፡፡ ሁለተኛ ወደ ቤተ መቅደስ ገብቶ የሚሸጡትንና የሚለውጡትን አስወጥቷል፡፡ (ማቴ.21÷12-17፤ ማር.11÷17፤ ሉቃ.19÷45-46፡፡)
መልእክት፦ ቤተ መቅደሱ እንዲሁም በለሷ የሚጠበቅባቸውን በተገቢው ሁኔታ አልያዙም።
👉 በለሷ ከፍሬ ጎድላ ተገኝታለች።
👉 ቤተመቅደሱ የማይጠበቅበትን ይዟል።
በቅዱስ ሉቃስ ወንጌል ላይ እንደተገለጸው ይህንም ምሳሌ አለ "ለአንድ ሰው በወይኑ አትክልት የተተከለች በለስ ነበረችው ፍሬም ሊፈልግባት ወጥቶ ምንም አላገኘም፡፡" ሉቃ 13፡6 በማለት በበለስ ስለተመሰለ የሰው ልጅ ሕይወት በማሰብ እንዲመለስ ንስሐ እንዲገባ በሕይወትም እንዲኖር እግዚአብሔር ኢየሱስ ክርስቶስ ማሳሰቡን ያጠይቃል፡፡ ንስሐ አልገባም አልመለስም ያለም በለሷ እንደጠወለገችና እንደተቆረጠች ሁሉ ፍሬ ባለማፍራታቸው እንደሚቆረጡ እንዲሁም ወደ እሳት እንደሚጣሉ መጽሐፍ ቅዱስ በግልጽ ያስረዳል፡፡ ፍሬ አልባ እንዳንሆን ጌታ ሲመጣም እንዳናፍር የመጽሐፉን ቃል ልንጠብቅና ልንፈጽም ይገባናል፡፡ በዚህ የሕማማት የመጀመሪያ ቀን ዕለተ ሰኞ የምናስበው የምንዘክረው የሰው ልጅ ሕይወት በከንቱ በቸልተኝነት እንዳይደክም እንዳይጠወለግ እንዳይደርቅ ወደ እሳትም እንዳይጣል ማድረግ ይገባናል፡፡
ጌታችን መድኃኒታችን ወደ ቤተ መቅደስ ግብቶ የሚሸጡትንና የሚለውጡትን እንዳስወጣ ሁሉ፤ ዛሬ የእግዚአብሔር ቤተሰቦች ጌታችን ወደ መቅደስ ሕይወታችን ቢመጣ ምን ያገኝ ይሆን? ፍፌስ እያፈራን ይሆን? የእግዚአብሔር ቃል ግን ለንስሐ የሚገባ ፍሬ አድርጉ ይለናል። ማቴ 3፡8
ምንጭ:- tesfalem7.blogspot.com

👍7
' ==❀❀❀===❀❀❀==
የዕለቱ ጥቅስ
==❀❀❀===❀❀❀==
“አቤቱ፥ መንገድህን አመልክተኝ፥ ፍለጋህንም አስተምረኝ።”
መዝሙር 25፥4
ወደ ቻናሉ ለመ🀄️ላ🀄️ል፦ @Holy_scriptures
የዕለቱ ጥቅስ
==❀❀❀===❀❀❀==
“አቤቱ፥ መንገድህን አመልክተኝ፥ ፍለጋህንም አስተምረኝ።”
መዝሙር 25፥4
ወደ ቻናሉ ለመ🀄️ላ🀄️ል፦ @Holy_scriptures
❤3👍3
#ማክሰኞ ኢየሱስ ለመጨረሻ ጊዜ በቤተ መቅድስ ያስተማረበት ቀን ነው።
ጌታ ከቃሉ ስንት ጊዜ አስተማረን? ምን ያህልስ ወደ ተግባር ለወጥነው? ወይስ እንደ ፈሪሳውያን በራሱ መጽሐፍ ላይ ጌታችንን እየተከራከርነውና አልፎ ተርፎም ከሕይወታችን ልናስወጣው እየከጀልን ይሆን? የማንስ ጽሕፈት በላያችን ይታያል?
ለመሆኑ ጌታችንና መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ምን አስተማረ? ወይም ምን ተማሩ አለ?
👉“እንግዲህ ከነዚህ ከሁሉ ካነሱት ትእዛዛት አንዲቱን የሚሽር ለሰውም እንዲሁ የሚያስተምር ማንም ሰው በመንግሥተ ሰማያት ከሁሉ ታናሽ ይባላል፤ የሚያደርግ ግን የሚያስተምርም ማንም ቢሆን እርሱ በመንግሥተ ሰማያት ታላቅ ይባላል።”
ማቴዎስ 5፥19
👉“የሰው ልጅ ብዙ መከራ ሊቀበል፥ ከሽማግሌዎችም ከካህናት አለቆችም ከጻፎችም ሊጣል፥ ሊገደልም ከሦስት ቀንም በኋላ ሊነሣ እንዲገባው ያስተምራቸው ጀመር፤ ቃሉንም ገልጦ ይናገር ነበር።”
ማርቆስ 8፥31
👉“ቀንበሬን በላያችሁ ተሸከሙ ከእኔም ተማሩ፥ እኔ የዋህ በልቤም ትሑት ነኝና፥ ለነፍሳችሁም ዕረፍት ታገኛላችሁ፤”
ማቴዎስ 11፥29
👉“ሲያስተምርም እንዲህ አለ፦ ረጃጅም ልብስ ለብሰው መዞርን፥ በገበያም ሰላምታን፥ በምኵራብም የከበሬታን ወንበር፥ በግብርም የከበሬታን ስፍራ ከሚወዱ ከጻፎች ተጠበቁ፤”
ማርቆስ 12፥38-39
👉 “እንግዲህ ሂዱና አሕዛብን ሁሉ በአብ በወልድና በመንፈስ ቅዱስ ስም እያጠመቃችኋቸው፥ ያዘዝኋችሁንም ሁሉ እንዲጠብቁ እያስተማራችኋቸው ደቀ መዛሙርት አድርጓቸው፤ እነሆም እኔ እስከ ዓለም ፍጻሜ ድረስ ሁልጊዜ ከእናንተ ጋር ነኝ።”
ማቴዎስ 28፥19-20

❤15👍3
' ==❀❀❀===❀❀❀==
የዕለቱ ጥቅስ
==❀❀❀===❀❀❀==
“ኢየሱስ ግን እንዲህ አለ፦ ተዉአት፤ ስለ ምን ታደክሙአታላችሁ? መልካም ሥራ ሠርታልኛለች።”
ማርቆስ 14፥6

❤10👍1
#ረቡዕ የአስቆሮቱ ይሁዳ ኢየሱስን የካደበት ቀንና ማርያም (በማርቆስ ስሟ አልተጠቀሰም) በኢየሱስ እግር ስር ሽቶ ያፈሰሰችበትና በጸጉሯ ያበሰችበት ቀን ነው። (ማር. 14 ) እዚህ ጋር አንድ ነገር ማስቀመጥ ወደድኩ። ይህ ቀን ብዙ ጊዜ ከኢየሱስ ጋር የተጓዙ ሰዎች ትጥቃቸው መፈታት የጀመረበትና እውነተኛ ማንነታቸው የተገለጠበት ቀን ነበር። ከዚህ በፊት በርትተው ይጓዙ የነበሩ ሁሉ የሥጋ ድካም በብርቱ መገዳደር እና መጣል የጀመራቸው ጊዜ ነበር። አንዳዶች ወድቀው ሲነሱ አንዱ እስከወዲያኛው ወደቀ። በነገራችን ላይ የዚህን የሥጋን ከመንፈስ ጋር ለማበር መቸገር መፍትሄ በጌቴሴማኒ ነገራቸው ። እንዲህ በማለት፦ “ወደ ፈተና እንዳትገቡ ትጉና ጸልዩ፤ መንፈስስ ተዘጋጅታለች ሥጋ ግን ደካማ ነው አለው።” (ማቴዎስ 26፥41)
ወደ ረቡዕ ቀን ስንመለስ ይሁዳ እንዲህ አይነት ሰው ነበር፦
"ይህንም የተናገረ ሌባ ስለ ነበረ ነው እንጂ ለድሆች ተገድዶላቸው አይደለም፤ ከረጢትም ይዞ በውስጡ ከሚገባው ይወስድ ስለ ነበረ ነው።" (ዮሐ. 12፡6) በሌላ በኩል ደግሞ በምን ሰዓት ምን ማድረግ እንዳለባት የምታውቅን ሴት እንመለከታለን። ኢየሱስ ከሞተ በኋላ ለአካሉ ሽቶ ለመቀባት አስበው የሄዱ ቢኖሩም መቅደላዊት ማርያም ግን መችና የት ኢየሱስን ማግኘት እንደሚቻል የምታውቅ ሴት ነበረች። እናም የዛሬው ቀን ከኢየሱስ ጋር ለዘለአለሙ ለመጓዝ ኃይል እንድናገኝ፣ ከእርሱ አሳብና አጀንዳ ጋር ደግሞ ተባብረን እንድንጓዝ ጌታ ይርዳን!

❤10👍5
' ==❀❀❀===❀❀❀==
የዕለቱ ጥቅስ
==❀❀❀===❀❀❀==
“እርሱም፦ ይህ ስለ ብዙዎች የሚፈስ የአዲስ ኪዳን ደሜ ነው።”
ማርቆስ 14፥24
ወደ ቻናሉ ለመ🀄️ላ🀄️ል፦ @Holy_scriptures
የዕለቱ ጥቅስ
==❀❀❀===❀❀❀==
“እርሱም፦ ይህ ስለ ብዙዎች የሚፈስ የአዲስ ኪዳን ደሜ ነው።”
ማርቆስ 14፥24
ወደ ቻናሉ ለመ🀄️ላ🀄️ል፦ @Holy_scriptures
❤7👍2
#ሀሙስ ጌታችንና መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ከመሞቱ በፊት ከደቀ መዛሙርቱ ጋር የመጨረሻውን እራት የበላበትንና በእውነት ለእርሱ ተከታይ ለሆኑት ብርቱና መሰረታዊ ትምህርት፣ ምክር፣ ተግጻጽ ሲያስፈልግም በተግባር የተደገፈ ትምህርት ያስተላለፈበት እንዲሁም አሁን በመንግስቱ ላሉ በኋላም ለሚመጡ የጸለየው አስደናቂ ጸሎት፣ የደቀ መዛሙርቱ ድካም. . . ወዘተ የሀሙስ ቀን ሁነቶች ናቸው።
በገነት አዳም ከእግዚአብሔር አሳብ ይልቅ የራሱን መርጦ ለሰው ፍዳን አመጣ ከገነትም ተባረረ። ኢየሱስ ግን ከራሱ መከራ ይልቅ የአባቱን ፈቃድ አስቀደመ። አምላክ እና ጌታ ሆኖ ሳለ ሰውን አገለገለ።
"እናንተ መምህርና ጌታ ትሉኛላችሁ፤ እንዲሁ ነኝና መልካም ትላላችሁ። እንግዲህ እኔ ጌታና መምህር ስሆን እግራችሁን ካጠብሁ፥ እናንተ ደግሞ እርስ በርሳችሁ እግራችሁን ትተጣጠቡ ዘንድ ይገባችኋል። እኔ ለእናንተ እንዳደረግሁ እናንተ ደግሞ ታደርጉ ዘንድ ምሳሌ ሰጥቻችኋለሁና።" (ዮሐንስ 13፥13-15 )
የሚገርመኝ ነገር ቢኖር ኢየሱስን ከመከራሁ እንዲቀርና እርሱን ለመርዳት ተማሪዎቹ በስጋ ቢጣጣሩም ፍቅራቸውን በመሃላ ለማጽናት ቢሞክሩም በኋላ እየሸሹና እየካዱ መገኘታቸው ነው። ለካ እውነተኛ ማንነት በወቅታዊ ስሜት ሳይሆን በፈተና ወቅት የሚገለጥ ነው! የዮሐንስ ወንጌልን ከምዕራፍ 13-18 አጋማሽ በመመልከት፣ በማጥናትና በማሰላሰል ተባረኩበት።
“እውነተኛ አምላክ ብቻ የሆንህ አንተን የላክኸውንም ኢየሱስ ክርስቶስን ያውቁ ዘንድ ይህች የዘላለም ሕይወት ናት።”
(ዮሐንስ 17፥3)

👍6
#ትንሣኤ
#ፋሲካ
"የአይሁድ የፋሲካ በዓል ዋዜማ ምሽት ነበር። ያች ሌሊት፥ ኢየሱስ ወደ አባቱ ከመሄዱ በፊት በዚች ምድር ላይ የሚያሳልፋት፥ የመጨረሻይቱ፥ መሆኗን አወቀ። በዚህ ዓለም ያሉትን ወገኖቹን፥ ቀድሞውንም ይወዳቸው ነበር። አሁን ደግሞ፥ እስከ መጨረሻው የቱን ያህል የሚወዳቸው መሆኑን ፥ ሊገልጥላቸው ፈለገ።"
ዮሐ. 13፥1(ሕያው ቃል)

👍9❤1🥰1
' ==❀❀❀===❀❀❀==
የዕለቱ ጥቅስ
==❀❀❀===❀❀❀==
“ለኃጢአት ሞተን ለጽድቅ እንድንኖር፥ እርሱ ራሱ በሥጋው ኃጢአታችንን በእንጨት ላይ ተሸከመ፤ በመገረፉ ቁስል ተፈወሳችሁ።”
1ኛ ጴጥሮስ 2፥24
ወደ ቻናሉ ለመ🀄️ላ🀄️ል፦ @Holy_scriptures
የዕለቱ ጥቅስ
==❀❀❀===❀❀❀==
“ለኃጢአት ሞተን ለጽድቅ እንድንኖር፥ እርሱ ራሱ በሥጋው ኃጢአታችንን በእንጨት ላይ ተሸከመ፤ በመገረፉ ቁስል ተፈወሳችሁ።”
1ኛ ጴጥሮስ 2፥24
ወደ ቻናሉ ለመ🀄️ላ🀄️ል፦ @Holy_scriptures
👍4❤2
#ትንሣኤ
#ፋሲካ
#የእግዚአብሔር_ቃል_ምን_ይላል?
ኢሳይያስ 53
¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯
¹ የሰማነውን ነገር ማን አምኖአል? የእግዚአብሔርስ ክንድ ለማን ተገልጦአል?
² በፊቱ እንደ ቡቃያ ከደረቅም መሬት እንደ ሥር አድጎአል፤ መልክና ውበት የለውም፥ ባየነውም ጊዜ እንወድደው ዘንድ ደም ግባት የለውም።
³ የተናቀ ከሰውም የተጠላ፥ የሕማም ሰው ደዌንም የሚያውቅ ነው፤ ሰውም ፊቱን እንደሚሰውርበት የተናቀ ነው፥ እኛም አላከበርነውም።
⁴ በእውነት ደዌያችንን ተቀበለ ሕመማችንንም ተሸክሞአል፤ እኛ ግን እንደ ተመታ በእግዚአብሔርም እንደ ተቀሠፈ እንደ ተቸገረም ቈጠርነው።
⁵ እርሱ ግን ስለ መተላለፋችን ቈሰለ፥ ስለ በደላችንም ደቀቀ፤ የደኅንነታችንም ተግሣጽ በእርሱ ላይ ነበረ፥ በእርሱም ቍስል እኛ ተፈወስን።
⁶ እኛ ሁላችን እንደ በጎች ተቅበዝብዘን ጠፋን፤ ከእኛ እያንዳንዱ ወደ ገዛ መንገዱ አዘነበለ፤ እግዚአብሔርም የሁላችንን በደል በእርሱ ላይ አኖረ።
⁷ ተጨነቀ ተሣቀየም አፉንም አልከፈተም፤ ለመታረድ እንደሚነዳ ጠቦት፥ በሸላቶቹም ፊት ዝም እንደሚል በግ፥ እንዲሁ አፉን አልከፈተም።
⁸ በማስጨነቅና በፍርድ ተወሰደ፤ ስለ ሕዝቤ ኃጢአት ተመትቶ ከሕያዋን ምድር እንደ ተወገደ ከትውልዱ ማን አስተዋለ?
⁹ ከክፉዎችም ጋር መቃብሩን አደረጉ፥ ከባለጠጎችም ጋር በሞቱ፤ ሆኖም ግፍን አላደረገም ነበር፥ በአፉም ተንኮል አልተገኘበትም ነበር።
¹⁰ እግዚአብሔርም በደዌ ያደቅቀው ዘንድ ፈቀደ፤ ነፍሱን ስለ ኃጢአት መሥዋዕት ካደረገ በኋላ ዘሩን ያያል፥ ዕድሜውም ይረዝማል፥ የእግዚአብሔርም ፈቃድ በእጁ ይከናወናል።
¹¹ ከነፍሱ ድካም ብርሃን ያያል ደስም ይለዋል፤ ጻድቅ ባሪያዬም በእውቀቱ ብዙ ሰዎችን ያጸድቃል፥ ኃጢአታቸውን ይሸከማል።
¹² ስለዚህም እርሱ ብዙዎችን ይወርሳል፥ ከኃያላንም ጋር ምርኮን ይከፋፈላል፤ ነፍሱን ለሞት አሳልፎ ሰጥቶአልና፥ ከዓመፀኞችም ጋር ተቈጥሮአልና እርሱ ግን የብዙ ሰዎችን ኃጢአት ተሸከመ፥ ስለ ዓመፀኞችም ማለደ።

❤9👍6🔥2