' 📜📜📜===📜📜📜
📜 የዕለቱ ጥቅስ 📜
📜📜📜===📜📜📜
“በገዛ ሥጋው የሚዘራ ከሥጋ መበስበስን ያጭዳልና፥ በመንፈስ ግን የሚዘራው ከመንፈስ የዘላለምን ሕይወት ያጭዳል።”
ገላትያ 6፥8
ወደ ቻናሉ ለመ🀄️ላ🀄️ል፦ @Holy_scriptures

❤4👍2
#እራሳችንን_እንመርምር
እግዚአብሔር ሰዎችን ያታልላልን? ሰው ምን ቢያደርግ እግዚአብሔር እንዲህ ያስብበታል? ለምን?
“እግዚአብሔርም፦ ወጥቶ በሬማት ዘገለዓድ ይወድቅ ዘንድ የእስራኤልን ንጉሥ አክዓብን የሚያታልል ማን ነው? አለ። አንዱም እንደዚህ፥ ሌላውም እንደዚያ ያለ ነገር ተናገረ።”
2 ዜና 18፥19

❤3👍1
' 📜📜📜===📜📜📜
📜 የዕለቱ ጥቅስ 📜
📜📜📜===📜📜📜
“ሐማም ለሚስቱ ለዞሳራና ለወዳጆቹ ሁሉ ያገኘውን ሁሉ አጫወታቸው። ጥበበኞቹና ሚስቱ ዞሳራም። በፊቱ መውደቅ የጀመርህለት መርዶክዮስ ከአይሁድ ወገን የሆነ እንደ ሆነ በፊቱ ፈጽሞ ትወድቃለህ እንጂ አታሸንፈውም አሉት።”
አስቴር 6፥13

👍3❤1
' 📜📜📜===📜📜📜
📜 የዕለቱ ጥቅስ 📜
📜📜📜===📜📜📜
“ፍቅራችሁ በጥልቅ እውቀትና በማስተዋል ሁሉ በዝቶ እንዲትረፈረፍ እጸልያለሁ።”
ፊልጵስዩስ 1፥9 (አዲሱ መ.ት)

❤2👍2
#ከተማ_ወይም_ቦታ_በቅዱሳት_መጻሕፍት
#አርሞንዔም፤ በሶርያ፥ በሊባኖስና በእስራኤል ድንበር ላይ ያለው ተራራ ከባሕር ጠለል እስከ 2777 ሜትር ከፍ ስለሚል በአቅራቢያው ካሉት ተራራዎች ከፍታ አለው። የአርሞንዔም በረዶ እየሟሟ ወደ ዮርዳኖስና ወደ ገሊላ ባሕር ይፈሳል፤ ዘዳ. 4፥48፤ መዝ. 133፥3። ክርስቶስ ክብሩን የገለጠው በዚህ ተራራ ሳይሆን አልቀረም፤ መዝ. 89፥12፤ ማቴ. 17፥1-8። አርሞንዔም ሢርዮን፥ ሳኔር፥ ኤርሞን ተብሎ ይጠራል፤ ዘዳ. 3፥8:9፤ መኃልይ 4፥8።
ምንጭ፦ የመጽሐፍ ቅዱስ መዝገበ ቃላት፤ ገጽ 147

👍7
' 📜📜📜===📜📜📜
📜 የዕለቱ ጥቅስ 📜
📜📜📜===📜📜📜
“በይሁዳም ሁሉና በገሊላ በሰማርያም የነበሩት አብያተ ክርስቲያናት በሰላም ኖሩ ታነጹም፤ በእግዚአብሔርም ፍርሃትና በመንፈስ ቅዱስ መጽናናት እየሄዱ ይበዙ ነበር።”
ሐዋርያት 9፥31

❤5👍2
ከእምነት ወደ እምነት-1.pdf
445.4 KB
👉ርዕስ፦ ከእምነት ወደ እምነት
✍️ጸሐፊ፦ ዋችማን ኒ
🗣ትርጉም፦ ዘካርያስ ጥላሁን
✏️አርትኦት፦ ጳውሎስ ፈቃዱ
🖨አሳታሚ፦ ራዕይ አሳታሚ
📄የገጽ ብዛት፦ 112
ወደ ቻናሉ ለመ🀄️ላ🀄️ል፦ @Holy_scriptures
✍️ጸሐፊ፦ ዋችማን ኒ
🗣ትርጉም፦ ዘካርያስ ጥላሁን
✏️አርትኦት፦ ጳውሎስ ፈቃዱ
🖨አሳታሚ፦ ራዕይ አሳታሚ
📄የገጽ ብዛት፦ 112
ወደ ቻናሉ ለመ🀄️ላ🀄️ል፦ @Holy_scriptures
👍3❤2
' 📜📜📜===📜📜📜
📜 የዕለቱ ጥቅስ 📜
📜📜📜===📜📜📜
“በድነታችሁ እንድታድጉ፣ አዲስ እንደ ተወለዱ ሕፃናት ንጹሑን መንፈሳዊ ወተት ተመኙ፤”
1ኛ ጴጥሮስ 2፥2 (አዲሱ መ.ት)

❤6👍1
የቀጠለ. . .
የኢየሱስ ክርስቶስ ክብር የሚበራበት ወንጌል
ጳውሎስ ሐዋርያ የሆነው የእግዚአብሔር ነው ለተባለውና ስለ ኢየሱስ ክርስቶስ ለሚናገረው ወንጌል አገልጋይ እንዲሆን በመለየት እንደሆነ ይናገራል። ጳውሎስ ባለቤቱ እግዚአብሔር ነው ለሚለው ወንጌል በመለየቱ ራሱን የክርስቶስ ኢየሱስ ባሪያ እንደሆነ ይናገራል። ጳውሎስ የኢየሱስ ባሪያ የሆነው ስለ ኢየሱስ የሚናገረውን ወንጌል እንዲያገለግል ስለ ተመረጠና ስለተለየ ነው። ሕይወቱ ለወንጌል እንደ ባሪያ የተሸጠ ነው። የኢየሱስ ወንጌል ታላላቅ ሐዋርያትን ባሪያ ያደረገ፥ ለሌላ ለምንም እንዳይውሉና እዳይሆኑ አድርጎ የሚለው ነው። የኢየሱስ ወንጌል ስለ ኢየሱስ ብቻ ስለሚናገር ለእግዚአብሔር ወንጌል የተለዩትም “በመካከላችሁ ሳለሁ ከኢየሱስ ክርስቶስ በቀር እርሱም እንደተሰቀለ ሌላ ነገር እንዳላውቅ ቆርጬ ነበርና” እያሉ ባሪያ ካሳዳሪው እንደማይለው እነርሱም ከኢየሱስ ውጪ ሌላ ስብከትም ሆነ ትምሕርት የላቸውም (1ኛ ቆሮ. 2፥2)። ወንጌል ስለ ኢየሱስ ብቻ የሆነ የገባቸው አገልጋዮች የኢየሱስ ክርስቶስ ብቻ ባሪያዎች ናቸው።
የወንጌል ተቀዳሚ መልእክት ምንድር ነው?
ጳውሎስ ከላይ በሮሜ ላይ በተናገረው እውነት ውስጥ የወንጌልን ምንነት በሚገባ ያሳየናል። ወንጌል በመጀመሪያ ደረጃ፥ በተቀዳሚነትና በዋናናነት የሚናገረው ስለ ኢየሱስ ክርስቶስ ማንነት እንደሆነ እናያለን። በጌታ በኢየሱስ ማንነት ላይ እደግማለሁ ማንነት ላይ ያላተኮረ ወንጌል፣ ወንጌል አይደለም። ዛሬ ብዙ መንፈሳዊ ኪሳራ ያመጣብን፥ እውነተኛ መንፈሳዊ ለውጥና የደቀ መዝሙር ሕይወት እንዳይኖር እንቅፋት የሆነብን ነገር ሊገጥመን የቻለው ኢየሱስ ተኮር የሆነ ወንጌል ስለ ጠፋ ነው። የደቀ መዝሙር ሕይወት ጌታን የመከተል ሕይወት ነው። ጌታን የምንከተለው ልንከተለው የሚገባ ጌታ መሆኑን ስናውቅ ነው። አገልጋዮችን የኢየሱስ ክርስቶስ ባሪያ ባላደረገ ወንጌል ኢየሱስ ክርስቶስን ሊከተሉ የሚችሉ ደቀ መዛሙርትን ማፍራት አያስችልም። ጌታ ያስተማረንን ሳንጠብቅ ከእርሱ የተማርነውን የሚጠብቁ ሰዎች እንዴት ማፍራት እንችላለን? ወንጌል ጳውሎስ ባሪያ ስለሆነለት ስለ ኢየሱስ ክርስቶስ የሚናገር ወንጌል ነው።
ይህ ሁሉ ወንጌል እየተሰበከ እንዴት እንዲህ ትላለህ የሚል ሊኖር እንደሚችል እርግጠኛ ነኝ። ይህንንን ጉዳይ በሰፊው እንመለከታለን። ዋናውና ደጋግሜ የማሳስበው ትልቅና ዋና ቁም ነገር ወንጌል ስለ ኢየሱስ ክርስቶስ ነው። ይህንን እውነት አቅልለን መመልከትና መያዝ የለብንም። ወንጌል በውስጡ በርካታ ታሪኮችን የያዘ፣ የብዙ ሰዎች ማንነት የተገለጠበት፣ ብዙ ነገር ልንማርበት የምንችል እንደሆነ እየታየ ወንጌል ስለ ኢየሱስ ክርስቶስ ብቻ ነው እንዴት ይባላል? ጳውሎስ ከላይ በሮሜ ላይ ያለውን ልብ ብንል ወንጌል በሥጋ ከዳዊት ዘር ስለ ተወለደው፣ ስለ ሞተውና ስለ ተነሳው፣ ከሙታን በመነሳቱ በኃይል የእግዚአብሔር ልጅ ሆኖ ስለ ተገለጠው ስለ ኢየሱስ ክርስቶስ ነው የሚለው የሚያሳየን ወንጌል በሰው ልጆች ታሪክ ውስጥ ሰው ሆኖ ተገልጦ የኖረውን ኢየሱስን ታሪካዊነቱንና መለኮታዊነቱን የጠበቀ ትምሕርት መሆኑን ነው። ይህ ማለት ወንጌል ፍልስፍና አይደለም። በአይነ ሕሊና የተሳለው ሰው በመንፈሱ ተቀስቅሶ የተደረሰ አይደለም። ሰዎች እንደ ሰው ፍላጎትና በየዘመኑ እንደሚለዋወጥ ፋሽን የሚለዋወጥ አይደለም። በሥጋ ከዳዊት ዘር የተወለደው የኢየሱስ ክርስቶስን ማንነትና ታሪካዊነቱን የሚያመለክት ነው። ወንጌል በኢየሱስ ላይ ያተኮረና በማንነቱ ላይ ያነጣጠረና ነው። ከዚህ የተነሳ የወንጌል ተቀዳሚ ትምሕርትም ሆነ ስብከት ኢየሱስ ነው።
ይቀጥላል. . .
ምንጭ፦ sermons.logos.com

👍6❤1
' 📜📜📜===📜📜📜
📜 የዕለቱ ጥቅስ 📜
📜📜📜===📜📜📜
“እንደ ልቤም በግ ጠባቆችን እሰጣችኋለሁ፥ በእውቀትና በማስተዋልም ይጠብቁአችኋል።”
ኤርምያስ 3፥15

#የእግዚአብሔር_ቃል_ምን_ይላል?
2ኛ ቆሮ 13
¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯
¹ ወደ እናንተ ስመጣ ይህ ሦስተኛዬ ነው፤ ሁሉ ነገር በሁለትና በሦስት ምስክር አፍ ይጸናል።
²-³ ሁለተኛ በእናንተ ዘንድ በነበርሁ ጊዜ እንደ ተናገርሁ አሁንም ደግሞ በሩቅ ስሆን፥ ክርስቶስ በእኔ አድሮ እንዲናገር ማስረጃ ከፈለጋችሁ፥ እንደ ገና ብመጣ እንዳልራራላቸው አስቀድመው ኃጢአት ላደረጉት ለሌሎችም ሁሉ አስቀድሜ ብዬአለሁ፥ አስቀድሜም እላለሁ። ክርስቶስም ስለ እናንተ አይደክምም ነገር ግን በእናንተ ኃይለኛ ነው።
⁴ በድካም ተሰቅሎአልና፥ ነገር ግን በእግዚአብሔር ኃይል በሕይወት ይኖራል። እኛ ደግሞ ከእርሱ ጋር እንደክማለንና፥ ነገር ግን ስለ እናንተ በሆነ በእግዚአብሔር ኃይል ከእርሱ ጋር በሕይወት እንኖራለን።
⁵ በሃይማኖት ብትኖሩ ራሳችሁን መርምሩ፤ ራሳችሁን ፈትኑ፤ ወይስ ምናልባት የማትበቁ ባትሆኑ፥ ኢየሱስ ክርስቶስ በእናንተ ውስጥ እንዳለ ስለ እናንተ አታውቁምን?
⁶ እኛ ግን የማንበቃ እንዳይደለን ልታውቁ ተስፋ አደርጋለሁ።
⁷ ክፉ ነገርንም ከቶ እንዳታደርጉ ወደ እግዚአብሔር እንጸልያለን፤ እኛ የምንበቃ ሆነን እንገለጥ ዘንድ አይደለም ነገር ግን እኛ ምንም እንደማንበቃ ብንሆን፥ እናንተ መልካሙን ታደርጉ ዘንድ ነው።
⁸ ለእውነት እንጂ በእውነት ላይ ምንም ለማድረግ አንችልምና።
⁹ እኛ ስንደክም እናንተም ኃይለኞች ስትሆኑ ደስ ብሎናልና፤ እናንተ ፍጹማን ትሆኑ ዘንድ ለዚህ ደግሞ እንጸልያለን።
¹⁰ ስለዚህ ጌታ ለማፍረስ ያይደለ ለማነጽ እንደ ሰጠኝ ሥልጣን፥ ከእናንተ ጋር ሳለሁ በቁርጥ እንዳልሠራ በሩቅ ሆኜ ይህን እጽፋለሁ።
¹¹ በቀረውስ፥ ወንድሞች ሆይ፥ ደኅና ሁኑ። ፍጹማን ሁኑ፥ ምክሬን ስሙ፥ በአንድ ልብ ሁኑ፥ በሰላም ኑሩ፥ የፍቅርና የሰላምም አምላክ ከእናንተ ጋር ይሆናል።
¹² በተቀደሰ አሳሳም እርስ በርሳችሁ ሰላምታ ተሰጣጡ።
¹³ ቅዱሳን ሁሉ ሰላምታ ያቀርቡላችኋል።
¹⁴ የጌታ የኢየሱስ ክርስቶስ ጸጋ የእግዚአብሔርም ፍቅር የመንፈስ ቅዱስም ኅብረት ከሁላችሁ ጋር ይሁን። አሜን።

👍4
' 📜📜📜===📜📜📜
📜 የዕለቱ ጥቅስ 📜
📜📜📜===📜📜📜
“በእምነት መሆናችሁን ለማወቅ ራሳችሁን መርምሩ፤ ራሳችሁን ፈትኑ። ከፈር የወጣችሁ ካልሆነ በስተቀር፣ ኢየሱስ ክርስቶስ በውስጣችሁ እንዳለ አታውቁምን?”
2ኛ ቆሮንቶስ 13፥5 (አዲሱ መ.ት)

👍5❤4
' 📜📜📜===📜📜📜
📜 የዕለቱ ጥቅስ 📜
📜📜📜===📜📜📜
“እርሱም በጀልባዋ ላይ ወጥቶ አብሮአቸው ሆነ፤ ነፋሱም ተወ፤ እነርሱም እጅግ ተደነቁ፤”
ማርቆስ 6፥51 (አዲሱ መ.ት)

❤3👍3
የያዕቆብ ልጆች እና በረከቶቻቸው
ክፍል - ፬
ስምዖን (ዘፍ. 49፥5-7)
ስምዖን ከልያ ለያዕቆብ የተወለደለት ሁለተኛው ልጁ ነው። ልያም እኔ እንደ ተጠላሁ እግዚአብሔር ስለ ሰማ ይህንን ደገመኝ ስትል የሁለተኛ ልጇን ስም ስምዖን ብላ ጠራችው (ዘፍ. 29፥33)፡፡ ያዕቆብም ልጆቹን ሊመርቅ በተነሳ ጊዜ ስምዖንና ሌዊ በሰኬም ሰዎች ላይ ያደረጉትን በማስታወስ በልቡ የቆየና የኖረ የምሬት ሀዘኑ ተገለጠ (ዘፍ. 34፥1-31)። በጊዜው ዲና የተባለችው የያዕቆብ ሴት ልጅ የአገሩን ሴቶች አኗኗር ለማየት ከምትኖርበትና በሰላም ከተጠበቀችበት ስፍራ ርቃ በመውጣቷ ምክንያት ያገኛት የሴኬም ሰው ወስዶ አስነወራት፡፡ ይህም ድርጊት ያዕቆብንና ልጆቹን አሳዘነ፡፡ በሀዘናቸው ላይ ግን ጨምሮ ስምዖንና ሌዊን እጅግ አስቆጣቸው:: በዚህም መካከል ሁኔታውን ለማብረድና እርቅንም ለመፍጠር በያዕቆብና በሴኬም ሽማግሌዎች በተደረገው የስምምነት ድርድር ውስጥ ዲናን ላስነወራት ለሴኬም ስው ሚስት እንድትሆን ለመስጠት የሴኬም ወንዶች ሁሉ እንዲገረዙ ተስማሙ። በስምምነቱም መሠረት የሴኬም ወንዶች ሁሉ ተገረዙ፡፡ በዚህም ሁኔታ ውስጥ እያሉና የሴኬምም ወንድ ሁሉ የግርዘት ቁስሉን ሲያስታምም ስምዖንና ሌዊ የቁጣቸውን ሰይፍ መዝዘው በሴኬም ወንዶች ላይ ዘመቱ፡፡ ገና በቁስል ህመማቸው ሲቃ ውሰጥ ያሉ የሴኬምም ሰዎች ምን እንደ መጣ እንኳ ሳያውቁ በነስምዖን የሰይፍ ስለት መውደቅ ጀመሩ (ዘፍ. 34፥25 )። ከምሬት የሚመጣ ቁጣና ከኩርፈት የሚነሳ በቀል መራራ ስለሆነ በሰይፋቸው የብዙዎችን ደም አፈሰሱ፡፡ ምን እንዳደረጉና እንዳጠፉ ያላወቁ ብዙዎች በቁጣቸው ሰይፍ ወደቁ፡፡ ምሕረትና ርኀራኄ የሌለበት ሀዘንና ቁጣ ፍሬው ሞት በመሆኑ የብዙዎች ሕይወት ጨለመ፡፡
የዚህ ድርጊታቸው ወሬ ለያዕቆብ ሲደርሰው እጅግ አሳዘነው፤ እስደነገጠውም፡፡ ከላባ ቤት ባርነት ተገላግሎ፥ እግዚአብሔርም በብዙ ባለጠግነት ባርኮት የአባቶቹንና የእርሱንም አምላክ ለማምለክ ይህቺ ያረፈባትን ሰፍራ መርጦና በዚያም መሠዊያውን ሠርቶ አምላኬ አሳረፈኝ ብሎ እፎይታውን ገና ሲጀምር ባላስበው ዱላ ያዕቆብ ተመታ፡፡ ከዚህም ድንጋጤ የተነሳ በቁጥር ብዙ የሆኑ የሴኬም ሰዎችና ሌሎችም ያጠፉናል ሲል ይህች የወደዳትን ቦታ ለቆ፥ ድንኳኑንም ነቅሎ እንዲጓዝ ተገደደ፡፡ ያለ ዕረፍት በአሳብና በሞት ሰቀቀን ውሰጥ እንዲወድቅ አደረገው፡፡ የስምዖንና የሌዊ የምሬትና የበቀል እርምጃ እጅግ መራራ ስለ ነበር ያዕቆብን ድንጉጥ እንዲሆን ዳረገው (ዘፍ. 34፥30)::
ከዚህም ከሰምዖንና ከወንድሙ የበቀል ፍሬ የተነሳ እርሱን ከነቤተሰቡ ተንከራታች እንዲሆን ስላደረጉት ያዕቆብ ስምዖንና ሌዊን የተከፈሉና የተበተኑ ሕዝብ እንዲሆኑ ያለበረከት ተዋቸው፡፡ ከእነርሱም ጋር ኅብረት አይኑረኝ በማለት ራሱን ከድርጊታቸው ታሪክ እየለየ እንዲህ በማለት ተናገር፦
“ስምዖንና ሌዊ ወንድማማች ናቸው፤ ሰይፎቻቸው የዓመፃ መሣሪያ ናቸው፤ በምክራቸው ነፍሴ አትግባ፤ ከጉባኤአቸውም ጋር ክብሬ አትተባበር፣ በቁጣቸው ሰውን ገድለዋልና፥ በገዛ ፈቃዳቸውም በሬን አስነከሰዋልና፡፡ ቁጣቸው ርጉም ይሁን፥ ጽኑ ነበርና፤ ኩርፈታቸውም ብርቱ ነበርና፤ በያዕቆብ እከፋፍላቸዋለሁ፥ እበትናቸዋለሁ (ዘፍ. 49፥5-7):: በእስራኤልም ስለ ስምዖን ሙሴም የእስራኤልን ነገድ ሁሉ በበረከት ሲባርክ ምንም ሳይናገር ቢያልፍም ለሌዊ ነገድ ግን እግዚአብሔር ምሕረት አደረገ፡፡ እንዲያውም ከእሰራኤል ነገድ ሁሉ ለራሱ ርስት አድርጎ ለያቸው፡፡ የስምዖን በሙሴ መዘለል እግዚእብሔር እንዲያው እረስቶት አይደለም፡፡ ምናልባትም ከዚህ ከሴኬም ድርጊቱ ጋር ዮሴፍም በጉድጓድ በሚጣል ጊዜ የከፋበትና እንዲገድሉትም ወንድሞቹን ያነሳሳበት ስምዖን ሳይሆን የሚቀር አይመስለኝም፡፡ የበቀልና የምሬት ሰው እንደ ሆነ የሴኬም ተግባሩ ስለሚያሳይ በወንድሙ ላይ ብዙ የጨከነበትና ሌሎቹም እንዲነሱበት ከግንባር ሆኖ የገፋፋው እርሱ ሊሆን ይችላል፡፡ የሰሙንም ስያሜ ያገኘው እናቱ ልያ ያዕቆብ ለራሔል ካለው ፍቅር የተነሳ ተጠልታ የምትኖር እንደ ሆነ ለመግለጥ ሰለ ነበር፥ የራሔልን የመጀመሪያ ልጅ ዮሴፍን ስምዖን መጥላቱና መጥፊያውን መፈለጉ አይቀርም ብሎ ማሰብ ለስምዖን ባህረ ብዙ ከመንገድ መራቅ አይሆንም፡፡
ረሀብ በከነዓን ጠንክሮ እህል ፍለጋ የያዕቆብ ልጆች ወደ ግብጽ በወረዱ ጊዜና በዮሴፍ ፊት ወንድሞቹ በቀረቡበት ወቅት የሚያስፈልጋቸውን እህል እንዲያገኙ ዮሴፍ ካደረገ በኋላ ብንያምን ይዘው እንዲመለሱ ለማድረግ ከመካከላቸው አንዱን በእስር ቤት ለማቆየት ዮሴፍ ሲወስን በእስር እንዲቆይ የበየነበት በስምዖን ላይ ነበር (ዘፍ. 42፥24-25)፡፡ ከወንድሞቹ ተለይቶ መኖርንና ከአባቱም ቤትና ከወገኑም መለየትን ለአጭር ጊዜም ቢሆን እንዲቀምስ ስምዖንን ያስቀረው እንደሆነ መገመት ይቻላል፡፡
ይቀጥላል...
ምንጭ፦ አበራ ጌታሁን (ዶ/ር)፤ የያዕቆብ ልጆች እና በረከቶቻቸው፤ ገጽ 13-15

👍4❤2
' 📜📜📜===📜📜📜
📜 የዕለቱ ጥቅስ 📜
📜📜📜===📜📜📜
“ሌላው በጣለው መሠረት ላይ እንዳልገነባ ብዬ፣ ክርስቶስ ባልተጠራበት ስፍራ ወንጌልን መስበክ የዘወትር ምኞቴ ነበር።”
ሮሜ 15፥20 (አዲሱ መ.ት)

👍5❤2