' 📜📜📜===📜📜📜
📜 የዕለቱ ጥቅስ 📜
📜📜📜===📜📜📜
“እርሱም በጀልባዋ ላይ ወጥቶ አብሮአቸው ሆነ፤ ነፋሱም ተወ፤ እነርሱም እጅግ ተደነቁ፤”
ማርቆስ 6፥51 (አዲሱ መ.ት)
ወደ ቻናሉ ለመ🀄️ላ🀄️ል፦ @Holy_scriptures

❤3👍3
የያዕቆብ ልጆች እና በረከቶቻቸው
ክፍል - ፬
ስምዖን (ዘፍ. 49፥5-7)
ስምዖን ከልያ ለያዕቆብ የተወለደለት ሁለተኛው ልጁ ነው። ልያም እኔ እንደ ተጠላሁ እግዚአብሔር ስለ ሰማ ይህንን ደገመኝ ስትል የሁለተኛ ልጇን ስም ስምዖን ብላ ጠራችው (ዘፍ. 29፥33)፡፡ ያዕቆብም ልጆቹን ሊመርቅ በተነሳ ጊዜ ስምዖንና ሌዊ በሰኬም ሰዎች ላይ ያደረጉትን በማስታወስ በልቡ የቆየና የኖረ የምሬት ሀዘኑ ተገለጠ (ዘፍ. 34፥1-31)። በጊዜው ዲና የተባለችው የያዕቆብ ሴት ልጅ የአገሩን ሴቶች አኗኗር ለማየት ከምትኖርበትና በሰላም ከተጠበቀችበት ስፍራ ርቃ በመውጣቷ ምክንያት ያገኛት የሴኬም ሰው ወስዶ አስነወራት፡፡ ይህም ድርጊት ያዕቆብንና ልጆቹን አሳዘነ፡፡ በሀዘናቸው ላይ ግን ጨምሮ ስምዖንና ሌዊን እጅግ አስቆጣቸው:: በዚህም መካከል ሁኔታውን ለማብረድና እርቅንም ለመፍጠር በያዕቆብና በሴኬም ሽማግሌዎች በተደረገው የስምምነት ድርድር ውስጥ ዲናን ላስነወራት ለሴኬም ስው ሚስት እንድትሆን ለመስጠት የሴኬም ወንዶች ሁሉ እንዲገረዙ ተስማሙ። በስምምነቱም መሠረት የሴኬም ወንዶች ሁሉ ተገረዙ፡፡ በዚህም ሁኔታ ውስጥ እያሉና የሴኬምም ወንድ ሁሉ የግርዘት ቁስሉን ሲያስታምም ስምዖንና ሌዊ የቁጣቸውን ሰይፍ መዝዘው በሴኬም ወንዶች ላይ ዘመቱ፡፡ ገና በቁስል ህመማቸው ሲቃ ውሰጥ ያሉ የሴኬምም ሰዎች ምን እንደ መጣ እንኳ ሳያውቁ በነስምዖን የሰይፍ ስለት መውደቅ ጀመሩ (ዘፍ. 34፥25 )። ከምሬት የሚመጣ ቁጣና ከኩርፈት የሚነሳ በቀል መራራ ስለሆነ በሰይፋቸው የብዙዎችን ደም አፈሰሱ፡፡ ምን እንዳደረጉና እንዳጠፉ ያላወቁ ብዙዎች በቁጣቸው ሰይፍ ወደቁ፡፡ ምሕረትና ርኀራኄ የሌለበት ሀዘንና ቁጣ ፍሬው ሞት በመሆኑ የብዙዎች ሕይወት ጨለመ፡፡
የዚህ ድርጊታቸው ወሬ ለያዕቆብ ሲደርሰው እጅግ አሳዘነው፤ እስደነገጠውም፡፡ ከላባ ቤት ባርነት ተገላግሎ፥ እግዚአብሔርም በብዙ ባለጠግነት ባርኮት የአባቶቹንና የእርሱንም አምላክ ለማምለክ ይህቺ ያረፈባትን ሰፍራ መርጦና በዚያም መሠዊያውን ሠርቶ አምላኬ አሳረፈኝ ብሎ እፎይታውን ገና ሲጀምር ባላስበው ዱላ ያዕቆብ ተመታ፡፡ ከዚህም ድንጋጤ የተነሳ በቁጥር ብዙ የሆኑ የሴኬም ሰዎችና ሌሎችም ያጠፉናል ሲል ይህች የወደዳትን ቦታ ለቆ፥ ድንኳኑንም ነቅሎ እንዲጓዝ ተገደደ፡፡ ያለ ዕረፍት በአሳብና በሞት ሰቀቀን ውሰጥ እንዲወድቅ አደረገው፡፡ የስምዖንና የሌዊ የምሬትና የበቀል እርምጃ እጅግ መራራ ስለ ነበር ያዕቆብን ድንጉጥ እንዲሆን ዳረገው (ዘፍ. 34፥30)::
ከዚህም ከሰምዖንና ከወንድሙ የበቀል ፍሬ የተነሳ እርሱን ከነቤተሰቡ ተንከራታች እንዲሆን ስላደረጉት ያዕቆብ ስምዖንና ሌዊን የተከፈሉና የተበተኑ ሕዝብ እንዲሆኑ ያለበረከት ተዋቸው፡፡ ከእነርሱም ጋር ኅብረት አይኑረኝ በማለት ራሱን ከድርጊታቸው ታሪክ እየለየ እንዲህ በማለት ተናገር፦
“ስምዖንና ሌዊ ወንድማማች ናቸው፤ ሰይፎቻቸው የዓመፃ መሣሪያ ናቸው፤ በምክራቸው ነፍሴ አትግባ፤ ከጉባኤአቸውም ጋር ክብሬ አትተባበር፣ በቁጣቸው ሰውን ገድለዋልና፥ በገዛ ፈቃዳቸውም በሬን አስነከሰዋልና፡፡ ቁጣቸው ርጉም ይሁን፥ ጽኑ ነበርና፤ ኩርፈታቸውም ብርቱ ነበርና፤ በያዕቆብ እከፋፍላቸዋለሁ፥ እበትናቸዋለሁ (ዘፍ. 49፥5-7):: በእስራኤልም ስለ ስምዖን ሙሴም የእስራኤልን ነገድ ሁሉ በበረከት ሲባርክ ምንም ሳይናገር ቢያልፍም ለሌዊ ነገድ ግን እግዚአብሔር ምሕረት አደረገ፡፡ እንዲያውም ከእሰራኤል ነገድ ሁሉ ለራሱ ርስት አድርጎ ለያቸው፡፡ የስምዖን በሙሴ መዘለል እግዚእብሔር እንዲያው እረስቶት አይደለም፡፡ ምናልባትም ከዚህ ከሴኬም ድርጊቱ ጋር ዮሴፍም በጉድጓድ በሚጣል ጊዜ የከፋበትና እንዲገድሉትም ወንድሞቹን ያነሳሳበት ስምዖን ሳይሆን የሚቀር አይመስለኝም፡፡ የበቀልና የምሬት ሰው እንደ ሆነ የሴኬም ተግባሩ ስለሚያሳይ በወንድሙ ላይ ብዙ የጨከነበትና ሌሎቹም እንዲነሱበት ከግንባር ሆኖ የገፋፋው እርሱ ሊሆን ይችላል፡፡ የሰሙንም ስያሜ ያገኘው እናቱ ልያ ያዕቆብ ለራሔል ካለው ፍቅር የተነሳ ተጠልታ የምትኖር እንደ ሆነ ለመግለጥ ሰለ ነበር፥ የራሔልን የመጀመሪያ ልጅ ዮሴፍን ስምዖን መጥላቱና መጥፊያውን መፈለጉ አይቀርም ብሎ ማሰብ ለስምዖን ባህረ ብዙ ከመንገድ መራቅ አይሆንም፡፡
ረሀብ በከነዓን ጠንክሮ እህል ፍለጋ የያዕቆብ ልጆች ወደ ግብጽ በወረዱ ጊዜና በዮሴፍ ፊት ወንድሞቹ በቀረቡበት ወቅት የሚያስፈልጋቸውን እህል እንዲያገኙ ዮሴፍ ካደረገ በኋላ ብንያምን ይዘው እንዲመለሱ ለማድረግ ከመካከላቸው አንዱን በእስር ቤት ለማቆየት ዮሴፍ ሲወስን በእስር እንዲቆይ የበየነበት በስምዖን ላይ ነበር (ዘፍ. 42፥24-25)፡፡ ከወንድሞቹ ተለይቶ መኖርንና ከአባቱም ቤትና ከወገኑም መለየትን ለአጭር ጊዜም ቢሆን እንዲቀምስ ስምዖንን ያስቀረው እንደሆነ መገመት ይቻላል፡፡
ይቀጥላል...
ምንጭ፦ አበራ ጌታሁን (ዶ/ር)፤ የያዕቆብ ልጆች እና በረከቶቻቸው፤ ገጽ 13-15

👍4❤2
' 📜📜📜===📜📜📜
📜 የዕለቱ ጥቅስ 📜
📜📜📜===📜📜📜
“ሌላው በጣለው መሠረት ላይ እንዳልገነባ ብዬ፣ ክርስቶስ ባልተጠራበት ስፍራ ወንጌልን መስበክ የዘወትር ምኞቴ ነበር።”
ሮሜ 15፥20 (አዲሱ መ.ት)

👍5❤2
የቀጠለ. . .
የኢየሱስ ክርስቶስ ክብር የሚበራበት ወንጌል
ወንጌል የኢየሱስን ማንነት በተቀዳሚነት ይናገራል ስንል ምን ማለታችን ነው?
ኢሳይያስ በብሉይ ኪዳን ከጌታችን ልደት በፊት 700 ዓመተ ዓለም ገደማ የተናገረው ከአዲስ ኪዳን በፊት የተነገረ ወንጌል ነበር።
“ሕፃን ተወልዶልናልና፥ ወንድ ልጅም ተሰጥቶናልና፤ አለቅነትም በጫንቃው ላይ ይሆናል፤ ስሙም ድንቅ መካር፥ ኃያል አምላክ፥ የዘላለም አባት፥ የሰላም አለቃ ተብሎ ይጠራል። ከዛሬ ጀምሮ እስከ ዘላለም ድረስ በፍርድና በጽድቅ ያጸናውና ይደግፈው ዘንድ በዳዊት ዙፋንና በመንግሥቱ ላይ አለቅነቱ ይበዛል፥ ለሰላሙም ፍፃሜ የለውም። የእግዚአብሔር ቅንዓት ይህን ያደርጋል” (ኢሳ. 9፥6-7)
ኢሳይያስ ትንቢታዊ ወንጌሉን ከጌታችን ልደት በፊት ሲያበስር የመልዕክቱ ትኩረት ያለው ምን ላይ እንደሆነ ልብ ማለት አለብን። “ሕፃን ተወልዶልናል”፥ “ወንድ ልጅም ተሰጥቶናል” እያለ እንደሚናገር ልብ ማለት አለብን። ኢሳይያስ የተሰጠንን ወንድ ልጅ የገለጠው፦ አለቅነት በጫንቃው ላይ የሆነ፣ ስሙ ድንቅ መካር የተባለ፣ ኃይል አምላክ የሆነ፣ የዘላለም አባት የሚባል፣ የሰላም አለቃ ተብሎ የሚጠራ፣ በዳዊት ዙፋንና በመንግሥቱ ላይ አለቅነቱ የሚበዛ፣ለሰላሙ ፍጻሜ የሌለው ልጅ ነው። ኢሳይያስ የተሰጠንን ወንድ ልጅ እንዲህ አድርጎ ሲያሳየን መግለጫዎቹ በሙሉ ወደ ማንነቱ እንድንመለከት የሚጋብዙን ናቸው። ተወልዶልናል፥ ተሰጥቶናል የሚሉት ቃላቶች የሚያመለክቱት ልጁን ከነሙሉ ማንነቱ ለእኛ እግዚአብሔር እንደሰጠን የሚያሳይ ነው። እግዚአብሔር የሰጠን የተወለደውን ልጁን ነው። ሰው ሆኖ እንዲወለድ የተደረገውን ልጁን ነው የሰጠን። በሥጋ ከዳዊት ዘር የተወለደው ለእኛ የተሰጠን ኢየሱስ ቃልም ሥጋ ሆነ በተባለበት ጊዜ ለእኛ ከተሰጠበት ሁኔታ ላይለየን ነው የተሰጠን። ወንድ ልጅ ተሰጥቶናል፥ ቃልም ሥጋ ሆኖ በእኛ መካከል ያደረበትን፥ ለዘላለም ገንዘቡ ባደረገው በሥጋ ከዳዊት ዘር ሲወለድ ሰው የሆነበትን፥ ከድንግል ማርያም በነሳው ማንነቱ ነው የተሰጠን። ይህ እውነት የዛሬ ሁለት ሺህ ዓመት ያለውን ልደቱን ብቻ እንድናስብ የሚያደርግ አይደለም። ለዘላለም የእኛ እንዲሆን ከእኛ ጋር በተጋራው ሥጋ፥ ከእኛ ጋር በነገር ሁሉ አንድ በሆነበት ሥጋ፥ ፍጹም አምላክነቱን ሳያጣ፥ ደግሞም ከእኛ ጋር አንድ የሆነበትንም ሳያጎድል፥ በነገር ሁሉ እኛን የመሰለበትን የሰው ልጅነቱን ጠብቆ፥ የምናመልከውና የምንሰግድለት መለኮትነቱንም ጠብቆ የተሰጠንን ጌታ ነው ሕጻን ተወልዶልናል የሚለው። ይህ የተሰጠን ወንድ ልጅ የሚታየውንና የማይታየውን ዓለምና በውስጡ ያሉትንም ፍጥረታት ሁሉ ካለመኖር ወደ መኖር ያመጣቸው ነው። ይህ የተሰጠን ወንድ ልጅ ከድንግል ማርያም ሲወለድ በነሳው ሥጋ ከእኛ ጋር በነገር ሁሉ አንድ ስለሆነ ሞታችንን የሞተልን የማንነሳውን ትንሣኤ በራሱ ሕይወትና ኃይል ያስነሳን ጌታ ነው።
አምላካችንና ፈጣሪያችን የሆነው የእግዚአብሒር ልጅ ለእኛ በነገር ሁሉ ከእኛ ጋር አንድ ሆኖ የእኛ ሆኖልናል።እንዲህ የመሰለውን ታላቅ ዜና ነው አዲስ ኪዳን ወንጌል የሚለው። መጥምቁ ዮሐንስን መወለድ የምሥራች መልእኩ ገብርኤል ያበሰረው ለአባቱ ዘካርያስ ነበር። የጌታችንን መወለድ ግን መልአኩ ሲያበስር ለእረኞች ነበር። መልአኩ ያለው በሉቃስ ወንጌል 2፥10-12 ላይ ያላቸው “… እነሆ፥ ለሕዝቡ ሁሉ የሚሆን ታላቅ ደስታ የምሥራች እነግራችኋለሁና አትፍሩ፤ ዛሬ በዳዊት ከተማ መድኃኒት እርሱም ክርስቶስ ጌታ የሆነ ተወልዶላችኋልና። ይህም ምልክት ይሆንላችኋል፤ ሕፃን ተጠቅልሎ በግርግምም ተኝቶ ታገኛላችሁ” ነበር ያላቸው። የኢየሱስ ክርስቶስ በዳዊት ከተማ መወለድ ለሕዝብ ሁሉ የሚሆን ታላቅ ደስታ የሚያመጣ የምሥራች ነው።
ጌታችን ሰው ሆኖ መወለዱ ለሰው ልጆች የተሰጠበትን ጥልቀትና ድምቀት የያዘ ትልቅ መንፈሳዊ ምስጢር ነው። ይህ የክርስትና ሕይወትና መሠረት የቆመበት ትልቅ መንፈሳዊ ምስጢር ነው። ይህንን ምስጢር በኢየሱስ በማመን ለሚገኘው ሕይወትና መዳን ሁሉ ዋና ምክንያትና መሠረት የሆነ እውነት ነው።
ይቀጥላል. . .
ምንጭ፦ sermons.logos.com

👍7❤1
' 📜📜📜===📜📜📜
📜 የዕለቱ ጥቅስ 📜
📜📜📜===📜📜📜
“እንደሚታዘዙ ልጆች ባለማወቃችሁ አስቀድሞ የኖራችሁበትን ምኞት አትከተሉ።”
1ኛ ጴጥሮስ 1፥14

👍2❤1
#ከተማ_ወይም_ቦታ_በቅዱሳት_መጻሕፍት
#ቤርሳቤህ፤
ቤርሳቤህ ማለት ሰባት የውሃ ጉድጓድ ወይም የመሐላ የውሃ ጉድጓድ ማለት ሊሆን ይችላል። ከኬብሮን በስተደቡብ በኩል አርባ ኪሎ ሜትር ርቆ የሚገኝ ከተማ። ለመጀመሪያ ጊዜ በአብርሃም ተሰየመ፤ ዘፍ. 21፥30:31። የይስሐቅም የውሃ ጕድጓድ ሳቤህ ከተባለ በኋላ ቤርሳቤህ ተብሏል፤ ዘፍ. 26፥33። ግን ሁሉም አንድ ቦታ ይመስላል። ቤርሳቤህ የእስራኤል ደቡብ ዋና ከተማ ስለነበረ፥ የእስራኤል ምድር ብዙ ጊዜ «ከዳን እስከ ቤርሳቤህ» እየተባለ ተጠቅሷል፤ መሳ 20፥1 2ኛ ዜና 30፥5። አብርሃም፥ ይስሐቅና ያዕቆብ በዚያ ተቀመጡ፤ ዘፍ. 22፥19፤ 26፥23፤ 46፥1። ኤልያስ በዚህ በኩል ወደ ደብረ ሲና ሄደ፤ 1ነገ. 19፥3። ይህ ቦታ ዛሬ ትልቅ ከተማ ነው።
ምንጭ፦ የመጽሐፍ ቅዱስ መዝገበ ቃላት፤ ገጽ 110

👍5
' 📜📜📜===📜📜📜
📜 የዕለቱ ጥቅስ 📜
📜📜📜===📜📜📜
“ምድሪቱም ሴቲቱን ረዳቻት፥ ምድሪቱም አፍዋን ከፍታ ዘንዶው ከአፉ ያፈሰሰውን ወንዝ ዋጠችው።”
ራእይ 12፥16

👍3❤1
Yetwilid inkifat 2.pdf
2.1 MB
👉ርዕስ፦ የትውልድ የእንቅፋት ድንጋዮች
✍️ጸሐፊ፦ ደረጀ ሙላት
🗓የታተመበት ዓመት፦ 2006 ዓ.ም
📑የገጽ ብዛት፦ 163
🔐ከዶ/ር ሔኖክ ገ/ሕይወት ትምህርት በመነሳት የተጻፈ
ወደ ቻናሉ ለመ🀄️ላ🀄️ል፦ @Holy_scriptures
✍️ጸሐፊ፦ ደረጀ ሙላት
🗓የታተመበት ዓመት፦ 2006 ዓ.ም
📑የገጽ ብዛት፦ 163
🔐ከዶ/ር ሔኖክ ገ/ሕይወት ትምህርት በመነሳት የተጻፈ
ወደ ቻናሉ ለመ🀄️ላ🀄️ል፦ @Holy_scriptures
👍5
' 📜📜📜===📜📜📜
📜 የዕለቱ ጥቅስ 📜
📜📜📜===📜📜📜
“ነገር ግን እውነትን በፍቅር እየያዝን በነገር ሁሉ ወደ እርሱ ራስ ወደሚሆን ወደ ክርስቶስ እንደግ፤”
ኤፌሶን 4፥15

👍6❤3
#የእግዚአብሔር_ቃል_ምን_ይላል?
ቲቶ 3
¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯
¹-² ለገዦችና ለባለ ሥልጣኖች የሚገዙና የሚታዘዙ፥ ለበጎ ሥራ ሁሉ የተዘጋጁ፥ ማንንም የማይሰድቡ፥ የማይከራከሩ፥ ገሮች፥ ለሰው ሁሉ የዋህነትን ሁሉ የሚያሳዩ እንዲሆኑ ኣሳስባቸው።
³ እኛ ደግሞ አስቀድመን የማናስተውል ነበርንና፤ የማንታዘዝ፥ የምንስት፥ ለምኞትና ለልዩ ልዩ ተድላ እንደ ባሪያዎች የምንገዛ፥ በክፋትና በምቀኝነት የምንኖር፥ የምንጣላ፥ እርስ በርሳችን የምንጠላላ ነበርን።
⁴ ነገር ግን የመድኃኒታችን የእግዚአብሔር ቸርነትና ሰውን መውደዱ በተገለጠ ጊዜ፥
⁵ እንደ ምሕረቱ መጠን ለአዲስ ልደት በሚሆነው መታጠብና በመንፈስ ቅዱስ በመታደስ አዳነን እንጂ፥ እኛ ስላደረግነው በጽድቅ ስለ ነበረው ሥራ አይደለም፤
⁶-⁷ ያን መንፈስም፥ በጸጋው ጸድቀን በዘላለም ሕይወት ተስፋ ወራሾች እንድንሆን፥ በመድኃኒታችን በኢየሱስ ክርስቶስ በእኛ ላይ አትርፎ አፈሰሰው።
⁸ ቃሉ የታመነ ነው። እግዚአብሔርንም የሚያምኑት በመልካም ሥራ በጥንቃቄ እንዲጸኑ፥ እነዚህን አስረግጠህ እንድትናገር እፈቅዳለሁ። ይህ መልካምና ለሰዎች የሚጠቅም ነው፤
⁹ ነገር ግን ሞኝነት ካለው ምርመራና ከትውልዶች ታሪክ ከክርክርም ስለ ሕግም ከሚሆን ጠብ ራቅ፤ የማይጠቅሙና ከንቱዎች ናቸውና፤
¹⁰-¹¹ መለያየትን የሚያነሣ ሰው ጠማማ እንዲሆን በራሱም ላይ ፈርዶ ኃጢአትን እንዲያደርግ አውቀህ፥ አንድ ጊዜ ሁለት ጊዜም ከገሠጽኸው በኋላ እንዲህ ከሚመስል ሰው ራቅ።
¹² አርጢሞንን ወይም ቲኪቆስን ወደ አንተ ስልክ፥ ወደ ኒቆጵልዮን ወደ እኔ እንድትመጣ ትጋ፤ በዚያ ልከርም ቈርጬአለሁና።
¹³ ሕግ አዋቂውን ዜማስንና አጵሎስን ምንም እንዳይጎድልባቸው በጉዞአቸው ተግተህ እርዳ።
¹⁴ ከወገናችንም ያሉት ደግሞ ፍሬ ቢሶች ሆነው እንዳይቀሩ፥ የግድ ስለሚያስፈልገው ነገር በመልካም ሥራ እንዲጸኑ ይማሩ።
¹⁵ ከእኔ ጋር ያሉት ሁሉ ሰላምታ ያቀርቡልሃል። በእምነት ለሚወዱን ሰላምታ አቅርብልን። ጸጋ ከሁላችሁ ጋር ይሁን፤ አሜን።

❤7👍2🔥1
' 📜📜📜===📜📜📜
📜 የዕለቱ ጥቅስ 📜
📜📜📜===📜📜📜
“ሕግ አዋቂውን ዜማስንና አጵሎስን ምንም እንዳይጎድልባቸው በጉዞአቸው ተግተህ እርዳ።”
ቲቶ 3፥13

❤4👍3
#እራሳችንን_እንመርምር
በእግዚአብሔር ፊት ታላቅ መሆን የአንድ ጤናማ አማኝ ፍላጎት ነው። ጥያቄው ግን ይህ ጥማት ያለን ሰዎች በምን ተሞልተን እንገኛል? የምንሞላበትን ነገር መምረጥ የሚያስፈልግ አይመስላችሁም?
“በጌታ ፊት ታላቅ ይሆናልና፥ የወይን ጠጅና የሚያሰክር መጠጥ አይጠጣም፤ ገናም በእናቱ ማኅፀን ሳለ መንፈስ ቅዱስ ይሞላበታል፤”
ሉቃስ 1፥15
“መንፈስ ይሙላባችሁ እንጂ በወይን ጠጅ አትስከሩ ይህ ማባከን ነውና፤”
ኤፌሶን 5፥18

❤4👍4
' 📜📜📜===📜📜📜
📜 የዕለቱ ጥቅስ 📜
📜📜📜===📜📜📜
“በዚያም ጊዜ እስራኤል ይህን መዝሙር ዘመረ። አንተ ምንጭ ሆይ፥ ፍለቅ፤ እናንተ ዘምሩለት፤”
ዘኍልቁ 21፥17

👍6❤5
ቅዱሳት መጻሕፍት
#የሮሜ_መልእክት_ጥናት እግዚአብሔር የሚፈርደው በትክክል ነው (9፥14-18) 14–16 አንዳንዶች እግዚአብሔር የሚፈርደው በትክክል አይደለም ብለው ያስባሉ። እንዲህ በማለትም ይጠይቃሉ፥ «እግዚአብሔር ያዕቆብን የወደደውና ኤላውን የጠላው ለምንድን ነው? በዚህ እግዚአብሔር ፍርድ አላጓደለምን?» ስለ እግዚአብሔር እንዲህ የመሰሉ አሳቦች ሊኖሩን አይገባም። በቁ. 15 ጳውሎስ እግዚአብሔር በዘጸ. 33፥19…
#የሮሜ_መልእክት_ጥናት
የቀጠለ...
እግዚአብሔር የሚፈርደው በትክክል ነው (9፥14-18)
በሌላ በኩል ምሕረት ማንም ሊያገኘው የሚገባ ነገር አይደለም። ይህ ከሆነ ምሕረት ሊሆን አይችልም። ምሕረት በተፈጥሮው የማይገባው ሰው የሚቀበለው ነው። ስለዚህ ምሕረት አልተቀበልኩም በማለት ማንም ሊያጉረመርም አይገባም። ምክንያቱም ማንም ሰው ምሕረትን ለመቀበል የበቃ አይደለም። እግዚአብሔርን ለምን ለእከሌ ምሕረት ሳታሳየው ቀረህ ብሎ የሚወቅሰው የለም። እግዚአብሔር ግን ለአንዳንድ ሰዎች ምሕረት ለማሳየት ቢወስን እዚህ ላይ ያለው ስሕተት ምንድን ነው? ይህን በማድረጉ ትክክለኛ አይደለም ማለት ነውን? በጭራሽ አይደለም።
ስለዚህ እግዚአብሔር ፍትሕን (ቅጣትን) ለሁሉም እንደሚሰጥ እናያለን። ነገር ግን ለአንዳንዶች ከዘላለማዊ ፈቃዱ የተነሣ ምሕረት ያሳያቸዋል። ክርስቶስ ወደዓለም ከመጣበት ጊዜ ጀምሮ በእርሱ ለሚያምኑበት ሁሉ እግዚአብሔር ምሕረቱን አሳይቶአል። ይህም ሲባል ለእኛ የሚገባንን ትክክለኛ ቅጣት ከእኛ አላራቀውም፤ ይልቁንም በእኛ ምትክ ለክርስቶስ ሰጥቶታል። የእግዚአብሔርን ፍትሕና ምሕረት በአንድነት ስለሆነም ልናያቸው እንችላለን። ደኅንነትን የሚቀበሉ እግዚአብሔርን ሊያመሰግኑ ይገባቸዋል። ምክንያቱም ደኅንነታቸው የተገኘው ከእግዚአብሔር ምሕረትና ጸጋ የተነሣ ነው። ዘላለማዊ ቅጣትን የሚቀበሉ ደግሞ በኃጢአታቸው ምክንያት ይቀበላሉ። ኃላፊነቱን ራሳቸው ይወስዳሉ፤ የሚገባቸውን ሙሉ ቅጣት ይቀበላሉ።
ንስሓ በመግባት ኢየሱስን ጌታና አዳኝ አድርገው ለሚቀበሉት እግዚአብሔር ምሕረቱን ማሳየት የሚፈልግ ሲሆን፣ ንስሓ መግባትን ባለመቀበል በኀጢአት ለመቀጠል የሚፈልጉትንና በክርስቶስ ያለውን ድነት የሚያጣጥሉትን ደግሞ ልባቸውን ያደነድናል። ይህም ለማንም ሰው ወይም ሕዝብ ሲባል የማይለወጥ ቋሚ መለኮታዊ ዐላማ ነው (ከ2፥4-11 ጋር ያነጻጽሩ)::
የፈርዖን ልብ መደንደን አንዳንዴ ከእግዚአብሔር እንደሆነ (ዘፀ 4፥21፤ 7፥3:13፤ 9፥12፤ 10፥1፤ 11፥10፤ 14፥17) በሌላ ጊዜ ደግሞ ከራሱ ከፈርዖን እንደነበር ተመልክቷል (ዘፀ 7፥22-23፤ 8፥15 ፡ 32 ) ፡፡ ከልቡ ትዕቢት የተነሣ ከእግዚአብሔር ጋር የተጣላው ፈርዖን ተገቢውን የእግዚአብሔርን ፍርድ ተቀበለ፡፡ ለእግዚአብሔር
ፈቃድም እምቢተኛ እየሆነ በመምጣቱም እግዚአብሔር የበለጠ ልቡን አደነደነው (ዘፀ 7፥3)። ስለዚህ እግዚአብሔር የፈርዖንን ልብ ያደነደነው በዘፈቀደ አይደለም፤ እግዚአብሔር ጽድቅ በሆነው መርሑ መሠረት በእርሱ ላይ የሚያምጹትን ሁሉ ልባቸውን ያደነድናል (ከ1፥12-32)፡፡
ምንጭ፦ የአዲስ ኪዳን ማብራሪያ፤ ገጽ 372-373፣ ምሉእ ሕይወት፤ ገጽ 1757

❤3👍1
ሐዋርያው ቅዱስ ጳውሎስ ወደ ኢየሩሳሌም ሄዶ ደቀመዛሙርት አልቀበል ሲሉት እንዲቀበሉት ያደረገ እና በአንጾኪያ ቤተክርስቲያን እንዲያገለግል ከጠርሴስ ያስመጣው ማን ነው?
Anonymous Quiz
5%
ሀ. ጴጥሮስ
7%
ለ. ያዕቆብ
71%
ሐ. በርናባስ
8%
መ. ሲላላ
3%
ሠ. ዮሐንስ
7%
ረ. ፊልጶስ
👍7👏1
' 📜📜📜===📜📜📜
📜 የዕለቱ ጥቅስ 📜
📜📜📜===📜📜📜
“በዚያም ዘመን በእስራኤል ዘንድ ንጉሥ አልነበረም፤ ሰው ሁሉ በፊቱ መልካም መስሎ የታየውን ያደርግ ነበር።”
መሳፍንት 21፥25
ወደ ቻናሉ ለመ🀄️ላ🀄️ል፦ @Holy_scriptures
📜 የዕለቱ ጥቅስ 📜
📜📜📜===📜📜📜
“በዚያም ዘመን በእስራኤል ዘንድ ንጉሥ አልነበረም፤ ሰው ሁሉ በፊቱ መልካም መስሎ የታየውን ያደርግ ነበር።”
መሳፍንት 21፥25
ወደ ቻናሉ ለመ🀄️ላ🀄️ል፦ @Holy_scriptures
❤4👍3
መዳን በሥራ ካልሆነ ለመልካም ሥራ ከጌታ የምናገኘው ምንድነው?
ክፍል-1
ሰው በእምነት ብቻ ሳይሆን በሥራም እንደሚጸድቅ በያዕቆብ ምዕራፍ 2 ውስጥ መገለጹ ሰው በእግዚአብሔር ዘንድ ስለመጽደቁ ሳይሆን አንድ ሰው መጽደቁ በሰው ዘንድ ስለመታየቱ ወይም ስለመረጋገጡ የሚገልጽ ነው፡፡ በመጽሐፍ ቅዱስ መሠረት ሰው የሚድነው ወይም የሚጸድቀው በእምነት እንጂ በሥራ እንዳልሆነ እርግጥ ነው፤ ይህ በእምነት የመጽደቅ ጉዳይም በሰው ዘንድ ሳይሆን በእግዚአብሔር ዘንድ የሚታየው ነው፡፡
በሮሜ 4፡1‐8 የምናገኘው የእግዚአብሔር ቃል ይህን የሚያረጋግጥ ነው፤ በቊ.1 ላይ «በሥጋ አባታችን የሆነ አብርሃም ምን አገኘ እንላለን? አብርሃም በሥራ ጸድቆ ቢሆን የሚመካበት አለውና፤ ነገር ግን በእግዚአብሔር ዘንድ አይደለም» ይላል፤ «በእግዚአብሔር ዘንድ አይደለም» የሚለው ይህ ቃል በእግዚአብሔር ዘንድ በሥራ መጽደቅ እንደሌለ የሚገልጽ ነው፡፡
በዚህ ክፍል ሰው ያለ ሥራ በእምነት እንደሚጸድቅ ለማሳየት ሁለት ሰዎች በምሳሌነት ተጠቅሰዋል፤ እነርሱም አብርሃምና ዳዊት ናቸው፡፡ እነዚህ ሁለት ሰዎች በአንድነት መጠቀሳቸው በመጽሐፍ ቅዱስ የተለመደ ሲሆን (ማቴ.1፡1፤ የሐ.ሥ.13፡26‐36) ይህንንም ታላቅ ርእሰ ጉዳይ ለማብራራት አብረው መጠቀሳቸው ወሳኝ ነው፡፡ አብርሃም የነበረው ሕግ ከመሰጠቱ በፊት ሲሆን ዳዊት ደግሞ በሕጉ ዘመን የነበረ ሰው ነው፤ ከሁለቱም ሰዎች አንጻር ሲታይ ግን በእግዚአብሔር ዘንድ ጽድቅ የሚቈጠረው በሥራ ሳይሆን በእምነት እንደሆነ ተብራርቷል፡፡
በቊ.3 ላይ አብርሃምን በተመለከተ ሲገልጽ «መጽሐፍስ ምን አለ? አብርሃም እግዚአብሔርን አመነ ጽድቅም ሆኖ ተቈጠረለት፤ ለሚሠራ ደመወዝ እንደ ዕዳ ነው እንጂ እንደ ጸጋ አይቈጠርለትም፤ ነገር ግን ለማይሠራ ኃጢአተኛውን በሚያጸድቅ ለሚያምን ሰው እምነቱ ጽድቅ ሆኖ ይቈጠርለታል» ይላል፡፡ በዚህም ቃል ውስጥ አብርሃም ጽድቅን ያገኘው እግዚአብሔርን ስላመነ ተቈጥሮለት እንጂ ጽድቅ ሠርቶ እንዳልሆነ እንገነዘባለን፡፡ ይህም ለሚያምን ሰው ሁሉ እግዚአብሔር የሚያደርገው መሆኑ ተገልጿል፡፡ በመቀጠል ደግሞ ዳዊት ይህን ጉዳይ በተመለከተ የተናገረው ተጠቅሷል፡፡ ይኸውም «እንደዚህም ደግሞ እግዚአብሔር ያለ ሥራ ጽድቅን ስለሚቈጥርለት ሰው ብፅዕና ይናገራል እንዲህ ሲል፤ ‘ዓመፃቸው የተሰረየላቸው ኃጢአታቸውም የተከደነላቸው ብፁዓን ናቸው፤ ጌታ ኃጢአቱን የማይቈጥርበት ሰው ብፁዕ ነው’»(ቊ.6‐8)፤ በአብርሃም ሕይወት እንዳየነው እግዚአብሔር ሊቈጠርልን የማይገባውን ጽድቅ በእምነት ሲቈጥርልን እናያለን፤ በዚህ ዳዊት በተናገረው ቃል ውስጥ ደግሞ እግዚአብሔር ሊቈጥርብን የሚገባውን ኃጢአት ባለመቊጠር ጸጋውን ሲያሳይ እንመለከታለን፡፡ ይህም «እግዚአብሔር ያለ ሥራ ጽድቅን ስለሚቈጥርለት ሰው ብፅዕና» የተነገረ መሆኑ ተገልጿል፡፡ ስለዚህ በሮሜ 4 ውስጥ የተሰጠው ትምህርት ሰው በእግዚአብሔር ዘንድ የሚጸድቀው ያለ ሥራ በእምነት መሆኑን የሚያሳይ ነው፤ ይህ እምነት በሥራ ሊገለጥ የሚችል እውነተኛ መሆኑን እግዚአብሔር ማወቅ ይችላልና፡፡
በያዕቆብ ምዕራፍ 2 ውስጥ የምናገኘው ትምህርት ግን ጽድቅ ወይም መዳን በሰው ዘንድ የሚታየው ወይም የሚረጋገጠው በእምነት ብቻ ሳይሆን በሥራም እንደሆነ የሚገልጽ ነው፡፡ በሰው ዘንድ የአንድ ሰው እምነት እውነተኛ እምነት መሆኑ ሊታይ የሚችለው በሥራ ነው፤ በቊ.14 ላይ «ወንድሞች ሆይ እምነት አለኝ የሚል ሥራ ግን የሌለው ሰው ቢኖር ምን ይጠቅመዋል፤ እምነቱስ ሊያድነው ይችላልን?» በማለት ያዕቆብ ጥያቄ ያነሳል፤ እዚህ ላይ «እምነት አለኝ» የሚለው ያ ሰው ራሱ ነው፡፡
ይቀጥላል...
ምንጭ፦ 1bible.page

👍9❤1