ቅዱሳት መጻሕፍት
7.46K subscribers
1.37K photos
61 videos
332 files
808 links
በዚህ ቻናል

👉ቅዱሳት መጻሕፍት ይጠናሉ::
👉መጽሐፍ ቅዱሳዊ ትምህርቶች ይቀርባሉ::
👉 ለቅዱሳት መጽሐፍት ጥናት የሚያግዙ መጻሕፍት ይለቀቃሉ።

⭐️⭐️⭐️⭐️⭐️

@Holy_scriptures
Download Telegram
በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ የእነጳውሎስን ስብከት ተከትሎ ከተመሰረቱት ቤተ ክርስቲያናት መካከል በሴቶች እንደተመሰረተች የምትገመት ቤተ ክርስቲያን የቷ ናት?
Anonymous Quiz
18%
ሀ. ሮሜ
10%
ለ. ቆሮንቶስ
27%
ሐ. ፊልጵስዩስ
10%
መ. ቆላስይስ
13%
ሠ. ኤፌሶን
22%
ረ. ተሰሎንቄ
👍72
'         📜📜📜===📜📜📜  
          📜    የዕለቱ ጥቅስ   📜
          📜📜📜===📜📜📜
“ከእርሱ ጋር እንዲሆኑ፣ ለስብከትም ይልካቸው ዘንድ ዐሥራ ሁለቱን ሾማቸው፤ ሐዋርያትም ብሎ ጠራቸው፤”
        ማርቆስ 3፥14 (አዲሱ መ.ት)



ወደ ቻናሉ ለመ🀄️🀄️ል፦ @Holy_scriptures
5
#የሮሜ_መልእክት_ጥናት


እግዚአብሔር የሚፈርደው በትክክል ነው (9፥14-18)

14–16 አንዳንዶች እግዚአብሔር የሚፈርደው በትክክል አይደለም ብለው ያስባሉ። እንዲህ በማለትም ይጠይቃሉ፥ «እግዚአብሔር ያዕቆብን የወደደውና ኤላውን የጠላው ለምንድን ነው? በዚህ እግዚአብሔር ፍርድ አላጓደለምን?» ስለ እግዚአብሔር እንዲህ የመሰሉ አሳቦች ሊኖሩን አይገባም። በቁ. 15 ጳውሎስ እግዚአብሔር በዘጸ. 33፥19 ለሙሴ የተናገረውን ቃል ይጠቅሳል። እግዚአብሔር ሰዎችን ይመርጣል፥ ሰዎችን ይጠራል፥ ሰዎችንም ይባርካል። ይህንንም የሚያደርገው ከሰው ምኞትና ጥረት ሳይሆን ከራሱ ምሕረት የተነሣ ነው (ቁ. 16)::

በእነዚህ ጥቅሶች ውስጥ ጳውሎስ፤ የእግዚአብሔር ምሕረት ፍርድን በማጓደል ላይ የተመሠረተ አይደለም በማለት ያስተምራል። እያንዳንዱ ሰው በአንድ መንገድ ወይም በሌላ እግዚአብሔርን ሳይታዘዝ በመቅረቱ፤ ደኅንነትን ለማግኘት የተገባው ማንም ሰው የለም። ነገር ግን እግዚአብሔር በምሕረቱና በጸጋው የራሱን ልጅ ኢየሱስን ለደኅንነታችን አሳልፎ ሰጥቶኣል። ያለ እግዚአብሔር ምሕረትና ያለ ጸጋው ደኅንነትን ለማግኘት የሚችል ማንም ሰው የለም።

ማንም ሰው ቢሆን በራሱ ምኞትና ጥረት የእግዚአብሔርን ጸጋና ምሕረት መቀበል አይችልም (ቁ. 16)። በእርግጥም እግዚአብሔር እንዲህ ብሎአል፥ «ትፈልጉኛላችሁ፥ የምትፈልጉኝም በሙሉ ልባችሁ ስለሆነ ታገኙኛላችሁ» (ኤር. 29፥13)። በእውነትም በተከፈተና በትሑት ልብ እግዚአብሔርን መፈለግ አለብን፤ ፊታችንንም ወደ እርሱ መመለስ ይገባል። ይህንንም ቢሆን የእግዚአብሔር ጸጋ ካላነሣሣን በቀር በራሳችን ምንም ማድረግ አንችልም (ዮሐ. 1፥12-13፤ 6፥44)። ከመጀመሪያ እስከ መጨረሻ ደኅንነታችን የእግዚአብሔር ጸጋ ሥራ ነው።
17-18 ፈርዖን ማን ነበር? በሙሴ ዘመን የግብጽ ገዢዎች ፈርዖን ይባሉ ነበር። ጳውሎስ በዚህ ጥቅስ የሚያነሣው ፈርዖን 2ኛ ራምሴስ የሚባለው ሲሆን፥ እርሱም በዚያን ጊዜ በግብጽ ይኖሩ በነበሩት አይሁዳውያን ላይ ስደት አነሣስቶ የነበረ በጣም ጨካኝና ክፉ መሪ ነበር። ከዚህ ከክፉ ፈርዖን እጅ አይሁዳውያንን ተቤዥቶ ነጻ እንዲያወጣቸው እግዚአብሔር ሙሴን ላከው። በዚህ ፈርዖን ልብ ውስጥ ፍርሃትን ለማምጣት ብሎ፥ እግዚአብሔር በሙሴ በኩል ታላላቅ ምልክቶችንና ድንቅ ነገሮችን አደረገ። እነዚህም ምልክቶችና ድንቅ ነገሮች በዘጸ. ከምዕራፍ 7-12 ባለው ክፍል ውስጥ ተገለጠዋል።

በቁ. 17 ጳውሎስ እግዚአብሔር ለፈርዖን የተናገረውን ቃል ይጠቅሳል (ዘጸ. 9፥16)፡፡ ይህን ክፉ መሪ ያስነሣውና ልቡንም ያጠነከረው፥ የእግዚአብሔር ኀይል እንዲገለጥና ስሙም እንዲታወጅ ነው። የፈርዖን ልብ ባይጠነክር ኖሮ፣ ለምሳሌ ፈርዖን ንስሓ የገባ ቢሆን ኖሮ፥ እግዚአብሔር ኀይሉን ለማሳየት ዕድሉ አይኖረውም ነበር። ከዚህም የምንረዳው እግዚአብሔር ለአንዳንዶች ምሕረቱን እንደሚያሳይ ሲሆን፤ ሌሎች የእግዚአብሔርን ያጠነክረዋል፡፡ ምሕረት እንዳይቀበሉ ልባቸውን ያጠነክረዋል።

ይህን ካነበብን በኋላ እግዚአብሔር እውነተኛ ፍርድ የለውም ለማለት እንፈተን ይሆናል። ለፈርዖንም በእውነት አልፈረደም እንላለን። እግዚአብሔር ለፈርዖን ዕድል አልሰጠውም፣ ምንም ዓይነት ደግነት አላሳየውም። ማንም ሰው ቢሆን የእግዚአብሔርን ደግነት ለማግኘት የተገባ አይደለም። የእግዚአብሔርን ምሕረት ለመቀበልም የተገባው ሰውም የለም። ማንም ሰው ቢሆን እግዚአብሔርን «እኔ ዕድል ማግኘት ይገባኛል» ሊለው አይችልም። ምክንያቱም እኛ ሁላችንም ብንሆን በእግዚአብሔር ፊት ደጋግመን ኃጢአት ሠርተናል (ሮሜ 3-10-12)። ሰው ከእግዚአብሔር ፊት ሊቀበለው የሚገባ ነገር ቢኖር ቅጣትን ብቻ ነው። እግዚአብሔር የሰዎችን ልብ የሚያጠነክረው ከኃጢአታቸው የተነሣ ነው። እግዚአብሔር የሰውን ልብ ሲያጠነክር ገልጦ የሚያሳየው የራሱን ፍትሕ ነው እንጂ ፍትሕ አጉዳይነቱን አይደለም።

ስለዚህ እግዚአብሔር የፈርዖንን ልብ ያጠነከረው በራሱ በፈርዖን ክፋት ነው፤ እግዚአብሔር የፈርዖንን ልብ በማጠንከሩ ያላየው ትክክለኛ ፍትሕ ነበር። ፈርዖን የእግዚአብሔርን ቅጣት ለመቀበል የተገባ ሰው ነበር።


ይቀጥላል. . .



ምንጭ፦ የአዲስ ኪዳን ማብራሪያ፤ ገጽ 372-373




ወደ ቻናሉ ለመ🀄️🀄️ል፦ @Holy_scriptures
👍51
'         📜📜📜===📜📜📜  
          📜    የዕለቱ ጥቅስ   📜
          📜📜📜===📜📜📜
“ብርቱ የሆነ እርሱ በእኔ ታላቅ ሥራ አድርጎአልና፤ ስሙም ቅዱስ ነው።”
              ሉቃስ 1፥49



ወደ ቻናሉ ለመ🀄️🀄️ል፦ @Holy_scriptures
2👍1🔥1
#የእግዚአብሔር_ቃል_ምን_ይላል?


ገላትያ 6
¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯
¹ ወንድሞች ሆይ፥ ሰው በማናቸውም በደል ስንኳ ቢገኝ፥ መንፈሳውያን የሆናችሁ እናንተ እንደዚህ ያለውን ሰው በየውሃት መንፈስ አቅኑት፤ አንተ ደግሞ እንዳትፈተን ራስህን ጠብቅ።
² ከእናንተ እያንዳንዱ የአንዱን ሸክም ይሸከም እንዲሁም የክርስቶስን ሕግ ፈጽሙ።
³ አንዱ ምንም ሳይሆን ምንም የሆነ ቢመስለው ራሱን ያታልላልና።
⁴ ነገር ግን እያንዳንዱ የገዛ ራሱን ሥራ ይፈትን፥ ከዚያም በኋላ ስለ ሌላው ሰው ያልሆነ ስለ ራሱ ብቻ የሚመካበትን ያገኛል፤
⁵ እያንዳንዱ የገዛ ራሱን ሸክም ሊሸከም ነውና።
⁶ ነገር ግን ቃሉን የሚማር ከሚያስተምረው ጋር መልካምን ነገር ሁሉ ይከፋፈል።
⁷ አትሳቱ፤ እግዚአብሔር አይዘበትበትም። ሰው የሚዘራውን ሁሉ ያንኑ ደግሞ ያጭዳልና፤
⁸ በገዛ ሥጋው የሚዘራ ከሥጋ መበስበስን ያጭዳልና፥ በመንፈስ ግን የሚዘራው ከመንፈስ የዘላለምን ሕይወት ያጭዳል።
⁹ ባንዝልም በጊዜው እናጭዳለንና መልካም ሥራን ለመሥራት አንታክት።
¹⁰ እንግዲያስ ጊዜ ካገኘን ዘንድ ለሰው ሁሉ ይልቁንም ለሃይማኖት ቤተ ሰዎች መልካም እናድርግ።
¹¹ እንዴት ባሉ ታላላቆች ፊደላት በእጄ እንደ ጻፍሁላችሁ እዩ።
¹² በሥጋ መልካም ሆነው ሊታዩ የሚወዱ ሁሉ እንድትገረዙ ግድ አሉአችሁ፥ ነገር ግን ስለ ክርስቶስ መስቀል እንዳይሰደዱ ብቻ ነው።
¹³ በሥጋችሁ እንዲመኩ ልትገረዙ ይወዳሉ እንጂ የተገረዙቱ ራሳቸው እንኳ ሕግን አይጠብቁም።
¹⁴ ነገር ግን ዓለም ለእኔ የተሰቀለበት እኔም ለዓለም የተሰቀልሁበት ከጌታችን ከኢየሱስ ክርስቶስ መስቀል በቀር ሌላ ትምክህት ከእኔ ይራቅ።
¹⁵ በክርስቶስ ኢየሱስ አዲስ ፍጥረት መሆን ይጠቅማል እንጂ መገረዝ ቢሆን ወይም አለመገረዝ አይጠቅምምና።
¹⁶ በዚህም ሥርዓት በሚመላለሱ ሁሉ ላይ በእግዚአብሔር እስራኤልም ላይ ሰላምና ምሕረት ይሁን።
¹⁷ እኔ የኢየሱስን ማኅተም በሥጋዬ ተሸክሜአለሁና ከእንግዲህ ወዲህ አንድ ስንኳ አያድክመኝ።
¹⁸ ወንድሞች ሆይ፥ የጌታችን የኢየሱስ ክርስቶስ ጸጋ ከመንፈሳችሁ ጋር ይሁን። አሜን።




ወደ ቻናሉ ለመ🀄️🀄️ል፦ @Holy_scriptures
👍2
'         📜📜📜===📜📜📜  
          📜    የዕለቱ ጥቅስ   📜
          📜📜📜===📜📜📜
“በገዛ ሥጋው የሚዘራ ከሥጋ መበስበስን ያጭዳልና፥ በመንፈስ ግን የሚዘራው ከመንፈስ የዘላለምን ሕይወት ያጭዳል።”
              ገላትያ 6፥8




ወደ ቻናሉ ለመ🀄️🀄️ል፦ @Holy_scriptures
4👍2
#እራሳችንን_እንመርምር


እግዚአብሔር ሰዎችን ያታልላልን? ሰው ምን ቢያደርግ እግዚአብሔር እንዲህ ያስብበታል? ለምን?


“እግዚአብሔርም፦ ወጥቶ በሬማት ዘገለዓድ ይወድቅ ዘንድ የእስራኤልን ንጉሥ አክዓብን የሚያታልል ማን ነው? አለ። አንዱም እንደዚህ፥ ሌላውም እንደዚያ ያለ ነገር ተናገረ።”
2 ዜና 18፥19





ወደ ቻናሉ ለመ🀄️🀄️ል፦ @Holy_scriptures
3👍1
'         📜📜📜===📜📜📜  
          📜    የዕለቱ ጥቅስ   📜
          📜📜📜===📜📜📜
“ሐማም ለሚስቱ ለዞሳራና ለወዳጆቹ ሁሉ ያገኘውን ሁሉ አጫወታቸው። ጥበበኞቹና ሚስቱ ዞሳራም። በፊቱ መውደቅ የጀመርህለት መርዶክዮስ ከአይሁድ ወገን የሆነ እንደ ሆነ በፊቱ ፈጽሞ ትወድቃለህ እንጂ አታሸንፈውም አሉት።”
                አስቴር 6፥13




ወደ ቻናሉ ለመ🀄️🀄️ል፦ @Holy_scriptures
👍31
'         📜📜📜===📜📜📜  
          📜    የዕለቱ ጥቅስ   📜
          📜📜📜===📜📜📜
“ፍቅራችሁ በጥልቅ እውቀትና በማስተዋል ሁሉ በዝቶ እንዲትረፈረፍ እጸልያለሁ።”
          ፊልጵስዩስ 1፥9 (አዲሱ መ.ት)




ወደ ቻናሉ ለመ🀄️🀄️ል፦ @Holy_scriptures
2👍2
#ከተማ_ወይም_ቦታ_በቅዱሳት_መጻሕፍት


#አርሞንዔም፤ በሶርያ፥ በሊባኖስና በእስራኤል ድንበር ላይ ያለው ተራራ ከባሕር ጠለል እስከ 2777 ሜትር ከፍ ስለሚል በአቅራቢያው ካሉት ተራራዎች ከፍታ አለው። የአርሞንዔም በረዶ እየሟሟ ወደ ዮርዳኖስና ወደ ገሊላ ባሕር ይፈሳል፤ ዘዳ. 4፥48፤ መዝ. 133፥3። ክርስቶስ ክብሩን የገለጠው በዚህ ተራራ ሳይሆን አልቀረም፤ መዝ. 89፥12፤ ማቴ. 17፥1-8። አርሞንዔም ሢርዮን፥ ሳኔር፥ ኤርሞን ተብሎ ይጠራል፤ ዘዳ. 3፥8:9፤ መኃልይ 4፥8።



ምንጭ፦ የመጽሐፍ ቅዱስ መዝገበ ቃላት፤ ገጽ 147




ወደ ቻናሉ ለመ🀄️🀄️ል፦ @Holy_scriptures
👍7
'         📜📜📜===📜📜📜  
          📜    የዕለቱ ጥቅስ   📜
          📜📜📜===📜📜📜
“በይሁዳም ሁሉና በገሊላ በሰማርያም የነበሩት አብያተ ክርስቲያናት በሰላም ኖሩ ታነጹም፤ በእግዚአብሔርም ፍርሃትና በመንፈስ ቅዱስ መጽናናት እየሄዱ ይበዙ ነበር።”
           ሐዋርያት 9፥31




ወደ ቻናሉ ለመ🀄️🀄️ል፦ @Holy_scriptures
5👍2
ወደ ቻናሉ ለመ🀄️🀄️ል፦ @Holy_scriptures
👍3
ከእምነት ወደ እምነት-1.pdf
445.4 KB
👉ርዕስ፦ ከእምነት ወደ እምነት
✍️ጸሐፊ፦ ዋችማን ኒ
🗣ትርጉም፦ ዘካርያስ ጥላሁን
✏️አርትኦት፦ ጳውሎስ ፈቃዱ
🖨አሳታሚ፦ ራዕይ አሳታሚ
📄የገጽ ብዛት፦ 112

ወደ ቻናሉ ለመ🀄️🀄️ል፦ @Holy_scriptures
👍32
'         📜📜📜===📜📜📜  
          📜    የዕለቱ ጥቅስ   📜
          📜📜📜===📜📜📜
“በድነታችሁ እንድታድጉ፣ አዲስ እንደ ተወለዱ ሕፃናት ንጹሑን መንፈሳዊ ወተት ተመኙ፤”
          1ኛ ጴጥሮስ 2፥2 (አዲሱ መ.ት)



ወደ ቻናሉ ለመ🀄️🀄️ል፦ @Holy_scriptures
6👍1
የቀጠለ. . .

የኢየሱስ ክርስቶስ ክብር የሚበራበት ወንጌል



ጳውሎስ ሐዋርያ የሆነው የእግዚአብሔር ነው ለተባለውና ስለ ኢየሱስ ክርስቶስ ለሚናገረው ወንጌል አገልጋይ እንዲሆን በመለየት እንደሆነ ይናገራል። ጳውሎስ ባለቤቱ እግዚአብሔር ነው ለሚለው ወንጌል በመለየቱ ራሱን የክርስቶስ ኢየሱስ ባሪያ እንደሆነ ይናገራል። ጳውሎስ የኢየሱስ ባሪያ የሆነው ስለ ኢየሱስ የሚናገረውን ወንጌል እንዲያገለግል ስለ ተመረጠና ስለተለየ ነው። ሕይወቱ ለወንጌል እንደ ባሪያ የተሸጠ ነው። የኢየሱስ ወንጌል ታላላቅ ሐዋርያትን ባሪያ ያደረገ፥ ለሌላ ለምንም እንዳይውሉና እዳይሆኑ አድርጎ የሚለው ነው። የኢየሱስ ወንጌል ስለ ኢየሱስ ብቻ ስለሚናገር ለእግዚአብሔር ወንጌል የተለዩትም “በመካከላችሁ ሳለሁ ከኢየሱስ ክርስቶስ በቀር እርሱም እንደተሰቀለ ሌላ ነገር እንዳላውቅ ቆርጬ ነበርና” እያሉ ባሪያ ካሳዳሪው እንደማይለው እነርሱም ከኢየሱስ ውጪ ሌላ ስብከትም ሆነ ትምሕርት የላቸውም (1ኛ ቆሮ. 2፥2)። ወንጌል ስለ ኢየሱስ ብቻ የሆነ የገባቸው አገልጋዮች የኢየሱስ ክርስቶስ ብቻ ባሪያዎች ናቸው።

የወንጌል ተቀዳሚ መልእክት ምንድር ነው?

ጳውሎስ ከላይ በሮሜ ላይ በተናገረው እውነት ውስጥ የወንጌልን ምንነት በሚገባ ያሳየናል። ወንጌል በመጀመሪያ ደረጃ፥ በተቀዳሚነትና በዋናናነት የሚናገረው ስለ ኢየሱስ ክርስቶስ ማንነት እንደሆነ እናያለን። በጌታ በኢየሱስ ማንነት ላይ እደግማለሁ ማንነት ላይ ያላተኮረ ወንጌል፣ ወንጌል አይደለም። ዛሬ ብዙ መንፈሳዊ ኪሳራ ያመጣብን፥ እውነተኛ መንፈሳዊ ለውጥና የደቀ መዝሙር ሕይወት እንዳይኖር እንቅፋት የሆነብን ነገር ሊገጥመን የቻለው ኢየሱስ ተኮር የሆነ ወንጌል ስለ ጠፋ ነው። የደቀ መዝሙር ሕይወት ጌታን የመከተል ሕይወት ነው። ጌታን የምንከተለው ልንከተለው የሚገባ ጌታ መሆኑን ስናውቅ ነው። አገልጋዮችን የኢየሱስ ክርስቶስ ባሪያ ባላደረገ ወንጌል ኢየሱስ ክርስቶስን ሊከተሉ የሚችሉ ደቀ መዛሙርትን ማፍራት አያስችልም። ጌታ ያስተማረንን ሳንጠብቅ ከእርሱ የተማርነውን የሚጠብቁ ሰዎች እንዴት ማፍራት እንችላለን? ወንጌል ጳውሎስ ባሪያ ስለሆነለት ስለ ኢየሱስ ክርስቶስ የሚናገር ወንጌል ነው።

ይህ ሁሉ ወንጌል እየተሰበከ እንዴት እንዲህ ትላለህ የሚል ሊኖር እንደሚችል እርግጠኛ ነኝ። ይህንንን ጉዳይ በሰፊው እንመለከታለን። ዋናውና ደጋግሜ የማሳስበው ትልቅና ዋና ቁም ነገር ወንጌል ስለ ኢየሱስ ክርስቶስ ነው። ይህንን እውነት አቅልለን መመልከትና መያዝ የለብንም። ወንጌል በውስጡ በርካታ ታሪኮችን የያዘ፣ የብዙ ሰዎች ማንነት የተገለጠበት፣ ብዙ ነገር ልንማርበት የምንችል እንደሆነ እየታየ ወንጌል ስለ ኢየሱስ ክርስቶስ ብቻ ነው እንዴት ይባላል? ጳውሎስ ከላይ በሮሜ ላይ ያለውን ልብ ብንል ወንጌል በሥጋ ከዳዊት ዘር ስለ ተወለደው፣ ስለ ሞተውና ስለ ተነሳው፣ ከሙታን በመነሳቱ በኃይል የእግዚአብሔር ልጅ ሆኖ ስለ ተገለጠው ስለ ኢየሱስ ክርስቶስ ነው የሚለው የሚያሳየን ወንጌል በሰው ልጆች ታሪክ ውስጥ ሰው ሆኖ ተገልጦ የኖረውን ኢየሱስን ታሪካዊነቱንና መለኮታዊነቱን የጠበቀ ትምሕርት መሆኑን ነው። ይህ ማለት ወንጌል ፍልስፍና አይደለም። በአይነ ሕሊና የተሳለው ሰው በመንፈሱ ተቀስቅሶ የተደረሰ አይደለም። ሰዎች እንደ ሰው ፍላጎትና በየዘመኑ እንደሚለዋወጥ ፋሽን የሚለዋወጥ አይደለም። በሥጋ ከዳዊት ዘር የተወለደው የኢየሱስ ክርስቶስን ማንነትና ታሪካዊነቱን የሚያመለክት ነው። ወንጌል በኢየሱስ ላይ ያተኮረና በማንነቱ ላይ ያነጣጠረና ነው። ከዚህ የተነሳ የወንጌል ተቀዳሚ ትምሕርትም ሆነ ስብከት ኢየሱስ ነው።


ይቀጥላል. . .


ምንጭ፦ sermons.logos.com



ወደ ቻናሉ ለመ🀄️🀄️ል፦ @Holy_scriptures
👍61
'         📜📜📜===📜📜📜  
          📜    የዕለቱ ጥቅስ   📜
          📜📜📜===📜📜📜
“እንደ ልቤም በግ ጠባቆችን እሰጣችኋለሁ፥ በእውቀትና በማስተዋልም ይጠብቁአችኋል።”
              ኤርምያስ 3፥15




ወደ ቻናሉ ለመ🀄️🀄️ል፦ @Holy_scriptures
4👍2
#የእግዚአብሔር_ቃል_ምን_ይላል?



2ኛ ቆሮ 13
¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯
¹ ወደ እናንተ ስመጣ ይህ ሦስተኛዬ ነው፤ ሁሉ ነገር በሁለትና በሦስት ምስክር አፍ ይጸናል።
²-³ ሁለተኛ በእናንተ ዘንድ በነበርሁ ጊዜ እንደ ተናገርሁ አሁንም ደግሞ በሩቅ ስሆን፥ ክርስቶስ በእኔ አድሮ እንዲናገር ማስረጃ ከፈለጋችሁ፥ እንደ ገና ብመጣ እንዳልራራላቸው አስቀድመው ኃጢአት ላደረጉት ለሌሎችም ሁሉ አስቀድሜ ብዬአለሁ፥ አስቀድሜም እላለሁ። ክርስቶስም ስለ እናንተ አይደክምም ነገር ግን በእናንተ ኃይለኛ ነው።
⁴ በድካም ተሰቅሎአልና፥ ነገር ግን በእግዚአብሔር ኃይል በሕይወት ይኖራል። እኛ ደግሞ ከእርሱ ጋር እንደክማለንና፥ ነገር ግን ስለ እናንተ በሆነ በእግዚአብሔር ኃይል ከእርሱ ጋር በሕይወት እንኖራለን።
⁵ በሃይማኖት ብትኖሩ ራሳችሁን መርምሩ፤ ራሳችሁን ፈትኑ፤ ወይስ ምናልባት የማትበቁ ባትሆኑ፥ ኢየሱስ ክርስቶስ በእናንተ ውስጥ እንዳለ ስለ እናንተ አታውቁምን?
⁶ እኛ ግን የማንበቃ እንዳይደለን ልታውቁ ተስፋ አደርጋለሁ።
⁷ ክፉ ነገርንም ከቶ እንዳታደርጉ ወደ እግዚአብሔር እንጸልያለን፤ እኛ የምንበቃ ሆነን እንገለጥ ዘንድ አይደለም ነገር ግን እኛ ምንም እንደማንበቃ ብንሆን፥ እናንተ መልካሙን ታደርጉ ዘንድ ነው።
⁸ ለእውነት እንጂ በእውነት ላይ ምንም ለማድረግ አንችልምና።
⁹ እኛ ስንደክም እናንተም ኃይለኞች ስትሆኑ ደስ ብሎናልና፤ እናንተ ፍጹማን ትሆኑ ዘንድ ለዚህ ደግሞ እንጸልያለን።
¹⁰ ስለዚህ ጌታ ለማፍረስ ያይደለ ለማነጽ እንደ ሰጠኝ ሥልጣን፥ ከእናንተ ጋር ሳለሁ በቁርጥ እንዳልሠራ በሩቅ ሆኜ ይህን እጽፋለሁ።
¹¹ በቀረውስ፥ ወንድሞች ሆይ፥ ደኅና ሁኑ። ፍጹማን ሁኑ፥ ምክሬን ስሙ፥ በአንድ ልብ ሁኑ፥ በሰላም ኑሩ፥ የፍቅርና የሰላምም አምላክ ከእናንተ ጋር ይሆናል።
¹² በተቀደሰ አሳሳም እርስ በርሳችሁ ሰላምታ ተሰጣጡ።
¹³ ቅዱሳን ሁሉ ሰላምታ ያቀርቡላችኋል።
¹⁴ የጌታ የኢየሱስ ክርስቶስ ጸጋ የእግዚአብሔርም ፍቅር የመንፈስ ቅዱስም ኅብረት ከሁላችሁ ጋር ይሁን። አሜን።




ወደ ቻናሉ ለመ🀄️🀄️ል፦ @Holy_scriptures
👍4
'         📜📜📜===📜📜📜  
          📜    የዕለቱ ጥቅስ   📜
          📜📜📜===📜📜📜
“በእምነት መሆናችሁን ለማወቅ ራሳችሁን መርምሩ፤ ራሳችሁን ፈትኑ። ከፈር የወጣችሁ ካልሆነ በስተቀር፣ ኢየሱስ ክርስቶስ በውስጣችሁ እንዳለ አታውቁምን?”
             2ኛ ቆሮንቶስ 13፥5 (አዲሱ መ.ት)




ወደ ቻናሉ ለመ🀄️🀄️ል፦ @Holy_scriptures
👍54