መዳን በሥራ ካልሆነ ለመልካም ሥራ ከጌታ የምናገኘው ምንድነው?
ክፍል-2
እግዚአብሔር ይህ እምነት እውነተኛ መሆን አለመሆኑን በራሱ አምላካዊ እውቀት ያውቃል፤ ሰው ግን ይህን የሚያውቀው ሥራውን አይቶ ነው፤ እዚህ ላይ የተጠቀሰው «እምነት አለኝ» ባዩ ሰው ደግሞ ሥራ እንደሌለው ታውቋል፤ ስለዚህ በቊ.17 ላይ «ሥራ የሌለው እምነት ቢኖር በራሱ የሞተ ነው» ተብሏል፡፡ በእግዚአብሔር ዘንድ እውነተኛ እንደሆነ የሚታወቅ እምነት ግን ሥራ የሌለው ሊሆን አይችልም፤ በጊዜው ባይገለጥ እንኳ እግዚአብሔር ጽድቅ አድርጎ የቈጠረው እምነት ከሆነ በሥራ መገለጡ አይቀርም፡፡ ያን ጊዜም በሰው ዘንድ ይታያል፤ ስለዚህ በቊ.18 ላይ እንደተጠቀሰው «አንድ ሰው አንተ እምነት አለህ እኔም ሥራ አለኝ እምነትህን ከሥራህ ለይተህ አሳየኝ እኔም እምነቴን በሥራዬ አሳይሃለሁ ይላል» ተብሎ በሁለት ሰዎች መካከል በዚህ ጉዳይ ሊባል የሚችለው ነገር ተነግሮናል፤ እነዚህ ሁለት ሰዎች አንዱ እምነት አለኝ የሚለው ሰው ሲሆን ሌላው ደግሞ ሥራ ያለውና እምነቱን በሥራው ማሳየት የሚችለው ሰው ነው፤ እየተናገረ ያለውም ይህ እምነቱን በሥራው ማሳየት የሚችለው ሰው ነው፡፡ «እምነቴን በሥራዬ አሳይሃለሁ» በሚለው አገላለጽም ሥራ እውነተኛ እምነት በሰው ዘንድ ወይም ፊት የሚገለጥበት ማሳያ መሆኑን እንረዳለን፤ ይህ እምነቱን በሥራው ማሳየት የሚችለው ሰው ሥራ የሌለው እምነት ያለውን ሰው እንዲህ እያለ ይወቅሰዋል፤
«እግዚአብሔር አንድ እንደሆነ አንተ ታምናለህ መልካም ታደርጋለህ፤ አጋንንት ደግሞ ያምናሉ ይንቀጠቀጡማል፡፡» ይለዋል (ቊ.19)፡፡ በዚህ ቃል ውስጥ ሥራ የሌለው እምነት ያለው ሰው እምነቱ የተነጻጸረው ከአጋንንት እምነት ጋር መሆኑ ሰውየው የዳነ ሰው እንዳልሆነ ያሳያል፤ ምክንያቱም መዳን በእምነት ነው ሲባል በእውነተኛ እምነት እንጂ እንደ አጋንንት እምነት ባለ በዚህ ዓይነት እምነት አይደለም፡፡
በመቀጠልም ለዚህ አፋዊ እምነት ላለው ሰው የአብርሃም እምነትና ሥራ በማስረጃነት ቀርቦለታል፤ «አንተ ከንቱ ሰው እምነት ከሥራ ተለይቶ የሞተ መሆኑን ልታውቅ ትወዳለህን? አባታችን አብርሃም ልጁን ይስሐቅን በመሠዊያው ባቀረበ ጊዜ በሥራ የጸደቀ አልነበረምን? እምነት ከሥራው ጋር አብሮ ያደርግ እንደነበረ በሥራም እምነት እንደተፈጸመ ትመለከታለህን? መጽሐፍም አብርሃም እግዚአብሔርን አመነ ጽድቅም ሆኖ ተቈጠረለት ያለው ተፈጸመ፤ የእግዚአብሔርም ወዳጅ ተባለ፡፡» ይላል (ቊ.20‐23)፡፡ በዚህ ክፍል አብርሃም ልጁን በመሠዊያው ላይ ማቅረቡ የአብርሃም ሥራ ሆኖ ቀርቧል፤ በዚህም ሥራ የአብርሃም እምነት እንደተፈጸመ ወይም ፍጹም እንደተደረገ(ቊ.22 አ.መ.ት.) ተገልጧል፤ ከዘፍ.15፡4‐6 እንደምንረዳው ደግሞ «አብርሃም በእግዚአብሔር አመነ ጽድቅም ሆኖ ተቈጠረለት» የተባለው እግዚአብሔር ለአብርሃም ከጉልበቱ የሚወጣው እንደሚወርሰው በተናገረውና የሰማይ ከዋክብትን አሳይቶ «ዘርህም እንደዚሁ ይሆናል» ባለው ጊዜ ነው፡፡ ከዚህ በኋላ ይስሐቅን በመሠዊያ ላይ እስከሚያቀርብበት ጊዜ ድረስ ብዙ ዓመታት ተቈጥረዋል፤ በ86 ዓመቱ እስማኤልን ወልዷል(ዘፍ.16፡16)፤ ከ13 ዓመታት በኋላ በ99 ዓመቱ ራሱ አብርሃምና ልጁ እስማኤልም ተገርዘዋል(ዘፍ 17፡24‐25)፤ በ100 ዓመቱ ይስሐቅን ወልዷል(ዘፍ.21፡5)፤ ከዚያም በፍልስጥኤም ምድር ብዙ ቀን እንግዳ ሆኖ ተቀምጧል(ዘፍ.21፡34)፤ እንግዲህ ልጁ ይስሐቅን በመሠዊያ ላይ ያቀረበው ከዚህ ሁሉ በኋላ ይስሐቅ ካደገ በኋላ እንደሆነ እንረዳለን፤ በዚህ ጊዜ አብርሃም በሥራም እንደጸደቀ ተነግሮናል፤ አብርሃም በእግዚአብሔር ዘንድ የጸደቀው ግን «ከጉልበትህ የሚወጣው ይወርስሃል»፣ ዘርህ እንደዚሁ ይሆናል» የሚለው የተስፋ ቃል በተሰጠው ጊዜ ማለትም ይስሐቅ ገና ባልነበረበት ጊዜ ነው(ሮሜ 4፡18)፡፡ ያን ጊዜ በእግዚአብሔር ስላመነ ጽድቅ ሆኖ ተቈጠረለት፡፡ ከብዙ ዓመታት በኋላ ደግሞ ልጁን ይስሐቅን በመሠዊያው ባቀረበ ጊዜ በሥራም ጸደቀ፤ ይህም ማለት በሰው ዘንድ ታየ ተረጋገጠ ማለት ነው፡፡ እግዚአብሔር ግን ለአብርሃም ጽድቅን ለመቊጠር ልጁ ይስሐቅን በመሠዊያ ላይ እስኪያቀርብ ድረስ መጠበቅ አላስፈለገውም፤ አብርሃም ባመነ ጊዜ እምነቱን ጽድቅ አድርጎ ቈጥሮለታል፡፡
አብርሃም የተገረዘው እምነቱ ጽድቅ ሆኖ ከተቈጠረለት ከ13 ዓመታት በኋላ በመሆኑ መገረዙም ቢሆን በእግዚአብሔር ዘንድ ለመጽደቁ ምክንያት አልነበረም(ሮሜ4፡9‐12)፤ ነገር ግን ይህ መገረዙ «ሳይገረዝ በነበረው እምነት ያገኘው የጽድቅ ማኅተም» የሆነ ምልክት ወይም ማረጋገጫ ነበር (ሮሜ4፡11)፡፡ እንዲሁም ሕግ የተሰጠው ከ430 ዓመታት በኋላ በሙሴ ጊዜ በመሆኑ አብርሃም በዘመኑ በሕግ ሥራ ሊጸድቅ አይችልም፡፡ ስለዚህ አብርሃም የጸደቀው በሕግ ሥራ ሳይሆን በእምነት ነበር፡፡ ዛሬም ቢሆን ሰው የሚጸድቀው በሥራ ሳይሆን በእምነት እንደሆነ ለማወቅ «ለማይሠራ ኃጢአተኛውን በሚያጸድቅ ለሚያምን ሰው» እምነቱ ጽድቅ ሆኖ እንደሚቈጠርለት የተነገረውን ማስተዋል ያስፈልጋል፡፡ በተጨማሪም ጽድቅ በእምነት የመቈጠሩ ጉዳይ ለአብርሃም ብቻ ሳይሆን ለእኛም እንደሆነ መጽሐፍ ቅዱስ ሲናገር «ነገር ግን ተቈጠረለት የሚለው ቃል ስለ እርሱ ብቻ የተጻፈ አይደለም ስለእኛም ነው እንጂ፤ ስለ በደላችን አልፎ የተሰጠውን እኛን ስለማጽደቅም የተነሣውን ጌታችንን ኢየሱስን ከሙታን ባስነሳው ለምናምን ይቈጠርልን ዘንድ አለው» ይላል (ሮሜ 4፡23‐25)፡፡
ይቀጥላል...
ምንጭ፦ 1bible.page
ወደ ቻናሉ ለመ🀄️ላ🀄️ል፦ @Holy_scriptures

👍5
' ==❀❀❀===❀❀❀==
የዕለቱ ጥቅስ
==❀❀❀===❀❀❀==
“የርኅራኄ አባት የመጽናናትም ሁሉ አምላክ የሆነ የጌታችን የኢየሱስ ክርስቶስ አምላክና አባት ይባረክ።”
2ኛ ቆሮ 1፥3

👍5❤4😁1
👍6❤4😁1
' ==❀❀❀===❀❀❀==
የዕለቱ ጥቅስ
==❀❀❀===❀❀❀==
“ከባሕርም እስከ ባሕር ድረስ፥ ከሰሜንም እስከ ምሥራቅ ድረስ ይቅበዘበዛሉ፤ የእግዚአብሔርን ቃል ለመሻት ይርዋርዋጣሉ፥ አያገኙትምም።”
አሞጽ 8፥12

❤5👍1🔥1
#ፋሲካ
#ትንሣኤ
ውድ የቻናላችን ቤተሰቦች ከዛሬ ጀምሮ የፋሲካን በዓል ምክንያት በማድረግ በእናንተ በቤተሰቦቻችን አእምሮ ውስጥ ጥያቄ የሚከስቱ ነገሮችን እና ከቅዱሳት መጻሕፍት አንጻር በዚህ በዓል ዙሪያ ሊዳሰሱ የሚገቡ ነገሮችን እናያለን። በዚህ መሠረት ጥያቄ የጫረባችሁን ነገር በነጻነት በአስተያየት መስጫ ወይም ኮሜንት ቦክስ ውስጥ ማስፈር ትችላላችሁ።

❤2
#ፋሲካ
#ትንሣኤ
የጌታችን እና የመድኃኒታችን የኢየሱስ ክርስቶስ ትንሣኤ በየትኛውም ሁኔታ ፍትህና ፍርድ ለተዛባባችሁ ትክክለኛ ፍርድ እና ፍትህ እንዳለ ማሳያ ነው። እስቲ አስቡት #ትንሣኤ ባይኖር የተዳፈነው፣ የተቀበረው እንዴት ይገለጣል? ክብር ለትንሣኤው ጀግና ይሁን እንጂ!
“ቀን ቀጥሮአልና፥ በዚያም ቀን ባዘጋጀው ሰው እጅ በዓለሙ ላይ በጽድቅ ሊፈርድ አለው፤ ስለዚህም እርሱን ከሙታን በማስነሣቱ ሁሉን አረጋግጦአል።”
ሐዋርያት 17፥31

👍7❤2
' ==❀❀❀===❀❀❀==
የዕለቱ ጥቅስ
==❀❀❀===❀❀❀==
“ስለ ሥጋ ማሰብ ሞት ነውና፥ ስለ መንፈስ ማሰብ ግን ሕይወትና ሰላም ነው።”
ሮሜ 8፥6

👍6❤3
"ሆሣዕና በአርያም እያሉ ይጮኹ ነበር" ማቴ ፳፩፣፱
🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿
ነገ "ሆሳዕና" ነው:: ለትንሣኤ በዓል አንድ ሳምንት ቀረው::
«#ሆሳዕና» ቃሉ ከሁለት አረማይክ ቃላት የተሰራ ሲሆን ትርጉም «እባክህ እርዳ፣ አሁን አድን» ማለት ነው። እብራይስጡም ይህንኑ ቃል ወርሶ «הושענא » ሆሻአና ሲል ይገኛል። አዎ «አሁን አድን፣ እባክህ እርዳን» ብሎ የአዳም ዘር ያጣውን ልጅነትና የደረሰበትን ሞት ለመላቀቅ የሚያሰማው የጩኸት ድምጽ ነው፣ «ሆሳዕና»!!!
ዳዊት ነቢይ በመንፈስ ቅዱስ ተመልክቶ ማዳኑን ሲጣራና አሁን ናልን ሲል ከዘመናት በፊት አድምጠነዋል። የውስጥ ዓይኖቹ ሩቅ አይተዋል። ማዳኑንም ሽተው እንዲህ ሲል ዘምሮለታል።
«አቤቱ፥ እባክህ፥ አሁን አድን አቤቱ፥ እባክህ፥ አሁን አቅና» መዝ ፻፲፰፣፳፭
ያ ማለት ደግሞ « אָנָּ֣א יְ֭הוָה הֹושִׁ֘יעָ֥ה נָּ֑א אָֽנָּ֥א יְ֝הוָ֗ה הַצְלִ֘יחָ֥ה נָּֽא » እና ያኽዌ ሆሳአና አና ያኽዌ ሆስሊኻ ና» የሚለው የእብራይስጡ ቃል ነው።
አዎ ንጉሥ ክርስቶስ ከዘጠና ዘጠኙ በጎች መካከል የጠፋውን አንዱን በግ ፍለጋ ንጉሥ ሆኖ ሳለ እንደንጉሥ ያይደለ በአህያ፣ ለዚያውም በውርንጫ ተቀምጦ «የአሁን አድን (ሆሳዕና)» ጩኸት ሊመልስ በጽዮን ከተማ ይመጣል፤ ይህንንም ዘካርያስ ከዘመረው ዘመናት ተቆጥረው ነበር።
«አንቺ የጽዮን ልጅ ሆይ፥ እጅግ ደስ ይበልሽ አንቺ የኢየሩሳሌም ልጅ ሆይ፥ እልል በዪ እነሆ፥ ንጉሥሽ ጻድቅና አዳኝ ነው ትሑትም ሆኖ በአህያም፥ በአህያይቱ ግልገል በውርጫይቱ ላይ ተቀምጦ ወደ አንቺ ይመጣል» ዘካ ፱፣፱
ምንኛ ይደንቅ? ምንኛስ ይረቅ? ንጉሥ ስለመምጣቱ አስቀድመው የተናገሩለትና ከዘመናት በፊት ማዳኑን አይተው በእልልታ የዘመሩለት!!
አዎ የደም ግባት ብቻ ሳይሆን የንጉሥ ወግ የሌለው፣ በአህያ ለዚያውም በውርንጫ የሚመጣ ንጉሥ እንዴት ለመቀበል ይቀላል?
አባቶቻቸው ለዘመናት «ሆሳዕና፣ ማዳንህ አሁን ይሁን» ያሉለትና የዘመሩለት በዕለተ ቀጠሮው ማዳኑን ሊያሳይ ከጽዮን ደጃፍ ቀርቦ ሳለ የማያውቁት፣ ያልሰሙት፣ ትንቢቱን ያላነበቡት «ሆሳዕና» ሲሉ ትልልቆቹ ዕብራውያን ግን ዝም አሉ፣ ዝም በሉም አሉ!
«ነገር ግን የካህናት አለቆችና ጻፎች ያደረገውን ድንቃ ድንቅ በመቅደስም፣ሆሣዕና ለዳዊት ልጅ እያሉ የሚጮኹትን ልጆች ባዩ ጊዜ፥ ተቈጥተው፣ እነዚህ የሚሉትን አትሰማምን? አሉት»
የማዳኑ ጌታም፣
«እሰማለሁ፤ ከሕፃናትና ከሚጠቡት አፍ ምስጋናን ለራስህ አዘጋጀህ የሚለውን ቃል ከቶ አላነበባችሁምን? አላቸው» ማቴ ፳፩፣ ፲፭-፲፮
ኢየሱስ ክርስቶስ የእነዚህን ሕፃናት ዝማሬና ምስጋናን የሰማው ከቤተ ፋጌ ወደ ኢየሩሳሌም ማዳኑን ሊፈጽም በመጣ ጊዜ ነበር። ቤተ ፋጌ ከኢየሩሳሌም ከተማ ምሥራቃዊ አቅጣጫ በቢታንያና በደብረ ዘይት ተራራ መካከል የምትገኝ መንደር ነበረች። ቤተ ፋጌ ማለት በአረማይክ «ያልበሰለ በለስ ቤት» ማለት ነው። ርቀቱም ከኢየሩሳሌም የሰንበት ያህል ምዕራፍ ነበር።
ጌታ ኢየሱስም ከኢያሪኰ ከተማ ወደ ኢየሩሳሌም ሲወጣ ካረፈባት ከቤተ ፋጌ መንደር ሁለቱን ደቀ መዛሙርት ልኰ ውርንጫይቱን ከታሰረችበት ፈትተው እንዲያመጡለት አዟል።
«ወደ ኢየሩሳሌምም ቀርበው ወደ ደብረ ዘይት ወደ ቤተ ፋጌ ሲደርሱ፥ ያንጊዜ ኢየሱስ ከደቀ መዛሙርቱ ሁለት ላከ፥እንዲህም አላቸው፦ በፊታችሁ ወዳለችው መንደር ሂዱ፥ በዚያን ጊዜም የታሰረችን አህያ ውርንጫም ከእርስዋ ጋር ታገኛላችሁ፤ ፈትታችሁ አምጡልኝ» ማቴ ፳፩፤፪
ያን ጊዜም በቀደምት አበው የተነገረው ትንቢትና ዝማሬ ፍጻሜ አገኘ ማለት ነው።
«የሚቀድሙትም ሕዝብ የሚከተሉትም። ሆሣዕና ለዳዊት ልጅ በጌታ ስም የሚመጣ የተባረከ ነው፤ ሆሣዕና በአርያም እያሉ ይጮኹ ነበር» ማቴ ፳፩፣፱
ይሁን እንጂ ኢየሩሳሌም ለሆሳዕና አልተዘጋጀችም ነበር። ይልቁንም ቤተ መቅደሱ አካባቢ ስለማዳኑ ዝማሬ በማቅረብ ፋንታ የጦፈ የንግድ ገበያ ደርቶበት ነበር። ቤተመቅደሱ የጸሎት ሥፍራ መሆኑ ቀርቶ የሻጮችና የለዋጮች መድረክ ሆኖ ነበር። ያኔ ማዳኑ የቀረበላት ኢየሩሳሌም በመቅደሱ በራፍ ስትሸጥ፣ ስትለውጥ መድኃኒቱን ሆሳዕና እያለች መቀበልን እንዳልቻለች ሁሉ የዛሬዋ ቤተክርስቲያንስ ንግድና ሸቀጥ የሌለበትን «ሆሳዕና» እያከበረች ነው ወይ? ብለን ብንጠይቅ ራስን ማታለል ካልተጨመረበት በስተቀር፣ መሸጥ መሸቀጡ የሌለበትን «ሆሳዕና» የሚያከብር የለም ነው መልሱ። ዐውደ ምሕረቱ ሱቅ በደረቴ ያልሆነበትን ሥፍራ ማግኘት ከባድ ነው።
ኢየሱስ ማዳኑን ከመፈጸሙ በፊት እነዚህን ነጋዴዎች አስወግዷል። ገበታቸውን ገልብጧል። እየገረፈ አስወጥቷል። የወንበዴዎች ዋሻ የሆነውን የጸሎት ቤት ጠራርጓል። ዛሬስ ቤቱ ስንት ወንበዴ መሽጎበት ይሆን? ወንበዴዎቹ ይዘምራሉ፣ ሆሳዕና ይላሉ፣ የዘንባባ ዝንጣፊ ይይዛሉ፣ በጣታቸው፣ በግንባራቸው ያስራሉ። ወንበዴዎች ናቸው ተብለው እንዳይርቋቸው የአምልኰ መልክ አላቸው። ቤተመቅደሱን የወንበዴዎች ዋሻ አደረጋችሁ ያለው በግብር ውንብድና በመልክ ግን አገልጋይ ይመስሉ የነበሩትን የመቅደሱን ሰዎች ነበር። ዛሬም እንደዚያው!!
በእድሜአችን ስንት «ሆሳዕና በአርያም» አሳለፍን? ማዳኑ በተደረገለት ማንነታችን ውስጥ ስንት ፍሬ አፈራን? የተራበው ኢየሱስ ከእኛ የሚፈልገውን ፍሬ ይዘናል? ወይስ ፍሬ አልባ ሆነን ለቁጣ የተዘጋጀን እንሆን? «ሆሳዕና በአርያም» ማለቱ ብቻውን አያድንም፣ ማዳኑንም አያመጣም። የወንበዴ ዋሻ ማንነታችንን እናጽዳ። ከዚህ ዓለም ሽቃጭና ልዋጭ ማስመሰያ ማንነት እንውጣ! በጎ ፍሬ እንዲያፈራ ለተላከው የወይኑ ባለቤት ወራሽ እንገዛ! ያኔ «ሆሳዕና በአርያም» ስንል ማዳኑ ፈጥኖ ይሆንልናል።
አዎ ሆሳዕና በአርያም! በዚህም በወዲያኛውም! ሆሳዕና በአርያም።ሃሌ ሉያ!!!!!!!
ምንጭ:- ደጀ ብርሃን

❤5👍4
' ==❀❀❀===❀❀❀==
የዕለቱ ጥቅስ
==❀❀❀===❀❀❀==
“የሚቀድሙትም ሕዝብ የሚከተሉትም፦ ሆሣዕና ለዳዊት ልጅ በጌታ ስም የሚመጣ የተባረከ ነው፤ ሆሣዕና በአርያም እያሉ ይጮኹ ነበር።”
ማቴዎስ 21፥9

❤7👍1
#ትንሣኤ
#ፋሲካ
#ሆሣዕና፣ ኢየሱስ ብዙ አጀብና ሙገሳ የገጠመው ቀን ነው። ነገር ግን "ስቀለው፣ ስቀለው" የሚል ተቃውሞም ከፊቱ ነበር። በዚህ ሁሉ ግን ዓላማውንና የምድር ጉዞውን በሚገባ ስለሚያውቅ በሰው ሁኔታ አልሞቀውም አልበረደውምም። እኛም ዓላማችንንና ፍጻሜያችንን በሚገባ በማወቅ በኑሮአችን ጸንተን ጌታችንን እንድናስከብር ጌታ ይርዳን!

👍4🔥2❤1
ሆሣዕና ማለት ምን ማለት ነው?
Anonymous Quiz
0%
ሀ. አሁን ንገሥ
61%
ለ. በእግዚአብሔር ስም የሚመጣ ንጉሥ የተባረከ ነው።
36%
ሐ. አሁን አድን
3%
መ. የነገሥታት ንጉሥ
👍5❤1
#ትንሣኤ
#ፋሲካ
#ሰኞ
ጌታ ሆይ፣ በቤትህ የምትናገረውን ሁሉ የምንሰማበት፣ የእኛም ጩኹት በአንተ ዘንድ የሚሰማበት የጸሎት ቤት ይሁን!
ወደ ቻናሉ ለመ🀄️ላ🀄️ል፦ @Holy_scriptures
#ፋሲካ
#ሰኞ
ጌታ ሆይ፣ በቤትህ የምትናገረውን ሁሉ የምንሰማበት፣ የእኛም ጩኹት በአንተ ዘንድ የሚሰማበት የጸሎት ቤት ይሁን!
ወደ ቻናሉ ለመ🀄️ላ🀄️ል፦ @Holy_scriptures
👍6❤2
' ==❀❀❀===❀❀❀==
የዕለቱ ጥቅስ
==❀❀❀===❀❀❀==
“ይህስ ስሜ የተጠራበት ቤት በዓይናችሁ የሌቦች ዋሻ ሆኖአልን? እነሆ፥ እኔ አይቻለሁ፥ ይላል እግዚአብሔር።”
ኤርምያስ 7፥11

#ሰኞ፣ ከሆሳዕና ማግሥት ጌታችን ከቢታንያ ወደ ኢየሩሳሌም ሲገባ ሁለት ነገሮችን አድርጓል፡፡ አንደኛ ከቅጠል በስተቀር ፍሬ ያልተገኘባትን ዕፀ በለስ ረግሟል፡፡ ሁለተኛ ወደ ቤተ መቅደስ ገብቶ የሚሸጡትንና የሚለውጡትን አስወጥቷል፡፡ (ማቴ.21÷12-17፤ ማር.11÷17፤ ሉቃ.19÷45-46፡፡)
መልእክት፦ ቤተ መቅደሱ እንዲሁም በለሷ የሚጠበቅባቸውን በተገቢው ሁኔታ አልያዙም።
👉 በለሷ ከፍሬ ጎድላ ተገኝታለች።
👉 ቤተመቅደሱ የማይጠበቅበትን ይዟል።
በቅዱስ ሉቃስ ወንጌል ላይ እንደተገለጸው ይህንም ምሳሌ አለ "ለአንድ ሰው በወይኑ አትክልት የተተከለች በለስ ነበረችው ፍሬም ሊፈልግባት ወጥቶ ምንም አላገኘም፡፡" ሉቃ 13፡6 በማለት በበለስ ስለተመሰለ የሰው ልጅ ሕይወት በማሰብ እንዲመለስ ንስሐ እንዲገባ በሕይወትም እንዲኖር እግዚአብሔር ኢየሱስ ክርስቶስ ማሳሰቡን ያጠይቃል፡፡ ንስሐ አልገባም አልመለስም ያለም በለሷ እንደጠወለገችና እንደተቆረጠች ሁሉ ፍሬ ባለማፍራታቸው እንደሚቆረጡ እንዲሁም ወደ እሳት እንደሚጣሉ መጽሐፍ ቅዱስ በግልጽ ያስረዳል፡፡ ፍሬ አልባ እንዳንሆን ጌታ ሲመጣም እንዳናፍር የመጽሐፉን ቃል ልንጠብቅና ልንፈጽም ይገባናል፡፡ በዚህ የሕማማት የመጀመሪያ ቀን ዕለተ ሰኞ የምናስበው የምንዘክረው የሰው ልጅ ሕይወት በከንቱ በቸልተኝነት እንዳይደክም እንዳይጠወለግ እንዳይደርቅ ወደ እሳትም እንዳይጣል ማድረግ ይገባናል፡፡
ጌታችን መድኃኒታችን ወደ ቤተ መቅደስ ግብቶ የሚሸጡትንና የሚለውጡትን እንዳስወጣ ሁሉ፤ ዛሬ የእግዚአብሔር ቤተሰቦች ጌታችን ወደ መቅደስ ሕይወታችን ቢመጣ ምን ያገኝ ይሆን? ፍፌስ እያፈራን ይሆን? የእግዚአብሔር ቃል ግን ለንስሐ የሚገባ ፍሬ አድርጉ ይለናል። ማቴ 3፡8
ምንጭ:- tesfalem7.blogspot.com

👍7
' ==❀❀❀===❀❀❀==
የዕለቱ ጥቅስ
==❀❀❀===❀❀❀==
“አቤቱ፥ መንገድህን አመልክተኝ፥ ፍለጋህንም አስተምረኝ።”
መዝሙር 25፥4
ወደ ቻናሉ ለመ🀄️ላ🀄️ል፦ @Holy_scriptures
የዕለቱ ጥቅስ
==❀❀❀===❀❀❀==
“አቤቱ፥ መንገድህን አመልክተኝ፥ ፍለጋህንም አስተምረኝ።”
መዝሙር 25፥4
ወደ ቻናሉ ለመ🀄️ላ🀄️ል፦ @Holy_scriptures
❤3👍3
#ማክሰኞ ኢየሱስ ለመጨረሻ ጊዜ በቤተ መቅድስ ያስተማረበት ቀን ነው።
ጌታ ከቃሉ ስንት ጊዜ አስተማረን? ምን ያህልስ ወደ ተግባር ለወጥነው? ወይስ እንደ ፈሪሳውያን በራሱ መጽሐፍ ላይ ጌታችንን እየተከራከርነውና አልፎ ተርፎም ከሕይወታችን ልናስወጣው እየከጀልን ይሆን? የማንስ ጽሕፈት በላያችን ይታያል?
ለመሆኑ ጌታችንና መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ምን አስተማረ? ወይም ምን ተማሩ አለ?
👉“እንግዲህ ከነዚህ ከሁሉ ካነሱት ትእዛዛት አንዲቱን የሚሽር ለሰውም እንዲሁ የሚያስተምር ማንም ሰው በመንግሥተ ሰማያት ከሁሉ ታናሽ ይባላል፤ የሚያደርግ ግን የሚያስተምርም ማንም ቢሆን እርሱ በመንግሥተ ሰማያት ታላቅ ይባላል።”
ማቴዎስ 5፥19
👉“የሰው ልጅ ብዙ መከራ ሊቀበል፥ ከሽማግሌዎችም ከካህናት አለቆችም ከጻፎችም ሊጣል፥ ሊገደልም ከሦስት ቀንም በኋላ ሊነሣ እንዲገባው ያስተምራቸው ጀመር፤ ቃሉንም ገልጦ ይናገር ነበር።”
ማርቆስ 8፥31
👉“ቀንበሬን በላያችሁ ተሸከሙ ከእኔም ተማሩ፥ እኔ የዋህ በልቤም ትሑት ነኝና፥ ለነፍሳችሁም ዕረፍት ታገኛላችሁ፤”
ማቴዎስ 11፥29
👉“ሲያስተምርም እንዲህ አለ፦ ረጃጅም ልብስ ለብሰው መዞርን፥ በገበያም ሰላምታን፥ በምኵራብም የከበሬታን ወንበር፥ በግብርም የከበሬታን ስፍራ ከሚወዱ ከጻፎች ተጠበቁ፤”
ማርቆስ 12፥38-39
👉 “እንግዲህ ሂዱና አሕዛብን ሁሉ በአብ በወልድና በመንፈስ ቅዱስ ስም እያጠመቃችኋቸው፥ ያዘዝኋችሁንም ሁሉ እንዲጠብቁ እያስተማራችኋቸው ደቀ መዛሙርት አድርጓቸው፤ እነሆም እኔ እስከ ዓለም ፍጻሜ ድረስ ሁልጊዜ ከእናንተ ጋር ነኝ።”
ማቴዎስ 28፥19-20

❤15👍3
' ==❀❀❀===❀❀❀==
የዕለቱ ጥቅስ
==❀❀❀===❀❀❀==
“ኢየሱስ ግን እንዲህ አለ፦ ተዉአት፤ ስለ ምን ታደክሙአታላችሁ? መልካም ሥራ ሠርታልኛለች።”
ማርቆስ 14፥6

❤10👍1