shoes-2.pdf
1.5 MB
ወደ ቻናሉ ለመ🀄️ላ🀄️ል፦ @Holy_scriptures
shoes-1.pdf
1.4 MB
👉ርዕስ፦ ካርቦን-ኮፒ ክርስትና፣ ሌላውን ከመምሰል ኢየሱስን እንምሰል
✍️ጸሐፊ፦ ዶ/ር መለሰ ወጉ
📑የገጽ ብዛት፦ 299
📆የታተመበት ዓ.ም፦ 2005 ዓ.ም/ 2013 እ.ኤ.አ
✍️ጸሐፊ፦ ዶ/ር መለሰ ወጉ
📑የገጽ ብዛት፦ 299
📆የታተመበት ዓ.ም፦ 2005 ዓ.ም/ 2013 እ.ኤ.አ
❤10👍4
' 📜📜📜===📜📜📜
📜 የዕለቱ ጥቅስ 📜
📜📜📜===📜📜📜
“ነገር ግን ኢየሱስ እርሱ ክርስቶስ የእግዚአብሔር ልጅ እንደ ሆነ ታምኑ ዘንድ፥ አምናችሁም በስሙ ሕይወት ይሆንላችሁ ዘንድ ይህ ተጽፎአል።”
ዮሐንስ 20፥31
ወደ ቻናሉ ለመ🀄️ላ🀄️ል፦ @Holy_scriptures
📜 የዕለቱ ጥቅስ 📜
📜📜📜===📜📜📜
“ነገር ግን ኢየሱስ እርሱ ክርስቶስ የእግዚአብሔር ልጅ እንደ ሆነ ታምኑ ዘንድ፥ አምናችሁም በስሙ ሕይወት ይሆንላችሁ ዘንድ ይህ ተጽፎአል።”
ዮሐንስ 20፥31
ወደ ቻናሉ ለመ🀄️ላ🀄️ል፦ @Holy_scriptures
❤4👍2
የቀጠለ...
መጽሐፍ ቅዱስ የእግዚአብሔር ቃል
4. የመጽሐፍ ቅዱስ ትምህርት።
የመጽሐፍ ቅዱስ ከሰው እውቀት በላይ የሆነ ባሕርይ የሚታየው፥ ሊታወቅ የማይቻልን እውነት ግልጥና እንዲታወቅ አድርጎ ማቅረቡ ነው። ዘላለምን ማለት ሰው ከመፈጠሩ በፊት የነበረውን ተፈጥሮ ሳይቀር ይገልጣል። የእግዚኣብሔር ባሕርይና ሥራዎቹም ተገልጠውበታል፡፡ እግዚኣብሔር ለዓለም፥ ለእስራኤልና ቤተ ክርስቲያን ያለው አሳብና ዘላለማዊ ዕቅዱ፥ መጽሐፍ ቅዱሳዊው ትንቢት ውስጥ ተጠቃሏል። በማንኛውም ጉዳይ ላይ የሚሰጠው ገለጣ የመጨረሻ፥ ትክክልና ጊዜ የማይገድበው ነው። ሁለንተናዊ ባሕርይው አንባቢዎቹን ከጊዜና ከዘላለም ጋር በተዛመደ ነገር ብልሆች አድርጓቸዋል።
5. መጽሐፍ ቅዱስ ስነ-ጽሑፍነቱ።
በሥነ-ጽሑፍነቱ ሲታይ፥ መጽሐፍ ቅዱስ ምጡቅ ነው። ታሪካዊ ዘገባዎችን ብቻ ሳይሆን፥ ዝርዝር ትንቢቶችን፥ ውብ የሆኑ ቅኔዎችን፥ ልዩ ውበት ያለው ተውኔትን፥ የፍቅርና የጦርነት ታሪኮችን፥ በመጽሐፍ ቅዱሳዊው እውነት ላይ የሚነሡ ፍልስፍናዎችን ያጠቃልላል። የጸሐፊዎቹ መለያየት ከያዛቸው ጉዳዮች ስብጥር ብዛት ጋር ይስማማል። እንደ መጽሐፍ ቅዱስ በዘመናት የኖሩትንና በሁሉም የእውቀት ደረጃ ላይ የነበሩትን ሰዎች የማረከ ጽሑፍ የለም።
6. የማያዳላው የመጽሐፍ ቅዱስ ሥልጣን።
መጽሐፍ ቅዱስ በሰዎች መጻፉ ለሰዎች እንዲያደላ አላደረገውም። ያለማመንታት የማንንም ኃጢአት እና ደካማነት ይገልጣል። ይህ ብቻ አይደለም፥ በራሳቸው በጎ ምግባር የሚታመኑ ፍጻሜያቸው ጥፋት መሆኑንም ያስገነዝባል። በሰዎች ብዕር ቢጻፍም፥ ከሰው ወደ ሰው ሳይሆን፥ ከእግዚአብሔር ወደ ሰው የተላለፈ መልእክት ነው። ስለ ምድራዊ ነገሮችና ስለ ሰዎች ልምምድ ቢገልጥም፥ የሰማይና የምድርን፥ የሚታዩና የማይታዩ ነገሮችን፥ ስለ እግዚአብሔር የሚገልጡ እውነቶችን፥ ስለ መላእክት፥ ስለ ሰው፥ ስለ ጊዜና ዘላለም፥ ስለ ሞትና ሕይወት፥ ስለ ኃጢአትና ድነት፥ ስለ መንግሥተ ሰማያትና ሲኦልም በግልጥነትና በሥልጣን ያብራራል። እንዲህ ያላን መጽሐፍ ሰው መጻፍ ቢፈልግ እንኳን፥ ያለመለኮታዊ ምሪት ሊጽፈው አይችልም ነበር። ስለዚህ መጽሐፍ ቅዱስ፥ ሰሰው ቢጻፍም፥ እግዚአብሔር ብቻ ከሚሰጠው እርግጠኛነት፥ ዋስትና እና ሠላም ጋር ከርሱ የተላከ ነው።
7. የመጽሐፍ ቅዱስ ሉዓላዊ ባሕርይ።
መጽሐፍ ቅዱስ፥ ከሁሉም ይልቅ እግዚአብሔር በልጁ በኩል እራሱን መግለጡን ያመለከተ፥ አካልነቱንና ክብሩን ያስገነዘበ ታላቅ መጽሐፍ ነው። እንደ ኢየሱስ ያለው ሰብእና የሟች ሰው ፈጠራ ሊሆን አይችልም፤ ምክንያቱም ፍጹምነቱ ከሁሉ የላቀ እንዲሁም ቅድስናና ጥበብ ያለው በመሆኑ የዚህ ምድር ሰው የሚገነዘበው አልነበረም። የመጽሐፍ ቅዱስ ዋና ባሕርይ የኢየሱስ ክርስቶስን ታላቅ ታሪክ በመግለጥ ተረጋግጧል።
መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ከተካተቱት ሰብአዊና ከሰብአዊነት በላይ በሆኑ ባሕርያት ኅብረት የተነሣ፥ የተጻፈ ቃል በሆነው መጽሐፍ ቅዱስና፥ ሕያው ቃል በሆነው ኢየሱስ ክርስቶስ መካከል ተመሳሳይነት ይታይ ይሆናል። ሁለቱም ከመሠረታቸው መለኮታዊ ናቸው። በመሆናቸውም የመለኮትንና የሰውን ምስጢራዊና ፍጹም ግንኙነት ይገልጣሉ። ሁለቱም በሚያምኑ ሰዎች ሕይወት ውስጥ የሚሠራ የመለወጥ ኃይል ያላቸው ሲሆን፥ የማያምኑ ሰዎችን ደግሞ እንዳይቀበሷቸው በሚፈልግ ፈቃዳቸው እንዲቀጥሉ እግዚአብሔር ትቷቸዋል። በሁለቱም ውስጥ የማይበከለውና የማይሻረው መለኮታዊ ፍጹምነት አለ። የሚገልጿቸው እውነቶች የሕፃን አእምሮ በሚገነዘበው ደረጃ ቀላል ናቸው። ያንኑ ያህል፥ ፍጻሜ የሌለው የመለኮታዊው ጥበብ እንዲሁም እውቀት ሀብቶች ሲሆኑ፥ እንደፈጠራቸው እንደ እግዚአብሔር ዘላለማዊ ናቸው።
ምንጭ፡- “ዋና ዋና የመጽሐፍ ቅዱስ ጭብጦች” መጽሐፍ በዶክተር ሉዊስ ስፔሪ ቼፈር የተጻፈ እና በተክሉ መንገሻ የተተረጎመ ነው፡፡

❤3👍2
' 📜📜📜===📜📜📜
📜 የዕለቱ ጥቅስ 📜
📜📜📜===📜📜📜
“ከእናንተ ማንም የእግዚአብሔር ጸጋ እንዳይጐድልበት ደግሞም መራራ ሥር በቅሎ ችግር እንዳያስከትልና ብዙዎችን እንዳይበክል ተጠንቀቁ።”
ዕብራውያን 12፥15 (አዲሱ መ.ት)

👍4❤1
የኢየሱስ ክርስቶስ ክብር የሚበራበት ወንጌል
ወንጌል ማለት ምን ማለት ነው?
የኢየሱስን የክብር ወንጌል ስንነጋገር መጀመሪያ የምናየው ቃል ወንጌል ማለት ምን ማለት ነው? ወንጌል የሚለው ቃል በብሉይም ሆነ በአዲስ ኪዳን በቃል ትርጉም ደረጃ ሲታይ አንድ ዓይነት ትርጉም አለው። በብሉይ ኪዳን ወንጌል የሚለው ቃል ስም ሆኖ ሲታይ የሚያሳየው “መልእክት፣ መልካም ዜና” የሚለውን ሲያሳይ በግስ መልኩ ደግሞ “ዜና ማብሰር፣ መልካም ዜናን ማካፈል” የሚል መልክን ያሳያል። አይሁዳውያኑ ቃሉን ለተለያየ ወሬ የሚጠቀሙበት ቢሆንም በአብዛኛው በጦርነት የተገኘ ድልን ለማብሰር ያውሉታል።
ኢሳይያስ በምዕራፍ 52፥7 ላይ “የምስራች የሚናገር፥ ሰላምንም የሚያወራ፥ የመልካምንም ወሬ የምስራች የሚናገር፥ መድኃኒትንም የሚያወራ፥ ጽዮንንም፦ አምላክሽ ነግሦአል የሚል ሰው እግሩ በተራሮች ላይ እጅግ ያማረ ነው” እያለ ሲናገር “የመልካምን ወሬ የምስራች” የሚለውን ቃል የገለጠው “መብሳር מְבַשֵּׂ֥ר” የሚል ቃል በመጠቀም ነው። እዚህ ላይ እንደምናየው ወንጌል መልካም የሆነ ወይንም ደስ የሚያሰኝ ዜና፣ የሰላም ወሬ፣ መልካም ወሬ፣ የምስራች፣ መድኃኒትን ማውራት፣ የጽዮን አምላክ መንገሡን መናገር እንደሆነ ይታያል።
ሰባ ሊቃናት ወይንም ሴፕቱዋጀንት በመባል የሚታወቀው የመጀመሪያው የብሉይ ኪዳን የግሪክኛ ቅጂ ከላይ በእብራይስጥኛ “ቤሶር” ወይንም “ባሳር” የሚለውን ቃል ሲተረጉም የተጠቀመበት ቃል በአማርኛ ወንጌል ተብሎ የተተረጎመውን በግሪክኛ “εὐαγγέλιον/ ኢዋንጌልዮን” በሚል ቃል ነው ያስቀመጠው።
የአዲስ ኪዳን አገልጋዮች በብሉይ ኪዳን እውነቶች ላይ በነበራቸው እምነት ላይ በመቆም የጌታ ኢየሱስን መወለድ፣ በእርሱ ሞትና ትንሳኤ ለሰው ልጆች የተገኘውን መዳን ለማሳየትና ለማስተማር በጥቅም ላይ ያዋሉት የግሪክኛውን ቃል ኢዋንጌሊዮን የሚለውን ቃል በመጠቀም ነው። አዲስ ኪዳን ወንጌልን የምሥራች አድርጎ የሚናገርበትን ጥልቀቱንና ይዘቱን ጠጋ ብለን መመልከት ይገባናል።
ወንጌል ምን እንደሆነ የመጽሐፍ ቅዱስ ተማሪዎች ሲናገሩ በአብዛኛው ተመሳሳይ መልክና ይዘት አለው። አንድ ጽሑፍ ላይ ስመለከት ወንጌልን እንዲህ በማለት ያስቀምጠዋል፦ “ወንጌል የኢየሱስ ሕይወት፣ ሞቱና ትንሳኤው ለእስራኤልና ለዓለም ያመጣውን መዳን የሚያበስር ነው” ይላል። ወንጌል እንዲህ መነገሩ ትክክል ነው። በዚህ ጠቅለል ባለ መረዳት ወንጌልን ወስኖና መጥኖ መናገሩ እንዳለ ሆኖ በዚህ ሳንገደብና ሳንቆጠብ ወንጌልን አዲስ ኪዳን በሚያሳየን ሙሉ መልኩ ለመመልከት በሚያስችለን በእግዚአብሔር ቃል ብርሃን መመልከት ይኖርብናል።
ሐዋርያው ጳውሎስ በሮሜ መጽሐፍ በምዕራፍ 1፥1-2 ላይ ስለ ወንጌል ምንነት የተናገረውን በመመልከት መጀመር ጠቃሚ ይሆናል። ሐዋርያው ጳውሎስ እንዲህ ይላል፦
“ ሐዋርያ ሊሆን የተጠራ የኢየሱስ ክርስቶስ ባሪያ ጳውሎስ በነቢያቱ አፍ በቅዱሳን መጻሕፍት አስቀድሞ ተስፋ ለሰጠው ለእግዚአብሔር ወንጌል ተለየ። ይህም ወንጌል በሥጋ ከዳዊት ዘር ስለ ተወለደ እንደ ቅድስና መንፈስ ግን ከሙታን መነሣት የተነሣ በኃይል የእግዚአብሔር ልጅ ሆኖ ስለ ተገለጠ ስለ ልጁ ነው፤ እርሱም ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ነው” (ሮሜ 1፥1-3)
ጳውሎስ ከላይ በተናገረው እውነት ስለ ወንጌል የሚከተሉትን ትልልቅ ሃሳቦች ያሳየናል፦
1) ወንጌል የእግዚአብሔር እንደሆነ ይናገራል
2) የአዲስ ኪዳኑ ወንጌል አስቀድሞ በቅዱሳን መጻሕፍት ተስፋ ሆኖ የተሰጠ እንደነበር ያሳያል
3) ይህ ወንጌል ስለ ኢየሱስ ክርስቶስ እንደሆነ ይናገራል።
4) ወንጌል የምሥራች አድርጎ የሚያሳየን ኢየሱስ ክርስቶስ
👉ወንጌል በሥጋ ከዳዊት ዘር የተለወደውን
👉 ወንጌል እንደ ቅድስና መንፈስ ግን ከሙታን የተነሳውን
👉 ወንጌል ከሙታን በመነሣቱ በኃይል የእግዚአብሔር ልጅ ሆኖ የተገለጠውን ኢየሱስ ክርስቶስን የሚመለከት እንደሆነ እናያለን።
ይቀጥላል. . .
ምንጭ፦ sermons.logos.com

Logos
Logos Sermons
Premium sermon illustrations, sermon outlines, sermon media, and archiving.
👍6❤2
' 📜📜📜===📜📜📜
📜 የዕለቱ ጥቅስ 📜
📜📜📜===📜📜📜
“በተናገረኝም ጊዜ መንፈስ ገባብኝ በእግሬም አቆመኝ፥ የሚናገረኝንም ሰማሁ።”
ሕዝቅኤል 2፥2
ወደ ቻናሉ ለመ🀄️ላ🀄️ል፦ @Holy_scriptures
📜 የዕለቱ ጥቅስ 📜
📜📜📜===📜📜📜
“በተናገረኝም ጊዜ መንፈስ ገባብኝ በእግሬም አቆመኝ፥ የሚናገረኝንም ሰማሁ።”
ሕዝቅኤል 2፥2
ወደ ቻናሉ ለመ🀄️ላ🀄️ል፦ @Holy_scriptures
👍5❤3
በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ የእነጳውሎስን ስብከት ተከትሎ ከተመሰረቱት ቤተ ክርስቲያናት መካከል በሴቶች እንደተመሰረተች የምትገመት ቤተ ክርስቲያን የቷ ናት?
Anonymous Quiz
18%
ሀ. ሮሜ
10%
ለ. ቆሮንቶስ
27%
ሐ. ፊልጵስዩስ
10%
መ. ቆላስይስ
13%
ሠ. ኤፌሶን
22%
ረ. ተሰሎንቄ
👍7❤2
' 📜📜📜===📜📜📜
📜 የዕለቱ ጥቅስ 📜
📜📜📜===📜📜📜
“ከእርሱ ጋር እንዲሆኑ፣ ለስብከትም ይልካቸው ዘንድ ዐሥራ ሁለቱን ሾማቸው፤ ሐዋርያትም ብሎ ጠራቸው፤”
ማርቆስ 3፥14 (አዲሱ መ.ት)
ወደ ቻናሉ ለመ🀄️ላ🀄️ል፦ @Holy_scriptures
📜 የዕለቱ ጥቅስ 📜
📜📜📜===📜📜📜
“ከእርሱ ጋር እንዲሆኑ፣ ለስብከትም ይልካቸው ዘንድ ዐሥራ ሁለቱን ሾማቸው፤ ሐዋርያትም ብሎ ጠራቸው፤”
ማርቆስ 3፥14 (አዲሱ መ.ት)
ወደ ቻናሉ ለመ🀄️ላ🀄️ል፦ @Holy_scriptures
❤5
#የሮሜ_መልእክት_ጥናት
እግዚአብሔር የሚፈርደው በትክክል ነው (9፥14-18)
14–16 አንዳንዶች እግዚአብሔር የሚፈርደው በትክክል አይደለም ብለው ያስባሉ። እንዲህ በማለትም ይጠይቃሉ፥ «እግዚአብሔር ያዕቆብን የወደደውና ኤላውን የጠላው ለምንድን ነው? በዚህ እግዚአብሔር ፍርድ አላጓደለምን?» ስለ እግዚአብሔር እንዲህ የመሰሉ አሳቦች ሊኖሩን አይገባም። በቁ. 15 ጳውሎስ እግዚአብሔር በዘጸ. 33፥19 ለሙሴ የተናገረውን ቃል ይጠቅሳል። እግዚአብሔር ሰዎችን ይመርጣል፥ ሰዎችን ይጠራል፥ ሰዎችንም ይባርካል። ይህንንም የሚያደርገው ከሰው ምኞትና ጥረት ሳይሆን ከራሱ ምሕረት የተነሣ ነው (ቁ. 16)::
በእነዚህ ጥቅሶች ውስጥ ጳውሎስ፤ የእግዚአብሔር ምሕረት ፍርድን በማጓደል ላይ የተመሠረተ አይደለም በማለት ያስተምራል። እያንዳንዱ ሰው በአንድ መንገድ ወይም በሌላ እግዚአብሔርን ሳይታዘዝ በመቅረቱ፤ ደኅንነትን ለማግኘት የተገባው ማንም ሰው የለም። ነገር ግን እግዚአብሔር በምሕረቱና በጸጋው የራሱን ልጅ ኢየሱስን ለደኅንነታችን አሳልፎ ሰጥቶኣል። ያለ እግዚአብሔር ምሕረትና ያለ ጸጋው ደኅንነትን ለማግኘት የሚችል ማንም ሰው የለም።
ማንም ሰው ቢሆን በራሱ ምኞትና ጥረት የእግዚአብሔርን ጸጋና ምሕረት መቀበል አይችልም (ቁ. 16)። በእርግጥም እግዚአብሔር እንዲህ ብሎአል፥ «ትፈልጉኛላችሁ፥ የምትፈልጉኝም በሙሉ ልባችሁ ስለሆነ ታገኙኛላችሁ» (ኤር. 29፥13)። በእውነትም በተከፈተና በትሑት ልብ እግዚአብሔርን መፈለግ አለብን፤ ፊታችንንም ወደ እርሱ መመለስ ይገባል። ይህንንም ቢሆን የእግዚአብሔር ጸጋ ካላነሣሣን በቀር በራሳችን ምንም ማድረግ አንችልም (ዮሐ. 1፥12-13፤ 6፥44)። ከመጀመሪያ እስከ መጨረሻ ደኅንነታችን የእግዚአብሔር ጸጋ ሥራ ነው።
17-18 ፈርዖን ማን ነበር? በሙሴ ዘመን የግብጽ ገዢዎች ፈርዖን ይባሉ ነበር። ጳውሎስ በዚህ ጥቅስ የሚያነሣው ፈርዖን 2ኛ ራምሴስ የሚባለው ሲሆን፥ እርሱም በዚያን ጊዜ በግብጽ ይኖሩ በነበሩት አይሁዳውያን ላይ ስደት አነሣስቶ የነበረ በጣም ጨካኝና ክፉ መሪ ነበር። ከዚህ ከክፉ ፈርዖን እጅ አይሁዳውያንን ተቤዥቶ ነጻ እንዲያወጣቸው እግዚአብሔር ሙሴን ላከው። በዚህ ፈርዖን ልብ ውስጥ ፍርሃትን ለማምጣት ብሎ፥ እግዚአብሔር በሙሴ በኩል ታላላቅ ምልክቶችንና ድንቅ ነገሮችን አደረገ። እነዚህም ምልክቶችና ድንቅ ነገሮች በዘጸ. ከምዕራፍ 7-12 ባለው ክፍል ውስጥ ተገለጠዋል።
በቁ. 17 ጳውሎስ እግዚአብሔር ለፈርዖን የተናገረውን ቃል ይጠቅሳል (ዘጸ. 9፥16)፡፡ ይህን ክፉ መሪ ያስነሣውና ልቡንም ያጠነከረው፥ የእግዚአብሔር ኀይል እንዲገለጥና ስሙም እንዲታወጅ ነው። የፈርዖን ልብ ባይጠነክር ኖሮ፣ ለምሳሌ ፈርዖን ንስሓ የገባ ቢሆን ኖሮ፥ እግዚአብሔር ኀይሉን ለማሳየት ዕድሉ አይኖረውም ነበር። ከዚህም የምንረዳው እግዚአብሔር ለአንዳንዶች ምሕረቱን እንደሚያሳይ ሲሆን፤ ሌሎች የእግዚአብሔርን ያጠነክረዋል፡፡ ምሕረት እንዳይቀበሉ ልባቸውን ያጠነክረዋል።
ይህን ካነበብን በኋላ እግዚአብሔር እውነተኛ ፍርድ የለውም ለማለት እንፈተን ይሆናል። ለፈርዖንም በእውነት አልፈረደም እንላለን። እግዚአብሔር ለፈርዖን ዕድል አልሰጠውም፣ ምንም ዓይነት ደግነት አላሳየውም። ማንም ሰው ቢሆን የእግዚአብሔርን ደግነት ለማግኘት የተገባ አይደለም። የእግዚአብሔርን ምሕረት ለመቀበልም የተገባው ሰውም የለም። ማንም ሰው ቢሆን እግዚአብሔርን «እኔ ዕድል ማግኘት ይገባኛል» ሊለው አይችልም። ምክንያቱም እኛ ሁላችንም ብንሆን በእግዚአብሔር ፊት ደጋግመን ኃጢአት ሠርተናል (ሮሜ 3-10-12)። ሰው ከእግዚአብሔር ፊት ሊቀበለው የሚገባ ነገር ቢኖር ቅጣትን ብቻ ነው። እግዚአብሔር የሰዎችን ልብ የሚያጠነክረው ከኃጢአታቸው የተነሣ ነው። እግዚአብሔር የሰውን ልብ ሲያጠነክር ገልጦ የሚያሳየው የራሱን ፍትሕ ነው እንጂ ፍትሕ አጉዳይነቱን አይደለም።
ስለዚህ እግዚአብሔር የፈርዖንን ልብ ያጠነከረው በራሱ በፈርዖን ክፋት ነው፤ እግዚአብሔር የፈርዖንን ልብ በማጠንከሩ™ ያላየው ትክክለኛ ፍትሕ ነበር። ፈርዖን የእግዚአብሔርን ቅጣት ለመቀበል የተገባ ሰው ነበር።
ይቀጥላል. . .
ምንጭ፦ የአዲስ ኪዳን ማብራሪያ፤ ገጽ 372-373

👍5❤1
' 📜📜📜===📜📜📜
📜 የዕለቱ ጥቅስ 📜
📜📜📜===📜📜📜
“ብርቱ የሆነ እርሱ በእኔ ታላቅ ሥራ አድርጎአልና፤ ስሙም ቅዱስ ነው።”
ሉቃስ 1፥49

❤2👍1🔥1
#የእግዚአብሔር_ቃል_ምን_ይላል?
ገላትያ 6
¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯
¹ ወንድሞች ሆይ፥ ሰው በማናቸውም በደል ስንኳ ቢገኝ፥ መንፈሳውያን የሆናችሁ እናንተ እንደዚህ ያለውን ሰው በየውሃት መንፈስ አቅኑት፤ አንተ ደግሞ እንዳትፈተን ራስህን ጠብቅ።
² ከእናንተ እያንዳንዱ የአንዱን ሸክም ይሸከም እንዲሁም የክርስቶስን ሕግ ፈጽሙ።
³ አንዱ ምንም ሳይሆን ምንም የሆነ ቢመስለው ራሱን ያታልላልና።
⁴ ነገር ግን እያንዳንዱ የገዛ ራሱን ሥራ ይፈትን፥ ከዚያም በኋላ ስለ ሌላው ሰው ያልሆነ ስለ ራሱ ብቻ የሚመካበትን ያገኛል፤
⁵ እያንዳንዱ የገዛ ራሱን ሸክም ሊሸከም ነውና።
⁶ ነገር ግን ቃሉን የሚማር ከሚያስተምረው ጋር መልካምን ነገር ሁሉ ይከፋፈል።
⁷ አትሳቱ፤ እግዚአብሔር አይዘበትበትም። ሰው የሚዘራውን ሁሉ ያንኑ ደግሞ ያጭዳልና፤
⁸ በገዛ ሥጋው የሚዘራ ከሥጋ መበስበስን ያጭዳልና፥ በመንፈስ ግን የሚዘራው ከመንፈስ የዘላለምን ሕይወት ያጭዳል።
⁹ ባንዝልም በጊዜው እናጭዳለንና መልካም ሥራን ለመሥራት አንታክት።
¹⁰ እንግዲያስ ጊዜ ካገኘን ዘንድ ለሰው ሁሉ ይልቁንም ለሃይማኖት ቤተ ሰዎች መልካም እናድርግ።
¹¹ እንዴት ባሉ ታላላቆች ፊደላት በእጄ እንደ ጻፍሁላችሁ እዩ።
¹² በሥጋ መልካም ሆነው ሊታዩ የሚወዱ ሁሉ እንድትገረዙ ግድ አሉአችሁ፥ ነገር ግን ስለ ክርስቶስ መስቀል እንዳይሰደዱ ብቻ ነው።
¹³ በሥጋችሁ እንዲመኩ ልትገረዙ ይወዳሉ እንጂ የተገረዙቱ ራሳቸው እንኳ ሕግን አይጠብቁም።
¹⁴ ነገር ግን ዓለም ለእኔ የተሰቀለበት እኔም ለዓለም የተሰቀልሁበት ከጌታችን ከኢየሱስ ክርስቶስ መስቀል በቀር ሌላ ትምክህት ከእኔ ይራቅ።
¹⁵ በክርስቶስ ኢየሱስ አዲስ ፍጥረት መሆን ይጠቅማል እንጂ መገረዝ ቢሆን ወይም አለመገረዝ አይጠቅምምና።
¹⁶ በዚህም ሥርዓት በሚመላለሱ ሁሉ ላይ በእግዚአብሔር እስራኤልም ላይ ሰላምና ምሕረት ይሁን።
¹⁷ እኔ የኢየሱስን ማኅተም በሥጋዬ ተሸክሜአለሁና ከእንግዲህ ወዲህ አንድ ስንኳ አያድክመኝ።
¹⁸ ወንድሞች ሆይ፥ የጌታችን የኢየሱስ ክርስቶስ ጸጋ ከመንፈሳችሁ ጋር ይሁን። አሜን።

👍2
' 📜📜📜===📜📜📜
📜 የዕለቱ ጥቅስ 📜
📜📜📜===📜📜📜
“በገዛ ሥጋው የሚዘራ ከሥጋ መበስበስን ያጭዳልና፥ በመንፈስ ግን የሚዘራው ከመንፈስ የዘላለምን ሕይወት ያጭዳል።”
ገላትያ 6፥8

#እራሳችንን_እንመርምር
እግዚአብሔር ሰዎችን ያታልላልን? ሰው ምን ቢያደርግ እግዚአብሔር እንዲህ ያስብበታል? ለምን?
“እግዚአብሔርም፦ ወጥቶ በሬማት ዘገለዓድ ይወድቅ ዘንድ የእስራኤልን ንጉሥ አክዓብን የሚያታልል ማን ነው? አለ። አንዱም እንደዚህ፥ ሌላውም እንደዚያ ያለ ነገር ተናገረ።”
2 ዜና 18፥19

❤3👍1
' 📜📜📜===📜📜📜
📜 የዕለቱ ጥቅስ 📜
📜📜📜===📜📜📜
“ሐማም ለሚስቱ ለዞሳራና ለወዳጆቹ ሁሉ ያገኘውን ሁሉ አጫወታቸው። ጥበበኞቹና ሚስቱ ዞሳራም። በፊቱ መውደቅ የጀመርህለት መርዶክዮስ ከአይሁድ ወገን የሆነ እንደ ሆነ በፊቱ ፈጽሞ ትወድቃለህ እንጂ አታሸንፈውም አሉት።”
አስቴር 6፥13

👍3❤1
' 📜📜📜===📜📜📜
📜 የዕለቱ ጥቅስ 📜
📜📜📜===📜📜📜
“ፍቅራችሁ በጥልቅ እውቀትና በማስተዋል ሁሉ በዝቶ እንዲትረፈረፍ እጸልያለሁ።”
ፊልጵስዩስ 1፥9 (አዲሱ መ.ት)

❤2👍2
#ከተማ_ወይም_ቦታ_በቅዱሳት_መጻሕፍት
#አርሞንዔም፤ በሶርያ፥ በሊባኖስና በእስራኤል ድንበር ላይ ያለው ተራራ ከባሕር ጠለል እስከ 2777 ሜትር ከፍ ስለሚል በአቅራቢያው ካሉት ተራራዎች ከፍታ አለው። የአርሞንዔም በረዶ እየሟሟ ወደ ዮርዳኖስና ወደ ገሊላ ባሕር ይፈሳል፤ ዘዳ. 4፥48፤ መዝ. 133፥3። ክርስቶስ ክብሩን የገለጠው በዚህ ተራራ ሳይሆን አልቀረም፤ መዝ. 89፥12፤ ማቴ. 17፥1-8። አርሞንዔም ሢርዮን፥ ሳኔር፥ ኤርሞን ተብሎ ይጠራል፤ ዘዳ. 3፥8:9፤ መኃልይ 4፥8።
ምንጭ፦ የመጽሐፍ ቅዱስ መዝገበ ቃላት፤ ገጽ 147

👍7
' 📜📜📜===📜📜📜
📜 የዕለቱ ጥቅስ 📜
📜📜📜===📜📜📜
“በይሁዳም ሁሉና በገሊላ በሰማርያም የነበሩት አብያተ ክርስቲያናት በሰላም ኖሩ ታነጹም፤ በእግዚአብሔርም ፍርሃትና በመንፈስ ቅዱስ መጽናናት እየሄዱ ይበዙ ነበር።”
ሐዋርያት 9፥31

❤5👍2