' 📜📜📜===📜📜📜
📜 የዕለቱ ጥቅስ 📜
📜📜📜===📜📜📜
“እንደሚታዘዙ ልጆች ባለማወቃችሁ አስቀድሞ የኖራችሁበትን ምኞት አትከተሉ።”
1ኛ ጴጥሮስ 1፥14
ወደ ቻናሉ ለመ🀄️ላ🀄️ል፦ @Holy_scriptures

👍2❤1
#ከተማ_ወይም_ቦታ_በቅዱሳት_መጻሕፍት
#ቤርሳቤህ፤
ቤርሳቤህ ማለት ሰባት የውሃ ጉድጓድ ወይም የመሐላ የውሃ ጉድጓድ ማለት ሊሆን ይችላል። ከኬብሮን በስተደቡብ በኩል አርባ ኪሎ ሜትር ርቆ የሚገኝ ከተማ። ለመጀመሪያ ጊዜ በአብርሃም ተሰየመ፤ ዘፍ. 21፥30:31። የይስሐቅም የውሃ ጕድጓድ ሳቤህ ከተባለ በኋላ ቤርሳቤህ ተብሏል፤ ዘፍ. 26፥33። ግን ሁሉም አንድ ቦታ ይመስላል። ቤርሳቤህ የእስራኤል ደቡብ ዋና ከተማ ስለነበረ፥ የእስራኤል ምድር ብዙ ጊዜ «ከዳን እስከ ቤርሳቤህ» እየተባለ ተጠቅሷል፤ መሳ 20፥1 2ኛ ዜና 30፥5። አብርሃም፥ ይስሐቅና ያዕቆብ በዚያ ተቀመጡ፤ ዘፍ. 22፥19፤ 26፥23፤ 46፥1። ኤልያስ በዚህ በኩል ወደ ደብረ ሲና ሄደ፤ 1ነገ. 19፥3። ይህ ቦታ ዛሬ ትልቅ ከተማ ነው።
ምንጭ፦ የመጽሐፍ ቅዱስ መዝገበ ቃላት፤ ገጽ 110

👍5
' 📜📜📜===📜📜📜
📜 የዕለቱ ጥቅስ 📜
📜📜📜===📜📜📜
“ምድሪቱም ሴቲቱን ረዳቻት፥ ምድሪቱም አፍዋን ከፍታ ዘንዶው ከአፉ ያፈሰሰውን ወንዝ ዋጠችው።”
ራእይ 12፥16

👍3❤1
Yetwilid inkifat 2.pdf
2.1 MB
👉ርዕስ፦ የትውልድ የእንቅፋት ድንጋዮች
✍️ጸሐፊ፦ ደረጀ ሙላት
🗓የታተመበት ዓመት፦ 2006 ዓ.ም
📑የገጽ ብዛት፦ 163
🔐ከዶ/ር ሔኖክ ገ/ሕይወት ትምህርት በመነሳት የተጻፈ
ወደ ቻናሉ ለመ🀄️ላ🀄️ል፦ @Holy_scriptures
✍️ጸሐፊ፦ ደረጀ ሙላት
🗓የታተመበት ዓመት፦ 2006 ዓ.ም
📑የገጽ ብዛት፦ 163
🔐ከዶ/ር ሔኖክ ገ/ሕይወት ትምህርት በመነሳት የተጻፈ
ወደ ቻናሉ ለመ🀄️ላ🀄️ል፦ @Holy_scriptures
👍5
' 📜📜📜===📜📜📜
📜 የዕለቱ ጥቅስ 📜
📜📜📜===📜📜📜
“ነገር ግን እውነትን በፍቅር እየያዝን በነገር ሁሉ ወደ እርሱ ራስ ወደሚሆን ወደ ክርስቶስ እንደግ፤”
ኤፌሶን 4፥15

👍6❤3
#የእግዚአብሔር_ቃል_ምን_ይላል?
ቲቶ 3
¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯
¹-² ለገዦችና ለባለ ሥልጣኖች የሚገዙና የሚታዘዙ፥ ለበጎ ሥራ ሁሉ የተዘጋጁ፥ ማንንም የማይሰድቡ፥ የማይከራከሩ፥ ገሮች፥ ለሰው ሁሉ የዋህነትን ሁሉ የሚያሳዩ እንዲሆኑ ኣሳስባቸው።
³ እኛ ደግሞ አስቀድመን የማናስተውል ነበርንና፤ የማንታዘዝ፥ የምንስት፥ ለምኞትና ለልዩ ልዩ ተድላ እንደ ባሪያዎች የምንገዛ፥ በክፋትና በምቀኝነት የምንኖር፥ የምንጣላ፥ እርስ በርሳችን የምንጠላላ ነበርን።
⁴ ነገር ግን የመድኃኒታችን የእግዚአብሔር ቸርነትና ሰውን መውደዱ በተገለጠ ጊዜ፥
⁵ እንደ ምሕረቱ መጠን ለአዲስ ልደት በሚሆነው መታጠብና በመንፈስ ቅዱስ በመታደስ አዳነን እንጂ፥ እኛ ስላደረግነው በጽድቅ ስለ ነበረው ሥራ አይደለም፤
⁶-⁷ ያን መንፈስም፥ በጸጋው ጸድቀን በዘላለም ሕይወት ተስፋ ወራሾች እንድንሆን፥ በመድኃኒታችን በኢየሱስ ክርስቶስ በእኛ ላይ አትርፎ አፈሰሰው።
⁸ ቃሉ የታመነ ነው። እግዚአብሔርንም የሚያምኑት በመልካም ሥራ በጥንቃቄ እንዲጸኑ፥ እነዚህን አስረግጠህ እንድትናገር እፈቅዳለሁ። ይህ መልካምና ለሰዎች የሚጠቅም ነው፤
⁹ ነገር ግን ሞኝነት ካለው ምርመራና ከትውልዶች ታሪክ ከክርክርም ስለ ሕግም ከሚሆን ጠብ ራቅ፤ የማይጠቅሙና ከንቱዎች ናቸውና፤
¹⁰-¹¹ መለያየትን የሚያነሣ ሰው ጠማማ እንዲሆን በራሱም ላይ ፈርዶ ኃጢአትን እንዲያደርግ አውቀህ፥ አንድ ጊዜ ሁለት ጊዜም ከገሠጽኸው በኋላ እንዲህ ከሚመስል ሰው ራቅ።
¹² አርጢሞንን ወይም ቲኪቆስን ወደ አንተ ስልክ፥ ወደ ኒቆጵልዮን ወደ እኔ እንድትመጣ ትጋ፤ በዚያ ልከርም ቈርጬአለሁና።
¹³ ሕግ አዋቂውን ዜማስንና አጵሎስን ምንም እንዳይጎድልባቸው በጉዞአቸው ተግተህ እርዳ።
¹⁴ ከወገናችንም ያሉት ደግሞ ፍሬ ቢሶች ሆነው እንዳይቀሩ፥ የግድ ስለሚያስፈልገው ነገር በመልካም ሥራ እንዲጸኑ ይማሩ።
¹⁵ ከእኔ ጋር ያሉት ሁሉ ሰላምታ ያቀርቡልሃል። በእምነት ለሚወዱን ሰላምታ አቅርብልን። ጸጋ ከሁላችሁ ጋር ይሁን፤ አሜን።

❤7👍2🔥1
' 📜📜📜===📜📜📜
📜 የዕለቱ ጥቅስ 📜
📜📜📜===📜📜📜
“ሕግ አዋቂውን ዜማስንና አጵሎስን ምንም እንዳይጎድልባቸው በጉዞአቸው ተግተህ እርዳ።”
ቲቶ 3፥13

❤4👍3
#እራሳችንን_እንመርምር
በእግዚአብሔር ፊት ታላቅ መሆን የአንድ ጤናማ አማኝ ፍላጎት ነው። ጥያቄው ግን ይህ ጥማት ያለን ሰዎች በምን ተሞልተን እንገኛል? የምንሞላበትን ነገር መምረጥ የሚያስፈልግ አይመስላችሁም?
“በጌታ ፊት ታላቅ ይሆናልና፥ የወይን ጠጅና የሚያሰክር መጠጥ አይጠጣም፤ ገናም በእናቱ ማኅፀን ሳለ መንፈስ ቅዱስ ይሞላበታል፤”
ሉቃስ 1፥15
“መንፈስ ይሙላባችሁ እንጂ በወይን ጠጅ አትስከሩ ይህ ማባከን ነውና፤”
ኤፌሶን 5፥18

❤4👍4
' 📜📜📜===📜📜📜
📜 የዕለቱ ጥቅስ 📜
📜📜📜===📜📜📜
“በዚያም ጊዜ እስራኤል ይህን መዝሙር ዘመረ። አንተ ምንጭ ሆይ፥ ፍለቅ፤ እናንተ ዘምሩለት፤”
ዘኍልቁ 21፥17

👍6❤5
ቅዱሳት መጻሕፍት
#የሮሜ_መልእክት_ጥናት እግዚአብሔር የሚፈርደው በትክክል ነው (9፥14-18) 14–16 አንዳንዶች እግዚአብሔር የሚፈርደው በትክክል አይደለም ብለው ያስባሉ። እንዲህ በማለትም ይጠይቃሉ፥ «እግዚአብሔር ያዕቆብን የወደደውና ኤላውን የጠላው ለምንድን ነው? በዚህ እግዚአብሔር ፍርድ አላጓደለምን?» ስለ እግዚአብሔር እንዲህ የመሰሉ አሳቦች ሊኖሩን አይገባም። በቁ. 15 ጳውሎስ እግዚአብሔር በዘጸ. 33፥19…
#የሮሜ_መልእክት_ጥናት
የቀጠለ...
እግዚአብሔር የሚፈርደው በትክክል ነው (9፥14-18)
በሌላ በኩል ምሕረት ማንም ሊያገኘው የሚገባ ነገር አይደለም። ይህ ከሆነ ምሕረት ሊሆን አይችልም። ምሕረት በተፈጥሮው የማይገባው ሰው የሚቀበለው ነው። ስለዚህ ምሕረት አልተቀበልኩም በማለት ማንም ሊያጉረመርም አይገባም። ምክንያቱም ማንም ሰው ምሕረትን ለመቀበል የበቃ አይደለም። እግዚአብሔርን ለምን ለእከሌ ምሕረት ሳታሳየው ቀረህ ብሎ የሚወቅሰው የለም። እግዚአብሔር ግን ለአንዳንድ ሰዎች ምሕረት ለማሳየት ቢወስን እዚህ ላይ ያለው ስሕተት ምንድን ነው? ይህን በማድረጉ ትክክለኛ አይደለም ማለት ነውን? በጭራሽ አይደለም።
ስለዚህ እግዚአብሔር ፍትሕን (ቅጣትን) ለሁሉም እንደሚሰጥ እናያለን። ነገር ግን ለአንዳንዶች ከዘላለማዊ ፈቃዱ የተነሣ ምሕረት ያሳያቸዋል። ክርስቶስ ወደዓለም ከመጣበት ጊዜ ጀምሮ በእርሱ ለሚያምኑበት ሁሉ እግዚአብሔር ምሕረቱን አሳይቶአል። ይህም ሲባል ለእኛ የሚገባንን ትክክለኛ ቅጣት ከእኛ አላራቀውም፤ ይልቁንም በእኛ ምትክ ለክርስቶስ ሰጥቶታል። የእግዚአብሔርን ፍትሕና ምሕረት በአንድነት ስለሆነም ልናያቸው እንችላለን። ደኅንነትን የሚቀበሉ እግዚአብሔርን ሊያመሰግኑ ይገባቸዋል። ምክንያቱም ደኅንነታቸው የተገኘው ከእግዚአብሔር ምሕረትና ጸጋ የተነሣ ነው። ዘላለማዊ ቅጣትን የሚቀበሉ ደግሞ በኃጢአታቸው ምክንያት ይቀበላሉ። ኃላፊነቱን ራሳቸው ይወስዳሉ፤ የሚገባቸውን ሙሉ ቅጣት ይቀበላሉ።
ንስሓ በመግባት ኢየሱስን ጌታና አዳኝ አድርገው ለሚቀበሉት እግዚአብሔር ምሕረቱን ማሳየት የሚፈልግ ሲሆን፣ ንስሓ መግባትን ባለመቀበል በኀጢአት ለመቀጠል የሚፈልጉትንና በክርስቶስ ያለውን ድነት የሚያጣጥሉትን ደግሞ ልባቸውን ያደነድናል። ይህም ለማንም ሰው ወይም ሕዝብ ሲባል የማይለወጥ ቋሚ መለኮታዊ ዐላማ ነው (ከ2፥4-11 ጋር ያነጻጽሩ)::
የፈርዖን ልብ መደንደን አንዳንዴ ከእግዚአብሔር እንደሆነ (ዘፀ 4፥21፤ 7፥3:13፤ 9፥12፤ 10፥1፤ 11፥10፤ 14፥17) በሌላ ጊዜ ደግሞ ከራሱ ከፈርዖን እንደነበር ተመልክቷል (ዘፀ 7፥22-23፤ 8፥15 ፡ 32 ) ፡፡ ከልቡ ትዕቢት የተነሣ ከእግዚአብሔር ጋር የተጣላው ፈርዖን ተገቢውን የእግዚአብሔርን ፍርድ ተቀበለ፡፡ ለእግዚአብሔር
ፈቃድም እምቢተኛ እየሆነ በመምጣቱም እግዚአብሔር የበለጠ ልቡን አደነደነው (ዘፀ 7፥3)። ስለዚህ እግዚአብሔር የፈርዖንን ልብ ያደነደነው በዘፈቀደ አይደለም፤ እግዚአብሔር ጽድቅ በሆነው መርሑ መሠረት በእርሱ ላይ የሚያምጹትን ሁሉ ልባቸውን ያደነድናል (ከ1፥12-32)፡፡
ምንጭ፦ የአዲስ ኪዳን ማብራሪያ፤ ገጽ 372-373፣ ምሉእ ሕይወት፤ ገጽ 1757

❤3👍1
ሐዋርያው ቅዱስ ጳውሎስ ወደ ኢየሩሳሌም ሄዶ ደቀመዛሙርት አልቀበል ሲሉት እንዲቀበሉት ያደረገ እና በአንጾኪያ ቤተክርስቲያን እንዲያገለግል ከጠርሴስ ያስመጣው ማን ነው?
Anonymous Quiz
5%
ሀ. ጴጥሮስ
7%
ለ. ያዕቆብ
71%
ሐ. በርናባስ
8%
መ. ሲላላ
3%
ሠ. ዮሐንስ
7%
ረ. ፊልጶስ
👍7👏1
' 📜📜📜===📜📜📜
📜 የዕለቱ ጥቅስ 📜
📜📜📜===📜📜📜
“በዚያም ዘመን በእስራኤል ዘንድ ንጉሥ አልነበረም፤ ሰው ሁሉ በፊቱ መልካም መስሎ የታየውን ያደርግ ነበር።”
መሳፍንት 21፥25
ወደ ቻናሉ ለመ🀄️ላ🀄️ል፦ @Holy_scriptures
📜 የዕለቱ ጥቅስ 📜
📜📜📜===📜📜📜
“በዚያም ዘመን በእስራኤል ዘንድ ንጉሥ አልነበረም፤ ሰው ሁሉ በፊቱ መልካም መስሎ የታየውን ያደርግ ነበር።”
መሳፍንት 21፥25
ወደ ቻናሉ ለመ🀄️ላ🀄️ል፦ @Holy_scriptures
❤4👍3
መዳን በሥራ ካልሆነ ለመልካም ሥራ ከጌታ የምናገኘው ምንድነው?
ክፍል-1
ሰው በእምነት ብቻ ሳይሆን በሥራም እንደሚጸድቅ በያዕቆብ ምዕራፍ 2 ውስጥ መገለጹ ሰው በእግዚአብሔር ዘንድ ስለመጽደቁ ሳይሆን አንድ ሰው መጽደቁ በሰው ዘንድ ስለመታየቱ ወይም ስለመረጋገጡ የሚገልጽ ነው፡፡ በመጽሐፍ ቅዱስ መሠረት ሰው የሚድነው ወይም የሚጸድቀው በእምነት እንጂ በሥራ እንዳልሆነ እርግጥ ነው፤ ይህ በእምነት የመጽደቅ ጉዳይም በሰው ዘንድ ሳይሆን በእግዚአብሔር ዘንድ የሚታየው ነው፡፡
በሮሜ 4፡1‐8 የምናገኘው የእግዚአብሔር ቃል ይህን የሚያረጋግጥ ነው፤ በቊ.1 ላይ «በሥጋ አባታችን የሆነ አብርሃም ምን አገኘ እንላለን? አብርሃም በሥራ ጸድቆ ቢሆን የሚመካበት አለውና፤ ነገር ግን በእግዚአብሔር ዘንድ አይደለም» ይላል፤ «በእግዚአብሔር ዘንድ አይደለም» የሚለው ይህ ቃል በእግዚአብሔር ዘንድ በሥራ መጽደቅ እንደሌለ የሚገልጽ ነው፡፡
በዚህ ክፍል ሰው ያለ ሥራ በእምነት እንደሚጸድቅ ለማሳየት ሁለት ሰዎች በምሳሌነት ተጠቅሰዋል፤ እነርሱም አብርሃምና ዳዊት ናቸው፡፡ እነዚህ ሁለት ሰዎች በአንድነት መጠቀሳቸው በመጽሐፍ ቅዱስ የተለመደ ሲሆን (ማቴ.1፡1፤ የሐ.ሥ.13፡26‐36) ይህንንም ታላቅ ርእሰ ጉዳይ ለማብራራት አብረው መጠቀሳቸው ወሳኝ ነው፡፡ አብርሃም የነበረው ሕግ ከመሰጠቱ በፊት ሲሆን ዳዊት ደግሞ በሕጉ ዘመን የነበረ ሰው ነው፤ ከሁለቱም ሰዎች አንጻር ሲታይ ግን በእግዚአብሔር ዘንድ ጽድቅ የሚቈጠረው በሥራ ሳይሆን በእምነት እንደሆነ ተብራርቷል፡፡
በቊ.3 ላይ አብርሃምን በተመለከተ ሲገልጽ «መጽሐፍስ ምን አለ? አብርሃም እግዚአብሔርን አመነ ጽድቅም ሆኖ ተቈጠረለት፤ ለሚሠራ ደመወዝ እንደ ዕዳ ነው እንጂ እንደ ጸጋ አይቈጠርለትም፤ ነገር ግን ለማይሠራ ኃጢአተኛውን በሚያጸድቅ ለሚያምን ሰው እምነቱ ጽድቅ ሆኖ ይቈጠርለታል» ይላል፡፡ በዚህም ቃል ውስጥ አብርሃም ጽድቅን ያገኘው እግዚአብሔርን ስላመነ ተቈጥሮለት እንጂ ጽድቅ ሠርቶ እንዳልሆነ እንገነዘባለን፡፡ ይህም ለሚያምን ሰው ሁሉ እግዚአብሔር የሚያደርገው መሆኑ ተገልጿል፡፡ በመቀጠል ደግሞ ዳዊት ይህን ጉዳይ በተመለከተ የተናገረው ተጠቅሷል፡፡ ይኸውም «እንደዚህም ደግሞ እግዚአብሔር ያለ ሥራ ጽድቅን ስለሚቈጥርለት ሰው ብፅዕና ይናገራል እንዲህ ሲል፤ ‘ዓመፃቸው የተሰረየላቸው ኃጢአታቸውም የተከደነላቸው ብፁዓን ናቸው፤ ጌታ ኃጢአቱን የማይቈጥርበት ሰው ብፁዕ ነው’»(ቊ.6‐8)፤ በአብርሃም ሕይወት እንዳየነው እግዚአብሔር ሊቈጠርልን የማይገባውን ጽድቅ በእምነት ሲቈጥርልን እናያለን፤ በዚህ ዳዊት በተናገረው ቃል ውስጥ ደግሞ እግዚአብሔር ሊቈጥርብን የሚገባውን ኃጢአት ባለመቊጠር ጸጋውን ሲያሳይ እንመለከታለን፡፡ ይህም «እግዚአብሔር ያለ ሥራ ጽድቅን ስለሚቈጥርለት ሰው ብፅዕና» የተነገረ መሆኑ ተገልጿል፡፡ ስለዚህ በሮሜ 4 ውስጥ የተሰጠው ትምህርት ሰው በእግዚአብሔር ዘንድ የሚጸድቀው ያለ ሥራ በእምነት መሆኑን የሚያሳይ ነው፤ ይህ እምነት በሥራ ሊገለጥ የሚችል እውነተኛ መሆኑን እግዚአብሔር ማወቅ ይችላልና፡፡
በያዕቆብ ምዕራፍ 2 ውስጥ የምናገኘው ትምህርት ግን ጽድቅ ወይም መዳን በሰው ዘንድ የሚታየው ወይም የሚረጋገጠው በእምነት ብቻ ሳይሆን በሥራም እንደሆነ የሚገልጽ ነው፡፡ በሰው ዘንድ የአንድ ሰው እምነት እውነተኛ እምነት መሆኑ ሊታይ የሚችለው በሥራ ነው፤ በቊ.14 ላይ «ወንድሞች ሆይ እምነት አለኝ የሚል ሥራ ግን የሌለው ሰው ቢኖር ምን ይጠቅመዋል፤ እምነቱስ ሊያድነው ይችላልን?» በማለት ያዕቆብ ጥያቄ ያነሳል፤ እዚህ ላይ «እምነት አለኝ» የሚለው ያ ሰው ራሱ ነው፡፡
ይቀጥላል...
ምንጭ፦ 1bible.page

👍9❤1
' ==❀❀❀===❀❀❀==
የዕለቱ ጥቅስ
==❀❀❀===❀❀❀==
“ናቡከደነፆርም መልሶ፦ መልአኩን የላከ፥ ከአምላካቸውም በቀር ማንንም አምላክ እንዳያመልኩ ለእርሱም እንዳይሰግዱ ሰውነታቸውን አሳልፈው የሰጡትን የንጉሡንም ቃል የተላለፉትን በእርሱ የታመኑትን ባሪያዎቹን ያዳነ፥ የሲድራቅና የሚሳቅ የአብደናጎም አምላክ ይባረክ።”
ዳንኤል 3፥28

❤4🔥2👍1
' ==❀❀❀===❀❀❀==
የዕለቱ ጥቅስ
==❀❀❀===❀❀❀==
“ከእናንተ የሆነ የክርስቶስ ባሪያ ኤጳፍራ ሰላምታ ያቀርብላችኋል፤ በእግዚአብሔር ፈቃድ ሁሉ ተረድታችሁና ፍጹማን ሆናችሁ እንድትቆሙ፥ ሁልጊዜ ስለ እናንተ በጸሎቱ ይጋደላል።”
ቆላስይስ 4፥12

❤5👍1
መዳን በሥራ ካልሆነ ለመልካም ሥራ ከጌታ የምናገኘው ምንድነው?
ክፍል-2
እግዚአብሔር ይህ እምነት እውነተኛ መሆን አለመሆኑን በራሱ አምላካዊ እውቀት ያውቃል፤ ሰው ግን ይህን የሚያውቀው ሥራውን አይቶ ነው፤ እዚህ ላይ የተጠቀሰው «እምነት አለኝ» ባዩ ሰው ደግሞ ሥራ እንደሌለው ታውቋል፤ ስለዚህ በቊ.17 ላይ «ሥራ የሌለው እምነት ቢኖር በራሱ የሞተ ነው» ተብሏል፡፡ በእግዚአብሔር ዘንድ እውነተኛ እንደሆነ የሚታወቅ እምነት ግን ሥራ የሌለው ሊሆን አይችልም፤ በጊዜው ባይገለጥ እንኳ እግዚአብሔር ጽድቅ አድርጎ የቈጠረው እምነት ከሆነ በሥራ መገለጡ አይቀርም፡፡ ያን ጊዜም በሰው ዘንድ ይታያል፤ ስለዚህ በቊ.18 ላይ እንደተጠቀሰው «አንድ ሰው አንተ እምነት አለህ እኔም ሥራ አለኝ እምነትህን ከሥራህ ለይተህ አሳየኝ እኔም እምነቴን በሥራዬ አሳይሃለሁ ይላል» ተብሎ በሁለት ሰዎች መካከል በዚህ ጉዳይ ሊባል የሚችለው ነገር ተነግሮናል፤ እነዚህ ሁለት ሰዎች አንዱ እምነት አለኝ የሚለው ሰው ሲሆን ሌላው ደግሞ ሥራ ያለውና እምነቱን በሥራው ማሳየት የሚችለው ሰው ነው፤ እየተናገረ ያለውም ይህ እምነቱን በሥራው ማሳየት የሚችለው ሰው ነው፡፡ «እምነቴን በሥራዬ አሳይሃለሁ» በሚለው አገላለጽም ሥራ እውነተኛ እምነት በሰው ዘንድ ወይም ፊት የሚገለጥበት ማሳያ መሆኑን እንረዳለን፤ ይህ እምነቱን በሥራው ማሳየት የሚችለው ሰው ሥራ የሌለው እምነት ያለውን ሰው እንዲህ እያለ ይወቅሰዋል፤
«እግዚአብሔር አንድ እንደሆነ አንተ ታምናለህ መልካም ታደርጋለህ፤ አጋንንት ደግሞ ያምናሉ ይንቀጠቀጡማል፡፡» ይለዋል (ቊ.19)፡፡ በዚህ ቃል ውስጥ ሥራ የሌለው እምነት ያለው ሰው እምነቱ የተነጻጸረው ከአጋንንት እምነት ጋር መሆኑ ሰውየው የዳነ ሰው እንዳልሆነ ያሳያል፤ ምክንያቱም መዳን በእምነት ነው ሲባል በእውነተኛ እምነት እንጂ እንደ አጋንንት እምነት ባለ በዚህ ዓይነት እምነት አይደለም፡፡
በመቀጠልም ለዚህ አፋዊ እምነት ላለው ሰው የአብርሃም እምነትና ሥራ በማስረጃነት ቀርቦለታል፤ «አንተ ከንቱ ሰው እምነት ከሥራ ተለይቶ የሞተ መሆኑን ልታውቅ ትወዳለህን? አባታችን አብርሃም ልጁን ይስሐቅን በመሠዊያው ባቀረበ ጊዜ በሥራ የጸደቀ አልነበረምን? እምነት ከሥራው ጋር አብሮ ያደርግ እንደነበረ በሥራም እምነት እንደተፈጸመ ትመለከታለህን? መጽሐፍም አብርሃም እግዚአብሔርን አመነ ጽድቅም ሆኖ ተቈጠረለት ያለው ተፈጸመ፤ የእግዚአብሔርም ወዳጅ ተባለ፡፡» ይላል (ቊ.20‐23)፡፡ በዚህ ክፍል አብርሃም ልጁን በመሠዊያው ላይ ማቅረቡ የአብርሃም ሥራ ሆኖ ቀርቧል፤ በዚህም ሥራ የአብርሃም እምነት እንደተፈጸመ ወይም ፍጹም እንደተደረገ(ቊ.22 አ.መ.ት.) ተገልጧል፤ ከዘፍ.15፡4‐6 እንደምንረዳው ደግሞ «አብርሃም በእግዚአብሔር አመነ ጽድቅም ሆኖ ተቈጠረለት» የተባለው እግዚአብሔር ለአብርሃም ከጉልበቱ የሚወጣው እንደሚወርሰው በተናገረውና የሰማይ ከዋክብትን አሳይቶ «ዘርህም እንደዚሁ ይሆናል» ባለው ጊዜ ነው፡፡ ከዚህ በኋላ ይስሐቅን በመሠዊያ ላይ እስከሚያቀርብበት ጊዜ ድረስ ብዙ ዓመታት ተቈጥረዋል፤ በ86 ዓመቱ እስማኤልን ወልዷል(ዘፍ.16፡16)፤ ከ13 ዓመታት በኋላ በ99 ዓመቱ ራሱ አብርሃምና ልጁ እስማኤልም ተገርዘዋል(ዘፍ 17፡24‐25)፤ በ100 ዓመቱ ይስሐቅን ወልዷል(ዘፍ.21፡5)፤ ከዚያም በፍልስጥኤም ምድር ብዙ ቀን እንግዳ ሆኖ ተቀምጧል(ዘፍ.21፡34)፤ እንግዲህ ልጁ ይስሐቅን በመሠዊያ ላይ ያቀረበው ከዚህ ሁሉ በኋላ ይስሐቅ ካደገ በኋላ እንደሆነ እንረዳለን፤ በዚህ ጊዜ አብርሃም በሥራም እንደጸደቀ ተነግሮናል፤ አብርሃም በእግዚአብሔር ዘንድ የጸደቀው ግን «ከጉልበትህ የሚወጣው ይወርስሃል»፣ ዘርህ እንደዚሁ ይሆናል» የሚለው የተስፋ ቃል በተሰጠው ጊዜ ማለትም ይስሐቅ ገና ባልነበረበት ጊዜ ነው(ሮሜ 4፡18)፡፡ ያን ጊዜ በእግዚአብሔር ስላመነ ጽድቅ ሆኖ ተቈጠረለት፡፡ ከብዙ ዓመታት በኋላ ደግሞ ልጁን ይስሐቅን በመሠዊያው ባቀረበ ጊዜ በሥራም ጸደቀ፤ ይህም ማለት በሰው ዘንድ ታየ ተረጋገጠ ማለት ነው፡፡ እግዚአብሔር ግን ለአብርሃም ጽድቅን ለመቊጠር ልጁ ይስሐቅን በመሠዊያ ላይ እስኪያቀርብ ድረስ መጠበቅ አላስፈለገውም፤ አብርሃም ባመነ ጊዜ እምነቱን ጽድቅ አድርጎ ቈጥሮለታል፡፡
አብርሃም የተገረዘው እምነቱ ጽድቅ ሆኖ ከተቈጠረለት ከ13 ዓመታት በኋላ በመሆኑ መገረዙም ቢሆን በእግዚአብሔር ዘንድ ለመጽደቁ ምክንያት አልነበረም(ሮሜ4፡9‐12)፤ ነገር ግን ይህ መገረዙ «ሳይገረዝ በነበረው እምነት ያገኘው የጽድቅ ማኅተም» የሆነ ምልክት ወይም ማረጋገጫ ነበር (ሮሜ4፡11)፡፡ እንዲሁም ሕግ የተሰጠው ከ430 ዓመታት በኋላ በሙሴ ጊዜ በመሆኑ አብርሃም በዘመኑ በሕግ ሥራ ሊጸድቅ አይችልም፡፡ ስለዚህ አብርሃም የጸደቀው በሕግ ሥራ ሳይሆን በእምነት ነበር፡፡ ዛሬም ቢሆን ሰው የሚጸድቀው በሥራ ሳይሆን በእምነት እንደሆነ ለማወቅ «ለማይሠራ ኃጢአተኛውን በሚያጸድቅ ለሚያምን ሰው» እምነቱ ጽድቅ ሆኖ እንደሚቈጠርለት የተነገረውን ማስተዋል ያስፈልጋል፡፡ በተጨማሪም ጽድቅ በእምነት የመቈጠሩ ጉዳይ ለአብርሃም ብቻ ሳይሆን ለእኛም እንደሆነ መጽሐፍ ቅዱስ ሲናገር «ነገር ግን ተቈጠረለት የሚለው ቃል ስለ እርሱ ብቻ የተጻፈ አይደለም ስለእኛም ነው እንጂ፤ ስለ በደላችን አልፎ የተሰጠውን እኛን ስለማጽደቅም የተነሣውን ጌታችንን ኢየሱስን ከሙታን ባስነሳው ለምናምን ይቈጠርልን ዘንድ አለው» ይላል (ሮሜ 4፡23‐25)፡፡

“የርኅራኄ አባት የመጽናናትም ሁሉ አምላክ የሆነ የጌታችን የኢየሱስ ክርስቶስ አምላክና አባት ይባረክ።”
2ኛ ቆሮ 1፥3

👍5❤4😁1